You are on page 1of 6

ቀን፡- 28/11/2014 ዓ.

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን በተመለከተ ኮሙኒኬሽን
ጽ/ቤት የህዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ የተዘጋጀ መጠይቅ ዳሰሳ ጥናት

o አድራሻ፡- ክ/ከተማ= 75 ወረዳ= 170 ድምር= 245


o የት/ት ደረጃ፡- ቀለም= 86 ዲፕሎማ= 42 ድግሪ= 86 ማስተር= 7 ድምር= 221
o እድሜ፡- 15-30= 90 31-45= 80 46-60= 32 ከ 60 እና በላይ= 3 ድምር= 205
1. በተደጋጋሚ አገልግሎት ፈልገው የመጡበትን ጽ/ቤት ቢነግሩን ተመላልሰው ከሆነ ምን ያህል ጊዜ ሆኖት?
 ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት 16 ሰዎች በተደጋጋሚ ማለትም ከስድስት ወር ያላነሰ ግዜ ተመላልሻለሁ የሚል
አስተያየት ሰጥተዋል፤
 ንግድ ፅ/ቤት 15 ሰዎች ከንግድ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ከሶስት ወር ባላነሰ ግዜ አመላልሰውኛል፤
 ጥቃቅንና አነስተኛ ፅ/ቤተ 8 ሰዎች ከሶስት ወር በላይ ጉዳዬ መልስ ሳያገኝ ተመላልሻለሁ የሚል
አስተያየት ሰጥተዋል፤
 ቤቶች ፅ/ቤት 11 ሰዎች በዚህ ፅ/ቤት በተደጋጋሚ ከአንድ ወር እና በላይ በቤት ጉዳይ ተመላልሻለሁ የመል
ምላሽ ሰጥተዋል፤
 ፍትህ ፅ/ቤት ሰው 4 ሰዎች ከአንድ እስከ ከ 6 ወር ጊዜ ተመላልሻለሁ የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፤
 ጤና ፅ/ቤት 3 ሰዎች የሚሆኑ አንድ ወር አካባቢ ከጤና ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተመላልሻለሁ የሚል አስተያየት
ሰጥተዋል፤
 ሴቶች እና ህፃናት 5 ሰዎች ከአንድ እስከ ሶስት ወራት ግዜ ያህል ተመላልሻለሁ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
 ትምህርት ጽ/ቤት 3 ሰዎች በተደጋጋሚ ተመላልሻለሁ ብለዋል፤
 መዝገብ ቤት የጀርባ ማህተም ከአንድ ወር በላይ 7 ሰዎች በተደጋጋሚ ተመላልሻለሁ የሚል አስተያየት
ሰጥተዋል፤
 የስራ እድል ፈጠራ 16 ሰዎች በተደጋጋሚ ማለትም ከስድስት ወር በላይ ምላሽ ሳላገኝ ተመላልሻለሁ፤
 ፐብሊክ ሰርቪስ ፅ/ቤት 6 ሰዎች ከምደባ ቅሬታ ጋር በተያያዘ ብዙጊዜ ተመላልሻለሁ፤
 ህብረተሰብ ተሳትፎ 4 ሰዎች የልማት ጥያቄዎችን ምላሽ ሳላገኝ ተመላልሻለሁ፤
 ገቢዎች ጽ/ቤት 7 ሰዎች ከግብር ችግር ጋር በተያያዘ ብዙጊዜ ተመላልሻለሁ፤
 ሰላም እና ፀጥታ 3 ሰዎች በተደጋጋሚ ተመላልሻለሁ፤
 አዲስ ብድርና ቁጠባ 3 ሰዎች የብድር ጉዳይን ለማስጨረስ በተደጋጋሚ ብዙጊዜ ተመላልሻለሁ
 ቤቶች ግንባታ ፍቃድ 45 ሰዎች በጣም ብዙጊዜ ማለትም ከዓመት በላይ ተመላልሻለሁ፤
 ይዞታ ማረጋገጫ ጽ/ቤት 35 ሰዎች በተደጋጋሚ የተለያየ አሳማኝ ያልሆነ ምላሽ በማቅረብ
ተመላልሻለሁ፤
 መሬት ይዞታ ከአንድ ዓመት 27 ሰዎች በተደጋጋሚ ከሶስት ዓመት ከዚያም ግዜ በላይ ያለምንም በቂ
መፍትሄ ተመላልሻለሁ፤
 መሬት አስተዳደር 11 ሰዎች ተመላልሻለሁ
 ግንባታ ፍቃድ 39 ሰዎች በተደጋጋሚ ከሁለት አመትና ከዚያም በላይ ለሆነ ግዜ ተመላልሻለሁ
 ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት፤ 8 ሰዎች በህጋዊ መንገድ ግንባታ ስራ ብጀምርም የማስቆም ተግባርን ለማስረዳት
ተመላልሻለሁ፤
2. ምን አገልግሎት ሊያገኙ መጡ?
 ቤት እድሳት አገልግሎት ለማግኘት 55 ሰዎች መጥተዋል፤

