You are on page 1of 9

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት

ደቡብ ነጋሪት ጋዜጣ


DEBUB NEGARIT GAZETA
OF THE SOUTHERN NATIONS NATIONALITIES AND PEOPLES
REGIONAL STATE

፳፪ ¾ ›mT q$_R ፭ bdb#B B/@éC½B/@rsïCÂ ?ZïC KL ል M ክር


Hêú HÄR ፱ qN ፪ሺ፰ ›.M b@T -ÆqEnT ywÈ ደንብ

ደንብ ቁጥር ፻፴፭/፪ሺ፰


የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት
ቁጥጥር ባለስልጣንን ለማቋቋም የወጣ ደንብ ቁጥር ፻፴፭/፪ሺ፰

የሕብረተሰቡ ጤና ደህንነቱ፣ ፈዋሽነቱና ጥራቱ ካልተረጋገጠ ዘመናዊም ሆነ ባህላዊ

መድኃኒት መጠበቅ ያለበት በመሆኑ፤

ደህንነቱና ጥራቱ ባልተጠበቀ ምግብ ምክንያት በሕብረተሰቡ ጤና ላይ ሊደርስ

የሚችለውን የጤና ችግር መከላከል እና የሕገ ወጥ መድሃኒቶችንና ምርት-ሥርዓትን መከልከልና መግታት


በማስፈለጉ፣

በጤናው ዘርፍ ሰፍኖ የቆየውን የተበታተነና ጥራት የጎደለውን የአስተዳደርና የቁጥጥር ስርዓት ቀልጣፋና
ውጤታማ ለማድረግ እንዲቻል አዲስና የተቀናጀ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር
ሥርዓት ማስፈን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን
ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፩፻፷፩/፪ሺ፰ አንቀጽ ፴ 5 በተሰጠው ስልጣን
መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡

፩. አጭር ርዕስ

1
ይህ ደንብ “የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣንን ለማቋቋም የወጣ ደንብ
ቁጥር 1 ፻፴፭/፪ሺ፰” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
፪. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡-
፩. “ምግብ” ማለት ማንኛውም በጥሬነቱ፣ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የተዘጋጀ ለንግድ
ወይም በሌላ መንገድ ለህብረተሰቡ አገልግሎት ቀርቦ ለሰው ምግብነት የሚውል ነገር ሲሆን
ውኃ ወይም ሌላ መጠጥ፣ የሚታኘክ ማስቲካ፣ ተጨማሪ ምግብ እንዲሁም ምግብ
ለማምረት፣ ለማዘጋጀት ወይም ለማከምና ማንኛውም ንጥረ ነገር የሚያካትት ሆኖ ትንባሆና
ለመድኃኒትነት ብቻ የሚያገለግሉ ንጥረ ነገሮችን አይጨምርም፤
2. “መድኃኒት” ማለት የሰውን በሽታ ለመመርመር፣ ለማከም፣ ለማስታገስ ወይም ለመከላከል
የሚያገለግል ማንኛውም ንጥረ ነገር ወይም የንጥረ ነገሮች ውህድ ሲሆን የናርኮቲክና
ሣይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን፣ ፕሪከርሰር ኬሚካሎች፣ የባህል መድኃኒ-ቶች፣ ተደጋጋፊ
ወይም አማራጭ መድኃ-ኒቶች፣ መርዞች፣ ደምና የደም ተዋጽኦዎች፣ ቫክሲኖች፣ ጨረራ
አፍላቂ መድኃ-ኒቶች፣ ኮስሞቲኮች፣ የሳኒተሪ ዝግጅቶች እና የሕክምና መሣሪያዎችን
ይጨምራል፤
3. “የናርኮቲክ መድኃኒቶች ወይም ሳይኮትሮፒክ ንጥረ ነገሮች” ማለት ኢትዮጵያ በተቀበለችው
የተባበሩት መንግሥታት የናርኮቲክ መድኃኒቶች ወይም የሳይኮትሮፒክ ንጥረ ነገሮች ቁጥጥር
ስምምነት መሠረት ዓለም-አቀፍ ቁጥጥር የሚካሄድበት መድኃኒት ሲሆን አስፈጻሚ አካሉ
የናርኮቲክ ወይም የሳይኮትሮፒክ መድኃኒት ብሎ የሚሰይመውንም ይጨመራል፤
፬. “የትምባሆ ዝግጅት” ማለት በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ከትምባሆ ቅጠል የተዘጋጀ
በማጨስ፣ በመሳብ፣ በማኘክ ወይም በማሽተት የሚወሰድ ማንኛውም ንጥረ ነገር ነው፤
፭. “የሕክምና መሣሪያ” ማለት የሰውን በሽታ ለመመርመር ወይም ለማከም በውስጥ ወይም
በውጭ አካል ላይ ጥቅም ላይ የሚ-ውል ማንኛውም መሣሪያ ወይም መገልገያ ሲሆን የተለያዩ
የመመርመሪያ፣ የላቦራቶሪ፣ የቀዶ ህክምና፣ የጥርስ ሕክምና መሣሪያ-ዎች እና የቁስል መስፊያ
ክሮችን፣ ሲሪንጆ-ችን፣ መርፌዎችን፣ ፋሻ፣ ጐዝ፣ ጥጥና መሰል ዝግጅቶችን፣ ሰው ሰራሽ
ጥርሶችን፣ ኬሚካሎችን፣ የጨረራ ፊልሞችንና ሌሎች መሰል መሳሪያዎችና መገልገያዎችን
ይጨምራል፤
፮. “የሳኒተሪ ዝግጅት” ማለት የሰው ወይም የቤት ውስጥ ንጽህናን ለመጠበቂያ የሚያገ-ለግል
ማንኛውም ዝግጅት ሲሆን ፓዶችን፣ ታምፖችን፣ የጥርስ ንጽሕና መጠበቂያ ዝግጅቶችን፣ የላብ
መምጠጫዎችን እና ዲተርጀንቶችን ይጨምራል፤

