You are on page 1of 13

የጤና ዘርፍ ሠራተኞች የትርፍ ሰዓት እና ሌሎች ማትጊያዎች ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች

ደንብ ቁጥር ---------/2013

ቀደም ብሎ ጸድቆ እና እየተሰራበት ባለው የጤና ተቋማት ሠራተኞች የተረኝነት እና ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞች ውስጥ

ያልተካተቱ አዳዲስ የጤና አገልግሎትና የትምህርት መስኮች በመከፈታቸው እና በእነዚህ የትምህርት መስኮች የሰለጠኑ

ባለሙያዎች በደንቡ ላይ ባለመካተታቸው የተነሣ ሲሰጡ የነበሩት ማትጊያዎች ባለማግኘታቸው የስራ ተነሳሽነታቸው

ከመቀሱ ባሻገር የመልካም አስተዳደር ችግር መንስኤ ሆኖ በመገኘቱ፤ በአዲስ መመሪያ ማካተት በማስፈለጉ፤

የጤና አገልግሎት ተቋማት ልዩ ልዩ የጥቅማጥቅም እና ሌሎች የማበረታቻ ዓይነቶች ውስጥ በርካታዎቹ ቀደም ሲል

በነበረው መመሪያ ያልተካተቱ በመሆናቸው እና በአሰራር ላይ ከፍተኛ ቅሬታ በመፍጠራቸው እንዲሁም በወቅቱ

የጸደቀው ማትጊያ በተወሰነ ደረጃ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ፤

መመሪያው በተዘጋጀበት ወቅት ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የሙያ ዘርፎችን በአግባቡ በመለየት በተገቢው

እና ሚዛናዊ ሆኖ ያልተካተተ በመሆኑ፤እንዲሁም የቀድሞው መመሪያ ማሻሻል በተወሰነ ደረጃ የጤና ባለሙያውን

በማትጋት የሚሰጠው የጤና አገልግሎት ላጥ ጥራት በመጨመር አወንታዊ አስተዋጽኦ ስለሚኖረው፤

የኢትዮጵያ ፌዳራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሉክ መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀፅ

34 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚከተለውን ደንብ አውጥቷል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ ድንጋጌዎች

1. አጭር ርዕስ

ይህ ደንብ ‹‹የጤና ተቋማት ባለሙያዎችና ሠራተኞች የትርፍ ሰዓት ክፍያ እና ሌሎች ማትጊያዎች ለመወሰን

የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በቁጥር ------------------/2013” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ

በዚህ ደንብ ውስጥ የቃለ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር፡-

1
1. “የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋም” ማለት በፌደራል መንግስት ስር የሚተዳደር የጤና
አገልግሎት የሚሰጥ ሆስፒታል፤ ጤና ጣቢያና ጤና ኬላ ነው፤

2. “ሠራተኛ” ማለት በጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች
የአስተዳደር ሠራተኞች ማለት ነው፤

3. “የትርፍ ሰዓት አበል” ማለት በጤና አገልግሎት ተቋም የሚሰሩ የጤናው ዘርፍ ሰራተኞች ከመደበኛ

የመንግስት የሥራ ሰዓት ውጭ ለተሰጠ የትርፍ ሰዓት አገልግልት የሚፈጸም ክፍያ ማለት ነው፤

4. “ሁለት ፈረቃ” ማለት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ አመሻሹ 11፡30 እና ከአመሻሹ 11፡30 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 2፡
30 ድረስ በሁለት ፈረቃ ተከፍሎ የሚሠራበት የጊዜ ሰሌዳ ማለት ነው፤

5. "የተረኝነት አበል" ማለት በአገልግሎት ሰጪ የጤና ተቋም ውስጥ ሠራተኞች ከመደበኛ የስራ ሰዓት
ውጭ በማታ፤በሳምንት የእረፍት ቀናት ወይንም በብሄራዊ በዓላት ቀን ተረኛ ሆኖ ሲመደብ ለሰራበት
የሚከፈል የአበል አይነት ማለት ነው፤

