You are on page 1of 70

.

1
ስና ጽንሠ-ሃሳብና የመከላክያ ስልቶች

በፌደራል የመግስት ተቋማት ለሚገኙ የስነ-


ምግባርና ፀረ-ሙስና ስራ አስፈፃሚዎች የተዘጋጀ
ስልጠና
መጋቢት /2015 ዓ.ም.
ቢሾፍቱ
Kilole Hotel
ትውውቅ

 ሙሉ ስም

 የትምህርት ዝግጅት

 የሚሰሩበት ተቋም

 የስራ ልምድ

 በጣም የሚወዱት እና የሚጠሉት ነገር


ስልጠናው የሚመራበት መርህ
 ተሳትፎ (Participation)
 ሀሳብ ማንሸራሸር (Adding ideas)
 መደማመጥ (Listening, No personal attacks
 ሰዓት ማክበር “Be Here Now!”
 ስልክን ማጥፋት (Cell phones off or on silent
mode)
 በማንኛውም ሰአት መጠየቅ
ySLጠና ዘዴዎች

 ገለ

 የ
አእም
ሮ ጓዳ
ማንኳ
ኳት
 የ
ቡድን
 ጥ ውይይ
ት,
ያቄና
መል ስ
የስልጠናው ዓላማ
በየተቋማቱ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ
አሠራሮችንበመለየት ሙስና የሚያስከትለው ጉዳትን
አስቀድሞ መከላከል ይቻል ዘንድ ግንዛቤን መፍጠር
ነው፡፡
ራሳቸውን ከሙስናና ብልሹ አሰራር በማራቅ ሙስናን
የማይሸከም ትውልድ ለመፍጠር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ
ማበርከት እንዲችሉ ነው፡፡
የስልጠናው ይዘቶች
 የሙስና ትርጉም
 የሙስና ወንጀል ልዩ ባህሪያት
 የሙስና ዓይነቶች
 የሙስና መገለጫዎች
 የሙስና መንስዔዎች
 ሙስና የሚያስከትላቸው ጉዳቶችና መፍተሄዎቹ
መግቢያ
 ሙስና ብዙ ዘርፎችን የሚዳስስ፣ መፈጸሚያ መንገዱም
በየጊዜው እየተለዋወጠና እየረቀቀ የሚሄድ ወንጀል ነው፣
 ለመከሰቱ ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮችም በርካታ ናቸው፣
 ይህን ተለዋጭ ባህርይ ያለውን ሙስና ለመዋጋት በየጊዜው
የሚሻሻል፣ መጠነሰፊ ጉዳዮችን የሚዳስስ የተቀናጀ ስልት
መንደፍና የግንዛቤ ስራ መስራት ያስፈልጋል፡፡
…የቀጠለ

 ከዚህ አንፃር በተቋማት የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ


ክፍል ሰራተኞች ሙስናና ብልሹ አሠራርን ከመታገል አኳያ
ተቀናጅተው መሥራት እንድችሉ ግንዛቤያቸዉን ማሳደግ
አስፈላጊ ያደርገዋል፡፡
የሙስና ጽንሰ-ሀሳብ
• ሙስና አደራን አለመጠበቅ፣ እምነትን ማጉደል ወይም
አለመታመን፣ በጉቦ፣ በምልጃና በአድሎ ሃቅን፣ ውሳኔን ወይም
ፍትህን ማዛባት ነው፡፡
• ሙስና ለግል ወይም ለቡድን ጥቅም ሲባል ሥርዓቶችን፣ ህጎችን፣
ደንቦችን፣ አሰራሮችን፣ መርሆዎችን የመጣስ ማንኛውም ተግባር
ነው፡፡
የቀጠለ…
• ሙስና የመንግስትን የሥራ ሥነ-ምግባራዊ እና
ህጋዊ መሠረት ባለው መመሪያና ደንብ ላይ
ተመርኩዞ ማከናወን አለመቻል ነው፡፡
C (Corruption) = M (Monopoly Power) + D
(Discretion) – A (Accountability)

