You are on page 1of 14

ምዕራፍ 3፡ የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት

ክፍል-1
 ታካሚዎች ምንም ዓይነት መጉላላት ሳይደርስባቸዉ የሚፈልጉትን
አገልግሎት አግኝተዉ የሚሄዱበትን ስርዓት ያመላክታል፡፡
 የሚያስፈልጉ ግብዓቶች:- የሰው ሃይል፤መሰረተ ልማት፤የሕክምና
መገልገያ መሳሪያዎች፤የተለያዩ የጤና ጣቢያ ቁሳቁሶችና የስራ
መመሪያን ያጠቃልላል፡፡
• ጠቀሜታ፡- ህሙማን አግባብ ባለዉ መልኩ ጊዜያቸዉን ቆጥበዉ
አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ
- የህሙማንን ቅሬታ ይቀንሳል
- የሠራተኛውን የስራ ቅልጥፍና ይጨምራል
- የህሙማን እርካታን ይጨምራል
የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት…
ክፍል 2

የአገልግሎት ፍሰት የትግበራ ስታንዳርዶች

1. የአገልግሎት ፍሰት እና አደረጃጀት የተሳለጠና ቀልጣፋ እንዲሆን ጤና ጣቢያዉ

የአሰራር መመሪያና ቅደም ተከተል /Procedure/ ሊኖሩት ያስፈልጋል፡፡

- ይህ አሰራር፡- የተመላላሽ፤ የድንገተኛ እና የማዋለድ አገልግሎት ላይ ትኩረት

ሰጥቶ የታካሚዎችን መጨናነቅ መቀነስ አለበት፡፡

2. ሁሉም የጤና ጣቢያዉ ሰራተኞች የተዘጋጀዉን የአሰራር መመሪያና ቅደም

ተከተል /Procedure/ ማወቅና መተግበር እንዲሁም ተግባራዊነቱን ማረጋገጥ

አለባቸዉ፡፡
የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት…
3. ጤና ጣቢያዉ የድንገተኛ ታካሚዎችን የህመም ደረጃ የሚለዩበት
/Emergency Triage/ አሰራር እና በስራዉ ላይ የሰለጠነ ባለሙያ
እንዲሁም የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ሊኖረዉ ይገባል፡፡
4. ጤና ጣቢያዉ የላይዘንና የህሙማን ቅብብሎሽ አሰራር እንዲሁም
የህሙማን ቅብብሎሽ አሰራር መመሪያ ይኖረዋል፡፡ ይህንን መመሪያ የጤና
ጣቢያዉ ሰራተኞች አዉቀዉ መተግበር አለባቸዉ፡፡

5. ጤና ጣቢያው ታካሚዎች/ደንበኞች ወደ ቅጥር ግቢው ከገቡ በኋላ


የሚፈልጉትን አገልግሎት የት ማግኘት እንደሚችሉ የሚያሳይ አቅጣጫ

ጠቋሚዎችን ማስቀመጥ ይኖርበታል ፡፡


የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት…
ክፍል 3
የአተገባበር መመሪያ
1. የጤና ጣቢያው አደረጃጀት
በተለያዩ ክፍሎች ላይ በደማቁ የተፃፈ የክፍል ቁጥር ወይም
የአገልግሎተ ስያሜ፡በየቦታው የአቅጣጫ መጠቆምያ
ምልክቶች እንዲሁም ተቀራራቢ አገልግሎት የሚሰጡ
ክፍሎች በአንድ ረድፍ እንዲደራጁ መደረግ ይኖርበታል፡፡
የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት…
2. የድንገተኛ ህክምና ክፍል
 የድንገተኛ ሕክምና ክፍል አጣዳፊና ድንገተኛ ህመምተኞች
ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአፋጣኝ ህክምና የሚያገኙበት ክፍል
ነው፡፡ ይህ ክፍል በቀን ለ24 ሰዓት በሳምንት ለ7 ቀናት በዓመት
ለ365 ቀናት ክፍት መሆን አለበት ፡፡
 የድንገተኛ ክፍሉ ከዋናው የውጭ በር የቀረበ መሆን አለበት፡፡
ለድንገተኛ ታካሚዎችና ለአምቡላንሰ በቀላሉ አገልግሎት
መስጠት እንዲችል ለመንገድ የቀረበ መሆን ይኖርበታል፡፡
በተጨማሪም በውጭ በሚታይ መልኩ በትልቁ “የድንገተኛክፍል”
ተብሎ መፃፍ ይኖርበታል ፡፡
የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት…

