You are on page 1of 8

1. ቀሰም ማኑፋክቸሪንግ አክሲዩን ማህበር ማነው? የማነው?

በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የነጻ ገበያ ሥርዓት ተጠቅመው በጤናው ዘርፍ ላይ በማተኮር
በገቢና ወጭ ንግድ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ሁሉ የተሻለ አማራጭ በመሆንና አገልግሎት በማቅረብ
ለሀገሪቱ አጠቃላይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚጠበቅባቸውን ተገቢ ድርሻ ለማበርከት
አስበውና ራዕይ ሰንቀው በተነሱ በጤናው ዘርፍ እና በሌሎች የሙያ ዘርፎች የካበተ ልምድ ባላቸው
ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ አክሲዮን ማኅበር ነው
2. ቀሰም ማኑፋክቸሪንግ አክሲዩን ማህበር ሕጋዊ እውቅና አለው?
የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ. የኢትዮጵያ የንግድ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ሁሉንም
መስፈርቶች አሟልቶ በኢትዮጵያ በንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር የተመዘገበ ሕጋዊ ተቋም ሲሆን
 በምዝገባ ቁጥር ፡ AR/AA/3/0006864/2013
 በምዝገባ ቀን፡ 12/01/2013 ዓ.ም. ተመዝግቧል
3. ቀሰም ማኑፋክቸሪንግ አክሲዩን ማህበር መሥራቾች እነማን ናቸው?
መሥራቾቹ 102 ሲሆኑ ከ 85 የሚበልጡት በጤናው ዘርፍ ሰፊ የሥራ ልምድ ከበቂ በላይ የሙያ
ስብጥርና የትምህርት ዝግጅት ያላቸው እንዲሁም በጨርቃጨርቅ፣ በጋመንት ፕሮዳክሽን፣
በአስተዳደር፣ ፋይናንስ እና ተቋማትን በመምራት ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ከ 15 የሚበልጡ
ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ናቸው።
4. ቀሰም ማኑፋክቸሪንግ አክሲዩን ማህበር የቦርድ አባላቱስ እነማን ናቸው?
ቦርድ አባላቱ ዘጠኝ ሲሆኑ በሙያ ስብጥራቸው፣ በልምዳቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ፤
የጨርቃጨርቅ እና ጋመንት/የአልባሳት ማምረቻ ኢንዱስትሪ እየመሩ የሚገኙ ፣ የቦርድ ስራ ልምድ
ያላቸው፣ ታማኞች እና ለቆሙለት ዓላማ ቆርጠው የሚሠሩ ናቸው።
5. አዲስ የሚገዙ ባለአክሲዮኖች መሥራች መሆን ይችላሉ?
በፍጥነት ከገዙ አዎ በትክክል ይችላሉ!!!
ቀሰም ማኑፋክቸሪንግ አ.ማ. ባደረገው አንደኛ አስቸኳይ ስብሰባ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ፈጥነው
እስከ ሀምሌ 30 ቀን 2015 ዓ.ም አክሲዮን ለሚገዙ ባለአክሲዮኖች መሥራች እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡
ስለዚህ መሥራች አባል መሆን ይቻላል፡፡
6. ቀሰም ማኑፋክቸሪንግ አክሲዩን የመሥራችነት ጥቅም አለው?
በትክክል!
መሥራች የሆኑ ባለአክሲዮኖች አክሲዮን ማኅበሩ ማትረፍ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ሶስት
ተከታታይ ዓመታት ከተጣራው ትርፍ 10-20 በመቶውን ባላቸው አክሲዮን መጠን ይከፋፈላሉ፡፡
ቀሪውን 90 በመቶውን ደግሞ ከሌሎች ጋር በመሆን ባላቸው አክሲዮን መጠን ይከፋፈላሉ፡፡
7. ቀሰም ማኑፋክቸሪንግ አክሲዩን ማህበር ዓላማው ምንድን ነው?
 እያደገ ያለውን የአልባሳት ምርት ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገቡ (import) የሚደረገውን የአልባሳት
ምርት ፍላጎት በሀገር ውስጥ በማሟላትና በማምረት ፣ በግሉ የአልባሳት እና የጨርቃጨርቅ
ኢንዱስትሪ ዘርፍ ጥራት ያለው ምርት በማምረት እና ለገበያ በማቅረብ የበኩሉን ድርሻ
በመወጣት ሀገራችንን ከከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለማዳን፤
 በምስራቅ አፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና እድል በመጠቀም ለጎረቤት ሀገሮች እና ለአውሮፓ ገበያ ጥራት
ያላቸው አልባሳት በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት እና የአክሲዮን ማህበሩን ትርፍ ማሳደግ
ነው።
 በሀገራችን ተወዳዳሪ የሆነ፣ የተጠቃሚውን ፍላጎት በማርካት ላይ ያተኮረ ተመራጭ የአልባሳት
ምርት በማምረት ለገበያ የሚያቅረብ ተቋም መሆንና ከሀገራችን ውጭ ወደ ምስራቅ አፍሪካ
ሀገራት እና አውሮፓ ገበያ ተመራጭ የአልባሳት ምርት በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት
ለሀገሪችን ኢኮኖሚ የበኩሉን ድርሻ ለመውጣ፤
 ለኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ተጨማሪ የሥራ ዕድል በመፍጠር የሥራ አጥነትን በመቀነስ
ድርሻን ለመወጣት፤
 የባለአክሲዮኖችና የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት ለማሟላት፤
 በውጭ ሀገራት የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ሌሎች ከፍተኛ ባለሙያዎች ወደ ሀገራቸው
መጥተው እንዲያገለግሉ ተገቢውን ለማድረግ፤
 ደረጃቸውን ከጠበቁ ዓለም ዐቀፍ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ/ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት
8. ቀሰም ማኑፋክቸሪንግ አክሲዩን ማህበር በምን በምን ዘርፎች ላይ ይሰማራል?
 የአልባሳት ምርት ዘርፍ (በጋርመንት ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት)፤
 በአግሪካልቸር፣ አግሮ-ፕሮሰሲንግ ዘርፍ፤
 ጅምላ ንግድ፣ አስመጭና አከፋፋይ ንግድ ሥራ ላይ ለመሰማራት፤
 የሰራተኛ ምልመላ እና የማገናኘት ስራዎች ዘርፍ፤
 በሂሳብ፣ ታክስ፣ የፋይናንስ አሰራር ማማከር እና የኦዲት ስራዎችን ዘርፍ፤
 የማማከርና ምርምር አገልግሎት ለመስጠት፤
 በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ
 በትምህርት ዘርፍ ይሰማራል
 ከዚህም ውስጥ በመጀመሪያ ዙር ከሚተገበሩ ተግባራት ውስጥ:
I. የአልባሳት ምርት ዘርፍ (በጋርመንት ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት)፤
II. በትምህርት ዘርፍ
III. በአግሪካልቸር፣ አግሮ-ፕሮሰሲንግ ዘርፍ፤ዘርፍ

