You are on page 1of 29

እንኳን ደህና

መጣችሁ
Welcome
የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን
Veterinary Drug and Animal Feed Administration and Control
Authority

በአዋጅ ቁጥር 728/2004 ላይ ያተኮረ ሥልጠና

በሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት


ለእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የተዘጋጀ
የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥርን
የተመለከቱ የሕግ ድንጋጌዎች
 የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር
አዋጅ ቁጥር 728/2004
 የእንስሳት መድኃኒት እና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር
ባለስልጣንን ለማቋቋም የሚኒስትሮች ምክር ቤት
ደንብ ቁጥር 272/2005
 ሌሎች ተዛማጅ ሕጎች
የገለጻው ይዘት
• ባለስልጣን መ/ቤቱ የተቋቋመበትን ዓላማ

• የአዋጁ ዓላማ

• የሕግ ትርጉም የተሠጠባቸው ቃላት

• የአዋጁ የተፈጻሚነት ወሰን

• ለባለስልጣኑ በአዋጁ መሰረት የተሰጡትን ስልጣንና ተግባሮች

• ከአዋጁ ጋር ተያዥነት ስላላቸው ሌሎች ሕጎች

• የአዋጁን ደንቦችና መመሪያዎችን እንዲሁም ሌሎች ሕጎችን ተላልፎ መገኘት

ስለሚያስከትለው አስተዳደራዊ እርምጃዎች እና የወንጀል ተጠያቂነት


የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና
ቁጥጥር
ባለስልጣን ለምን ዓላማ ተቋቋመ?
የእንስሳት ምርትና ምርታማነት
እንዲያድግና ጤናማ የእንስሳት ምርት
ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ እንዲቀርብ
ማስቻል ነው፡፡ (ደንብ 272 (2))
የአዋጁ ዓላማ
1. ደህንነቱ፣ ጥራቱ፣ እንዲሁም ፈዋሽነቱ የተጠበቀ የእንስሳት መድሃኒት
አቅርቦትን፣ አጠቃቀምን እንዲሁም ቁጥጥርን በማሻሻል የእንስሳት
ሃብት ልማትና ጤንነት አጠባበቅን በማሳደግ በዘርፉ ያለንን ምርታማነትን
ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ፣
2. በሃገሪቱ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የእንስሳት ጤና አጠባበቅ መርሃ ግብር በተሻለ
ሁኔታ ውጤታማ በማድረግ በእንስሳትና በእንስሳት ውጤቶች ዓለም አቀፍ
ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት በማስፈለጉ፣
3. የእንስሳት መድሃኒት ሕገ-ወጥ ምርት ስርጭትና አጠቃቀምን መከላከልና
መቆጣጠር በማስፈለጉ፣
4. ከላይ የተጠቀሱትን አላማዎች ለማሳካት ውጤታማ የሆነ የቁጥጥር ስርአት
መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ
በሕገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት ታወጀ
ትር¹ሜ
በአዋጁ የተጠቀሱና ትርጉም የተሰጣቸው ቃላት በጥቂቱ፡-
 "እንስሳ": ማለት ለማዳና የዱር እንስሳት አእዋፍን የውሃ ውስጥ እንስሳትን ንብንና
የሃር ትልን ያጠቃልላል፡፡ አንቀጽ2(1)
• "የእንስሳት መድሃኒት": ማለት ደግሞ የእንስሳት በሽታን ለመመርመር ፤
ለማከም ወይም ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውል ማንኛውም ንጥረ -
ነገር ወይም የንጥረ -ነገር ውህድ ሲሆን የሳኒታሪ መገልገያዎችንና
የእንስሳት ህክምና መሳሪያዎችን ይጨምራል ፡፡ አንቀጽ2(2)
• "ባህላዊ የእንስሳት መድሃኒት": ማለት በልምምድ የዳበረ በህብረተሰቡ ዘንድ
ተቀባይነት ያገኘ በሙከራ የተረጋገጠ የእንስሳት መድሃኒት ነው፡፡ አንቀጽ2(5)
(የቀጠለ) ትር¹ሜ
• "የእንስሳት መድሃኒት ንግድ" ማለት የእንስሳት መድሃኒትን ለትርፍ አላማ ማምረት፤

እንደገና ማሸግ ፤ ከውጪ ማስመጣት ወደ ውጪ መላክ በጅምላ ወይም

በችርቻሮ ማከፋፈል የእንስሳት መድሃኒት ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ አገልግሎትን