1
 መሬት ይዞታ አገልግሎት ለማግኘት 53 ሰዎች፤
 ለግንባታ ፍቃድ ለማስፈቀድ 39 ሰዎች ፤
 ስም ዝውውር አገልግሎት ለማግኘት 3 ሰዎች ሰዎች፤
 የሊዝ ቦታ አገልግሎት ለማግኘትለመጠቅ 25 ሰዎች፤
 የፕላን ተቃርኖ ችግር አገልግሎት ለማግኘትለማሰራት 35 ሰዎች ፤
 ካርታ አገልግሎት ለማግኘት 31 ሰዎች ፤
 የቤተሰብ የቤት ውርስ ባለቤትነት ለማረጋገጥ እና ማህበር ቤት የጀርባ ማህተም ለማስመታት አገልግሎት
ለማግኘት 12 ሰዎች ፤
 መታወቂያ እድሳት አገልግሎት ለማግኘት 18 ሰዎች ፤
 አዲስ መታወቂያ የማውጠት አገልግሎት ለማግኘት 55 ሰዎች ፤
 የልደት ሰርተፊኬት ለማውጣት አገልግሎት ለማግኘት 29 ሰዎች፤
 ያላገባ ሰርተፊኬት አገልግሎት ለማግኘት 13 ሰዎች፤
 የገበሬ ልጅነትን መረጃ ለማግኘት አገልግሎት ለማግኘት 13 ሰዎች ፤
 የአርሶ አደር አገልግሎት ለማግኘት 16 ሰዎች፤
 ንግድ ፍቃድ ለማውጣት አገልግሎት ለማግኘት 40 ሰዎች ፤
 ንግድ ፍቃድ ለማሳደስ አገልግሎት ለማግኘት 17 ሰዎች ፤
 የስራ አጥ መታወቂያ አገልግሎት ለማግኘት 23 ሰዎች ፤
 በጥቃቅንና አነስተኛ የመደራጀት አገልግሎት ለማግኘና ስራ ለከመስራት 18 ሰዎች፤
 የተለያዩ አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት 13 ሰዎች ፤
 ግብር ክፍያ ስህተት ለማስተካከል አገልግሎት ለማግኘት 5 ሰዎች ፤
3. አመራሮች እና ሰራተኞች የስራ ሰአታቸውን ጠብቀው አገልግሎት ይሰጣሉ?

ሀ. ይሰጣሉ= 125 ለ.አይሰጡም= 83


መልሶ አይሰጡም ከሆነ የት ሄዱ ይባላል?