9. ቀሰም ማኑፋክቸሪንግ አክሲዩን ማህበር አክሲዮን ለመግዛት መስፈርቱ ምንድን ነው?

 በዓላማው ማመን፤
 እድሜው ከ 18 ዓመት በላይ የሆነው
 ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሁሉ

 ማንነትን የሚገልጽና የታደሰ መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ/ፓስፖርት በማቅረብ አክሲዮን ለመግዛት


ይችላል።

10. ቀሰም ማኑፋክቸሪንግ አክሲዩን ማህበር ካፒታሉስ ምን ያህል ነው?


ቀሰምማኑፋክቸሪንግ አ.ማ የተፈቀደ ካፒታል ብር 127 ሚሊዮን ሲሆን በመጀመሪያ ደረጃ
ለሚሠራቸው ሥራዎች የሚያስፈልገው የብር መጠን ብር 50,698,813.16 ብር ነው፡፡

11.ከቀሰም ማኑፋክቸሪንግ አ. ማ. አክሲዮን መግዛት የሚችሉት እነማን ናቸው?


 ኢትዮጵየውያን
 ትውልደ ኢትዮጵያውያን
 ግለሰብ በተናጠል እና በጣምራ
 የንግድ ድርጅቶች
 የሃይማኖት ተቋማት
 ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች
 የእርዳታ ድርጅቶች
12.ትውልደ ኢትዮጵያውያን አክሲዮን መግዛት የሚችሉት እንዴት ነው?
 ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ
 የጸና ፓሰፖርት ኮፒ
 የሚገዙትን የአክሲዮን መጠን ባሉበት ሀገር ሆነው በተከፈቱት የባንክ ሒሳቦች በሀገራችን ተቀባይነት
ባላቸው የሐዋላ መንገዶች ገቢ ማድረግ ወይም ከውጪ ምንዛሬ ሒሳባቸው ላይ በመክፈል
 የተዘጋጀውን ቅጽ በድረ ገጹ ላይ በኦን ላይን ወይም ከድረ ገጽ በማውረድ መሙላትና በኢሜል መላክ
ወይም በተወካይ በኩል ቅጹን በመሙላት በቀላሉ መግዛት ይችላሉ
13. የትውልደ ኢትዮጵያዊ ካርዴ በተለምዶ ቢጫ ካርድ/Yellow card/ የሚባለው

የአገልግሎት ዘመኑ አብቅቷል፡፡ አክሲዮኑን መግዛት እችላለሁ?