መስጠት እንዲሁም በንግድ ወኪልነት መስራትን ይጨምራል፡፡ አንቀጽ2(9)

• "የእንስሳት መድኃኒት ባለሙያ”: ማለት የእንስሳት ሃኪም ወይም ረዳት የእንስሳት ሃኪም

ወይም ከእንስሳት መድኃኒት ጋር የተያያዘ የሙያ አገልግሎት የሚሰጥ የእንስሳት ጤና

ፋርማሲስት፣ የእንስሳት ጤና ድራጊስት ወይም የእንስሳት ጤና ፋርማሲ ቴክኒሽያን ነው ::

አንቀጽ2(20)
(የቀጠለ) ትር¹ሜ
 "የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት" ማለት ደግሞ ባለስልጣኑ ያወጣውን መስፈርት በማሟላት

በእንስሳት መድሃኒት ንግድ ለመሰማራት ብቁ መሆንን የሚያረጋግጥ በባለስልጣኑ ወይም

ሥልጣን በተሰጠው የክልል መንግስት የሚሰጥ ምስክር ወረቀት ነው፡፡ አንቀጽ2(13)

 "የእንስሳት ሐኪም" ማለት ከታወቀ ዩኒቨርስቲ በእንስሳት ሕክምና ሙያ ዶክትሬት ዲግሪ ወይም ከዚያ

በላይ የተመረቀ ነው፣ አንቀጽ2(21)

 "ሌሎች የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች" ማለት ከታወቀ ተsም በእንስሳት ሕክምና ሙያ በቢ.ኤስ.ሲ ዲግሪ

ወይም በዲፕሎማ ወይም በሰርተፍኬት የተመረቀ ነው፣ አንቀጽ2(22)

 " የሙያ ፍቃድ" ማለት የእንስሳት መድሃኒት ወይም መኖ ባለሙያ በሙያው መስራት እንዲችል

በባለስልጣኑ ወይም ስልጣን በተሰጠው የክልል መንግስት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት

ነው፡፡ አንቀጽ2(23)

 "የእንስሳት መድሃኒት ቤት" ማለት yእንስሳት መድሃኒት ብቻ የሚሸጥበት ተsም ነው፣ አንቀጽ2(24)
የተፈጻሚነት ወሠን
 በአንቀጽ 3 በንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት አዋጁ በሀገሪቱ በሚደረግ የእንስሳት መድኃኒትና መኖ

የቁጥጥር ስራዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ (በመድሃኒቱም በመኖውም ሆነ በእንስሳት

መድኃኒት ባለሙያው ላይ በሚደረጉ የቁጥጥር ስራዎች)

 በአንቀጽ 3 በንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት በፌደራል ደረጃ የአዋጁ ተፈጻሚነት የሚከተሉትን