 የት እንዳሉ ምንም አይታወቅም 7 ሰዎች የሚል ምላሽ ተሰጥተቸዋል፤


 ለስራ(ቀጠና) ወጥዋል 27 ሰዎች የሚል ምላሽ ተሰጥቶቸዋል፤
 15 ሰዎች በስራ ገበታቸው ላይ እያሉ በቸልተኝነት አልግሎት አይሰጡም የሚል ማላሽ ሰጥተዋል፤
 ነገ በተመልሰው ይምጡ 16 ሰዎች የሚል ምላሽ ተሰጥቶቸዋል ነገር ግን በማግስቱም ተመሳሳይ ምለላሽ
ነው የሚሰጡን፤
 በትክክል አይናገሩም 13 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
 ለስብሰባ ወጥተዋል እንባላልን 18 ሰዎች የሚል ምላሽ ተሰጥዋል፤
 በተለያየ ሁኔታ ጊዜአቸውን አይጠቀሙም እንዲሁም ቶሎ ቢሮ አይገቡም 17 ሰዎች ከታዘብነው የሚል
መላሽ ሰጥተዋል፤
 አሁን ነው የወጡት ግን አይመጡም ቀኑን ሙሉን እንዲሁ ነው ምላሹ 16 ሰዎች የሚል ምላሽ
ተሰጥቶቸዋል
 ክ/ከተማ ተጠርተው ሄደዋል 11 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
 አመራሮች ብዙን ግዜ ቢሮ አይገኙም 7 ሰዎች የሚል ምላሽ ተሰጥቶቸዋል
 የሉም 26 ሰዎች የሚል ምላሽ ተሰጥቶቸዋል፤ ነገርግን እዚያው በስራ በአካባቢ እያሉ፤

2
 አመራሮች በቀጠና በተለያዩ ስብሰባ ምክንያት በማድረግ ቢሮ ተገኝተው ለባለጉዳይ በሰዓቱ አለማስተናገድ
ባለጉዳዩን በተለያዩ በታኪሲ በተለያዩ ነገሮች በመፍጠር በሰዓቱ ቢሮ አይገኙም 9 ሰዎች ምላሻቸውን
ሰጥተዋል፤
4. አመራሮች እና ባለሙያዎች ራሳቸውን የሚገልጽ ባጅ ያደርጋሉ?
 አዎ ያደርጋሉ 76 ሰዎች ሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
 አንዳንዶች/የተወሰኑ ብቻ ያደርጋሉ 56 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
 አያደርጉም 55 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
 ባለሙያዎች ይሁኑ አመራር ወይም ባለጉዳይ በትክክል አይታወቅም አስር ሰዎች መልሰዋል፤
 አንዳንዶቹ ያደርጋሉ አመራሮቱ ግን አድርገው አይቼ አላውቅም 7 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤

5. ስለ አገልግሎት አሰጣጥ እስታንዳርድ ያውቃሉ?


ሀ. አውቃለሁ= 105 ለ አላውቅም= 85 ድምር= 190
በስታንዳርዱ መሰረት ለመገልገል ጠይቀው ያውቃሉ?

 አገልግሎት ለማግኘት እንጂ በስታንዳርድ አላቅም 38 ሰዎች በስታንዳርዱ መሰረት ለመገልገል ተጠይቀው
ምላሽ ሰጥተዋል፤
 አንዳንድ ጽ/ቤቶች እስታዳርድ የላቸውም 3 ሰዎች ምላሽ ሰጥተዋል፤
 በግልጽ ቦታ ስታዳርድቸውን አይለጥፉም ስለጽ/ቤት ለማወቅ ከባድ ነው 7 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
 በጭራሽ አላውቅም 47 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
6. አገልግሎት ፈልገው ሲመጡ የእጅ መንሻ ይጠየቃሉ?

ሀ. አዎ= 72 ለ. አይ አላጋጠመኝም = 129 ድምር= 201


 መልሶ አዎ ከሆነ የሚጠየቁት ሀ. በአመራር= 65 ለ. በፈጻሚ= 56
 በአብዛኛው የእጅ መንሻ የሚጠየቀው ሀ. በክ/ከተማ= 82 ለ. በወረዳ= 72

7. እንደ ተገልጋይ ወደ ተቋሙ ሲመጡ ቀድመው ምን ምን ሟሟላት እንዳለበት ያውቃሉ?