 ሙስና = ገደብ የለሽ ሥልጣን + ውሳኔ ሰጪነት - ተጠያቂነት

ክሊትጋርድ፣1998
ግልጽነትና ተጠያቂነት
በተቋማት አሰራር ውስጥ የግልፅነትና የተጠያቂነት አሰራር
ማለት ምን ማለት ነው

• እያንዳንዱ መሥሪያ ቤት የሚሰጠውን መንግስታዊ አገልግሎት


በተመለከተ ምን ዓይነት አገልግሎት፣ በምን መስፈርት፣ ለማን
እንደሚሰጥ በዝርዝር የሚያብራራ መመሪያ ማውጣትና
ተጠቃሚው ህብረተሰብ ይህንኑ በሚገባ እንዲያውቅ ማድረግ
ይኖርበታል፡፡
ተጠያቂነት

የተጠያቂነት አሰራር ማለት ስራውን የሚሰራው አካል ስራውን


በአግባቡ በኃላፊነት መስራት እንዳለበት እና እንዲሰራ የተሰጠውን
በአግባቡ ካልተወጣ፣ ለፈፀመው ጥፋት የሚጠየቅበት ስርአት ማለት
ነው፡፡

 አንቀፅ12- የመንግስት አሰራርና ተጠያቂነት


የቀጠለ…
 ሙስና የህዝብንና የመንግሥትን ሥልጣን ለራስ ጥቅም

ማዋል፤ ህግና የአሠራር ሥርዓትን መጣስ፣ በመመሪያ

መሰረት ያለመሥራት ድርጊትና የሥነምግባር ጉድለት ነው፡፡

 የሙስና ትርጓሜ ‹‹ሃላፊነትን አላግባብ በመጠቀም ተገቢ

ያልሆነ ጥቅም ማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ማስገኘት››

የሚል ነዉ፡፡
የቀጠለ…
Understanding
corruption is
the first step
in fighting
Corruption !!
የሙስና ልዩ ባህርያት
 ሙስና ከሚከሰትበት ሁኔታ አንጻር:

1. በተለያዩ ዘርፎች የሚከሰት (Multi-Sectoral)


2. በተለያዩ የላፊነት ደረጃዎች በሚገኙ ሰዎችና
በሌሎች/የመንግስት ሠራተኞች ባልሆኑ ግለሰቦች (Multi-Level)
የሚፈጸም ነው፣
3. በተለያዩ መንገዶች የሚከሰት (Manifasted in many
ways) ነው::
Multi-Sectoral
ሙስና በተለያዩ ሴክተሮች የሚፈጸም ነዉ ሲባል
• የመልካም አስተዳደርና የኢኮኖሚ ችግር
• በልማት እና በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ወዘተ
 ውጤቱም ብልሹ አስተዳደር ደካማ የኢኮኖሚ ስርአት
እንዲሁም አዝጋሚ የሆነ የልማት እንቅስቃሴ እንዲፈጠር
ምክንያት ይሆናል፡፡
Multi-level
 ከቀበሌ አስከ ማእከል፤በተለያዩ እርከኖች ላይ
በሚገኙ
ኃላፊዎች፣
ባለስልጣናት፣
ሠራተኞች እና
 ሌሎች ግለሰቦች በሚሳተፉበት ሁኔታ የሚፈጸም
መሆኑን ነው፡፡
Manifasted in Many Ways
 በከፍተኛ ሙስና (grand)፣
 በዝቅተኛ (petty)፣
 ተቋማዊ (institutional)፣
 በግለሰብ ደረጃ (individual)፣
 ግለሰቦች ተደራጅተው (organized)
 እንዲሁም ሳይደራጁ (disorganized) በተለያየ
መንገድ እና መጠን የሚፈጸም መሆኑን ያመለክታል፡፡
bmNG|T G™ xfÉiM z#¶Ã y¸¬† ê ê ySnMGÆR
CGéC MDN Âcý)
XdTS l!kst$ YC§l#)
በአፈጻጸሙ ከሌሎች ወንጀሎች አንጸር ሲታይ የተለየና ውሰብስብ የሚያደርጉት
ባህርያት

