You are on page 1of 10

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት

ደቡብ ነጋሪት ጋዜጣ


DEBUB NEGARIT GAZETA
OF THE SOUTHERN NATIONS NATIONALITIES AND PEOPLES
REGIONAL STATE
11 ኛ ›mT q$_R 1 bdb#B B/@éC½B/@rsïCÂ ?ZïC KL ል M ክር
b@T -ÆqEnT ywÈ
hêú ከመስከረም 6 ቀን 1997 ›.M

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት የሚሊሽያ አካላት አስተዳደርና


አደረጃጀት ሥርአት ደንብ ቁጥር 28/1997

በደ/ብ/ብ/ክ/መ/ አዋጅ ቁጥር 04/95 ለሚሊሺያ ጽ/ቤት የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት በአግባቡ እንዲወጣ
ለማስቻል በተዋረድ ለዞን፣ ለልዩ ወረዳና በወረዳ ደረጃ ጽ /ቤቶችን በመክፈት በሰው ሀይል ማደራጀት
በማሰፈለጉ፤-

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩትን ህዝቦች ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና
የሚጫወተው የሚሊሻ ሀይል መብትና ግዴታውን አውቆ ተልእኮውን በትጋት፣በታማኝነት፣በግልጽነትና
በተጠያቂነት መንፈስ እንዲወጣው የሚያስችለውን ሁኔታ ማመቻቸት በማስፈለጉ፤-

በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት የአስፈጻሚና ፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር
ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 64/95 አንቀጽ 56 (1) በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የሚከተለውን ደንብ
አውጥቷል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ

1. አጭር ርዕስ

A/K
ይህ ደንብ ‹‹ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት የሚሊሺያ አስተዳደርና
አደረጃጀት ሥርዓት ደንብ ቁጥር 28/1997 ዓ/ም ›› ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡-
1. ‹‹ሚሊሺያ›› ማለት ከምርት ተግባሩ ሳይነጠል በህዝብ የተመረጠና ምንም አይነት የደመወዝ
ክፍያ የማያገኝ ታጣቂ ማለት ነው፡፡
2. ‹‹ የቴክኒክ አመራር ሰራተኞች ›› ማለት በየደረጃው የሚሰሩ የሚሊሻና የቴክኒክ አመራሮች
ናቸው፡፡
3. ‹‹መረጃ ሐላፊ ›› ማለት በሚሊሺያ አደረጃጀት ውስጥ የፀጥታ ችግሮችንና መንስኤዎችን
የሚከታተል ኃላፊ ነው፡፡
4. ‹‹ፅ/ቤቶች ››ማለት የክልል፣ የዞን ፣የልዩ ወረዳ እና የወረዳ የሚሊሺያ ፅህፈት ቤቶች ማለት
ነው ፡፡
5. ‹‹ሕዋስ›› ማለት የሚሊሺያ ሀይል አደረጃጀት የመጨረሻና ትንሹ 3 ሰው ብቻ የያዘው ክፍል
ማለት ነው፡፡
6. ‹‹ጋንታ›› ማለት በቀበሌው ውስጥ በየጎጡ የሚደራጁ ህዋሶች አንድ ላይ ተሰባስበው የሚፈጥሩት
ቡድን ማለት ነው›› (በአንድ ቀበሌ ውስጥ ያሉት ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ህዋሶች ሰብስብ
ማለት ነው)
7. ‹‹ኮማንደር ›› ማለት የሚሊሺያ ሀይሉን ወታደራዊ ጉዳዮችን የሚከታተል ሰው ነው፡፡
8. ‹‹አስተዳደር ኃላፊ›› ማለት የሚሊሺያውን ጤናማ ፖለቲካዊ ህይወትና ሎጀስቲክስ የሚከታተል
ነው፡፡
9. ‹‹ሎጀስቲክስ›› ማለት የስልጠና ቦታና የቁሳቁስ አደረጃጀት ነው፡፡
10. ‹‹የድጋፍ ሰጪ›› ማለት በመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር አዋጅ የሚተዳደር ሆኖ ለሚሊሻና
ለቴክኒክ ሀይሉ ድጋፍ የሚሰጥ አካል ማለት ነው፡፡
3. የደንቡ ተፈጻሚነት ወሰን
1. ይህ ደንብ ከክልል ሚሊሺያ ጽ/ቤት ጀምሮ እስከ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤቶች የተሾሙ ኃላፊዎች
እና ሌሎች የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በስተቀር በሁሉም የቴክኒክ አመራር ሰራተኞች እና
ሚሊሺያ አባላት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
2. በዚህ ደንብ በወንድ ጾታ የተገለጸ ድንጋጌዎች ለሴት ጾታ ያገለግላሉ፡፡
ክፍል ሁለት
ስለሚሊሺያ ጽ/ቤት አደረጃጀት