ሀ. አውቃለሁ= 105 ለ. አላውቅም= 70 ድምር= 175

8. በተቋሙ ከዚህ በፊት ተገልግለው የሚያውቁ ከሆነ አሁን ላይ ምን የተለየ ነገር አለ?
 እንግልቱ፤ ግልምጫው፤ሌብነቱለ 100% እጥፍ ጨምሯል ፤
 የተሻለ መስተንግዶ እና አገልግሎት አለ የሚል ምላሽ 46 ሰዎች ሰጥተዋል፤
 ምንም የተለየ ነገር የለም የሚል ምላሽ 23 ሰዎች ሰጥተዋል፤
 ምንም የተለየ ነገር አላየሁም እንደውም በየምክንያቱ ባለጉዳይን ማገላታታቸውን ቀጥለዋል በተግባር
ያለው እና የሚወራው ይለያያል፤
 ጠንካራ አመራርና ባለሙያ እንዲሁም በስራ ሰዓት ስራ ቦታ ላይ ይገኛሉ 3 ሰዎች ሠጥተዋል፤
 በተለይ ወሳኝ ኩሁነት ስራዎች በሲስተም ነው የሚሰሩት እየተባለ የሲስተም ወቆራረጥ ብዙውን ግዜ
ችግር አለ የሚል 15 ሰዎች ሠጥተዋል፤
 የተለየ ነገር ምንም ነገር አላየሁም የሚል 17 ሰዎች ሠጥተዋል፤
 የሰራተኛው ቀና አመለካከት እና በትግስት በማስረዳት፤ እንዲሁም በአግባቡ ለማስተንግዶ በተወሰነ
ተሻሽሏል የሚል 7 ሰዎች ሠጥተዋል፤
 ሰራተኛው ለተገልጋይ የሚሰጠውን ትኩረት በጣም ጥሩ ነው የሚል 11 ሰዎች ሠጥተዋል፤

