You are on page 1of 4

መግቢያ

በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የነጻ ገበያ ሥርዓት ተጠቅመው በጤናው ዘርፍ በማተኮር

በገቢና ወጭ ንግድ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ሁሉ የተሻለ አማራጭ በመሆንና አገልግሎት በማቅረብ

ለሀገሪቱ አጠቃላይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚጠበቅባቸውን ተገቢ ድርሻ ለማበርከት

አስበውና ራዕይ ሰንቀው ከዚህ በታች ስማቸው የተጠቀሱት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የቀድሞው

አደራጆች በወጠኑት አላማ መቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ. ሊከውናቸው ካሰባቸው ተግባራት

ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ቢተገበሩ ያላቸው የጠቅላላ ሆስፒታል፣የኢሜጂንግ ዲያግኖስቲክ

ማዕከል፣ የመድኃኒት እና የሕክምና እቃዎች አስመጪና አከፋፋይ ፣ ፋርማሲ እንዲሁም የማማከር

አገልግሎት ለመፈጸም የካፒታል ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አምነንበታል፡፡ በቀጣይ ደግሞ የቴርሺያሪ

ሆስፒታል ግንባታን ጎን ለጎን መሥራት፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እና በትምህርት ዘርፍ የመሰማራት

እቅድ አለው፡፡ ቦርዱ ይህንንም ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት በታላቅ ታማኝነት ፣ቁርጠኝነት እና ሥነ

ምግባር በተላበሰ መልኩ ለመከወን ዝግጁ ነው፡፡

ስለሆነም ቦርዱ በማያወላዳ ሁኔታና በማናቸውም ጊዜ የመልካም አስተዳደር የአሠራር ሥርዓት

መኖሩን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ የ 1952 ዓ.ም የንግድ ሕግ በተለይ የአክሲዮን ማኀበር አሠራር እና

የካፒታል ማሳደግ ሒደትን በሚመለከት የተቀመጡትን ድንጋጌዎችና የሚመለከታቸው የመንግሥት

ተቆጣጣሪ ባለሥልጣናት የሚያወጧቸውን ደንቦችና መመሪያዎች ሳይጣሱ በጥብቅ መፈጸማቸውን

ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ግዴታ ገብተዋል፡፡ ዘላቂነቱ በሂደት ከተረጋገጠ እንዲሁም ከንቁና ታታሪ

የማኔጅሜንት ቡድን ጋር፣ ከሰለጠነ የሰው ኃይል እንዲሁም ዘመኑ ካፈራው ተፎካካሪ ቴክኖሎጂ ጋር በተቀናጀ የጤና
ተቋማቱ ወደፊት በዓለም ደረጃ ስኬታማ ከሚባሉት መሰል ተቋማት ተርታ ሊሰለፉ እንደሚችል ይታመንበታል፡፡

አጭር የኘሮጀክቱ እቅድ መግለጫ


የመሥራች ባለአክሲዮኖች ብዛት 102

የተከፈለ የአክሲዮን ብዛት 4,170


የእያንዳንዱ አክሲዮን የነጠላ ዋጋ በብር 1,000.00

የተከፈለ ጠቅላላ የአክሲዮን መጠን 4,170,000.00


ለመጀመሪያ ደረጃ ሥራዎች በተጨማሪ የሚያስፈልግ የአክሲዮን ብዛት 518,000

ለመጀመሪያ ደረጃ ሥራዎች በተጨማሪ የሚያስፈልግ የአክሲዮን መጠን በብር 518,000,000.00

ድርጅቱን ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስፈልግ የካፒታል መጠን በብር 250,000,000.00


የአገልግሎት ክፍያ በእያንዳንዱ አክሲዮን በመቶ 5%

መግዛት የሚፈቀደው ዝቅተኛ የአክሲዮን መጠን (ቁጥር) 20


መግዛት የሚፈቀደው ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን (ቁጥር) 6,000
የክፍያ ሁኔታ
–         50% በምዝገባ፣ 50% በ 6 ወራት

–         የአገልግሎት ክፍያ በአንድ ጊዜ በሙሉ ይከፈላል


የተፈረመ ካፒታል ያልተከፈለው መጠን ተከፍሎ መጠናቀቅ ያለበት ጊዜ 6 ወራት
አክሲዮኖች ተሽጠው የሚጠናቀቁበት ጊዜ 9 ወራት
ከወጭ ቀሪ የአገልግሎት ክፍያ=ለድርጅቱ ካፒታል ማሳደጊያ እንዲውል ይደረጋል
የዋና መሥራቾች አደራጅ ኮሚቴ አባላት ጥቅም = አደራጆች የተቋማቱ ዕውን መሆን የሚሰጣቸውን እርካታን
በማስቀደም ምንም ዓይነት ከትርፍ በመቶኛ ክፍያ አይኖራቸውም