4. አደረጃጀት

A/K
ጽ/ቤቱ የሚከተለውን አደረጃጀት ይኖረዋል፡፡
ሀ/ በክልል ደረጃ የተቋቋመ የሚሊሺያ ጽ/ቤት
ለ/ በዞን ደረጃ የተቋቋመ የሚሊሺያ ጽ/ቤት
ሐ/ በልዩ ወረዳ ደረጃ የተቋቋመ የሚሊሺያ ጽ/ቤት
መ/ በወረዳ ደረጃ የተቋቋመ የሚሊሺያ ጽ/ቤት
ሠ/ በየቀበሌው የሚቋቋሙ የሚሊሺያ ማስተባበሪያዎች ናቸው፡፡
ረ/ እንደአስፈላጊነቱ የሰው ሀይል ይኖረዋል ፡፡
5. በአንቀጽ 4 መሰረት በየደረጃው የተቋቋሙት የሚሊሻ ጽ/ቤት የሚከተሉት ኃላፊዎችና ክፍሎች
እንደአስፈላጊነቱ ይኖራሉ፡፡

ሀ/ የጽ/ቤቱ ኃላፊ
ለ/ ፕላን፣ ፕሮግራምና ዶክመንቴሽን አገልግሎት ኃላፊ
ሐ/ የሥልጠናና ትጥቅ ዋና ክፍል ኃለፊ
መ/ የሥልጠና ክፍል ኃላፊ
ሠ/ የትጥቅና ጥገና ክፍል ኃላፊ
ረ/ የስምሪትና መረጃ ዋና ክፍል ኃላፊ
ሰ/ የስምሪት ክፍል ኃላፊ
ሸ/ የመረጃና የስታስቲክስ ክፍል ኃላፊ

ሲሆኑ ስለኃላፊነትና ተግባራቸው ዝርዝሩ የክልሉ ፍትህና አስ/ጉ/ማስ/ቢሮ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡

ክፍል ሶስት

6. ሚሊሻ ጽ/ቤቶች የቴክኒክ አመራር ሰራተኞች ደመወዝ ምደባ፣ስለመሰናበት እና የእረፍት ፈቃድ አሰጣጥ
6.1. ስለ ደመወዝ
በሚሊሻ ጽ/ቤቶች በድጋፍ ሰጪነት ከሚሰሩ ሰራተኞችና የክልል፣ የዞንና የልዩ ወረዳ
ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ደመወዝ በስተቀር የሌሎች የሚሊሻ ፅ/ቤቶች የቴክኒክ
ሰራተኞች ደመወዝ በዚህ ደንብ አባሪ ተደርጎ በፀደቀው መሰረት ይሆናል፡፡
6.2. የሚሊሻ ፅ/ቤት የቴክኒክ አመራር ሰራተኞች ደመወዝ ጭማሪ ፣ምደባ የደረጃ እድግት
ዝውውር ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል፡፡