3
 በአንድ ማዕከል መገልገል ችለናል ለፀጥታ ሲባል ከበር ጀምሮ ራሳችንን የሚገጽ መታወቂያ ተጠይቀን ባጅ
ለብሰን ነው የምንገባው ይህ ጥሩ ነው ይቀጥል የሚል 3 ሰዎች ሠጥተዋል፤
 ለአገልግሎት ውሳኔ የመወሰን ችግሮች አለ በጣም እጅግ የመዘግየት ነገር አለ የሚል 3 ሰዎች ሠጥተዋል፤
 ከቀድሞው የተለየ ነገር የአሰራር ሁኔታ አለ ጥሩ ነው በአግባቡ ነው አመራሩን በአንድ ቦታ ባለጉዳዩ ማግኘት
ያስቻለ ነው በዚሁ ይቀጥል 19 የሚል 5 ሰዎች ሠጥተዋል፤
 በመጀመሪያ ነበር ሲገባ መታወቂያ አስይዘን ባጅ የምንፈልግበት ተቋም ጠይቀን ይሰጠናል ውስጥም
ለተገልጋይ ምቹ ነበር ግን አሁን ቀረ የሚል 3 ሰዎች ሠጥተዋል፤
 ምንም የተለየ ነገር የለም ባለሙያው በመጣበት ሰዓት እንደበፊትም እየተስተናገድን ነው የሚል 5 ሰዎች
ሠጥተዋል፤
9. በቅርቡ ስለተጀመረው የአንድ ማእከል አገልግሎት መረጃ አሎት? ካለው ምን ለውጥ አምጥቷል ብለው
ያምናሉ?
 መረጃ የለኝም 27 ሰዎች የአንድ ማእከል አገልግሎት መረጃ እንደሌላቸው ምላሽ ሰጥተዋል፤
 የአንድ ማእከል አገልግሎት ምንም ለውጥ አላመጣም በአንድ ቦታ ተሰብስቦ ወሬ ነው 25 ሰዎች የሚል
ምላሽ ሠጥተዋል፤
 የአንድ ማእከል አገልግሎት በጣም ጥሩ ነው እግልትን ይቀንሳል በአንድ ቦታ በርካታ ጉዳይን ለማግኘት
ያግዛል 33 ሰዎች የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
 ጥሩ ነው ሁሉም ባለጉዳይ በአንድ ማዕከል አገልግሎት ፈልገው ሲመጡ በአግባቡ ይስተናገዳሉ 13 ሰው
የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤
 የሙስናን በር እንዲዘጋ አድርጓል ጥሩ ነው የሚል ምላሥ 3 ሰው አስተያየጥ ሰጥተዋል፤
 በአንድ ማዕከል ስንገለገል ለሚመለከተው ሀላፊ ተጠርቶ ችግሩ ወዲያው ይቀረፋል 10 ሰው ምላሽ
ሰጥተዋል፤
 አዎ እናምናለን ለውጡ ሳይመጣ በፊት አመራሩን በመስኮት ነበር የምናገኘው አሁን ግን ፊት ለፊት
ስለምነገኘው የተሸለ ለውጥ መጥቷል 5 ሰው ይህንን አስተያየት ሰጥተዋል፤
10. በተቋሙ ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘት ከህብረተሰቡ ምን ይጠበቃል
 መብትን ማስጠበቅና ግዴታን መወጣት አለበት የሚል ምላሽ 19 ሰዎች አስተያየታቸውን መልሰዋል፤
 አስፈላጊውን መረጃ ይዞ መገኘት እንዲሁም ተራ ጠብቆ መስተናገድ እና እጅ መንሻ አለመስጠት
የሚል ምላሽ 13 ሰዎች መልሰዋል፤
 መብት እና ግዴታውን አውቆ ለሚጠየቀውን ጥያቄ ማሟላት ያለበትን ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ
መገኘት አለበት የሚል ምላሽ 6 ሰው አስተያየቱ ሰጥቷል፤
 የነቃ ተሳትፎ ማድረግ የሚል ምላሽ 3 ሰዎች አስተያየታቸውን መልሰዋል፤
 ንቁ ተሳትፎ እና ብልሹ አስራሮች የሚታገል መሆን አለበት የሚል ምላሽ 5 ሰዎች መልሰዋል፤
 ህብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት አለበት የሚል ምላሽ 15 ሰዎች
አስተያየታቸውን መልሰዋል፤
 ባለጉዳዮች ለአገልግሎት ሲመጡ የሚፈልጉትን ማሟላት እንጂ እጅ መንሻ አለመስጠት በየደረጃው
መብትን ማስጠበቅ የሚል ምላሽ 25 ሰዎች አስተያየታቸውን መልሰዋል፤
 ህብረተሰቡ መተጋገል አመራሩም ማዳመጥ አስተዳደሩ መከታተል ቅሬታዎች መፈታት አለበት የሚል
ምላሽ 3 ሰዎች መልሰዋል፤
 መመሪያዎችን ማውቅ ፤አገልግሎት ማግኘት መብት መሆኑን ማወቅ፤ አገልግሎትን በገንዘብ ለማግኘት
አለሞከር የሚል ምላሽ 13 ሰዎች መልሰዋል፤