፯. “ባህላዊ መድኃኒት” ማለት የእጽዋት፣የእንስሳት ወይም የማዕድን ተዋጽኦ ሆኖ በነጠላም


ሆነ በመቀላቀል ለሰውም ሆነ ለእንስሳት ሕክምና አገልግሎት የሚውል ዝግጅት ነው፤

2
፰ “ኮስሞቲክ” ማለት ሰውነትን ለማጽዳት፣ለማስዋብ፣ ደምግባት ለመጨመር ወይም የአካልን
ቅርጽና አሠራሩን ሳይቀይር ገጽታን ለመቀየር በገላ ላይ የሚደረግ ማንኛውም ዝግጅት
ሲሆን የቆዳ ቅባቶችን፣ሎሽኖችን፣ ሽቶዎችን፣የከንፈር ቀለሞ-ችን፣ የጥፍር ቀለምና
ማስለቀቂያ፣ የዓይንና የፊት ማስዋቢያ፣ የጸጉር ማቅለሚያዎችን፣የጠረን መቀየሪያ
ዝግጅቶችን፣ ሜዲኬ-ትድ ሳሙናዎችን እና ለእነዚህ ዝግጅቶች መሥሪያ የሚውሉ ንጥረ
ነገሮችን ይጨምራል፤
፱. “የመድኃኒት ንግድ ሥራ” ማለት መድኃ-ኒቶችን ለትርፍ አላማ ማምረት፣እንደገና ማሸግ፣
ማስመጣት፣ መላክ፣ በጅምላ ማከፋ-ፈል ወይም በችርቻሮ ማደል ሲሆን ጥራት
መመርመርን፣ ሳይንሳዊ ቢሮ ማቋቋምና ምርምር ማካሄድን እና በንግድ ወኪልነት
መሥራትን ይጨምራል፤
፲. “የመድኃኒት ማዘዣ ወረቀት” ማለት ፈቃድ ባለው የሕክምና ባለሙያ ተጽፎ ለሕሙማን
የሚሰጥ የመድኃኒት ዕደላ ትዕዛዝ ነው፤
፲ 1. “የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት” ማለት በወጣው የጤና ቁጥጥር ደረጃ መስፈርት
መሰረት በምግብ፣ በመድኃኒት ወይም በጤና ወይም በጤና ነክ አገልግሎት ወይም የንግድ
ሥራ ለሚሰማራ ሰው የሚሰጥ የሥራ ፈቃድ ነው፤
፲፪. “አስመስሎ ማቅረብ” ማለት የምግብ ወይም የመድኃኒት ማሸጊያ፣ መለያ፣የንግድ ምልክት፣
የንግድ ስም ወይም ማንኛውንም ዓይነት ልዩ ምልክት በመጠቀም ምግቡ ወይም መድኃኒቱ
በእውነተኛው አምራች እንደተመረተ በማስመሰል ወይም የምግብነት ወይም የመድኃኒትነት
ይዘትና ባህርይ ለውጦ በማቅረብ በሰው ጤና ላይ ጉዳት ማስከተል ነው፤
፲፫. “ተቆጣጣሪ” ማለት በዚህ ደንብ መሠረት የቁጥጥር ተግባራትን ለማከናወን አግባብ ባለው
አካል ሥልጣን የተሰጠው ማንኛውም ባለሙያ ነው፤
፲፬. “ቆሻሻ” ማለት ከኢንዱስትሪዎች፣ከእርሻ ቦታዎች፣ ከትምህርት ቤቶች፣ከመኖሪያ ቤቶች፣
ከንግድ ስፍራዎች፣ከጤናና ምርምር ተቋማት፣ ከመጸዳጃ ቤት ወይም ከሌሎች መሰል
ተቋሞች የሚወጣና በሰው ወይም በእንስሳት ጤና ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ፈሳሽ፣ደረቅ
ቆሻሻ ወይም ሌላ ቆሻሻ ነው፤
፲፭. “የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ጉድለት” ማለት ሰው በሚኖርበት አካባቢ የሚገኝ በአካላዊ እድገት፣
በጤና ወይም በአኗኗር ዘይቤ ላይ ተጽዕኖ ሊያስከትል የሚችል ማናቸውም ሁኔታ ነው፤
፲፮. “የጤና ባለሙያ” ማለት የሰውን ጤና ለመጠበቅ ወይም አገልግሎት ለመስ-ጠት አግባብ
ባለው አካል እንደ ጤና ባለሙያ የተመዘገበ ሰው ነው፤
፲፮ “ የሕክምና ባለሙያ” ማለት ሕመምተ-ኛውን በመመርመር የበሽታውን ዓይነት የሚለይና
በመድኃኒት ወይም አካልን በመቅደድ የሚያክም የሰው ሐኪም ወይም እነዚህኑ ተግባራት
እንዲያከና-ውን በአስፈጻሚው አካል የተፈቀደለት የጤና ባለሙያ ነው፤