6.3. ምደባ

A/K
1. የሚሊሻ ጽ/ቤት የቴክኒክ አመራር ሰራተኞች በዚህ ደንብ መሰረት ስለቅጥር
በሚፀድቀው የምደባ መስፈርት መመሪያ መሰረት አሟልተው የሚገኙ ሰራተኞች
የሚመደቡበት ይሆናል ፡፡
2. የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በሚመለከት ግን የሲቪል ሰርቪስ መመሪያና ደንብ
የሚያሟሉ ሰራተኞች ብቻ የሚቀጠሩ ይሆናል፡፡
3. በሚሊሻ ጽ/ቤት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የዓመት እረፍት፣ የወሊድ እረፍት
ፈቃድ፣ የህመምና የጋብቻ የእረፍት ፈቃድ አሰጣጥ በመንግስት ሰራተኞች
አስተዳደር ደንብ ውስጥ የተጠቀሰው ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
6.4. ስለስንብት (አገልግሎት ስለማቋረጥ)
1. በዲስፕሊን ምክንያት ከስራ ስለመሰናበት የተጠቀሰው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣
ማንኛውም በሚሊሻ ጽ/ቤቶች የቴክኒክ አመራር ሆኖ ተመድቦ የሚሰራ ሰራተኛ
የአንድ ወር የቅድሚያ የጽሁፍ ማስታወቂያ ለጽ/ቤቱ በመስጠት ስራውን በገዛ
ፈቃዱ መልቀቅ ይችላል፡፡
2. ሌሎች ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በተመለከተ ግን በመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር
ደንብና መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ክፍል አራት
ስለ ዲስፕሊን
7. የዲስፕሊን ቅጣት ዓላማ
የዲስፕሊን ቅጣት ዓላማው የቴክኒክ ሰራተኛ እና የሚሊሻ አባል በፈጸመው የዲስፕሊን ጉድለት
ለወደፊት ተጸጽቶ እንዲታረምና ስራውንም በአግባቡ እንዲያከናውን ለማስቻል ወይም የማይታረም
ሆኖ ሲገኝም ከስራው ለማሰናበት ነው፡፡
8. ከባድ የዲስፕሊን ጥፋቶች
1. በህገ-መንግስቱ የተረጋገጡ የዜጎችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን መጣስ ፣
2. የህዝቡን ሠላማዊ ህይወት ከሚያበላሹ በአገር ሉአላዊነትላይ ችግር የሚፈጥሩ እና
ህገመንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ ለመጣል ከሚያዘጋጁ ቡድኖች ጋር በማበር ሀሳብ
መስጠት ሚስጢር ማካፈል፣
3. ትዕዛዝ አለማክበር፣ በስራ ላይ መለገም፣የአሰራር ሥነ-ሥርዓትን አለመከተል ፣
4. በጽ/ቤቱ ሥራ እንዳይሰራ ሆን ብሎ ማወክ ወይም ከሚያወኩት ጋር መተባበር ፣
5. በተለያዩ መጠጦች ፣በጫት፣በአደንዛዥ ዕጽ ሱስ በመመረዝ ሥራን በመደል፣
6. ጉቦ መቀበል ወይም መጠየቅ፣
7. የሌብነት ወይም የእምነት ማጉደል ድርጊት መፈጸም ፣
8. በመ/ቤቱ ንብረት ላይ ሆነ ብሎ ወይም በቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ ፣

