You are on page 1of 30

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን

የምግብ ዘይት አምራች ድርጅቶች የምግብ ደህንነትና ጥራትን


ለማረጋገጥ የውስጥ ጥራት ስርዓት እንዲዘረጉ ለማስቻል የተዘጋጀ
የመነሻ ሰነድ

ጥቅምት 2011

አዲስ አበባ

1|Page
ማውጫ ገጽ
ክፍል አንድ
1.1 አጭር ርእስ……………………………………………………………………………………….…11
1.2 ትርጓሜ………………………………………………………………………………………...........11
1.3 ዓላማ……………………………………………………………………………………….……...…11
1.4 የመመሪያው ተፈፃሚነት ወሰን…………………………………………………………….………..11
1.5 የውስጥ ጥራት ቁጥጥር ሥርዓትን በተቋማት መዘርጋት …………………………………….…11
1.6 የውስጥ ቁጥጥር አባላትን ስለመመደብ……………………………………………………………..11
1.7 የውስጥ ቁጥጥር የሚካሄድባቸው ቀናት……………………..……………………………………..11
1.8 የውስጥ ቁጥጥር ተግባራዊነት ቁጥጥርና ክትትል………………………………….……………..11
ክፍል ሁለት፡ ስለ ማምረቻ አካባቢ
2.1 የምግበ ዘይት ማምረቻ የሚቋቋምበት አካባቢ እና የህንፃ ሁኔታ (Establishment and
Location)………………………………………………………………………….……………………....11
2.2. የምግብ ዘይት ማምረቻ ህንፃ ሁኔታ (Premises and Rooms)…………………………………11
2.2.1 የህንፃ ዲዘይንናአሰራር(Design and Layout)………..………………………………………….11
2.2.2 የምግብ ዘይት ማምረቻ ህንጻ በር፤መስኮት፤ ወለል፤ ግድግዳና ኮርኒስ (doors, windows floor,
wall and ceiling)…………………….………………………………………………………..………...11
2.2.3 ማብራትና አየር ማቀዝቀዣ(Lighting and Ventilation)...………………………………………11
2.2.4 የማመረቻ መሰሪያዎች እና የሰረተኞች ንፅህና መጠበቂያ ና አገልግሎት መስጫ /sanitation
facilites/……………………………………………………………………………………………….…..11
2.2.5 ቆሻሻ ማስወገጃ አገልገሎት መስጫዎች/Drainage system waste disposal facility……...…11
2.2.6 የውሃ………………………………………………………………………………………………...11
2.2.7 የምግብ ዘይት ማምረቻና መለኪያ መሳሪዎች/ Machineries & Measuring
Devices/…………………………………………………………………………………………..………11
2.2.8 ለምግብ ዘይት ማምረት ጥቅም ላይ ስለሚውሉ እንፋሎት፣ የታመቀ ንፋስ /compresed air/፣
ዘይት ሁኔታ……………………………………………………………………………………………….11
ክፍል ሦስት፡ ስለ ሰራተኛ ደህንነት፣ ጤንነትና መገልገዎች (Personal hygiene and employee
facilities)
3.1. የሰራተኞች ንጽህና መገልገያዎች(Employees' Hygiene and facilities)………...……..………11
3.2. የማጽጃ መገልገያዎች (Disinfection facilities)…………………………………………………..11
3.3. የጤና ሁኔታ/ Health status/……………………………………………………..………………..11

2|Page
3.4. የሰራተኛ የግል ንጽህና ሁኔታ/ Personal cleanliness/……………………………..……………11
3.5. ሰልጠና/Training/……………………..………………………………………………….………….11
ክፍል አራት፡ ስለ ምርት አመራረት ሂደት ስርዓት ቁጥጥር
4.1 የምግብ ዘይት አመራረት ሂደት ስርዓት ቁጥጥር (Processing and Operational
control)……………………………………………………………………………………………….……11
4.1.1ለምግብ ምርት አመራረት ስለሚያስፈልጉ የአሰራር ስርዓት ስለማዘጋጀት……………………11
4.2.2 ስለ ማጣቀሻ አጠቃቀም (Reference standard)………………………………………………...11
4.2.3 የምግብ ዘይት ጥሬ እቃዎች ቅበላና አያያዝ (ጥሬ እቃ፣የምግበ ጭማሪ፣ማሽጊያ
ማቴሪያል)………………………………………………………………………………………………….11
4.2.4 በቅድመ ማምረት ሊሟሉ ስለሚገባቸው ሁኔታዎች……………………………………………...11
4.2.5 በምግብ ዘይት ማምረት ሂደት ሊደረግ ስለሚገባ ቁጥጥር (In Processing quality
control)…………………………………………………………………………………………………....11
4.2.5.1 የምግበ አደጋ ቁጥጥር/Control of food hazards/…………………………………………..11
4.2.5.2 የሙቀት መጠን ቁጥጥር/Temperature control/……………………………………………11
4.2.5.3 መሳሪያዎችና ማሽነሪ ጥገና/Equipment, tools and machinery maintenance/……….....11
4.2.5.4 የምግብ ዘይት አመራረት ፍሰት ሂደት/Processing of edible oil and Process flow
diagram/…………….…………………………………………………………………………………….11
4.2.5.5 በድጋሚ ስለሚመረቱ ምርቶች ግቦች (Reprocessing products)……….…………………...11
4.2.6 ምርት ስለማሸግና ገላጭ ፅሁፍ አደራረግ…………………………………………………………11
4.2.6.1 ምርትስለ ማሸግ /Packaging/……………………………….………………………………….11
4.2.6.2 ገላጭ ጽሁፍ/Labeling/………………………………………………………………………….11
ክፍል አምስት፡ የጥራትና ደህንነት ቁጥጥር ስለማካሄድ (Finished product safety & quality assurance)
5.1 የላቦራቶሪ ግበዓቶችመሳሪያዎችና ኬምካሎች/Laboratory facilities and equipment and reagents/……11
5.2 ስለ ናሙና አወሳሰድ/Sampling/………………………………………………………………………...11
5.3 ስለ ማጣቀሻ አጠቃቀም/Standard/…………..……………………………………………………….11
5.4 ምርመራ/Analysis/………………………………………………………………………………………..11
5.5 ስለ ጥሬ እቃዎች አቀባበል፣ ምርት ምርመራናምረትን ማሰራጨት/Ingredient receiving, product
holds and releases/ ………..………………………………………………………………………………….11
5.6 መጠባበቅያ ናሙና/Retention product/………………………..…………………………………….11
5.5 ማረጋጋትና የምርት ቆይታ ጊዜ/Stability and shelf life/…..…….……………………………………..11
5.6 ስለ ውጫዊ ላቦራቶሪ/External laboratories/……...…………………………………………………….11
3|Page
ክፍል ስድሰት፡ ስለማከማቸትና ማጓጓዝ (Storage and transportation)
6.1 ግበዓት፤ኬሚካሎችና ምርትን ስለ ማከማቸት/Chemicals, materials and product storage/….11
6.2. ምርትንራ ስለ ማጓጓዝና ስለ ማሰራጭጨት……………………………………………………….11
ክፍል ሰባት የውስጥ ጥራት ቁጥጥር (Internal Audits/self inspections)
ክፍል ስምንት፡ ስለ ኮንትራት /Sub-contracting/
ክፍል ዘጠኝ፡አስፈላጊ የአሰራር ሥርዓት ሰነዶች እና መረጃ ስለመያዝ (Document management)
9.1. አስፈላጊ የአሰራ ሥርዓት ሰነዶች………………………………………………………….……….11
9.1.1. ምግብ ከገበያ ላይ ስለመሰብሰብ/Product withdrawal and recall procedure/…………..…..11
9.1.2. የጥራትና ደህንነት ጉድለት ያለበት ጥሬ ዕቃና ምርት አያያዝ/ Nonconforming product
handling procedure/……………………………………………………………………………….....…11
9.1.3 ስለ ቅሬታ አቀባበል/Complaint handling procedures/………………………………………..11
9.1.4 የድህረ ገበያ ቅኝት ስርዓት ስለመዘርጋት (PMS)……………………………………………….11
9.2 ስለ ሰነዶች አያያዝ/ Document and records management/…………………………………..11
ክፍል አስር፡ የሐይጅንና አካባቢ ጤና አጠባበቅ
10.1. የሕንጻና የማምረቻ መሳሪያዎች ንጽህና አጠባበቅ…………………………………………….…11
10.2. የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አሰባሰብ፣ አያያዝ፣ አጓጓዝ እና አወጋገድ…………………………..……11
10.3. የፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝ፣ ማቆያ (ማከም) እና አወጋገድ………………………………………...…11
10.4. የነፍሳት እና የቆርጣሚ እንስሳት ቁጥጥር/Pest and rodent control system/…………..…11
ክፍል አስራ አንድ፡ ስለ ሰው ኃይልና ስልጠና
11.1. በተቋሙ ሊኖሩ ስለሚገቡ ባለሙያዎች………………………………………………….….11
11.2. ስለሚሰጠው ስልጠና………………………………………………………………….……....11
ክፍል አስራ ሁለት፡ ምግብ ስለማስተዋወቅ

4|Page
ክፍል አንድ

1 መግቢያ

በምግብ ዘይት ማምረት ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች የሚያመርቱት ምርት ጥራትና ደህንነት


ለማረጋገጥ የሚያስችል የምግብ ዘይት ማምረቻ ተቋማት የጥራትና ደህንነት ማረጋገጫ ስርዓት
ዝርጋታ መስፈርት ማዘጋጀት በማስፈለጉ፤

በዘመናዊ የምግብ ደህንነት ቁጥጥር ውስጥ የምግብ ዘይት ጥራትና ደህንነት ማረጋገጥ ስራ የአንበሳው
ድርሻ የምግብ አምራች ድርጅቱ ሲሆን ይህ ደግሞ ስርዓትን መሰረት ያደረጉ እና በየጊዜው
ውጤታማነታቸውን እየመዘገቡ ክትትል ማድረግን የሚጠይቅ ሲሆን ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት
የቅድመ መከላከል ተግባራት ናቸው፡፡

መመሪያው ማንኛውም የምግብ ዘይት ማምረቻ ተቋም በማምረት ሂደቱ የምግብ ዘይት ደህንነትና
ጥራት ከማስጠበቅ አኳያ ሊዘረጋው የሚገባውን የምግበ ዘይት ማረጋገጫ የአሰራር ስርዓት ምን ሊሆን
እንደሚገባ የያዘ ሲሆን መስፈርቱ የማይመለከተው ከሆነ ይህንኑ በግልጽ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ
ማሳወቅ የተቋሙ ኃላፊነት ሲሆን በምትኩ ሌሎች መስፈርቶች እንደስፈላጊነቱ ሊካተቱ ይችላሉ፡፡

በምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 661/2002 አንቀፅ
55(3) እና በምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር የሚኒስትሮች ምክር ቤት
ደንብ ቁጥር 299/2006 አንቀጽ 4(1) መሰረት የምግብን ጥራትና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል
የምግብ ዘይት ማምረቻ ተቋማት የምርት ጥራትና ደህንነት ማረጋገጫ ስርዓት ዝርጋታ መስፈርት
መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡
1.1 አጭር ርእስ
ይህ መመሪያ የምግብ ዘይት ማምረቻ ተቋማት የጥራትና ደህንነት ማረጋገጫ ስርዓት ዝርጋታ
መስፈርት መመሪያ ቁጥር ------/2011” ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡
1.2 ትርጓሜ/Terminology/
1. በአዋጅ ቁጥር 661/2002 እና በደንቡ ቁጥር 299/2006 ላይ የተሰጡ ትርጓሜዎች እንደተጠበቁ
ሆነው የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠዉ ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ዉስጥ፡-
2. “በካይ ነገር” ማለት ከምርቱ ተፈጥሯዊ ይዘት ውጪ ሆኖ በህብረተሰብ ጤናና ደህንነት ላይ ጉዳት
የሚያስከትል ባዕድ ነገር ነው፤

