You are on page 1of 5

/@rsïCÂ ?

ZïC KLL mNGST


db#B nU¶T Uz@È
DEBUB NEGARIT GAZETA OF THE SOUTHERN NATIONS, NATIONALITEIS AND
PEOPLES REGIONAL STATE

ሦስተኛ ዓመት ቁጥር  bdb#B B/@éC½B/@rsïCÂ ?ZïC


KL§êE mNGST M ክር b@T 3rd Year No. 1
አዋሳ ጥር / ጠባቂነት የወጣ አዋጅ Awassa 27rd September 1997

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሐረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰሮች አሠራር፣ ሹመት እና
ደመወዝ ለመወሰን የወጣ ደንብ ቁጥር 17/96

መግቢያ
“የመንግሥት አሠራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት” የሚለውን ሕገ መንግሥታዊ መርሀ
ለመተግበር እና የሕዝብን የማወቅ መብት ለማረጎገጥ እንዲቻል ሕዝብ ወቅታዋ፣ የተሟላ እና ተፈላጊ መረጃን
የሚያገኝበት አሠራር ለመዘርጋት በማስፈለጉ፣

የመንግሥት ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች ዕቅዶች እና አሠራሮች ለሕዝብ በተሟላ መልክ ታውቀው ሕዝቡ
ባለቤትነቱን በማረጋገጥ በቀጥተኛ ተሳትፎው እንዲተገብራቸው ለማድረግ እና ከተሞክሮው የሚገኙ
ውጤቶችን በማስረጽ በልማት እና በዴሞክራሲየዊ ሥረዓት ግነባታ መርሆዎች ላይ ብሔራዊ መግባባት
እንዲፈጠር ለማገዝ የሚያስችል የሕዝብ ግንኙነት ሥራ በጋራ ራዕይና ተልዕኮ መመራት ያለበት መሆኑን
በመገንዘብ፣

በተሻሻለው የ 1994 ዓ.ም የደቡብ ብሔሮች፣ ብሐረሰባችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት ሕገ መንግሥት አንቀጽ 66
ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት የማከተለው ደንብ ወጥቷል፡፡

ክፍል አንድ
ጠቅላላ
1. አውጭው ባሥልጣን
በደቡብ ብሐሮች ብሐረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት አስፈፃሚና ፈፃማ አካላትን ሥልጣንና
ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 65/95 በአንቀጽ 56 ንዑስ አንቀጽ 1 ለክልሉ መስተዳድር
ም/ቤት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቲል፡፡
2. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ “የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የሕዝብ ግንኙነት
ኦፊሰሮች አሠራር፣ ሹመት እና ደመወዝ ለመወሰን የወጣ የክልል መስተዳድር ም/ቤት ደንብ ቁጥር
17/1996” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
3. ትርጓሜ
1.3. “የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ 6 ያለው የወል ተግባርና ኃላፊነት
የተሠጠው የተለያየ ደረጃ የተሾመ የመንግሥት ቃለ አቀባይ ማለት ነው፡፡
1.4. “ቢሮው” ማለት የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል የማስታወቂያና ባህል ቢሮ ማለት ነው፡1
1.5. “ደረጃ” ማለት የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር የኃላፊነት መጠን እና የደመወዝ ልክ የሚገናዘብበት
ከሲቪል ሰርቪስ የተወሰደ ወይም የሹመተ መጠሪያ ነው፡፡
4. የተፈፃሚነት ወሰን፣
ይህ ደንብ ተፈፃሚ የሚሆነው ዝርዝራቸው በዚህ ደንብ ውስጥ በተመለከተ መሥሪያ ቤቶተ እና
በቀጣይም እንደየአግባቡ እንዲሾምላቸው በማደረጉ መ/ቤቶችውስጥ ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለት
የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰሮች የአሠራር መርሆዎች

5. የማንኛውም መ/ቤት ተመድቦ የሚሰራ የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ሥራውን የሚያከናውነው