3
፲፰ “የመድኃኒት ባለሙያ” ማለት አግባብ ባለው አካል የሙያ ሥራ ፈቃድ የተሰጠው
ፋርማሲስት፣ ድራጊስት ወይም ፋርማሲ ቴክኒሻን ነው፤
፲፱. “ባህላዊ ሕክምና” ማለት አገር በቀል የሆነና በልምድ የካበተ እንዲሁም በህብረተሰቡ
ተቀባይነት ያገኘ ዕውቀት ሆኖ የዕጽዋትን ወይም የእንስሳትን ተዋጽኦ፣ የማዕድናት ወይም
የእጅ ጥበብ በመጠቀም የሚሰጥ የሕክምና አገልግሎት ነው፤
፳ “የባህላዊ ሕክምና አዋቂ” ማለት ባህላዊ ሕክምና ለመስጠት አግባብ ባለው አካል የሥራ ፈቃድ
የተሰጠው ሰው ነው፤
፳፩. “የሙያ ሥራ ፈቃድ” ማለት የጤና አጠባበቅ አገልግሎት ወይም ሌሎች ተዛማጅ
አገልግሎቶችን ለማበርከት እንዲችል ለጤና ባለሙያ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ነው፤
፳፪ “የጤና ተቋም” ማለት የጤና ማበልጸግ፣የበሽታ መከላከል፣ ማከምና መልሶ ማቋቋም
ሥራዎችን ወይም የመድኃኒት ንግድ ሥራን ወይም አገልግሎት የሚያከናውን ማንኛውም
የመንግሥት፣መንግሥታዊ ያልሆነ ወይም የግል ተቋም ነው፤
፳፫. “ጤና ነክ ቁጥጥር የሚደረግበት ተቋም” ማለት ማንኛውም የኅብረተሰብ መገልገያ ተቋም
ሲሆን፣ ትምህርት ቤት፣ ማረሚያ ቤት፣ የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከላት፣የአሳዳጊ አልባ
ህፃናት ማዕከላት፣ መዋዕለ ህፃናት፣ የገበያ ቦታዎች፣ የስፖርት ቦታዎች፣ የመታሻ
ማዕከላት፣ የመዝናኛ ማዕከላት፣ የጸጉር ቤቶችና የውበት ሳሎኖችን ይጨመራል፤
፳፬. “ሥራ ነክ ጤና አጠባበቅ” ማለት በሥራ አካባቢ የሚከሰቱ ወይም ከሥራ ጋር ግን-ኙነት
ያላቸው ኬሚካላዊ፣ ፊዚካላዊና ሥነ ሕይወታዊ ጎጂ ንጥረ ነገሮች በመከላከልና በመቆጣጠር
ሠራተኞች ለአደጋ እንዳይ-ጋለጡ በማድረግ ሳይንሳዊ፣ ቴክኖሎጂያዊና አስተዳደራዊ ዘዴዎችን
በመጠቀም የሠራ-ተኞችን ጤንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ሳይንስ ነው፤
፳፭ “ክልል” ማለት የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግሥት ነው
፳፮.. #አስፈጻሚው አካል$ TKƒ ¾¡MK< የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር
ባለስልጣን ነዉ፡፡
፳፯. “ዳይሬክተር”TKƒ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የጤናና ጤና ነክ
አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዳይሬክተር ነው፡፡
፳፰. “አግባብነት” ያለው አካል$ TKƒ እ”Å ›Óvu< ¾¡MK< vKeM×” ¨ÃU ¾Ö?““ Ö?“
’¡ ›ÑMÓKA„‹“ Ów›„‹ Ø^ƒ lØØ` እ”Ç=ÁÅ`Ó eM×” ¾}cÖ¨< ¾µ” ¨ÃU M¿ ¨[Ç ¨ÃU
¨[Ç“ Ÿ}T ›e}ÇÅ` ¨ÃU K?L }sU ነው፡፡
፳፱ “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፣
፴. “ቢሮ” ማለት የክልሉ ጤና ቢሮ ነው፣
፴፩. “የፌደራል ባለሥልጣን” ማለት የኢትዮጵያ የምግብ፣ መድኃኒት ጤና አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን ነው፡፡
፴፪ ማንኛውም በወንድ ፆታ የተደነገገው ሴትንም ያካትታል፣

4
፫ የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ ደንብ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሁሉም አካባቢዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

፬. መቋቋም
፩. የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከዚህ በኋላ ባለስልጣኑ
እየተባለ የሚጠራ የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የክልሉ መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ
ደንብ ተቋቁሟል፡፡
፪. የባለስልጣንው ተጠሪነት ለቢሮው ይሆናል፡፡

፭. ዋና መሥሪያ ቤት
የባለስልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት ሀዋሳ ሆኖ እንዳስፈላጊነቱ በየአሰተዳደር ዕርከኖቹ ቅርንጫፍ መስሪያ
ቤቶች ሊያቋቋም ይችላል፡፡

፮. ዓላማ
የባለስልጣኑ ዓላማ፡-
፩ የምግብ ደህንነትና ጥራትን፣
፪ የመድኃኒት ደህንነት፣ፈዋሽነት፣ጥራትና አግባባዊ አጠቃቀምን፣
፫ የጤና፣የህክምናና የመድኃኒት ባለሙያዎችን ሙያዊና የስነ-ምግባር ብቃትን፣
፬ የጤና ተቋሞችን ድርጅታዊ ብቃትን፣ እና
፭ የሀይጂንና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ለግልና ለሕብረተሰብ ጤና ተስማሚ መሆኑን፣
፯. ስልጣንና ተግባራት
ባለስልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣

፩. የምግብ፣ የመድኃኒትና በጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥርን ለማስፈጸም የወጡ ሌሎች ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች
ተግባራዊ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፣
፪. የምግብ፣ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥርን ለማስፈጸም የወጡ ሌሎች ህጎችን፣ ደንቦችና መመሪያዎችን
ተግባራዊ ለማድረግ ተቆጣጣሪዎችን ይመድባል፣
፫. የምግቦችን ደህንነትና ጥራት፣ የመድኃኒቶችን ደኅንነት፣ ፈዋሽነት፣ ጥራትና አግባባዊ አጠቃቀም፣ የጤና ባለሙያዎችን
የአገልግሎት አሰጣጥና የሙያ ስነምግባር፣ የሀይጅንና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ጉድለት እና የጤናና ጤና ነክ ቁጥጥር
የሚደረግባቸዉ ተቋማት የቁጥጥር ሥራዎችን ይሠራል፡፡

5
፬. አግባብ ያለው አካል የናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶች አገልግሎት ላይ በሚውሉባቸው ተቋማት ለህሙማን ማዘዝን፣
ማደልን፣ አጠቃቀምን፣ መመዝገብንና ሪፖርት ማድረግን ይቆጣጠራል፣ አለአግባብ መጠቀምን ይከላከላል፣ አጠቃቀምን
አስመልክቶ ለፌደራሉ ባለስልጣንና ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ያደርጋል፡፡
፭. ለመንግስት፣ መንግስታዊ ላልሆኑ ጤና ተቋማት፣ ለጠቅላላና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ጤና
ኬላዎች፣ ክሊኒኮች፣ የመድኃኒት ችርቻሮ ንግድ ድርጅቶች፣ ሚዲካል ላቦራቶሪዎች፣ ዲያግኖስቲክ ኢሜጅንግ፣ የምግብ
አገልግሎት መስጫ ተቋማትና ቁጥጥር የሚደረግባቸዉ ጤና ነክ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣
ያድሳል፣ ያሽጋል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤
፮. በክልሉ የምግብ፣ የመድኃኒት፣ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ፣ የጤና ባለሙያዎች እና የጤናና ጤና ነክ ቁጥጥር
የሚደረግባቸዉን ተቋማት በሚመለከት የመረጃ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፤
፯. በምግብ ወይም በመድኃኒት መመረዝ ወይም መበከል ምክንያት ለሚደርስ የሞት፣ የጤንነት መታወክ መንስኤ የሆነውን
ንጥረ ነገር ልዩ ልዩ ናሙናዎችን በመውሰድ ወይም በመቀበል ለምርመራ ይልካል፣ ምንነታቸውን ያረጋግጣል፣
በዉጤቱም መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፤
፰. የትምባሆ ዝግጅትን፣ ሽያጭን፣ አጠቃቀምን፣ የሚሸጡ ወይም የሚቸረችሩ ድርጅቶችን ማስተዋወቅን፣ አስተሻሸግንና
መለያ አሰጣጥንና አወጋገድን ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊዉን እርምጃ ይወስዳል፤
፱. በክልሉ ውስጥ የወረርሽኝ በሽታ ሲከሰት አስፈላጊ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ መካሄዱን ያረጋግጣል፤ አስፈላጊውን
