You are on page 1of 9

ምዕራፍ 10፡ የጤና ጣቢያ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያና መረጃ አያያዝና

አላላክ
መግቢያ
• የአገልግሎት ጥራት ሲባል በጤና ተቋማት የሚሰጠውን ማንኛውንም
አገልግሎት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ተደራሽ፣ አዋጭ፣ ወቅታዊ፣
የሚፈለገውን ውጤት የሚያመጣ እና ተገልጋዪን የሚያረካ አገልግሎት
ማለት ነው፡፡ የአገልግሎት ጥራት ከሚያተኩርባቸው አብይ ጉዳዮች ውስጥ
መረጃ በየስራ ሂደቱ በየወቅቱ እና በየደረጃው በመሰብሰብ ብሎም
በመተንተን እና የማሻሻያ እቅድ አውጥቶ መተግበር ናቸው፡
• የአገልግሎት ጥራት በጤና ጣቢያ ውስጥ ለማምጣት የሁሉም ማህበረሰብ
ሀላፊነት ሲሆን ጤና ተቋማቶች ባለሙያዎች እርስ በእርሳቸው
የሚማማሩበት የሚመካከሩበት መድረክ ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
በተጨማሪም ጤና ጣቢያ ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎች ከተገልጋዩ
ማህበረሰብ፣ከጤና ኬላዎች እና ከጤና ኤክቴንሽን ሰራተኞች
የሚወያዩበት እና በጋራ የአገልግሎት ማሻሻያ አሳቦችን የሚያመነጩበት
መድረክ ሊኖር ይገባዋል፡፡
የጤና ጣቢያ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያና መረጃ አያያዝና አላላክ
የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያ እስታንዳርዶች
• ጤና ጣቢያው የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል እና አፈፃፀማቸውን
ለመገምገም የሚያስችሉ ዝቅተኛው እስታንዳርዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
• ጤና ጣቢያው የአገልግሎት ጥራት የሚከታተል፣ ሪፖርት የሚያጠናቅር፣
ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጣ ኮሚቴ ያቋቁማል፤
• ጤና ጣቢያው በጊዜ ገደብ የተከፋፈለ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያ ዕቅድ
ሊኖረው ይገባል (ወርሀዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት እና አመታዊ)
• ጤና ጣቢያው የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያ ስልቶችንና ሂደቶችን
በተመረጡ እና አንገብጋቢ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ላይ ይተገብራል፡፡
• ጤና ጣቢያው በጤና መረጃ ስርዓት በተቀመጠው ጊዜ ገደብ መሰረት
በተመረጡ ጠቋሚ መለኪያዎች በመሰብሰብ፣ በመተንተን ለአገልግሎት
ጥራት መጠቀም ብሎም ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ሪፖርት ያደርጋል፡፡
• የተገልጋይ እርካታ እና ሌሎች የጥራት መለኪያዎችን ምዘና ያከናውናል፣
ይተነትናል ለጥራት ማሻሻይ ያውላል፡፡
የጤና ጣቢያ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያና መረጃ አያያዝና አላላክ