በሚመለከት ነው፡-

1. የእንስሳት መድሃኒት፣ የመኖና የእንስሳት መድኃኒት ባለሙያዎችን ደረጃ ማውጣት፣

2. ክልል ተሻጋሪ የእንስሳት መድሃኒትና መኖ ማምረትን፤ ማከፋፈልን ፤ ማከማቸትን ፤

ማስተዋወቅንንና የጥራት ቁጥጥር ላቦራቶሪ አገልግሎት መስጠትን ፤ መድሃኒትና

መኖ መላክንና ከውጪ ማስገባትን መቆጣጠር

 በአንቀጽ 3 በንኡስ አንቀጽ 3 መሰረት በአዋጁ በአንቀጽ 20 ለባለስልጣኑ ከተሰጡት

ስልጣንና ተግባራት ውጪ ያሉት የቁጥጥር ተግባራት በክልል መንግስታት ተቆጣጣሪ

አካላት የሚፈጸሙ ይሆናሉ፡፡


ክፍል ሁለት
የእንስሳት መድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር
አንቀጽ ርዕስ
4 ………………………………………………..ስለ ምዝገባ
5 ………………………………………………..ስለ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
6 ………………………………………………..የእንስሳት መድኃኒት የጥራት ደረጃዎችና አጠቃቀም
7 ………………………………………………..ድህረ ገበያ ቅኝት
8 ………………………………………………..ቅድመ ክሊኒካልና ክሊኒካል ሙከራ ስለማድረግ
9 ………………………………………………..ስለ እንስሳት መድኃኒት ማሸጊያና ገላጭ ጽሁፍ
10 ………………………………………………..መድኃኒት ስለማዘዝና ስለማደል
11 ………………………………………………..ስለ እንስሳት ሕክምና ባዮሎጂካል ውጤቶች
12 ………………………………………………..የእንስሳት መድኃኒት ንግድ
13 ………………………………………………..ስለ ባህላዊና ተደጋጋፊ ወይም አማራጭ የእንስሳት
መድኃኒት
14-19 ……………………………(ክፍል ሶስት) የመኖ አስተዳደርና
ቁጥጥር
አንቀጽ 12
1. ማንኛውም ሰው አግባብ ባለው አካል
የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር
ወረቀት ሳይኖረው በእንስሳት
መድኃኒት ንግድ ሊሰማራ አይችልም፡፡
2. ማንኛውም ሰው የሙያ ፈቃድ
የተሰጠው የእንስሳት መድኃኒት
ባለሙያ በሌለበት የእንስሳት
መድኃኒት ቤት ንግድ ሊያካሂድ
አይችልም፡፡
ክፍል አራት
ስለ ባለሥልጣኑና ስለ ተቆጣጣሪዎች

የባለስልጣኑ ሥልጣንና ተግባራት (አንቀጽ 20) (13 ንኡስ አንቀጾች)

1. የእንስሳት መድሃኒትና መኖ ጥራትና ደህንነትን በተመለከተ ደረጃ

አውጥቶ ስልጣን ለተሰጠው አካል ያቀርባል (ስልጣን የተሰጠው አካል


በአዋጁ አንቀጽ 2(31) መሰረት የኢትጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ነው)

2. በእንስሳት መኖ ወይም መድሃኒት ንግድ ለሚሰማሩ ሰዎች የብቃት

መመዘኛ ያዘጋጃል፣
(የቀጠለ) የባለስልጣኑ ሥልጣንና
ተግባራት
3. ለክልል ተሻጋሪ የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አምራቾች ፤ ላኪዎች

አስመጪዎች ፤ አከፋፋዮች ፤ አስተዋዋቂዎችና የጥራት ቁጥጥር ላቦራቶሪ

አገልግሎት ሰጪዎች የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል ያግዳል

ይሰርዛል፡፡

4. በእንስሳት መድሃኒትና መኖ አያያዝና አጠቃቀምን አስመልክቶ ለሚመለከታቸው

አካላት ስልጠና ይሰጣል፡፡

5. አስፈላጊ የሆኑ የጥራት ምርመራ ላቦራቶሪዎችን ያደራጃል፡፡


6. ሀገር ውስጥ የሚመረቱም ሆነ ከውጪ ሀገር የሚመጡ የእንስሳት መድሃኒቶችንና
የመኖ ተጨማሪ ንጥረ ነገሮችን ገምግሞ ይመዘግባል፣ ምዝገባውን ያድሳል፣
ያግዳል፣ ይሰርዛል፡፡
በሌሎች አንቀጾች ላይ የተዘረዘሩ የባለስልጣኑ
ስልጣንና ተግባራት፡
1. ድህረ ገበያ ቅኝት የማድረግ፡- (አንቀጽ 7)
2. አስተዳደራዊ እርምጃ የመውሰድ ፡- (አንቀጽ 24)
• አዋጁን ደንቡን ወይም መመሪያዎችን የጣሰ ሰው የሙያ ፍቃድ
ወይም የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትን ማገድን መሰረዝን
የሚያካትት እርምጃ ነው (ከተሰጣቸው ፍቃድ ውጪ የሚሰሩትን፣
ፍቃድ የማያሣድሱትን እና የመሳሰሉት ላይ የሚወሰድ እርምጃ
ነው፡፡
• ለአገልግሎት ብቁ ያልሆነን መድሃኒት በባለቤቱ ወጪ እንዲወገድ
የማድረግ
• የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሳይኖራቸው በመድኃኒት ንግድ
የተሰማራን ሰው የንግድ ተቋም በማሸግ አስፈላጊውን እርምጃ
ስለ ተቆጣጣሪዎች ፡- (አንቀጽ 21)
1/ ባለስልጣኑ ወይም የቁጥጥር ተግባራትን የማከናወን ሥልጣን የተሰጠው የክልል