እርምጃ ይወስዳል፤
፲. በክልሉ ዉስጥ የጤና አገልግሎት ስራ ላይ ለሚሰማሩ የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ይሰጣል፣ የሙያ ስነ-
ምግባራቸውን ጠብቀው ስለመስራታቸው እያረጋገጠ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤ በፌዴራሉ ባለስልጣን የሙያ
ምዝገባና ፈቃድ ለሚሰጣቸው የጤና ባለሙያዎች፣ ለአማራጭና ተደጋጋፊ ህክምና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃዳቸዉ
እንዲታደስ የድጋፍ ደብዳቤ ይሰጣል፣
፲፩. የአገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃ ምግቦች፣ መድኃኒቶችና ጥሬ ዕቃዎቻቸው በአግባቡ መወገዳቸውን ያረጋግጣል፤
፲፪. ከተለያዩ ተቋማት የሚወጡ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ በሕዝብ ጤና ላይ ጉዳት የማያስከትል መሆኑን
ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፣ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን አሰፈላጊውን ዕርምጃ ይወስዳል፣ በቅንጅት ይሰራል፣
፲፫. ሕገ-ወጥ ምግቦችን፣ መድኃኒቶችንና የጤና አገልግሎቶችን ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊ እርምጃዎችንም ይወስዳል፤
፲፬. ለህብረተሰቡ የሚቀርብ የመጠጥ ውኃ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል፤
፲፭. ለሽያጭ የሚቀርቡ ምግቦች፣ መድኃኒቶችንና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች በፌደራሉ ባለስልጣን
መመዝገባቸውን ይቆጣጠራል፤ ያረጋግጣል፤
፲፮. በክልል ደረጃ የጤና ነክ ቁጥጥር የሚደረግባቸዉ ተቋማት ተገቢውን የሐይጅንና አካባቢ ጤና አጠባበቅ መስፈርት
ማሟላታቸውን ያረጋግጣል፤ ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፤
፲፯. ለባህል ህክምና አዋቂዎች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና የሙያ ፈቃድ ይሰጣል፤ ይቆጣጠራል፤ በህጉ መሰረት
አስፈላጊዉን እርምጃ ይወስዳል፤
፲፰. የሥራ ነክ ጤና አጠባበቅን ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊዉን እርምጃ ይወስዳል፤
፲፱. ለሽያጭ የቀረበው ማንኛውም ምግብ፣ መድኃኒት ለሰው ምግብነት ወይም መድኃኒትነት የማይስማማ መሆኑ ሲረጋገጥ
ወይም በህብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል የታመነበትን አደገኛ ኬሚካል በህግ መሰረት ይሰበስባል፤
በአግባቡ መወገዱንም ያረጋግጣል፤
፳. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የመካከለኛ፣ የቅድመ ወይም ድህረ ምረቃ የጤና ተማሪዎች የሚማሩትን ትምህርት
በተግባር እንዲለማመዱ ወደ ጤና ተቋማት እንዲሰማሩና በአግባቡ ልምምድ ማድረጋቸውን ይቆጣጠራል፣ ያረጋግጣል፣