አክሲዮኑን ለመግዛት የግድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሚለው ካርድ አስፈላጊ ነው። ቢሆንም ለማሳደስ
የሚወስደው ጊዜ ስላለ መሥራች የመሆኑን እድል እንዳያጡት በማሰብ አክሲዮኑን አሁን ገዝተው እና
ቅጹን ሞልተው ቢጫ ካርድዎን በፍጥነት አሳድሰው እንደላኩልን የድርጅቱን ደረሰኝ ቆርጠን
የምንልክልዎ መሆኑን ሆኖም ግን በተባለው የአክሲዮን ሽያጭ ወቅት(እስከ ሐምሌ 1 2013 ዓ.ም)
አሳድሰው የማይልኩልን ከሆነ ምዝገባውን የምንሰርዘው እና ገንዘብዎን ድርጅቱ ሥራ ከጀመረ በኋላ
የምንመልስልዎ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን

14.የአንድ አክሲዮን ዋጋ ስንት ነው? ከስንት ብር ጀምሮ መግዛት ይቻላል?


 የአንድ አክሲዮን ዋጋ ብር 10,000
 ዝቅተኛው የግዢ መጠን ብር 50,000 ብር ሲሆን ከፍተኛው መጠን ብር 1,500,000
15.የአክሲዮን አከፋፈል ሁኔታውስ እንዴት ነው?
የአክሲዮን ክፍያ በአንድ ጊዜ ወይም በሁለት ጊዜ ሊከፍሉ ይችላሉ።
በአንድ ጊዜ ሙሉውን መክፈል አልያም ደግሞ በመጀመሪያ 25 በመቶውን ከፍለው ቀሪውን 75 በመቶውን ደግሞ
በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ መክፈል ያቻላል።
16.የአገልግሎት ክፍያው ስንት ነው?

በሚገዙት የአክሲዮን መጠን አምስት በመቶ (5% ) ይኸም የአገልግሎት ክፍያ ከመጀመሪያው ክፍያ ጋር
በተፈረመው ልክ ተሰልቶ በአንድ ጊዜ ብቻ ይከፈላል

17.ለሕጻናት ልጆች አክሲዮን መግዛት ይቻላል? እንዴት?

በትክክል!

ለልጆችዎ አክሲዮኑን በመግዛት የወደፊት ሕልማቸውን ማሳካት ይችላሉ፡፡ ለልጆችዎ ለመግዛት ሲቀርቡ
የልደት ምስክር ወረቀት ኮፒ፤ የእርስዎ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት/መንጃ ፈቃድ ኮፒ እና ባንክ ያስገቡበትን
ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ የአሳዳጊውን ስም አስቀድሞ ለሕጻን እገሌ/እገሊት ብሎ የአክሲዮን መግዣ ቅጹ ላይ
በመሙላት በስማቸው ሊገዙላቸው ይችላሉ
18. ከትዳር አጋር ጋር በጣምራ እንዴት መግዛት ይቻላል ? ዘመድ ወዳጅ እና ሸሪክስ?
ይቻላል!

የጋብቻ ምስክር ወረቀት በማቅረብና የእያንዳንዳቸውን መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ/ፖስፖርት ኮፒ በማያያዝ


እና የሚገዙትን የአክሲዮን መጠን በባንክ በማስገባት መግዛት ይቻላሉ
ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ዘመድ፣ ወዳጅና ሽሪክ ሁሉም መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ/ፖስፖርት ኮፒ በማያያዝ
እና የሚገዙትን የአክሲዮን መጠን በባንክ በማስገባት መግዛትይችላሉ

19.የአክሲዮን መሸጫ ቦታው የት ነው?

በኢትዮጵያ 10 ባንኮች የባንክ አካውንት የተከፈተ ሲሆን ባንኮቹም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣
አቢሲንያ፣ አዋሽ፣ ሕብረት፣ቡና፣ ንብ፣ወጋገን፣ አባይ፣ ኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ና ዳሸን ባንኮች ናቸው

20. ከውጪ ሀገር ሆኖ አክሲዮን እንዴት መግዛት ይቻላል?


