Professional Documents
Culture Documents
የምግብ ደህንነት ጥበቃ
የምግብ ደህንነት ጥበቃ
o ጥቃቅን ተህዋስያን ማለት በአይን ሊታዩ የማይችሉ በጣም ደቃቅ የሆኑ ህይወት
ያላቸው ፍጡር ሲሆኑ
በሶስት ክፍል ይመደባሉ
ጥሩ ፤መጥፎ እና አደገኛ ይባላሉ
ጥሩ የሚባሉት ለምግብ እና መጠጦች ዝግጅት የሚያገለግሉ ሲሆን
( አይብ፤እርጎ፤ቢራ እና ወይን ) ፤ለመድሃኒት (ፔኒሲሊን)
መጥፎ የሚባሉት ደግሞ የምግብን ሽታ እና ጣዕም የሚለውጡ ሲሆን፤ ባብዛኛው
ሰዎችን አያሳምሙም
አደገኛ የሚባሉት ደግሞ ሰዎችን የሚያሳምሙ አልፈውም ለሞት ሊያደርሱ የሚችሉ
ሲሆን (ጀርሞች)፤ባክቴርያ፤ቫይረስ፤ጥገኛ
ምሳሌዎች
ባክቴርያ፡-ሳልሞኔላ፣ሺጌላ፣ኢ-ኮላይ፣ካምፓይሎባክተር
ቫይረስ ፡-ሄፓታየተስ ኤ፣ ኖሮቫይረስ
ጥገኛ ፡- ጃርዲያ፣ትሪቺኔላ
እርሾ(YEAST) & ሻጋታ(MOULD )
ጥቃቅን ተህዋስያን የት ይኖራሉ?
ተህዋስያን ማንኛውም ቦታ ሊኖሩ ቢችሉም በበለጠ የሚገኙት
ዓይነ ምድር
አፈር፣ውሃ
አይጦች ፣ተባይዎች
የቤትም ሆኑ የዱር እንስሳት ላይ
ሰዎች ላይ(መገጣጠሚያ፣ አፍ፣ አፍንጫ፣ አንጀት፣ እጆች፣ ጥፍሮች እና
ቆዳችን ላይ)
መጠናቸውስ ?
አንድ የእስፒል ጭንቅላት አንድ ሚሊዮን ጥቃቅን ተህዋስ ሊሸፍን ይችላል
10000 ተህዋስያን ጎን ለጎን ቢያያዙ የ1 ሴ.ሜ ቦታ ሊሸፍኑ ይችላሉ
1 ማንኪያ አፈር ውስጥ 1 ቢሊየን ጥቃቅን ህዋስ ሊኖር ይችላል
በ 1 ሴ.ሜ ስኩዌር የሰው ቆዳ ላይ 100000 ተህዋስያን ሊገኝ ይችላል
ጀርሞች እንዴት ይንቀሳቀሳሉ?
በእንስሳት እግር፣ፀጉር፣ በሰው እጅ፣በንፋስ ከቦታ ቦታ ይዘዋወራሉ
በዚህ ሂደት ውስጥ ምግብ ይበከላል
አንድ ምግብ አምራች ግለሰብ በቫይረስ ተጠቅቶ የማምረት ሂደቱን ከቀጠለ
ቫይረሶች በምግቡ ውስጥ በመግባት ደምበኛውን ሊበክል ይችላል
(ሄፓታይተስ ኤ፣ኖሮቫይረስ)
ዙኖዝስ ተላላፊ በሽታዎች ሲሆኑ ከእንስሳት ወደ ሰው ይተላለፋሉ ለምሳሌ
አቭያን ኢንፍልዌንዛ ፣ ኢ ኮላይ
እድገት እና አረባብ
ጀርሞች ለማደግ እና ለመራባት ምግብ፣ውሃ፣ግዜ እና ሙቀት ያስፈልጋቸዋል
አንድ ባክቴርያ በ15 ደቂቃ 2 ይሆናል፤ይህ ማለት በ6 ሰዓት ውስጥ
ከ16000000 በላይ እራሱን ያባዛል
አንዳንድ ባክቴርያዎች ጉዳት ለማድረስ በከፍተኛ ቁጥር መኖር አለባቸው፣
አንዳነዶች ደግሞ ጥቂቶችም ቢሆኑ ጎጂ ናቸው
ቫይረሶች ከባክቴርያዎች በብዙ እጥፍ ያነሱ ደቃቅ ሲሆኑ በምግብ /ውሃ
ውስጥ አያድጉም ፣ነገር ግን የመተላለፊያ መንገድ ግን ይሆናቸዋል
የሩብ ሊትር ውሃን መልክ ለመለወጥ (ደመና) 2.5 ቢልዮን ባክቴርያ
የወስዳል ነገር ግን አነድን ሰው ጉዳት ላይ ለመጣል ከ15 እስከ 20 ጎጂ
ባክቴርያ በቂ ነው
ምልክቶች
በየአመቱ በቢልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አንዴ ወይም ከዚያ በላይ በምግብ
ወለድ በሽታዎች ይጠቃሉ ምንም እንኩዋ የበሽታቸው መንስዔ ምግብ
መሆኑን ባያውቁም
የተለመዱ ምልክቶቹ የጨጓራ ህመም፣ማቅለሽለሽ፣ተቅማጥ
አብዛኞቹ ምግብ ወለድ በሽታዎች ምግቡ ከተወሰደ ከ 24-72 ሰዓታት
ውስጥ ምልክት የሚያሳዩ ሲሆን
የምግብ ወለድ በሽታዎች ጉዳት ከባድ ለሆኑ በሽታዎች እስከማጋለጥ
የሚደርስ ሲሆን ካንሰር፣የደም እና የነርቭ ስርዓት መዛባትን ሊያስከትሉ
ይችላሉ(3%)
ምልክቶች
ከታመሙ ያሳውቁ
የምርት አሻጊ ሰራተኞች በተለይ ከሚከተሉት በሽታዎች ባንዱ እንኳ
ከተጠቁ ማሳወቅ አለባቸው ምርት ከመጀመራቸው በፊት ለምሳሌ፡-
ሄፓታይተስ ኤ ፣ተቅማጥ፣ማቅለሽለሽ፣የቆዳ ኅመም(እብጠት እና መቁሰል)፣
ከጆሮ ከዓይን እና ከአፍንጫ ፈሳሽ መምጣት እና የመሳሰሉት
ቢቻል ከታመሙ እና ምልክቶች ከተወገዱ ከ48 ሰዓት በፊት ምግብ
አያዘጋጁ ካልተቻለ ደግሞ እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና እና በውሀ ይታጠቡ
ኬሚካል በካዮች
የተፈጥሮ መርዞች (አፍላቶክሲን) ምግቦች በሚሻግቱ ስዓት ሊፈጠር
ይችላል ጉዳቱ የጉበት ካንሰር ድረስ
ብረቶች ፣ ፀረ ተባይ ኬሚካሎች፣ለጽዳት የሚውሉ ፣ ከመጠን ያለፉ
የምግብ መቀመሚያዎች
ለምሳሌ ፡-ሜታይል ሜርኩሪ ፣አርሴኒክ፣
ጥጥር በካዮች
ጠጠር፣ብረት፣አጥንት፣ፕላስቲክ
የምግብ ወለድ በሽታን ለመከላከል