በሚከተሉት መርሆዎች መሠረት ይሆናል፡፡
5.1. ሕገ መንግሥታዋ ዕውቀትን እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማራመድ፣
5.2. መልካም አስተዳደርን እና የሕዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎን ማረጋገጥ፣
5.3. የመንግሥታዋ ፖሊሲ ዕቅድ አፈፃፀም እና የወጤት ምዘና ባህልን ማስረጽ
5.4. የመንግሥት የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት መሠረታዊ የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት መሆኑን
ማረጋገጥ፣
5.5. የሕዝብ የመረጃ ተደራሽነት ማረጋገጥ፣
5.6. ስትራቴጂክ አስተሳሰብን እና የአቅም ግነባታ እውቀትን ማስረጽ፣
5.7. የልማት አስተሳሰብን ማስፋፋት እና የልማት ኢንፎርሜሽን ተደራሽነትን ማረጋገጥ፣
ክፍል ሦስት

6. የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰሮች የወል ተግባርና ኃላፊነት


በማንኛውም መ/ቤት ተመድቦ የሚሰሩ የሕዝብ ግግኙነት ኦፊሰር የማከተሉት ተግባር እና ኃላፊነት
ይኖረዋል፡፡
6.1. የተመደበበት መ/ቤት ቃል አቀባይ ሆኖ ይሰራል፡፡
6.2. የመ/ቤቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ መሠረት ያደረገ ዓመታዊ የሕዝብ ግነኙነት ሥራ ዕቅድያዘጋጃል፣
የዕቅዱን እና የዕቅድ አፈፃፀም መርሃ ግብሩን ለቢሮው ያስተላልፋል፡፡
6.3. በመ/ቤቱ ውስጥ የኢንፎርሜሽን አሰባሰብ፣ አደረጃጀት እና ልውውጥ የሥራ ክፍሎችን
በማቀናጀት የመ/ቤቱን የመረጃ ሥርጭት አቅም ይገነባል፣ የአቅም ግነባታ ሃሳቦችን ለመ/ቤቱ
ማኔጅመንት ያቀርባል፡፡
6.4. የተለያዩ የሕዝብ ግነኙነት አግባቦችና መሳሪያዎች በመጠቀም ወቅታዊ፣ ተፈላጊ እና የተሟላ
መረጃ ያሰራጫል፣
6.5. ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጁዎችን፣ ሕጐችን፣ ደንቦችን እና መመሪያዎችን በማመንጨት ሥራ
ይሳተፋል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፡፡
6.6. በመ/ቤቱ ዕቅዶች ጥናት፣ ቀረፃ የአፈፃፀም ክትትል እና ግምገማ ሥራዎተ ይሳተፋል፣
6.7. በመ/በቱ አሰራር ላይ ችግሮች ይፈጠራሉ ብሎ በማገምትበት ወቅት ወይም ችግሮች
መከሰታቸውን ሲየውቅ በተቻለ ፍጥነት የችግሮቹን መግለጫ ከመፍትሔ ሃሳቦች ጋር
አዘጋጅቶ ለመ/ቤቱ ኃላፊ ያቀርባል፡፡
6.8. የሙስና ድርጊቶች፣ አስተሳሰቦችን እና ብልሹ አሰራሮችን በጽናት ይታገላል፣ ራሱንም አርአያ
አድርጐ ያቀርባል፡፡
6.9. የሕዝብ ግንኙነት ሥራው ያለበትን ደረጃ በጊዜው እያጠና የማሻሻያ እምርጃዎችን ይወስዳል፣
እንዲወስዱ ያደርጋል፡፡
7. የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰሮች አሠራር