6. “የቤት አበል” ማለት በመንግሥት የጤና ተቋማት አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኝ ሠራተኛ
የሚከፈል የመኖሪያ ቤት ክፍያ ነው፤

7. "የኃላፊነት አበል" ማለት የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በአመራር ወይም በኃላፊነት የስራ ደረጃ

ላይ ለሚመደቡ ሠራተኞች ሥራ ላይ እስከለ ድረስ ብቻ የሚከፈል የአበል ዓይነት ነው፤

8. “ተጠባባቂ ተረኝነት አበል” (On-Call Payment) ማለት ለድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ከቤት ወይም
ከመደበኛ የስራ ቦታቸው ውጭ ለሚጠሩ ስፔሻሊስትና ሰብ-ስፔሻሊስት ሐኪሞችና እና የድንገተኛ ቀዶ
ሕክምና ባለሙያዎች የሚከፈል ማለት ነው፤

9. “ምቹ ባልሆነ የስራ ቦታ የሚመደቡ ስፔሻሊስት ሃኪሞች ልዩ አበል” ማለት ደረጃው “A” “B” እና “C”
ተብሎ ስልጣን ባለው አካል ለተለዩ የሚከፈል አበል ማለት ነው፡፡

2
10. “ልዩ ክሊኒክ speciality clininc” ማለት በማስተማሪያ ሆስፒታል ውስጥ ለአገልግሎት መስጫ እና
ለመማር-ማስተማር የሚከፈቱ የተለያዩ ልዩ ክሊኒኮች እንደ የልብ፤ የኩለሊት፤ የሳንባና የመሳሰሉት
ማለት ነው፤

11. “የተጋላጭነት አበል” ማለት በጤና ተቋም ውስጥ ለህሙማን አገልግሎት በሚሰጥበት ጊዜ
በባለሙያው ወይም ሰራተኛው ላይ ይደርሳል ተብሎ ለሚታሰብ የህመም፣ የአካል ጉዳት ወይም የስነ-
ልቦና ችግር ማካካሻ ማለት ነው፤

12. “የጋራ ቅጥር” ማለት በገበያ ላይ በቀላሉ የማይገኝ እና እጥረት ያለበት ባለሙያ በሁለት ተቋማት
መካከል በሚደረግ ስምምነት መሰረት ለሁለቱም ተቋማት እንዲያገለግል ተደርጎ የሚከናወን ቅጥር
ነው፤

13. “የጤና ጣቢያ ዳይሬክተር እና ምክትል ዳይሬክተር ማለት” ማለት ሐኪም በሌለበት ጤና ጣቢያ በሃላፊነት
የሚመሩ ባለሙያ ማለት ነው፡፡

14. "ከፍተኛ ባለሙያ" ጠቅላላ ሐኪሞች እና በየደረጃ ያሉ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ማለት ነው፤

15. "የመግቢያ ኬላ" ማለት ከውጪ ወደ አገር ውስጥና በአየርና በየብስ ወደ አገሪቱ የሚገቡ ሰዎች፤
ዕቃዎች፤ መድሃኒት፤ አስክሬን ቁጥጥር ላይ 24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ ባለሙያ ማለት

16. "ሚኒስትር እና ሚኒስቴር" ማለት የጤና ሚኒስትር እና ሚኒስቴር ነው፤

17. በዚህ ደንብ ማንኛውም በወንድ ጾታ የተገለጸዉ የሴትንም ጾታ ይጨምራል፡፡

3. የደንቡ የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ ደንብ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙና የሕክምና አገልግሎት በሚሰጡ የመንግሥት የጤና ተቋማት የመግቢያ

ኬላ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

4. የደንቡ ዓላማ

1. የጤና ዘርፍ ሰራተኞች በስራቸው ረክተውና ተረጋግተው የሚፈለግባቸውን አገልግሎት በትጋት እና

በጥራት እንዲያከናውኑ የማድረግ፤

3
2. በአደጋና በወረርሽኝ ወቅት የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው መደገፍ እንዲሁም ሞት ለሚያጋጥማቸው

