Professional Documents
Culture Documents
Debub Negarit Gazeta of The Southern Nations Nationalities and Peoples Regional State
Debub Negarit Gazeta of The Southern Nations Nationalities and Peoples Regional State
1
፩. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ “የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣንን ለማቋቋም
የወጣ ደንብ ቁጥር 1፻፴፭/፪ሺ፰” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
፪. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡-
፩. “ምግብ” ማለት ማንኛውም በጥሬነቱ፣ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ
የተዘጋጀ ለንግድ ወይም በሌላ መንገድ ለህብረተሰቡ አገልግሎት ቀርቦ ለሰው
ምግብነት የሚውል ነገር ሲሆን ውኃ ወይም ሌላ መጠጥ፣ የሚታኘክ
ማስቲካ፣ ተጨማሪ ምግብ እንዲሁም ምግብ ለማምረት፣ ለማዘጋጀት ወይም
ለማከምና ማንኛውም ንጥረ ነገር የሚያካትት ሆኖ ትንባሆና ለመድኃኒትነት
ብቻ የሚያገለግሉ ንጥረ ነገሮችን አይጨምርም፤
2. “መድኃኒት” ማለት የሰውን በሽታ ለመመርመር፣ ለማከም፣ ለማስታገስ
2
የጥርስ ሕክምና መሣሪያ-ዎች እና የቁስል መስፊያ ክሮችን፣ ሲሪንጆ-ችን፣
መርፌዎችን፣ ፋሻ፣ ጐዝ፣ ጥጥና መሰል ዝግጅቶችን፣ ሰው ሰራሽ ጥርሶችን፣
ኬሚካሎችን፣ የጨረራ ፊልሞችንና ሌሎች መሰል መሳሪያዎችና መገልገያዎችን
ይጨምራል፤
፮. “የሳኒተሪ ዝግጅት” ማለት የሰው ወይም የቤት ውስጥ ንጽህናን ለመጠበቂያ
የሚያገ-ለግል ማንኛውም ዝግጅት ሲሆን ፓዶችን፣ ታምፖችን፣ የጥርስ ንጽሕና
መጠበቂያ ዝግጅቶችን፣ የላብ መምጠጫዎችን እና ዲተርጀንቶችን ይጨምራል፤
3
በማስመሰል ወይም የምግብነት ወይም የመድኃኒትነት ይዘትና ባህርይ ለውጦ
በማቅረብ በሰው ጤና ላይ ጉዳት ማስከተል ነው፤
፲፫. “ተቆጣጣሪ” ማለት በዚህ ደንብ መሠረት የቁጥጥር ተግባራትን ለማከናወን
አግባብ ባለው አካል ሥልጣን የተሰጠው ማንኛውም ባለሙያ ነው፤
፲፬. “ቆሻሻ” ማለት ከኢንዱስትሪዎች፣ከእርሻ ቦታዎች፣ ከትምህርት ቤቶች፣
ከመኖሪያ ቤቶች፣ ከንግድ ስፍራዎች፣ከጤናና ምርምር ተቋማት፣ ከመጸዳጃ
ቤት ወይም ከሌሎች መሰል ተቋሞች የሚወጣና በሰው ወይም በእንስሳት ጤና
ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ፈሳሽ፣ደረቅ ቆሻሻ ወይም ሌላ ቆሻሻ ነው፤
፲፭. “የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ጉድለት” ማለት ሰው በሚኖርበት አካባቢ የሚገኝ
በአካላዊ እድገት፣ በጤና ወይም በአኗኗር ዘይቤ ላይ ተጽዕኖ ሊያስከትል የሚችል
ማናቸውም ሁኔታ ነው፤
፲፮. “የጤና ባለሙያ” ማለት የሰውን ጤና ለመጠበቅ ወይም አገልግሎት ለመስ-
ጠት አግባብ ባለው አካል እንደ ጤና ባለሙያ የተመዘገበ ሰው ነው፤
፲፮ “ የሕክምና ባለሙያ” ማለት ሕመምተ-ኛውን በመመርመር የበሽታውን ዓይነት
የሚለይና በመድኃኒት ወይም አካልን በመቅደድ የሚያክም የሰው ሐኪም
ወይም እነዚህኑ ተግባራት እንዲያከና-ውን በአስፈጻሚው አካል የተፈቀደለት
የጤና ባለሙያ ነው፤
፲፰ “የመድኃኒት ባለሙያ” ማለት አግባብ ባለው አካል የሙያ ሥራ ፈቃድ
የተሰጠው ፋርማሲስት፣ ድራጊስት ወይም ፋርማሲ ቴክኒሻን ነው፤
፲፱. “ባህላዊ ሕክምና” ማለት አገር በቀል የሆነና በልምድ የካበተ እንዲሁም
በህብረተሰቡ ተቀባይነት ያገኘ ዕውቀት ሆኖ የዕጽዋትን ወይም የእንስሳትን
ተዋጽኦ፣ የማዕድናት ወይም የእጅ ጥበብ በመጠቀም የሚሰጥ የሕክምና
አገልግሎት ነው፤
፳ “የባህላዊ ሕክምና አዋቂ” ማለት ባህላዊ ሕክምና ለመስጠት አግባብ ባለው አካል
የሥራ ፈቃድ የተሰጠው ሰው ነው፤
፳፩. “የሙያ ሥራ ፈቃድ” ማለት የጤና አጠባበቅ አገልግሎት ወይም ሌሎች
ተዛማጅ አገልግሎቶችን ለማበርከት እንዲችል ለጤና ባለሙያ የሚሰጥ የምስክር
ወረቀት ነው፤
፳፪ “የጤና ተቋም” ማለት የጤና ማበልጸግ፣የበሽታ መከላከል፣ ማከምና መልሶ
ማቋቋም ሥራዎችን ወይም የመድኃኒት ንግድ ሥራን ወይም አገልግሎት
4
የሚያከናውን ማንኛውም የመንግሥት፣መንግሥታዊ ያልሆነ ወይም የግል
ተቋም ነው፤
፳፫. “ጤና ነክ ቁጥጥር የሚደረግበት ተቋም” ማለት ማንኛውም የኅብረተሰብ
መገልገያ ተቋም ሲሆን፣ ትምህርት ቤት፣ ማረሚያ ቤት፣ የአረጋውያን
መንከባከቢያ ማዕከላት፣የአሳዳጊ አልባ ህፃናት ማዕከላት፣ መዋዕለ ህፃናት፣
የገበያ ቦታዎች፣ የስፖርት ቦታዎች፣ የመታሻ ማዕከላት፣ የመዝናኛ
ማዕከላት፣ የጸጉር ቤቶችና የውበት ሳሎኖችን ይጨመራል፤
፳፬. “ሥራ ነክ ጤና አጠባበቅ” ማለት በሥራ አካባቢ የሚከሰቱ ወይም ከሥራ
ጋር ግን-ኙነት ያላቸው ኬሚካላዊ፣ ፊዚካላዊና ሥነ ሕይወታዊ ጎጂ ንጥረ
ነገሮች በመከላከልና በመቆጣጠር ሠራተኞች ለአደጋ እንዳይ-ጋለጡ በማድረግ
ሳይንሳዊ፣ ቴክኖሎጂያዊና አስተዳደራዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የሠራ-ተኞችን
ጤንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ሳይንስ ነው፤
፳፭ “ክልል” ማለት የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግሥት ነው
፳፮.. #አስፈጻሚው አካል$ TKƒ ¾¡MK< የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች
ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ነዉ፡፡
፳፯. “ዳይሬክተር”TKƒ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የጤናና ጤና ነክ
አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዳይሬክተር ነው፡፡
፳፰. “አግባብነት” ያለው አካል$ TKƒ እ”Å ›Óvu< ¾¡MK< vKeM×” ¨ÃU ¾Ö?““
Ö?“ ’¡ ›ÑMÓKA„‹“ Ów›„‹ Ø^ƒ lØØ` እ”Ç=ÁÅ`Ó eM×” ¾}cÖ¨<
¾µ” ¨ÃU M¿ ¨[Ç ¨ÃU ¨[Ç“ Ÿ}T ›e}ÇÅ` ¨ÃU K?L }sU ነው፡፡
፳፱ “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፣
፴. “ቢሮ” ማለት የክልሉ ጤና ቢሮ ነው፣
፴፩. “የፌደራል ባለሥልጣን” ማለት የኢትዮጵያ የምግብ፣ መድኃኒት ጤና አስተዳደር
ቁጥጥር ባለስልጣን ነው፡፡
፴፪ ማንኛውም በወንድ ፆታ የተደነገገው ሴትንም ያካትታል፣
፫ የተፈጻሚነት ወሰን
5
፬. መቋቋም
፩. የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከዚህ በኋላ
ባለስልጣኑ እየተባለ የሚጠራ የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የክልሉ መንግሥት
መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል፡፡
፪. የባለስልጣንው ተጠሪነት ለቢሮው ይሆናል፡፡
፭. ዋና መሥሪያ ቤት
የባለስልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት ሀዋሳ ሆኖ እንዳስፈላጊነቱ በየአሰተዳደር ዕርከኖቹ
ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ሊያቋቋም ይችላል፡፡
፮. ዓላማ
የባለስልጣኑ ዓላማ፡-
፩ የምግብ ደህንነትና ጥራትን፣
፪ የመድኃኒት ደህንነት፣ፈዋሽነት፣ጥራትና አግባባዊ አጠቃቀምን፣
፫ የጤና፣የህክምናና የመድኃኒት ባለሙያዎችን ሙያዊና የስነ-ምግባር ብቃትን፣
፬ የጤና ተቋሞችን ድርጅታዊ ብቃትን፣ እና
፭ የሀይጂንና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ለግልና ለሕብረተሰብ ጤና ተስማሚ መሆኑን፣
፯. ስልጣንና ተግባራት
ባለስልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣
6
፭. ለመንግስት፣ መንግስታዊ ላልሆኑ ጤና ተቋማት፣ ለጠቅላላና የመጀመሪያ ደረጃ
ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ጤና ኬላዎች፣ ክሊኒኮች፣ የመድኃኒት ችርቻሮ ንግድ
ድርጅቶች፣ ሚዲካል ላቦራቶሪዎች፣ ዲያግኖስቲክ ኢሜጅንግ፣ የምግብ አገልግሎት መስጫ
ተቋማትና ቁጥጥር የሚደረግባቸዉ ጤና ነክ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት
ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያሽጋል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤
፮. በክልሉ የምግብ፣ የመድኃኒት፣ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ፣ የጤና ባለሙያዎች እና የጤናና
ጤና ነክ ቁጥጥር የሚደረግባቸዉን ተቋማት በሚመለከት የመረጃ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፤
፯. በምግብ ወይም በመድኃኒት መመረዝ ወይም መበከል ምክንያት ለሚደርስ የሞት፣ የጤንነት
መታወክ መንስኤ የሆነውን ንጥረ ነገር ልዩ ልዩ ናሙናዎችን በመውሰድ ወይም በመቀበል
ለምርመራ ይልካል፣ ምንነታቸውን ያረጋግጣል፣ በዉጤቱም መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ
ይወስዳል፤
፰. የትምባሆ ዝግጅትን፣ ሽያጭን፣ አጠቃቀምን፣ የሚሸጡ ወይም የሚቸረችሩ ድርጅቶችን
ማስተዋወቅን፣ አስተሻሸግንና መለያ አሰጣጥንና አወጋገድን ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊዉን
እርምጃ ይወስዳል፤
፱. በክልሉ ውስጥ የወረርሽኝ በሽታ ሲከሰት አስፈላጊ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ መካሄዱን
ያረጋግጣል፤ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፤
፲. በክልሉ ዉስጥ የጤና አገልግሎት ስራ ላይ ለሚሰማሩ የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ
ይሰጣል፣ የሙያ ስነ-ምግባራቸውን ጠብቀው ስለመስራታቸው እያረጋገጠ ያድሳል፣
ያግዳል፣ ይሰርዛል፤ በፌዴራሉ ባለስልጣን የሙያ ምዝገባና ፈቃድ ለሚሰጣቸው የጤና
ባለሙያዎች፣ ለአማራጭና ተደጋጋፊ ህክምና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃዳቸዉ እንዲታደስ
የድጋፍ ደብዳቤ ይሰጣል፣
፲፩. የአገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃ ምግቦች፣ መድኃኒቶችና ጥሬ ዕቃዎቻቸው በአግባቡ
መወገዳቸውን ያረጋግጣል፤
፲፪. ከተለያዩ ተቋማት የሚወጡ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ በሕዝብ ጤና ላይ
ጉዳት የማያስከትል መሆኑን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፣ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን
አሰፈላጊውን ዕርምጃ ይወስዳል፣ በቅንጅት ይሰራል፣
፲፫. ሕገ-ወጥ ምግቦችን፣ መድኃኒቶችንና የጤና አገልግሎቶችን ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊ
እርምጃዎችንም ይወስዳል፤
፲፬. ለህብረተሰቡ የሚቀርብ የመጠጥ ውኃ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል፤
፲፭. ለሽያጭ የሚቀርቡ ምግቦች፣ መድኃኒቶችንና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች በፌደራሉ
ባለስልጣን መመዝገባቸውን ይቆጣጠራል፤ ያረጋግጣል፤
7
፲፮. በክልል ደረጃ የጤና ነክ ቁጥጥር የሚደረግባቸዉ ተቋማት ተገቢውን የሐይጅንና አካባቢ
ጤና አጠባበቅ መስፈርት ማሟላታቸውን ያረጋግጣል፤ ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊውን እርምጃ
ይወስዳል፤
፲፯. ለባህል ህክምና አዋቂዎች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና የሙያ ፈቃድ ይሰጣል፤
ይቆጣጠራል፤ በህጉ መሰረት አስፈላጊዉን እርምጃ ይወስዳል፤
፲፰. የሥራ ነክ ጤና አጠባበቅን ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊዉን እርምጃ ይወስዳል፤
፲፱. ለሽያጭ የቀረበው ማንኛውም ምግብ፣ መድኃኒት ለሰው ምግብነት ወይም መድኃኒትነት
የማይስማማ መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም በህብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል
የታመነበትን አደገኛ ኬሚካል በህግ መሰረት ይሰበስባል፤ በአግባቡ መወገዱንም ያረጋግጣል፤
፳. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የመካከለኛ፣ የቅድመ ወይም ድህረ ምረቃ የጤና
ተማሪዎች የሚማሩትን ትምህርት በተግባር እንዲለማመዱ ወደ ጤና ተቋማት እንዲሰማሩና
በአግባቡ ልምምድ ማድረጋቸውን ይቆጣጠራል፣ ያረጋግጣል፣
፳፩. በክልሉ የሚከናወኑ የምግብ፣ የመድሃኒትና የጤና አገልግሎት የንግድ ማስታወቂያዎች ላይ
የቁጥጥር ስራዎችን ይሰራል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፣
፳፪. የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሳል ከሰሳል፣
፳፫. ዓላማውን ለመፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
፰. የባለስልጣንው አቋም
ባለስልጣኑ፡-
፩ በመንግስት የሚሾም ዋና ዳይሬክተርና እንደ አስፈላጊነቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች
እንዲሁም፤
፪ ሌሎች አስፈላጊ ሰራተኞች ይኖሩታል፡፡
8
ለ. የባለስልጣኑን ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ ዓመታዊ ዕቅድ፣ የሥራ ፕሮግራምና በጀት
አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፤
፲፪. ስለተቆጣጣሪዎች፣
በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ፪ መሠረት የተመደቡ ተቆጣጣሪዎች
የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖራቸዋል፣
፩. በክልሉ የሚገኙ የጤናና ጤና ነክ ተቋማትን ክፍት በሆኑበት በማንኛውም ሰዓት
ይቆጣጠራሉ፣ አስፈላጊውን ዕርምጃ ይወስዳሉ፣
፪. ጤናን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ሁኔታ ተፈጥሯል የሚያሰኝ መረጃ ሲኖረው
ወደ ማንኛውም ግቢ ወይም ቤት ወይም ህንጻ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመግባት
ፍተሻ ያደርጋል፣
፫. ምርመራ ለማድረግ ወይም መረጃ ለመሰብሰብ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የተጠረጠሩ
ምግቦችና መድኃኖቶች ላይ ናሙናና ልኮችን የመውሰድ፣ በቪዲዮ የመቅረጽ፣
ፎቶግራፍ የማንሳት፣ መረጃዎችን ፎቶኮፒ የማድረግ እና ውጤቱ እስከሚታወቅ
9
ድረስ በጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል ተብሎ የታመነ ዕቃ ወይም ማቴሪያል ተለይቶ
እንዲቀመጥ ያዛል ያሽጋል፣
፬. የተከለሱ፣ የተበላሹ፣ የተጭበረበሩ፣ የተበከሉ ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት
በተጠቃሚው ላይ ጉዳት ያደርሳሉ ተብሎ የተጠረጠሩ ምግቦችና መድሃኒቶች ላይ
የላቦራቶሪ ምርመራ እንዲካሄድ የማድረግና ውጤቱ እስከሚታወቅ ድረስም
በአገልግሎት ላይ እንዳይውሉ ታሽገው እንዲቀመጡ ያደርጋል፣
፭. ምግቦችና መድኃኒቶች የአገልግሎት ዘመናቸው ሲያበቃ ወይም በዚህ ደንብ
መሠረት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ሲወሰን በተገቢው መንገድ እንዲወገዱ
መደረጋቸውን ይቆጣጠራል፣
፮. በማናቸውም ቁጥጥር በሚደረግባቸው የጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ የጤና
ባለሙያዎችን መረጃ በመጠየቅ፣ በማየት፣ በመመርመር፣ ማረጋገጥና
አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፣
፯. የሃይጅንና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ቁጥጥር ደርጋል አስፈላገውን እርምጃ
ይወስዳል፣
፲፪. በጀት
ባለስልጣኑ የሚከተሉት የበጀት ምንጮች ይኖሩታል፡፡
ሀ. ከክልሉ መንግሥት የሚመደብ በጀት፣
ለ. ከሌሎች ምንጮች የሚገኝ ገቢ፡፡
10
የተሸፈኑ ጉዳዮችን በሚመለከት ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡
፲፯. መመሪያ የማውጣት ሥልጣን
ቢሮው ይህንን ደንብ በሥራ ላይ ለማዋል የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ሊያወጣ
ይችላል፣
፲፰. ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ ደንብ ከጸደቀበት ከህዳር ፱ ቀን ፪ሺ፰ ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡
ደሴ ዳልኬ
ርዕሰ መስተዳድር
11
ydb#B B/@eke B/@Rica ?ZïC KILL mNGST db#B
nU¶T Uz@È
DEBUB NEGARIT GAZETA OF THE SOUTHERN NATIONS,
NATIONALITIES AND PEOPLE’S REGIONAL STATE
ዋጅ
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል “Southern, Nations, Nationalities and Peoples’
መንግሥት ጤና ተቋማት የመድኃኒት Regional State Health Institutions Pharmacy
አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ደንብ ቁጥር Service Delivery System Regulation No 118/2014
፻፲፰/፪ሺ፯
መግቢያ Preamble
ጤና ለአንድ ህብረተሰብ የአካል፣ የአዕምሮ እና Whereas; it has been applicable to ensure the
የማህበራዊ ደህንነት መሠረት ሲሆን መድኃኒት appropriate usage and availability of enough amount
ደግሞ ለጤና አገልግሎቱ ስኬታማነት ወሳኝ of the necessary medicine and medical equipments in
ድርሻ ያለው በመሆኑ እና በክልሉ ውስጥ the region as health is the foundation for physical,
አስፈላጊ መድኃኒቶችና የሕክምና መሳሪያዎች mental and social security of a society, and medicines
have major contribution to the success of health
በበቂ መጠን መኖራቸውንና በአግባቡ ጥቅም ላይ
service as well;
መዋላቸውን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የመድኃኒት አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጡ Whereas; it has been found necessary to correct
ጠንካራ የሆነ ስርዓት የተከተለ ካለመሆኑ ጋር social and economical impediment resulted from
ተያይዞ እየተከሰተ ባለው ብክነትና ምዝበራ፣ ህገ misuse and fraudulent, illegal medicine transfer and
ወጥ የመድኃኒት ዝውውር እና ኢ-ፍትሃዊ unfair pharmaceutical budget usage which come due
የመድኃኒት በጀት አጠቃቀም የተነሳ to rigorous pharmaceutical administration service
የሚደርሰውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር system not being followed
ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
አግባብነት በሌለው የመድኃኒት አጠቃቀምና Whereas, it has been found very pivotal to eradicate
health problem as well as economic crisis that occur
አያያዝ ምክንያት በተለይም ከጸረ-ተህዋስያን
upon the people due to irrelevant pharmaceutical
መድኃኒቶች ፍቱንነት አቅም መዳከም ጋር usage and handling especial associated with the
ተያይዞ በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የጤና weakness of antimicrobials cureability power;
መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋና ቀጣይነት their ability to buy and with affordable price and
2
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል Now therefore, southern Nation, Nationalities and
peoples’ Regional state has issued this regulation in
መንግሥት የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር
accordance with sub-article /1/ ariticle /45/ of the
እንደገና ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር ፻፴፫/፪፼፫ proclamation No 133/2010 issued to redetermine the
አንቀጽ ፵፭ ንዑስ አንቀጽ ፩ በተሰጠዉ ስልጣን power and duty of executive bodies;
ጠቅላላ General
2. Definition
2. ትርጓሜ
Unless the context requires otherwise, in this
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው regulation;
ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ፡-
1. “Region” means Southern Nation,
1. "ክልል" ማለት የደቡብ ብሔሮች
Nationalities and peoples’ Region;
ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ነው፤
2. “Bureau” means Southern Nation,
2. "ቢሮ" ማለት የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና Nationalities and Peoples’ Region Health
ሕዝቦች ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ነው፤ Bureau;
3. "የጤና ተቋም" ማለት ለህብረተሰቡ የጤና
3. “Health Institution” means government
አገልግሎት የሚሰጥ ሆኖ በቢሮ ስር
institution which is administrated under
የሚተዳደር የመንግስት ተቋም ነው፤
the bureau and deliver health service to
4. "አስፈጻሚ አካል" ማለት የቢሮ፣ የዞን
the community.