A/K
9. በስራ ቦታ በጠብ አጫሪነት መደብደብ ፣
10. በስራ ቦታ ለሕብረተሰቡ ሞራል ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶችን መሥራት ፣
9. ቀላል የዲስፕሊን ጥፋቶች
1. ያለበቂ ምክንያት ያለፈቃድ ከሥራ ገበታ ላይ መቅረት ፣
2. በስራ ቦታ ተገኝቶ የሥራ ሰዓቱን ለትክክለኛ የመንግስት ሰራ አለማዋል፣
3. የግል ንጽህና አለመጠበቅ
4. በስራ ላይ ተገቢውን ጥረትና ትጋት አለማሳየት፣
5. ከስራ ባልደረቦች ጋር በመግባባት ተባብሮ መስራት ባለመቻሉ ለስራ እንቅስቃሴ እንቅፋት
መሆን፣
6. ሌሎች ተመሳሳይ ደረጃ የሚታዩ ቀላል ጥፋቶችን መፈጸም ፣
10. በዲስፕሊን ጥፋት ምክንያት ስለሚወሰዱ ቅጣቶች
1. በቀላል የዲስፕሊን ጥፋት ምክንያት የሚወሰዱ ቅጣት
ሀ. ምክር
ለ. ቀላል ተግሳጽ - ለመጀመሪያ ጊዜ ሲፈጽም
ሐ. የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ - ተመሳሳይ ወይም ሌላ ጥፋት በተደገመ ጊዜ
መ. ከሁለት ወር የማይበልጥ የደመወዝ ቅጣት - የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ደርሶት ያልታረመ በሆነ
ጊዜ፣
2. በከባድ የዲስፕሊን ጥፋት ምክንያት የሚወሰዱ ቅጣቶች
ሀ. የአንድ እርከን የደመወዝ ክልከላ አንቀጽ 8 ንዑስ 3 እና 4 የተመለከቱት በተፈጸሙ ጊዜ፣
ለ. አንድ ደረጃ ዝቅ ማድረግ ፣ በአንቀጽ 8 ንዑስ 5,8,9, እና 10 የተመለከቱት በተፈጸሙ ጊዜ
ሐ. ከስራ የማሰናበት ቅጣት በአንቀጽ 8 ንዑስ 1, 2, 6 እና 7 የተመለከቱት በተፈጸሙ ጊዜ ወይም
ሌሎች ጥፋቶች በተደገሙ ጊዜ ሊወሰን ይችላል፡፡
11. የዲስፕሊን ቅጣት አፈጻጸም
ከባድ የዲስፕሊን ጥፋት የፈጸሙ ሰራተኞች በየደረጃው በጽ/ቤቶች በሚቋቋሙ የዲስፕሊን ኮሚቴ
የሚታይና የሚወሰን ሆኖ በተዋረድ ይግባኝ የሚጠየቅባቸው ይሆናል፡፡
12. የዲስፕሊን ክስ የይግባኝ አቀራረብ ጊዜ
የዲስፕሊን ክስ አቀራረብ፣ የይግባኝ ጊዜ የመሳሰሉት ወደፊት በመመሪያ ይወሰናሉ፡፡
13. መደበኛ የሥራ ጊዜ
የመንግስት ሰራተኞች መደበኛው የስራ መግቢያና መውጫ ቀንና ሰአት ለሚሊሻና ለቴክኒክ ሰራተኞች
ተፈፃሚ ሆኖ ለሚሊሻው ግን በመመሪያ ሊወሰን ይችላል፡፡

ክፍል አምስት

A/K
ስለሚሊሺያ አባላት ምልመላ መብት፣ግዴታ፣ ስምሪት አደረጃጀትና ሥልጠና፣
14. ለአባልነት የሚያበቁ መመዘኛዎች ፣
የሚሊሺያ አባል የሚሆን ሰው በአካባቢው በሕዝብ የሚመረጥ ሲሆን ከዚህ በታች የተመለከቱትን
መመዘኛዎች የሚያሟላ ሰው የሚሊሺያ አባል መሆን ይችላል፡፡
ሀ. ዜግነት ኢትዬ É ያዊ የሆነ፣
ለ. ዕድሜው ከ 18 ዓመት በላይ ከ 50 ዓመት ያልበለጠ፣
ሐ. ለኢፌዲሪና ለክልል ህገ-መንግስት መሰረታዊ መርሆዎች ተገዥ የሆነ፣
መ. በሚኖርበት አካባቢ ሕዝብ መሀል በመልካም ሥነ-ምግባሩ የሚታወቅ ፣
ሠ. ቋሚ የመተዳደሪያ ገቢ ያለው፣
ረ. ከማናቸውም ፀረ- ሕዝብ ተግባራት ያልተሰማራና በወንጀል የጥፋተኛነት ሪኮርድ የሌለበት፣
ሰ. ለሚሊሻ አባላት የሚሰጠውን ሥልጠና ለመከታተል ፈቃደኛ የሆነና ስልጠናውን በአግባቡ
ተከታትሎ የወሰደ፣
ሸ. ለወታደራዊ እንቅስቃሴ ብቃት ያለው
15. የሚሊሻ አባል ግዴታና ኃላፊነቶች
1. የአገርን ሉአላዊነትና ህገ- መንግስታዊ ሥርዓቱን ከማንኛውም የውስጥና የውጭ ጣላቶች
የመጠበቅ፣
2. በህገ-መንግስቱ የተረጋገጠ የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ማክበርና የማስከበር፣
3. የሚሰጠውን ተገቢ የሥራ ተልዕኮ በተወሰነው ጊዜ አጠናቅቆ ለበላይ ሓላፊ በተቀመጠው ጊዜ
ውስጥ ሪፖርት የማድረግ፣
4. አስፈላጊውን መረጃ የመጠየቅ የመቀበል፣
5. የአካባቢውን ሕዝብ ፀጥታ አደጋ ላይ የሚጥሉ መረጃዎች ሲደርሱት ወዲያውኑ ባገኘው
ፈጣን የመገናኛ ዘዴ ለበላይ አካል የማስተላለፍ ፣
6. ሕዝብ በሚያካሂዳቸው የልማት ስራዎች ግንባር ቀደም በመሆን አካባቢውን የማልማት፣
7. ከፖሊስና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ተቀናጅቶ በመስራትና የሰራዊቱ እንቅስቃሴ ያለ እክል
ይካሄድ ዘንድ አስፈላጊ የሆኑትን መረጃ የማሰባሰብና ለሚመለከተው የሚሊሻ ጽ/ቤት
የማስተላለፍ፣
8. ወንጀል ሲፈጽሙ የተገኙ ግለሰቦችን ይዞ ለፖሊስ አካል ማቅረብ፣
9. በማንኛውም መንገድ የህብረተሰቡን ፀጥታ የሚያውኩ ሀይሎችን በመከላከል ፀጥታውን
አስተማማኝ የማድረግ፣
10. ከበላይ ኃላፊ የሚሰጡ ማንኛውንም ህጋዊ የሆኑ ትእዛዞችን በመቀበል የመፈጸም መታወቂያ
የመያዝ፣
16. የሚሊሺያ አባላት መብቶች