የአተገባበር መመሪያ
የጤና ጣቢያ አገልግሎት ጥራት ማሻሻያ እና የአፈጻጸም ግምገማ አደረጃጀት
• ጤና ጣቢያው የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያ ሂደቶችን
ለመከታተል፣ ሪፖርት ለማጠናቀር እና የአፈፃፀም ግምገማ
ለማድረግ የሚያስችል ኮሚቴ ማቋቋም ይኖርበታል፡፡
የኮሚቴው ስብጥር
• ኮሚቴው በጤና ጣቢያው ኃላፊ የሚመራ ሲሆን ከ 4- 6 አባላት
ይኖሩታል፡፡ አባላቶቹም ልምድ እና በጤና ጣቢያው ቆይታ
ካላቸው ከህክምና አገልግሎት፣ ከፋርማሲ፣ ከላቦራቶሪ፣ ከጤና
መረጃ እና አስተዳደር የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ ይሆናል፡፡
የጤና ጣቢያ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያና መረጃ አያያዝና አላላክ
የኮሚቴው ተግባር እና ኃላፊነት
• የጤና ጣቢያው የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን ይገመግማል፣ ምርጥ
ተሞክሮዎችን ማነቆዎችን በዝርዝር የለያል እንዲሁም የማሻሻያ ዕቅድ
ያወጣል፡፡
• የጤና ጣቢያውን ያገልግሎት ሥራ አፈፃፀም መረጃ ያሰባስባል፣
ያጠናቅራል፣ ይተነትናል ብሎም በተለዩ ክፍተቶች ላይ የጥራት ማሻሻያ
ሀሳቦች እና ዕቅዶች በማውጣት ለጤና ጣቢያው ማኔጅሜንት
በማፀደቅ ይተገብራል፡፡
• የጤና ጣቢያው የጤና መረጀ ከተሰበሰበ በኋላ ከአጠቃላይ የጤና
ጣቢያው ሰራተኞች ጋር እና ከተገልጋዩ ማህበረሰብ ጋር ውይይት
በማድረግ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማቅረብ፡፡
• የጤና ጣቢያውን ውስጣዊ አሰራርን ይፈትሻል፣ ማነቆዎችን ይለያል
የለውጥና የጥራት ማሻሻያ እቅዶችን ያወጣል በጤና ጣቢያው
ማኔጅሜንት በማፀደቅ ይተገብራል፡፡
የጤና ጣቢያ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያና መረጃ አያያዝና አላላክ
ዕቅድ ማቀድ
• ጤና ጣቢያው ግልጽ፣ ሁሉን አቀፍ እና በቀላሉ
ሊተገበር የሚችል የወር፣ የሶስት ወር፣ የስድስት ወር
እንዲሁም የአመት ዕቅድ ማቀድ ይኖርበታል፡፡ ዕቅዱ
ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዋና ዋና ፕሮግራሞች
ለምሳሌ የእናቶች እና ህጻናት፣የቲቢ
በሽታ፣የኤችአይቪ ኤድስ እና የመሳሰሉት ያካተተ
መሆን ይኖርባታል፡፡
• ዕቅዱ የሚከተሉትን ነጥቦች መዳሰስ ይኖርበታል
የጤና ጣቢያ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያና መረጃ አያያዝና አላላክ
• የህሙማን ደህንነት የሚያስጠብቁ ተግባራት
• ለተገልጋዮች አስጊ የሆኑ ሁኔታዎች መለየት፡፡
• በተለዩ አስጊ ሁኔታዎች ለሰራተኞች እና ለህሙማ ግንዛቤ ማስጨበጥ
• ለሚከሰቱ ማንኛውም ችግሮች ሪፖርት የሚደረግበት እና መፍትሄ
የሚሰጥበት ስርዓት መዘርጋት፡፡
• የአገልግሎት ውጤታማነት የሚያስጠብቁ ተግባራት
• ጤና ጣቢያው የሚሰጠውን አገልግሎት ውጤታማ እንዲሆን ታካሚዎች
አስተያየት የሚሰጡበት፣ መድሀኒት እና የላቦራቶሪ ምርመራ
የሚያገኙበት፣ ህክምና ሲያቋርጡ ክትትል የሚደረግበት ብሎም ከተገልጋዩ
ማህበረሰብ ጋር ውይይት የሚደረግበት ስርዓት መዘርጋት ይኖርበታል፡፡
• በጤና ጣቢያው የሚሰጠውን አገልግሎት ኦዲት ማድረግ፣ የሚከሰቱትን
ማንኛውም ሞት ኦዲት ማድረግ እና የሚሰጠውን አገልግሎት ከተቀመጡ
እስታንዳርዶች መሰረት መሆኑን ማረጋገጥ፡፡
የጤና ጣቢያ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያና መረጃ አያያዝና አላላክ
• የጤና ጣቢያ አገልግሎት ተገልጋይ ተኮር የማድረግ ተግባር
• የጤና ጣቢያ አገልግሎት የተገልጋዩን ማህበረሰብ ፍላጎት እና
መብት የጠበቀ መሆን ይኖርበታል
• ማህበረሰቡ በጤና ጣቢያው አገልግሎት አሰጣጥ ቀጥተኛ
ተሳትፎ የሚያደርጉበት ሁኔታ ማመቻቸት ለምሳሌ ቀጣይነት
ያላቸው የውይይት መድረኮች፣ የአስተያየት መስጫ ሳጥኖች እና
የተገልጋይ አቀባበል እና ስንብት ስርዓት ማኖር ኛቸው፡፡
የጤና ጣቢያ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያና መረጃ አያያዝና አላላክ
የጥራት ማሻሻያ ሂደት ትግበራ
• የጤና ጣቢያ የሥራ አፈፃፀም በየጊዜው መገምገም እና የማሻሻያ
ሀሳቦች እያፈለቁ መተግበር ያስፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን ነጥቦች በቅደም
ተከተል በመተግበር የአገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ ይረዳሉ
• የሥራ አፈፃፀም እና የአገልግሎት ጥራት መገምገም፡፡
• ችግሮችን መለየት እና በቅደም ተከተል ማስቀመጥ
• የችግሮችን መንስኤ መተንተን
• ለተተነተኑት ችግሮች ለእንዳንዱ አማራጭ የመፍትሄ ሀሳቦች መንደፍ
• ለተነደፉ የመፍትሄ ሃሳቦች ዝርዝር የትግበራ ዕቅድ ማዘጋጀት
• የተዘጋጀውን ዕቅድ መተግበር እና ትግበራ መከታተል እና በየጊዜው
የመፍትሄ ሀሳቦችን ማስቀመጥ፡፡
የጤና ጣቢያ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያና መረጃ አያያዝና አላላክ
የመሰረታዊ የጤና አገልግሎት አህድ ተጠቃሚዎች እርካታ ምዘና
የመሰረታዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሲባል የህክምና እና
የመከላከል አገልግሎት ለማግኘት ጤና ተቋም የሚመጡ፣ የህክምና እና
የመከላከል አገልግሎት ቤት ለቤት የሚያገኙ ህብረተሰብ ማለት ነው፡፡
የህብረተሰቡን የአገልግሎት ማግኘትና በአገልግሎቱ መርካትን ለመለካት
50 ቤተሰቦች እና 50 ተገልጋዮች ከጤና ጣቢያ እና ጤና ኬላ
አገልግሎት ያገኙ በሚዘጋጅ መጠይቅ መሰረት መረጃ ሰብስቦ
በመተንተን ማግነት ይቻላል፡፡
ሪፖርት ማጠናቀር እና ማቅረብ
• የጤና ጣቢያው የጤና መረጃ ባለሙያ የጤና ጣቢያው ወቅታዊ ሪፖርት
በዝርዝር በማዘጋጀት ለጥራት ማሻሻያ ኮሚቴ ያቀርባል በመቀጠልም ኮሚቴው
የቀረበለትን ሪፖርት በመገምገም ከአጠቃላይ ሰራተኞው እና ከተገልጋይ
ማህበረሰብ ጋር ውይይት በማድረግ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያቀርባል፡፡
Check list

You might also like