1. የአፈፃፀሙ ሂደትና ሥልት ውስብስብ መሆን፣


2. በአብዛኛው ለጉዳዩ ባለቤት ነኝ ባይ አለመኖር፣
3. የፈፃሚዎቹ ማንነት፣
4. በብዙ ሰዎች ዘንድ እንደ ነውር አለመታየቱና
ሙስናን በመዋጋት ተግባር ላይ የተሠማሩትን
ማሸማቀቁ ነው::
የሙስና ዓይነቶች

1. ዝቅተኛ ሙስና (Petty Corruption)

2. ከፍተኛ ሙስና (Grand Corruption)


1.ዝቅተኛ ሙስና (Petty Corruption)

ዝቅተኛ የሙስና ወንጀል የሚፈጸመው ከመንግስትና ከህዝብ


አገልግሎት አሰጣጥና አቅርቦት ጋር በተያያዘ ሲሆን፣
በዚህ የሙስና ወንጀል ውስጥ ተሳታፊ የሚሆኑት በቢሮክራሲው
መዋቅር ውስጥ በየደረጃው የመንግስት ሠራተኞችና ባለስልጣናት
እንዲሁም ህገወጥ አገልግሎት ፈላጊ ግለሰቦች ናቸው፡፡
የቀጠለ…

ዝቅተኛ ሙስና በአፈጻጸሙ አንድ ጊዜ ተፈጽሞ


የማያበቃ፣ በዕለት ተዕለት ህይወት በመንግስትና
በህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ውስጥ የሚከሰት ነው፡፡
የቀጠለ…

 አገልግሎት ለማግኘት በሚኬድባቸው የመንግስትና የህዝብ ተቋማት


ውስጥ
 አገልግሎት ፈላጊው ማግኘት የሚገባውን አገልግሎት በመከልከል ወይም
 አገልግሎት ፈላጊው የማይገባ አገልግሎት በሚጠይቅበት ጊዜ
• በየደረጃው ያሉ አንዳንድ ቢሮክራቶች በቀላሉ ሊፈጽሙት የሚችሉት
በመሆኑ
• ቶሎ የሚሰማ እና አብዛኛውን ህዝብ የሚያማርር ነው።
2. ከፍተኛ ሙስና (Grand Corruption)

 መጠኑ ሰፊ የሆነ የህዝብና የመንግስት ሀብት በአጭር ጊዜ


ውስጥ የሚመዘበርበትና የሚዘረፍበት ነዉ፡፡
 በአፈጻጸሙም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣
ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር አካላት
ሀብትና ዕውቀት ያላቸው ግለሰቦች
የሚሳተፉበት ነው፡፡
የቀጠለ…

በአፈጻጸሙ በአጭር ጊዜ በረቀቀና ሚስጢራዊ በሆነ ስልት


በሚሊዮን የሚቆጠር የሀገር ሀብት የሚመዘበርበት፣
ስርቆትና ማጭበርበር የሚፈጸምበት ነው፡፡
ይህ የሚሆነው ፈጻሚዎቹ ከፍተኛ ስልጣን፣ እውቀትና ሃብት
ያላቸው በመሆናቸው ድርጊቱን በረቀቀ ስልት የመፈጸምና
ሚስጢራዊ የማድረግ አቅሙ ስላላቸው ነው፡፡
የከፍተኛ ሙስና መገለጫ መንገዶች

Grand Corruption በዋነኛነት


 በጉቦ፣
 በማጭበርበርና
 በዝርፊያ
የሚገለፅ ነዉ፡፡
የሙስና መገለጫዎች

ጉቦ
አንድን ኃላፊ ወይም የመወሰን ሥልጣን ያለው ሠራተኛ፡-
• ተግባሩን ወይም በሕግ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ
በማከናወን ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ሲገባው
• የተሰጠውን ኃላፊነት ተገቢ ያልሆነ ጥቀም ለማግኘት
ወይም
የቀጠለ…

• በሕግ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዳያከናውን


ሐሳቡን፤ድርጊቱን ለማስለወጥ ወይም
• በኃላፊነቱ ማድረግ የሚገባውን ትክክለኛ ተግባር
እንዳይፈጽም ለማድረግ የሚሰጥ ወይም የሚጠየቅ
ተግባር ነው፡፡
የቀጠለ…