7.1. የሚዲያ ውጤቶችን ይከታተላል፣ አስፈላጊ የሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ አጭር መግለጫ
(media digest) ያጠናቅራል፣ ለሥራው በግብዓትነት ይጠቀማል፣
7.2. ለጋዜጠኞች የመግባቢያ ፈቃድ ይሰጣል፡፡
7.3. በክልል ውስጥ ካሉ የመገናኛ ብዙሃን ጋር ግንኙነት ይፈጥራል፣ የሚዲያ ጽሁፎችን
አዘጎጅቶ ያሳትማል፣ የሚዲያ መግለጫ ይሰጣል፣
7.4. የኘሬስ የሊዝ የውስጥ ሕትመቶችን፣ ንግግሮችን እና መጣጥፎችን ያዘጋጃል፣ የአርትኦት
ሥራም ይሰራል፣፣
7.5. በስብሰባዎች፣ በፓናል ውይይቶች እና ተመሳሳይ መድረኮች ላይ በመገኘት መግለጫ እና
ማብራሪያ ይሰጣል፡፡
8. ተጠሪነት
8.1. የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰሩ ተጠሪነቱ ለመ/ቤቱ ኃላፊ ይሆናል
9. ሪፖርት፣
የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰሩ የዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የሩብ ዓመት እና የወር ዕቅድ እና የአፈፃፀም
ሪፖርት ለቢሮው እና ለመ/ቤቱ ኃላፊ ያቀርባል፡፡
10. ስለቅንጅት
ቢሮው የክልሉን የሕዝብ ግነኙነት ኦፊሰሮች ሥራ ያቀናጃል /ዝርዝሩ ቢሮው በሚያወጣው የአፈፃፀም መመሪያ
ይወሰናል፡፡/
10.1. የውይይት መድረክ፣ ፓናል፣ ኤግዚቪሽን፣ ወርክሾኘ ያዘጋጃል፣ ያስተባብራል፣

ክፍል አራት
የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰሮች ደረጃ ደመወዝ እና ሹመት

11. የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰሮች የሚከተሉት ደረጃዎች ይኖራቸውል፡፡


11.1. የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ደረጃ I እና II በወረዳ
11.2. የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ደረጃ III እና IV በዞን
11.3. የሕዝብ ግግኙነት ኦፊሰር ደረጃ V እና VI በክልል
12. የአንቀጽ 11 ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ደመወዝና የሥራ ኃላፊነታቸው በሚመለከት እንደየሥራ ስፋቱ
ሁኔታ እየታየ በመስተዳድር ም/ቤት የሚወሰን ይሆናል፡፡
13. ቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰሮችን መልምሎ በማቅረብ በርዕሰ መስተዳድሩ ያፀድቃል፡፡
14. እያንዳንዱ መ/ቤት ለሹመት የሚቀርበውን የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር አስመልክቶ ከቢሮው ጋር
እየተመካከረ የሚፈፀም ይሆናል፡፡

ክፍል አምስት
ስለሥራ ዝውውር እና ምደባ
15. ይህ ደንብ ከመውጣቱ በፊት በሕዝብ ግነኙነት የሥራ መደብ ላይ ከነበሩ ሠራተኞች መካከል የሹመት
መሥፈርቱን የሚያሟሉ ወደ ተመሳሳይ የሲቪል ሰርቪስ መደብ ተዛውረው በመ/ቤቱ ውስጥ ይመደባሉ፡፡
በመ/ቤቱ ውስጥ ክፍት የሥራ መደብ ከሌለ ወደ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ተልከው የሥራ
ምደባእንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡

ክፍል ስድስት

16. የሥራ መመሪያ ስለማዘጋጀት፣


በዚህ ደንብ ያልተሸፈኑ ዝርዝር የሥራ መመሪያዎች በማስታወቂያ ባህል ቢሮ ይዘጋጃል፣
17. ተፈፃሚነት የማይኖራቸው ደንቦች፣
ከዚህ ደንብ ጋር የሚቃረኑ ማናቸውም ሌሎች ደንብ በዚህ ደንብ ውስጥ በተሸፈኑት ጉዳዮች ላይ ተፈፃማ
አይሆኑም፡፡
18. በደንብ ያልተካተቱ ቀሪ የክልል መ/ቤቶችና በዞንና በልዩ ወረዳ የሚኖሩን የሕዝብ ግግኙነቶች ኦፊሰሮች
የማስታወቂያና ባህል ቢሮ ከክልሉ የአቅም ግነባታ ማስተባበሪያ ቢሮ ጋር በመሆን በማያወጡት ደረጃ
ይወሰናል፡፡
19. ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ ደንብ በመስተዳድር ም/ቤቱ ከፀደቀበት ከመጋቢት 23 ቀን 1996 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

ኃ/ማሪያም ደሳለኝ
የደቡብ ብ/ብ/ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት
ርዕሰ መስተዳድር

You might also like