A/K
1. ሠላምና ፀጥታን ለማስከበር የሚሆኑ መሳሪያዎችን ጠይቆ የመታወቅ፣
2. ሚሊሻው ፀጥታን የማስከበር ተልእኮውን በመወጣትና ተያዥነት ባላቸው ተግባራት
ተሰማርተው እያሉ ከተሰዋና፣ የአካል ጉዳት ቢደርስበት ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ ያገኛል፡፡
ዝርዝሩ ወደፊት በመመሪያ ይወሰናል፡፡
3. የተሰጠውን ጉልህ ተግባር እያከናወነ ባለበት ጊዜ ለሚያደርሰው ጉዳት ህጋዊ ተጠያቂነት
አይኖረውም፡፡
4. እንደአስፈላጊነቱና አቅም በፈቀደ መጠን ህብረተሰቡን በማስተባበር ደንብ ልብስ የማግኘት
17. የተከለከሉ ተግባራት
አግባብ ባለው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ የሚሊሻ አባላት
የሚከተሉትን ተግባራት መፈፀም የተከለከለ ይሆናል፡፡
1. ተልእኮውን ላለመቀበል ምክንያት ፈጥሮ ከአካባቢው መጥፋት
2. ያለስራ ትጥቅ ይዞ በየትኛውም ቦታ መዘዋወር፣
3. በጥበቃ ወቅት መጠጥ መጠጣት፣ተዳራራቢ ስራ መያዝ፣ ጉዳዩ ከማይመለከተው ሰው ጋር
በመሆን ከጥበቃ ቦታ መራቅና የጥበቃ ስራን የሚያደናቅፍ ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት
መፈጸም፣
4. በመንግስትና በህዝብ የተሰጠን ኃላፊነትና ትጥቅ ለቤተሰብ ወይም ለግል ጥቅም ማዋል
5. ያለፈቃድ ከሰራ ቦታ መጥፋት፣
6. መታወቂያን የመያዝ ግዴታን አለመፈጸም፣
7. ለስራ የተሰጠን ንብረትና ትጥቅ ከስራ ውጭ ለሆነ ግልጋሎት ማዋል፣ማበላሸትና ማጥፋት፣
8. ከወንጀል አድራጊዎች ጋር በጥቅም በመተሳሰር ወደ ህግ እንዳይቀርቡ ማድረግ፣
9. አግባብ ካለው አካል በህግ ስር የሚገኙ ተጠርጣሪዎች እንዲያምልጥ ማድረግ በጉቦና
በዝምድና መስራት ፡፡
10. ከሌቦችና ሽፍቶች ጋር ማበር፣ ለነሱም መሳሪያ ማከራየት ፣ሚስጢር ማካፈል፣
11. ለጸጥታ ማስጠበቅ ስራ በተረከበው ትጥቅ የህዝቡን መብት መዳፈር ፣ሰዎችን በመሳሪያ
ማስፈራራት፣ መምታት ፣
18. ስለ ትጥቅ
1. ሚሊሻ ትጥቅ የሚታጠቀውና የሚፈታው በቀበሌው ህዝብ ውሳኔና በወረዳው ሚሊሻ ጽ /ቤት ድጋፍ
ነው፤
2. በወንጀል የተጠረጠረ አባል ጉዳይ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚያገኝ ድረስ ትጥቅ በፖሊስ ጣቢያ
ይቀመጣል፡፡ ለረጅም ጊዜ ከአካባቢው ርቆ ሄዶ በሚቆይበት ጊዜም እንዲሁ፡፡ ዝርዝሩ በመመሪያ
ይወሰናል፡፡
3. ማንኛውም የሚሊሺያ አባል ያልተመዘገበና ህጋዊ ያልሆነ ትጥቅ መያዝ አይችልም፡፡