መምሪያ፣የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
መምሪያ፣ የልዩ ወረዳ፣ የወረዳ ጤና
4. ”Executive Body” means an executive
ጽ/ቤት፣ የከተማ አስተዳደር እና ጤና
who serve with in health institution, city
ተቋማት ውስጥ ሆነው የሚያገለግል administration, wordea health office,
አስፈጻሚ ነው፤ special woreda health office, Hawassa City
administration department, zone
department and Bureau.
3
5. "የጤና አገልግሎት" ማለት የሰውን ልጅ 5. “Health Service” means an act of disease
ጤንነት ለመጠበቅ የሚደረግ በሽታን prevention, diagnosis, treatment, counseling and
8. “የሕክምና መገልገያ” ማለት በሽታን 8. “Medical Utility” means any utility that may be
ለመመርመር ወይም ለማከም በውስጥ used on the inner or outer part of the body for
ወይም በውጭ የሰውነት አካል ጥቅም ላይ diagnosis or treatment of a dsease in human, and
የቁስል መስፊያ ክር፣ መርፌ፣ ፋሻ፣ ጎዝ፣ gauze, Cotton and similar preparations; artificial
teeth, chemicals, x-ray film and other similar
ጓንት፣ ሲሪንጅ፣ ጥጥና መሰል
instruments and utilities;
ዝግጅቶችን፤ ሰው ሠራሽ ጥርሶችን፣
ኬሚካሎችን የጨረር ፊልሞችንና መሰል
መሳሪያዎችን እና መገለገያዎችን
ይጨምራል፤
4
፱ “የሕክምና መሣሪያ” ማለት የሰውን በሽታ 9. “Medical Instrument” means any instrument
ለመመርመር ወይም ለማከም በውስጥ ወይም or utility that may be used on the inner or outer
በውጭ አካል ላይ ጥቅም ላይ የሚውል
part of the body medical instruments as well as
ማንኛውም መሣሪያ ወይም መገልገያ ሲሆን
those various machines, beds, stretcher,
የተለያዩ የመመርመሪያ የላብራቶሪ፣ የቀዶ
ህክምና መሣሪያዎች፣ እንዲሁም ለላብራቶሪ፣ wheelchair, BP apparatus and other familiar
ለራጅ እና ለድንገተኛ ክፍል አገልግሎት instruments and utilities used in laboratory, x-ray
የሚውሉ የተለያዩ ማሽኖች፣ አልጋዎች፣ and emergency room;
ስትሬቸር፣ ዊልቸሮች፣ የደም ግፊት
መለኪያና የመሳሰሉ መሣሪያዎችን እና
መገልገያዎችን ያካትታል፤
፲. “የመድኃኒት ማዘዣ ወረቀት” ማለት ፈቃድ 10. “Prescription Paper” means a legal document
of instruction written by a duly licensed medical
ባለው የሕክምና ባለሙያ የሚጻፍና በመድኃኒት
professional and interpreted by a pharmacy
ባለሙያ ተተርጉሞ መድኃኒትን ከበቂ መረጃ ጋር
personnel which will serve to dispense medicines
ለህሙማን ለማደል የሚያገለግልና ለዚሁ ዓላማ
to patients together with adequate information;
ተብሎ በተገቢው አካል ደረጃ ወጥቶለት የተዘጋጀ
ህጋዊ የማዘዣ ወረቀት ነው፡፡
11. “Medicine Accessibility” means providing
01. “የመድኃኒት ተደራሽነት” ማለት ጥራታቸውን
quality and applicable medicines in sustainable
የጠበቁ አስፈላጊ መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ
way with fair price to the community at the
ዋጋ ቀጣይነት ባለው መልኩ በተፈለገበት demanded time and place;
ቦታና ጊዜ ለተገልጋዩ ኀብረተሰብ ማቅረብ
ነው፤
02. “የመግዢያ ዋጋ” ማለት በመድኃኒት 12. “Purchasing Price” means the price of
አቅራቢዎች ወይም ዕርዳታ ሰጪዎች ሠነድ medicines indicated on the document of either
ላይ የሰፈረው የመድኃኒት ዋጋ ማለት ሲሆን medicine supplier or donors, whereas cost shall
be estimated by the health facility for those
በእርዳታ ለሚመጡና በሠነዳቸው ላይ ዋጋቸው
medicines acquired through donations without
ያልተቀመጠላቸው መድኃኒቶች በተቋሙ
cost;
ባለሙያዎች የሚተመንላቸው ዋጋ ነው፤
5
03. “ነጠላ መሸጫ ዋጋ” ማለት የነጠላ 13. “Unit Selling Price” means a unit price in
ወይም የአንድ እሽግ የመድኃኒት which the health institution sales medicines to
የመግዣ ዋጋና ለትራንስፖርትና መሰል the customers by adding not more than 30%
profit margin on purchase price and transport
ወጪዎች ዋጋ ላይ ሥራውን
and other related expense of one unit or pack of
ለማቀላጠፍ የሚረዳ ከ30 በመቶ
medicine;
ያልበለጠ የትርፍ ምጣኔ በመጨመር
ጤና ተቋሙ መድኃኒቶችን የሚሸጥበት
ዋጋ ነው፤
04. “የችርቻሮ ዋጋ” ማለት ከነጠላ 14. “Retail Price” means a price, which calculated
የመድኃኒት ዋጋ በመነሳት የሚሰላ by taking a unit price as a bench-mark, of a
ሲሆን መድኃኒቱን ጤና ተቋሙ በሽያጭ medicine in which the health institution transfers
ለተጠቃሚው የሚያስተላልፍበት ሲሆን the drug to the consumer by sale, the amount of
ከነጠላ ዋጋ ጋር እኩል ወይም ሊያንስ which might be less than or equal to the price set
05. “የመድኃኒት ዝውውር ወይም ቅብብሎሽ” 15. “Medicine Transfer and Supply Chain “ means
ማለት የተፈቀደ መድኃኒትን በተፈቀደለት where taking permitted medicine over to health
የመድኃኒት ባለሙያ፣ ከህጋዊ አቅራቢ፣ institution, issuing thereof to the various sections
የሙያ ደረጃው በሚፈቅደው መልኩ
and transferring to the patient in appropriate way
ደህንነትን በጠበቀ አያያዝ፣ ህጋዊ የአቅርቦት
by allotted pharmacy professional, from legal
ሰንሰለቱን ተከትሎ ወደ ጤና ተቋማት
supplier, in manner that profession level allows by
ማስገባት፣ ወደ ልዩ ልዩ ክፍሎች ማውጣት
keeping its security and following legal supply
እና ለህሙማኑ በተገቢው መንገድ
chain; it also includes the function that
ማስተላለፍ ሲሆን የአገልግሎት ጊዜያቸው
transferring medicines, among health institutions
በመቃረቡ ምክንያት ወይም ከፍላጎት በላይ
following legal system when medicines are not
ክምችት በመኖሩ ወይም ድንገተኛ
fully utilized within the expiry date or over
የመድኃኒት እጥረት ሲያጋጥም በጤና
stocked or there is in urge at shortage of such
ተቋማት መካከል ህጋዊ አሰራርን ተከትሎ
medicines in another institution.
መድኃኒትን አዘዋውሮ አገልግሎት ላይ
እንዲውል የማድረግ ተግባርንም
ይጨምራል፤
6
06. “ህገ ወጥ የመድኃኒት ዝውውር” 16. “Illegal Transfer of Medicines” means an
ማለት መድኃኒትን ባልተፈቀደለት illegal medicine transfer that to carry out through
ሰው ወይም ካልተፈቀደ ምንጭ
unlicensed person or source, or unprofessional
ወይም የሙያ ደረጃው በማይመጥን
person, or not well handled medicine, or harming
ሰው ወይም ደህንነቱ ባልተጠበቀ
አያያዝ ወይም በማንኛውም ከህግ the community which is an act against the law in
7
፳፩ “ከክፍያ ነጻ የሆኑ መድኃኒቶች” ማለት 21. “Payment Free Medicine” means dispense of
በዕርዳታ የተገኙ ወይም በበጀት those medicing obtained from donation or by
ባለው አካል በየደረጃው የሙያ ፈቃድ professional trained in the field of pharmacy and
licensed at each level by appropriate organ to
የተሰጠው ፋርማሲስት፣ ድራጊስት፣
carry out his duty as pharmacist, druggist or
ወይም ፋርማሲ ቴክኒሽያን ማለት
pharmacy technician;
ነው፤ [[[
፳፫ “የመድኃኒት የምርት መለያ ቁጥር” 23. “Drug Production Identification Code” means
ማለት በአንድ የምርት ሂደት ወቅት a number assigned to identify each batch of
የተመረቱ መድኃኒቶችን ለመለየት medicines produced by its manufacturing entity
በአምራቹ ድርጅት የሚሰጥ በማሸጊያው ,and written on donation list document or on
ላይ እና በግዥ ወይም በእርዳታ both its package and purchasing documents;
8
፳፮ “የተስተካከለ ሽያጭ” ማለት በቀን ሽያጭ 26. “Adjusted Sale” means the correct value of
አማካይነት ከተሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ medicines sold per day which shall be
ማለት ትክክለኛ የመድኃኒት አጠቃቀምን means pharmacy service section that enable
ለማረጋገጥ ፋርማሲስቶች በአስተኝቶ ማከም፣ to get the intended medical outcome through
በተመላላሽ ህክምና አሰጣጥና የክትትል ሂደቱ prohibiting harmful medicinces and making
ፕሮቶዞዋ የመሳሰሉት) ከመድኃኒቶች ጋር the factor that being familiar with disease
አንድ መድኃኒት በተገቢው አቀማመጥ ሆኖ with the right storage, the period of effective
የይዘት ለውጥ ሳያመጣ ሊቆይ የሚችልበት service which medicines are meant to endure
without an occurance of change to its content
ጊዜ ተብሎ በአምራቹ ድርጅት ላይ በግልጽ
as prescribed by its manufacture
የተፃፈ ነው፤
9
፴ “ጥቅም ላይ የማይውሉ መድኃኒቶች” ማለት 30. “Unfit for Use Medicine” means those
የተበከሉ፣ በተገቢው ሁኔታ ያልተቀመጡ፣ medicines which are rather contaminated, in
አላግባብ የተከፈቱ፣ የቀዝቃዛ ሰንሰለት appropriately packed, not maintaining cold
ያልጠበቁ፣ በተገቢው አካል ጥቅም ላይ chains, prohibited from use by the appropriate
እንዳይውሉ የተከለከሉ፣ የአገልግሎት ዘመን body, expired medicines as well as those with
ማብቂያ ያለፈባቸው እና በሌሎች ምክንያቶች change in content due to any other similar
የይዘት ለውጥ ያስከተሉና ለሰው ጤና አደገኛ reasons and henceforth dangerous to human
የሆኑ መድኃኒቶች ናቸው፤ health
፴፩. “የፅንስ ስም” ማለት ከአገር አገር ወይም 31. “Scientific Name” means medicine
ከፋብሪካ ፋብሪካ የማይለዋወጥ identification name given based medicine
በመድኃኒቱ ንጥረ ነገር ላይ ተመስርቶ ingredient and unchangeable from country to
የወጣ የመድኃኒት መለያ ስም ነው፡፡
country or manufacturing to manufacturing;
፴፪ “የመድኃኒት ሂሣብ ሠራተኛ” ማለት
በአካውንቲንግ ወይም በተመሳሳይ ሙያ 32. “Pharmacy Accountant” means an accountant
graduated with accounting and other related
መስመሮች ተመርቆና ተቀጥሮ የመድኃኒት
field and employed and work as pharmacy
ሂሳብ ስራ የሚሠራ ባለሙያ ነው፡፡
accountant ;
፴፫ “መድኃኒት ማስወገድ” ማለት በተለያየ
33. “Medicine Disposal” means an action to
ምክንያት ጥቅም ላይ መዋል የማይችሉ dispose those medicines which may no longer
መድኃኒቶችን ማስወገድ ነው፤ be usable for various reasons:’
፴፬ “የመድኃኒት መጋዘን” ማለት ከቢሮ እስከ ጤና 34. “Medicine store” means storage that exist from
ተቋም ያሉ የመድኃኒት ማከማቻ ነው፤ bureau up to health institution
፴፭ “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ 35. “Person” Means natural or juridical person.
የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፡፡
ይህ ደንብ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና This regulation shall apply to the Southern
ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ እና በስሩ እስከ Nations, Nationalities and Peoples’ Regional
ጤና ተቋማት ባለው የጤና መዋቅር ላይ bureau and health structure found under it up to
ተፈጻሚ ይሆናል:: health institutions.
10
6. Objectives
5. ዓላማ
The regulation shall have the following
ደንቡ የሚከተሉት ዓላማዎች
objectives:-
ይኖሩታል፡-
1. ለህብረተሰቡ የመሠረታዊ መድሐኒቶችና 1. To enhance the customers’ satisfaction
የሕክምና መሳሪያዎች በበቂ መጠን through providing fundamental medicine and
11
ክፍል ሁለት Part Two
የአስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር Power and Duty of Executive Bodie
12
5. ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ጋር 5. Facilitate the conditions to prepare suitable
በመሆን ለመድኃኒት አገልግሎት አሰጣጥ receiving voucher, issuing voucher, sales
አመች የሆኑ የገቢ፣ የወጪ፣ የሽያጭ
tickets and other forms in collaboration with
መሰብሰቢያ ሠነዶችንና ሌሎች አሠራሩን
Finance and Economic Development Bureau;
የሚያግዙ ቅፆች እንዲዘጋጁና ሥራ ላይ
እንዲውሉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤ 6. Lay-down procedural and organizational
6. የመድኃኒት ሥራ አመራሩን በተመለከተ systems; give professional capacity building
training to those pharmacy professionals and
ለመድኃኒት ባለሙያዎችና ሌሎች ፈፃሚ
other executive body regarding the medicines
አካላት የሙያ አቅም ግንባታ ስልጠና
management; follow-up the implementation
ይሰጣል፤ የአሠራርና አደረጃጀት ስርዓት
thereof;
ይዘረጋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ 7. So as to supervise the existence of
7. የመድኃኒት አቀርቦት፣ ስርጭትና standardized practice in medicine supply,
አጠቃቀም ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን distribution and utilization in the
ለመከታተል ያመች ዘንድ በየጤና ተቋማቱ administration, provide the necessary support
የመድኃኒትና ሕክምና ኮሚቴ እንዲቋቋምና and follow-up to establish drug and
ኃላፊነቱን እንዲወጣ ድጋፍና ክትትል therapeutic committee and execute their
ያደርጋል፤ ስለ አፈፃፀሙ ዝርዝር መመሪያ responsibilities, and issue detail directive for
ያወጣል፤ implementation;
8. በጤና ተቋማት በሚገኙት የመድኃኒት 8. Issue detailed guideline that describe the
መጋዝኖችና የመድኃኒት ማደያ ክፍሎች responsibilities of pharmacy professionals
working in the pharmacy whore house and
ውስጥ የሚሠሩ የመድኃኒት ባለሙያዎች
distribution centers of health institution with
በየክፍላቸው በጋራ የመስራት፣
regard to collective responsibility and
መድኃኒቶችን በጋራ የመረከብ፣
accountability while working as a team in
የማስተዳደር እና የመንከባከብ የጋራ receiving medicines, managing medicines and
ኃላፊነትና ተጠያቂነት እንዳለባቸው taking care of medicines;
የሚገልጽ ዝርዝር መመሪያ ያወጣል፤ 9. Where it is acknowledged that there are
9. በጤና ተቋማት ውስጥ ከፍጆታ በላይ
medicines stockpiled in excess of current
ሆነው የተከማቹ መድኃኒቶች መኖራቸው
consumption in health institution or due to
ሲታወቅ ወይም በልዩ ልዩ ምክንያት
የህይወት አድን የመድኃኒቶች ድንገተኛ different reasons, incidental scarcity of life
እጥረት ሲከሰት ወደ ሌሎች የጤና saver drugs exist, introduces a system in
ተቋማት ተዛውረው አገልግሎት ላይ which such medicines may be transferred into
የሚውሉበትን የአሠራር መመሪያ
other locations which running out of stock
ያወጣል፤
and be utilized.
፲ የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱና በልዩ 10. Monitor the disposal of any expired
ልዩ ምክንያት ጥቅም ላይ የማይውሉ
medicines and unfit for use medicines due to
መድኃኒቶች ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው
የአሠራር መመሪያ መሠረት መወገዳቸውን various reasons in accordance with the
ይከታተላል፤ directive prepared for this purpose;
13
01. ለመድኃኒት አገልግሎት አሰጣጥ 11. Put in place an information management and
የሚያገለግል የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም utilization system in support of the provision
02. በጤና ተቋማት ውስጥ ገቢና ወጭ ሆነው 12. Formulated and implement a system whether
medicines that received and issued are to be
ወደተለያዩ ክፍሎች የሚሠራጩ
handed-out to different departments in the
መድኃኒቶች ለተጠቃሚው በትክክል
health institutions are correctly delivered to
መድረሳቸውን እና የተገልጋይ እርካታ
users and ensure customer’s satisfaction;
የሚረጋግጥበትን የአሠራር ስርዓት
ይዘረጋል፤
03. በመድኃኒት አገልግሎት አሰጣጥና 13. Issue a guideline on compensation for
shortage vulnerability and indemnity to those
ሥርጭት ተግባር ላይ ለተሰማሩ
professionals and staff working on
ሠራተኞች ባለሙያዎች የካዝና
pharmaceutical service delivery and
መጠበቂያና የጉድለት ተጋላጭነት ማካካሻ
distribution;
መመሪያ ያወጣል፤ [[
04. የመድኃኒት አቅርቦትና አጠቃቀም ኦዲት 14. Ensure that drug prevision and utilization
ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በውስጥና audit made at least once a year by internal and
ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፤ ጥፋት ሲከሰት effective manner, and take corrective measure
up on muddle happen;
ወቅታዊ የማሰተካከያ እርምጃ ይወስዳል::
14
17. Cause to examine in every three months
07. የቢሮዉን የመድኃኒት አቅርቦትና ስርጭት
pharmaceutical provision and distribution of
በየሦስት ወሩ በኦዲተር ያስመረምራል፤
the bureau by the auditor;
በኦዲት ግኝት መሠረት ተገቢውን እርምጃ
ይወስዳል፡፡
08. የመድኃኒት ግዥ፣ አቅርቦትና ስርጭት 18. Perform drug procurement, supply and
ጊዜው ያላለፈ መሆኑንና ከማለፉ በፊት expired and used before expiration;
መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
፳፪ በቢሮው የመድኃኒት ገቢና ወጪ 22. Monitor the drug received and issued copy
የተሰራባቸዉ ቅጂ ሰነዶች በክምችት voucher have been filed by the concerned
ተቆጣጣሪ ሰራተኛ ፋይል መደረጋቸውን worker;
ይቆጣጠራል፡፡
15
፳፫ ወደ ቢሮ የመድኃኒት መጋዘን ለተለያዩ 23. Follow-up those madicines to issue to
ተቋማት ወጪ የሚደረጉ መድኃኒቶች different institutions from the bureau
የመድኃኒቱን የምርት መለያ ቁጥር፣ according to their budget sources by depicting
የማንነት መግለጫ፣ መጠን፣ መለኪያ፣ the production identification number, identity
description, quantity, measurement, unit price,
የነጠላ ዋጋ፣ የውስጥ መለያ ኮድ እና
internal ideatification code, and service period
የአገልግሎት ዘመኑን በሚገልጽ ለዚሁ ዓላማ
based on medicine issuing voucher which
ተብሎ በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
printed for such porpose by finance and
በሚታተም የመድኃኒት የወጪ ደረሰኝ
economy development bureau;
በየበጀት ምንጫቸው ተለይቶ ወጪ
መደረጉን ይከታተላል፤
፳፬ በቢሮው መጋዘን የሚገኙ መድኃኒቶችን 24. Ensure that an inveatory made once in every
መ. በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር d) monitor and supervise over the entire
process governing the pharmaceutical
ፖሊሲዎች፣ ህጎችና መርሆዎች አፈፃፀም service delivery, and follow up its
መሠረት የመድኃኒት አቅርቦትና implementation; take, as appropriate,
corrective measure; follow-up the
ሥርጭት ሂደቱን ይቆጣጠራል፤አመራር
performance there of;
ይሰጣል፤ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የማስተካከያ እርምጃ
እንዲወሰድ ያደርጋል፤
16
ሠ. የመድኃኒት ሥራ አመራሩን በተመለከተ e) coordinate professional capacity building
ለመድኃኒት ባለሙያዎችና ሌሎች ፈፃሚ training to those pharmacy professionals
አካላት የሙያ አቅም ግንባታ ስልጠና and other executive bodies regarding the
እንዲሰጥ ያስተባብራል፤ የአሠራርና medicinal management; ensure the lay
አደረጃጀት ስርዓት መዘርጋቱን ያረጋግጣል፤ down of procedural and organizational
system;
አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
17
ቸ. የመድኃኒት አቅርቦትና አጠቃቀም ቢያንስ l) Ensure that drug provision and usage
በሦስት ወር አንድ ጊዜ ኦዲት መደረጉን audit made at least once in every three
ያረጋግጣል፤ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፤ months by auditor; take the necessary
measure.