• አንድን ወይም ከአንድ የበለጡ ግለሰቦችን በማባበልና


መደለያ በመስጠት ሕጋዊ አሠራርን በማስለወጥ ወይም
በመለወጥ ሕገወጥ ጥቅም ለማግኘት የሚከናወን ተግባር
ነው፡፡
ጉቦን በሁለት ከፍለዋለን

ጉቦ (Bribery)
ከአገልግሎት ተቀባይ /ከተገልጋይ/ የሚነሳ ሲሆን
ለአገልግሎት ሰጪው መደለያ በመስጠት ሕጋዊ አሠራርን
ለማስለወጥ የሚፈጸም ተግባር ነው።
ጉቦ (Extortion or Extraction)

መሰጠት የሚገባውን ህጋዊ አገልግሎት በመከልከል ከአገልጋይ


የሚጠየቅ ሲሆን ተገልጋዩን በማስፈራራት፣
በማስጨነቅ፣
ተጽእኖ በማሳደር
ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሚፈጸም ተግባር ነው፡፡
ምዝበራ (Embezzlement)

• በመንግስትና በሕዝብ በተሰጠው ኃላፊነትና ሥልጣን


በመጠቀም
• በሥራው አጋጣሚ የሚያገኘውን የመንግስትና የሕዝብ
ሃብት፣
• የመንግሥት ንብረቶችን ለማስተዳደር ባለው ቀረቤታ
በመጠቀም ወይም
የቀጠለ…

በቀጥታ በኃላፊነት እንዲጠብቃቸው የተሰጠውን ኃላፊነት ከለላ


በማድረግ
መስረቅ፣
መመዝበር
መውሰድ ወይም
ማስወሰድ ወይም
ያለአግባብ መገልገል ነው፡፡
ማጭበርበር (Fraud)

 በዋነኛነት የኢኮኖሚ ወንጀል በመባል


የሚፈረጅ ሲሆን በከፍተኛ ተንኮልና
ቅንብር የሚፈጸም ነው፡፡
 የመንግስት ተቋማትና ወኪሎች ሕገወጥ
በሆነ የንግድ ሥራ ላይ ሲሰማሩ /
 በኮትሮባንድ ንግድ ውስጥ ሲገቡ፣
የቀጠለ…

 የተጭበረበሩ ሰነዶች በማዘጋጀትና እንዲዘጋጁ


ሁኔታዎችን በማመቻቸት ሲሳተፉ፣
 እንዲጠብቁና እንዲቆጣጠሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው
የመንግስት ባለሥልጣኖች
 በንግድም ሆነ በሰነዶች ዙሪያ ሙስና ሲፈጸም እያዩ
እንዳላዩ በመሆን የሚፈጽሙት ድርጊት ነው፡፡
አድልዎ መፈጸም (Nepotism, Favoritism, Clientlism)

ይህ የሙስና ወንጀል በዝምድና፣ በዘር፣


በቋንቋ፣
በኃይማኖትና በፆታ፣
በአምቻ ጋብቻ ወይም
በወዳጅነት ላይ ተመርኩዞ
ከህዝብና ከመንግስት የተሰጠን ሥልጣን በመጠቀም የግል ወይም የቡድን
ፍላጎት ለማሟላትና ጥቅም ለማስገኘት ሲባል የሚፈጸም አድልዎ ነው፡፡
የቀጠለ…

 ለዘመድ ወይም ለወዳጅ የሚደረግ የውለታ ሥራ ሲሆን


ይህም
 ሹመትን በዝምድና መስጠትን፣
 በያዙት ሥልጣን ተጠቅሞ ዘመዶችን፣ ወዳጆችን
ለመጥቀም
 ሕግና ደንብ በጣሰ መንገድ ኮንትራቶች መስጠትን፣
ሥራ ማስቀጠርን … ወዘተ. የሚያካትት ነው፡፡
To minimize the risk of incurring
criminal liability for corruption offenses,
the primary principle is:

Always act honestly!