ለቤተሰቦቻቸው አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግና እና

3. በወረርሽኝ ወቅት ባለሙያዎቹ ተበራርተው የሚፈላግባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ ልዩ የማትጊያ

በመዘርጋት የሚሰጡት አገልግሎት የተሸለ ለማድረግ ነው፤

ክፍል ሁለት

የጤና አገልግሎት ሠራተኞች የተረኝነትና ልዩ ልዩ የጥቅማ-ጥቅም ክፍያዎች

5. የተረኝነት የትርፍ ሰዓት ምደባና ክፍያ

1. የህክምና ጥራትን እና ተደራሽንትን ከማስጠበቅ አንፃር ማንኛውም ተቋም ተጨማሪ ባለሙያዎችን በበቂ ቁጥር
በመቅጠር በሁለት ፈረቃ የሚሰሩበት አሰራር በሁሉም የጤና ተቋማት ሥራ ላይ እንዲውል መደረግ አለበት፤

2. የትርፍ ሰዓት ምደባን አስመልክቶ ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት ግምት ውስጥ በማስገባት ሥራን ማዕከል ባደረገ
መልኩ ብቻ ተረኛን መመደብ ይችላል፤

3. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ቢኖርም በተኝቶ ማከሚያ የሚመደቡ ነርሶች ለ 5 ተከሚዎች ከ 1 ነርስ

በላይ መመደብ አይቻልም፤

4. ማንኛውም የጤና ተቋም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ አመሻሹ 11፡30 ሰዓት ድረስ የሥራ ሰዓትን

በማቻቻል ከማሰራት ውጪ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አይፈጸምበትም፤

5. ማንኛውም ባለሙያ ከ አመሻሹ 11፡30 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ድረስ በፈረቃ ተመድቦ ከሚጠበቅበት
ሳምንታዊ መደበኛ የመንግሥት የሥራ ሰዓት በላይ አገልግሎት ከሰጠ፤ የሠራው ትርፍ ሰዓት ብዛት በአንድ ሰዓት
የደመወዙ ስሌት ተባዝቶ በገንዘብ ይከፈለዋል፤

6. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5 የተጠቀሰው ክፍያ በማታ ክፍለ-ጊዜ፤ ቅዳሜና እሁድና በብሔራዊ በዓላት

ተመድበው የሚሠሩ የመግቢያ ኬላ፤ የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢና የካርድ ክፍል ሠራተኛንም ይጨምራል፤

6. የተጠባባቂ ተረኝነት ባለሙያ አመደደብ

4
ማንኛውም በሰንጠረዡ የተመለከተው የጤና ተቋም ከታች በዝርዝር በተመለከተው መሰረት የጤና ባለሙያ እንዲመደብ
ያደርጋል

ተ. ቁ ተጠባባቂ ተራና ባለሙያ የስፔሻላይዝድ ጠቅላላ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና


ሆስፒታል ሆስፒታል ሆስፒታል ጣቢያ

1. የድንገተኛ ቀዶ ህክምና ኦፊሰር 1 1

2. ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት 2 1 1

3. የማህጸንና ፅንስ ስፔሻሊስት 2 1 1

4. የሕጻናት ሕክምና ስፔሻሊት 2 1

5. የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት 2 1

6. የሕጻናት ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት 1

7. የአዋቂ የልብ ሕክምና ስፔሻሊስት 1

8. የሕጻናት የልብ ሕክምና ስፔሻሊስት 1

9. የኩላሊት ህክምና ስፔሻሊስት 1

10. የድገተኛ ሕክምና ስፔሻሊስት 1

11. የአጥንት ሕክምና ስፔሻሊስት 1

12. አንስቴዥዮሎጅስት ስፔሻሊስት 1

13. ፎረንሲክ ስፔሻሊስት 1

14. ማክሲሎፌሻል ስፔሻሊስት 1

15. ኒውሮሰርጂን ስፔሻሊስት 1

16. ራዲዎሎጂ ስፔሻሊስት 1

17. ካርዲቶራሲክ ሰርጅን 1

18. ሳይካትሪስት ስቴሻሊቲ 1

7. ተጠባባቂ ተረኝነት አበል አከፋፈል (On-Call Payment)

