You are on page 1of 19

የኢትዮ á ያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ

ሪፐብሊክ

የፌዴራል የመንግስት ሠራተኞች


ሥነ ምግባር ኮድ

ሐምሌ 2009 ዓ.ም.

ማውጫ
0
ርዕስ ገጽ

መግቢያ….………………………………………………………………………………………….….3

ክፍል አንድ፡

ጠቅላላ…………………………………………………………………………………………………4

፩. አጭር ርዕስ…………………………………………………………………………………………4

፪. ትርጓሜ………………………………………………………………………………………….….4

፫. የጾታ አገላለጽ……………………………………………………………………………….….….5

፬. የስነ - ምግባር ኮዱ ዓላማ…………………………………………………………………….…..6

፭. የስነ - ምግባር ኮዱ አስፈላጊነት……………………………………………………………………6

፮. የስነ-ምግባር ኮዱ የተፈፃሚነት ወሰን……………………………………………………………7

ክፍል ሁለት፡

፯.. የመንግስት ሰራተኞች ሊከተሉዋቸው የሚገቡ የስነምግባር መርሆዎች-----------------------------7

1. ቅንነት/ የተሟላ ስብእና -----------------------------------------------------------------------------------7

2. ታማኝነት------------------------------------------------------------------------------------------------------8

3. ግልጽነት-------------------------------------------------------------------------------------------------------9

4. ምስጢር መጠበቅ-------------------------------------------------------------------------------------------10

5. ሐቀኝነት-----------------------------------------------------------------------------------------------------10

6. ተጠያቂነት--------------------------------------------------------------------------------------------------10

7. የሕዝብ ጥቅም ማስቀደም--------------------------------------------------------------------------------11

8. ህጋዊ በሆነ ስልጣን መገልግል--------------------------------------------------------------------------11

9. አድልኦ አለመፈጸም--------------------------------------------------------------------------------------12

10. ህግ ማክበር-----------------------------------------------------------------------------------------------12

11. ለህዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መሰጠት-----------------------------------------------------------13

12. አርአያ መሆን---------------------------------------------------------------------------------------------13

፰. ከተለያዩ አካላት ጋር ስለሚኖር ግንኙነት----------------------------------------------------------------14

1. ከዜጎች ጋር መኖር ስለሚገባው ግንኙነት-------------------------------------------------------------14

1
2. ከበላይ ኃላፊ ጋር ስለሚኖር ግንኙነት-----------------------------------------------------------------14

3. ከቅርብ ኃላፊ ጋር ስለሚኖር ግንኙነት----------------------------------------------------------------15

4. ከሥራ ባልደርቦች ጋር ስለሚኖር ግንኙነት-----------------------------------------------------------15

5. ከኩባንያዎች/ ከማህበራት/ ጋር ስለሚኖር ግንኙነት-------------------------------------------------15

6. ከተቋማት ጋር ስለሚኖር ግንኙነት---------------------------------------------------------------------16

7. ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ስለሚኖር ግንኙነት------------------------------------------------------------16

8. ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች----------------------------------------------------------------------------------16

9. መካከለኛ አመራር ከፈፃሚዎች ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት---------------------------------------17

፱. የሴቶችን መብት ማክበር------------------------------------------------------------------------------------18

ክፍል ሦስት፡

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች--------------------------------------------------------------------------------------------18

፲. የስነ-ምግባር ኮዱ አፈፃፀም …………………………………………………………………..….18

፲፩. በስነ ምግባር ጉድለት ስለሚወሰድ እርምጃ-------------------------------------------------------------19

፲፪. የስነ ምግባር ኮዱን በሥራ ላይ የማዋል ግዴታ-------------------------------------------------------19

፲፫. ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች…………………………………………………………..…19

፲፬. ኮዱን ስለማሻሻል…………………………………………………………………………………19

፲፭. ኮዱ የሚጸናበት ጊዜ----------------------------------------------------------------------------------------19

መግቢያ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከደረሰችበት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማህራዊ የእድገት ደረጃ በመነሳት የፐብሊክ ስርቪስ
ሥርዓቱ ወቅቱን ያገናዘበ፣ ዘመናዊና የተሻለ ለማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣

 ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብን የሚሽከም የመንግስት ሰራተኛ ለመፍጠር፣

2
 ከሙስናና ብልሹ አሰራር የጸዳ፣ ለህዝብ አገልግሎት የሚተጋ እና የሥነ-ምግባር መርሆዎችን ተግባራዊ
የሚያደርግ ትጉህ ባለሙያ ለመፍጠር፣
 በሙያው ብቁና ውጤታማ ፣ በሥነ-ምግባሩ ምስጉን፣ አገር ወዳድ ባለሙያና አመራር ለማፍራት፣
 በመንግስት መስሪያ ቤቶች ዜጎች ፍትሓዊና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት የሚያገኙበት
ተቋም እንዲሆንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣

ይህ የሥነ-ምግባር ኮድ በሁሉም የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች ላይ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ የአስፈጻሚ አካላትን
ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው በአዋጅ ቁጥር 916/2008 አንቀፅ 7(1) (ሰ) ለፐብሊክ ሰርቪስና
የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር ለማስፈጸም እንዲቻል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ
ይህን ኮድ በስራ ላይ እንዲውል አውጥቷል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ ድንጋጌዎች