5|Page
3. "የምግብ ደህንነት"፡- ማለት አንድ ምግብ ማንኛውም ምግብን ሊበክሉና የሰውልጅ ጤናን
ሊያውኩ ከሚችሉ ነገሮች ነጻ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡
4. "ኦዲት ኢንስፔክሽን"ማለትየውስጥ ጥራት ስርአት በዘረጉ ድርጅቶች ላይ በባለስልጣን
መስሪያቤቱ ተቆጣጣሪዎች የሚደረግ የውስጥ ጥራት ስርአቱ መዘርጋቱና መተግበሩ
የሚፈተሽበትና የሚረጋገጥበት እንዲሁም በተገኙ ክፍተቶች ላይ ከድርጅቱ ኃላፊዎች ጋር
በመወያየትና ግብረመልስ በመስጠት በቀጣይ ድርጅቱ የምግብ ደህንነትና ጥራትን
በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲያረጋግጥ የሚደረግበት የአሰራር ስርአት ነው፡፡
5. የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት"ማለት ተቋማትየራሳቸው ባለሙያ በመመደብ በተለይከምግብ
ደህንነትና ጥራት ጋር በተያያዘ በሚያስመጧቸው ወይም በሚያከፋፍሏቸው ምግቦች ላይ
ከምግብ ደህንነትና ጥራት አንጻር ባለስልጣኑ ከሚያስቀምጣቸው መስፈርቶች አንጻር
ራሳቸውን በራሳቸው ቁጥጥር የሚያካሂዱበት አሰራር ነው፡፡
6. Crude Oil means unrefined oil which contains impurities that make it unhealthy for consumption.
7. Bleaching means the removal of color producing pigments from fats and oils during the refining
procedure usually through the use of an adsorbent.
8. Degumming means the treatment of additives that are added to crude oil to remove impurities with the
use of dilute acids or soda
9. Deodorization means usage of steam to remove unwanted odors from degummed oil.
10. Fortificant is the micronutrient that is added to a food.
11. Hazard is a risk factor present in food in any specific part of the supply chain that can cause harmful
health effects
12. Quality assurance is the process of planning, documenting and agreeing on a set of guidelines those are
necessary to prevent contaminants from entering into the food product right from the procurement of raw
materials to the distribution of the finished goods.
13. Quality control: All activities that are designed to determine the level of quality of the delivered food
product. It involves verification and comparison of the output to desired quality levels.
14. Rancidity: The presence of an off flavor or odor in oil due to oxidation.
15. “ባለስልጣን” ማለት የኢትዮጽያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር
ባለስልጣን ነው፡፡

6|Page
16. “አዋጅ’’ ማለት የኢትዮጵያ የምግብ፤ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ
661/2002 ነው፡፡
17. “ደንብ” ማለት የኢትዮጵያ የምግብ፤ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ደንብ
ቁጥር 299/2006 ነው፡፡
18. “ሰው’’ ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፡፡
19 በዚህ መመሪያ በወንድ ጾታ የተገለጸ ማንኛውም አገላለጽ ሴትንም ይጨምራል፡፡

1.3 የውስጥ ቁጥጥር ዓላማ


 ጥራትን ደህንነቱ የተረጋገጠ ምግብ ዘይት ለህብረተሰቡ ለማድረስ ቁጥጥሩን በተቆጣጣሪዎች
ብቻ ከመቆጣጣር ባሻገር አምራች ድርጅቶች በራሳቸው የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት እንዲዘረጉ
ለማድረግና የቁጥጥር ስርዓቱን የበለጠ ለማጠናከር ነው
 የዚህ ሰነዱ ዓላማ ለህብረተሰቡ የሚያቀርቡ የምግብ ዘይት አምራቾች ድርጅቶች የሚያምርቱት
ምርት በዘሌቀታዊነት ጥራትና ደህንነት አረጋግጠው በራሳቸው ማቅረብ እንዲችል የሚያስችል
የውስጥ የአሰራር ስረዓት እንዲዘረጉና ሊያሟሉት የሚገባውን መስፈርት አውቀው እንዲተገብሩት
በማድረግ እና በተዘረጋው የአሰራር ስርዓት በተቀመጠው መስፈርት መሠረት በተቆጣጣሪ አካል
የኦዲት ቁጥጥር ማድረግ እንዲቻል ነው፡፡
1.4 የመመሪያው ተፈፃሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ በሀገሪቱ በምግብ ዘይት በማምረት ሥራ ላይ በተሰማሩ አምራች ተቋማቶች ላይ
ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
1.5 የውስጥ ጥራት ቁጥጥር ስርዓትን በተቋማት መዘርጋት

የምግብ ዘይት አምራች ድርጅቶች የምርት ጥራትና ደህንነት እንዲጠብቁ ያለባቸውን ኃላፊነት
በአግባቡ እንዲወጡ ለማድረግና ጤናማ የሆነ ምርት ለህበረተሰቡ እንዲያሰራጩ ያስችላል፡፡ይህ
የውስጥ ጥራት ስርዓት ቁጥጥሩን ቀልጣፋና ተደራሽ እንዲሁም ውጤታማ ከማድረግ ባሻገር የድርጅቱ
ተክኒካል ሀላፊም ሆነ በድርጅቱ ውስጥ የሚመለከተው አካል ለሚከሰተው ችግር ሀላፊነትና ተጠያቂነት
እንዲወስዱ በማስቻል ተቋሙ ውስጥ የምግብ ጥራትና ደህንነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡
የተዘረጋውን ስርዓት በተፈለገው መልኩ ስለመዘርጋቱ ለማረጋገጥ ብሎም ድርጅቱ የተዘረጋውን
ስርዓት እየተጠቀመበት ስለመሆኑ ድርጅቱን በምግብ ደህንነት በኦዲቲንግ መከታተል እና
በእንስፔክሽን ወቅት በሚገኘው ጉድለቶች ላይ ትኩረት ተሰጥተው እንዲሰሩ በማድረግ በምግብ
ደህንነትና ጥራት ቁጥጥር ያለው አሰራር ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንዲችሉ ይረዳል፡፡
በተጨማሪም የቁጥጥር ስራው በሀሉም ድርጅቶች ላይ ወጥ የሆነ ስርዓት ኖሮት እንዲመራ ያስችላል፡፡

7|Page
1.6 የውስጥ ቁጥጥር አባላትን ስለመመደብ
በተቋሙ ውስጥ የውስጥ አሰራርን ስርዓትን ለመዘርጋት ቢያንስ አራት ወይም ከአራት በላይ ሆኖ
ከምርት ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው ባለሙያዎች እንደ ምርት ክፍል ኃላፍ፤የጥራት ቁጥጥር
ኃለፍ፤ የአካባቢ ጤና ባለሙያ እና ሌሎች ከምርቱ ጋር ቀጥታ ተዛማጅ የሆኑ ባለሙያዎች ሊመደቡ
ይገባል፡፡ ይህን የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት በኃለፊነት እንዲመራ የሚጠበቀው የተቋሙ የቴክኒክ ኃለፊ
ቢሆን ይመረጣል፡፡ ሆኖም እንዳአስፈላጊነቱ ከቴክኒክ ሃላፊው ጋር ተመሳሳይ ወይም ከዛ በላይ የሙያ
ችሎታ ያለውና ከምርቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ባለሙያ የውስጥ ቁጥጥሩን በሃላፊነት ሊመራ
ይችላል፡፡የሚመደቡት ባለሙያዎች የስራ ዝርዝር በተለይ ከውስጥ ቁጥጥሩ ጋር ተያይዞ
የሚያከናውኑት ተግባር በግልጽ ተጽፎ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
1.7 የውስጥ ቁጥጥር የሚካሄድባቸው ቀናት
ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት የውስጥ ጥረት ቁጥጥር በየስንት ጊዜው ማካሄድ
አንዳለበት የአሰራር ስርዓት ልኖረው ይገባል፡፡ በአሰራር ስርዓት ላይ በዝርዝር በቀናቱ የሚከነወነው
ተግባርና በዕለቱ ተግባራዊ የማይሆን ከሆነ በምን ምክንያት ሊካሄድ እንዳልቻለና በሌሎች ቀናት
ለማካነወን የተወሰነበት ሌሎች በእለቱ መሰራት ስላለባቸው ስራዎች በዝርዝር የሚገልጽ መሆን
ይኖርበታል፡፡
1.8 የውስጥ ቁጥጥር ተግባራዊነት ቁጥጥርና ክትትል
ማንኛውም ተግባር አስፈላጊው የክትትልና ግምገማ ስራ የማይከናወንበት ከሆነ የተፈለገውን አላማ
ላይ ላይደረስ ይችላል፡፡ ስለሆነም ድርጅቱ እንዲተገብረው የቀረጸው የቁጥጥር የተቀመጠው የአሰራር
ስርዓት ተግባራዊ ስለመሆኑ በየጊዜው የክትትልና የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት አለበት፡፡ የክትትልና
የቁጥጥር ስርዓቶቹ በሚመለከተው በተቆጣጣሪ አካል ስጠየቅ ድርጅቱ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
ክፍል ሁለት፡ ስለ ማምረቻ አካባቢ

2 የምግበ ዘይት ማምረቻ የሚቋቋምበት አካባቢ እና የህንፃ ሁኔታ (Establishment and


Location)

2.1 የምግበ ዘይት ማምረቻ የሚቋቋምበት አካባቢ


2.1.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት ማምረቻ ተቋማት የሚቋቋምብት ቦታ የምርቱን ጥራትና ደህንነት
ሊያጓድሉ ለሚችሉ በካይ ነገሮች እናደ ጎርፍ፣ረግረጋማ ቦታና ናዳ ተጋላጭ መሆን የለበትም ከነብሳት
መራብያ፣ከቆሻሻ መጣያ፣መጥፎ ሽታ፣ከኬሚካል ወይም መርዝ ከሚከማችበትና በአጠቃላይ ምግብን
ሊበክሉ ከሚችሉና በምርት ጥራት እና ደህንነት ላይ አደጋ ለሚያስከትሉ ነገሮች ተጋላጭ መሆን
የለበትም

8|Page
2.1.2 የምግብ ዘይት ማምረቻ ድርጅቱ ቅጥር ግቢው በዘላቂነት ከአካባቢው ሊነሱ ወይም ሊፈጠሩ
ለሚችሉ በካይ ነገሮች፣ ለእንስሳት ወይም ለነብሳትን የሚከላከልበትና ምቹ የመራቢያ ሁኔታን
የማይፈጥሩ የአሰራር ሥርዓቶች መዘርጋት አለበት፣
2.1.3 በአሰራር ስርዓቱ መሰረት ተግራዊ መደረጉ መረጃ ተጠናቅሮ መያዝ አለበት
2.2 የምግብ ዘይት ማምረቻ ህንፃ ሁኔታ (Premises and Rooms)
2.2.1 የህንፃ ዲዘይንና አሰራር (Design and Layout)
2.2.1.1 ማንኛውም የምግበ ዘይት ማምረቻ የህንፃ ስፋት እንደሚያመርተው ምርት ዓይትና መጠን
በቂ የማምረቻ ቦታ፣ ማከማቻዎች ቦታ፣ ጥራት ቁጥጥር ላቦራቶሪ የተበላሹና ጥቅም ላይ የማይውሉ
ምግቦች ማቆያ ቦታ የቁሳቁስና ኬሚካሎች ማከማቻ እና የሰራተኞች መታጠቢያና መፀደጃ ክፍል
የያዘ ሆኖ የሚከተሉትን ሁኔታዎች ያሟላ መሆን አለበት፡-
2.2.1.2 የማምራቻ ህንፃው የሚገነበባት ግብዓት በሚመረተው ምግብ ጥራትና ደህንነት ላይ ተፅእኖ
የማይፈጥር መሆን አለበት፣
2.2.1.3 የህንፃው ዲዛይንና አሰራር የህንፃውን ንጽህ አጠባበቅ፣ እርስ በርስ ብክለት፣ የምርት ፍሰት
እና የጥገና ስራን ለማከናወን በሚያስችል መለኩ የተገነባ መሆን አለበት፣
2.2.1.4 የፍሳሽ ፣ የኤልክትሪክ፣ የውሃ እና ሌሎች መስመሮች ዝርጋታ የአመራረት ሂደቱን በሚጻረር
እና ምርቱን ሊበክል በሚችል አግባብ መሆን ለበትም፣
2.2.1.5 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት የጥሬ እቃ መቀበያና ያለቀለት ምርት መጫኛ
ቦታ አሰራር ተግባሩን ለማከናውን ምቹ ሆኖ ምርቱን ለብክለት በማያጋልጥ እና ንጽሀናውን
ለመጠበቅ በሚያስችል ሁኔታ የተገነባ መሆን አለበት
2.2.1.6 የህንጻው ንጽህና አጠባበቅ፣ የጥገና አካሄድ የአሰራር ስርዓት ሊኖረው ይገባል፣
2.2.1.7 የህንፃው ንጽህና አጠባበቅ እና የጥገና ስራ በተዘረጋው አሰራር ስርዓት አግባብ መሆኑን
ክትትል በማድረግ መረጃ መያዝ አለበት
2.2.2 የምግብ ዘይት ማምረቻ ህንጻ ወለል፤ ግድግዳ፤ ኮርኒስ፤በር፤መስኮት (floor, wall
ceiling, doors and windows)
2.2.2.1 ማንኛውም የምግበ ዘይት አምራች ድርጅት ወለል፤ ግድግዳ እና ጣሪያ የሚመረተውን ምርት
ጥራትና ደህንነት ላይ ተፅእኖ በማይፈጥር ሁኔታ የተገነባ መሆን አለበት
2.2.2.2 ማንኛውም የምግብ ምርት አምራች ድርጅት ወለል፤ግድግዳና ጣሪያ አሰራር የሚመረተውን
ምግብ ሊበክሉ የሚችሉ በካይ ነገሮችን ለመያዝ የሆና ለተባይ መረቢያነት ምቹ መሆን የለበትም
2.2.2.3 የህንጸው ወለል፣ ግድግዳና ጣሪያ ልሙጥ፣ ያልተሰነጣጠቀ ቆሻሻና ውሃ የማያቁር በቀላሉ
ሊፀዳ የሚችልና እርጥበት የማይዝ መሆን አለበት፣

