You are on page 1of 2

ለአንድ ሀላፊ ውክልና መነሳት መስፈርቱ ምንድነው ?

አንድን በውክልና የተቀመጠን ሰራተኛ ከውክልናው ለማንሳት ምናልባትም የህግ ግድፈት ከፈፀመ በሰራተኛው ካልታመነበት እና ሌሎችም
ቅቡልነትን የሚያሳጡ ተግባራትን ከፈፀመ እንኳም ከሀላፊነት መነሳት ይቅርና በመደበኛ የህግ አግባብ ተጠይቆ አስፈላጊውን ቅጣት እና እርምጃ
ያገኛል ብለን እናምናለን ።
በመሆኑም እኛ የአክርሚት ጤና ጣቢያ ሥራተኞች አቶ አይሳሳም አቤ ከሀላፊነታቸው ይነሱልን ጥያቄ ለበረኸት ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት
አቅርበናል ።የ ይነሱልን ጥያቄም ስናነሳ ከ ስሜታዊነት ፣ከግል ጥላቻ፣ከግድየለሽነት በመራቅ በስክነት እና በብስለት በመወያየት ከላይ
የጠቀስናቸው ማለትም የህግ ግድፈት፣ ስርአት አልበኝነት ፣ሰርቶ የማሰራት ውስንነት ፣አድሎአዊ ነት እና የማንአለብኝነት የመልካም አሰተዳደር
ችግር በተቋማችን ውስጥ በስፋት እና በጥልቀት መኖራቸውን በማመናችን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቋሚነት መቋጨት አለበት በማለት
ጥያቄያችንን ለጤና ጥበቃ ፅ/ቤት አቅርበናል። የጤና ጥበቃ ፅ/ቤትም ከወቅቱ አስቸጋሪነት በመነሳት የማኔጅመንት አባላትን ጤና ጣቢያ ድረስ
በመላክ አወያይቶናል።የመጣው የማኔጅመንት ቡድንም የተለያዩ ፋይሎችን በማዬት እና ከሰራተኛው ጥያቄ በመነሳት አውነትም ችግሩ ከመሬት
ያለ እና ጥያቄያችን ትክክለኛ ምላሽ እንደሚፈልግ መግባባት ላይ በመድረስ ሊወከልልን የምንፈልገውን ሰው በድምፅ መርጠን የሰጠን መሆኑ
እና ቀጣይ በተቋሙ ሊታዩ የማይፈለጉ በተባሉት ችግሮች ላይ አቅጣጫ እና ማስተካከያ ሰጥተውን ተለያይተናል።ነገር ግን ለጤና ጣቢያችን
ከተላከው ደብዳቤ እንደተረዳነው ለጥያቄያችን ትክክለኛ እና ቀጥተኛ ምላሽ አልተሰጠንም ብለን ነው።ለዚህ ደግሞ በበላይነት ውሳኔ የሚሰጠው
አካል(ማናዬ)የችግሩን አንገብጋቢነት ቀጥተኛ ከሰራተኛው ስላልሰማ የችግሩን ጥልቀት እና የባለሙያውን ህመም በሚገባ ስላልተረዳው ሊሆን
ይችላል ብለን በማመናችን በድጋሚ ችግራችንን ለማስረዳት ከጤና ጥበቃ ቢሮ ተገኝተናል።
ከዚህ በላይ የጠቀስነው እንዳለ ሆኖ በጤና ጣቢያው ሀላፊ የተፈጠሩ የአሰራር ክፍተቶችን እያዬን ለውክልና መነሳት በቂ መክንያት
ሊሆኑ እንደሚችሉ በማሳያ እያዬን ጥያቄያችንን እንደሚከተለው እናቀርባለን ።
1 ኛ የስነ-ምግባር ችግር ከሀላፊነት ከመነሳትም በላይ በመደበኛ የወንጀል ህግ ሊያስጠይቅ አይችልም ወይ? ይህም ስንል ባሙያን
መስደብና እና መጣላት
ማሳያ
sr fanaye መሳደብ
teshome habitamu ድብድብ
ato shiferaw ለድብድብ መጋበዝ
sr ይለፍ መሣደብ
ጤና ኤክስቴንሽን
2 ኛ. በህክምና ስራ ጣልቃ በመግባት ታካሚ ተገቢውን ህክምና እንዳያገኝ መከልከል እና ለባለሙያ ያልሆነ ስም በመስጠት ስም በማጥፋት
(ሌባ)ማለት በወንጀል አያስጠይቅም ወይ?
ማሳያ
Sr fanaye በጥይት የተመታ የመከላከያ አባልን ስታክም ለምን TAT አዘዝሽ ይህ ማለት በመደራደር መድሀኒት እየሻጣችሁ ነው
ማለት። ይህ ወንጀል አይደለም ወይ?
3 ኛ. የሲቪል ሰርቪስን ደንብ እና ስርአት አክብሮ አለመስራት ተጠያቂ አያደርግም ወይ?
ማሳያ
የስራ አቴንዳንስ አለመፈረም ለምሳሌ የ 2 ወር ያልተፈረመ አቴንዳንስ
በተቋም ውስጥ የደንብ ልብስ አለማድረግ
በተረኝነት ስአት በስራ ቦታ አለመገኘት
4 ኛ. ለሰራተኛው መንግሥት ያመቻቸለትን ጥቅማ ጥቅም መከልከል በህግ ተጠያቂ አያደርግም ወይ?
መሳያ
የደንብ ልብስ መከልከል
የጤና ባለሙያ ለ 2 አመት
ለፖርተር የ 3 አመት
ለንብረት ክፍል ሀላፊ የ 3 አመት
ከዚህ በተጨማሪ ምንም አይነት የደንብ ልብስ ቀርቶባቸው የማያውቁ መደቦች አሉ የህ አድሎአዊነት አይደለም ወይ?
የአመት ፈቃድ ሆነ ተብሎ እንዲቃጠል ማድረግ
5 ኛ. የአንድን ሀላፊ ውክልና ለማንሳት ከዋና ጉዳዩ በለይ የድምፅ ብልጫ መስፈርት ነወይ
6 ኛ. በተደጋጋሚ ክስ እየቀረበበት ያለ ሰው አውነት የስነምግባር ችግር የለበትም ተብሎ ይታሰባል ወይ?
ማሳያ
በእንጎቻ
በፋናዬ
ከ 04,ጤና ጣቢያ
ከቀበሌ ሊቀመንበር
በ 2015 በጠቅላላ ሠራተኛ
7 ኛ. ሰራተኛው በእናት መስሪያ ቤቱ ላይ እምነት አያጣም ወይ?
8 ኛ. ሲጀምር የጤና ጣቢያ ሀላፊ የአመራረጥ መስፈርትን ተከትሎ ነወይ ውክልና የተሰጠው?
ማሳያ
1. የጤና ጣቢያ ሀላፊ አመራረጥ መመሪያን ተመልከቱ