፪ የራሱን ተቋም የመድሃኒት አያያዝና 2. Concerning medicine handling and
dissemination of its institution
ስርጭትን በተመለከተ፡-
ሀ. ገቢ የሆኑ መድኃኒቶችን ውጤታማ በሆነ a) Ensure the drugs that took over have
18
ረ. የመድኃኒት ግዥን የፈፀመውና የሚረከበው f) Make sure that the one who purchased
የፋርማሲ ባለሙያ የተለያዩ መሆናቸውን and to take-over drugs are different in
ያረጋግጣል፡፡ profession;
g) Ensure that an inventory made atleast
ሰ. በመጋዘን የሚገኙ መድኃኒቶች ቢያንስ
once in a year on drugs found in the
በዓመት አንድ ጊዜ ቆጠራ መደረጉን
store.
ያረጋግጣል፡፡
2. በተለያዩ ምክንያቶች መሠረታዊ 2. Let the higher official know on time when it
19
4. በጤና ተቋም የተመደቡ የሥራ ኃላፊዎችና 4. Ensure whether their officials and staff are
ሠራተኞች በተለያዩ ህጋዊ መንገዶች ወደ
using those received medicines effectively and
ተቋሙ የገቡ መድኃኒቶችን ውጤታማ በሆነ
for intended purpose, and take timely
ሁኔታና ለታለመለት ዓላማ ሥራ ላይ
መዋሉን ያረጋግጣሉ፤ ጥፋት ሲከሰት corrective action in case of violations;
ወቅታዊ የማሰተካከያ እርምጃ ይወስዳሉ::
5. በመድኃኒት አገልግሎት አሰጣጥና ሥርጭት 5. Implement compensation shortage
ሥራ ላይ ለተሰማራ ሠራተኛ ወይም vulnerability and indeminity to those
ባለሙያ የካዝና መጠባበቂያና የጉድለት employee or professional deployed on
ተጋላጭነት ማካካሻ በመመሪያ መሠረት medicine service delivery and dissemination
ተፈፃሚ ያደርጋል፡፡
work based on the directive;
20
0. የመድኃኒት አቅርቦትና አጠቃቀም ኦዲት 10. Cause to audit in every three month the
በየሦስት ወሩ በውስጥ ኦዲተር pharmaceutical provision and utilization by
ያስመረምራል፤ በኦዲት ግኝት መሠረት internal auditor; take the relevant measure based
on the audit result;
ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
11. Perform medicine procurement, supply and
01. የመድኃኒት ግዥ፣ አቅርቦትና ስርጭት
distribution based on finance procurement and
በተመለከተ በፋይናንስ ግዥና ንብረት
property administration law;
አስተዳደር ህግ መሠረት ያከናውናል፡፡
21
4. በመድኃኒት አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት 4. Non-discrimination in cases of
ላይ አድልዎ አለማድረግ፣ pharmaceutical service delivery;
1. የአካባቢውን የበሽታ ስርጭት፣ የጤና 1. Prepare medicine lists that may be calibrated
ተቋሙን አይነት፣ አገር አቀፉን timely by sequencing according to the
የመድኃኒት መዘርዝር እና ሌሎች
necessary they have to health service based
መመዘኛዎችን መሰረት በማድረግ
on the expansion of the disease, type of
በየወቅቱ የሚከለስ ለተቋሙ
የሚያስፈልጉ የመድኃኒቶችን ዝርዝር health institution, pharmacy list of the
ለጤና አገልግሎቱ ካላቸው ተፈላጊነት country and other standard;
አንጻር ቅደም ተከተል በመስጠት
በመድኃኒትና ህክምና ኮሚቴ አማካይነት
የማዘጋጀት፣
22
2. Provide timely procurement request about
2. የመድኃኒት ፍላጎቱ በምክንያት የተደገፈ፣
medicine need supported with clear reason,
ህይወት አድን የሆኑትን መድኃኒቶች
offer priority to life-savior medicine and
ቅድሚያ የሰጠ፣ ካለው የመድኃኒት በጀት
compatible with the existing medicine
ጋር የተጣጣመ በማድረግ የግዥ
budget;
ጥያቄውን በወቅቱ የማቅረብ፣
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ 3. Without prejudice the prescription under sub-
የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ article /2/ of this article and pharmacy fund
ማንኛውም ጤና ተቋም የመድኃኒት
and proclamation No 553/2006 issued to
ግዥ ዕቅድ ሲያዘጋጅ የመድኃኒት ፈንድ
እና የመድኃኒት ፈንድ አቅርቦት establish pharmacy fund supply agency,
ኤጀንሲን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ while any health institution preparing
ቁጥር ፭፻፶፫/፺፱ የተደነገገው እንደተጠበቀ pharmacy procurement plan, choose
ሆኖ በፋይናንስ የግዢ መመሪያ መሠረት procurement system, schedule effective time
የግዥ ዘዴን የመምረጥ፣ የመፈፀሚያ
and facility condition for improvement and
ጊዜ የመወሰንና ዕቅድ የሚሻሻልበትንና
የሚፀድቅበትን ሁኔታ የማመቻቸት፣ approval plan;
4. በተቀናጀ የመድኃኒት መረጃ አያያዝ 4. Offer the demand of supply to the concerned
ስርዓት መሰረት የአቅርቦት ፍላጎቱን body based on the system of medicine
ለሚመለከተው አካል በወቅቱ የማቅረብ፣ information handling;
5. በግዥም ሆነ በእርዳታ የቀረቡ 5. Ensure that the pharmacy provide both by
23
፲፩. መድኃኒቶችን ገቢ ስለማድረግ 11. Receiving Medicines
የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈና ከማለፉ expire date and capable of use before
ከሆነ በተቋሙ የፋርማሲና የመድኃኒት advance such price shall be set by the
institution pharmacy and finance professional
ሂሳብ ክፍል ባለሙያዎች ዋጋው
and the same is approved by higher official of
ተገምቶና በተቋሙ የበላይ ኃላፊ ጸድቆ
the institution thereof with remaining
ከቀሪ የገቢ ደረሰኝ ጋር ተያይዞ መቀመጥ
receiving voucher;
ይሮርበታል፡፡
5. ማንኛውም የጤና ተቋም የመድኃኒት 5. any health institution ascertain that medicine
ግዥን የፈፀመውና የሚረከበው የፋርማሲ procurer and receiver are different in
ባለሙያ የተለያዩ መሆናቸውን professions
ያረጋግጣል፡፡
24
12. Medicine Storage and Handling
፲፪. የመድኃኒት ክምችትና አያያዝ
1. Any health institution shall ensure the proper
1. ማንኛውም የጤና ተቋም ገቢ ያደረገውን
storage of those medicines received by it in a
መድኃኒት ለዚሁ ዓላማ ተብሎ ደረጃውን
standard where house prepared for this
ጠብቆ በተዘጋጀ የመድኃኒት መጋዘን
purpose;
በተገቢው ስርዓት ተደርድሮ መቀመጠን
ያረጋግጣል፡፡
2. የመድኃኒት መጋዘን እና የመድኃኒት ማደያ 2. Medicine wherehouse and medicine
ያረጋግጣል::
4. ማንኛውም የመድኃኒት ባለሙያ 4. Any pharmacy professional shall segregate and
የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን እና በልዩ store those expired and other unfit for use
ልዩ ምክንያት አገልግሎት ሊሰጡ
medicine for various reasons in a separate
የማይችሉ መድኃኒቶችን አገልግሎት
place from those useable medicines, report the
ከሚሰጡ መድኃኒቶች ለይቶ ማስቀመጥና
በወቅቱ ሪፖርት ማድረግ አለበት:: same timely;
25
6. ማንኛውም የመድኃኒት ባለሙያ 6. Any pharmacy professional shall issue or
የሚይዛቸውን መድኃኒቶች በመጠቀሚያ
use those medicine to expire in accordance
ጊዜያቸው ቅደም ተከተል መሰረት
with the order of their expiry date;
የአገልግሎት ጊዜ የሚያልፍባቸውን ቀድሞ
ማውጣት ወይም ጥቅም ላይ ማዋል
አለበት:: 7. Any health institution shall monitor
7. ማንኛውም የጤና ተቋም የመድኃኒት
appropertely and timely registration of
ክምችት እና እንቅስቃሴን ለመከታተልና
ለመቆጣጠር የሚያስችል ቢን ካርድ፣ ስቶክ medicines using bin card ,stock card or soft
ካርድ ወይም ዘመናዊ ሶፍት ዌር ware as well as other mechanisms that
እንዲሁም ሌሎች መንገዶችን በመጠቀም enable to follow up and control the storage
በአግባቡ እና በወቅቱ መመዝገባቸውን and movement of medicines;
መከታተል አለበት፡፡
8. Any health institution shall evaluate the level
8. ማንኛውም የጤና ተቋም በመዘርዝሩ
of the store by taking into consideration the
ያካተታቸውን መድኃኒቶች ባልተቆራረጠ
medicine included in the list are to dispense
ሁኔታ ለህብረተሰቡ እንዲደርሱና
continuousely to the society and not to
እንዳይባክኑ ወቅታዊ የፍጆታ መዋዠቅን
misuse as well as timely fluctuation of
እና የመጠቀሚያ ጊዜን ባገናዘበ መልኩ
consumption and usage period; give a
ክምችቱ ያለበትን ደረጃ መገምገምና ለችግሩ remedial solution for the problem identified;
መፍትሄ መስጠት አለበት፡፡
9. ማንኛውም የጤና ተቋም ልዩ ጥንቃቄ 9. Any Health institution shall make always a
የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒቶች ማለትም follow up on the medicines, which need
ናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን፣
special care, such as narcotic and
መርዞችን እና የቅዝቃዜ ሰንሰለት
የሚፈልጉትን መድኃኒቶችን በየጊዜው Psychotropic, poisons and medicine that
ክትትል ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ demand cooling chain;
፲ ማንኛውም በግዥ ወይም በእርዳታ የተገኘ 10. Where any donated or procured medicine
መድኃኒት የምርት እንከን ያለበት ሆኖ that may have production defect and the
ሲገኝ ይኸው ዓይነት መድኃኒት በሌላ same may be distributed to other place, the
ቦታም ተሰራጭቶ ሊሆን ስለሚችል health institution shall make report to
26
፲፫. የመድኃኒት ስርጭት 13. Medicine Distribution
1. Medicine to issue from various service
1. ከጤና ተቋሙ የመድኃኒት መጋዘን
delivery sections, which are in the health
ለተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች
institution medicine store, shall be in
ወጪ የሚደረጉ መድኃኒቶች ክፍሎቹ
accordance with the lists to be prepared by
ከሚሰጡት አገልግሎት አኳያ የመድኃኒትና
pharmaceutical and medical committee for
ህክምና ኮሚቴ ለየክፍሎቹ በሚያዘጋጀው
each sections on the basis of the services they
መዘርዝር መሰረት መሆን አለበት፡፡ delivery;
2. የጤና ተቋሙ የተለያዩ የአገልግሎት 2. While various service delivery sections of the
መስጫ ክፍሎች የመድኃኒት መጠይቅ health institution provide medicine request,
ሲያቀርቡ ለዚሁ በተዘጋጀው መጠየቂያ ቅጽ it has to be with the request form which
ላይ አስፈላጊ መረጃዎችን በመሙላት prepared for such purpose by filling the
መሆን ይኖርበታል፡፡ necessary information on it;
ባለሙያ የአገልግሎት ክፍሎች በወጣላቸው the institution records the necessary quantity
on the issuing receipt by calculating the
የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመድኃኒት ጥያቄ
consumption based on the information which
በቅፁ መሰረት ተሞልቶ እና በፋርማሲ
filled on the request format according to the
ክፍል አስተባባሪ ተፈቅዶ ሲቀርብለት
schedule issued for each service department,
በቀረበው መረጃ መሰረት ፍጆታቸውን
upon the permission and provision of
በማስላት የሚያስፈልገውን መጠን
pharmacy department coordinator; hand over
በመድኃኒት ወጪ ደረሰኝ መዝግቦ thereof;
ማስረከብ አለበት፡፡
4. የመድኃኒት ገቢና ወጪ የተሰራባቸዉ ቅጂ 4. Copy documents on which receiving and
ሰነዶች በክምችት ተቆጣጣሪ ሰራተኛ ፋይል issuing medicine made shall be filed by store
መደረግ ይኖርበታል፡፡ supervisor;
5. መድኃኒት የተጠየቀባቸው እና ወጪ 5. Documents by which medicine requested and
የተደረገባቸው ሰነዶች በመድኃኒት መጋዘን issued shall be filed by store head and service
27
6. ማንኛውም መድኃኒት ከመጋዘን ወጪ 6. While any medicine to issue from store, it
በሚደረግበት ጊዜ አሰራሩ የመጠቀሚያ shall be based on the principle that give
ጊዜያቸው ቀድሞ የሚያበቁትን መድኃኒቶች priority to those medicine to expire early than
ቅድሚያ በመስጠት መርህ ላይ የተመሰረተ other;
መሆን ይኖርበታል፡፡
7. ማንኛውም መድኃኒት ከመጋዘን ወጪ 7. Any medicine separated from store for
ይወሰናል፡፡
2. በጤና ተቋም የእጅ በእጅ የመድኃኒት 2. In health institution cash sale of medicine
ሽያጭ የሚከናወነው ለዚሁ ሲባል
shall be carried out using medicine cash sale
የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
በሚያሳትመው የእጅ በእጅ የመድኃኒት tickets printed by Finance and Economy
ሽያጭ መሰብሰቢያ ደረሰኝ መሠረት መሆን Development Bureau;
ይኖርበታል::
28
3. ማንኛውም የእጅ በእጅ የመድኃኒት ሽያጭ 3. Any medicines cash sales ticket shall be
reproduced in three copies based on retail
በችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መሰረት በሶስት ቅጅ
selling price and the principal shall be
ተዘጋጅቶ ዋናው ለተገልጋዩ፣ የመጀመሪያዉ delivered to the customer, where as its first
ቅጅ ለገንዘብ ተቀባይ ሲሰጥ ሁለተኛዉ copy shall be given to the cash recipient and
the second copy shall be kept with the main
ደግሞ ከሰነዱ ጋር መቀመጥ አለበት፡፡ document;
4. የመድኃኒት ሽያጭ ለማከናወን የተመደበው 4. Any pharmacy professional assigned to
የመድኃኒት ባለሙያ ስለመድኃኒቱ ዋጋ እና perform such duty shall first inform the price
ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ለተጠቃሚው of the medicines and other particulars to the
customer;
በቅድሚያ መግለጽ አለበት፡፡
5. Any pharmacy professional deployed on
5. ማንኛውም በመድኃኒት ዕደላ ላይ የተሰማራ
pharmacy disperse shall receive sales ticket
የመድኃኒት ባለሙያ የሽያጭ ደረሰኞችን
by his name and implement the same in
በስሙ በመረከብ በተገቢው መንገድ ስራ ላይ
appropriate way;
ማዋል አለበት፡፡
6. የእጅ በእጅ ሽያጩን ለማከናወን የተመደበ 6. Any pharmacy professional assigned to
የመድኃኒት ባለሙያ የመድኃኒቱን መለያ perform cash sales shall write identification
ኮድ፣ የመድኃኒቱን ስም፣ የችርቻሮ ዋጋ፣ code of the medicine, name, retail price, sum
and other detail matter, both in figures and
ድምር እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን ኮድ
letters on sales tickets and sign thereof;
ሽያጭ ደረሰኙ ላይ በቁጥርና በፊደል መጻፍና
መፈረም አለበት፡፡
7. The pharmacy accountant shall prepare daily
7. የመድኃኒት ሂሳብ ሰራተኛው የእለት የሽያጭ
summary of medicines transactions in
ማጠቃለያ ለዚሁ ዓላማ ጤና ተቋሙ
accordance with the form prepared for such
በሚያዘጋጀው ቅጽ መሰረት መሥራት
purpose by health institution;
አለበት፡፡
8. Any health institution wherever there is
8. ማንኛውም የጤና ተቋም በብልጫ ወይም
overage or shortage of sales shall follow up
በጉድለት የተሸጡ መድኃኒቶች ካሉ
that the issue thereof included in daily
በመድኃኒት ሂሳብ ሰራተኛ በየዕለቱ summary report by pharmacy accountant,
የማጠቃለያ ሪፖርት ላይ መካተቱን and take appropriate measure.
ይከታተላል፤ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
29
፲፮. መድኃኒትን በዱቤ ወይም በመድን 16.Credit or Insurance Sale of Medicines
ሽፋን ስለመሸጥ
1. The provision under sub-article /1/ of article
1. በአንቀጽ ፲፭ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተደነገገዉ
/15/ shall be applicable for credit and
በዱቤ ወይም በመድን ሽፋን ለሚሸጡ
insurance medicine sale;
መድኃኒቶችም ተግባራዊ ይሆናል፡፡
2. Where any body request pharmaceutical
2. ማንኛውም አካል በዱቤ ወይም በመድን
service either by credit or by insurance
ሽፋን የመድኃኒት አገልግሎት ሲጠይቅ
ቀደም ብሎ ከጤና ተቋሙ ጋር የዱቤ coverage, first ensure whether there is credit
አገልግሎት ውል የፈጸመ ወይም የጤና service agreement or health insurance
መድን ሽፋን ያለው መሆኑ መረጋገጥ
coverage with the health institution;
ይኖርበታል፡፡
3. እያንዳንዱ የጤና ተቋም የጎዳና 3. The value of medicine given to street
ተዳዳሪዎች፣ ከውጭ አገር ስደት persons, displaced persons, a person found
ተመላሾች፣ በድንገት ህሊናቸውን ስተው
unconscious due to accident and treated or
ወድቀው የተገኙና የታከሙ ህሙማን
በልዩ ልዩ ምክንያት የታከሙበትን anyone who is unable to afford medicines
የመድኃኒት ዋጋ ሊከፍሉ የማይችሉ price for various reasons shall medicine price
ከሆነ፤ የታደሉትን መድኃኒቶች ከከተማ be received from city administration or
አስተዳደር ወይም ከሠራተኛና ማህበራዊ labour and social affair office or health office
ጉዳይ ጽ/ቤት ወይም ከጤና ጽ/ቤት ጋር
by sending detail service upon the mutual
አስቀድሞ በገባው ስምምነት መሰረት
ዝርዝር አገልግሎቱን በመላክ agreement made with health office;
የመድኃኒቱን ዋጋ መቀበል ይኖርበታል፡፡
4. የተጠየቀው መድኃኒት ለህሙማኑ 4. Before delivery to patients the name of the
የአሳካሚ ድርጅት ስም፣ የጤና መድን patient, insurance identification number if the
patient has health insurance coverage, card
ሽፋን ያለው ከሆነ የመድን መለያ
number and other information that describe
ቁጥር፣ የካርድ ቁጥርና ሌሎች
the patient identity shall be ascertained;
የህሙማኑን ማንነት የሚገልጹ
መረጃዎች መረጋገጥ አለባቸው፡፡
30
5. የመድኃኒት ባለሙያው የመድኃኒቱን 5. The pharmacy professional upon registration
ስም፣ ዓይነት፣ ጥንካሬ፣ የእሽግ መጠን፣ of medicine name, type, strength, pack size,
ሽፋን በሰጠው ተቋም ስም ፋይል entered into credit contract and given
insurance coverage;
መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡
8. where those patient who unable to pay and
8. የመክፈል አቅም ለሌላቸዉና መንግስት
government covers their medicine expenses;
የመድኃኒት ወጪያቸዉን ለሚሸፍንላቸዉ
health institutions shall collect their money
ታካሚዎች ጤና ተቋማት ለዱቤ
following the laws proclaimed for credit;
የተደነገጉ ህጎችን ተከትለዉ ገንዘባቸዉን
መሰብሰብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጤና ተቋሙ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፭ 9. upon notification to credit client health
ንዑስ አንቀጽ ፯ ላይ የተገለጸውን የየቀኑ institution shall make the daily summary
ማጠቃለያ ውሉን ለፈጸመው አካል stated under sub article /7/ of article /15/ of
አለበት::
31
፲. በዚህ አንቀጽ የተደነገጉ ድንጋጌዎች 10. without prejudice the provisions stated under
እንደተጠበቁ ሆነዉ መድኃኒትን በጤና this article, selling medicine with insurance
መድን ሽፋን መሸጥ ሌሎች የጤና መድን coverage shall follow other regulations and
directives of health insurance coverage.