1. ከመንግሥት የሥራ ሰዓት ውጪ ተጠባበቂ ተረኛ ሆኖ የሚመደብ ሰራተኛ ተጠባባቂ ሆኖ የሠራበት ሰዓት ብዛት
በአንድ ሰአት የደሞዙ ስሌት ተባዝቶ ይከፈለዋል፤

5
2. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 እንደተጠበ ሆኖ ተጠባባቂ ሆኖ የተመደበ ሠራተኛ በቀን የሠራው ሥራው ድምር
ከ 30% በታች ከሆነ የሚታሰበው የትርፍ ሰዓት ክፍያ የስሌቱ 30% ማነስ የለበትም፤

3. ተጠባበቂ ተረኛ ሆኖ የሚመደብ ሰራተኛ ስራ ሳይኖር ቀርቶ ካልተጠራ የተመደበበት የሥራ ሰዓት በአንድ ሰዓት
የደሞዝ ስሌት ተባዝቶ 30% ይከፈለዋል፤

4. በተጠባባቂ ተረኝነት የሚመደብ ሰራተኛ ከመንግሥት የሥራ ሰዓት ውጪ በቀን ከ 15 ሰዓት መብለጥ የለበትም፤

5. ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሚቀርብ ጥያቄ አሳማኝ ሆኖ ከተገኘ በተጠባባቂ ተረኝነት የሚሰሩ ሌሎች ባለሞያዎችን ሊፈቅድ
ይችላል፡፡

8. የኃላፊነት አበል (Position Allowance)

1. የጤና አገልግሎት ለኅብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ በከፍተኛ የሙያ ደረጃ ላይ ያለ
ሲኒየር ባለሙያ ወደ አመራርና ኃላፊነት ለማምጣት እንዲቻል የሚከተለው የማበረተቻ ክፍያ ተፈቅዷል።
ተ.ቁ. ኃላፊነት የጤና አገልግሎት ተቋማት
ስፔሻላይድ አጠቃላይ የመጀመሪያ ጤና
ሆስፒታል ሆሰፒታል ደረጃ ጣቢያ
ሆስፒታል
የጤና ተቋሙ ዋና ኃላፊ
1. ዋና ኤክስክዩቲቭ ዲይሬክተር/ ፕሮቮስት 2500
2. ምክትል ኤክስክዩቲቭ ዲይሬክተር/ ምክትል ፕሮቮስት 2000
3. ዋና ክሊኒካል ዲይሬክተር/ ም/ፕሮቮስት 2000
4. ዋና የትምህርት ዲይሬክተር/ ም/ፕሮቮስት 2000
5. ዋና ሥራ አስፈጻሚ 2000 1500 1300
6. ሜዲካል ዳይሬክተር 1750 1400 1200 1100
7. የጤና ጣቢያ ዳይሬክተር(ሐኪም በሌለበት) 900
8. የጤና ጣቢያ ምክትል ዳይሬክተር(ጤና መኮንን) 700

የኬዝ ቲም ኃላፊ
የድንገተኛ ክፍል 900 700 500

የተመላላሽ ክፍል 900 700 500

የተኝቶ ታካሚ ክፍል 900 700 500


9. ሜትረን/ ነርሲንግ ዳይሬክተር 900 700 500
10. ምክትል ሜትረን/ ምክትል ነርሲንግ ዳይሬክተር 800 600 400

6
የሕክምና ክፍል ኃላፊ
11. የውስጥ ዳዌ ሕክምና ክፍል 700 500 300
12. የማህጸንና ጽንስ ሕ/ክፍል 700 500 300
13. የሕጻናት ሕክምና 700 500 300
14. የቀዶ-ጥገና ሕክምና 700 500 300
13. የአጥንት ሕክምና 700 500 300
14. የጥርስ ሕክምና 700 500 300
15 የዓይን ሕክምና 700 500 300
16 የፊዚኦቴራፒ ሕክምና 700 500 300
17 የሥነ አህምሮ ሕክምና 700 500 300
14. መድሃኒት የተለማመደ ቲቢ ሕክምና 700 500 300
15. ከአንገት በላይ ሕክምና 700 500 300