የድንገተኛ ክፍሉ የሚከተሉት ስፍራ ክፍሎች እና ቁሳቁሶች


ሊኖሩት ይገባል፡፡
1. የአምቡላንስ ማቆሚያ ስፍራ
2. የተለያዩ ክፍሎች Examination, Resuscitation &
Procedure
3. ለአጭር ጊዜ ቆይታ የሚያገለግል የአልጋ ክፍልና አልጋዎች
4. ለአስታማሚዎች የመቆያ ስፈራ
5. ቀጥታ የስልክ መስመር እንዲሁም
6. ለድንገተኛ ህክምና የሚያስፈልጉ መድሃኒቶች፡፡
የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት…
የድንገተኛ ክፍል ባለሙያዎች
 አስተባባሪ፡-
 ተመድቦ የሚሰራ ጤና ባለሙያ ጠቅላላ ሐኪም/ጤና መኮንን/
ቢኤስ.ሲ.ነርስ ቢሆን/ብትሆን ይመረጣል፡፡ ካልሆነም በድንገተኛ ህክምና
በቂ ዕውቀት ያለው ማንኛውም የጤና ባለሙያ ተመድቦ ሊሠራ ይችላል፡፡
በድንገተኛ ክፍሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች ተፅፈው መቀመጥ አለባቸው፡፡
 ታካሚዎች በድንገተኛ ክፍሉ አፋጣኝ እርዳታ ከተደረገላቸው በኃላ እንደ
ሕመማቸው ሁኔታ እስከ 24 ሰዓት እዚያው ተኝቶ ክትትል ሊደረግላቸው
ይችላል፡፡
 በ24 ሰዓት ውስጥ ከተሻለው እንደ አስፈላጊነቱ በቀጠሮ ወደ ቤቱ እንዲሄድ
ይደረጋል፡፡
 የታካሚው የጤና ችግር ከጤና ጣቢያው አቅም በላይ ከሆነ ወደ ሆስፒታል
ይላካል ፡፡
 ታካሚው ወደ ሆስፒታል ከመላኩ በፊት የጤና ጣቢያው ላይዘን ኦፊሰር
ወደ ሚላክበት ሆስፒታል ደውሎ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት፡፡
የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት…
3. የተመላላሽ ህክምና አገልግሎት
• የህፃናት እና የአዋቂዎች ህክምና ክፍል፤የቅድመ ወሊድ ክትትል፤ የቤተስብ
ምጣኔ አገልግሎት፤ የክትባትና እና የመሳሰሉት የህክምና ክፍሎችን
አጠቃሎ ይይዛል፡፡
• የሚያስፈልጉ ባለሙያዎች ጠቅላላ ሀኪም፤ጤና መኮንን እና ነርስ ናቸዉ፡፡
 አንድ ታካሚ መጀመሪያ ወደ ትሪያዥ ክፍል ይሄዳል፡፡ የትሪያዥ
ባለሙያው ታካሚው ላይ ምንም ዓይነት የድንገተኛ ህመም ምልክቶች
አለመኖራቸውን ሲያረጋግጥ በየትኛው የተመላላሽ ህክምና ክፍል ገብቶ
መታየት እንዳለበት ይወስናል፡፡ በመቀጠልም ታካሚው/ደንበኛው
ተመዝግቦ ካርድ ካወጣና ተገቢውን ክፍያ ከፈፀመ በኋላ ወደ ሚታይበት
ክፍል እንዲሄድ ይደረጋል፡፡
 የትራያዥ አገልግሎት የማያስፈልጋቸው ሁኔታዎች የድንገተኛ ህመም
በምጥ ላይ ያሉ እናቶች እና ከዚህ በፊት ታይተው በቀጠሮ ቀን የመጡ
ታካሚዎች ናችዉ፡፡
የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት…
4. የቀላል ቀዶ ሕክምና ክፍል
ሁሉም የጤና ጣቢያዎች ቀላል የቀዶ ጥገና ክፍል
ይኖራቸዋል፡፡ ለቀላል ቀዶ ሕክምና ተብሎ የተዘጋጀ ክፍል
ከሌለ ለሌሎች ሥራዎች የተዘጋጀ ክፍል/ ፕሮሲጀር
ሩም/ ውስጥ ይህ ስራ ሊሰራ ይችላል በጤና ጣቢያ ደረጃ
የሚሰሩ ቀላል የቀዶ ጥገና ሕክምናዎች የሚባሉት
ለምሳሌ ፡ እንደግርዛት፤ መጠነኛ የቁስል ሕክምናዎች እና
የመሳሰሉት ይሠራሉ፡የጤና ጣቢያ የቀላል ቀዶ ሕክምና
ክፍል በኢትዮጵያ የምግብ የመድሃኒትና ቁጥጥር
ባለስልጣን ባወጣው ደረጃ መሠረት መድሃኒቶችና
መሣሪያዎች መሟላት አለባቸው
የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት…
5. የማዋለጃ አገልግሎት
• ለወሊድ አገልግሎት ወደ ጤና ጣቢያው የሚመጡት እናቶች ቀጥታ ወደ
ማዋለጃ ክፍል ይወሰዳሉ፡፡ በማዋለጃ ክፍል ውስጥ ባሉ ባለሙያዎች
(አዋላጅ ነርስ ጠቅላላ ሀኪም ጤና መኮንን ወይም ነርስ) የምጡን ደረጃ
እና የፅንሱን ሁኔታ ለማወቅ ምርመራ ይደረጋል፡፡
• የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ ከተደረገ በኃላ ምጡ በትክክለኛ ሁኔታ
የጀመረ ከሆነ አልጋ ይዛ እዚያው ጤና ጣቢያ እንድትወልድ ይደረጋል፡፡
ነገር ግን በፅንሱ ወይም በእናትየው ላይ ከእርግዝና ጋር ተያይዘው
የሚመጡ ችግሮች ካሉ እና ችግሩ በጤና ጣቢያው ደረጃ የማይፈታ
ከሆነ አገልግሎት ወደ ሚሰጥበት የጤና ድርጅት መላክ አለበት፡፡
• ይህ ተግባር ከመፈፀሙ በፊት ከላይዘን ኦፊሰር ጋር በመነጋገር የተሻለ
የማዋለጃ አገልግሎት ወደምታገኝበት ሆስፒታል በአምቡላንስ
እንድትላክ ይደረጋል፡፡
የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት…