ሽፋን ደንቦችና መመሪያዎችን የተከተለ
መሆን ይኖርበታል፡፡
የሰራቸውን በነጻ የሚታደሉ የመድኃኒት dally prescription for free of charge sales and
arranging them orderly shall hand over to
ማዘዣዎችን መዝግቦና በቅደም ተከተላቸው
pharmacy accountant;
አደራጅቶ ለፋርማሲ ሂሳብ ባለሙያ ማስረከብ
ይኖርበታል፡፡
4. Pharmacy department accountant shall collect
4. የመድኃኒት ክፍል ሂሳብ ባለሙያ በየቀኑ
daily dispensed free of charge medicines from
በነጻ የታደሉትን መድኃኒቶች ከመዝገቡ the record or free voucher and prepare
ወይም ከነጻ ደረሰኙ ላይ ለቅሞ የችርቻሮ monthly report about these medicines
ዋጋቸውን በማረጋገጥ እና ሪፖርት confirming their retail price by the name of a
በሚቀርብለት አካል ስም በማደራጀት በነጻ body to whom it is submitted; submit the
ስለታደሉት መድኃኒቶች ወርሃዊ ሪፖርት same to the concerned body.
ለሚመለከተው አካል ማቅረብ አለበት፡፡
32
፲፰. ጥቅም ላይ የማይውሉ መድኃኒቶች 18.Disposal of Unfit Medicine
አወጋገድ
1. በጤና ተቋማት መድኃኒት መጋዘን እና 1. Unfit medicine found in health institution
በተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች medicine store and various service delivery
የሚገኙ ጥቅም ላይ የማይውሉ sections shall be put in separate place
መድኃኒቶች እስኪወገዱ ድረስ ከስድስት
according to their characteristics until they
ወር ላልበለጠ ጊዜ እንደ የባህሪያቸው
ተለይተው አንድ ቦታ መቀመጥ are disposed off;
አለባቸው፡፡
2. በበጀት ዓመቱ የተወገዱ መድኃኒቶች 2. Though during the fiscal year the disposed
አጠቃላይ ለጤና ተቋሙ ከቀረበው medicine wastage quantity has to be
መድኃኒት አንፃር የብክነት መጠን calculated interms many in relation to the
በገንዘብ መሰላት ያለበት ቢሆንም total medicine provide to health institution,
ይኖርበታል፡፡
3. ጥቅም ላይ የማይውሉ መድኃኒቶች 3. Information handling and disposal of unfit
የመረጃ አያያዝና አወጋገድ የኢትዮጵያ medicine shall be carried out based on the
33
2. በጤና ተቋሙ ለታካሚዎች የሚታዘዙ 2. Unless other sounding reasons, the medicine
መድኃኒቶች አሳማኝ በሆነ ምክንያት prescribed to the patient shall be part of those
ካልሆነ በስተቀር በተቋሙ የመድኃኒት medicine lists in the health institution;
መዘርዝር ውስጥ የተካተቱ መሆን
አለባቸው፡፡
3. ማንኛውም የጤና ተቋም በባለሙያዎቹ 3. Any health institution shall ensure whether
የሚታዘዙ መድኃኒቶች የታካሚውን ያለፈ medicine prescription has been carried out by
considering the patient’s past medication,
የህክምና፤ የመድኃኒት አወሳሰድና አስረጂ
way of taking medicine and history as well as
ታሪክ፤ የአመጋገብ ስርዓትና የስራ ሁኔታ
his diet and work condition and by making
ማእከል ያደረገና ታካሚውን ባሳተፈ
the patient part of the medical treatment
መልኩ መከናወኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡
process;
4. በማንኛውም ጤና ተቋም መድኃኒት
4. In any health institution, prescription of
ሲታዘዝ የመድኃኒት ማዘዣ ደረጃውን
medicine shall keep prescription standard;
የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
5. Narcotic and Sycotropic medicines, upon
5. ልዩ ቁጥጥር የሚደረግባቸው መድኃኒቶች which special control made, shall be
ማለትም ናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ
prescribed by the prescription papers
መድኃኒቶች ለዚሁ ተግባር በሚመለከተው
አካል በተዘጋጁት ማዘዣ ወረቀቶች ብቻ prepared by concerned body for such
መታዘዝ አለበት፡፡ purpose;
6. መድኃኒት የሚታዘዘው የሙያ ደረጃው 6. Drugs shall only be prescribed by a
በሚፈቅድለት ባለሙያ ብቻ መሆን professional whose level of profession allows
አለበት፡፡ to do so;
7. አስገዳጅ ወይም አሳማኝ ምክንያት ከሌለ 7. Unless there is compelling or convincing
34
፳. ስለመድኃኒት ዕደላ 20.Dispensing of Medicine
1. መድኃኒቶች ለታካሚ ወይም ደንበኛ 1. Before medicine dispensed to patient or
በተመለከተ ስለአወሳሰድ፣ ተጓዳኝ ችግሮች፣ be disclosed how it is taken, its side effect,
the problem it has with food and other
ከምግብና ሌሎች መድኃኒቶች ጋር ስላለው
medicine, its storage and related information
ተቃርኖ፤ የአቀማመጥ ሁኔታና የመሳሰሉት
to patients;
አስፈላጊ መረጃዎች ለህሙማን መነገር
አለበት፡፡
4. Dispensing of medicine shall be carried out
4. የመድኃኒቶች ዕደላ የሚከናወነው የሙያ
only by professional whose level of
ደረጃው በሚፈቅድለት ባለሙያ ብቻ መሆን profession allows;
አለበት፡፡
5. የመድኃኒት ማዘዣ ወረቀቶቹ ልዩ ቁጥጥር 5. Prescription papers to those medicines which
ለሚያስፈልጋቸውም ሆነ ለሌሎች
need special supervision and other medicines
መድኃኒቶች የኢትዮጵያ የምግብ፣
shall be put for specified time and disposed
የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና
ቁጥጥር ባለስልጣን ያወጣው መመሪያ in accordance with the directive issued by
በሚያዘው መሠረት በአግባቡ ፋይል Ethiopian food, medicine and health care
ተደርገው ለተወሰነላቸው ጊዜ መቀመጥና administration control authority;
መወገድ አለባቸው፡፡
6. የመድኃኒት እደላ ስርዓትን በተመለከተ 6. Without prejudice the provisions in this
በዚህ አንቀጽ የተደነገጉት እንደተጠበቁ article concerning dispensing medicine,
ሆነው ጤና ተቋማት አገር አቀፉን የጤና health institution shall implement in a
35
፳፩. የመድኃኒት መረጃ አገልግሎት 21. Pharmacy Information Service
1. በጤና ተቋሙ ውስጥ ለጤና 1. Medicine information desk, which give
ባለሙያዎች የመድኃኒት መረጃ information service to health professionals
አገልግሎት የሚሰጥ እና ህሙማንን
and organized with latest standardized
ስለመድኃኒት አጠቃቀም የሚያስተምር
ደረጃቸውን በጠበቁ ወቅታዊ የመረጃ information that teach the patients about the
ምንጮች የተደራጀ የመድኃኒት መረጃ medicine, shall be established;
ማዕከል መቋቋም አለበት፡፡
2. ማዕከሉ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች 2. The services which offered by the center
በአግባቡ መመዝገብና ፋይል ማድረግ
shall be recorded and filed;
ይኖርበታል፡፡
3. የመረጃ ማዕከሉ ከመድኃኒት አጠቃቀም 3. The information desk shall report expected as
ጋር የተያያዘ የተጠበቁም ሆነ ያልተጠበቁ well as unexpected and heavy side effects of
እና ከበድ ያሉ የመድኃኒት ጉዳቶችን medicine that connected with medicine
36
፳፪. የክሊኒካል ፋርማሲ አገልግሎት 22. Climical Pharmacy Service
37
6. Pharmacist shall give the appropriate
6. ፋርማሲስቶች ተኝተው ስለሚታከሙ
ህሙማን ተከታታይነት ያለው መረጃ counseling to and make attentive follow-up on
በመያዝ ከመድኃኒት አጠቃቀምና the professionals and patients in connection to
የህክምና ውጤት ጋር በተያያዘ የቅርብ medicine utilization and medical result through
ክትትል ማድረግና ተገቢውን ምክር
sustainable handling of information about the
ለባለሙያዎችና ለህሙማን መስጠት
አለባቸው፡፡ inpatients;
ሊሰጧቸው ይገባል፡፡
፳፫. ረጅም ጊዜ ለሚታከሙ ህሙማን 23. Offering Pharmacy Service for Long
የሚሰጥ የፋርማሲ አገልግሎት Time Patient
በአግባቡ መያዝ የሚያስችል ፎርም information about the patient shall be prepared
and implement.
ተዘጋጅቶ ስራ ላይ መዋል አለበት፡፡
38
ክፍል አምስት Part Five
የመድኃኒት ቆጠራ፣ ኦዲትና ሪፖርት ለማድረግ Inventory, Audit and Report of Drug
1. ማንኛውም የመንግስት ጤና ተቋም 1. Any health institution shall carry out physical
በመጋዘንና በመድኃኒት ማደያ ክፍሎች inventory for all its medicines available at
የሚገኙ መድኃኒቶችን ተቋሙ
stores and dispensaries in accordance with its
በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት
schedule at least once per year and at least
በመድኃኒት መጋዘን ቢያንስ በዓመት
አንድ ጊዜ እና በመድኃኒት ማደያ once in every three months respectively;
ክፍሎች ቢያንስ በየሦስት ወሩ ቆጠራ
ማከናወን አለበት፡፡
2. Without prejudice to the provision of sub
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ድንጋጌ
article (1) of this article, any health
እንዳለ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ ማንኛውም
organization may conduct incidental inventory
የጤና ተቋም ድንገተኛ የመድኃኒት ቆጠራ
of medicines as deemed necessary.
ሊያካሂድ ይችላል፡፡
3. በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) እና 3. After reconciling the inventory result obtained
(፪)የተገለጸው የቆጠራ ውጤት under sub-article (1) and (2) of this article
ከመድኃኒት መቆጣጠሪያ መዝገቦች (ቢን with the inventory control records (bin-card,
ካርድ፣ ስቶክ ካርድና ሶፍት ዌር) እና stock –card and soft ware) and financial
ከሂሳብ ሪፖርት ጋር ተገናዝቦ ለጤና reports, the inventory report shall be submitted
ተቋሙ ኃላፊ ሪፖርት መደረግ አለበት፡፡ to the higher body of the health institution.
39
2. ማንኛውም የመድኃኒት ሂሳብ ባለሙያ 2. Any pharmacy accountant shall report the
በወሩ የመጀመሪያ ቀን የነበረውን ድምር transaction balance to the head of health
የመድኃኒት ዋጋ እና በወሩ ውስጥ ወደ institution by deducting the total price of the
ክፍሉ እና ጤና ተቋሙ የገባውን
beginning inventory of the month and total
ጠቅላላ የመድኃኒት ዋጋ በመደመር፣
ከዚሁ ላይ በወሩ ውስጥ የተሸጠውን price of medicines received during the month
ድምር የመድኃኒት ዋጋ እና ጥቅም ላይ from total sold and total price of unused
የማይውሉ መድኃኒቶችን በመለየት፣ medicines during the month.
ከወጭ ቀሪ ያለውን መድኃኒት ለጤና
ተቋሙ ኃላፊ ሪፖርት ማድረግ
አለበት፡፡
1. የፋርማሲ አስተባባሪ በመድኃኒት መዘርዝሩ 1. The pharmacy coordinator shall report those
የተካተቱ ነገር ግን በክምችት እጥረት medicines which are encompassed in the
ያለባቸውንና ሊበላሹ የተቃረቡ መድኃኒቶችን
medicines list; however, rarely available in
በየወሩ ለተቋሙ ኃላፊ ሪፖርት ማድረግ
store and nearly perishable to the head of the
አለበት፡፡
institution on monthly basis ;
2. ማንኛውም የጤና ተቋም ያቀረበው 2. Any health institution shall ascertain that
መድኃኒት የህብረተሰቡን የመግዛት ፍላጎትና medicines available for service are affordable
አቅም ያገናዘበ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡ to the community;
3. ማንኛውም የመድኃኒት ሂሳብ ባለሙያ 3. Any pharmacy accountant shall have the
የተስተናገደውን የተገልጋይ ቁጥር፣ responsibility to keep records of the number of
የተሰጠውን አገልገሎት በዓይነት ጠቅሶ በወሩ patients and the type of service delivered by
መጨረሻ ሪፖርት ማድረግ አለበት፡፡
him in the health institution and report same at
the end of the month,
4. ማንኛዉም የጤና ተቋም አጠቃላይ 4. Any health institution shall report concerning
የፋርማሲ ክፍሉን የሥራ እንቅስቃሴ the overall activities of the pharmacy
በተመለከተ ቢሮ በሚያዘጋጀዉ ሪፖርት
department based on the format that prepared
ማድረጊያ ቅጽ መሰረት ሪፖርት መላክ
አለበት፡፡ by the bureau,
5. ማንኛውም የጤና ተቋም ስለ መድኃኒት 5. Any health institution shall review monthly,
አገልግሎት የሚፈለጉ ሪፖርቶችን በየወሩ፣ quarterly and annual reports regarding
በየሩብ ዓመቱ እና በየዓመቱ የማጠቃለያ pharmaceutical services, and take supportive
ሪፖርት ሰርቶ የማጠናከሪያ እና የማስተካከያ
and corrective measures.
እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡
40
፳፯. ጥቅም ላይ የማይውሉ መድኃኒቶችን 27. Reporting Unfit for Use Medicine
ሪፖርት ስለማድረግ
1. Without prejudice to the provisions
1. ማንኛውም የተቋሙ የስራ ክፍል
stipulated in other laws, any pharmacy
በሌሎች ህጎች ላይ የተደነገጉት
ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው በክፍሉ professional shall record the type ,quantity,
የያዛቸውን የአገልግሎት ጊዜያቸው batch number ,expiry date, name of
ያለፈባቸው፣ የተበከሉ፣ አላግባብ manufacturer unit selling and retail prices of
የተከፈቱ፣ የቅዝቃዜ ሰንሰለት ያልጠበቁ፣
medicines which are expired, contaminated,
በተገቢው አካል ጥቅም ላይ እንዳይውሉ
and in appropriately packed , not kept as
የተከለከሉ፣ እና በሌሎች ተመሳሳይነት
ባላቸው ምክንያቶች ጥቅም ላይ per cold chain, prohibited from use by the
የማይውሉ መድኃኒቶችን የመድኃኒቱን appropriate body, as well as other unfit for
ስም፣ መጠን፣ የምርት መለያ ቁጥር፣ use due to other similar reasons and have the
የአገልግሎት ማብቂያ ቀን፣ የአምራች
responsibility to transfer same to the
ፋብሪካ ስም፣ የነጠላ ዋጋ እና የችርቻሮ
ዋጋ በመመዝገብ በየወሩ ለመድኃኒት pharmacy accountant and coordinator in
ሂሳብ ሰራተኛ እና ፋርማሲ አገልግሎት every month by registering thereof;
አስተባበሪ ሪፖርት ማድረግ አለበት፡፡ 2. Medicines mentioned under sub-article (1) of
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ (፩) this article shall be kept and secured in
የተጠቀሱትን መድኃኒቶች በሙሉ
isolation from active medicines till the time
እስከሚወገዱበት ጊዜ ድረስ ከሌሎች
አገልግሎት ከሚሰጡ መድኃኒቶች of their complete disposal;
ተለይተው ለብቻቸው መቀመጥ
አለባቸው፣
3. የተቋሙ የመድኃኒት ሂሳብ ሰራተኛ 3. the pharmacy accountant shall report such
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) mentioned under sub-article(1) of this article
41
፳፰. ኦዲት ስለማስደረግ 28. Auditing
1. ማንኛውም የጤና ተቋም በጤና ተቋሙ 1. Any health institution shall audit the
ውስጥ የሚከናወነውን የመድኃኒት appropriateness of the overall health institution
አገልግሎት አሰጣጥ አግባብነት pharmaceutical services by the joint cooperation
በመድኃኒትና ህክምና ኮሚቴ እና ጥራት of the drug and therapeutic committee and quality
ኮሚቴ የጋራ ትብብር ቢያንስ በየስድስት compliance committee at least in every six months;
ወሩ ማስገምገም አለበት፡፡
2. ማንኛውም የጤና ተቋም በአጠቃላይ 2. Any health institution shall cause to audit and
በጤና ተቋሙ ውስጥ የሚከናወነውን
submit to higher official the overall health
የመድኃኒት ቅብብሎሽ ስርዓቱን እና
institution pharmaceutical supply chain system
አገልግሎት አሰጣጡን ቢያንስ በየሦስት
ወሩ በውስጥ ኦዲተር እና ቢያንስ and its operation at least in every three months
በዓመት አንድ ጊዜ በዋና ኦዲተር ወይም by internal auditor, and at least once in a year
ዋና ኦዲተር በሚሰይመው ኦዲተር by major auditor or auditor to be assigned by
ኦዲት በማስደረግ ለተቋሙ የበላይ ኃላፊ
auditor general;
ማቅረብ አለበት፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) 3. Without prejudice the prescription in sub-
የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ አስፈላጊ article /2/ of this article, the health institution
ሆኖ ሲገኝ ጤና ተቋሙ በማንኛውም may make an audit when found necessary.