16. የመካንነት ሕክምና 700 500 300


17. የልብ ሕክምና 700 500 300

18. የድንገተኛ ሕክምና 700 500 300

19. ኦንኮሎጂ ሕክምና 700 500 300


20. ፎረንሲክ ሕክምና 700 500 300

የክፍል/ቡድን ኃላፊ ነርስ


21. የውስጥ ዳዌ ሕክምና ክፍል 350 300 200
22. የማህጸንና ጽንስ ሕ/ክፍል 350 300 200
23. የሕጻናት ሕክምና 350 300 200
24. የቀዶ-ጥገና ሕክምና 350 300 200
25. ድንገተኛ 350 300 200
26. የጥርስ ሕክምና 350 300 200
27. የድንገተኛ ሕክምና 350 300 200
28. የሕጻናትና ዐዋቂ ጽኑ ሕሙማን 350 300 200

የክፍል አስተባባሪ
29. የራጂ 350 300 200
30. የላቦራቶሪ 350 300 200
31. የፋርማሲ 350 300 200
32. የማዋለጃ 350 300 200
33. የሕናቶችና ሕጻናት 350 300 200
34. የ”ART” 350 300 200

7
35. ላይዘን 350 300 200

2. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 ከተዘረዘሩት የኃላፊነት ክፍያ ውጪ ሌላ የሥራ ክፍል ካለ እና አስፈላጊነቱ
በሚኒስትሩ ከታመነበት የኃላፊነት ክፍያ ሊወሰን ይችላል፤

9. የተገላጭነት አበል

1. የሥራ ጸባያቸው ተገላጭ የሚያደርጋቸው ከዲፕሎማ እስከ ማስተርስ ድግሪ ድረስ ያሉ ባለሙያዎችና ሌሎች
ሠራተኞች እንደሚከተለው የተጋላጭነት ያገኛሉ

ተ. የሙያ ዘርፍ ወራዊ ክፍያ ማብራሪያ



1. ሚድዋይፌሪ 705
2. አንስቴዢያ 705

3. የአህምሮ ሕክምና 705

4. የራጅ ባለሙያ 705

5. የድንገተኛ ሕክምና ቴክኒሻን 705

6. ጨረርና ኒውክሊየር ሕክምና ውስጥ የሚሠሩ 705

7. በመዋላጅ ክፍል የሚሠሩ ነርሶች 705

8. የጨቅላ ሕጻናት ክፍል የሚሰሩ ባለሙያዎች 705

9. የቀዶ ጥገና ክፍል የሚሰሩ ባለሙያዎች 705

10. ድንገተኛ ክፍል የሚሠሩ ባለሙያዎች 705

11. የታማሚ መለያ (ትሪያጅ)ክፍል የሚሠሩ ባለሙያዎች 705

12. የላቦራቶሪ ክፍል ሠራተኞች 705

የአስተዳደር ሰራተኞች

13. ታማሚን የሚያመላልሱ (ፖርተርስ) ሠራተኞች 450

14. በተመላላሽና ሕክምና መስጫ የሚሠሩ የጽዳት ሠራተኞች 450

15. እስቴራላይዜሽን ክፍል የሚሰሩ 450


16. ላውንደሪ ክፍል የሚሰሩ ሰራተኞች 450

17.