• እናትየው በጤና ጣቢያው እንድትወለድ ከተወሰነ


በተላላኪዎች /Porters/ እርዳታ ካርድ እንድታወጣ ይደረጋል፡፡
አልጋ ከያዘች በኃላ በጤና ባለሙያ ምጡን በፓርቶግራፍ ቅጽ
ክትትል ይደረግላታል፡፡
• አስፈላጊ የላብራቶሪ ምርመራ ናሙና እዚያው ማዋለጃ ክፍል
ውስጥ ተወስዶ በተላላኪዎች /Porters/ ወደ ላቦራቶሪ ክፍል
ይላካል፡፡ እናትየዋ ከወለደች በኃላ እሷና ጨቅላ ህፃኑ ለ6 ሰዓት
እዚያው ጤናጣቢያ መቆየት አለባቸው፡፡
• የጤንነታቸው ሁኔታ ደህና መሆኑ ሲረጋገጥ ለድህረ ወሊድ
ክትትል ልጁን ይዛ አንድትመጣ ከተመከረች በኃላ ወደ ቤቷ
እንድትሄድ ይደረጋል፡፡
የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት…
6. የህሙማን ቅብብሎሽና የላይዘን ስርዓት
• እያንዳንዱ ጤና ጣቢያ በሕማሙን ቅብበሎሽ ላይ የሚሠራ
ባለሙያ /ላይዘን ኦፊሰር / ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡
• የላይዘን ቢሮው፡-
• ተኝተው ለሚታከሙ የድንገተኛ አልጋ ያመቻቻል፡፡
• የሪፈራል አገልግሎትን ይሠራል፡፡
• ለድንገተኛ እና ተመላላሽ ታካሚዎች የማህበራዊ አገልግሎት
/social services/ ይሰጣል፡፡
• የላይዘን ኦፊሰሩ በጤና ጣቢያው የሚሰጡ አገልግሎት ጠቋሚ/
service directory/ ከየአገልግሎት ክፍሎች ስልከ ቁጥር ጋር
በጽሁፍ አዘጋጅቶ ማስቀመጥ አለበት ፡፡
 
የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት…
የህሙማን ቅብብሎሽ
• እያንዳንዱ ጤና ጣቢያ ህሙማንን ከሌሎች ጤና ተቋማት
የሚቀበልበት ወይም የሚልክበት መመሪያ ማውጣት አለበት፡፡
• ይህንንን መመሪያ ሁሉም የህሙማን ቅብብሎሽ የሚመለከተው
ባለሙያ ሊያውቀው ይገባል፡፡ ይህ መመሪያ ህሙማንን ለመቀበል
ወይም ለመላክ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ያጠቃልላል፡፡
• በነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ በቅብብሎሽ ስርዓት መረብ ውስጥ
ያሉ ጤና ተቋማት ሊስማሙበት ያስፈልጋል፡፡
• በተጨማሪም ጤና ጣቢያው የሚሰጠውን አገልግሎት /service
directory/ ታካሚዎቹን የሚልክበትና የሚቀበልበት የጤና ተቋማት
ዝርዝር እስከነ አድራሻቸው/የስልክ ወይም ፋክስቁጥር/ ሊኖረው
ይገባል፡፡
የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሕሙማን ፍሰትና አደረጃጀት…
• ጤና ጣቢያው በሚከተሉት ምክንያቶች ታካሚዎችን ወደ ሌላ
ተቋም ሊልክ ይችላል፤
1. የተፈለገው የህክምና አገልግሎት ከሌለ
2. የሚፈለገዉ የህክምና ባለሙያ ከሌለ ወይም
3. አልጋ ከሌለ፡፡
• ጤና ጣቢያው ህሙማንን ከሌሎች ጤና ተቋማት ተቀብሎ
ከሆነ፤ የመረመረውን ባለሙያ ስም፣የታካሚውን ህመምና
ሁኔታ አጠቃሎ የያዘ ግብረ መልስ /feed-back/ ለላከለት
ተቋም መፃፍ አለበት፡፡

Check list

You might also like