9|Page
2.2.2.4 ግድግዳ፣ወለልና ጣሪያ የሚገናኙበት የመገጣጠሚያ ቦታዎች በካይ ነገሮችን የማይዝና ለተባይ
መረቢያነት ምቹ በሆነ አግባብ መገኘት የለበትም፣
2.2.2.5 የህንፃው በርና መስኮት በቂ የአየር ዝውውርና ብርሃን በሚሰጡ መልኩ የተገነቡ ሆነው
የምግቡን ጥራትና ደህንነት ለያጓድሉ የሚችሉ ነብሳት፣ ቆርጣሚ እንስሳት ወይም ሌሎች በካይ
ነገሮችን ወደ ውስጥ የማያስገቡ መሆን አለበት፣
2.2.2.6 የህንጻው ወለል፤ ግድግዳ፤ ጣሪያ፤በር እና መስኮት የንፀህና አጠባባቅ ስርዓት ሊዘረጋ ይገባል
2.2.2.7 በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ተግባራዊነቱን መከታተል እና መረጃ አጠናቅሮ መያዝ አለበት
2.2.3 ማብራትና አየር ማቀዝቀዣ(Lighting and Ventilation)
2.2.3.1 በክፍሎቹ ውስጥ በቂ የሆነ ብርሃንና የአየር ዝውውር ሊኖረው ይገባል
2.2.5 ቆሻሻ ማስወገጃ አገልገሎት መስጫዎች /Waste disposal facility/

2.2.5.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት ክፍሎች ዝግ ፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መስመር

ልኖረው ይገባል
2.2.5.2 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት ፈሳሽና ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ ለመያዝና
ለማስወገድ የሚያስችል በቂ ቦታና የተሟላ መሳሪያ ሊኖረው ይገባል፣
2.2.5.3 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት ፈሳሽ ቆሻሻ ማከሚያና የተሟላ የፍሳሽ

የደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ ወይም ኢንስነሬተር ልኖረው ይገባል


2.2.5.4 በምግብ ዘይት ማምረቻ ድርጅቱ የሚገኙ ማንኛውም የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታች፣ የፍሳሽ
መስመሮች የሚመረተውን ምግብ ሊበክሉ በማይችሉ መልኩ መጽዳት፣ መያዝ እና መጠገን አለበት፣
2.2.5.5 እንደቆሻሻው ባህሪ ለይቶ እና አደራጃቶ ለመያዝ በሚያስችል የየራሳቸው መለያ ምልክት
/መገለጫ/ ሊኖራቸው ይገባል፣
2.2.5.6 በምግብ ዘይትማምረቻ ድርጅቱ የሚገኙ ማንኛውም የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎች፣ የፍሳሽ
መስመሮች ለጎጂ ተዋስያንና ነብሳት መራቢያና እንስሳቶችና አእዋፋትን የሚስቡ መሆን የለባቸውም፣
2.2.5.7 በምግብ ዘይት ማምረቻ ድርጅቱ የሚገኙ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎች፣ የፍሳሽ መስመሮች
ምግብን እንዳይበክሉ አግባባዊ የአያያዝና አጠባበቅ ሥርዓት መኖር አለበት
2.2.6 ውሃ
2.2.6.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት ውስጥ ለተለያዩ ግልጋሎት የሚውል ውሃ
የሚመረተውን ምግብ ጥራትና ደህንነት የማያጓድል ሆኖ የሚከተሉትን ነጥቦች የሚያሟላ መሆን
አለበት፡-

10 | P a g e
2.2.6.2 የውሃ ምንጩ የሚታወቅ መሆን አለበት
2.2.6.3 ለአገልግሎት የሚውል ውሃ ንጹህ እና የመጠጥ ውሃ ደረጃን የሚያሟላ መሆን በላቦራቶሪ
የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፤
2.2.7 የምግብ ዘይት ማምረቻና መለኪያ መሳሪዎች/ Machineries & Measuring Devices/
2.2.7.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት ለሚያመርተው ምግብ የሚያለግሉ እና
ለሚመረተው ምግብ ዓይነትን መጠን በቂና ተስማሚ ሆኖ ከምርት ሂደቱ ጋር ንክኪ ያላቸው
ማናቸውም መሳሪያዎችና ማሽኖች ከዝገት የፀዱና ከስቴንለስ ስቲል ወይም በምግቡ ላይ ምንም
ዓይነት ለውጥ ሊያስከትል ከማይችል ማተሪያል /food grade/ የተሰሩ መሆን አለባቸው
2.2.7.2 በድርጅቱ ውስጥ የምግብ ዘይት ማምረቻ መሰራይዎቹ ለምግብ ማምረት ተስማሚ/food
grade/ ስለ መሆናቸው ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ ይኖርበታል
2.2.7.3 የማሽነሪዎቹ ተከላና ዲዛይን ለንፅህና አጠባበቅና ጥገና ምቹ በሆነና የመበከል አደጋ
ሊያስከትል በማይችል መልኩ የተተከሉና የተዘረጉ መሆን ይኖርበታል
2.2.7.4 የልኬት (Calibration) ማረጋገጥ የሚያስፈልጋቸው ማሽነሪዎችና መለኪያ መሳርያዎች
ተለይተው የአሰራር ስርዓቱ በሚፈቅደው መሰረት ልኬታቸው ከማነፃፀርያ ደረጃ አንፃር በማረጋገጥ
መስተካከል አለበት፡፡
2.2.7.5 የማምረቻና መለኪያ መሳሪያዎች አግባባዊ ልኬት ማረጋገጥ፤ ጥገና ለማድረግና ንጽህና
ለመጠበቅ የሚያስችል መርሃ ግብርን ያከተተ የአሰራር ስርዓት መኖር አለበት፡፡
2.2.7.6 የማምረቻና መለኪያ መሳሪያዎች የአሰራር ስርዓቱ በሚፈቅደው መሰረት ንፅህናቻው
ስለመጠበቁ፤ ወቅታዊ የልኬት ሁኔታቸው ስለመረጋገጡ፣ ጥገና ስራዎች ስለመደረጉ የሚያረጋግጥ
መረጃ ተደራጅቶ መያዝ አለበት፡፡
2.2.7.7 የማምረቻና መለኪያ መሳሪያዎች ማሽነሪዎችና መገልገያ መሳሪዎች የሚገኙበት ወቅታዊ
ሁኔታ ሊያሳይ የሚችል ገላጭ ጽሁፍ (Label of Machine Status) ሊኖራቸው ይገባል፡፡
2.2.7.8 ከማምረቻ መሳሪያዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ሰራተኞች ስለ መሳሪያዎቹ
አጠቃቀም፣ አያያዝና ደህንነት አጠባበቅ በተመለከተ በየጊዜው ስልጠና መውሰድ አለባቸው፡፡
2.2.7.9 ሰራተኛው ለአደጋ ሊዳርጉ የሚችሉ የማምረቻ መሳሪያዎች አስፈላጊው የአደጋ መከላከያ
ሽፋን ሊደረግላቸውና እንዳስፈላጊነቱ ሰራተኛው ሊያደርገው ስለሚገባ ጥንቃቄ ማሳሰቢያ ገላጭ ፅሁፍ
ሊኖረው ይገባል፡፡
2.2.8 ለምግብ ዘይት ማምረት ጥቅም ላይ ስለሚውሉ እንፋሎት፣የታመቀ ንፋስ /Compresed
air/ዘይት ሁኔታ

11 | P a g e
2.2.8.1 ቅባቶች /Lubricants/
2.2.8.1.1 በምግብ ዘይት ማምረቻ ተቋሙ ውስጥ ከምግቡ ጋር ቀጥተኛ ንክኪ ያለቸው የምርት
ማምረቻ መሳሪያዎችን መገጣጠሚያ ለማለስለስ አገልግሎት የሚውሉ ቅባቶች የምግብ ደረጃ /food
grade lubricants/ መሆን ይኖርባቸወል
2.2.8.1.2 አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቅባቶች በሚመረተው ምርት ጥራትና ደህንነት ላይ ብክለት
በሚፈጥሩ መልኩ መያዝና መከማቸት የለበትም
2.2.8.1.3 ቅባቶቹ ለምግብ ተስማሚ ስለመሆናቸው የምገልጽ መረጃዎቸ ልኖረው ይገባል
2.2.8.1.4 አገልግሎት ላይ ስለሚውሉት ቅባቶች አያያዝና አግባባዊ አጠቃቀም የአሰራር መመሪያ
ሊኖረው ይገባል
2.2.8.1.5 በማለስለሻ ቅባቶቹ አምራች ድርጅቱ በሚያስቀመጠው የአጠቃቀም መመሪያ መሰረት
ጥቅም ላይ መዋሉ በየጊዜው መረጃ አደራጅቶ መያዝ አለበት፣
2.2.8.2 የምግብ ዘይት ማምረት ጥቅም ላይ ስለሚውሉ እንፋሎት፣ የታመቀ ንፋስ
/compresed air/፣ ዘይት ሁኔታ
2.2.8.2.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት ማምረቻ ተቋማ ለምርት አገልግሎት ሂደቱ የሚጠቅም
እንፋሎት፣ የታመቀ ንፋስ /Compresed air/፣ ዘይት እና ሌሎች በማንኛውም መልኩ ምግቡን
ለብክለት ማጋለጥና እርስ በርሳቸው ለመለየት የሚያስችል ምልክት ሊኖራቸው ይገባል፣
2.2.8.2.2 ወቅቱን የጠበቀ ጽዳትና ጥገና ሊደረግላቸው የሚያስችል አሰራር ስርዓት ሊኖራቸው ይገባል
2.2.8.2.3 በአሰራር ስርዓቱም መሰረት ተግባራዊ ስለመደረጋቸውን መረጃ ማደረጀት አለበት፣
ክፍል ሦስት
3 የግል ንፅህና እና የሰራተኞች መገልገያዎች (Personal hygiene and employee facilities)
3.1 የሰራተኞች ንጽህና መገልገያዎች (Employees' Hygiene and facilities)
3.1.1 የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት በቂ የሆን መገልገያዎች እንደ መፀዳጃ ቤት፣የእጅ
መታጠቢያ፣የገላ መታጠቢያ፣የልብስ መቀየሪያ፤ የመመገቢያ ክፍል፤ የመጀመሪያ ህክምና መስጫና
የላውንደሪ አገልግሎት ልኖረው ይገባል
3.1.2 ሁሉም የሰራተኞች ንጽህና መገልገያዎች በቂ የሆነ የብርሃንን የአየር ዝውውር ልኖረው ይገባል
የሰራተኞች የደህንነት መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ነጭ ጋዎን፣ጓንት፤የፀጉር መሸፈኛ፣የአፍ ማስክና የመሳሰሉት
ሊኖሩው ይገባል፡፡
3.1.3 በድርጅቱ ውስጥ ለሚከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎችና የጤና ችግሮች ለመከታተልና ለማከም
የሚያስችል ስርዓት ሊኖረው ይገባል፡፡