ጊዜ ኦዲት ማስደረግ ይችላል፡፡
1. ማንኛውም የጤና ተቋም በእርዳታ 1. Any health institution shall ensure that of a
የሚያገኛቸው ወይም የሚገዛቸው medicine found through donation or bought
42
2. ማንኛውም የጤና ተቋም ለሚገዛቸው 2. Any health institution shall receive legal
መድኃኒቶች ህጋዊ የግዥ ደረሰኝ እና procurement receipt for medicine being
በእርዳታ ለሚያገኛቸው የሰጪው ደረሰኝ purchased, and donor’s receipt for donation
medicine or identity of medicine and loading
ወይም የመድኃኒቱን ማንነት እና
receipt that describe the sources;
ምንጩን የሚገልጹ የማስጫኛ ሰነዶችን
መቀበል አለበት፡፡
3. Any health institution shall not offer a
3. ማንኛውም የጤና ተቋም ያለ ህጋዊ
medicine to patient without any appropriate
መረጃ ምንም ዓይነት መድኃኒት ለታካሚ
legal information;
መስጠት የለበትም፡፡
4. ማንኛውም የጤና ተቋም ህጋዊ ካልሆኑ 4. Any health institution shall immediately
አለበት፡፡
7. Pharmaceutical supply chain transfer or
7. የአስፈጻሚ አካላት በዚህ ደንብ
የተደነገገውን የመድኃኒት አገልግሎት exchange among health institutions shall be in
አሰጣጥ ስርዓት በተገቢው ሁኔታ the system that ensure transparency and
መፈጸም ይኖርባቸዋል፡፡ accountable;
8. የጤና ተቋም ይህንን ደንብ ለማስፈጸም
8. Executive body shall appropriately implement
የሚረዱ ዝርዝር የአሰራር ሂደቶችን
በመቅረጽ ለሰራተኛው ግልጽ ማድረግ the medicine service delivery system declared
አለበት፡፡ under this regulation,
43
9. የጤና ተቋሙ እያንዳንዱ የስራ ክፍል 9. Health institution has to disclose to each
የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ሳይፈጽም department’s employee the consequency that
ሲቀር የሚያስከትለውን ተጠያቂነት comes from failing to do the given
ለሰራተኞች ማሳወቅ እና ተግባራዊነቱን responsibility and follow-up its
መከታተል አለበት፡፡ implementation;
፲. የመድኃኒት ቅብብሎሽና የመረጃ አያያዝ 10. Health institution has to make there shall be
Part Seven
ክፍል ሰባት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች Miscellaneous Provision
፴፩. የመተባበር ግዴታ 31. Duty to Cooperative
ማንኛውም ሰው ለዚህ ደንብ
Any person shall have the duty to cooperate on
ድንጋጌዎች አፈጻፀም የመተባበር ግዴታ
the performance of this regulation
አለበት፡፡
32. Penalty
፴፪. ቅጣት
በዚህ ደንብ የተጠቀሱትን ድንጋጌዎች Any person violate the provisions under this
regulation and directive to issue the regulation
ወይም ደንቡን ለማስፈፀም የሚወጣውን
shall be penalized based on criminal law
መመሪያ የተላለፈ ማንኛውም ሰው
በወንጀል ህግ መሰረት ይቀጣል፡፡
ይህን ደንብ የሚቃረን ማናቸውም ደንብ፣ No regulation, directive or customary practice in-
consistent with this regulation shall apply
መመሪያ ወይም ልማዳዊ አሠራር
ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡
44
፴፬. መመሪያ የማውጣት ስልጣን 34. Power to Issue directive
ቢሮው ይህን ደንብ ለማስፈፀም መመሪያ The bureau may issue directive to implement
this regulation
ሊያወጣ ይችላል፡፡
35. Effective date
፴፭. ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ ደንብ በደቡብ ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ This regulation shall come in to force as of the
data of its official publication on debub negarit
ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡ gazeta.
45
ydb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ ?ZïC KLL mNGST
db#B nU¶T Uz@È
DEBUB NEGARIT GAZETA OF THE
FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA
የሀገሪቱን የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግና In order to implement the country’s health policy
and to enable the provision of health services in
የክልሉም የቴና አገልግሎ አሰጣጥ ደረጃውን
the Southern Nations, Nationalities and Peoples
የጠበቀና በሥርዓት የሚመራ እንዲሆን
regional state have certain standards and systems,
ለማስቻል የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች
the regional council has proclaimed health service
ክልላዊ መንግሥት የጤና አገልግሎ አሰጣጥና
delivery and administration proclamation, No.
አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 84/1996 ማጽደቁ
84/2004. For the proper implementation of this
ይታወሳል፡፡ ይህንንም አዋጅ ለማስፈጸም ይረዳ
proclamation, it has become necessary to issue a
ዘንድ ደንብ ማዘጋጀት አስፈላጊ ስለሆነ የደቡብ regulation; and hence the Council of the SNNP
ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ Regional Government in accordance with powers
መንግስት ምክር ቤት በክልሉ መንግስት የጤና vested in it by Article 22 sub articles 1 of SNNP
አገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር Regional Government Health Service Delivery,
84/1996 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ፩ ሥር Administration and Management Proclamation
በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ No. 84/2004 has issued this regulation.
አውጥቷል፡፡
1. Short title
1. አጭር ርዕስ
This regulation may be cited as the “Heath
ይህ ደንብ "የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና
Service Delivery, Administration and
ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የጤና Management Regulation of the Southern
አገልግሎ አሰጣጥና አስተዳደር ደንብ ቁጥር Nations, Nationalities and Peoples regional
46/1998" ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ Government No 46/2005
2. ትርጉም
የቃሉ አገባብ ሌላ የሚያሰጠው 2. Definitions
ትርጉም
Unless the context requires otherwise in this
ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡
regulation
1. "ገቢ" ማለት ሆስፒታሎችና ጤና
a. “Revenue” means all revenue accruing to
ጣቢያዎች ከሚሰጧቸው ማናቸውም
health institutions from health services they
የጤና አገልግሎቶች፣ የመድኃኒት
render sales of drug, other goods and
ሽያጭና ከሌሎች አገልግሎቶችና ዕቃዎች
services and donations they obtain in cash or
ሽያጭ የሚገኝ ገቢ እንዲሁም በዓይነትም in kind;
ሆነ ነጥሬ ገንዘብ የሚገኝ እርዳታ ነው፣
b. “Third Party” means public or private
2. "ሶስተኛ ወገን" ማለት የአገልግሎት organization which finances expenses of
ተጠቃዎችን ወጪ /በኢንሹራንስም ሆነ beneficiaries of diseases, monitoring of
በሌላ መልክ/ የሚሸፍን የግል ወይም contagious diseases, physical, laboratory, x-
የመንግሥት አካል ማለት ነው፡፡ ray and other schemes;
ከመንግሥት ከሚመደ ብላቸው በጀት 1. Enable health facilities to use their retained
በተጨማሪ እንዲጠ ቀሙ በማድረግ income, in addition to the block budget
የተቋማቱን የጤና አገልግሎ ጥራት apportioned by the government, for better
ሊሆን ይችላል፡፡
ለ/ ከጤና፣ ከተለያዩ ዲያግኖስቲክ ከመኝታና 2. Fees collected from health care and
ከሕክምና አገልግ ሎቶች ክፍያ፣ diagnostic services and other services
related with medical treatment;
ሐ/ ከመድኃኒትና አላቂ የሕክምና መገልገያ
3. Sale of drugs and medical supplies,
ዕቃዎች ሽያጭ፣
መ/ ከነፃ ሕክምናና ከጤና ኢንሹ ራንስ ጋር 4. Revenue collected from third parties in
በተያያዘ ከሶስተኛ ወገን ከሚበሰብ ገቢ፣ connection with waiver and health
insurance schemes.
5. የገቢ አሰባሰብ
1. የሆስፒታሎች/ጤና ጣቢያዎች ገቢ 5. Collection of Revenue\
የሚሰበሰበው በክልሉ መንግሥት 1. Collection of revenue of hospitals/health
የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅና ደንብ centers hall only be made in accordance with
ስለገቢ አሰባሰብ የተደነገገውን በመከተል the rules laid down in the Regional
ተቋሙስም በተከፈተ መደቡ "A" በሆነ only put in a Bank account A Kept under
the name of the facility.
ልዩ የባንክ አካውንት ውስጥ ይቀመጣል፡፡
ለማሳደግ ፣
b. To improve the supply of drugs, medical
ለ/ የመድኃኒትና የሌሎች የሕክምና equipment and supplies;
መገልገያ መሣሪያዎችንና ቁሳቁሶችን
አቅርቦት ለማሻሻል፣
ሐ/ በጤና ተቋሙ የሚሰጡ አገልግ ሎቶችን c. To improve procurement and carry out
construction works to improve the health
ለማስፋፋት የሚረዱ ግዥዎችንና
care services of the hospital;
ግንባታዎችን ለመፈፀም፣
d. To develop health care information
መ/ የጤና ድርጅቱን መረጃ አያያዝ ስርዓት
system and manuals and to improve
እና ሌሎች የአሠራር ሥርዓቶችን
procedures;
ለማሻሻል፣
e. To conduct on job raining programs and
ሠ/ የጤና ድርጅቱን ሠራተኞች ብቃትና
other similar health related researches so
ውጤታማነት ለማሳደግ የስራ ላይ
as to improve the efficiency and
ስልጠና ለመስጠትና ጤና ነክ productivity of employees in the
ምርምሮችን ለማካሄድ፣ facilities;
በጀት በቀጣዩ የበጀት ዓመት ከሚፈቀደው hospitals/health centers in the budget year
9. ሪፖርት አቀራረብ
9. Reporting
1. ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች መሪ
1. Hospitals/health centers shall prepare and
ዕቅድና ዓመታዊ መረጃ ዝርዝር ዕቅድ
submit indicative and annual detailed
ለቦርድ/ለጤና ጣቢያ ሥራ አመራር፣ ለጤና activity and financial plans to the
ቢሮ እና ለፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ board/health centers management, health
ያቀርባሉ፡፡ bureau and Finance and Economic
Development Coordination Bureau.
2. ሆስፒታሎች/ጤና ጣቢያዎች የሥራ
2. Hospital/health centers shall submit
ክንውንን፣ የገንዘብ አሰባሰብን፣
quarterly activity and revenue collection
አጠቃቀምንና አያያዝን ያጋጠሙ and utilization report to the board/health
ችግሮችንና የተወሰዱ እርምጃዎችን centre management every quarter together
የሚያሳይ ሪፖርት ለቦርዱ/ለጤና ጣቢያው with a report that states problems
ሥራ አመራር በየ3 (ሶስት) ወሩ ያቀርባሉ፡፡ encountered and measures taken.
2. የጎዳና ተዳዳሪዎች ሆነው ከቀበሌ/ወረዳ/ 2. Street children who can provide evidence
ሐ/ የተሰጠው የነጻ ህክምና ማስረጃ 5.1.3. Waivers shall not give the waiver
ለሌላ አካል አሳልፎ አለመስጠት certificate to the other bodies.
2. የቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት የሥራ
ድርሻ 5.2.Responsibility of the kebele
5. የሆስፒታሉን የሥራ አካሄድ የሚወስኑ 5. Issue directives that shall guide the
መመሪያዎችን ያወጣል፣ proper carrying out of the activities of the
hospital.
6. የሆስፒታሉን የሥራ አስኪያጅ
6. Employ the general manager and deposes
ይቀጥራል የስራ ድክመት ካሳየ
when and if he is inefficient, and approve
ከሀላፊነት ያነሳል፣ የመምሪያና
the employment and promotion of heads
አገልግሎት ኃላፊዎች ቅጥርና ዕድገት
of departments of the hospital;
ያጸድቃል፣
የበጀት ረቂቅ መርምሮ ለቢሮው ኃላፊ examine the budget proposal and refer
the same to the bureau head for approval;
ያቀርባል፣
10. Follow up the budget utilization of the
፲. የሆስፒታሉን የበጀት አጠቃቀም
hospital.
ይከታተላል፡፡
11. Ensure that all activities of the hospital
፲፩. የሆስፒታሉ የሥራ እንቅስቃሴዎች
are carried out with transparency and
ግልጽነት እና ተጠያቂነት ባለበት
ሁኔታ እንዲ ከናወኑ ያደርጋል፣ accountability;
፲፫. በሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ 13. Examine and decide upon all matters that
የሚቀርቡለትን ሌሎች ጉዳዮች are presented to it by the General
መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፣ Manager.
፲፬. የአገሪቱ የጤና ፖሊሲና ጤና ነክ 14. Ensure that the country’s health policy
መመሪያዎች በሆስፒታሉ በአግባቡ and directives related to health matters
መተዳደሪያ ደንብ ሊያወጣ ይችላል፡፡ 8. Rights and duties of Members the Board.
8. የቦርድ አባላት መብትና ግዴታ 1. Each member has the duty to strictly be
1. እያንዳንዱ የቦርድ አባል በመደበኛውና present at each ordinary and extra-
በአስቸኳይ ስብሰባ ላይ ሰዓቱን ordinary meeting and shall observe the
እንዲቀጥሉ ይደረጋል
10. Accountability
፲. ተጠሪነት
The Board, according to the level of the
ቦርዱ ተጠሪነቱ እንደ ሆስፒታሉ ደረጃ
hospital, shall be accountable to the Bureau.
ለጤና ቢሮው ይሆናል፡፡
4. ሆስፒታሉ ተጨማሪ የሰው ኃይል 4. Create the condition that enables the
ቁሳቁስና ገንዘብ የሚያገኝበትን ሁኔታ hospital obtain the necessary manpower,
ያመቻቻል፣ material and finance.
ማድረግ፣
5. በውል ለሌላ ወገን የሚሰጡትን 5. Quantify,price and measure the services to
አገልግሎቶች በዋጋ፣ በመጠንና በጥራት be outsourced;
መመዘን በሚያስችል ሁኔታ በዝርዝር
ማስቀመጥ፣
አገልግሎት፣ services
Part Five
ክፍል አምስት
Private Wings in Public Hospitals
የግል ሕክምና መስጫ ዩኒቶች
16. Establishment of Private Wings:
፲፮. የግል ሕክምና መስጫ ዪኒቶች ስለ ማቋቋም
1. የግል የሕክምና መስጫ ዩኒቶች ለቋቋም 1.Conditions to be fulfilled to establish
በቅድሚያ ሊሟሉ ስለሚገባቸው private wings.
ሁኔታዎች፣
1. The hospital shall establish private wings
1. አንድ ሆስፒታል የግል የሕክምና