የመሥራች ባለአክሲዮኖች ጥቅም =የመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት ትርፍ የዓመታዊ ትርፍ 10% ለመሥራች
ባለአክሲዮኖች (መሥራች አደራጆችን ጨምሮ)
ለአማካሪዎች=ምሥጋናና የምሥክር ወረቀት በሁለተኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ይሰጣል፡፡
ድርጅቱ ሥራ የሚጀምረው ደረጃውን በጠበቀ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ በኢሜጂንግ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ፣ መድኃኒትና
የሕክምና መገልገያ ዕቃዎች አስመጭና አከፋፋይ ፣ ፋርማሲ እና የማማከር ገንዘብ ለሕዝብ ለሽያጭ በሚቀርቡ ተራ
አክሲዮኖች የሚሰበሰብ ይሆናል፡፡ እንደአስፈላጊነቱና አቅም በፈቀደ መጠን በጠቅላላ ጉባዔ ጸድቆ የተፈቀደው ካፒታል
ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲያድግ እየተደረገ መጀመሪያ እስከ ብር ሁለት ቢሊዮን በሂደት ደግሞ ከዚያም በላይ ከፍ እንዲል
ይደረጋል፡፡

መቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር ወደ ጤና አገልግሎት ዘርፍ ሲሰማራ ዋና ዓላማ ያደረጋቸው ጉዳዮች
የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ/ እያደገ ያለውን የታካሚዎች ከኢትዮጵያ ውጭ የህክምና አገልግሎት ፍላጎት በሀገር ውስጥ በማሟላትና በመስጠት፣
በግሉ የጤና አገልግሎት ዘርፍ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ሀገራችንን ከከፍተኛ
የውጭ ምንዛሬ ለማዳን፤

ለ/ በሀገራችን ተወዳዳሪ የሆነ፣ የታካሚዎችን ፍላጎት በማርካት ላይ ያተኮረ ተመራጭ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ
ተቋም መሆንና ከሀገራችን ውጭ ለሚገኙ ዜጎች ተመራጭ የህክምና ማዕከል በመሆን የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት
ለሀገሪችን ኢኮኖሚ የበኩሉን ድርሻ ለመውጣ፤

ሐ/ ለኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ተጨማሪ የሥራ ዕድል በመፍጠር የሥራ አጥነትን በመቀነስ ድርሻን ለመወጣት፤

መ/ ጠቅላላ ሆስፒታል ለማቋቋም፤

ሠ/ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ለማቋቋም፤


ረ/ መድኃኒትና የህክምና መገልገያ ዕቃዎች አስመጭና አከፋፋይ ንግድ ሥራ ላይ ለመሰማራት፤
ሰ/ ተርሸሪ ሆስፒታል ለማቋቋምና ሚዲካል ሲቲ ለመመስረት፤
ሸ/ የማማከርና ምርምር አገልግሎት ለመስጠት፤
ቀ/ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለመሠማራት፤

በ/ በትምህርት ዘርፍ መሠማራት፤


ተ/ የባለአክሲዮኖችና የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት ለማሟላት፤

ቸ/ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ሌሎች ከፍተኛ ባለሙያዎች ወደሀገራቸው መጥተው
እንዲያገለግሉ ተገቢውን ለማድረግ፤

አ/ ደረጃቸውን ከጠበቁ ዓለም ዐቀፍ የህክምና ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት እና የመሳሰሉት ዓላማዎች አሉት፡፡

መንግሥታዊ ኤጀንሲዎች ሕጋዊ/ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በየዕለቱ የኦኘሬሽን ሥራ ስለሚያገናኘን

እንዲሁም አብዛኛው የሀገሪቱ የንግድ ማኅበረሰብን ያካተተ የቴክኖሎጂ መረጃ የመለዋወጥ

አገልግሎቶች ስለሚሰጡበት የዋናው መሥሪያ ቤታችን ሕጋዊ መቀመጫ በአዲስ አበባ ከተማ

አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ 2 ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር

210/ 1-17 ለ ነው፡፡

በቀጣይም በክልል ከተሞች እንዲሁም መለስተኛ ከተሞች በመሄድ ቅርንጫፍ እንዲከፈትበት

የውሣኔ ሃሳብ በቀረበበት ሥፍራ የሕዝብ ብዛት የሚያሳይ ጥናት (የሕዝብ ቁጥር፣ የጾታ

ስብጥር፣ዕድሜ) ፣በገጠሩ በቂ የጤና አገልግሎት የሌለበት አካባቢ በመሄድ ተደራሽ የመሆን

ተግባራትም ይከወናሉ፡፡

5. የመቅረዝ አ.ማ. ርዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴት

ርዕይ

ለጥራት የሚተጋ በተገልጋዮች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው እና እጅግ ተመራጭ የሆነ የጤና

እንክብካቤ ሰጪ መሆን

ተልዕኮ
በፍቅር የሚንከባከቡ ባለሙያዎችንና ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጅዎች በመጠቀም በማኅበረሰቡ

ዘንድ ተቀባይነት ያለው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጤና አገልግሎት መስጠት

ዕሴቶቻችን

የድርጅት ስኬት የሚመሠረተው ፈሪሃ እግዚአብሔር ባለው፣ በሰለጠነ፣ በሥነ- ምግባር  በሚመራ

የሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ ግኝቶች ጣምራ እንቅስቃሴ ውህደት ነው፡፡

ስለሆነም ቦርዱ፣ ማኔጅመንቱና የድርጅቱ ሠራተኛ  ተጠያቂነትን የተላበሰ ሆኖ በጤናው ዘርፍና

በአጠቃላይ ደግሞ ለሰፊው ሕዝብ አድናቆት የሚቸረው እሴት ማበርከት ሲሆን ለዚሁም ተቋሙ

ከፍተኛውን የሞራልና የሥነ-ምግባር ደረጃ እንዲኖረው ማድረግና የሚከተሉትን ዕሴቶች በዋነኝነት

ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፣

You might also like