2. የሥራ ጸባያቸው ተጋላጭ የሚያደርጋቸው ከፍተኛ ባለሙያዎችና እንደሚከተለው የተጋላጭነት ያገኛሉ

8
ተ.ቁ ባለሙያ ወርሃዊ የተጋላጭነት ማብራሪያ
ክፍያ
1. የቀዶ ሕክምና 1838
2. የማህጸንና ጽንስ 1838
3. የአጥንት ሐኪም 1838
4. የተቀናጀ ድንገተኛ ቀዶ ጥገና ኦፍሰር 1838
5. የድንገተኛ ሕክምና ስፔሻሊስት 1838
6. የድንገተኛ ሕክምና ሐኪም 1838
7. ክሊኒካል ፓቶሎጅ 1838
8. ኦንኮሎጂስት 1838
9. የአኒስቴዥያ ስፔሻሊስት 1838
10. ፓቶሎጂስት 1838
11. ራዲዮሎጂስት 1838
12.
13.

3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 የተጠቀሰው እንተጠበቀ ሆኖ ከላይ ከተጠቀሰው ሙያ አዲስ የሙያ ዘርፍና የሥራ
ጠባዩ ለተገላጭነት የሚደርግ መሆኑ ሚኒስትሩ ካመነበት ተመጣጣኝ የተገላጭነት እንዲከፈለው መወሰን ይችላል፤

10. የቤት አቅርቦት እና አበል

1. ከፍተኛ ባለሙያዎች በሚሠሩበት የጤና ድርጅት ውሰጥ ወይም አቅራቢያ መንግሥት የመኖሪያ ቤት ያቀርባል፤
የመኖሪያ ቤት ማቅረብ ካልተቻለ በየወሩ የሚከተሉት ክፍያ ያገኛሉ፤

ሀ). ለስፔሻሊስትና ሰብ-ሰፔሻሊስት ሐኪሞች …… ብር 5,000.00


ለ). ለጠቅላላ ሐኪሞች …………….…………….… ብር 2,000.00
ሐ). ለተቀናጀ የቀዶ-ጥገና ኦፊሰር …………………….ብር 2,000.00

2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 (ሀ፤ለ እና ሐ) የተጠቀሰው ቢኖርም ከ 15 ዓመት በላይ ያገለገሉ የጤና ዘርፍ
ሠራተኞችም መኖሪያ ቤት ይቀርባል፤ የመኖሪያ ቤት ማቅረብ የማይቻል ከሆነ የሰራተኛውን ደመወዝ 30%
ለቤት ኪራይ መደጎሚያ ይከፈላል፤

9
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ባለሙያ ከ 15 ዓመት በላይ ከገለገለና የወር ክፍያው የደመወዙ
30% በታች ከሆነ በንዑስ አንቀጽ 2 የተጠቀሰውን ክፍያ ያገኛል፤

4. በተቋሙ ያለው መኖሪያ ቤት በቅድሚያ የሚሰጣቸውን ባለሙያዎችን በተመለከተ በተቋሙ ነባራዊ ሁኔታ
ላይ ተመስርቶ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፤

5. ከተቋሙ መኖሪያ ቤት ለመቀበል ፈቃደኛ ላልሆነና ለተሰጠው ሠራተኛ ምንም የቤት ኪራይ ማካካሻ ክፍያ
አያገኝም፤

11. ከታክስ ነጻ የሆነ ተሸከርካሪ ግዥ ጥቅማ-ጥቅም

ባለሙያ እና ሠራተኛ ተረጋግቶና ለረዥም ጊዜ በሥራ ገበታው ላይ ቆይቶ ለኅብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት
ለመስጠት እንዲችል የሚከተለው ሁኔታ ሲሟላ ከታክስ ነጻ የቤት ተሸከሪካሪ ግዥ ተፈቅዷል፤

1. ለስፔሻሊቲ፤ ሰብ-ስፔሻሊቲ እና ሱፐር-ስፔሻሊቲ ከታክስ ነጻ የሆነ ተሸከሪካሪ በግዥ ተፈቅዷል፤

2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 በተመለከተው መሠረተት ከታክስ ነጻ የተሸከሪካሪ ግዥ ታጠቃሚ የሆነ
ባለሙያ ለ 10 ዓመት በጤና ሴክተሩ የማገልገል ግዴታ አለበት፤