6
፳፩. በክልሉ የሚከናወኑ የምግብ፣ የመድሃኒትና የጤና አገልግሎት የንግድ ማስታወቂያዎች ላይ የቁጥጥር ስራዎችን ይሰራል፣
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፣
፳፪. የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሳል ከሰሳል፣
፳፫. ዓላማውን ለመፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

፰. የባለስልጣንው አቋም
ባለስልጣኑ፡-
፩ በመንግስት የሚሾም ዋና ዳይሬክተርና እንደ አስፈላጊነቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች እንዲሁም፤
፪ ሌሎች አስፈላጊ ሰራተኞች ይኖሩታል፡፡

፱. የዋና ዳይሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር

፩ ዋና ዳይሬክተሩ የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የባለስልጣኑን ሥራዎች ይመራል፣


ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፤
፪ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተመለከተው አጠቃላይ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ዋና ዳይሬክተሩ ፡-
ሀ. በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ የተመለከቱ የባለስልጣኑን ሥልጣንና ተግባራት በሥራ ላይ ያውላል፤
ለ. የባለስልጣኑን ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ ዓመታዊ ዕቅድ፣ የሥራ ፕሮግራምና በጀት አዘጋጅቶ
ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፤

ሐ. ለባለስልጣኑ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል፤ሂሳብ


ያንቀሳቅሳል፤

መ. ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ባለስልጣኑን ይወክላል፤


ሠ. የባለስልጣኑን የሥራ አፈጻጸምና የሂሳብ ሪፖርቶች አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
ረ. ሌሎች አግባብ ካላቸው አካላት የሚሰጡትን ሥራዎች ያከናውናል

፫ ዋና ዳይሬክተሩ ለባለስልጣኑ ሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለባለስልጣኑ


ሌሎች ሃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል፡፡

፲. የምክትል ዳይሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር


ምክትል ዳይሬክተሩ፣

፩ በባለስልጣኑ መዋቅር መሠረት የሥራ ሂደቱን ይመራል፣


፪ ዋና ዳይሬክተሩ በማይኖርበት ወይም ስራውን ለማከናወን በማይችልበት ጊዜና ሁኔታ ሲወከል ተክቶት
ይሰራል፡፡
፫ የምክትል ዳይሬክተሩ ተጠሪነት ለዋና ዳይሬክተሩ ይሆናል፣