in services that it has strength and are of
መስጫ ዩኒት ሊያቋቁም የሚችለው
greater public demand.
በአንጻራዊ ሲታይ በኅብረተሰቡ ዘንድ
ተቀባይነት ያለው አገልግሎ
የሚሰጥባቸው የሕክምና ዘርፎች
ሲኖሩት ነው፣
መስጫ ጊዜና ክፍሎ በማጣበብና the space and time provided for the
ይሆናል
2. የካፒታል 2.Capital
ተኝተው ለሚታከሙ የግል የሕክምና The hospital may mobilize funds for in
መግለጽ አለባቸው፡፡
7. Working Hours
7. የሥራ ሰዓት The working hours of the private wing,
የግል የሕክምና መስጫ ዩኒት የስራ depending up on the objective conditions of
ሰዓት እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ zones/woredas,will be as follows:
1. ለግል የሕክምና መስጫ ዩኒቶች የባለሙያ always be arranged in such a way that the
የሚያወጣውን መመሪያ ተከትሎ ቦርዱ board between the hospital and staff who
devoted their part-time in the private wing.
በሚያፀድቀው የድልድል ቀመር መሠረት
The distribution guideline shall incorporate
ለሆስፒታሉ እና በትርፍ ጊዜያቸው
a scheme of payment that increases
በሥራው ተሳታፊ ለሆኑ ሠራተኞች
proportional to the rate of profitability of the
የሚከፋፈል ይሆናል፡፡ የድልድል መመሪያ
Private Wing.
በሚዘጋጅበት ወቅት የግል ሕክምና
መስጫ ዩኒቱን ትርፋማነት መሠረት
አድርጎ ደረጃ በደረጃ እያደገ የሚሄድ
የክፍያ አሰራር ስልት መዘርጋት
ይኖርበታል፡፡ 10. Use of surplus
፲. የተራፊ ሒሣብ አጠቃቀም 1. The surplus generated from the activities
1. ሆስፒታሉ ከግል የሕክምና መስጫ of private wing shall principally be used to
ሂሣብ በዋነኝነት የግል እና መደበኛ both the private and general wards;
፲፩. የግል የሕክምና መስጫ ዩኒት አስተዳደር supported by the staff of the hospital and
shall have a coordinator who will report
1. የግል ሕክምና መስጫ ዩኒት አስተዳደር
to the Hospital Management
በሆስፒታሉ የአስተዳደር ሠራተኞ
የሚታገዝ ሆኖ፣ ተጠሪነቱ ለሆስፒታሉ 2. The Hospital Management shall oversee
ስራ አመራር የሆነ አስተባባሪ ይኖረዋል፣ the activities of the Private wing
1. የሆስፒታሉ የግል ሕክምና መስጫ ዩኒት rendered by the Private wing and submit
its proposal to the Board for its approval;
የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ዓይነት
በማጥናት ለቦርዱ የውሳኔ ሃሳብ
2. Monitor the day to day functioning of the
ያቀርባል፣ private wing;
ያረጋግጣል፣
4. የግል የሕክምና መስጫ ዩኒቱን የሥራ 5. Ensure that the financial and medical
Hailemariam Desalegn
ህዳር 22 ቀን 1998 ዓ.ም Chief of SNNPR Regional Government
Awassa
ኃይለማሪያም ደሣለኝ
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች
ክልል መንግሥት
ርዕሰ መስተዳድር
ydb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ ?ZïC KLላዊ mNGሥT
db#B nU¶T Uz@È
DEBUB NEGARIT GAZETA
OF THE SOUTHERN NATIONS, NATIONALITIES AND
PEOPLES REGIONAL STATE
bdb#B B/@éC½B/@rsïCÂ ?ZïC
17¾ ›mT q$_R 7 KLል Mክር b@T -ÆqEnT ywÈ ደንብ
ሀêú ከጥር 5 ቀን 2003
ማውጫ
ደንብ ቁጥር 87/2003
በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የይርጋዓለም ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ
ለማቋቋም የወጣ ደንብ
መግቢያ
በሀገሪቱም ሆነ በክልሉ ያሉትን የመለስተኛና የመካከለኛ ደረጃ ሐኪሞች የከፍተኛ ደረጃ
ስፔሻሊቱ ሕክምናን ስልጠና የሚያገኙበትን ዕድል በማመቻቸት በአጭር ጊዜ ውስጥ
የማፈለገውን የከፍተኛ ሕክምና ባለሙያዎችን በብዛትና በጥራት ማምረት ሀገሪቱ ካለችበት
ነባራዊ ሁኔታ አኳያ አንገብጋቢ እየሆነ በመምጣቱ፤
በዓይነታቸው ከባድና ከፍተኛ በሚባሉ በሽታዎች የተጋለጡ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በሀገሪቱ
የጤና ሽፋን ተጠቃሚ ለማድረግ በዘርፉ በልዩ ሁኔታ ምርምር የሚደረግና ሥልጠና የሚሰጥ
ተቋም መመስረት አስፈላጊነት ላይ በመታመኑ፤
የክልሉን የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳና በጤናው ዘርፍ የተፈለገውን ለውጥ
ለማስመዝገብ የሚያስችል የተለየ የሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ማቋቋም በማስፈለጉ፣
1
በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ክልል መንግሥት የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር
ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 133/2003 አንቀጽ 44/3/ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት
የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡
ክፍል አንድ
ጠቅላላ
1. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ “የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰበቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የይርጋዓለም
ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 87 /2003” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ትርጓሜ
በዚህ ደንብ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በቀር፡-
1. “ክልል” ማለት የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰበቦችና ሕዝቦች ክልል ነው፡፡
2. “ቢሮና ኃላፊ” ማለት እንደቅደም ተከተላቸው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰበቦችና
ሕዝቦች ክልል ጤና ቢሮ እና የጤና ቢሮ ኃላፊ ነው፡፡
3. “ኮሌጅ” ማለት የይርጋዓለም ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ነው፡፡
4. “ሚኒስቴር” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፖብሊክ ትምህርት
ሚኒስቴር ነው፡፡
5. “የአካዳሚክ ማህበረሰብ” ማለት በኮሌጁ ውስጥ በመደበኛነት ወይም በጊዜያዊነት
በመማር፣ በማስተማር እና በምርምር ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሰዎችን
ያቀፈ ነው፡፡
6. “የአካዳሚክ ሠራተኛ” ማለት በኮሌጁ በማስተማር ወይም የምርምር ጉዳዮችን
የሚመራና ኃላፊነት የተሰጠው አካል ነው፡፡
7. “የአካዳሚክ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኛ” ማለት የአስተዳደር፣ የቢዝነስ አመራር፣
የፋይናንስና የሂሣብ ሥራ፣ የምግብ አገልግሎት ማቅረብ፣ የጥገና፣ የጥበቃና
ደህንነት ወይም የመሳሰሉትን ተግባራት የሚያከናውን የኮሌጁ ሠራተኛ ነው፡፡
8. “ቦርድ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ 14 መሠረት የሚሰየም የኮሌጁ አመራርና ቦርድ
ነው፡፡
2
9. “አካዳሚክ ኮሚሽን” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ 23 መሠረት የተቋቋመው ኮሚሽን
ነው፡፡
10.“ሰው” ማለት የተፈጥሮ ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፡፡
3. መቋቋም
የይርጋዓለም ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ከዚህ በኋላ “ኮሌጅ” እየተባለ የሚጠራ የከፍተኛ
ሕክምና ስልጠና የሚሰጥ ሆኖ ሕጋዊ ሰውነት ያለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም
በመሆን በዚህ ደንብ ተቋቋሟል፡፡
4. ተጠሪነት
ኮሌጁ አግባብ ባላቸው የሀገሪቱ ሕግ መሠረት ለሚኒስቴሩ ያለው ተጠሪነት እንደተጠበቀ
ሆኖ በክልል ደረጃ ተጠሪነቱ ለቢሮው ነው፡፡
5. የኮሌጁ አቋም
1. ኮሌጁ
ሀ/ የአመራር ቦርድ ፣ አካዳሚክ ኮሚሽን፣ ዲንና ምክትል ዲኖች፣
ለ/ የአካዳሚክ ሠራተኞች
ሐ/ የአስተዳደርና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች እና
2. ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ፋካልቲዎችና ሌሎች የሥራ ክፍሎች ይኖሩታል፡፡
6. ዓላማ
ኮሌጁ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡-
1. የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን የከፍተኛ ሕክምና ባለሙያዎች እጥረት ለመፍታት
በሚያስችል መልኩ በእውቀት፣ ክህሎትና በመልካም ሥነ ምግባር የታነፁ የከፍተኛ
ሕክምና ባለሙያዎች በማሰልጠን በቂ የሰው ኃይል ማፍራት፣
2. ተገቢውን የመማር ማስተማር ሥርዓት በመዘርጋት ትኩረት በሚሹ የጤና ጉዳዮች
ላይ ችግር ፈቺና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ምርምሮችን ማካሄድና ማስረጽ፤
3. በአገሪቱ የጤና ፍላጐት ላይ የተመሠረተና ትኩረቱ በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር
ላይ የሆነ ምርምርን ማራመድና ማጐልበት፤
4. አገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን የማያስችሏትን፣ ጥራቱን የጠበቀና
ሀገራዊ ፋይዳ ያለውን የጤና አካዳሚክ ማህበረሰብን በመፍጠር በአርአያነት ተጠቃሽ
የሆነ ተግባራትን መፈፀም፤፡
3
7. ስለኮሌጁ አካዳሚያዊ ነፃነት
1. ኮሌጁ ዓላማውን ለማሳካት በሀገሪቱ ባለው ሕግ መሠረት አካዳሚያዊ ነፃነት
ይኖረዋል፣
2. ኮሌጁ በዚህ ደንብና አግባብነት ባላቸው የአገሪቱ ሕጐች እንዲሁም በዓለም አቀፍ
መልካም ልምድ መሠረት የአካዳሚያዊ ነፃነት አተገባበር በሥርዓት እንዲመራ
ማድረግ ይኖርበታል፣
3. ኮሌጁ በዚህ ደንብና አግባብነት ባላቸው የአገሪቱ ሕጐች እንዲሁም በዓለም አቀፍ
መልካም ልምድ መሠረት የአካዳሚያዊ ነፃነት አተገባበር በሥርዓት እንዲመራ
ማድረግ ይኖርበታል፣
8. የትምህርት መርሃ-ግብር
1. የኮሌጁ የትምህርት መርሃ-ግብር
ሀ/ በመደበኛ
ለ/ በተከታታይ ወይም
2. በብቃት ማሻሻያ አስፈላጊነት በሚኖራቸው መስኮች እውቀትና ክህሎትን
ለማስተላለፍ የአጭር ጊዜ ስልጠናዎችን ሊሰጥ ይችላል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡
9. የሥርዓተ ትምህርት ይዘት
1. ኮሌጁ የሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ፣ ትግበራና የምዘና ዓላማ ተማሪው ተገቢው
ሳይንሳዊ እውቀት፣ በነፃ የማሰብን የሚያበረታታ፣ ተግባር ተኮር የሆነ ነባራዊ
ሁኔታን ያገናዘበና መልካም ሙያዊ ስብእናን እንዲጨብጥ በማድረግ ብቁ የጤና
ባለሙያን ማዘጋጀት ይሆናል::
2. ኮሌጁ የትምህርት ክፍሎቹ የሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ ሚኒስቴሩ ባስቀመጠው
በተገቢ የምሩቃን ብቃት መመዘኛዎች እንዲመራ ማድረግ አለበት::
10. የአካዳሚክ ዘመንና የበጀት ዓመት
1. ኮሌጁ የሚያሰለጥነው የሙያ መስክ የአካዳሚክ ዘመን በሚኒስቴሩ በተቀመጠው
የአካዳሚክ ዘመን ይሆናል፡፡
2. የኮሌጁ የበጀት ዓመት የመንግሥት በጀት ዓመት ይሆናል፡፡
11. የኮሌጅ ደረጃ
1. የኮሌጁ ደረጃ አግባብ ባለው ሕግ መሠረት በሚኒስቴሩ ይወሰናል፡፡
4
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሌጁ ከዲግሪ በላይ
የሆነ ማዕረግ የሚያስመርቅ ነው፡፡
12. የኮሌጁ ተግባርና ኃላፊነት
ኮሌጁ የሚከተሉት ተግባራትና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡
1. ሚኒስቴሩ በሚያወጣው የምልመላ መስፈርትና መመሪያ መሠረት ተማሪዎችን
መቀበል፤
2. የክልሉን የከፍተኛ ሕክምና ባለሙያን ፍላጐት መሠረት በማድረግ ብቃት ያላቸውን
የሰለጠኑ ሐኪሞች በብዛትና በጥራት የማፍራት፤
3. አገር አቀፍ መለኪያዎችን መሠረት ያደረገ የትምህርትና ስልጠና መርሃ ግብር
በመቀየስ ቦርድ ሲያፀድቅለት በሥራ ላይ ማዋል፤
4. እንደአግባብነቱ በትምህርቱ ኘሮግራሞች በመሰልጠንና ተገቢውን የተማሪዎች ምዘና
በማድረግ ተፈላጊውን ውጤት ላስመዘገቡ ሰልጣኞች ተገቢውን የትምህርት ማስረጃ
የዲግሪ፣ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪ ማስረጃ የመስጠት፤
5. እንደአስፈላጊነቱ የተለያዩ የስልጠና፣ ጥናትና ምርምር ክፍሎችን ማቋቋምና
ማጠናከር፤
6. የትምህርትና ስልጠና መረጃ መሣሪያዎችንና መፃሕፍትን በማሰባሰብ የቤተሙከራና
ቤተመፃሕፍትን በማዘጋጀትና በማደራጀት የመማር ማስተማሩን ሂደት ምቹ
የማድረግ፤
7. ከሀገር ውጭ ከሚገኙ መሰል ዩኒቨርሲቲዎችና የሕክምና ተቋማት ጋር ግንኙነት
የመፍጠርና የሕክምና ቴክኖሎጂዎችንና መሣሪያዎችን በግዢም ሆነ በእርዳታ
እንዲገኝ በማድረግ የኮሌጁን አቅም ማሳደግ፤
8. ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት ለሕብረተሰቡ የመስጠት፣
9. ልዩ የትኩረት አቅጣጫ በሚፈልጉ የጤና ዘርፎች ቢሮው ወይም በመንግሥት
ሲፈለግ በልዩ ኘሮግራም የአጭርና የመካከለኛ ደረጃ ስልጠናዎችን በማዘጋጀትና
በመተግበር የሰርተፊኬትና ዲኘሎማ ማስረጃ የመስጠት፣
10.የኮሌጁ ሠራተኞችና ተማሪዎች ስለሚያገኙት የሕክምና አገልግሎት ቦርዱ
በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የመፈፀም፤
11.ጤና ነክ የሆኑ ትምህርታዊ መረጃዎችን በኤሌክትሮኒክስና በሕትመት ሚዲያዎች
ወይንም በዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም የማሰራጨት፣
5
12.የተማሪዎች ትምህርት ወጪ ክፍያ፣ የአገልግሎት ክፍያና ሌሎች ከተለያዩ
ምንጮች የሚያገኛቸውን ገቢዎች በአግባቡ የመሰብሰብ በቦርድ ሲፈቀድም በሥራ
ላይ የማዋል፡፡
13.ለኮሌጁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የአካዳሚክ ማዕረግና ሰርተፊኬቶችን
የመስጠት፣
14.ሌሎች ዓላማውን ለማሳካት የሚያስችሉ ተዛማጅ ተግባራትን የማከናወን ኃላፊነት
ይኖርበታል፡፡
ክፍል ሁለት
ስለኮሌጁ አመራር አካላት ተግባርና ኃላፊት
13. ኮሌጁ የሚከተሉት የአመራረ አካላት ይኖሩታል፡-
1. የአመራር ቦርድ፣
2. ዲንና ምክትል ዲኖች፣
3. የአካዳሚክ ኮሚሽን፡፡
ምዕራፍ አንድ
ስለቦርድ
14. ስለኮሌጁ የአመራር ቦርድና ምልዓተ-ጉባዔ
1. የአመራር ቦርድ ሰብሣቢውን ጨምሮ 7 አባላት ይኖሩታል፡፡ ቦርዱ የሴቶች ተሣትፎ
ያለበት መሆን ይኖርበታል፡፡
2. ከቦርዱ ሰብሣቢ በተጨማሪ ሦስት ድምፅ መስጠት የሚችሉ አባላት በቢሮው እጩ
አቅራቢነት በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ይሰየማሉ፡፡
3. የኮሌጁ ዲን ከአካዳሚክ ኮሚሽኑና ከኮሌጁ የአስተዳደር አካላት ጋር በመመካከር
ሦስት የቦርድ አባል እጩዎችን በማቅረብ በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት
ይሰየማሉ፡፡
4. የኮሌጁ ዲን ድምጽ የማይሰጥ የቦርድ አባልና ፀሐፊ ይሆናል፡፡
5. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /2/ እና /3/ መሠረት የሚሰየሙ የቦርድ አባላት
በኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያሉ ወይም ያገለገሉና በተለይ በማስተማር ወይም
በምርምርና በግል ስብዕናቸው፣ እውቀታቸው፣ ልምዳቸውና አትኩሮታቸው የታወቁ
ግለሰቦች በአጠቃላይ ለኮሌጁ ዓላማና ተልዕኮ መሳካት አስተዋጽኦ ለማበርከት
የሚችሉ መሆን ይገባቸዋል፡፡
6
6. በርዱ በራሱ ውሣኔ ማንኛውንም ሰው በአስረጂነት በስብሰባዎች ሊያሳትፍ ይችላል፡፡
7. አምስት ድምፅ መስጠት የሚችሉ የቦርዱ አባላት ሲገኙ መልዓተ ጉባዔ ይሆናል፡፡
8. የቦርዱ ሰብሣቢ ጊዜ በተቆረጠለት ስብሰባ የሚመራ ሰብሣቢ ከመሀከላቸው
በመምረጥ የስብሰባውን አጀንዳ ይፈጽማሉ፡፡
9. ቦርዱ የስብሰባው አካሄድ የሚመለከት የአሠራር ሥነ-ሥርዓት ሊያወጣ ይችላል፤
10.ቦርድ በጉዳዮች ላይ ውሣኔ የሚያሳልፈው በአብላጫ ድምፅ ይሆናል፡፡ እኩል ድምፅ
በተሰጠ ጊዜ የቦርዱ ሰብሣቢ የሚደግፈው አቋም በአብላጫ ድምፅነት ይፈረጃል፡፡
15.ስለቦርዱ መደበኛ ስብሰባዎች
1. የቦርዱ መደበኛ ስብሰባዎች በዓመት ከሦስት እስከ አራት ጊዜ ይሆናል፡፡
2. የመደበኛ የስብሰባው ጊዜ ቦርዱ ኃላፊነቱን ለመወጣት በሚያስችለው መልኩ
በተለይም የእቅድና የበጀት ዝግጅቶች እንዲሁም አፈፃፀም ላይ አስተዋጽኦ ለማድረግ
እንዲችል በሚያደርገው ወቅቶች እንዲሆን ያደረጋል፡፡
3. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /2/ እንደተጠበቀ ሆኖ ቦርድ በሰብሣቢው ጥሪ ወይም
ድምፅ የመስጠት መብት ካላቸው አባላቱ አንድ ሦስተኛው (1/3) በሚጠይቁበት ጊዜ
አስቸኳይ ስብሰባ ማድረግ ይችላል፡፡
4. የቦርዱ ሰብሣቢ ሁሉም የቦርድ ስብሰባዎች በቂ ዝግጅት የተደረገባቸው መሆኑን፣
ሠነዶቹ በጥንቃቄ መጠበቃቸውንና መያዛቸውን፣ ቦርድ በሚያዘው መሠረት
ውሣኔዎቹ በትክክል ለሚመለከታቸው መተላለፋቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
16. የቦርዱ አባልነት መቋረጥ
የቦርድ አባልነት በሚከተሉት ምክንያቶች ሊቋረጥ ይችላል፡፡
1. ቢሮው በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የአገልግሎት ዘመን ሲያበቃ፤
2. በፈቃደኝነት ከአባልነት በመልቀቅ፤