12 | P a g e
3.1.4 ድርጅቱ የድንገተኛ እሳት አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያናየመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መስጫ
መሳሪያ ሊኖረው ይገባል/first aid kit/
3.1.5 ወቅቱን የጠበቀ የሰራተኞች ንጽህና መገልገያዎች ጽዳትና ጥገና ሊደረግላቸው የሚያስችል
የውስጥ የአሰራር ስርዓት ሊኖራቸው ይገባል
3.1.6 በአሰራር ስርዓቱም መሰረት ተግባራዊ ስለመደረጋቸውን መረጃ ማደረጀት አለበት
3.2 የማጽጃ መገልገያዎች (Disinfection facilities)
3.2.1 የምግብ ዘይት አምራች ተቋማት በቂ የሆነ የፅዳት እና የእቃ ማጠቢያ ኬሚካሎች ልኖረው
ይገባል
3.2.2 ለጽዳት የሚያገለግሉ ኬሚካሎች ብክለት እንዳይፈጥሩ በተከለለ ቦታ ተለይተው መቀመጥ
ይኖርባቸዋል
3.2.3 የማጸዳቻ ኬሚካሎች የአጠቃቀም የሚያስችል የውስጥ የአሰራር ስርዓት ሊኖራቸው ይገባል
3.2.4 በአሰራር ስርዓቱም መሰረት ተግባራዊ ስለመደረጋቸውን መረጃ ማደረጀት አለበት
3.3 የጤና ሁኔታ/Health Status/
3.3.1 የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት ከሚመረተው ምግብ ጋር ንክኪ ያለቸው ሠራተኞች ስራ
ከመጀመሩ በፊት ብያንስ በየ ስድስት/6/ ወር ህጋዊ በሆነ የጤና ተቋም አስመርምሮ በምግብ
ምክንያት ከሚተላለፉ በሽታዎች ነፃ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ለዚህም ማረጋገጫ
ማሰረጃ ሊኖው ይገባል፡፡
3.4 የሰራተኛ የግል ንጽህና ሁኔታ/Personal Cleanliness/
3.4.1 የምግብ ዘይት አምራች ሰራተኞች ምርት ማምረት ከመጀመራቸው በፍት የግል ንጽህናቸውን
ማረጋገጥ አለባቸው
3.4.2 የሰራተኞች የደህንነት መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ነጭጋዎን፤የፀጉር መሸፈኛ፣የአይን መነፅር፣የአፍ
ማስክና የመሳሰሉት ልኖራቸው ይገባል፡፡
3.4.3 የግል ንፅህና አጠባበቅ የሚያስችል የውስጥ የአሰራር ስርዓት ሊኖራቸው ይገባል
3.4.4 በአሰራር ስርዓቱም መሰረት ተግባራዊ ስለመደረጋቸውን መረጃ ማደረጀት አለበት
3.5. ሰልጠና/Training/
3.5.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት በምርት ማምረት ስራ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን
ስራዎች የሚሰሩ ባለሙያዎች የግል ንፅህ እና የመልካም አመራረት ስርዓት መመሪያዎችን በግልጽ
ግንዛቤ መፍጠሪ አለበት
3.5.2 ማንኛውም ከማምራት ስራ ጋር ተጓዳኝ የስራ ሁኔታ የሚያከናውን ሰው በስራ ገበታዊ ቦታ
የአደገኛ መድኋኒቶችና እፆችን አጠቃቀም የሚከለክል አሰራር ስርዓት በመዘርጋት ተፈፃሚነቱን
ክትትል ማድረግ አለበት፣
13 | P a g e
3.5.3 ድርጅቱ ምርት በምመረትበት ወቅት አግባብነት ያሌላቸው ባህሪያት እንደ ምግብ መብላትም
ሆነ መጠጣት፣ ማስቲካ ማኘክ፤ ጫት መቃም፤ ትንቧሆ ማጬስ፤ መተኛት እና ሌሎች መሰል
ባህሪያትን ተፈፃሚነት የሚከለክሉ አሰራር ስርዓቶች ላይ ለባለሙያ ግንዛቤ በመስጠት ተግባራዊ
ማድረግ አለበት፣
3.5.4 ሠራተኞች በስራ ላይ እያሉ ስለ ምግብ ጥራትና ደህንነት ጠብቆ የምርት አመራረት ሂደት፣
የምርት አያያዝና አከመቻቸት፣ ስለ ምግብ መልካም የንጽህና አጠባበቅ ዙሪያ መደረግ ስላለበት
ጥንቃቄ እና የመሳሰሉ አጫጭር ስልጠናዎችን የባለሙያዎችን ክፍተት ትንተና በመስራት በእቅድ
በመያዝ ስልጠና መስጠት እና የተሰጡ ስልጠናውችን መረጃ በአግባቡ መያዝ እና በስልጠናው
የመጣውን ለውጥ በየጊዜው እየተነተኑ መሄድ ያስፈልጋል፡፡
3.5.5 ማንኛውም የምግብ አምራች ድርጅት በምግብ ማምረት ጋር የሚሰራ በለሙያ እና ሀላፊ
የምግብን ጥራትና ደህንነት አሰጠብቆ ለማምረት የሚያስችል መሰረታዊ ስልጣናዎችን በእቅድ
በመያዝ ተከታታይነት ያለው፣ ስልጠናውን ለመስጠት እውቅና ባለው ተቋም የመሰልጠንና
የስልጠናውን ሁኔታ መረጃ የመያዝ ሃላፊነት አለበት፣
3.5.6 በምግብ አምራች ድርጅቱ ውስጥ ከምርቱ ጋር ቀጥተኛ ንክኪ ያላቸው ሠራተኞች ሥራ
ከመጀመራቸው በፊት ከሰው ወደ ምግቡ በምግብ፣ በምግብ ማምረቻው ቁስና በምርት ማሸጊያ ቁሱ
ንክኪ አማካኝነት ከሚተላለፉ በሽታዎች ነፃ ስለመሆናቸው የሚረጋገጡበትን አሰራር መዘርጋትና
ተግባራዊነታቸውን የሚከታተሉበት አሰራር ሊዘረጉ ይገባል፡፡
3.5.7 ማንኛውም በምግብ ማምረት ስራ ላይ የተሰማራ ሰራተኛ በስራ ጊዜ በማንኛውም ተላላፊ
በሽታዎች ታሞ እንደ ተቅማጥ፣ ትውከትና የመሳሰሉት የተላላፊ በሽታዎች ምልክት እንዲሁም
በተለያየ ምክንያ ቁስል ካለበት በሽታው/ቁስሉ እስኪድን ድረስ ከመደበኛ ስራው ታቅቦ የሚቆይበት
አሰራር ተግባራዊ ማድረግ እና ስለአተገባበሩም የሚሳዩ መረጃዎች አደራጅቶ መያዝ አለበት፡፡
3.5.8 በድርጅቱ ውስጥ ከምርቱ ጋር ቀጥተኛ ንክኪ ያላቸው ሰራተኞች እንደየ ስራው ባህሪያቸው
በስራ ወቅት የደህንነት መጠበቂያ አልባሳት እና የግል ደህንነት መከላከያ መሳሪያዎች ሊጠቀሙ
ይገባል፡፡
3.5.9 ድርጅቱ በማንኛውም ሁኔታ የማምረቻ ቦታውን ለሚጎበኙ ጎብኚዎች በምርቱ ላይ የደህንነትና
ጥራት ችግር እንዳያስከትል ሊደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄና ለጎብኚዎች አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት
መጠበቂያ አልባሳትን አዘጋጅቶ ሊይዝ እና ተግባራዊ ሊያደርገው ይገባል፡፡
3.5.10 ሠራተኞቹ በስራ ወቅት ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ
መሳሪያዎችና አሰራሮች እንደ እሳት አደጋ ማጥፊያ፤ የመጀመሪያ ህክምና እርደታ መስጫ በቂ
ስልጠና መውሰድ አለባቸው፡፡

14 | P a g e
3.5.11 ድርጅቱ በምርት ክፍል ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎች የሰራተኞችን ጤንነት እና የንጽህና
አጠባበቅ እና የደህንነት መጠበቂያ አልባሳትን አጠቃቀም አስመልክቶ የአሰራር ስርዓት ሊዘጋጅ
ይገባል፣ በአሰራር ስርዓቱ መስረትም ተግባራዊነታቸውንም ክትትል በማድረግ እና መረጃ ማጠናቀር
አለበት፣
3.5.12 ድርጅቱ ከምርትም ሆን ምርት ከሚመረትብት እና ከሚታሸግበት ቁስ ቀጥተኛ ንክኪን
በማይኖረው እና እርስ በርስ የመበካከልን/cross contaminations/ ሁኔታ የሚከላከልና የሚቆጣጠር
ስርዓት መዘርጋት እና በተዘረጋው ስርዓት መሰረትበየጊዜው ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ ይኖርበታል፡

ክፍል አራት፡ ስለ ምርት አመራረት ሂደት ስርዓት ቁጥጥር
4.1 የምግብ ዘይት አመራረት ሂደት ስርዓት ቁጥጥር (processing and operational control)
4.1.1 ለምግብ ምርት አመራረት ስለሚያስፈልጉ የአሰራር ስርዓት ስለማዘጋጀት
4.1.1.1 የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት የሚያመርተውን ምርት ጥራትና ደህንነት ለማረጋገጥ
የሚያስችል አጠቃላይ የምርት አመራረትና ጥራትና ደህንነት ማረጋገጥ የአሰራር ስርዓት ሊኖረው
ይገባል፡፡
4.1.1.2 ለእያንዳንዱ የስራ ሂደት ለማስፈፀም የሚያስችልና ከዋናው የአሰራር ስርዓት የሚመነጭ
ቢያንስ የምርት ቀመር ስሌት፤የምርት ማምረቻ መሳሪያዎችና ማምረቻ ቦታዎች ንፅህና አጠባበቅ
ቁጥጥር አሰራር ስርዓት፤የምርት አስተሸሸግና ገላጭ ፅሁፍ አደራረግ አሰራር ስርዓት፤የምርት
አከመቻቸት፤ አጓጓዝና ስርጭት አሰራር ስርዓት ሰነዶች ማዘጋጀት አለበት፡፡
4.1.2 የመግብ ዘይት ጥሬ እቃዎች ቅበላና አያያዝ (ጥሬ እቃ፣የምግበ ጭማሪ፣ማሽጊያ
ማቴሪያል)
4.1.2.1 የምግብ ዘይት ለማምረት አገልግሎት የሚውሉ ጥሬ እቃዎች የተቀመጠውን ብሔራዊ ደረጃ
ደረጃ የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡
4.1.2.2 ምርት በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውጣለት ከሆነ እንደአግባቡ የአህጉራዊ ወይም የኮዴክስ ደረጃ
የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
4.1.2.3 ማንኛውም የምግብ ማሸጊያ እንደ ምግቡ ዓይነት ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀው ብሔራዊ የምግብ
ማሸጊያ ደረጃ የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡
4.1.2.4 የእያንዳንዱ የጥሬ እቃዎቹ ምንጭና የአቅራቢ ድርጅቶች ስምና አድራሻ መረጃ መያዝ
አለበት
4.1.2.5 ጥሬ እቃዎቹ ዓይነትና ባህሪ ጥራታቸውና ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ ለማቆየት
በሚያስችል ቦታና ሁኔታ ላይ መቀመጥ አለባቸው፡፡