A/K
19. ስለ ተጠያቂነት
ማንኛውም አባል ለሰራው ህገ-ወጥ ተግባር በግሉ ተጠያቂ ነው፡፡
20. ስለ አደረጃጀት
አደረጃጀቱ የመንግስትን አወቃቀር የተከተለ ይሆናል፡፡ ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል፡፡
21. ስለ ስምሪት
1. የሚሊሺያ አባላት ስምሪት ተልእኮውንና አደረጃጀታቸውን መሰረት ያደረገ ሆኖ የጸጥታ ችግር
ሲኖር ብቻ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
2. ስምሪቱ በሚሊሺያ ሕይወትና ኑሮ ላይ ጉዳትና ምስቅልቅል የሚፈጥር መሆን የለበትም፡፡
3. ማንኛውም ሚሊሻ በሰላም ጊዜ ከምርት ተግባሩ ተፈናቅሎ ስምሪት አይሰጠውም፡፡
4. በዋነኛነት የሚሊሻያው ስምሪት በጎጥና በቀበሌ ክልል ውስጥ ይሆናል፣
5. በአገር ሉኡላዊነት ላይ ችግር ካልገጠመ በስተቀር ማንኛውም የሚሊሺያ አባል ከቀበሌው ክልል
ውጪ ስምሪት አይሰጠውም፡፡
22. ስለ ሥልጠና
የአካባቢውን ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ የሚሊሻውን የህግ ግንዛቤ ብቃት ለማሳደግ
ከሚመለከተው የፍትህ አካላት ጋር በመቀናጀት ወሳኝነት ያለው የሚሊሻ አባላት ስልጠና በአጭር
ጊዜ የሚሰጥ ሆኖ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ይሆናል፡፡
ሀ. ስለወንጀል መከላከል፣
ለ. ስለኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ
ሐ. ስለሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች አጠባበቅ
መ. ወታደራዊ ትምህርት /በንድፈ ሀሳብና በተግባር / የተደገፈ
ሠ. ስለመረጃ አያያዝን ማስተላለፍ
23. ሚሊሺያው ከሕዝብ ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት
1. ሚሊሻው የሚፈጽማቸው ተግባሮች በጠቅላላው የመላው ሕዝብ ጥቅም የሚመለከቱ መሆናቸውን
ምን ጊዜም መዘንጋቱ የለበትም፡፡
2. ሕዝቡ ተጠቃሚ የሚሆንባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እሴቶች ሁሉ ሚሊሺያውም
ተጠቃሚ ይሆናል፡፡
3. ሚሊሻ በማንኛው ልማትና በመልካም አስተዳደር ተግባሮች የመሳተፍ
4. ሚሊሻ በማንኛውም ጊዜ የህዝብ አመኔታ ባጣ ጊዜ ከኃላፊነት ተግባሩ ይገለላል፡፡

24. ምስጢር ስለመጠበቅ


1. መረጃው ተራ ወይም በሕዝብ ዘንድ የታወቀ ካልሆነ በቀር በስራ አጋጣሚ ወይም በሌላ አኳኃን
ያገኘውን መረጃ ለማንኛውም ሰው መግለጽ የለበትም፡፡