፩.አጭር ርዕስ

ይህ ኮድ “የፌዴራል የመንግስት ሠራተኞች ሥነ-ምግባር ኮድ” ተብሎ ሊጠቀስ

ይችላል፡፡

፪.ትርጓሜ

3
የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር፣ በዚህ ኮድውስጥ፡-

፩. “የፌዴራል የመንግስት ሰራተኛ" ማለት በፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ

በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ሲሆን የሚከተሉትን አይጨምርም፡፡

ሀ. ሚኒስትር ዴኤታዎችን ምክትል ዋና ዳይሬክተሮችን፣ እንዲሁም በተመሣሣይ ደረጃና ከዚያ በላይ የሆኑ
ኃላፊዎችን፤
ለ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትንና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትን፣
ሐ. የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኞችንና ዓቃቢያነ ሕግን፣
መ. የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባሎችን እንዲሁም በመከላከያ ወይም በፖሊስ ደንብ
የሚተዳደሩ ሌሎች ሰራተኞችን
ሠ.አግባብ ባለው ሌላ ሕግ በዚህ የሥነ-ምግባር ኮዱ እንዳይሽፈኑ የተደረጉ ሰራተኞችን፣
፪. “ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር” ማለት እንደ ቀደም ተከተሉ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት
ሚኒስቴር ወይም ሚኒሰትር ነው፡፡
፫. “የበላይ ሃላፊ” ማለት የመንግስት መስሪያ ቤትን በበላይነት የሚመራ ወይም ምክትሎቹ ናቸው፡፡
፬. “መካከለኛ አመራር” ማለት በሜሪት በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሰራ ዳይሬክተር ወይም ቡድን መሪ ነው፡፡

፭. “ሥነ-ምግባር” ማለት በእያንዳንዱ ተቋም ወይም ማህበረሰብ ውስጥ ስህተት የሆኑት ድርጊቶች ወይም
ተግባሮች እንዳይፈጸሙ፣ ትክክል የሆኑት ደግሞ በቀና አስተሳሰብ እንዲፈጸሙ የሚያስችል ድርጊት ነው፡፡

፮. “የሥነ-ምግባር መርሆ” ማለት በአንድ ተቋም ውስጥ ጥሩና መጥፎ ድርጊት፣ መደረግ ያለበትና የሌለበት
ድርጊቶች የሚገለጽበት አጠቃላይ የአስተሳሰብ፣ የአመለካከት እና የተግባር አፈጻጸሞች የሚመሩበት
ሥርዓት ነው፡፡
፯. "የጥቅም ግጭት" ማለት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከመንግስት ወይም ከሕዝብ ጥቅም ጋር
የሚጋጭ ወይም የሚቃረን ከመንግስት ስራ ጋር በተያያዘ የሚፈጠር ማንኛውም ጥቅም ማለት ነው፡፡
፰."ሀብት" ማለት በሠራተኛው ይዞታ ስር የሚገኝ ማናቸውም የሚንቀሳቀስ፣ የማይንቀሳቀስ እና አዕምሯዊ
ንብረት ነው፡፡
፱. "ጥቅሞችን ማሳወቅ" ማለት ሠራተኛው በባለቤትነት ወይም በይዞታው ስር የሚገኝ ሐብትን ለፌዴራል
ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ማሳወቅ ነው፡፡
፲."ስጦታ" ማለት በፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ባለው የሥራ ደረጃና ኃላፊነት ወይም በሥራው
አጋጣሚ ምክንያት የተሰጠው ዋጋ ወይም ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው ነገር ማለት ነው፡፡

4
፲፩. "መስተንግዶ" ማለት ለሠራተኛው ከሥራው ጋር በተያያዘ ምክንያት የተደረገ በነፃ የተሰጠ የምግብ፣
የመጓጓዣ፣ የሆቴል ወይም ተመሳሳይነት ያለው የመዝናኛ አገልግሎት ነው፡፡

፲፪ "ሚስጥር" ማለት የመንግስት ሰራተኛው በስራው ምክንያት ያወቀውን የመንግስት፣ የህዝብና የግለሰብ
ጥቅም የሚጎዱ በመሆናቸው በሕግ ወይም በሚመለከተው አካል ውሳኔ እንዳይገለጹ የተደነገጉ
መረጃዎች ናቸው፡፡

፫. የጾታ አገላለፅ

በሥነ-ምግባር ኮዱ ውስጥ በወንድ ፆታ የተገለፀው ሴትንም ይጨምራል፡፡

፬. የሥነ-ምግባር ኮዱ ዓላማ

ዋና ዓላማ

በየደረጀው ባሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፈጣን ፣ ቀልጣፈና ውጤታማ አገልግሎት ለዜጋው መስጠት
እንዲቻል መልካም ሥነ-ምግባር ያላቸው ሠራተኞችንና መስሪያ ቤቶችን በጥራትና በብዛት ማፍራት
ነው፡፡