መንግስት አካል ይህን አዋጅና አዋጁን ለማስፈጸም የሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎች

መከበራቸውን ለማረጋገጥ የእንስሳት መድኃኒትና መኖ ተቆጣጣሪዎችን ይመድባሉ፡፡


2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ መሠረት የተመደበ ተቆጣጣሪ የሚከተለው ሥልጣንና
ተግባር ይኖረዋል፡-
ሀ/ የእንስሳት መድኃኒት ንግድ ሥራ ወደ ሚካሄድበት ወይም የእንስሳት
መድኃኒት ወደ ተከማቸበት ግቢ በሥራ ሰዓት በመግባት ወይም
የእንስሳት መድኃኒት የጫነን ማጓጓዣ በማስቆም የቁጥጥር ተግባር
የማከናወን፣
(የቀጠለ) ተቆጣጣሪዎች
ለ/ ከእንስሳት መድኃኒትና ሥራ ጋር የተዛመደ ማንኛውንም መዛግብት፣ ሰነድ፣ ማዘዣና

ኮምፒውተር መመልከትና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ኮፒ ተደርጎ እንዲሰጠው የማድረግ፤

ሐ/ ባለሥልጣኑ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ናሙናዎችን የመውሰድ፤

መ/ የተከለሱ፣ የተበላሹ፣ በማስመሰል የቀረቡ፣ የተበከሉ ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት

በተጠቃሚዎች ላይ ጉዳት ያደርሳሉ ተብለው በተጠረጠሩ መድኃኒቶች ላይ የጥራት

ምርመራ እንዲካሄድ ለማድረግና ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ተለይተው እንዲቆዩ የማዘዝ፤

ሠ/ የአገልግሎት ዘመናቸው ሲያበቃ ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ

ሲወሰን በተገቢው መንገድ እንዲወገዱ መደረጋቸውን የመቆጣጠር፡፡


ክፍል አምስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
አንቀጽ ርዕስ
22 ………………………………………………..ስለ እንስሳት መድኃኒት አወጋገድና የንግድ ስራ
ስለማቆም
23 ………………………………………………..ስለ ንግድ ማስታወቂያና መረጃ ስለመስጠት
24 ………………………………………………..አስተዳደራዊ እርምጃዎች
25 ………………………………………………..ስለ ቅሬታ አቀራረብ
አንቀጽ 26
ቅጣት
(የወንጀል ተጠያቂነት)
በአዋጁ የተከለከሉ ድርጊቶችና
የሚያስከትሉት ኃላፊነት (አንቀጽ 26)

1. በወንጀል ህጉ የበለጠ ካላስቀጣ


በስተቀር
ሀ. በአንቀጽ 21 መሰረት የቁጥጥር ስራን
እንዲያከናውን የተመደበ ሰራተኛ ላይ
ሁከት መፍጠር -- ከ6ወር በማያንስ
ቀላል እስራት እና እስከ 10 ሺህ ብር
ለ. ብቃት ማረጋገጫን የሰጠውን አካል
ሳያስፈቅዱ የብቃት ማረጋገጫውን ለሌላ
ሰው አሳልፎ መስጠት ከ1አመት እስከ
3አመት ቀላል እስራት እና ከ5-20 ሺህ
ብር ቅጣት
2. መድሃኒት አምራች፤ አከፋፋይ ወይም
አስመጪ ሆኖ ፍቃድ ለሌለው ሰው
ማከፋፈል ከ2-5 አመት እስራት እና
ከ10 - 20 ሺህ ብር ቅጣት
3. ማንኛውም ሰው የብቃት ማረጋገጫ
ምስክር ወረቀት ሳይኖር በመድኃኒት ንግድ
መሰማራት ከ5 ዓመት እስከ 7 ዓመት ጽኑ
እስራት እና ከ20ሺህ-50 ሺህ የገንዘብ
ቅጣት( አንቀጽ 19)
(የቀጠለ) የወንጀል ተጠያቂነት