15 | P a g e
4.1.2.6 ማንኛውም የምግብ ግብዓቶች ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት የሚፈለገውን የጥራት ደረጃ
የሚያሟላ ስለመሆኑ በቅድሚያ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
4.1.3 በቅድመ ማምረት ሊሟሉ ስለሚገባቸው ሁኔታዎች
4.1.3.1 ማንኛውም የምግብ ድርጅት ማምረት ከመጀመሩ በፊት የሚከተሉት ሁኔታዎች
መሟላታቸውን ድርጅቱ በቅድምያ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
ሀ) ምርቱን ለማምረት የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎች እና በሚንያህል መጠን እንደሚወሃዱ
ማዘጋጀት
ለ) የማምረቻ ቦታውና የማምረቻ ማሽነሪዎች በንፅህና አጠባበቅና ቁጥጥር አሰራር ስርዓት
መሰረት በሚፈለገው ደረጃ የፀዱ መሆናቸውን ድርጅቱ ምርት ማምረት ከመጀመሩ
በፍት ማረጋገጥ ይኖርበታል
ሐ) የማምረቻ ማሽነሪዎችና መለኪያ እቃዎች ወቅታዊ የማምረት ብቃት እና ትክከለኛ
ልኬት ላይ መገኘታቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል
4.1.3.2 ድርጅቱ ከላይ በዝርዝር የተገለጹ ሁኔታዎች በተዘረጋው የአሰራር ስርዓት መሰረት በአግባቡ
ማረጋገጥና መረጃውም በአግባቡ አደራጅቶ መያዝ አለበት፡፡
4.1.4 በምግብ ዘይት ማምረት ሂደት ሊደረግ ስለሚገባ ቁጥጥር (Processing quality
control)
4.1.4.1 የአመራረት ሂደት ቁጥጥር/Control of food hazard/
4.1.4.1.1ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት ምርት በሚያመርትበት ጊዜ ምርቱ
በተቀመጠው የጥራትና ደህንነት መስፈርት መሰረት እየተመረተ ስለመሆኑ እንዲሁም የአመራረት
ሂደቱ ዘለቄታው ጥራትና ደህንነት ለመከታተልና ለማረጋገጥ የሚያስችል የአመራረት ሂደት ቁጥጥር
አሰራር ስርዓት (In process control) ሊኖረው ይገባል፡፡
4.1.4.1.2 የማምረቻ ማሽነሪዎችና መሳርያዎች ምርቱን በሚፈለገው ደረጃ እያመረቱ ስለመሆናቸው
አስፈላጊውን ቁጥጥር ማድረግ አለበት፡፡
4.1.4.1.3 የሚመረተው ምርት በአመራረት ሂደት ውስጥ ሊያማላው የሚገባ የጥራትና ደህንነት
መስፈርቶች ጠብቆ እየሄደ ስለመሆኑ ከተመረጡት የናሙና ማውሰጃ ቦታዎች ላይ ናሙና በመውሰድ
በየጊዜው ማረጋገጥ አለበት፡፡
4.1.4.1.4 ማንኛውም የምግብ ዘይት ማምረቻ ድርጅት በማምረት ሂደት የምርቱን ጥራትና ደህንነት
ሊያጓድሉ በሚችሉ በካይ ነገሮች እንዳይበከል ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ አለበት፡፡
4.1.4.1.5 በምርት ሂደት የተከናወኑ የቁጥጥር ስራዎች እንዲሁም የተለዩ የጥራትና ደህንነት
ጉድለቶች እና የተወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎች መረጃ በአግባቡ አደራጅቶ መያዝ አለበት፡፡

16 | P a g e
4.1.4.1.6 ማንኛውም የምግብ ዘይት ማምረቻ ድርጅት አጠቃላይ ከምርት ማምረት ሂደት ጋር
ተያያዥነትና ንክኪ ያላቸው ማሽነሪዎች፣ መገልገያ መሳሪያዎች፣ ማምረቻ ቦታ እንዲሁም ሰራተኞች
ንፅህና ለማስጠበቅና ለማረጋገጥ የመልካም ንፅህና አጠባበቅ አሰራር ስርዓት (Good hygieni
practice) ስለመተግበሩ በየጊዜው ክትትል ማድረግን ማረጋገጥ አለበት፡፡
4.1.4.1.7 ማንኛውም የምግብ ምርት አምራች ድርጅት የሚያመርተውን ምርት ደህንነት ሊያጓድሉ
የሚችሉ በካይ ነገሮች (Hazards) ዓይነት የመለየት፡ በካይ ነገሮቹ ለመቆጣጠር የሚቻልበት ዋና ዋና
ቦታዎች (critical control point) መለየት፤ የማስተካከያ እርምጃ ሊያስወስድ የሚችል ከፍተኛ መጠን
(Critical limit)፤ ቸግሩን በሚከሰትበት ጊዜ ሊወሰድ ስለሚገባ የማስተካከያ እርምጃ እንዲሁም ችግሩ
በቀጣይ በድጋሚ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል የሚከናወኑ ስራዎች (corrective and
preventive action) በዝርዝር ሊያሳይ የሚችል የምግብ ደህንነት ማረጋገጥ አሰራር ስርዓት ሊኖረው
ይገባል፡፡
4.1.4.1.8 በየጊዜው የሚከናወኑ ማንኛውም ከምርት ጥራት አጠባበቅ ጋር ተያያዥነት ያላቸው
የቁጥጥር ተግባራት መረጃዎችተመዝግቦ በአግባቡመያዝ አለበት፡፡
4.1.4.2 የሙቀት ቁጥጥር (Time-Temperature control)
4.1.4.1.ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት የሚያመርተውን ምርት ጥራትና ደህንነት
ለማረጋገጥ የሚያስችል የሙቀትናምርት ቆይታ ጊዜ የሚያረጋግጥ የአሰራር ስርዓት ሊኖረው ይገባል፡

4.1.4.2.1 ማንኛውም በማምረቻ ተቋሙ ውስጥ ከምርት ሂደት ጋር ግንኙነት ያለው ማሞቂያዎች
በአግባቡ እየሰራ ስለመሆኑ ትክክለኛነቱ መረጋገጥ አለበት፤
4.1.4.2.2 በምርት ሂደት ተግባር ላይ እየዋለ ያለው የሙቀት መጠንና የምርት ቆይታ ጊዜ ተመዝግቦ
መያዝና የሚመለከተው ባለድርሻ/ተቆጣጣሪ አካል ስጠይቅ ማረጃውን ማቅረብ ይኖርበታል፡

4.1.4.2 የምርት መገልገያ መሳሪያዎች ጥገና (Maintenance)


4.1.4.2.1 ማንኛውም ከምርት ጋር ንክኪ ያለው የምርት መገልገያ መሳሪያ ምርቱን ከሚበክሉ ነገሮች
ነጻ መሆን አለበት
4.1.4.2.2 ጥገና የሚያስፈልጋቸው የማምረቻ መሳሪያዎችእና ሌሎች መለካያዎች በተዘረጋው የአሰራር
ስርዓት መሰረት አስፈላጊውን ጥገና ሊደረግላቸው ይገባል፤
4.1.4.2.3 ስለ ማምረቻ መሳሪያዎች ጥገና የሚገልጹ መረጃዎች በአግባቡ መያዝ ይኖርባቸዋል፤

17 | P a g e
4.1.4.3 የምግብ ዘይት አመራረት ፍሰት ሂደት/Processing of edible oil and Process
flow diagram/
4.1.4.3.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት ማምረቻ ድርጅት እንደሚያመርተው ምርት አይነት ሆኖ ብያንስ
የሚከተሉትን ሂደቶች መከተል አለበት፡
ሀ) Degumming
ለ) Neutralization
ሐ) Bleaching
መ) Deodorization
4.1.4.3.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት ማምረቻ ድርጅት ስለሚያመርታቸው ምርቶች የሚያሳይ የምርት
ፍሰት ሂደት እንደሚከተለው (Process flow diagram) ሊኖረው ይገባል፤