ዝርዝር ዓላማ

ሀ. ተገልጋዩ ሕብረተሰብ በመንግስት ባለሥልጣናትና ሠራተኞች በሚሰጡ የመንግስት


አገልግሎቶች ላይ እምነት እንዲኖረው ለማድረግ፣
ለ. የመንግስት ሠራተኞች የመንግሥትን ፖሊሲዎችን፣ ተልዕኮዎችንና ተግባራትን
በውጤታማነትና በጥራት መፈፀም እንዲችሉ፣ አፈፃፀሙ ግልፅነትና ተጠያቂነት
የሰፈነበት እንዲሆን ለማስቻል፤
ሐ. የጥቅም ግጭት ሊከሰት እና ሊወገድ የሚችልበትን ሁኔታ ለማመላከት፣
መ. የመንግስት ሠራተኞች የኪራይ ሰብሳቢነትን አመለካከትና ተግባርን በመታገል
እንዲያከስሙ ለማድረግ፣
ሠ. የመንግስት ሠራተኞች ህዝባዊ ወገንተኝነትን በመላበስ የሚሰጡት አገልግሎት
ሕዝቡን የሚያረካ እንዲሆን ለማድረግ፣
ረ. የመንግስት ሰራተኛው በአገልግሎት አሰጣጥ መጓደል የተጠያቂነት ስርኣትን
ለመዘርጋትና ለማስፈን፡፡
፭. የሥነ-ምግባር ኮዱ አስፈላጊነት

5
ሀ. የመንግስት ተቋማት እና ሰራተኞች የሚመሩበትን የሥነ-ምግባር መርሆዎችን

ስራ ላይ በማዋል በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ እና በአቅሙ የጎለበተ የመንግስት ሰራተኛ ለማፍራት፣

ለ. የሪፎርም መሳሪያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳ የዲሲፕሊን ማጎልበቻ

መሳሪያ ለማድረግ፣

ሐ. የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ በዜጎች ቻርተር መሰረት ለመተግበር፣

መ. ሕዝብና ዜጋው ከመንግስት ሰራተኛው የሚጠብቁትን ከፍተኛ የአገልጋይነት

ባህርይና ተግባር ለማመላከት፣

ሠ. ከእያንዳንዱ መካከለኛ አመራርና ሰራተኛ የሚጠበቅ ግዴታና መብት ለማመላከት፣

ረ. የሥነ ምግባር መጓደል ሲያጋጥም ስለሚወሰዱ የዲሲፕሊን እርምጃዎች ግልጽ

ለማድረግ፣

ሰ. በተለያዩ ሕጎች ውስጥ የሚገኙትን የሥነ-ምግባር መርሆዎችን በማሰባስብ ወጥና

የተቀናጀ ኮድ እንዲሆን ለማድረግ፡፡

፮. የሥነ- ምግባር ኮዱ የተፈፃሚነት ወሰን

በፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ በሜሪት በቋሚነት ተቀጥረው በሚሰሩ


ሰራተኞች ላይ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለት
፯. የመንግስት ሰራተኞች ሊከተሏቸው የሚገቡ የሥነ ምግባር መርሆዎች
የመንግስት ሰራተኞች የተጣለባቸውን ሀገራዊና ህዝባዊ አደራ በብቃት፣ በታማኝነት፣
በውጤታማነት ለመፈፀም የሚከተሉትን መርሆዎች ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው፡፡
1. ቅንነት/ የተሟላ ስብዕና /Integrity

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣

ሀ. የሚሠጠውን አገልግሎት በሃቀኝነት እና በተሟላ አኳኋን በመስጠት ተገልጋዩን

ማርካት፤

ለ. ለመንግሥት፤ ለሕዝብና ዜጋው የገባውን ቃል ኪዳን ማክበርና በቅንነት

6
የተሰጠውን የሥራ ኃላፊነት የመፈፀም ግዴታ አለበት፣
ሐ. በሥራ ሰዓትም ሆነ ከሥራ ሰዓት ውጭ ቅንና ሥነ-ምግባር የተላበሰ መሆን አለበት፣

መ. የሚሠጠው ምክር እና አገልግሎት ያልተዛባና ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፣

ሠ. ለሥራ ባልደረቦቹ ተገቢውን ክብር በመስጠት መታመን መቻል ፤

ረ. በሥራ አፈፃፀሙና በግል ባህርይው ሕብረተሰቡ በመሥሪያ ቤቱ ላይ ሙሉ እምነት

እንዲያሳድር ማድረግ፣

ሰ. ተገቢ ካልሆኑ ድርጊቶች (ከአደንዛዥ እፆች ተጠቃሚነት፣ ከቁማርተኝነት፣ ከስካር፣

መጠጥ ጠጥቶ በሥራ ገበታ ላይ ከመገኘትና መሰል አድራጎቶች) ራሱን መጠበቅ

አለበት፣

ሸ. ተገልጋዩ በአገልግሎት አስጣጡ ላይ ለሚያቀርባቸው ጥያቄዎችን በቅንንት ተቀብሎ

ተገቢ ማብራሪያ፣ ምላሽ እና መረጃ መስጠት፡፡

2. ታማኝነት /Loyality

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣

ሀ. ለሕገ መንግስቱ፣ ለሀገሪቱ ሕጎች፣ ደንቦች ፣ መመሪያዎች እና አሠራሮች ታማኝ

መሆን አለበት፣

ለ. የሀገሪቱን ሕገ መንግስት ማክበርና ማስከበር፤ ሕገ መንግሥቱን መጠበቅ፣ ሕገ መንግሥቱን ከሚፃረሩ


ማናቸውም ተግባሮች መራቅና ሥራውን በታማኝነት የማከናወን ግዴታ አለበት፣

ሐ. የዜጎችና የሕዝቡን ጥቅሞች ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ እንዲሁም ልዩ ትኩረት


የሚሹ አካላትን በተገቢው መንገድ በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል አለበት፣
መ. የመንግሥትን የሥራ ጊዜና ሃብት ለግል ጥቅም አለማዋል፤