7
፲፪. ስለተቆጣጣሪዎች፣
በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ፪ መሠረት የተመደቡ ተቆጣጣሪዎች የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት
ይኖራቸዋል፣
፩. በክልሉ የሚገኙ የጤናና ጤና ነክ ተቋማትን ክፍት በሆኑበት በማንኛውም ሰዓት ይቆጣጠራሉ፣
አስፈላጊውን ዕርምጃ ይወስዳሉ፣
፪. ጤናን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ሁኔታ ተፈጥሯል የሚያሰኝ መረጃ ሲኖረው ወደ ማንኛውም ግቢ ወይም
ቤት ወይም ህንጻ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመግባት ፍተሻ ያደርጋል፣
፫. ምርመራ ለማድረግ ወይም መረጃ ለመሰብሰብ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የተጠረጠሩ ምግቦችና መድኃኖቶች
ላይ ናሙናና ልኮችን የመውሰድ፣ በቪዲዮ የመቅረጽ፣ፎቶግራፍ የማንሳት፣ መረጃዎችን ፎቶኮፒ
የማድረግ እና ውጤቱ እስከሚታወቅ ድረስ በጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል ተብሎ የታመነ ዕቃ ወይም
ማቴሪያል ተለይቶ እንዲቀመጥ ያዛል ያሽጋል፣
፬. የተከለሱ፣ የተበላሹ፣ የተጭበረበሩ፣ የተበከሉ ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት በተጠቃሚው ላይ
ጉዳት ያደርሳሉ ተብሎ የተጠረጠሩ ምግቦችና መድሃኒቶች ላይ የላቦራቶሪ ምርመራ እንዲካሄድ
የማድረግና ውጤቱ እስከሚታወቅ ድረስም በአገልግሎት ላይ እንዳይውሉ ታሽገው እንዲቀመጡ
ያደርጋል፣
፭. ምግቦችና መድኃኒቶች የአገልግሎት ዘመናቸው ሲያበቃ ወይም በዚህ ደንብ መሠረት ጥቅም ላይ
እንዳይውሉ ሲወሰን በተገቢው መንገድ እንዲወገዱ መደረጋቸውን ይቆጣጠራል፣
፮. በማናቸውም ቁጥጥር በሚደረግባቸው የጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎችን መረጃ
በመጠየቅ፣ በማየት፣ በመመርመር፣ ማረጋገጥና አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፣
፯. የሃይጅንና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ቁጥጥር ደርጋል አስፈላገውን እርምጃ ይወስዳል፣

፲፪. በጀት
ባለስልጣኑ የሚከተሉት የበጀት ምንጮች ይኖሩታል፡፡
ሀ. ከክልሉ መንግሥት የሚመደብ በጀት፣
ለ. ከሌሎች ምንጮች የሚገኝ ገቢ፡፡

፲፫. የበጀት ዓመት


የባለስልጣኑ የበጀት ዓመት የክልሉ መንግስት የበጀት ዓመት ይሆናል፡፡
፲፬. የሂሳብ መዛግብትና የሂሳብ ምርመራ
፩. ባለስልጣኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል፡፡
፪ የባለስልጣኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በየዓመቱ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ
በሚሰይማቸው ኦዲተሮች ይመረመራል፡፡
፲፭. የመተባበር ግዴታ

8
ማንኛውም ሰው ይህን ደንብ ለማስፈፀም የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡ 
፲፮. ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ሕጎች
ይህንን ደንብ የሚቃረን ማንኛውም ደንብና መመሪያ ወይም የአሠራር ልምድ በዚህ ደንብ የተሸፈኑ
ጉዳዮችን በሚመለከት ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡
፲፯. መመሪያ የማውጣት ሥልጣን
ቢሮው ይህንን ደንብ በሥራ ላይ ለማዋል የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል፣
፲፰. ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ ደንብ ከጸደቀበት ከህዳር ፱ ቀን ፪ሺ፰ ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

ደሴ ዳልኬ

የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት

ርዕሰ መስተዳድር

You might also like