3. በሞት፣ በሕመም ወይም በከባድ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘት፣
4. በከባድ ጥፋት፣ ችሎት ማጣት ወይም ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ከባድ የሆነ
ድክመት በማሳየት ወይም ባለመቻል/
5. ቢሮው ቦርዱን ሙሉ ለሙሉ ለመቀየር ወይም በከፊል ለመለወጥ ውሣኔ ላይ
ሲደርስ፡፡
7
17. ስለቦርዱ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ
1. ቦርዱ የተሻለ አመራር ለመስጠት የሚያስችለውን ግንዛቤ ለማግኘት የራሱን የሥራ
አፈፃፀም ግምገማ ማድረግ ይኖርበታል፣
2. የቦርዱ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ድምጽ የመስጠት መብት ባላቸው አባላትና የኮሌጁ
ዲን በተገኙበት በዝግ ስብሰባ ያካሄዳል፡፡
3. የቦርዱ ሰብሣቢ የግምገማውን ውጤቶች በየወቅቱ ለመስተዳድር ምክር ቤትና
ለቢሮው ሪፖርት ያደርጋል፡፡ የቦርድ ሰብሣቢው ከቢሮው ጋር መደበኛ የጋራ
መድረክም በዓመት ሁለት ጊዜ ይኖራል፡፡
4. ቦርዱ ግምገማውን መቼና እንዴት እንደሚያካሄድ ይወስናል፤ ሆኖም በዓመት
ቢያንስ አንድ የክትትል ግምገማና አንድ የማጠቃለያ ግምገማ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
18. የኮሌጁ የአመራር ቦርድ ኃላፊነት
1. የኮሌጁ ቦርድ የተቋሙ የበላይ አመራር ሆኖ የሚከተለው ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡
8
ሰ/ የኮሌጁን የስትራቴጂክ እቅድ፣ ዓመታዊ እቅድና በጀት ማቅረብና ሲፀድቁም
ተፈፃሚነታቸውን መከታተል፣ የተቋሙን የክንውን ሪፖርትና የፋይናንስ
መግለጫን ማቅረብና ማፀደቅ፤
ሸ/ የኮሌጁ ዋና ዋና እና ጥቃቅን ገቢዎቹን ትክክለኛ የሂሣብ መዝገብ መያዙንና
ወጪዎቹ በበጀት መሠረት መሆናቸውን መከታተልና ማረጋገጥ፣
ቀ/ የኮሌጁ ሌሎች የአመራር አካላት ከባድ የሕግ መጣስ ተግባር በሚፈጽሙበት
ጊዜ ወይም ከባድ የሆነ የገንዘብ ብክነት ስለመከሰቱ ጥርጣሬ ካለ ወይም
በእርግጥ ተከስቶ ከሆነ በራሱ ስልጣን ክልል ተገቢውን የመፍትሔ እርምጃ
መውሰድና ወዲያውኑ ለቢሮው ሪፖርት ማቅረብ፤
በ/ የክልሉ መንግሥት የሠራተኞች አዋጅና ደንቦች መሠረታዊ መርሆች ላይ
በመመስረት የአስተዳደርና የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችን ቅጥር፣ እድገት፣
ዲስፒሊን፣ ደመወዝ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን የሚመለከት ፖሊሲን
እንደአስፈላጊነቱ እንዲዘጋጅ ማድረግና ማጽደቅ፤
ተ/ ኮሌጁን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መረጃ የመጠየቅና የማግኘት እና ለቢሮው
ወይም ለሚኒስቴሩ ሪፖርት ማድረግ፣
ቸ/ በኮሌጁ ውሣኔዎች ላይ ቅሬታ ሲቀርብ መመርመርና የመጨረሻ ውሣኔ
መስጠት፤
ኃ/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ተራ ፊደል /ቸ/ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሌጁ
ቅሬታዎችን በተፋጠነ መንገድ ተቀብሎ የሚፈታበት የተሟላ ተቋማዊ ሥርዓት
ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፣
ነ/ የኮሌጁን አካዳሚክ ክፍሎች፣ የአስተዳደር አካላቱን የሥራ አፈፃፀም በዲኑ
ሪፖርት መሠረት ከእቅድ አኳያ መገምገም፤
አ/ የአካዳሚክ ኮሚሽን ውሣኔዎችና የሚያወጣቸው የአካዳሚክ ሕጐች
መፈፀማቸውን መከታተል፤
ከ/ ከኮሌጁ ዲን ወይም በአካዳሚክ ኮሚሽኑ የተላለፈ ውሣኔዎች የተቋሙን ተልዕኮ
የሚጐዱ ወይም ይህንን ደንብ ወይም ሌሎች የሀገሪቱን ሕጐች የሚቃረኑ ሆነው
ሲገኙ ውሣኔዎቹን መሻር፣
ኸ/ የራሱን የአሠራር ሥነ ሥርዓትና የውስጥ አስተዳደር ደንብና አባላቱን
የሚመለከት የዲሲኘሊን ደንብን ማውጣት፤
9
ወ/ የኘሮፌሰርነት የማዕረግ እድገትን በአካዳሚክ ኮሚሽን ሲቀርብለት ማፀደቅ፣
ዐ/ በዲኑ በሚቀርብ ምክር ላይ ተመስርቶ ኮሌጁ ለትምህርት የሚያስከፍላቸውን
የተለያዩ ክፍያዎች ዓይነትና መጠን መወሰን እንዲሁም የክልሉ መስተዳድር
ምክር ቤት በወሰነው መሠረት የተቋሙን ገቢ ግምት ውስጥ በማስገባት
የተለያዩ ተካፋይ አበሎችን፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያዎችንና የመሳሰሉትን መወሰን፣
2. የቦርዱ ተጠሪነት ለቢሮው ነው፡፡
ምዕራፍ አራት
10
20. የኮሌጁ ዲን ኃላፊነትና ተግባር
1. የቦርዱ ኃላፊነት እንደጠበቀ ሆኖ የኮሌጁ ዲን ዋና ሥራ አስፈፃሚ በመሆን
የሚከተሉት ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡
ሀ/ የኮሌጁን ዓላማና ተልዕኮ ለማሣካት ይችል ዘንድ ይመራል፣ ያስተዳድራል፤
ለ/ የኮሌጅ አካላትና ማህበረሰብ የከፍተኛ ትምሀርት ዓላማዎችንና የኮሌጁን መሪ
እሴቶች ማክበራቸውን ያረጋግጣል፤
ሐ/ ኮሌጁ ክልሉ በጤናው ዘርፍ በሚፈልገው መጠንና ዓይነት ከፍተኛ ጥራትን
የተከተለ ብቃት ያላቸውን የጤና ምሩቃንን ማፍራቱን ያረጋግጣል፤
መ/ መማር፣ ማስተማርንና ምርምርን የሚያበረታታ ምቹ የኮሌጁ ማህበረሰብን
ይፈጠራል፣ በቀጣይነት ይገነባል፤
ሠ/ የኮሌጁ የምርመራና የማማከር ተግባራት ሁሉ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ሀገራዊና
ክልላዊ ጉዳዮች ላይ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፤
ረ/ ኮሌጁ ዓላማውን ለማሳካት ከሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ
አካላት፣ አግባብነት ካላቸው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች
ጋር በዘላቂነት ግንኙነት እንዲፈጠር ያደርጋል፤
ሰ/ ኮሌጁ በሰው ኃይሉ፣ በአደረጃጀቱና አሠራሩ ለተቋሙ ተልዕኮ የሚመጥን ብቃት
ያለው የውስጥ አመራርና አስተዳደር ሥርዓት እንዲኖረው ያደርጋል፤
ሸ/ የአካዳሚክ ኃላፊዎችና የአካዳሚክ ኮሚሽን አባላትን የአሰያየም ሥርዓትን
በማዘጋጀትና በቦርድ በማፀደቅ በተግባር ላይ ያውላል፤
ቀ/ በትምህርትና ምርምር አግባብነትና ጥራት፣ በተቋማዊ ነፃነትና ተጠያቂነት፣
በአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነትና በወጪ ቆጣቢነት መርሆች ላይ
በመመስረት የትምህርት ክፍሎች አደረጃጀትን ለአካዳሚክ ኮሚሽኑና ለቦርዱ
አቅርቦ ያስወስናል፤ ሲፈቀድም በተግባር ላይ ያውላል፤
በ/ የቅጥር ኃላፊነት ቦታዎች በውድድር የሚያዙ መሆኑንና ከኃላፊነት መነሳትም
በሥራ አፈፃፀም ግምገማ፣ በዲሲኘሊን ጉዳይ እና በአገልግሎት ዘመን ማብቃት
ብቻ ላይ ተመስርቶ መሆኑን ያረጋግጣል፣
ተ/ ተቋማዊ የደረጃ መለኪያዎችን ያዘጋጃል፣ የኮሌጁ የአካዳሚክና የአስተዳደር
ሥራዎች በወጡት መለኪያዎች መሠረት መፈፀማቸውን ያረጋግጣል፣
11
ቸ/ የኮሌጁን ገቢና ወጪ አግባብነት ባላቸው የፋይናንስ ሕግ መሠረት
መንቀሳቀሳቸውንና መያዛቸውን ያረጋግጣል፣
ኃ/ የአካዳሚክ ኮሚሽኑና ሌሎች አስተዳደራዊና ውስጣዊ ስብሰባዎች በበቂ ዝግጅትና
ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲካሄዱ ያደርጋል፤
ነ/ በኮሌጅ ውስጥ ወይም በኮሌጁና በሦስተኛ ወገኖች መካከል የሚነሱ
አለመግባባቶችን የተቋሙን ተልዕኮና ጥቅሞች ከማሳካት አኳያ በሰላማዊና
ሕጋዊ መንገድ እንዲፈቱ ያደርጋል፤
ኘ/ የኮሌጁ እንቅስቃሴና መሠረታዊ ግንኙነቶች በተገቢው የመረጃ ሥርዓት
መመዝገባቸውን፣ መረጃው በአግባቡ መጠበቁንና አግባብነት ላላቸውም ተደራሽ
መሆኑን ያረጋግጣል፣
አ/ የኮሌጁን እቅድና በጀት ያዘጋጃል፣ ሲፀድቁም ያስፈጽማል፤
ከ/ ስለኮሌጁ እቅድ አፈፃፀም ለቦርዱና ለሚመለከተው ክፍል ወቅቱን የጠበቀ
ሪፖርት እና መረጃ ያቀርባል፤
ኸ/ ኮሌጁ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርገው ማናቸውም ግንኙነት ተቋሙን
ይወክላል፤
ወ/ በኮሌጁ ስም የባንክ ሂሣብ ይከፍታል፣ ያንቀሳቅሳል፡፡
ዐ/ የወጪ ጉዞዎቹን በታቀዱና ለተቋሙ ባላቸው ፋይዳ ላይ የተመሠረቱ
መሆናቸውን ያረጋግጣል፣
2. ዲኑ ሙሉ ጊዜውን ለኮሌጁ ሥራዎች ያውላል፤ ለአገልግሎቱ ተገቢውን ደመወዝና
ጥቅማ ጥቅሞች ያገኛል፣
3. ዲኑ በሁኔታዎች አስገዳጅነት ሥራው ላይ በማይገኝበት ጊዜ ከምክትል ዲኖቹ
አንዱን ሊወክል ይችላል፣
21. ስለምክትል ዲኖች ኃላፊነትና ተግባር
1. የምክትል ዲኖች ቁጥር ቦርዱ ከቢሮው ጋር በመመካከር አስፈላጊ ናቸው ብሎ
የሚወስነውን ያህል ይሆናል፡፡
ሀ/ የኮሌጁን ተግባራት በማቀድ፣ በማደራጀት፣ በመምራትና በማስተባበር ዲኑን
ያግዛሉ፡፡
ለ/ በዲኑ ተለይተው የሚሰጧቸውን ሥራዎች ያከናውናሉ፡፡
12
ሐ/ ዲኑ በማይኖርባቸው ጊዜ ተለይቶ ውክልና የሰጠው ምክትል ዲን ለዲኑ
የተሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፡
2. ምክትል ዲኖች አብዛኛውን የሥራ ጊዜያቸውን ለኮሌጅ ሥራ ያውላል፤
ለአገልግሎታቸውም ተገቢ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅሞች ያገኛሉ፡፡
22. ስለዲኑና ምክትል ዲኖች አገልግሎት መቋረጥ
1. የኮሌጁ ዲን ወይንም ምክትል ዲኖች ከሚከተሉት ምክንያቶች በአንድ ከኃላፊነቱ
ሊሰናበት ይችላል፡-
ሀ/ በፈቃዱ ሥራ በመልቀቅ፣
ለ/ በችሎታ ማጣት፣ በከባድ ጥፋት፣ በህመም ወይም በሞት ምክንያት የተሰናበተ
ከሆነ፣
ሐ/ በፈቃድ ከ180 ተከታታይ ቀናት በላይ ከሥራ ከተለየ፤
መ/ ያለፈቃድ ከ45 ተከታታይ ቀናት በላይ ከሥራ ከተለየ፤ ወይንም
ሠ/ የአገልግሎት ጊዜው ሲያበቃ፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ በተደነገገው መሠረት ከቦርድ በሚቀርብለት ሃሣብ
መሠረት ወይም የቦርዱ ሃሣብ ባይቀርብም ተገቢ እርምጃ ነው ብሎ ካመነ
እንደአግባቡ ርዕሰ መስተዳድሩ ዲኑን ከሥራ ማሰናበት ይችላል፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ መሠረት ቦርዱ ምክትል ዲኖችን ከኃላፊነት
ሊያሰናብት ይችላል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በሦስት ተከታታይ
የክትትል ወይም በአንድ ጥቅል የሥራ አፈፃፀም ግምገማው የዲኑ ወይም የምክትል
ዲኖች በኃላፊነት መቀጠል ተቋሙን ይጐዳል ተብሎ ቦርድ ካመነ እንደአግባብነቱ
ከኃላፊነቱ እንዲሰናበት እርምጃን ሊያስወስድ ይችላል፡፡
ምዕራፍ ሦስት
ስለአካዳሚክ ኮሚሽን
23. ስለአካዳሚክ ኮሚሽን ኃላፊነት
የቦርዱ ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አካዳሚክ ኮሚሽኑ አካዳሚክ ጉዳዮችን በሚመለከት
መሪ አካል በመሆን የሚከተለው ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡
1. የኮሌጁን የትምህርት ዘመን መወሰን፣
13
2. የኮሌጁን አካዳሚክ ኘሮግራሞችና ሥርዓተ ትምህርቶቻቸውን መወሰን፣ የትምህርት
ክፍሎች የሚሰጡትን ትምህርት እና የሚያካሄዱበትን ምርምር ጥራትና አግባብነት
ለማረጋገጥ እንዲችሉ መመራትና አቅጣጫ ማስያዝ፣
3. የትምህርትና ምርምር ኘሮግራሞችን በሚመለከት የአካዳሚክ ማህበረሰቡ
የሚተዳደርበትን ደንብ ማውጣትና ስለመከበሩም መከታተል፤
4. የዶክትሬት ዲግሪ የሚሰጥበትን ወይም የሚሰረዝበትን ሁኔታዎች መወሰን፤
5. ኮሌጅ አቀፍ የትምህርት አግባብነትና ጥራት ማጐልበቻና የተማሪዎች ምዘና
ሥርዓትን ማውጣት፤
6. በአካዳሚክ ኃላፊነት ስለሚሾሙት ጥያቄ ሲቀርብለት ለዲኑ ምክር መስጠት፤
7. የኘሮፌሰር ማዕረግ ተገቢ ሆኖ ሲያገኘው ደግፎ ለቦርድ ማቅረብና በተባባሪ ኘሮፌሰር
ዕድገት ላይ የመጨረሻውን ውሣኔ መስጠት፤
8. በትምህርት ክፍሎች በሚቀርብ በኘሮፌሰር ደረጃ የሚፈፀም የአዲስ ቅጥር ጥያቄ
ላይ መወሰን፤
9. በዲኑ በሚቀርበው የውሣኔ ሃሣብ መሠረት በተቋሙ እውቅና ሊሰጣቸ የሚገባ ልዩ
አስተዋጽኦ ላስመዘገቡ ሰዎች የክብር ዲግሪ ወይም ሌሎች ሽልማቶችን መስጠት፤
10.በኮሌጁ ሥር ስለሚኖሩት የትምህርት ክፍሎች መከፈት፣ መዝጋት ወይም መዋሃድ
በኮሌጁ ዲን በሚቀርበው የውሣኔ ሃሣብ መሠረት መርምሮ ማጽደቅ፤
11.የትምህርትና ሥልጠና ነክ ጉዳዮችን በማጠናት የመፍትሔ ሃሣብ ለቦርድ ወይም
ለቢሮው ማቅረብ፤
12.የፈተና አሰጣጥ ዘዴና የተማሪዎችን የማለፍና ያለማለፍ ሁኔታዎችን ይወስናል፤
13. የኮሌጁን የተማሪዎች የትምህርትና ሥልጠና ደረጃ አወሳሰን፣ ምረቃን የሚመለከቱ
መመዘኛ መስፈርቶችን ያወጣል፤ በነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችና
ቅሬታዎችን መርምሮ ውሣኔ ይሰጣል፤
14.የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ያወጣል፤
15.በሌሎች ሕጐች የሚሰጠውን ኃላፊነት ወይም በኮሌጁ ዲን የሚመራለትን ጉዳይ
ያከናውናል፡፡
24.የአካዳሚክ ኮሚሽን አባላት
1. የኮሌጁ የአካዳሚክ ኮሚሽን አባላት ቁጥር በኮሌጁ የትምህርት ክፍሎች ብዛት አኳያ
በቦርድ የሚወሰን ሆኖ የሚከተሉት የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት ናቸው፡፡
14
ሀ/ የኮሌጁ ዲን - ሰብሣቢ፣
ለ/ የኮሌጁ ምክትል ዲኖች - አባልና አስረጂ፣
ሐ/ የኮሌጁ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ዲን - አባል
መ/ የሬጅስትራር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ - አባል
ሠ/ የተማሪዎች ዲን - አባል
ረ/ የትምህርት ክፍሎች የበላይ ተጠሪዎች - አባል
ሰ/ የመምህራን ተወካይ ሁለት / ከወንድና ሴት/ - አባልና ፀሐፊ
ሸ/ የተማሪዎች ካውንስል ተወካይ ሁለት / ከወንድና ሴት/ - አባል
2. የአባላቱ አብላጫው ቁጥር በኮሌጁ ዲን የሚመረጡ ሆኖው ለኃላፊነት የሚመጥኑና
በተቋሙ ውስጥ በተነፃፃሪ ረጅም አገልግሎት ያላቸው የአካዳሚክ ሠራተኞች
ይሆናሉ፡፡
3. ለአፈፃፀም ውጤታማነት ሲባል በአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባልነትና የአባላት ብዛትን
እንዲሁም የሥራ ዘመን ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በኮሌጁ ዲን ምክር
መሠረት ቦርዱ ማሻሻያ ማድረግ ይችላል፡፡
25.ስለአካዳሚክ ኮሚሽኑ ሰብሰባዎች
1. የአካዳሚክ ኮሚሽኑ የአባላቱን ዲሲኘሊን ጨምሮ የራሱን መደበኛና አስቸኳይ
ስብሰባዎች በሚያወጣው ደንብ ውስጥ ይወስናል ፣
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ድንጋጌ ሲጠይቅ ወይም ከአባላቱ አንድ ሦስተኛው
ሲጠይቁ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሄድ ይችላል፡፡
3. ኮሚሽኑ የኮሌጁ ዲን ወይም ቦርዱ ሲጠይቅ ወይም ከአባላቱ አንድ ሦስተኛው
ሲጠይቁ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሄድ ይችላል፡፡
4. ኮሚሽኑ የኮሌጁ ዲን ስብሰባዎች በበቂ ዝግጅት እንዲካሄዱ፣ በተገቢ መንገድ በቃለ
ጉባዔ መዘገባቸውንና መጠበቃቸውን፣ ውሣኔዎች ለሚመለከታቸው በትክክል
መተላለፋቸውንና መተግበራቸውን ያረጋግጣል፡፡
5. ከኮሚሽኑ አባላት ከግማሽ በላይ በስብሰባው ላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል፣
ውሣኔዎቹም በአብላጫ ድምጽ ይሆናል፤ ለውሣኔ የሚሰጡ ድምፆች እኩል ከሆኑ
የሰብሣቢው ድምጽ ወሣኝ ይሆናል፡፡
15
6. ኮሚሽኑ በኃላፊነቱ መሠረት የትምህርት ክፍሎችን፣ የኮሚቴዎቹንና እንደ አንድ
አካል የራሱን የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል፣ የግምገማው ውጤት በዲኑ አማካኝነት
ለቦርዱ ይቀርባል፡፡
7. ኮሚሽኑ ለሥራው አስፈላጊና አስረጂ የሆኑ ሰዎችን በስብሰባው ሊያሳትፍ ይችላል፡፡
26. ስለኮሌጁ ሬጅስትራር ተግባርና ኃላፊነት
ሬጅስትራሩ ተጠሪነቱ ለኮሌጁ ዲን ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡
1. ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፈ መዘክር/ሪኮርድ/ እንዲኖር ያደርጋል፣ የመመዝገቢያ
ሌሎች አስፈላጊ ቅፃቅፆችን ያዘጋጃል፣
2. የኮርስ ካታሎጐችን ያዘጋጃል፤ በአካዳሚክ ኮሚሽኑ ሲፈቀድ ሥራ ላይ ያውላል፤
3. የዓመቱን የአካዳሚክ ካላንደር ያዘጋጃል፤ እንደአስፈላጊነቱ በየሴሚስተሩ መጨረሻ
ለቀጣይ ሴሚስተር የሚሆን ኮርስ በአካዳሚክ ኮሚሽን ያስወስናል፣ ያስፈጽማል፤
4. የተማሪዎች ውጤት በአካዳሚክ ካሌንደሩ መሠረት አጠናቅሮ ለኮሚሽኑ ውሣኔ
ያቀርባል፣ ለሰልጣኞች ውጤታቸውን ይሰጣል፣ የወደቁና የሚመረቁ ሰልጣኞችን
በመለየት ለሚመለከታቸው አካላት በወቅቱ ያስተላልፋል፤
5. የተማሪዎችን ስታስቲካዊ መረጃ ለኮሌጁ የሥራ ክፍሎችና ለበላይ አካላት በወቅቱ
ያሰራጫል፤
6. የተመረቁና ተሸላሚ ተማሪዎችን ስም ዝርዝር ለኮሚሽኑ አቅርቦ ያስወስናል፤
7. በተለያዩ ትምህርት ስልጠና መርሃ ግብሮች፣ የሰልጣኞች አመዘጋገብ፣ ሪኮርድ
አያያዝና ግንኙነት አመቺ ሁኔታ ይቀይሳል፤
8. የየኘሮግራሙን ሰልጣኞች ይመዘግባል፣ ያስመርቃል፣ ኮሌጁን ሲለቁ ማንኛውም
በተገቢው ጊዜ ይሰጣል፤
9. ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትና በዲኑ የሚመሩለትን ሥራዎች ያከናውናል፡፡
ክፍል ሦስት
ስለሌሎች የኮሌጁ አካላት መብትና ግዴታ
ምዕራፍ አንድ
ስለኮሌጁ ተማሪዎች
27. የኮሌጁ ተማሪዎች መብት
1. የዚህ ደንብ ሌሎች ድንጋጌዎችና አግባብነት ያላቸው ሌሎች ሕጐች እንደተጠበቁ
ሆነው የኮሌጁ ተማሪዎች የሚከተሉት መብቶች ይኖራቸዋል፡፡
16
ሀ/ በመመራመር እውነትን የመፈለግና ሃሣብን በነፃነት የመግለጽ፤
ለ/ በመማሪያ ክፍል፣ በተቋም ጊቢና በሕብረተሰቡ ውስጥ ለመማር አመቺ ሁኔታን
የማግኘትና የመጠቀም፤
ሐ/ በኮሌጁ ውስጥ ሰብዓዊ መብታቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ የመኖርና የግል
ንብረታቸውን ደህንነት የማስጠበቅ፤
መ/ በኮሌጁ ጉዳዮች ላይ በሕጋዊና ሰላማዊ አግባብ አቋማቸውን በነፃነት የማራመድ፤
ሠ/ ማንኛውም ዓይነት አድልዎና ትንኮሣ እንዳይደርስባቸው ሕጋዊ ከለላን
የማግኘት፤
ረ/ ለማንኛውም የመምህርና ተማሪ ግንኙነት ገጽታዎች የፍትሐዊነት ተጠቃሚ
የመሆንና ለመማር የሚያነሳሳ መልካም ተቋማዊ ድባብን የማግኘት፤
ሰ/ በኮሌጁ ንብረት የመጠቀም፤
ሸ/ ስለአካዳሚያዊ ብቃታቸው በዚህ ደንብ በተደነገጉ መርሆዎችና በኮሌጁ አካዳሚክ
መመዘኛዎች መሠረት የመመዘን፤ ኢፍትሐዊ ምዘና ሲፈፀም ቅሬታን በተቋሙ
ሥርዓት መሠረት በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ የማቅረብና ፍትህ የማግኘት፤