ሠ. ከማታለል፤ ጉቦ ከመቀበል፣ እምነት ከማጉደል፣ ሙስና ከመፈጸምና በስልጣን


ያለአግባብ ከመጠቀም መታቀብ አለበት፣
ረ. የመንግሥት ሀብትን ለታለመለት ዓላማና ግብ በቁጠባ ጥቅም ላይ ማዋል አለበት፡፡
ሰ. በእውነት ላይ ተመስርቶ መስራት፣ የሀሰት መረጃዎች እና ማስረጃወችን ከመጠቀም

7
ሆነ ከመስጠት መራቅ አለበት፣
ሽ. በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ባለው የሥራ ደረጃና ኃላፊነት የተገኘ እውነተኛ
መረጃን ለዜጎች እና ለተገልጋይ አገልግሎት ብቻ እንዲውል የማድረግ ኃላፊነት
አለበት፣
ቀ. የቅርብ ኃላፊውን ሕገወጥ ትዕዛዝ አለመፈጸም፣
በ. በመስሪያ ቤቱ ውስጥ ሕገወጥ ድርጊት የተፈጸመ መሆኑን ካወቀ ለቅርብ ኃላፊው
ወይም ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ወይም ለሚመለከተው የመንግሥት አካል የማሳወቅ ግዴታ አለበት፣
ተ. ሙስና እንዳይፈጸም ማስተማር፣ መታገል እና ተፈጽሞ ሲገኝ ማጋለጥ አለበት፣

ቸ. ለሚሠጠው አገልግሎት ከተገልጋዩ ስጦታ መቀበል የለበትም፣

ቸ. ህዝብንና ሀገርን በታማኝነት ማገልገል የክብር ሁሉ ክብር መሆኑን መረዳት አለበት፡፡

3. ግልፅነት /Transparency

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣


ሀ. አግባብነት ባለው ሕግ በምስጢርነት መጠበቅ ከሚገባቸው መረጃዎች በስተቀር
ለዜጎች እና ለተገልጋይ ማንኛውንም መረጃ እና ማብራሪያ መስጠት፣
ለ. የሚያከናውናቸውን የሥራ ተግባራትና የሚሰጠውን ውሳኔ ግልጽ ማድረግ ግዴታ
አለበት፣
ሐ. በስራ ቦታው የራሱን ማንነት የሚገልጽ ባጅ ማድረግ ይጠበቅበታል፣
መ. ተገልጋዮች ፍትሐዊ አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ

ሁኔታዎች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች የማሳወቅ፤ የሚሰጡ መረጃዎች

ትክክለኛ፤ ተደራሽና ወቅታዊ መሆናቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት፣

ሠ. በስራ አጋጣሚ የተፈፀሙ ስህተቶችን ለማረም ዝግጁ መሆን፣ ፈጣን የማስተካከያ

እርምጃዎችን በመውሰድ ለሚለከተው አካል የማሳወቅ ግዴታ አለበት፣

ረ. ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ማቅረብና ሲጠየቅ ማብራሪያ የመስጠት

ሃላፊነት አለበት፡፡

ሰ. ከስራው ጋር በተያያዘ በተለያዩ አካላት የሚደረግለትን መስንግዶ ማሳወቅ አለበት፡፡

8
4. ምስጢር መጠበቅ /Confidentiality
ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣

ሀ. በስራ አጋጣሚ ያወቃቸውን የመንግስት ወይም የተገልጋይ ሚስጥሮችን

ከባለቤቶቹ ፈቃድ ውጭ ለሶስተኛ ወገን መስጠት የለበትም፣

ለ. በስራ አጋጣሚ ያወቃቸውን ሀገርን፣ ህዝብንና መንግሥትን ሊጎዳ የሚችሉ

መረጃዎች በምስጢር በመያዝ በፍጥነት ጉዳዩ ለሚመለከተው ለመንግስት አካል

ማሳወቅ አለበት፡፡

5. ሐቀኝነት /Honesty

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣

ሀ. ሥራን ዕውነትን በተከተለና ቅንነት ባለው አኳኋን መሥራት፣


ለ. ህግ ከሚፈቅደው ውጪ ከመስራት ፣ ከስነምግባር ብለሹነትና ተገቢ ካልሆኑ
ድርጊቶች መራቅ አለበት፣

ሐ. ለተገልጋዩ ህብረተሰብ የሚሰጠውን አገልግሎት ከማታለል እና ከአድሎ በጸዳ

ሁኔታ መስጠት አለበት፡፡

6. ተጠያቂነት /Accountability

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣


ሀ. ከሕግ ውጭ ለሰጠው ውሳኔና አለአግባብ ጥቅም ላይ ላዋለው የሕዝብ ሀብት

እንደጉዳዩ ሁኔታ በተናጠልና በጋራ ተጠያቂ ይሆናል፣

ለ. ለመንግሥት ሥራ የተመደበለትንና ስራ ላይ ያዋለውን ሐብትና ንብረት መጠን

ሪፖርት ማድረግና ለሚፈጠር የአጠቃቀም ጉድለት ተጠያቂ ይሆናል፣

9
ሐ. ትዕዛዝ ባለማክበር በቸልተኝነት፣ በመለገም ሆን ብሎ ጉዳዮችን በማዘግየት፣

ባለጉዳዮችን በማጉላላት፣ የአሰራር ስነ-ስርዓት እና የመንግስትን ፖሊሲ ባለመከተል

በስራ ላይ ላደረሰው ጥፋት ተጠያቂ ይሆናል፣

መ. የመንግስት ስራ እንዳይሰራ ሆን ብሎ በማወክ እንዲሁም ከሚያወኩት ጋር መተባባር

ያስጠይቃል፣

ሠ. የሀገቱን ባህልና ወግ የሚቃረን የአለባበስ ስርዓት በስራ ቦታ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡


ረ. የሚመለከተው የመንግስት ሰራተኛ ጥቅምን የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡

7. የሕዝብ ጥቅም ማስቀደም /Serving the Public Interest

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣

ሀ. በማናቸውም ጊዜና ቦታ በሚያከናውኗቸው ተግባራትና በሚያስተላልፏቸው


ውሳኔዎች ለሕዝብ ጥቅም ቅድሚያ መስጠት አለበት፣
ለ. ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮችን አግባብነት ያላቸውን መረጃዎችንና ማስረጃዎችን መሰረት በማድረግ
ውሳኔ መስጠት አለበት፣
ሐ. ከመንግሥት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በፍትሐዊነትና በታማኝነት ለሕዝቡና ለዜጋው የመስጠት
ኃላፊነት አለበት፡፡
8. ህጋዊ በሆነ ሥልጣን መገልገል /Exercising Legitimate Authority

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛው፣


ሀ. በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችና መካካለኛ አመራር ስራቸውን ሲያከናወኑ በሕግ
የተሰጣቸውን ሃላፊነት መሰረት በማድረግ መሆን አለበት፣
ለ. የተሰጠውን የመንግስት የስራ ሃላፊነት ለግል ጥቅም ማግኛ ማድረግ የለበትም፣
ሐ. በሕግ ከተሰጠው የስራ ሃላፊነት ውጪ የሆነ ተግባር መፈጸም የለበትም፣
መ. ስልጣኑን መሰረት በማድረግ በሚሰጠው አገልግሎት በብሔር ብሔረሰብ፣ ሃይማኖት፣ በጾታ እና
በፖለቲካ አመለካካት ልዩነት ማድረግ የለበትም፡፡
ሠ. በሕግ ከተፈቀደ ጥቅማ ጥቅም በስተቀር በያዘው ተግባርና ኃላፊነት ምክንያት የተለየ ጥቅም
መቀበል የለበትም፡፡

10
9. አድልዎ አለመፈፀም /Impartiality

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛው፣


ሀ. በዘር፤ በቀለም፤ በፆታ፤ በቋንቋ፤ በሃይማኖት፣ በብሄር በብሄረሰብ፤ በአካል ጉዳት፣ በሀብት፣ በፖለቲካ
አመለካከት፣ በአካባቢ ወገናዊነት፣ ወይም በሌላ ምክንያት ልዩነት ሳያደርግ በፍትሐዊነት ሕዝብንና ዜጋን
ማገልገል አለበት፣
ለ. የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ግልፅነትን ማዕከል በማድረግ ሥራውን ያለአድልዎ የመፈፀም ግዴታ አለበት፣
ሐ.ሙያዊ ግዴታውን በሚወጣበት ወቅት ሆንብሎ ወይም በቸልተኝነት ሕግን በመጣስ
ማንኛውንም ሰው፤ ቡድን ወይም አካል የሚጎዳ የአድልዎ ተግባር መፈፀም
የለበትም፡፡

10. ህግን ማክበር /Respecting the Law

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣


ሀ. ውሳኔ በመስጠት የዕለት ተዕለት ተግባሩን ሲያከናውን የመንግሥትን ፖሊሲና ስትራቴጂን፣ የሀገሪቱን ሕገ
መንግስት፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን መሠረት በማድረግ የመፈፀምና የማስፈጸም
ኃላፊነት አለበት፣
ለ. ለሕግ ተገዢ በመሆን ፍትሃዊነትን በተግባር የማረጋገጥ ግዴታ አለበት፡፡
ሐ. የሰጠው ውሳኔ ወይም አገልግሎት ህግንና ሕጋዊ አሠራርን ብቻ መሰረት አድርጎ የተፈጸመ መሆኑን
የማረጋገጥና በተጠየቀ ጊዜ መልስ የመስጠት ግዴታ አለበት፣
መ. ህገወጥ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ መከላከልና ተፈጽሞ ሲገኝ ለሚመለከተው
የመንግስት አካል የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡

11. ለሕዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት /Responsiveness

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣

ሀ. ሕዝብን በታላቅ አክብሮትና ትህትና መቀበል፣ በጥሞና ማዳመጥ፣ ፍትሃዊና

ተገቢውን ፈጣን ምላሽ መስጠት አለበት፣

11
ለ. ተገልጋይ የሚሰጠውን አስተያየት በቅንነት ተቀብሎ ማስተካከል አለበት፣

ሐ. የመልካም አስተዳደር እጦት ሊቀርፍ በሚችል አግባብ ሕዝብን የማገልገል

ግዴታ አለበት፡፡
መ. እውቀቱንና ክህሎቱን በመጠቀም የመንግስት ፖሊሲዎችንና የልማት ዕቅዶችን
በውጤታማነት መፈጸም አለበት፡፡

12. አርአያ መሆን /Exercising Leadership

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣


ሀ. በስነምግባር ኮዱ ውስጥ የተዘረዘሩትን መርሆዎችን በመቀበልና በመተግበር አርአያ

መሆን አለበት፣
ለ. ሰራተኛው የህዝብ ፍላጎትን የሚያረካ አገልግሎት መስጠት አለበት፣

ሐ. በመልካም ስነምግባር በመታነጽ አርአያ መሆን አለበት፣

መ.ከብልሹ አሰራርና የተቋሙን መልካም ስምና ዝና ከሚያጎድፉ ተግባራት በመቆጠብ አርአያ መሆን
አለበት፣

ሠ. ለስራ ባልደረቦቹ በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ሀሳብ በማቅረብ መተማመን፡፡