ከዚህ በመቀጠል በአክርሚት ጤና ጣቢያ የጤና ጥበቃ ፅ/ቤት የማኔጅሜንት አባላት ከአወያዪ በኋላ ነገሮች ከመስተካከላቸው ይልቅ በአዲስ
መልክ አያገረሹ እና እየባሱ የመጡ አንደሆነ ከብዙ በጥቂቱ በማሳያ እናንሳ
በተቋሙ የሰራተኛ ተወካይ(ቴክኒክ ከኦርድኔተር)በሰራተኛው (በባለሙያዎች )መመረጥ እያለበት ለእኔ ይመቸኛል በማለት በራሱ ውክልና
ሰጥቷል
ወቅቱን እና አጋጣሚውን በመጠቀም ባለሙያዎች ጥያቄ ለማቅረብ ወረዳ በወረዱበት ሰላም እና ደህንነት ቢሮ በመደወል ከፅንፈኛው ጋር
ይደዋዎላል በማለት አንዲታሰር ማዘዝ። ይህ ከመብት አንፃር እንዴት ይታያል እንደ ህግስ?
በማኔጅመንት አባላቱ እንዲያስተካክል የተነገረው ቢሆንም ከማስተካከል ይልቅ ከውይይቱ ማግስት ስድብ፣ማንቋሸሽ እና ዛቻ የቀጠለ መሆኑ።
ለዚህም ማሳያ ሳሳሁ እና ፋናዬ የችግሩ ተጋፋጭ ነበሩ።
የጥቅማጥቅም(የደንብ ልብስ)ይገባናል ጥያቄ የሚመለከታቸው ሰራተኞች በ 10/07/2017 ጥያቄ የጠየቁ ቢሆንም በ 11/07/2016
የሰራተኛውን ጥያቄ በመተው ለ 3 የስራ መደቦች ብቻ በኮዱ ለይ ከተያዘው 28000 በላይ 36000 ብር ተከፋፍሏል ይህ እንዴት ይታያል
?
የጤና ባለሙያ በሙያው ምስጉን ለታካሚዎች የሚራራ ሆኖ ሳለ ከሙያው ስነምግባር ባፈነገጠ መልኩ በመድረክ ላይ ጠቅላላ ሰራተኛ ፊት
በእኔ ላይ አትምጡብኝ በስሜ የተመዘገበ ሽጉጥ አለ ብሎ መናገር እንዴት ይታያል?
ማጠቃለያ
የሀላፊ መነሳት መስፈርቱ ምንድነው
ከዚህ ቀላይ እንዲያደርግ የሚጠበቀው ምንድነው
ችግሩ ከመሬት ላይ እንዳለ ማረጋገጫው ከሰራተኛው በላይ ምንድነው
ሌላን ባለሙያ ማብቃትስ አስፈላጊ ነው ተብሎ አይታመንም ወይ

በእኛ በኩል ያለው ውሳኔ ምናልባትም ከዚህ በላይ በዚህ ችግር ውስጥ ቀጥሉ የምትሉን ከሆነ ስምሪት ለመቀበል የምንቸገር መሆኑን
እያሳወቅን ወደሌላ ክላስተር እንድታነሱን እንጠይቃለን

You might also like