4. የጅምላ /ችርቻሮ ንግድ ላይ ተሰማርቶ


የብቃት ማረጋገጫ ከሌለው ሰው ላይ
መድሃኒት ወይም መኖ መግዛት --ከ2-5
አመት ጽኑ እስራት እና ከ10 ሺህ -20
ሺህ የገንዘብ ቅጣት
5. መድሃኒትን አስመስሎ ማቅረብ መከለሰ፣
ደረጃውን ያልጠበቀ፣ የመጠቀሚያ ጊዜው
ያለፈበትን ለገበያ ማቅረብ ከ10-20
አመት ጽኑ እስራት እና ከ20ሺህ-50 ሺህ
የገንዘብ ቅጣት
(ማስመሰል በአንቀጽ2(16) መሰረት
የእውነተኛ ምርት ማሸጊያ የንግድ ስምና
የመሳሰሉትን በመጠቀም እውነተኛ
ምርት እንደሆነ አስመስሎ ማቅረብ በሚል
ትርጉም የተሰጠው ሲሆን መከለስ ደግሞ
በአንቀጽ 2(17) መሰረት ከተሰራበት
ንጥረ ነገር ውጪ መደባለቅ የሚል ትርጉም
ተሰጥቶታል፡፡
(የቀጠለ) የወንጀል ተጠያቂነት

6. ሌሎች በአዋጁ የተመለከቱትን ድንጋጊዎች መጣስ እሰከ 2


አመት ቀላል እስራትና እሰከ ብር 10ሺህ ቅጣት
ይጠብቀዋል፡፡

8.1 (አንቀጽ 10(1) የባህል መድኃኒት የሚታዘዘው

በባለስልጣኑ በተመዘገበና እውቅና በተሰጠው የባህል

የእንስሳት መድኃኒት አዋቂ ነው

8.2 (አንቀጽ 9 እና 16) የእንስሳት መድሃኒት

በትክክል ሳይታሸግና ተገቢው ገላጭ ጽሁፍ

ሳይደረግበት ለገበያ መቅረብ የለበትም፡፡

(መድኃኒቱ በአግባቡ ካልታሸገ፣ ስለ መድኃኒቱ

ሁኔታ ገላጭ ጽሁፍ ከሌለበት፣ ገላጭ ጽሁፍ

በአማርኛ ወይም በእንግልዝኛ ቋንቋ መጻፍ እና‹‹

ለእንስሳት ሕክምና ጥቅም ብቻ›› የሚል ገላጭ

መያዝ አለበት

8.3 (አንቀጽ 10(2) የመድሀኒት አስተዛዘዝ

ስርአትን ተከትሎ ደረጃውን ጠብቆ

በተዘጋጀ ማዘዣ መድሀኒት መታዘዝ


(የቀጠለ) የወንጀል ተጠያቂነት

8.4 (አንቀጽ 10(1) የእንስሳት መድኃኒት

የሚታዘዘው በእንስሳት ሀኪም ብቻ ነው፡፡

8.5 (አንቀጽ 10 (3) የእንስሳት መድኃኒት

የሚታደለው የሙያ ፈቃድ በተሰጠው

የእንስሳት መድኃኒት ባለሙያ ነው፡፡

8.6 (አንቀጽ10(4) ስለመድሃኒቱ በቂ መረጃ

በእንስሳት መድሃኒት ባለሙያው

መሰጠት አለበት፡፡

8.7 (አንቀጽ 6) ማንኛውም የእንስሳት መድኃኒት፣

የመድኃኒቱ ጥሬ ዕቃ ወይም ማሸጊያ ሥልጣን

የተሰጠው አካል ባወጣው ወይም በተቀበለው

ደረጃ የተካተቱ የጥራት መስፈርቶችን

የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡


8.8 አንቀጽ 12(2) ማንኛውም ሰው የሙያ ፈቃድ

የተሰጠው የእንስሳት መድኃኒት ባለሙያ በሌለበት


(የቀጠለ) የወንጀል ተጠያቂነት

8.9 ( አንቀጽ 14 ) ማንኛውም መኖ ወይም የመኖ

ተጨማሪ ነጥረ ነገር ሥልጣን የተሰጠው አካል

ያወጣውን ወይም የተቀበለውን የጥራት

ደረጃዎችን የሚያሟላ መሆኑ አግባብ ባለው

አካል ካልተረጋገጠ በስተቀር ለአገልግሎት

ሊውል አይችልም፡፡

8.10 (አንቀጽ18) ማንኛውም ወደ ውጭ አገር

የሚላክ መኖ በባለሥልጣኑ የተሰጠ የጥራት

ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለው መሆን

አለበት፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም ወደ

አገር ውስጥ የሚገባ የመኖ ምርት በላኪው

አገር የሚመለከተው አካል የተረጋገጠ

የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት

ያለው መሆን አለበት፡፡


 እነዚህን ከላይ ያሉትን ድንጋጌዎች የጣሰ
ከእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር
ስራዎች ጋር የተገናኙ ሥራዎችን የሚያከናውን
ሠራተኛ ወይም ባለሥልጣን በወንጀል ተጠያቂ
ስለሚሆንባቸው ሁኔታዎች (አንቀጽ 26(7) )
7. አዋጁ ወይም መመሪያዎች ካስቀመጡት ውጪ