3. ከ 10 ዓመት በታች አገልግሎት ስጥቶ ከመንግሥት ተቋም የለቀቀ ባለሙያ የተሰጠው የታክስ ነጻ ዕድል
ይነሳበታል፤

4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ቢኖርም በሴክተሩ ከ 15 አመት በላይ ያገለገሉ ሌሎች የጤና
ዘርፍ ሰራተኞች ከታክስ ነጻ የተሸከሪካሪ ግዥ ታጠቃሚ ይሆናሉ፤

12. ለሥራ ምቹ ባልሆነ ቦታ ተመድበው ለሚሰሩ ባለሙያዎች አበል

የልማት ዝርጋታው ባልተሟላላቸው እና በአንጻራዊነት ለስራ ምቹ ያልሆነ ቦታ ተብለው ሥልጣን

በተሰጠው አካል የጤና ተቋሙ ደረጃ “C” ላይ ተመድበው ለሚሰሩ ስፔሻሊስትና ከዚያ በላይ የጤና

ባለሙያ የደመወዙ 30% ጭማሪ ክፍያ ክፍያ ያገኛል፤

10

13. እውቅና ወይም ማበራታቻ የሽልማት ስለመስጠት

1. በሁሉም የጤና ተቋም ደረጃ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ የተሻለ አገልግሎት የሰጠ ባለሙያ

የሥራ አፈፃፀሙን መሰረት ያደረገ ዕውቅና እንዲሰጠው ይደረጋል፤

2. የዕውቅና የሽልማት ማበራታቻ ይዘቶችም እንደ ተቋሙ አቅምና የስራ አመራር ውሳኔ

ከሚከተሉት ዓይነቶች መካከል አንዱ ወይም ሁለቱ ሊሆን ይችላል

ሀ). የገንዘብ ሽልማት፣

ለ). ተገዝቶ የሚሠጥ ስጦታ (ሰዓት፤ ስልክ፤ ቴሌቪዥን፤ ኮምፒዩተር….)

ሐ). የዕውቅና ምስክር ወረቀት

መ). ሀገር ውስጥ ወይም የውጪ ሀገር ጉብኝት

ሠ). ዋንጫ

ረ). ሜዳሊያ

ሰ). ከሥራው ጋር የተያያዘ የውጪ አገር የሥራ ጉብኝት

3. በጡረታ ለሚገለሉ ሽልማት


ለራዥም ጊዜ በተቋሙ አገልግለው በጡረታ ለሚገለሉ ሠራተኞች የሚከተለው የማበራታቻ
ሽልማት ይሰጣቸዋል
ሀ). የመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊዎች በተገኙበት የምስጋና የሽኝት ፕሮግራም

ለ). ለሰጡት ራዥም አገልግሎት የዋንጫ ወይም ሜዳሊያ ወይም የምስክር ወረቀት

ሐ). በገንዘብ፤

መ). በአይነት፣

ሠ). በጡረታ የተሰነበተው ሠራተኛ ከፍተኛ ሙያ ያለው ከሆነ እና በኮንትራት ወይም

በአማካሪነት ተቀጥሮ ቢሠራ ለኅብረተሰቡ እና ለመ/ቤቱ ውጤታማ ሥራ ለማከናወን

ይችላል ተብሎ በመ/ቤቱ የበላይ አመራር ከታመነበት እንዲሁም ሠራተኛው

11
ለመሥራት ፍላጎት ካለው በለው ክፍት ቦታ ተቀጥሮ እንዲሠራ የስራ ዕድል

ሊመቻችለት ይችላል፤

4. እውቅና እና ማበራታቻ ወይም የሽልማት የሚሰጠው ተቋሙ በሚያወጣው ዝርዝር

የማስፈጸሚያ መመሪያ መሰረት ይሆናል፤

5. እውቅና እና ማበራታቻ ወይም የሽልማት አሰጣጡ በማንኛውም ሁኔታ ከአድልዎ እና

ወገንተኝነት የጸዳ ሊሆን ይገባል፤

14. የጋራ ቅጥር

1. ለጤና ትምህርት ወይም ለጤና አገልግሎት ተቋማት ተፈላጊ የሆነ ባለሙያ ለመቅጠር ከሁለት ጊዜ በላይ
ማስታወቂያ ወጥቶ ከጠፋ በላኪና ተቀባይ መ/ቤት በሚደረግ ስምምነት የጋራ ቅጥር ማከናወን ይቻላል፡፡