/
የሙስና መንስዔዎች

1. ከመልካም ሥነምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ


• የመስረቅና የስግብግብነት ባህሪ መኖር፣
• ሳይሰሩ በአቋራጭ የመክበር፣
• የተደላደለና የተንደላቀቀ ሕይወት የመኖር ፍላጐት፣
• ለተለያዩ ሱሶች መጋለጥ ለምሳሌ ቁማር፣ መጠጥ ወዘተ፣
የቀጠለ…

2. ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች፣

3. ፖለቲካዊ ምክንያቶች፣
4. ባህላዊ ምክንያቶች እና
5. ተቋማዊ ምክንያቶች ናቸው፡፡
ሙስና የሚያስከትለው ጉዳት

ሙስና በኢኮኖሚ፣በፖለቲካ፣ በማህበራዊና አካባቢያዊ ላይ ቀውስ በመፍጠር


የአገር ልማት እንዲቀጭጭ ያደርጋል፤

የሕግ የበላይነት ስሜትን ከኅብረተሰቡ ዘንድ በማጥፋት ማኅበረሰቡን


ላልተረጋጋ ሕይወት ይዳርጋል፡፡

የዜጎችን ሕይወት ያመሰቃቅላል፤ማሕበራዊ እሴቶችን ይበጣጥሳል፤


በመጨረሻም አገርን ያፈርሳል፡፡

44
ሙስናን መከላከል

ሙስናን መከላከል ማለትስ ምን ማለት ነው?


 መከላከል ማለት አንድ ሁኔታ ወይም ድርጊት ወይም ችግር
ከመድረሱና መጠነ ሰፊ ጉዳት ከማድረሱ በፊት አስፈላጊውን ቅድመ
ዝግጅት በማድረግ እንዳይከሰት ማድረግ ወይም ተከስቶ ከሆነ
በመከሰቱ ምክንያት ይደርስ የነበረውን የጉዳት መጠን ዝቅተኛ
እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡
 ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ኪሳራ ለማስቀረት ወይም
ለመቀነስ በሚያስችል መልኩ የችግሩን ምንጭ የማድረቅ ተግባር ነው፡
ሙስና የመከላከል አስፈላጊነት

ሃገራዊ ሃብት ለታለመለት ሥራ ለማዋል


ማህበራዊ ቀውስ ለመቀነስ
በተቋማት ጠንካራ የአሰራር ሥርዓት እንዲፈጠር
የሙስና መከላከያ ስልቶች
1, አስተዳደራዊ አሰራርና ቁጥጥርን መሰረት ያደረገ

2, የትስስር ስርዓት መዘርጋት


3, ህግን በማስፈጸም ሙስናን መከላከል
4,
ግንዘቤን በማሳደግ ሙስናን መከላከል
አስተዳደራዊ አሰራርና ቁጥጥርን መሰረት ያደረገ

1,ግልፅነትና ተጠያቂነትን በተም ውስጥ በማስፈን 8, ሰራተኞችን እያዘዋወሩ ማስራት

2,የስነምግባር ደንብን ተግባራዊ በማድረግ 9, የቅሬታ መስተንግዶ ሥርዓት መዘርጋት

3,የውጤት ተኮር ስራ አመራር 10, የጥቅም ግጭትን መከላከል

4,ውስብስብ አሰራሮችን በማቅለል

5,ሀብትን ማሳወቅና በማስመዝገብ ፣

6, ምቹ የሥራ አካባቢን መፍጠር

7, ጠንካራ ተቋማዊ ባህልን ማዳበር


1.1, ግልጽነትና ተጠያቂነት
በተቋማት አሰራር ውስጥ የግልፅነትና የተጠያቂነት አሰራር
ማለት ምን ማለት ነው

• እያንዳንዱ መሥሪያ ቤት የሚሰጠውን መንግስታዊ አገልግሎት


በተመለከተ ምን ዓይነት አገልግሎት፣ በምን መስፈርት፣ ለማን
እንደሚሰጥ በዝርዝር የሚያብራራ መመሪያ ማውጣትና
ተጠቃሚው ህብረተሰብ ይህንኑ በሚገባ እንዲያውቅ ማድረግ
ይኖርበታል፡፡
ተጠያቂነት
የተጠያቂነት አሰራር ማለት ስራውን የሚሰራው አካል ስራውን በአግባቡ በኃላፊነት መስራት እንዳለበት
እና እንዲሰራ የተሰጠውን በአግባቡ ካልተወጣ፣ ለፈፀመው ጥፋት የሚጠየቅበት ስርአት ማለት ነው፡፡