ማባበያ በመቀበልም ሆነ በዝምድና ወይም በሌላ ግንኙነት

ሳቢያ

ሀ. የመድኃኒት ንግድን በተመለከተ የብቃት ማረጋገጫ

የምስክር ወረቀት ወይም የሙያ ስራ ፈቃድ መስጠት

ማደስ ወይም እንዲታደስ ማድረግ፣ ወይም

ለ. መድሃኒት የጥራት፣ የደህንነት እና እንደአግባቡ የፈዋሽነት

ደረጃ ግምገማ ሳያልፍ አገልግሎት ላይ እንዲውል

መፍቀድ ወይም እንዲፈቀድ ማድረግ ከ10አመት -

15አመት ፅኑ እስራትና በብር 30ሺህ-50ሺህ

ያስቀጣል፡፡

8. ይህም ቅጣት መደለያ በሰጠው ሰው ላይም ተፈጻሚ

ይሆናል፡፡

9. ከዚህ በላይ የገለጸውን ጥፋት በመፈጸም ተግባር ላይ

የተሳተፈ ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት ከመቅረቡ በፊት


አንቀጽ 27፡- ተፈጻሚ ስለማይሆኑ ሕጎች
ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሕግ ወይም
የአሠራር ልማድ በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ
ተፈጻሚነት አይኖረውም
አንቀጽ 28፡- ደንቦችና መመሪያዎች የማውጣት
ሥልጣን
አንቀጽ 29፡- አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ
ጥር 10 ቀን 2004 ዓ.ም
ተያያዥነት ያላቸው ሕግጋት
- በ1996 ዓ.ም የተሸሻለው የኢፌድሪ የወንጀል ህግ የከብት በሽታን ማሰራጨትን ግጦሽ መበከልን መርዛማ መድሃኒቶችን
 

ወይም እጾችን ማምረትንና ሌሎችንም ከእስሳት ጤና ጉዳት ጋር የተያያዙ ድርጊቶችን በአንቀጽ 515 እና 525

ተከታዮቹ መሰረት ወንጀል አድርጓል፡፡


አንቀጽ 515
የእንስሳት በሽታን ማሰራጨት

•የቤት እንስሳትን ፣ ዶሮዎችን ፣ ለማዳ አዕዋፋትን ፣በአሣ፣ በንቦች ፣ በመሳሰሉት ላይ በሽታን ያሰራጨ እንደሆነ ወይም

በክፋት ፣ በችለትኛነት አስቦ ከፍ ያለ ጉዳት ያደረሰ፣ እንደነገሩ ሁኔታ በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ወይም በሁለቱም

ይቀጣል ፤
አንቀጽ 518
ግጦሽን መበከል
•የእንስሳት ሕይወትን ወይም ጤና አደጋ ላይ ለመጣል
•መርዛማ ነገሮችን በግጦሽ ቦታ ያሰራጨ ፣
•በጎጂ በሆኑ ነገሮች ግጦሽና መስኩን የበከለ
•በመቀጮ ወይም በቀላል በእስራት ይቀጣል፡፡ ነገሩ ከበድ ያለ ከሆነ ከ 7ዓመት በማይበልጥ እስራት ይቀጣል፡፡
አንቀጽ 525
መርዛማ መድሃኒቶችን ወይም ዕጾችን ያመረተ ፣ ያበቀለ ፣የሰራ ፣የለወጠ፣ የፈበረከ፣ ከ 5 ዓመት በማያንስ ጽኑ እስራት ይቀጣል
ሌሎች ተዛማጅ ሕግጋት
- የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ፣ ይህም
…… ችርቻሮ፣ ጅምላ ንግድ፣ ማምረት እና ሌሎች በኛ አዋጅ
ትርጉም ያልተጣቸውን ከንግድ ጋር የተያያዙ ቃላትን ትርጓሜን
ለማጣቀስ ይረዳናል፡፡

- የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006


ጥያቄ

You might also like