2. በጋራ በሚደረግ የቅጥር ስምምነት ወደ ተቀባይ መ/ቤት የሚመጣ ባለሙያዎች በላኪ መ/ቤት የሚከፈለው
ደመወዝ 70% ድረስ ሊከፈለው ይችላል፡፤

3. በጋራ ቅጥር በተቀባይ ተቋም ቢያንስ በሳምንት 20 ሰዓት አገልግሎት መስጠት አለበት፡፡

15. የትምህርትና ስልጠና ዕድል ያገኙ ስለመስጠት

1. በስራ አፈጻጸማቸው የተሻለ ውጤት ያገኙ ሰራተኞች ተቋሙ ባለው የሰው ሀብት ልማት ዕቅድ መሰረት
አስፈላጊውን መስፈርት ሲያሟሉ ቅድሚያ የትምህርት ዕድል ያገኛሉ፡፡

2. ተቋሙም የትምህርት ዕድል አግኝተው ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ ሰራተኞች የስራ ዕድል ይሰጣል፡፡

16. ወረርሽኝ ሲከሰት ሊተገበሩ የሚችሉ ጥቅማ-ጥቅሞች

1. አለማቀፋዊ ወይም ሀገራዊ ወረርሽኞች መከሰቱን በመንግሥት ሲታወጅ ለጤና ዘርፉ ሰራተኞች የህይወት
መድን ዋስትና በመንግስት እንዲሸፈን ይደረጋል፡፡

12
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተገለጸ ወረሪሽኝ በሚከሰትበት ወቅት በሥራ ላይ ተሳታፊ የሆኑ
ሠራተኞች ወረርሽኙ መቆሙ አስኪታወጅ ጊዜ ድረስ በአገልግሎት ላይ ከተሰማሩ ባለሙያዎች
እየተሰበሰበ ያለው ታክስ በመንግሥት እንዲሸፈን፤

17. የነጻ ሕክምና አገልግሎት


የጤና ሴክተር ሠራተኞች የነጻ ሕክምና ጉዳይ በኢትዮጵያ የማኅበራዊ ጤና መድኅን አዋጅ ቁጥር
690/2002 በአንቀጽ 9 ሥር የተዘረዘረው የመዋጮ አከፋፈል ተፈጻሚ እስኪሆን ድረስ የጤና ዘርፍ
ሠራተኞች በሀገር ውስጥ የነጻ ሕክምና ያገኛሉ፡፡

ክፍል ሶስት
ልዩ-ልዩ ድንጋጌዎች
18. ከጤና ዘርፉ ሠራተኞች የተረኝነትና ልዩ ልዩ ጥቅማ-ጥቅም የሚገኝ ገቢ ሥራ ግብሩ በመንግሥት
የሚሸፈን ሆኖ ለሠራተኛው ምንም ሳይቆረጥ እንዳለ ይከፈለዋል፤

19. የተሻሩ መመሪያዎች፤ ሰርኩላሮችና የአሠራር ሥርዓቶች


1. ከሰኔ 2005 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ የነበረ የጤና ባለሙያዎች የተረኝነትና ሌሎች ጥቅማ-ጥቅሞች በዚህ
ደንብ ተሻሽሏል፡፡

2. ይህንን ደንብ የሚቃረኑ መመሪያዎች፤ ሰርኩላሮችና የአሠራር ሥርዓቶች በዚህ ደንብ ተሸሯል፡፡

20. ደንቡ ተፈጻሚ የሚሆንበት ጊዜ

ይህ ደንብ ከ-------- 20…… ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ዶ/ር አቢይ አህመድ/ፒኤችዲ/


የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

13

You might also like