18 | P a g e
Raw oil seed
Raw oil seed

Fail inspection criteria Inspection of


Rejected oil seeds

Storage

Cleaning
Pressing Cleaning De hulling Milling/cracking

Extract cake Crude oil

Rejected
Filtration
Animal feed

Degumming Lecithin

De-waxing

Neutralizatio
n

Bleaching

Deodorizatio Filtratio Testing of oil


n n

Dispatch Approved
Storage in silo

Warehousing
Fortification of
Rejected
micro nutrient

Tempering Packaging Storage in silo


Approved Test of micro
nutrient
19 | P a g e
4.1.4.3.2 የምርት ፍሰት ሂደት በመግለጫ/ማብራሪያ የተደገፈ ሊሆን ይገባል፤
4.1.4.3.3 ተቋሙ ስለ ምርት ፍሰት ሂደት (process flow diagram) በተቆጣጣሪዎች በተጠየቀ ጊዜ
መረጃውን በአግባቡ በመያዝ ማሳየት ይጠበቅበታል፤
4.1.4.4 የምግብ ዘይት ምርትን ስለማበልጸግ
4.1.4.4.1 ማንኛውም የምግብ ዘይቶችን በተለያዩ ማዕድናትና ቫይታሚን የሚያበለጽግ ተቋም በደንብ
ቁጥር 299/2006 አንቀጽ 7 (1 እና 2) የተቀመጠውን አስገዳጅ ህጎች ከላይ በተጠቀሰው የሚያሳይ
የምርት ፍሰት ሂደት መሰረት ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል፤
4.1.4.4.2 የበለጸገው ምርት በአገር አቀፍ ደረጃ የወጣውን ደረጃ ማሟላት ያለበት ሲሆን በአገር አቀፍ
ደረጃ መስፈርት ከሌለ በዓለም አቀፍ ደረጃ የወጣውንና አገሪቷ የተቀበለችውን መስፈርት ማሟላት
ይኖርበታል፤
4.1.4.4.3 ድርጅቱ ስለሚያበለጽገው የምግብ ዘይት በተመለከተ ያለውን መመሪያዎችና የአሰራር
ሂደቶች በአግባቡ አደራጅቶ መያዝና ለሚመለከተው ተቆጣጣሪ አካል ሲጠየቅ ማሳየት ይኖርበታል፤
4.1.4.5 በድጋሚ ስለሚመረቱ ምርቶች (Reworking/reprocessing products)
4.1.4.5.1 ድርጅቱ የምርት ሂደታቸው ያላለቁ ምርቶች በድጋሚ ለማምረት የሚከተልበት
የአሰራር ስርዓት ሊኖረው ይገባል፡፡
4.1.4.5.2 በምርት ሂደት ወቅት በተለያየ ምክንያት የምርት ሂደታቸው ያላለቁ ወይም በተገቢው
ደረጃ የአመራረት ሂደት ያላለፉ ምርቶች በድጋሚ ማምረት የሚቻለው የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲሟሉ
ብቻ ነው፡፡
ሀ) ምርቶቹ ተገቢው ምርመራ ተደርጎላቸው ተገቢውን ጥራትና ደህንነት መስፈርት የሚያሟሉ
መሆናቸውን ሲረጋገጥ
ለ) በምርቱ ላይ ምንም ዓይነት የደህንነት ችግር የማያስከትሉ መሆናቸውን ሲረጋገጥ ነው፡፡
4.1.4.5.3 በድርጅቱ ውስጥ በድጋሚ የተመረቱ ምግቦች ዓይነት፣ መለያ ቁጥር፣ መጠን፣ በድጋሚ
የተመረቱበት ምክንያትና የምግቡ የጥራትና ደህንነት ምርመራ ውጤት የሚገልፁ መረጃዎች በአግባቡ
መዝግቦ መያዝናማንኛውም የሚመለከተው አካል ስጠይቅ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
4.1.4.6 ምርት ስለማሸግና ገላጭ ፅሁፍ አደራረግ (packaging and labeling)
4.1.4.6.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት ተመርቶና ጥራትና ደህንነቱ ከተረጋገጠ በኋላ በመመሪያው
የተገለፀው የምግብ ማሸጊያ መስፈረት በሚያሟላ ማሸጊያ ከማንኛውም ብክለት ነፃ በሆነ መልኩ
በአግባቡ መታሸግ አለበት፡፡
4.1.4.6.2 ማንኛውም የምግብ ዘይት ምርት በማሸግያው ላይ ስለምርቱ እውነተኛ ምንነት የሚገልፅ
ሊሆን ይገባል፡፡
20 | P a g e
4.1.4.6.3 ማንኛውም የምግብ ዘይት ገላጭ ፅሁፍ ብሔራዊ የምግብ ዘይት ገላጭ ፅሁፍ ደረጃ
እንዲሁም በምግቡ ብሔራዊ ደረጃ ላይ በተቀመጠው የገላጭ ፅሁፍ መስፈርቶች የሚያሟላና አሳሳች
ያልሆነ፤ በቀላሉ ሊነበብ የሚችልና የማይለቅ ገላጭ ፅሁፍ ሊኖረው ይገባል፡፡
4.1.4.6.4 በምግቡ ላይ የNutrition & Health claim ሲኖረው በሀገራዊ ወይም በኮዴክስ የኑዩትሪሽንና
የጤና መግለጫ “በተቀመጠው ደረጃ መሰረት ተግባራው መደረግ ይኖርበታል፡፡
ክፍል አምስት፡ የጥራትና ደህንነት ቁጥጥር ስለማካሄድ (Finished product safety & quality assurance)
5.1 የላቦራቶሪ ግበዓቶችመሳሪያዎችና ኬምካሎች/Laboratory facilities and equipment and
reagents/
5.1.1 ማንኛውም ምግብ ዘይት አምራች ድርጅት መሰረታዊ የሆነ የጥራትና ደህንነት የሚያስጠብቅ
እንደ አስፈላግነቱ የፊዝኮ ኬሚካል እና የማይክሮ ባዮሎጅይ ጥራት የምርመራ ላቦራቶሪ ሊኖረው
ይገባል፡፡
5.1.2 መሰረታዊ የላቦራቶሪ መመርመርያ መሳሪያዎች፣ መገልገያ እቃዎች፣ የደህንነት መጠበቂያ
ማቴሪያሎች ልኖረው ይገባል
5.1.3 በቅ የሆነ የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶችና ኬሚካሎች ልኖር ይገባል
5.1.4 የላቦራቶሪ መሳሪያዎቹ እንደ አስፈላጊነቱ ወቅታዊ ጥገናና በትክክል ስለመለካተቸው መረጋገጥ
ይኖርባቸዋል (Calibiration) ይኖርባቸዋል
5.1.5 እንደሚከናወኑ የጥራት ምርመራ ዓይነት በዘርፉ የሚጠየቀውን የትምህርት ደረጃና ዝግጅት
ያላቸው የጥራት ምርመራ ቴክኒካል ባለሙያዎች በመመሪያው መሰረት ድርጅቱ ሊኖሩት ይገባል፡፡
5.1.6 ድርጅቱ ለጥራት ምርመራ የሚጠቀምባቸው የምርመራ ስልቶች (Test method) በሀገራ አቀፍ
ወይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው የምርመራ ዘዴዎች የተከተለ መሆን አለበት፡፡
5.1.7 ድርጅቱ አጠቃላይ የጥራት ምርመራ ስራዎችን አግባብነትና ትክክለኛነት በበላይነት
የመከታተልና የእርምት እርምጃ ለመውሰድ የሚስችል የጥራት ማረጋገጥ አሰራር ስርዓት (quality
assurance system) ሊኖረው ይገባል፡፡
5.1.8 ማንኛውም ድርጅት የጥራት ምርመራ ከተደረገላቸውን ያለቀላቸው ምግቦች ውስጥ ወካይ
ናሙና የምግቡ የመጠቀሚያ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ መያዝ አለበት፡፡
5.1.9 ድርጅት የሚያከናውናቸው የጥራት ምርመራ ስራዎች ተአማኒነት ያለው ውጤት ለማውጣት
የሚያስችልና ከናሙና አወሳሰድ እስከ ሪፖርት ማድረግ ድረስ ያለው ሂደት የሚያሳይ የአሰራር
ስርዓት ሊኖረው ይገባል፡፡
5.1.10 ድርጅቱ ባዘጋጀው የአሰራር ስርዓት መሰረት የሚከናወኑ የጥራት ምርመራ ስራዎችና
ስለመከናወናቸው እና የባለሙያዎች የስልጠና ሁኔታ የሚያሳይ መረጃ አደራጅቶ መያዝ አለበት፡፡

21 | P a g e
5.2 ስለ ናሙና አወሳሰድ/Sampling/
5.2.1 ማንኛውም የዘይት ምግብ አምራች ድርጅት ባዘረጋው የናሙና አወሳሰድ የአሰራር ስርዓት
መሰረት መከናወን አለበት
5.3 ስለ ማጣቀሻ አጠቃቀም (Reference standard)
5.3.1 ማንኛውም የዘይት ምግብ አምራች ለማምረት የሚጠቀምበት ግብዓቶች፣ የሚጠቀምበት
ኬሚካሎችና የሚመረተው ምርት የጥራትና ደህንነት ደረጃ እንደ ማጣቀሻነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ
ደረጃ መጠቀም ይኖርበታል፡፡
5.3.2 በድርጅቱ የሚመረተው ምርት በብሄራዊ ደረጃ ያልወጣለት ከሆነ በአህጉር ደረጃ የአፍሪካ
ደረጃዎች፤ በዓለማቀፍ ደረጃ እንዲሁም በኮዴክስ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው ደረጃዎች መጠቀም
ይችላል፡፡
5.3.3 የምግቡ አምራች ድርጅት የራሱን የመስፈርት ደረጃ (company standard) መጠቀም የሚችል
ሆኖ ከብሔራዊና አለም አቀፍ ደረጃዎችን መሰረት ያደረግ መሆን ይኖርበታል፡፡
5.4 ምርመራ/Analysis/
5.4.1ድርጅቱ አጠቃላይ የጥራት ምርመራ ስራዎችን አግባብነትና ትክክለኛነት በበላይነት
የመከታተልና የእርምት እርምጃ ለመውሰድ የሚስችል የጥራት ማረጋገጥ አሰራር ስርዓት (quality
assurance system) መሰረት መረጃ አደራጅቶ መያዝ አለበት፡፡
5.5 ስለ ጥሬ እቃዎች አቀባበል፣ ምርት ምርመራናምርትን ማሰራጨት/Ingredient receiving,
product holds and releases/
5.1ተቋሙ ስለጥሬ ዕቃ አቀባበልና አግልግሎት ላይ እንዲውል መፍቀድና ወይም እንዳይውል
የሚከለክልበት አስፈላጊ የጥራት ቁጥጥር ስርዓት ሊዘረጋ ይገባል፤
5.2 ያለቀለት ምርቶችም ወደ ገበያ ከማሰራቸታቸው በፍት ጥራትና ደህንናተቸው በማረጋጋጥ
አስፈላግውን መረጃ አዳርጅቶ መያዝ አለበት፡፡
5.6 ምግብን ስለማቆየት (Retention of product)
5.6.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት የመጠባበቅያ ናሙና /Retention sample/ አያያዝ
አሰራር ስርዓት ልኖረው ይገባል፡፡
5.6.2 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት ከሚያመርተው ምርት ውስጥ ከእያንዳንዱ የምርት
የመጠቀሚያ ጊዜ፣የተመረተበት ቀን እና መለያ ቁጥር ድርጅቱ በተዘረጋው የአሰራር ስርዓት መሰረት
ቀሪ ናሙና መያዝ (Retention sample) ይኖርበታል፡፡
5.6.3 የሚያዘው የምርት ናሙና ቢያንስ የምርቱ የመጠቀሚያ ጊዜው እስከሚያልቅ ድረስ ማቆየት
አለበት፡፡

22 | P a g e
5.6.4 የተያዘው ምርት የመጠቀሚያ ጊዜ፤የተመረተበት ቀን፤ መለያ ቁጥር እና የምግቡ መጠን
በአግባቡ መዝግቦ መረጃ መያዝ እና የሚመለከተው ተቆጣጣሪ አካል ስጠይቅ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
5.7 ማረጋጋትና የምርት ቆይታ ጊዜ/Stability and shelf life/
5.71 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት በምርት ቅንብር እና በአመራረት ሂደትን ዝርጋታ
ወቅት የምርቱን መጠቀሚያ ጊዜ እና የአከመቻቸት ሁኔታ ለመወሰን በሚያስችል መልኩ የአሰራር
ስርዓት መዘርጋት አለበት
5.8 ስለ ውጫዊ ላቦራቶሪ/External laboratories/
5.8.1 የምግብ አምራች ድርጅት ለሚያመርተው ምርት ጥራት ቁጥጥሩ አስፈላጊ የሆኑ የላቦራቶሪ
ምርመራዎችን በራሱ የማያከናውን ከሆነ በሌላ እውቅና ባለው ተቋም ጋር የአሰራር ስርዓት ልኖረው
ይገባል፤
5.8.2 በሌላ አካል የተመረመሩ ማንኛውም የላቦራቶሪ የምርመራ ውጤቶች በአግባቡ መያዝና ሲጠየቅ
ለሚመለከተው አካል ማሳየት ይኖርበታል
ክፍል ስድሰት፡ ስለማከማቸትና ማጓጓዝ (Storage and transportation)
6.1 ግበዓት፤ኬሚካሎችና ምርትን ስለ ማከማቸት/Raw materials, chemicals and product

storage/
6.1.1 ማንኛውም ምርት እንደምርቱ ዓይነትና ባህሪ እርጥበት በሌለበት፤ ንፁህና በምርቱ ማሸጊያ
ገላጭ ፅሁፍ ላይ በተጠቀሰው መሰረት መከማቸት አለበት፡፡
6.1.2 የምርቱ ማከማቻ ክፍሉ በመመሪያው የተቀመጡ መስፈርቶች የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡
6.1..3 ምግቡ ከመሬት 20 ሴንቲ ሜትር ከፍ ብሎ ከጣሪያው 30 ሴንት ሜትር ዝቅ ብሎ እና
ከግድግዳ 50 ሴንቲ ሜትር ራቅ ብሎ መከማቸትና በሁለት ድርድሮች መካከል ቢያንስ የአንድ
ሜትር ክፈተት ሊኖረው ይገባል
6.1.4 ድርጅቱ ምርቱን ሊበክሉ ከሚችሉ ፀረ ተባይ ኬሚካሎችና ሌሎች በካይ ነገሮች ጋር አብሮ
ማከማቸት የለበትም፡፡
6.1.5 የተበላሹ ወይም የመጠቀሚያ ጊዜያቸዉ ያለፈባቸው ምርቶችና ጥሬ ዕቃዎች እስኪወገዱ ድረስ
በአግባቡ ተቆጥረውና ተመዝግበው እንዲሁም ከሌሎች ምርቶች ተለይተው ጥቅም ላይ እንደማይውሉ
የሚገልፅ ፅሁፍ በመለጠፍ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀ ቦታ መቀመጥ አለባቸው፡፡
6.1.6 በእያንዳንዱ የምርት ዓይነትና መጋዘን ላይ የምርቱን ዓይነት፣ ምርቱ ያለበትን ሁኔታ (አያያዝ፣
አቀማመጥና የቆይታ ጊዜው ያለበትን ደረጃ) እና ሌሎች ስለ ምግቡ የሚገልፁ መረጃዎች በየጊዜው
መለጠፍ አለባቸው፡፡