፰. ከተለያዩ አካላት ጋር ስለሚኖር ግንኙነት


1. ከዜጎች ጋር መኖር ስለሚገባው ግንኙነት
ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣

ሀ. ዜጎች ተገቢ፣ ውጤታማና ክብር የተላበሰ አገልግሎት ማግኘት እንደሚገባቸው ማመንና ተግባራዊ
ማድረግ አለበት፣

12
ለ. ለሕዝብ አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት በሕግ ሚስጥር ሆነው እንዲጠበቁ ከተለዩት ጉዳዮች በስተቀር
የጠየቁትን መረጃ ለዜጎች መስጠት አለበት፣
ሐ. ሕዝብንና ዜጎችን በእኩልነት የማገልገልና የማስተናገድ ግዴታ አለበት፣
መ. ሕዝብና ዜጎች ባገኙት አገልግሎት ላይ ያላቸውን አስተያየት፣ ቅሬታ፣ አቤቱታና ጥቆማ ማቅረብ
መቻላቸውን በማመን ላቀረቡት ሀሳብ ህጋዊና ወቅታዊ ምላሽ መስጠት አለበት፡፡
2. ከበላይ ኃላፊ ጋር ስለሚኖር ግንኙነት

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣

ሀ. ጥቅም ለማግኘት በበላይ ኃላፊ ላይ ጫና ማሳደር የለበትም፡፡


ለ. የበላይ አመራሩን የሥራ መመሪያና የሚሰጠውን የሥራ አቅጣጫ በቅንነት፣
በመልካም ስነምግባርና በሙያዊ ክብር መቀበልና ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት
አለበት፡፡
ሐ. ለበላይ አመራሩ ወቅታዊ፣ ተጨባጭ፣ ሐቀኛ፣ ግልፅና ተጠያቂነትን የሚያመላክቱ
ሪፖርቶችን የማቅረብ ሃላፊነት አለበት፡፡
መ. ወቅታዊ እና ተአማኒነት ያለው መረጃ የመስጠት ሃላፊነት አለበት፡፡
ሠ. ለበላይ አመራሩ የሚያቀርበው ሀሣብና ውሳኔ የተለየ ዝና ወይም ጥቅም ለማግኘት
አለመሆኑን የማረጋገጥ ሃላፊነት አለበት፡፡
ረ. ለተፈፀመ ጉድለትና ግድፈት ተገቢ እና እውነተኛ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ምላሽ
መስጠት አለበት፡፡

3. ከቅርብ ኃላፊ ጋር ስለሚኖር ግንኙነት


ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣

ሀ. ሥራውን በድርጊት መርሀ-ግብር መሰረት በተቀመጠው የአፈጻጸም ደረጃ እያከናወነ መሆኑን ለማወቅ
የቅርብ ኃላፊው የሚያደርገውን ክትትልና ድጋፍ በአግባቡ መቀበል አለበት፡፡
ለ. ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ችግር ካጋጠመው የቅርብ ኃላፊውን በማማከር የተሻለ መፍትሔ
የሚያስገኝ ውሳኔ መወሰን አለበት፡፡
ሐ. አዲስ አመራሮች ሲመደቡ ተገቢውን መረጃ የመስጠት ኃላፊነት አለበት፡፡
መ. ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከቅርብ ኃላፊው ልዩ ጥቅም እንዲያገኝ ማድረግ የለበትም፡፡
ሠ. ከቅርብ ሃላፊ የሚሠጡ ገንቢ አስተያየቶችን ተቀብሎ መተግበር አለበት፡፡

13
4. ከስራ ባልደረቦች ጋር ስለሚኖር ግንኙነት
ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣

ሀ. የዕለት ተዕለት ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት ከሌላው ሠራተኛ ጋር በመልካም ሥነ ምግባር


የታነፀ ትብብርና የስራ ግንኙነት የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
ለ.ከሁሉም የሥራ ባልደረቦች ጋር የሚኖረው ግንኙነት በሐቀኝነት፣ በትህትና በመከባበር ላይ
የተመሠረተ መሆን አለበት፡፡
ሐ.የሥራ ባልደረቦቹን በቅንነት ለማረምና ለመገንባት ያለውን ዝግጁነት በተግባር ማሳየት አለበት፡፡
መ. የቡድን ተልዕኮ የማሳካት፣ እውቀትና ክህሎትን ለስራ ባልደረቦች የማካፈል ኃላፊነት
አለበት፡፡
ሠ. በቡድን ውይይት ወቅት ለሚቀርቡ አስተያየቶች ክብር መስጠትና ተቀብሎ
ተግባራዊ ማድረግ አለበት፡፡
5. ከኩባንያዎች /ማህበራት/ ጋር ስለሚኖር ግንኙነት
ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣

ሀ.ሕጋዊ ሰውነት ባላቸው ተቋማት ውስጥ የሚያደርገውን የግል ተሳትፎ እና የሚያከናውነውን ማንኛውንም
ሥራ ለመስሪያ ቤቱ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡
ለ.ከስራው ጋር ተያያዥ የሆነ የንግድ ኩባንያ /ማህበራት/ ውስጥ በመሳተፉ ምክንያት የሚፈጠረውን
የጥቅም ግጭት ሲከሰት ለቅርብ ኃላፊው ወይም ለሚመለከተው አካል ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
ሐ.በሚሰራበት መስሪያ ቤት ተወክሎ የሚያደርገው ግንኙነት ሕግና የአሰራር ሥርዓትን መሠረት ያደረገ
መሆን አለበት፡፡
6. ከተቋማት ጋር ስለሚኖር ግንኙነት
ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣

ሀ. ማንኛውንም ግንኙነቶች በሕግና ደንብ መሠረት መፈፀም አለበት፡፡


ለ. ሕጋዊ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሚደረግ ጥረትን ማስወገድ እና የሚሳተፉትን
የማጋለጥ ግዴታ አለበት፡፡
ሐ. የተቋማትን የእርስ በእርስ ግንኙነት ሊያጐለብት የሚችል ቀና ትብብር የማድረግ
ኃላፊነት አለበት፡፡
7. ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ስለሚኖር ግንኙነት
ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣
ሀ. በከፍተኛ አመራሩ ወይም ጉዳዩ በሚመለከተው የስራ ክፍል ሊገለጽ የሚገባውን መረጃ መስጠት
የለበትም፣
ለ. ምስጢራዊ ወይም በሕግና በመመሪያ እንዳይገለጹ የተከለከሉ መረጃዎችን

14
ማስተላለፍ የለበትም፣
ሐ. ከተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት አንጻር በቅንነት፣ በታማኝነት፣ ተገቢና ወቅታዊ መረጃ የመስጠት ኃላፊነት
አለበት፣
መ. በመገናኛ ብዙሃን መረጃ ሲሰጥ የሀገር፣ የሕዝብ፣ የተቋም፣ የአመራሮች፣ የግለሰቦች መብት፣ መልካም
ስምና ዝና የሚያጎድፍ መሆን የለበትም፡፡

8. ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች


ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣
ሀ.መንግስት መስሪያ ቤቱን በመወከል በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ስብሰባዎች ላይ ሲካፈል የሀገርን አቋምና
ክብር በጠበቀ መንገድ በታማኝነት ሃሳቡን መግለጽና ማቅረብ አለበት፣
ለ. በዓለም አቀፋዊ ስብሰባዎች ላይ የመንግሥት ፖሊሲዎችና የሴክተሩን ብሔራዊ ፖሊሲ በማብራራት
ማቅረብ አለበት፡፡
ሐ. ከተሰጠው የውጭ ሀገር ተልዕኮ ወደ ሀገር እንደተመለሰ በአግባቡ የተደራጀ ሪፖርት
ለላከው አካል የማቅረብ ግዴታ አለበት፣
መ. በዓለም ዓቀፍና አህጉራዊ ስብሰባዎች ላይ ከድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር በሚደረግ ግንኙነት የሀገርን፣
የመንግሥትን፣ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ የዜጎችን ክብርና መብት የሚነኩ
ሃሳቦችን ማራመድና ይህን የሚደግፉ ጉዳዮችን መፈጸም የለበትም፣ የሚፈፅሙ ወገኖችንም በጥብቅ
መቃወም አለበት፡፡
9. መካከለኛ አመራር ከፈጻሚዎች ጋር ስለሚኖራው ግንኙነት
ማንኛውም መካከለኛ አመራር፣
ሀ. ለፈጻሚዎች ግልፅ፣ ተጨባጭነት ያለው ተልእኮ መስጠት አለበት፣
ለ. ፈፃሚዎች የተሰጣቸውን ተግባር በውጤታማነት፣ በቅልጥፍናና በመልካም ስነ ምግባር
እንዲፈፅሙ ተገቢውን አመራር መስጠት አለበት፣
ሐ. በአፈፃፀም ለሚከሰቱ ችግሮች ፈፃሚ ሠራተኞችን ከመውቀስ አስቀድሞ ኃላፊነቱን
በመውሰድ ለማረምና ለማስተካከል ጥረት ማድረግ አለበት፣
መ. ጥሩ የሥነ-ምግባር ባሕሪ በማሳየት ለሌሎች ሠራተኞች አርአያ መሆን አለበት፡፡
ሠ. ለፈፃሚዎች ስብዕናና አስተሳሰቦች ክብር መስጠት አለበት፡፡
ረ. በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ተጠያቂነትን መውሰድ አለበት፡፡
ሰ. ሠራተኞች መብታቸውንና ግዴታቸውን እንዲያውቁ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
ሸ.ሠራተኞች የሥራ ተግባራቸውን በቅንነት፣ በሥነ ምግባርና በውጤታማነት መፈፀማቸውን በተጨበጠ
መረጃ ላይ ተመስርቶ የመገምገም ኃላፊነት አለበት፡፡

15
ቀ.ሠራተኞችን በእኩል ዓይን ማየት፣ ለተቋሙ ተልእኮና ስኬት ድርሻ እንዳላቸው መገንዘብ አለበት፡፡
በ.ማንኛውም ፈፃሚ ሠራተኛ የተለየ ጥቅም እንዲያገኝ ከሦስተኛ ወገን የሚመጡ አስተያየቶችን መቀበል
የለበትም፡፡
ተ. በየትኛውም ጊዜ ከፈጻሚ እና ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ጋር የሚያደርገው የሥራ ግንኙነት ከግል
ጥቅም ጋር የተያያዘ መሆን የለበትም፡፡