ቀ/ ግልጽነት ባለው ሥርዓት በአካዳሚክ ሠራተኞች የሥራ አፈፃፀምና በአካዳሚክ
ኘሮግራሞች አፈፃፀም ግምገማ ላይ የመሳተፍ፤
በ/ የግል ትምህርት ማህደራቸውና መረጃዎች ሚስጥር ለመጠበቅ የሚያስችል
ሥርዓት ተጠቃሚ የመሆን፤
ተ/ በሕግ አግባብ በተቋቋሙ የተማሪዎች ሕብረት ውስጥ የመሳተፍ እና በኮሌጁ
መገልገያዎች የመጠቀም፤
ቸ/ ኮሌጁ ሥርዓተ ትምህርት ሲያዘጋጅ ወይም ሲከልስ እና ሥራ ላይ ሲያውል
አስተያየት የመስጠት መብት፤
ኃ/ በኮሌጁ ውስጥ የመገናኛ ዘዴዎችን የመጠቀም፤
ነ/ በዚህ ደንብ መሠረት የወጪ መጋራት ሥርዓት ተጠቃሚ የመሆንና የምክር
አገልግሎት የማግኘት፤
28. ስለኮሌጁ ተማሪዎች ግዴታ
1. የዚህ ደንብ ሌሎች ድንጋጌዎችና አግባብነት ያላቸው ሕጐች ተፈፃሚነት እንደጠበቀ
ሆኖ ማንኛውም የኮሌጁ ተማሪ የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩበታል፤
17
ሀ/ በክፍል የመገኘትና ትምህርቱን በሚገባ የመከታተል፣ የማንኛውም አካዳሚክ
ሠራተኛ የመማር ማስተማር ሂደቱን የመምራትና የመቆጣጠር ሥልጣንን
የማክበር፤
ለ/ በተመዘገበበት ትምህርት የተቀመጡ የብቃት መመዘኛዎችን የማሟላት፤
ሐ/ የኮሌጁን ዓላማዎችንና የተቋሙን መሪ እሴቶች የማወቅና የማራመድ፤
መ/ በክፍል ውስጥም ሆነ በተቋሙ ግቢ ውስጥ በሕግ የተጠበቀውን የሌሎች ሰዎችን
መብት የማክበር፤
ሠ/ አግባብነት ያላቸውን ሕጐች እንደዚሁም በዚህ ደንብ ድንጋጌዎች ላይ
የተመሠረቱትን የኮሌጁን መመሪያዎችና ደንቦች የማክበር፤
ረ/ ከማንኛውም ሕገ-ወጥ ድርጊት እና ከማንኛውም ከሥነ ምግባር ውጭ ከሆኑ
ተግባራት የመቆጠብ፤
ሰ/ የግልም ሆነ የጋራ የተማሪ ጥቅሞች አደጋ ላይ የሚወድቁበት ጊዜ በሠላማዊና
በሕጋዊ መንገድ ቅሬታን በማሰማት መፍትሔን የመሻት፤
ሸ/ የኮሌጁን ንብረት በጥንቃቄ የመያዘና የመጠቀም፣ ሆን ተብሎ ወይም
በቸልተኝነት ምክንያት በተቋሙ ንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ተጠያቂ የመሆን፣
ቀ/ በዚህ ደንብ ድንጋጌዎች መሠረት ተቋሙ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች መከፈል
የሚገባውን ክፍያ የመፈፀም፡፡
2. ኮሌጁ የተማሪዎች የሥነ-ምግባር ደንብና የዲስኘሊን እርምጃ ለመውሰድ የማያስችል
ተገቢ ሥርዓት የማውጣት ግዴታ አለበት፡፡
29. የተማሪዎች ቅበላ
1. ኮሌጁ በዶክትሬት ዲግሪ ለሚሰጠው ትምህርት በጤና መስክና በተዛማጅ ዘርፎች
ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸውና በሚኒስቴሩ ደንብ መሠረት አስፈላጊውን
መመዘኛ የሚያሟሉ ይሆናል፡፡
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ እንደተጠበቀ ሆኖ የመግቢያ ፈተና ሊዘጋጅ
ይችላል፡፡
3. ከዚህ በላይ በንዑስ /1/ እና /2/ ላይ የተደነገገው ቢኖርም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ
በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት መስፈርት መሠረት ተማሪዎችን
ተቀብሎ ማሰልጠን ይችላል፡፡
18
30. ስለኮሌጁ ሠራተኞች
ኮሌጅ፡-
ሀ/ የአካዳሚክ ሠራተኛ፣
19
ተ/ በዲሲኘሊን ጉዳይ የመሰማት ዕድል የማግኘትና ተገቢ ያልሆነ ውሣኔ
እንዲነሳለት የመጠየቅና ፍትህን የማግኘት፤
2. ኮሌጁ የአካዳሚክ ሠራተኞቹን በሚመለከቱ የመብት ጉዳዮች ላይ በአሳታፊ ሂደት
ላይ የውስጥ ደንብና የአፈፃፀም ሥርዓትን የመቅረጽና ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት
አለበት፤
32. የአካዳሚክ ሠራተኛ ግዴታ
1. የዚህ ደንብና በሌሎች አግባብነት ባላቸው ሕጐች የተደነገጉ ድንጋጌዎች እንደተጠበቀ
ሆኖ የኮሌጁ አካዳሚክ ሠራተኛ የሚከተሉትን ግዴታዎች ይኖሩበታል፡፡
ሀ/ መላ ዕውቀቱንና ክህሎቱን ለሠልጣኞች የማድረስ ወይም የማስተላለፍ፣
ለ/ ልዩ ድጋፍ ለማያስፈልጋቸው ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ ማድረግን ጨምሮ
የአካዳሚክ ምክር አገልግሎትና የሕብረተሰብ አገልግሎት የመስጠት፤
ሐ/ በራሱ የሙያ መስክ ችግር ፈቺና ለሀገር ጠቃሚ የሆነ ምርምር የማካሄድ፣
ዕውቀትና ክህሎትን የማሸጋገር፣ የሚያስተምረውን ትምህርት በጥናትና ምርምር
ላይ የተመሠረተ የማድረግና በየጊዜው የማሻሻል፣
መ/ በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ተማሪዎች በሚዛናዊነት የማስተናገድ ሙያዊ
ሥነ ምግባርን በተላበሰ ሁኔታ ሙያዊ ብቃትን የማረጋገጥ፣
ሠ/ ኮሌጁ የሚመራባቸውን እሴቶች የማክበር፣ የመተግበርና አካዳሚክ ነፃነቱን
በሙያዊ ሥነ ምግባር እና አግባብ ባላቸው የዚህ ደንብ ድንጋጌዎች የመጠቀም፤
ረ/ ሙሉ የሥራ ጊዜውን ለኮሌጁ የማዋል፤
ሰ/ በመማር ማስተማር ሂደት የራስን የፖለቲካ አመለካከት ወይም ሐይማኖት
በተማሪዎች አመለካከት ላይ ከመጫን የመቆጠብ፤
ሸ/ ኮሌጁ በዚህ ደንብና በአካዳሚክ ኮሚሽኑ ደንብ መሠረት የሚሰጡትን ሌሎች
ተግባራት የማከናወን፤
በ/ ከሌላ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ጋር አስቀድሞ በሚደረግ ስምምነት መሠረት
የአካዳሚክ ሠራተኛን በጋራ ስለመቅጠር በዚህ ደንብ የተደነገገው እንደተጠበቀ
ሆኖ፣ ሙሉ ኃይሉን፣ የሥራ ጊዜውንና ትኩረቱን ለኮሌጁ የማዋል፣
ተ/ የኮሌጁ የጤና ባለሙያ የሆኑ የአካዳሚክ ሠራተኞች በኮሌጅ የማስተማሪያ
ሆስፒታል ውስጥ በሙያቸው ተገቢውን አገልግሎት የመስጠት፤፡
20
33. አካዳሚ ሠራተኛን በጋራ ስለመቅጠር
1. አካዳሚክ ሠራተኛን በጋራ መቅጠር ተፈፃሚ የሚሆነው የትምህርት አግባብነትንና
ጥረትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የአካዳሚክ ሠራተኛ እጥረት ሲገጥም
እንደመልካም መፍትሔ ሆኖ ሲገኝ ነው የጋራ ቅጥር ተግባራዊ ሲደረግ ከሌሎች
ተቋማት ወይም የምርምር ማዕከሎች ለጋራ ጥቅም የሚያበቃ ሙያዊ አቅም
ያለውን ባለሙያ የሚመለከት ይሆናል፡፡
2. አንድ አካዳሚክ ሠራተኛ ወይም መንግሥት ሠራተኛ አቅሙ ካለው በራሱ ፈቃድ
የሆኑ አካዳሚክ ሠራተኞችን የጋራ ቅጥር የሚመለከቱ አግባብነት ያላቸው ሌሎች
ሕጐች እንደተጠበቁ ሆነው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የመተባበር ግዴታ
ይኖርባቸዋል፡፡
3. የቅጥሩ ሁኔታ፣ ቅጥሩ የሚቆይበት ጊዜ፣ ደመወዝና ሌላ ጥቅማ ጥቅሞችን
እንዲከውኑ የሚፈለጉ ተግባራትና ጊዜን ማደላደል የመሳሰሉት ለተቀጣሪውና ደንብና
ሥርዓት መሠረት ይወሰናሉ፡፡
4. የጋራ ቅጥር የሚመለከቱ ድንጋጌዎች የግል ተቋማትን አይመለከትም፡፡
34. የአስተዳደርና የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች መብትና ግዴታ
1. የኮሌጁ የአስተዳደርና የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ሕግ
መሠረት ይተዳደራሉ፡፡
2. የኮሌጁ ቦርድ አግባብ ባለው የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መርሆዎች ላይ
በመመስረትና የተቋሙን አቀም በማገናዘብ የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች አሰተዳደር
ዝርዝር መመሪያን ማውጣት ይችላል፡፡
3. ማንኛውም የኮሌጁ የአስተዳደርና የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኛ አግባብነት ላላቸው
ሕጐችና የተቋሙ መመሪያዎች የመገዛትና በተግባርም የከፍተኛ ትምህርት
ዓላማዎችንና የተቋሙን መሪ እሴቶች የማክበር ግዴታ አለባቸው፡፡
ምዕራፍ ሁለት
ስለኮሌጁ ሆስፒታል
35. የኮሌጁ ሆስፒታል
1. ኮሌጁ የይርጋዓለም ሆስፒታልን ለተግባር ልምምድ ያለማንም ከልካይነት
ይጠቀምበታል፡፡
21
2. አካዳሚክን በተመለከተ የተግባር ልምምድን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ
ዝርዝር መመሪያዎችን ቦርዱ ያወጣል፣
3. የይርጋዓለም ሆስፒታል መደበኛ ሥራዎችና አስተዳደር ቀደም ሲል በነበረው
አኳኋን የሚመራ ይሆናል፡፡
4. የኮሌጁ አካደሚክ ሠራተኞች የጤና አገልግሎት በሆስፒታሉ መስጠት በሚችሉበት
ሁኔታ ላይ ቢሮው መመሪያ ሊያወጣ ይችላል፡፡
5. ኮሌጁ እንደአስፈላጊነቱ ሌሎች ሆስፒታሎችንና የሕክምና ምርምር ማዕከሎችን
የማቋቋምና የማስፋፋት መብት ይኖረዋል፡፡
ክፍል አራት
ምዕራፍ አንድ
ስለአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር
36.የጤና ቢሮ ስልጣንና ተግባር
1. ቢሮው በዚህ ደንብና በሌሎች ሕጐች ድንጋጌዎች የሰጠው ኃላፊነት እንደተጠበቀ
ሆኖ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡
ሀ/ ኮሌጁ የሀገሪቱን ብሎም የክልሉን የጤናውን ዘርፍ የትኩረት አቅጣጫ ተክተሎ
መጓዝን የማረጋገጥ፤
ለ/ የኮሌጁ ቦርድ ሰብሣቢና ሌሎች የቦርድ አባላትን እንዲየሰሙ በእጩነት
የማቅረብና የማሰወሰን፣
ሐ/ ኮሌጁ የሚያቋቁማቸው የጤና አገልግሎት መስጫና የምርምር ማዕከሎች ሁኔታ
የመገምገም፤
መ/ በክልሉ ያለውን የከፍተኛ ሕክምና ባለሙያ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ
ዘዴዎችን በመቀየስ ከኮሌጁ ጋር ተባብሮ የመስራት፤
ሠ/ ኮሌጁ ዓላማውን ለማሳካት የሚያስችል አደረጃጀት እንዲኖራቸውና ሌሎች
አስፈላጊ ተግባራትን የማከናወን ተግባራት ይኖሩታል፡፡
2. የኮሌጁ የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት ካሪኩለም፣ የአካዳሚክ ደረጃ እና የጥራት
መመዘኛዎችን በተመለከተ በትምህርት ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ መመዘኛዎች
መሠረት የሚተገበር ሲሆን በዚህ ረገድ ክትትልና ግምገማውም በሚኒስቴሩ
ይሆናል፡፡
22
ምዕራፍ ሁለት
ስለኮሌጁ በጀት፣ የገንዘብ አስተዳደርና ኦዲት
37. የኮሌጁ በጀት
1. ኮሌጁ በጀቱ በክልሉ መንግሥት የሚመደብለት ሲሆን በአደረጃጀቱም በስትራቴጂክ
ዕቅድ ስምምነት ላይ በተመሠረተ የጥቅል በጀት ሥርዓት መሠረት ይሆናል፡፡
2. በጀቱ የአምስት ዓመት ጠቋሚ ጥቅል በጀት ሲሆን በየዓመቱ እየተገመገመ
የሚስተካከል ይሆናል፡፡
3. ኮሌጁ የገንዘብ ፍላጐቱን ለማሟላት በዚህ ደንብ መሠረትና በሌሎች ሕጐች
ከተፈቀዱ ሌሎች ምንጮች ገቢዎችን ማሰባሰብ ይችላል፡፡
4. ኮሌጁ የጥቅል በጀት አሠራር ተጠቃሚ ለመሆንና አስተዳደሩን በአግባቡ ለመምራት
ይችል ዘንድ የገንዘብ መረጃዎችን የሚያስተዳድርበትን አቀም መገንባት ይኖርበታል፡፡
5. የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኮሌጁ የዚህን አንቀጽ ድንጋጌዎች ተግባራዊ
ለማድረግ እንዲችል ተገቢውን እገዛ ያደርጋል፡፡
6. ኮሌጁ ከሦስተኛ ወገኖች ስጦታዎችን መቀበል ይችላል፤ ሆኖም የሚያገኘው ስጦታ
ከተቋሙ አቋም ተልዕኮና ዓላማ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የማይኖረው መሆን
ይኖርበታል፤
7. ኮሌጁ ከሦስተኛ ወገን ስለሚያገኘው ገንዘብና ኢንቨስትመንት፣ ስለሚያገኘው ገቢ
ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ፣ ለቢሮውና ለሚመለከተው አካል የማሳወቅ ግዴታ
አለበት፡፡
38.የድጐማ በጀት
1. ኮሌጁ በአገልግሎት ላይ ያልዋለ የቀዳሚው ዓመት ጥቅል በጀት የተቋሙ ድጐማ
በጀት ሆኖ ወደሚቀጥለው የበጀት ዓመት እንዲተላለፍና ለተቋሙ አገልግሎት
እንዲውል ሊደረግ ይችላል፡፡
2. ኮሌጅ የድጐማ በጀትን በካፒታል በጀት መልክ ብቻ ይጠቀምበታል፡፡
3. የድጐማ በጀት ከዓመቱ ጥቅል በጀትና ከተቋሙ ገቢ ከሚገኘው ገንዘብ ጋር
እንደተቋሙ አጠቃላይ ዓመታዊ በጀት በቦርዱ የሚፀድቅ ይሆናል፡፡
23
39. የገንዘብ አስተዳደር
1. የኮለጁ ዲን የተቋሙን የገንዘብ ጉዳይ በሕግ፣ በቅልጥፍና፣ በውጤታነት፣ በቁጠባና
በግልጽነት መርሆዎች ላይ ተመስርቶ የመምራትና የማስተዳደር ኃላፊነትና
ተጠያቂነት ይኖርበታል፡፡
2. ሕግ በሌላ ሁኔታ ያስቀመጣቸውን በጀትን አስቀድሞ በቦርድ ማጽደቅ አሠራር
እንደተጠበቀ ሆኖ በፀደቀለት የሥራ ዕቅድ መሠረት ገቢውን በነፃነት የመጠቀም
መብት ይኖረዋል፡፡
3. በጀት ባልፀደቀበት ወቅት ቦርድ በጀቱን እስኪያፀድቀው ድረስ የኮሌጁ ዲን የተቋሙ
መደበኛ ሥራ እንዳይስተጓጐል በቀዳሚው የበጀት ዘመን አሠራርና መጠን መሠረት
ወጪ እንዲያደርግ ለቦርድ ስልጣን ሊሰጠው ይችላል፡፡
40.ገቢን ስለማግኘት
ኮሌጁ የሚከተሉት የገቢ ምንጮች ሊኖሩት ይችላል፡፡
ሀ/ ኮሌጅ ከሚሰጠው አገልግሎት ወይም ከሚያከናውነው ሥራ የሚገኝ ገቢ፣
ለ/ የኮሌጁ ሠራተኞች በፈቃደኝነት ከሚያደርጉት መዋጮ፤
ሐ/ ለኮሌጁ ከሚሰጡ ስጦታዎችና እርዳታዎች፤
መ/ ከሌሎች ሕጋዊ የገቢ ምንጮች
41. የገቢ ፈንድ
1. ኮሌጁ በቦርዱ አስወስኖ በቢሮ ሲፀድቅ የገቢ ፈንድ ማቋቋም ይችላል፤
2. የፈንዱ የገቢ ምንጮች የሚከተሉት ይሆናሉ፤
ሀ/ በኮሌጅ የገቢ ማስገኛ ድርጅቶች የሚደረግለት መዋጮ፤
ለ/ በበጀት ዓመቱ ሥራ ላይ ያልዋለ የፈንዱ ገንዘብ፤
ሐ/ ስጦታዎች እና ሌሎች ሕጋዊ የገንዘብ ምንጮች፡፡
3. ፈንዱ ቦርድ በሚያፀድቀው መሠረት ለኮሌጁ ልዩ ልዩ የአቅም ግንባታ ተግባራት፣
ለሽልማትና ለሌሎች ተግባራት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡
4. የፈንዱ አጠቃቀም የበጀት ሥርዓትን የተከተለ ይሆናል፡፡
42. ሪፖርት ስለማቅረብና ቁጥጥር
1. ኮሌጁ
ሀ/ በስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ በመመስረት በአግባቡ ተመዝኖ የፀደቀውን ዓመታዊ
የአፈፃፀም ሪፖርትና በኦዲተር የተመረመረ የሂሣብ ሪፖርት እንደአግባብነቱ
24
ለቢሮው ወይም ለሚመለከታቸው የክልል አካላት ማቅረብና የበጀት ዓመቱ
ትምህርታዊና ሌሎች መረጃዎችን የማሳተም፣
ለ/ በማናቸውም ጊዜ በሚኒስቴሩ ወይም በሚመለከተው የክልል አካል የሚጠየቀውን
መረጃ መስጠት ይኖርበታል፡፡
2. ኮሌጅ እንደአግባብነቱ በሚኒስቴሩ ወይም በሚመለከተው የክልል አካል ሕግንና
የስትራቴጂክ ዕቅድ ስምምነቱን ማክበሩን ለማረጋገጥ ቁጥጥር ሊደረግበት ይችላል፡፡
3. እንደአግባብነቱ ሚኒስቴሩ ወይም ቢሮው ከሕግ፣ ከመንግሥት ፖሊሲ፣ ከኮሌጁ
ተልዕኮ ወይም ደንቦች ጋር የሚጋጩ የቦርድ፣ የዲን ወይም የአካዳሚክ ኮሚሽን
ውሣኔዎችን ሊሽር ይችላል፡፡
43. የሂሣብ መዛግብት
1. ኮሌጁ በዲኑ ኃላፊነትና አስተዳደር ሥር የሚመራ የተቋሙ ግዴታዎችንም ታሣቢ
ያደረገ የገቢና የወጪ ሂሣብን ጨምሮ አግባብነት ያለው የሂሣብ አያያዝና ሪፖርት
የማቅረቢያ ሥርዓትን መዘርጋት ይኖርበታል፤
2. ኮሌጁ የደብል ኢንትሪ ሂሣብ አያያዝን የመከተል፣ ተቀጽላ የሆኑ ተግባራት ገቢና
ወጪዎችን ከሌሎች ገቢዎችና ወጪዎች ለይቶ የመያዝ እና ለሁሉም የገቢና
ወጪ ጉዳዮች የሂሣብ አያያዝ አጠቃላይ ሥርዓትን የመከተል ግዴታዎች
ይኖረታል፡፡
3. ኮሌጁ የተቋሙን ሃብትንና እዳን ለመለካት ቀለል ያለ የመመዘኛና የኦዲት ሥርዓት
ለመጠቀም የሚያስችሉ የሂሣብ አያያዝና ሪፖርት አቀራረብ መመሪያዎች መሠረት
የሂሣብ መዛግብቱን ያደራጃል፡፡
44. ኦዲት
1. በኮሌጁ ውስጥ ራሱን የቻለና ለዲኑ ተጠሪ የሆነ የውስጥ ኦዲት ያቋቁማል፤
2. የኮሌጁ የውስጥ ኦዲት ክፍል ኃላፊ በዲኑ አቅራቢነት በቦርድ ይሰየማል፤
3. የውስጥ ኦዲት የኮሌጁን የአፈፃፀም፣ የፋይናንስና ንብረት ኦዲት አከናውኖ ለዲኑና
ለቦርድ ያቀርባል፣
4. የክልሉ ዋና ኦዲተር ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የኮሌጁ ሂሣብ በቦርድ በተሰየመ
የውጭ ኦዲተር በየዓመቱ ተመርምሮ ውጤቱ ለዲኑ፣ ለቦርዱና እንደአግባብነቱ
ለሚመለከተው የክልል አካል መቅረብ ይኖርበታል፡፡
25
ክፍል አምስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
45. የአገልግሎት ክፍያዎች
ኮሌጁ ለትምህርት አገልግሎቶች ክፍያ መጠየቅ ይችላል፤ የሚጠየቀው ክፍያ ዓይነት፣
መጠንና የክፍያ አፈፃፀም አግባብ በዚህ ደንብ ሌሎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው
ቦርድ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡
46. ወጪ መጋራት
በኮሌጁ የሚሰጠውን ሥልጠና ተከታትለው የሚጨርሱ ሰልጣኞች በሙሉ የትምህርቱን
ወጪ በአገልግሎት ብቻ እንዲሸፍኑት ይደረጋል፡፡ ለዚህም ማረጋገጫ የውል ግዴታ
መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
47. አገልግሎት በሌሎች ወገኖች እንዲሰጥ ስለማድረግ
1. ኮሌጁ ተገቢና ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ሆኖ ሲያገኘው የድጋፍ ሰጪ
አገልግሎቶችን በሌሎች አገልግሎት አቅራቢዎች እንዲሰጥ ሊያደርግ ይችላል፤
2. ኮሌጅ አገልግሎት በሌሎች አቀራቢዎች እንዲሰጥ ሲያደርግ የአገልግሎቱ
ተጠቃሚዎች ለዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ አገልግሎት ለማግኘት መቻላቸውን
ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
48. የመማሪያ ሕንፃዎችና ቁሳቁሶች በተመለከተ
1. የሀዋሣ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ይርጋዓለም ቅርንጫፍ የማስተማሪያ ሕንፃና ንብረት
በዚህ ደንብ ለተቋቋመው የይርጋዓለም ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተላልፏል፡፡
2. የንብረት ርክክቡ አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ይፈፀማል፡፡
49. መመሪያ የማውጣት ሥልጣን
1. ቢሮው /ቦርዱ/ ይህን ደንብ ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ መመሪያዎች ሊያወጣ
ይችላል፡፡
2. የኮሌጁ ቦርዱ ይህን ደንብና በዚህ ደንብ ተለይቶ በተሰጠው ጉዳዮች ላይ ለማስፈፀም
ሚያስፈልጉ የውስጥ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡
50. የተሻሩ ሕጐች
ከዚህ ደንብ ጋር የሚቃረኑ ማንኛውም ሕጐች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች ወይም የአሠራር
ልምዶች ተፈፃሚነት አይኖራቸውም፡፡
26
51. ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ ደንብ በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ከፀደቀበት ከጥር 5 ቀን 2003 ዓ/ም ጀምሮ
የፀና ይሆናል፡፡
ጥር 2 ቀን 2003 ዓ.ም.
ሽፈራው ሽጉጤ
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት
ርዕሰ መስተዳድር
27