 አንቀፅ12- የመንግስት አሰራርና ተጠያቂነት

C (Corruption) = M (Monopoly Power) + D (Discretion) – A (Accountability)

 ሙስና = ገደብ የለሽ ሥልጣን + ውሳኔ ሰጪነት - ተጠያቂነት


ክሊትጋርድ፣1998
1.2. የሥነምግባር ደንብ

• በተቋም ውስጥ የሥነምግባር ደንብ መኖሩ በተቋሙ ውሰጥ ተቀባይነት


ያለው የሥነምግባር ደረጃ እንዲሰፍን ይረዳል፡፡
• የተቋሙ ሃብት ባግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል፣ አድሎዊነት እንዲወገድ፣
ቅንነትና ታማኝነት እንዲሰፍን ይረዳል፡፡

 ሥነምግባር እንዲሰፍን

 ሙስና እና ለብልሹ አሰራር ለመግታት


1.3, የውጤት ተኮር ስራ አመራር

የስራ ቅልጥፍና፣ ግልጽነት፣ የስራ ድርሻ እና ተጠያቂነት እንዲኖር


ይጠቅማል

 ይህ አሰራር ለቁጥጥር አመቺ ከመሆኑም ባሻገር ደካማ ውጤት (ደካማ


አገልግሎት አሰጣጥ) በታየበት አካባቢ ሁሉ የችግሩን ምንጭ/መንስኤ
በቀላሉ ለመለየት ያስችላል፡፡
1.4, ውስብስብ አሰራሮችን ማቅለል
ብዙውን ጊዜ ደንቦች፣ መመሪያዎች ውስብስብ መሆናቸው፣
እንዲሁም ጉዳይን በማስፈጸም ሂደት ውስጥ የተራዘሙና የተወሳሰቡ
አስተዳደራዊ ፕሮሲጀሮች ለሙስና ያጋልጣሉ፡፡

 የተቀላጠፈ አገልግሎትን ማረጋገጥ ሙስናን ለመከላከል ያግዛል


1.5, የሃብት ማሳወቅ

 ጥቅም ግጭት በመከላከል ለሙስና እና ለብልሹ አሰራር ለመግታት


1.6, ምቹ የሥራ አካባቢን መፍጠር

 ሰራተኞችን ማበረታታት
 የሥነምግባር ስልጠና
 ቅሬታ ያለው ሰራተኛ ባግባቡ ማስተናገድ
1.7, ጠንካራ ተቋማዊ ባህልን ማዳበር

 በተቋሙ ውስጥ ለሚተገብረው ባህል ተገዢ መሆን


1.8, ሰራተኞችን እያዘዋወሩ ማስራት

 በሰራተኞችና በደንበኞች መካከል ተገቢ ያልሆነ

ወዳጅነት እናዳይፈጠር

 በተለይ ቁልፍ የሆኑ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቦታዎች


1.9, የቅሬታ መስተንግዶ ሥርዓት መዘርጋት

 ግንዛቤ መፍጠር
 የተለያዩ ዘዴዎችን መጠቀምና መከታተል
1.10,የጥቅም ግጭትን
የሚፈጥሩ ሁኔታዎችን መከላከል
• የጥቅም ግጭት ማለት በስራ ኃላፊነት የሚሰጡ ውሳኔዎች እራስን፣
ቤተሰብን፣ ዘመድን፣ ድርጅትን ወይም ትውውቅ ያላቸውን ሌሎች
ግለሰቦችን በገንዘብ፣ በቅጥር ወይም በተለያዩ መንገዶች ለመጥቀም
መሞከር(ማሰብ) ነው፡፡
 የጥቅም ግጭት ሊፈጥሩ የሚችሉትን መለየት