A/K
2. ሥልጣን ባለው ኃላፊ በአግባቡ ካልታዘዘ በቀር በአሰራር ሚስጢር የተባሉትን ሚስጢራዊ
ጉዳዮችን ሁሉ በስራ ላይም ሆነ ከስራ ውጪ ጉዳዩን እንዲያውቀው በደንቡ ለተፈቀደለት ሰው
ካልሆነ በቀር ለሌላ ማንኛውም ሰው መግለጽ የለበትም፡፡
25. ስለ ዲስፕሊን ቅጣት
በዚህ ደንብ አንቀጽ 10 ስለ ዲስፕሊን ጥፋቶች ቅጣት የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በአንቀጽ 17
የተጠቀሱትን የተከለከሉ ተግባራት ፈጽሞ የተገኘ አባል የወንጀል ተጠያቂነት የተጠበቀ ሆኖ በአንቀጽ
8,9 እና 10 በተመለከቱት መሰረት በዲስፕሊን ይቀጣል፡፡

ክፍል ስድስት

ስለሚሊሺያ አባላት ስንብትና የአርበኝነት ክብር

ስለሚሊሺያ አባላት ስንብትና የአርበኝነት ክብር

26. ስለ ስንብት
1. ማንኛውም የሚሊሺያ አባል ከሚሊሺያ አባልነት ለመሰናበት በሚፈለግበት ጊዜ
ምክንያቱን ገልጾ በጽሁፍ ለቀበሌ የሚሊሺያ ሀላፊዎች በማቅረብ ጥያቄው በቀበሌውና
በወረዳው ሚሊሺያ ጽ/ቤት ተቀባይነት ሲያገኝ የመንግስትና የህዝብ ንብረት አስረክቦ
ይሰናበታል፡፡
2. ስንብት የጠየቀ የሚሊሽያ አባል ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ግዴታውን እየፈጸመ መጠባበቅ
ይኖርበታል የፈጸመውም ጥፋት ካለ ተቀጥቶ ይወጣል፡፡
3. ስንብት የጠየቀ የሚሊሺያ አባል ጥያቄውን ካቀረበ ከሁለት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ
ውሳኔ ይሰጣል፡፡
4. ሚሊሻ የህዝብ አመኔታ ባጣ ጊዜ ( የህዝብን ጥቅም በጎዳ ጊዜ) ሕዝቡ ሊሽረውና
ሊያነሳው ይችላል፡፡
27. ስለ አርበኝነት ክብር
1. በእርጅና ምክንያት ትጥቅ መያዝ የማይችሉ የሽማግሌ አባላት የታጠቁትን የጦር መሳሪያ
ለሚሊሻ ጽ/ቤት አስረክበው በክብር ከአባልነት ይሸኛሉ፡፡
2. አካውንት የሚሊሺያ አባላት ልዩ ክብር ይሰጣቸዋል ፡፡ በሕይወት እስካሉ ድረስ ስማቸው
በሚሊሺያ አባላት መዝገብ ውስጥ ሰፍረው ይተዳደራሉ፤ ሆኖም ሁሉንም የሚሊሻውን

A/K
ግዴታዎች ለመፈጸም አይገደዱም ፡፡ የክብር የምስክር ወረቀትም ይሰጣቸዋል፡፡ ዝርዝሩ
በመመሪያ ይወሰናል፡፡
ክፍል ሶስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

28. መመሪያ የማውጣት ሥልጣን


የፍ/አ/ጉ/ ማስ/ቢሮ ለዚህ ደንብ የአፈፃፀም መመሪያዎችን ማውጣት ይችላል፡፡
29. ተፈጻሚነት የሌላቸው ህጎች
ይህንን ደንብ የሚቃረን ደንቦች መመሪያዎች የልማድ አሰራሮች በዚህ ደንብ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ
ተፈፃሚነት አይኖራቸውም፡፡
30. ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ ደንብ በክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ከፀደቂበት ከመስከረም 6 ቀን 1997 ዓ/ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አዋጅ
ኃይለማሪያም ደሳለኝ
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ርዕሰ መስተዳድር

A/K

You might also like