፱..የሴቶችን መብት ማክበር


ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ፣
ሀ. የልማትና ዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ውጤታማነትና ዘላቂነት እንዲረጋገጥ
የሴቶችን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን የማክበር ግዴታ አለበት፣
ለ. ሴቶች በልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ወሳኝና የማይተካ ድርሻ እንዳላቸው አምኖ
መቀበልና ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፣
ሐ. በየደረጃው የሚገኙ ሴቶችን ለማብቃት መንግስት ያስቀመጠውን የሴቶች
ፓኬጅና ፖሊሲን በማወቅ የመፈፀምና የማስፈጸም ኃላፊነት አለበት፣
መ. በማንኛውም ጉዳይ የሴቶችን ተሳትፎ ማመጣጠን የሴቶችን መብት ማክበር
መሆኑን በመረዳት ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለበት፣
ሠ. በማናቸውም ጊዜ ፆታዊ ጥቃቶችን ማውገዝ፤ አለመፈፀም እና ተፈፅሞ ሲገኝም
የማጋለጥ ግዴታ አለበት፣
ረ. በሁሉም ቦታ የሴቶችን እኩልነት ሁልጊዜ ማክበር፣ መከበሩን ማረጋገጥ፣ የሴቶች እኩልነትን የሚፃረሩ
ድርጊቶች፣ አስተሳሰቦችና አመለካከቶችን መታገል ለሚመለከታቸው የመንግስት አስፈፃሚ
አካላት የማሳወቅና የማጋለጥ ግዴታ አለበት፣
ሰ. በሴቶች ላይ የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶችና ፀረ ዲሞክራሲያዊ ድርጊቶች ላይ
የፍትህ አካላት ተገቢና ወቅታዊ እርምጃ የማይወስዱ ከሆነ የመቃወምና
የማጋለጥ ግዴታ አለበት፡፡

ክፍል ሦስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
፲. የሥነ-ምግባር ኮዱ አፈፃፀም

ሀ. ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የሥነ-ምግባር ኮዱ ተግባራዊ እንዲሆን በተለያዩ የመገናኛ

ዘዴዎች ሕዝቡ እንዲያውቃቸውና በአተገባበሩ ላይ የራሱን ቀጥተኛና ጉልህ አስተዋፅዖ

16
ለማድረግ የሕዝብ ንቅናቄ መፍጠር፤

ለ. ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ መንግስት ሠራተኛው በሥነ-ምግባር ኮዱ አተገባበር ላይ

ተገቢውን ግንዛቤ እንዲጨብጥ እቅድ በመንደፍ ስራ ላይ ማዋል፣

ሐ.ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ ማህበራት፣ የግል ተቋማት፣

እንዲሁም ሙያ ማህበራት የመሳሰሉት ኮዱን እንዲያውቁት መድረክ መፍጠር፤

መ. ሁሉም የመንግስት መስሪየያ ቤቶች የመንግስት ሠራተኛው የሥነ-ምግባር ኮዱ

በእምነት በመቀበል የቃል ኪዳን ሰነድ አድርጎ በመውሰድ በዕለት ተዕለት ሥራው

ውስጥ እንዲተገበር ማድረግ፣

ሠ. ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሠራተኞቻቸውን በማሰልጠንና የኮዱን አተገባበር

ሥርዓት በመዘርጋት ወደ ትግበራ እንዲያሸጋግሩት፣ በየጊዜውም የአተገባበር ግምገማ

በማድረግ ስለአፈጻጸሙ ሪፖርት አዘጋጅተው ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲያቀርቡ

ማድረግ፤

ረ. ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በየጊዜው በሚያደርገው የሱፐርቪዥን ሥራ የኮዱን አፈፃፀም

መከታተል፡፡

፲፩. በሥነ-ምግባር ጉድለት ላይ ስለሚወሰድ እርምጃ


የሥነ-ምግባር ግድፈት ሲፈጸም የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር ------ እና የፌዴራል
መንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊን አፈፃፀምና የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ስርዓት የሚኒስትሮች ምክር ቤት
ደንብ ቁጥር ---- መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

፲፪. የሥነ-ምግባር ኮዱን በሥራ ላይ የማዋል ግዴታ

የመንግስት ሰራተኞች እና ተቋማት በኮዱ የተደነገጉትን የሥነ-ምግባር መርሆዎችን

በእምነት ተቀብለው የአመለካከት ለውጥ በማምጣት በሕግ አግባብ የተሰጣቸውን የሥራ

ተግባርና ኃላፊነት በሥራ ላይ የማዋል ግዴታ አለባቸው፡፡

፲፫. ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች


ከዚህ ኮድ ጋር የሚጻረሩ ማንኛውም ሕግ ወይም ልማዳዊ አሰራር ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡
፲፬. ኮዱን ስለማሻሻል
ይህን ኮድ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የፐብሊክ ስርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር ሊያሻሽለው
ይችላል፡
፲፭. ኮዱ የሚጸናበት ጊዜ

17
ይህ ኮድ ከ-------------ቀን-------------ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
ሐምሌ 2009 ዓ/ም
ታገሰ ጫፎ
ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሐብት ልማት ሚኒስትር
አዲስ አበባ

18

You might also like