 ማሰልጠን ተግባራዊነቱንም መከታተል


2. ብሄራዊ የትስስር ስርዓት

 ሃላፊነትና ስልጣንን በማከፋፈል እና ተጠያቂነትን ጎናዊ


(horizontal accountability) የማድረግ ነው
…የቀጠለ

61
ተቋማዊ አምዶችና አስፈላጊ ደንቦች
ተቋማዊ አምዶች የሚያስፈልጓቸው ደንቦች/ተግባራት
(Institutional pillar) (Corresponding core rules/practices)
ህግ አስፈጻሚ የጥቅም ግጭት ህጎች
(Executive) (Conflict of interest rules)
ህግ አውጪ/ፓርላማ ፍትሃዊ ምርጫ
(Legislature/Parliament) (Fair elections)
ኦዲተር ጀነራል ለህዝብ ሪፖርት
(Auditor General) (Public reporting)
የመንግስት ሰራተኛ ሥነምግባርዊ አገልግሎት
(Public service) (Public service ethics)
ፍርድ ቤት የዳኝነት ነጻነት
(Judiciary) (Independence)
ሚዲያ የመረጃ ነጻነት
(Media) (Access to information)
ሲቪል ማህበረሰብ የመናገር መብት
(Civil society) (Freedom of speech)

እንባ ጠባቂ የማኔጅመንት ሪከርድ


(Ombudsman) ( Records management)

የፀረ-ሙስና ተቋማት አስገዳጅ ህጎች


(Anti-corruption/ (Enforceable and enforced
watchdog agencies) laws)

የግሉ ዘርፍ የውድድር ፖሊሲ፣ የመንግስት ግዥ


(Private sector) ህግና ደንብ
(Competition policy, including
public procurement rules)

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ውጤታማ የህግ ትብብርድጋፍ


(International (Effective mutual legal/judicial
community) assistance)
3. ህግን በማስፈጸም ሙስናን የመከላከል
 ህጎች በተግባር ሲተረጎሙ
 ወንጀለኛ ቅጣት ተቀጥቶ እንዲታይ ማድረግ
 በሙስና የተገኘው ሀብትና ንብረት ተወርሶ
 አጥፊዎች እንዲታረሙ
 ሌሎች ከተሞክሮ እንዲማሩ
4. ግንዘቤን በማሳደግ ሙስናን የመከላከል

 ሙስናን ለመከላከል ያለው ፋይዳ


 መሰረታዊ የስልጠና ሂደት
 የግንዛቤ መፍጠሪያ መንገዶች
ሙስናን ለማምከን ሊወሰዱ የሚገቡ
ተግባራት( መፍቴሄዎቹ)
 ሁሉም በሙስናና ሙሰኞች ላይ መዝመት፣
 ሙስና እንዳይፈጸም የመከላከል ሥራዎች
 የሙስና ወንጀል ሕጎችና ሕግ የማስከበር ሥራዎች
 የዲሞክራሲ ተቁማት ማጠናከር፣
 የሲቪክ ማህበራት/ህዝብ ተሳትፎ ማጠናከር፣
 ተጠያቂነት ማስፈን፣
 የትብብርና የቅንጅት ሥራዎች
 የአመራር ወይም የፖለቲካ ቁርጠኝነት
የቀጠለ…

እርስ በእርሳችንን ተጋግዘን የጋራ የሆነው ጠላታችንን ሙስናን መጠየፍና ሙሰኞችን


መከላከልና ማጋለጥ ካልቻልን ነገ እኛ ራሳችን የችግሩ ተካፋይ መሆናችን አይቀርም፡፡
ማጠቃለያ

 በአጠቃላይ የሙስና ወንጀል ጎጂነት ላይ


የምንስማማውን ያህል በጋራ መታገሉ ላይ ካልበረታን
ለነገው ትውልድ የተሻለች አገር ልናስተላልፍ
አንችልም፡፡

 ስለዚህ ከወዲሁ በላቀ ሞራልና ሥነ ምግባር፣


በታታሪነትና ትጋት እንዲሁም በፀረ ሌብነትና በፀረ
ሙስና ባህል ውስጥ ሆነን ለፀረ-ሙስና ትግሉ እንነሳ፡፡

68

You might also like