23 | P a g e
6.2 ምርትን ስለ ማጓጓዝና ስለ ማሰራጭጨት
6.2.1 ማንኛውንም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት ምርቱን ለብክለት በሚያጋልጥ ሁኔታ ማጓጓዝ
የለበትም፡፡
6.2.2 ምርቱ ንፁህ፣ ደረቅና ምግብን ሊበክሉ ከሚችሉ ከፀሐይ፣ ከአቧራና ከማናቸውም እርጥበት
አዘል ወይም ሌሎች ነገሮች በተጠበቀ መልኩ መጓጓዝ አለበት፡፡
6.2.3 ምርቱን ሊበክል የሚችል ማንኛውም ዓይነት እቃ በተጫነበት ወይም በተቀመጠበት የመጓጓዣ
እቃ ምርቱን መጫን ወይም ማጓጓዝ የተከለከለ ነው፡፡
6.2.4 የቅዝቃዜ ሰንሰለታቸው መጠበቅ ያለባቸው ምርቶች ተገቢውን የቅዝቃዜ መጠን ሊጠብቅ
በሚችል ማቀዝቀዣ በተገጠመለት እቃ ወይም ተሸከርካሪ መጓጓዝ አለባቸው፡፡
ክፍል ሰባት የውስጥ ጥራት ቁጥጥር (Internal Audits/self inspections)
7.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት በእቅድ የሚመራና ወቅታዊነቱን በጠበቀ ምልኩ
የውስጥ ኦዲት ሥራ መስራት አለበት፣
7.2 ድርጅቱ ኦዲት የሚያደርግበት የአሰራር ስርዓት ሊኖረው ይገባል፡፡
7.3 ድርጅቱ ባዘጋጀው የአሰራር ስርዓት መሰረት አግባብነት ባላቸው ቢያንስ ሁለትና ከዚያ በላይ
በሆኑ ባለሙያዎች በየሦስት ወሩ ኦዲት በማድረግ ለድርጅቱ ማናጅመንት ቀርቦ መገምገም አለበት፡፡
7.4 በድርጅቱ ማናጅመንት የተገመገመ የኦዲት ሪፖርት በየ 6 ወሩ ለባለስልጣን መስሪያቤቱ መላክ
አለበት፡፡
7.5 ለባለስልጣኑ የሚቀርበው የኦዲት ሪፖርት ቢያንስ የውስጥ ኦዲት አደራረግ ሂደት፤ በኦዲቱ
የተገኙ ክፍተቶችን የክፍተቶቹ መንሴዎች ትንተና ክፍተቶቹ ለማስተካከል የሚያስችል የእርምት
እርምጃ አፈፃፀም መርሀ ግብር (Corrective & Preventive action plan) ጉዳዮች ማካተት አለበት፡፡
7.6 ድርጅቱ በኦዲት ግኝት የተገኙ ክፍተቶች ስርወ ምክንያት ትንተና በማካሄድ በተዘጋጀው
የክፍተት ማስተካከያ እቅድ መሰረት ተግባራዊ ማድረግና ችግር በድጋሚ እንዳይፈጠር ስርነቀል
መፍትሄና የቅድመ መከላከል አሰራር መዘርጋት አለበት
7.7 ድርጅቱ የውስጥ ኦዲት አደራረግ ሂደት፤የተገኙ ክፍተቶችና የተወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎች
በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃ አደራጅቶ መያዝ አለበት፡፡
ክፍል ስምንት፡ ስለ ኮንትራት /Sub-contracting/
8.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት በራሱ መከናወን ያለበት አገልግሎት በሌላ ሁለተኛ
ተመሳሳይ ምርት አምራች ወይም አገልግሎት ሰጪ ድርጅት በኮንትራት እንዲያከናወን ሲፈልግ
ኮንትራት የሚሰጠው ድርጅት የሚፈለገውን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ብቃት ያለው መሆኑ
በባለስልጣኑ ወይም በሌላ አግባብ ባለው አካል የብቃት ማረጋገጫ ሊነረው ይገባል፡፡

24 | P a g e
8.2 በስምምነቱ መሰረት የስራው ዝርዝር ይዘትና ሀላፊነት በተመለከተ ህጋዊ ውል ሊኖራቸው
ይገባል፡፡
ክፍል ዘጠኝ፡አስፈላጊ የአሰራር ሥርዓት ሰነዶች እና መረጃ ስለመያዝ (Document
management)
9.1 አስፈላጊ የአሰራር ሥርዓት ሰነዶች
9.1.1 የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት በዚህ መመሪያ እንዲሰሩ የተጠቀሱ አሰራሮችን በተለይ
ለምርት ድህነትና ጥራት ለማስጠበቅ የሚረዱ የአሰራር ሰነዶች ማዘጋጀት ይኖርበታል
9.1.2 ድርጅቱ ያዘጋጀው የአሰራር ሰነዶቹ በአግባቡ ስራ ላይ መዋልና እንዳስፈላጊነቱ የአሰራር
ስረዓቱ ሰነዶቹ ሊከለሱ ይችላሉ፤
9.1.3 ሰነዶቹ በተፈለገ ጊዜ ለሚመለከተው የተቆጣጣሪ አካል ማቅረብ ይገባል
9.1.1. ምግብ ከገበያ ላይ ስለመሰብሰብ/Product withdrawal and recall procedure/
9.1.1.1 የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት በሚያመርተው ምርት የጥራት እና ደህንነት ችግር
ያለባቸው ምርቶች በገበያ ላይ በሚያጋጥሙት ጊዜ የምርት አሰባሰብ አሰራር ስርዓት ሊኖረው ይገባል
9.1.1.2 የምርት መሰብሰቢያ እና መከታተያ አጠቃላይ ክትትል ለማድረግ የሚያስችል የምዝገባ
ስርዓት ሊኖረው ይገባል
9.1.1.3 የተዘረጋው የምርት ማሰባሰብ ስርዓት በአግባቡ ተግባራዊ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል
የምርት አሰባሰብ ሙከራ በተቀመጠ የጊዜ ሰሌዳ አማካኝነት መፈጸም ይኖርበታል
9.1.1.4 ድርጅቱ ምርቱ ወደ ገበያ ያሰራጨው ምርት የጥራት እና ደህንነት ችግር እናደለበት በራሱ
ሲያረጋግጥ ምርት በአፋጣኝ ማሰባሰብ ይኖርበታል በህዝብ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ
ለህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው ሊያሳውቅ የሚያስችልበት አሰራር ስርዓት ሊኖረው ይገባል
9.1.1.5 ምርት የማሰባሰቡ ሂደት እንደ ምርቱ ብልሽት ወይም የህብረተሰብ ጤና ላይ
እንደሚያስከትለው ጉዳት በአፋጣኝ ለመሰብሰብ የሚያስችል እና ቅዲሚያ መስጠትን ታሳቢ ያደረገ
አሰራር ስርዓት ሊኖር ይገባል፡፡
9.1.1.6 ምርቱ በአግባቡ መሰብሰቡን ከስርጭቱ ጋር በማመዛዘን የሚያረጋግጡበት አሰራር ስርዓት
ሊኖረው ይገባል፡፡
9.1.1.7 ምርቱ ከገበያ እንዲሰበሰብ የተፈጠረውን ችግር መልሶ እንዳይከሰት ከምንጬ የማስተካከያ
የአሰራር ስርዓት መዘርጋና መፈጸም ይኖርበታል

25 | P a g e
9.1.2. የጥራትና ደህንነት ጉድለት ያለበት ጥሬ ዕቃና ምርት አያያዝ/ Nonconforming
product handling procedure/
9.1.2.1 ማንኛውም ድርጅት የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት በሚያመርተው ምርት የጥራት እና
ደህንነት ችግር ያለባቸው ምርቶች በሚያጋጥሙት ጊዜ የምርት አያያዝ ስርዓት ሊኖረው ይገባል
9.1.2.2 ማንኛውም ጥቅም ላይ የማውሉ ጥሬ እቃዎች ወይም ምግቦች ተለይተውና ጥቅም ላይ
የማውሉ ስለመሆናቸው የሚገልፅ ገላጭ ጽሁፍ ተደርጎው በአግባቡ መያዝ አለባቸው፡፡
9.1.2.3 ተለይተው የተያዙት አግልግሎት ላይ የማይውሉት ጥሬ ዕቃዋችም ሆኑ ምርቶች አገልግሎት
ላይ የማይውሉ ምርቶች የአወጋገድ አሰራር ስርዓት መሰረት በአግባቡ ማስወገድ አለበት፡፡
9.1.2.4 የተወገዱ ምርቶች ዓይነት፤ መለያ ቁጥር፤ የተመረተበት ቀንና የምርቱ መጠን እንዲሁም
እንዲወገድ የተደረገበት ምክንያት በአግባቡ ተመዝግቦ መረጃ መያዝ አለበት፡፡
9.1.2.5 አገልግሎት ላይ የማይውሉ ጥሬ ዕቃዎችና ምርቶች መለያ መስፈርትን እና የተለዩበትን
ምክንያት እና ዝርዝር የሚገልፁ ዶክመንቶች የሚለይበትን የአሰራር ስርዓት ማዘጋጀት አለበት
9.1.2.6 ድርጅቱ ስለሚወገዱ ምርቶች ዝርዝር መረጃ ለባለስልጣኑ ማሳወቅና በአወጋገድ መመሪያ
መሰረት ማስወገድ አለበት፡፡
9.1.2.7 አገልግሎት ላይ የማይውሉ ምግቦች ተብለው የተለዩት ምግቦች እንዲወገድለት ሲጠይቅ
የምግቡን መጠን፣ ስም፣ የተመረተበትን ቀን፣ የባች መለያ ቁጥር፣ የአምራች ስም፣ የተመረተበት
ሀገርን እና የሚወገድበትን ምክንያት የያዘ ዝርዝር እንዲወገድለት ከሚጠይቅበት ደብዳቤ ጋር
ማቅረብ አለበት፡፡
9.1.2.8 ለማስወገድ የሚያስፈልገውን ክፍያ መፈፀም አለበት፡፡
9.1.2.9 ከተወገደለት በኃላ የሚሰጠውን ሰርተፊኬት ፋይል አድርጎ ማስቀመጥ እና ሲፈለግ ወይም
ሲጠየቅ የማሳየት ግዴታ አለበት፡፡
9.1.3 ስለ ቅሬታ አቀባበል/Complaint Handling Procedures/
9.1.3.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት የሚመርተው ምርት ጥራትና ደህንነት
በተመለከተ ተጠቃሚዎች ቅርታቸውና አስተያየት በቀላሉ የሚየቀርብበት አሰራር ስርዓት መዘርጋት
አለበት፡፡
9.1.3.2 ድርጅቱ የቀረበውን ቅሬታ በአግባቡ የማጣራት ስራዎች እና አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ
አለበት፡፡
9.1.3.3 የቀረበው ቅሬታ ከፍተኛ የምርት ደህንነት ችግር መኖሩንና በህብረተሰቡ ላይ የጤና ችግር
የሚያስከትል መሆኑን ሲያረጋግጥ በዘረጋው የአሰራር ስርዓት መሰረት ህብረተሰቡ ምግቡ

26 | P a g e
እንዳይጠቀም በተለያየ የመገናኛ ዘዴ እንዲያውቀው የማድረግና ምርቱ ከገበያ የመሰብሰብ ግዴታ
አለበት፡፡
9.1.3.4 ድርጅቱ ጉዳዩን ባወቀ በ 1 ሰዓት ውስጥ ለሚመለከተው ተቆጣጣሪ አካል ሪፖርት ማድረግ
አለበት፡፡
9.1.3.5 ድርጅቱ ማንኛውም ከምርት ጥራትና ደህንነት ጋር የተያያዘ የሚቀርቡ ቅሬታዎች
በዘለቄታዊ መልኩ እንዲስተካከሉ ዘለቄታዊ ማስተካከያ እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
9.1.3.6 ድርጅቱ አጠቃላይ ከሚያመርተው ምርት ጥራትና ደህንነት ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ

ቅሬታዎች፤ የተወሰዱ እርምጃዎች እና ሌሎች መረጃዎች በአግባቡ መያዝ አለበት፡፡


9.1.4 የድህረ ገበያ ቅኝት ስርዓት ስለመዘርጋት (PMS)
9.1.4.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት ስለምርቱ ጥራትና ደህንነት በዘለቄታዊነት
ክትትል ለማድረግ የቅኝትና ክትትል ማድረጊያ የአሰራር ስርዓት/Post marketing surveillance and
vigilance/ መዘርጋት፣ የተዘረጋው የአሰራር ስርዓት ውጤታማነት መገምገምና ቀጣይነት ባለው መልኩ
ተግባራዊ ማድረግ አለበት፡፡
9.1.4.2 በቅኝትና ክትትል ሂደት የተለዩ ችግሮችን በመተንተን የማስተካከያ እና ስር ነቀል እርምት
ተግባራዊ ማድረግ አለበት /Corrective and preventive action/
9.1.4.3 በመደበኛነት የተከናወኑ የቅኝትና የክትትል ስራዎችን እንዲሁም የተወሰዱ የማስተካከያ
እርምጃዎች በመረጃ አደራጅቶ መያዝ አለበት፣
9.2 ስለ ሰነዶች አያያዝ/Document and records management/
9.2.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት ለምርት ጥራትና ደህንነት ስርዓት ዝርጋታ
የሚጠቀምባቸውን የአሰራር ስርዓቶች ሲያዘጋጅ ተግባራቱ የሚፈጸሙበትን አላማ በሚሳካ እና ተግባሩ
የሚፈፀምበትን አሰራር ሂደትና ፍሰት በግልፅ በሚያመላክት መልኩ መሆን አለበት፣
9.2.2 ድርጅቱ የተዘጋጁ የጥራትና ደህንነት ማረጋገጫ የአሰራር ስርዓቶችን በመመዝገብ እና
አደራጅቶ በአግባቡዋናውን ቅጅ በማስቀመጥ እና ሌሎች ቅጂዎች አሰራሮቹ ተገብረዊ በሚሆኑበት
ቦታ ሊገኙ እና ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው፡፡
9.2.3 የሚዘገጁ የአሰራር ስርዓቶች በአምራች ድርጀቱ ማነጅምት ኮሚቴ ውይይት የተደረገብትና
በበላይ ሃላፊ የፀደቀ መሆን አለበት፡፡
9.2.4 በዚህ መመሪያ ውስጥ አስፈላጊ ተብለው እንዲዘጋጁ የተጠቀሱት አሰራር ስርዓቶች በቀላሉ
ሊገኙ በሚችሉበት ሁኔታና ለተጠቀሰው አላማ ማጣቀሻ ሆነው ጥቅም ላይ ማዋል በሚችሉበት አግባብ
ተደራጅተው መያዝ አለባቸው፣

27 | P a g e
9.2.5 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት ስላመረተው፣ ስለተሰራጨ፣ ስለተበላሸ፣
የመጠቀሚያ ጊዜ ስላለፈበት፣ ስለተወገደ ምግብና ሌሎች የክምችት መቆጣጠሪያ ስቶክና ቢን
ካርዶችና ተያያዥ የሆኑ መረጃዎች በአግባቡ በመመዝገብ መረጃ መያዝና ተቆጣጣሪ አካል ሲጠየቅም
የማሳየት ግዴታ አለበት፡፡
9.2.6 ድርጅቱ ምርቱ የሸጠላቸው ድርጅቶች ስምና ሙሉ አድራሻ እና ሌሎች መረጃዎች የምርቱ
መጠቀሚያ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ መረጃ አደራጅቶ መያዝ አለበት፡፡
ክፍል አስር፡ የሐይጅንና አካባቢ ጤና አጠባበቅ
10.1. የሕንጻና የማምረቻ መሳሪያዎች ንጽህና አጠባበቅ
10.1.1 የጥራጥሬና የጥራጥሬ ውጤቶች አምራች ድርጅት ምርት ለማረት ጥሬ ዕቃና ያለቁ ምርቶች
ለማከማቸት የሚገለገሉበት ህንጻ የተገነባት ቁሳቁስ በምርቱ ላይ ተጽእኖ የማያስከትል መሆን
አለበት፤
10.1.2 በማምረቻ ስራ ላይ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶች በምርቱ ላይ ለብክለት ተጽእኖ
የማያስከትል መሆን ይኖርበታል፤
10.1.3 ተቋሙ የማምረቻ ተቋሙና የመገልገያ መሳሪያዎች ጽዳትና ንጽህና አጠባቅን አስመለክቶ
የአሰራ ስርዓት ሊዘረጋ ይገባል፤
10.1.4 የማምረቻ አካባቢና የመገልገያ መሳሪያዎች ንጽህና አጠባበቅን አስመልክቶ ስለተከናወኑ
ተግባራት የሚያስረዱ መረጃዎች በአግባቡ መያዝ ይኖርባቸዋል፤
10.2. የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አሰባሰብ፣ አያያዝ፣ አጓጓዝ እና አወጋገድ
10.2.1 ማንኛውም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ በአግባቡ ለመየዝና
ለማስወገድ የሚያስችል ቁሳቁስ ወይም ማሽን፣ ማፅጃ ኬሚካል፣ ጊዜያዊ ማጠራቀሚያ፣ የፅዳት
ሰራተኞች የደህንነት መጠበቂያ፣ አጠቃላይ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ እና ማጓጓዣ የሚሆን ደረጃውን
የጠበቀ፣ በቀለም የተለየ እና የምርትን ደህንነት እና ጥራት አደጋ ላይ የማይጥል ግብዓቶችን
/ፋሲሊቲ/ ማሟላት አለበት ፡፡
10.2.2 ተቋሙ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አሰባሰብ፣ አያያዝ እና አጓጓዝ ቆሻሻው ከተፈጠረበት ቦታ
አንስቶ እስከሚወገድበት ቦታ ድረስ የምርትን ደህንነት እና ጥራት አደጋ ላይ በማይጥል ሁኔታ
በአግባቡ እና ጊዜን እና ወቅቱን በጠበቀ መልኩ መሆኑን የሚከታተሉበትና የሚያረጋግጥ የአሰራር
ስርዓት መዘርጋት አለበት፡፡

28 | P a g e
10.3. የፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝ፣ ማቆያ (ማከም) እና አወጋገድ
10.3.1 ማንኛውም የምግብ ምርት አምራች ድርጅት የፍሳሽ ቆሻሻ መሄጃ እና ማስወገጃ የሚሆን ዝግ
መስመር አከባቢውን እና የሚመረተውን ምግብ ደህንነት እና ጥራት የማይበክል ተደርጎ መዘርጋት
አለበት፡፡
10.3.2 ከተለያዩ ቦታዎች የሚለቀቀውን ፍሳሽ ቆሻሻ የመጨረሻ የሚጠራቀምበትና የሚታከምብት በቂ
ማጠራቀሚያ ቦታ ሊኖረው ይገባል፡፡
10.3.3 ከተቋሙ የሚለቀቁ የፍሳሽ ቆሻሻዎች በአካባቢ፣ በሰው እና በእንስሳት ጤና ጉዳት ማድረስ
የለበትም፣
10.3.4 ከተቋሙ የሚወጡ የፍሳሽ ቆሻሻዎች ታክመው እና መስፍርቱን የሚያሟሉ መሆናቸው
ከተረጋገጠ በኋላ ብቻ መወገድ አለበት፣
10.3.5 የአጠቃላይ ፍሳሽ ቆሻሻ ማጠራቀሚያው በቂ፣ ፍሳሽ የማያስወጣ እና የማያስገባ ተደርጎ
መገንባት አለበት፡፡ በወቅቱ እና አከባቢውን በማይበክል መልኩ በየጊዜው ለመመጠጥ የሚያስችል
ተደርጎ መገንባት አለበት
10.3.6 የደረቅ እና የፍሳሽ ቆሻሻ መሰብሳቢና ማጠራቀሚያ ቁስና መስመር የጥገና የፅዳት የአሰራር
ስርዓት መዘርጋት አለበት፡፡
10.3.7 ድርጅቱ በተዘረጋው አሰራር ስርዓት መሰረት ተግባራት መተግባሩን የሚያሳዩ መረጃዎችን
አደራጅቶ መያዝ አለበት፡፡
10.4. የነፍሳት እና የቆርጣሚ እንስሳት ቁጥጥር/Pest and rodent control system/
10.4.1 ድርጅቱ የነፍሳት እና ቆርጣሚ እንስሳት መከላከለያና መቆጣጠሪያ ስልት መዘርጋትና
ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
10.4.2 የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት አከባቢው፣ ግቢው እና ክፍሎቹ ለበራሪ ነፍሳት እና ቆርጣሚ
እንስሳት መራቢያ፤ መግቢያ እና መውጫ ምቹ ያልሆነ ሆኖ መገንባት አለበት፡፡
10.4.3 ማንኛውም የምግብ አምራች ድርጅት በማንኛውም መልኩ የነፍሳት እና ቆርጣሚ እንሳስት
ለመቆጣጠር መራዛማና የምግብን ጥራትና ደህንነት አዳጋ ላይ የሚጥል ነገር መጠቀም የለበትም፡፡
10.4.4 ማንኛውም የዘይት ምግብ አምራች ድርጅት የነፍሳትን እና የቆርጣሚ እንስሳትን መከላከለያ
መሳሪያዎች በተገቢው ቦታ ሊኖረው ይገባል፡፡
10.4.5 ድርጅቱ የነፍሳት እና የቆርጣሚ እንስሳት መካለከያና መቆጣጣሪያ መሳሪያዎች በየጊዜው
ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ ውቅታዊ ጥገናና ፅዳት ሊያደረግላቸው ይገባል፡፡
10.4.6 አስፈላጊ የሆኑ ዲክመንቶችን፣ የአሰራር ሂደት ቅደም ተከተሎችን እና ሪከርዶቸን መያዝ፣
አግባብ ባለው ቦታ ማስቀመጥ እና ሲጠየቅ ማሳየት አለበት፤

29 | P a g e
ክፍል አስራ አንድ፡ ስለ ሰው ኃይልና ስልጠና
11.1 የቴክኒካል ባለሞያዎች ሃላፊነትና ግዴታዎች
11.1.1 ማንኛዉም የቴክኒካል ባለሞያ በድርጅቱ ውስጥ የምግብ ዘይት ደህንነትና ጥራትን የማረጋገጥ
ሀላፊነት አለበት፣
11.1.2 ማንኛውም ቴክንካል በለሙያ በድርጅቱ ውስጥ የሚከሰት የምርት ደህንነትና ጥራት መጓደል
ጋር ተያይዞ ለሚከሰቱ ማንኛውም የጤና ችግሮች ከድርጅቱ በተጨማሪ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
11.1.3 የምግብ ዘይት አምራች ድርጅቱ ባለሞያዎች በተለያየ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ በስራ
በማይኖርበት ጊዜ ተክቶ ሊሰራ የሚችል ተመሳሳይ ሙያ ያለው ባለሙያ ድርጅቱ መተካት
ይኖርበታል የተተካው ባለሙያ ምርትን ደህንነትና ጥራትን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት
11.1.4 ቴክኒካል ባለሙያዉ በድርጅቱ የተመረተ ምርት ጥራትና ደህንነቱን የማያሟላ መሆኑን
ሲያውቅ ሁኔታዉን በድርጅቱ ውስጥ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ አለበት፡፡
11.1.5 ድርጅቱ የሚቀርብለትን መረጃ በአፋጣኝ የማያስተካክልና ተደጋጋሚ ጥፋቶች ሲፈፅም
ባለሞያው ለባለስልጣኑ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡
11.1.6 የምግብ ዘይት አምራች ድርጅት ስለ እያንዳንዱ ባለሙያ የስራ ድርሻና ኃላፊነት የሚገልጽ
የስራ መዘርዘር ሰነድ ማዘጋጀትና ለባለሙያዎች የማሳወቅ ግዴታ አለበት፣ በዚህን መሰረት
ባለሙያዎቹ ግዴታቸውን መወጣት አለባቸው
11.2. ስለሚሰጠው ስልጠና
11.2.1 ተቋሙ ከምርት ስራ ጋር ግንኝኑነት ያላቸውን ባለሙያዎች አስፈላጊውን ስልጠና መስጠት
አለበት፤
11.2.2 ማንኛውም ከምርት ደህነትና ጥራት ጋር በተያያዘ የተሰጡ ስልጠናዎች መረጃ በአግበቡ
ተደራጅቶ መያዝና ሲጠየቅ ማሳየት ይኖርበታል፤
ክፍል አስራ ሁለት፡ ምግብ ስለማስተዋወቅ
ማንኛዉም የምግብ ዘይት አምራች ድርጅቶች በማንኛውም ህጋው የማስታወቂያ መንገድ ተጠቅሞ
ያመረተውን ምርት ማስተዋወቅ የሚችለው በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባወጣው የምግብ ማስታወቂያ
መሰረት ምርቱን ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

30 | P a g e

You might also like