4
 ከህብረተሰቡ ማድረግ ያለበት በስራ ሰዓት ጊዜውንና ሰዓቱን ጠብቆ እንዲሁም መሟላት ያለበትን ነገሮች
አሟልቶ ወደ ተቋሙ መቅረብ አለበት የሚል ምላሽ 5 ሰዎች አስተያየታቸውን መልሰዋል፤
o መንግስትስ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ምን ማድረግ ይጠበቅበታል?
 ከላይ ያሉ አካላት ወረድ ብሎው ደረጃ በደጃ ያለውን መዋቅር መፈተሸ አለበት፤
 ሰራተኛውን ብቁ ማድረግና ቁጥጥር ማድረግ፤
 በየጊዜው ምደባ ከመስራት ይልቅ ባለሙያው ተረዳድቶ እንዲሰራ በማድረግ ተጠያቂነትን ማስፈን፤
 ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አለበት ጥፋት የጠፋ አካላትን ለህግ እና ህጋዊ እርምጃ መውሰድ፤
 ለባለሙያው ስልጠና መስጠት እና ማብቃት፤
 እታች ወርዶ የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ መመልከት ጠንካራን ድክመት ታችኛውን በሚገባ
መከታተል፤
 አገልግሎት ፈልጎ የሚመጣውን ህብረተሰብ በአግባቡ ማስተናገድ የሚፈልገውን በተገቢው መንገድ
እንዲያገኙ ማድረግ፤
 አስፈላጊውን ሰው በቦታው መመደብ እና ጥብቅ ክትትል ማድረግ እንዲሁም በዘር በዘመድ አዝማድ ስራ
ማስቆም ህጋዊ እርምጃ መውሰድ፤
 በቂ የሰው ሀይል መመደብና አነቃቂ ደሞዝ መክፈል፤
 የተሻለ ስነ- ምግባርና በትምህርት የተነፁ ሰዎችን ወደ ስራ ማምጣት፤
 የቢሮ ግብዓት ማሟላት፤ እንዲሁም ተጠያቂነት ያለበት አሰራርን ማስፈን አለበት፤
 ለህብረተሰቡ መብቱንና ግዴታውን የማሳወቅ ስራ መስራት አለበት፤
 በባለጉዳይ ቀን አመራሮችን ከቀጠና ስራ ውጪ አድርጎ በቢሮ ለህብረተሰቡ አገለልግሎት እንዲሰጡ
ማድረግ አለበት፤
 የዘመነ ቀልጣፋ መንገድ አሰራሩን ማዘመን ቦታውን የሚመጥን ባለሙያና ብሎም አመራሩ በቦታው
እንዲገኝ ክትትል ማድረግ፤
 መንግሰት ለተገልጋይ በቂ የአገልግሎት ቦታ መመቻቸት አለበት፤ ሰራተኛውንም በደንብ ሊከታተል ይገባል፤
o የቀረ ሃሳብ ካለ ይግለጹ
 አቅም ያለው አመራርና ፈፃሚዎችን በቦታው መመደብ፤
 በአግባቡ የሚጠበቀውን አገልግሎት ለህብረተሰብ እየተሰጠ ስላልሆነ የተጠያቂነት አግባብ መዘርጋት፤
 አገልግሎትን ከእጅ መንሻ ውጪ ማግኘት እንደሚቻል ለህብረተሰቡ ማስገንዘብ እንዲሁም
አገልግሎትን ማግኘት የህብረተሰቡ መብት ስለመሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት፤
 በመሬት እና በይዞታ አካባቢ ያለውን እንግልት የሚቀንስ አሰራር ማስፈን፤
 ሰዎች የነዋሪነት መታወቂያ ያለገንዘብ የማግኘት ችግር መፍታት ከብዶታል መንግስት ይህንን ችግር
ከመሰረቱ መፍታት አለበት፤
 የቀሩ ክፍተቶችን ለመሸፈን ከባድርሻ አካላት ጋር ለለውጥ መስራት፤
 የተጀመረው የአንድ ማዕከል አከልግሎት አሰጣኝ ወደ ወረዳ ማስፍት የጠቀላጠፈ አገልግሎት አሰጣጥን
ማሳደግ፤
 የአመራር መዋቅር ማስተካከል በዘመድ አዝማድ ሳይሆን በትክክለኛ የሚመጥን አመራር ይመድብ፤
 በቀልጣፋና በተሸለ ህዝቡን እንዲያገለግል አመራሩ ላይ በደንብ መሰራት አለበት፤
 የሰው ልጅ ሰላም ማግኘት አለበት ሰላም ላይ ብዙ ስራ መሰራት አለበት ስራ የሌላቸውን ስራ መፍጥር፤
የኑሮ ውድነት በጣም ችግር ውስጥ ነው ያለው ይህንን ችግር በአፋጣኝ መፍታት አለበት፤

5
 ኑሮ እንዲረጋጋ ንግድ ኢንዱስትሪ ስራ አልሰራም ፈጻሚዎች በተለየ በንግድ ቁጥጥር ባለሙያዎች በትክክል
ለደሃው የማያስብ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድባቸው እጅግ በጣም ቁጥጥር ማደረግ
አለበት፤
 ግልጽ መመሪያ ማዘጋጀት በየጊዜው ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ የሚሰጥ መመሪያ ማዘጋጀት ወደ ሃላፊነት
የሚመጣ ሰው በችሎታ ቢሆን ኔትወርክ በዘር ባይሆን፤

You might also like