ሀገር ውስጥ ውክልና ያለው ሰው ካለ ወይም ካሉበት ሆነው አስፈላጊውን መረጃ በድረ ገጹ ላይ ባለው
ቅጽ በመሙላት መግዛት ይቻላል
ከኢትዮጵያ ውጪ በመካከለኛው ምሥራቅ፣በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ ነዋሪ ሆነው
ከሚያስተባብሩ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ገንዘቡን ከላይ በተዘረዘሩ ባንኮች በተመዘገቡ ሕጋዊ የሐዋላ
መንገዶች በመላክ ወይም በባንኮች በተከፈቱት የውጪ ምንዛሬ ሒሳቦች ገንዘቡን በመላክ መግዛት
ይቻላል
21.ትውልደ ኢትዮጵያዊ ነኝ አክሲዮኑን ስገዛ መክፈል የምችለው ባለሁበት አገር ገንዘብ
ብቻ ነው ወይስ በኢትዮጵያ ብርም ጭምር?

አክሲዮኑን ሲገዙ ከፈለጉ ባሉበት ሀገር ገንዘብ በቀጥታ መግዛት ወይም በኢትዮጵያ ብር ልከው መግዛት
ይችላሉ

22. የአክሲዮን ክፍያውን በሌላ ሀገር ምንዛሬ ሳስገባ ምንዛሬው እንዴት ነው የሚሆነው ?
ያስገቡት የገንዘብ መጠን የሚሰላው በእለቱ ባለው ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው የኢትዮጵያ ብር
የግዢ ምንዛሬ ይሆናል
ከ 1000 ብር በታች የሆነ ትርፍ የሚመጣ ካለ ተጨማሪ የጎደለውን በመሙላት አንድ አክሲዮን
ማድረግ ይችላሉ

23. ገንዘቡን በባንክ ገቢ ካደረኩ በኋላ ምን ማድረግ ይኖርብኛል ?


ማንነትዎን ከሚገልጽ ከታደሰ መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ/ፓስፖርት ጋር ባንክ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ
በመያዝ መቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ የፕሮጀክት ጽ/ቤት መምጣትና በምትኩ የመቅረዝ የጤና
አገልግሎት አ.ማ ደረሰኞች መውሰድ ይኖርብዎታል፤
ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆኑ ሲመችዎት ጽ/ቤት በመምጣት ወይም ለዘመድ ወዳጅ በመላክ ወይም ስካን
አድርገው በድርጅቱ ኢሜይል በመላክ ወይም በአክሲዮን ማኅበሩ ድረ ገጽ አስፈላጊው ሰነድ
በማስገባት የኦላይን ምዝገባ በመፈጸም እና የባንኩን ደረሰኝ በመላክ የአክሲዮን ማኅበሩን ደረሰኞችን
መውሰድ ይኖርቦታል።
24.የአክሲዮን ግዢውን በኦላይን ማድረግ እችላለሁ?

የሚገዙበትን ሁኔታ አመቻችቷልበኦላይን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች 1. የታደሰ


መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ/ፓስፖርት

2. ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከሆኑ የትውልደ ኢትዮጵያዊ ካርድ (yellow card)

3. ተወካይ ከሆኑ የተሰጠዎትን ሕጋዊ ውክልና

4. ገንዘቡን ባንክ ያስገቡበት ደረሰኝ

5. ፊርማ

ከ 1-5 ያሉትን አስፈላጊ ሰነዶች ስካን በማድረግ ወይም ፎቶ በማንሳት ያዘጋጁ

ከዚያም በድረ ገጻችን www.meqrezhealth.com ላይ ለ ግለሰብ ወይም ለትውልደ ኢትዮጵያዊ ወይም


ለድርጅት ከሚለው የሚፈልጉትን በመምረጥ መሙላት ይቻላል።

በተጨማሪም ከላይ ከ 1-5 ያሉትም መረጃዎች ካደራጁ በኋላ በ ድረገጻችን ላይ በ Pdf ፎርማት የተቀመጠውን
የአክሲዮን መግዣ ቅጽ በማውረድ በእጃችን ከሞላንና ከፈረምን በኋላ ከላይ ካዘጋጀናቸው መረጃዎች ጋር
ስካን በማድረግ በ shares@meqrezhealth.com መላክ ይችላሉ።

እነዚህን መረጃዎች በላኩ 48 ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ባስመዘገቡት ኢሜይል እንልክሎታለን


25.አክሲዮን አሁን በሌላ ሰው ስም ገዝቼ በኋላ ወደ ራሴ ስም ማዞር እችላለሁ ?

በትክክል!አክሲዮኑን እርስዎ በሚመችዎ ወቅት እና ጊዜ ወደ ራስዎ ስም እንዲዛወርልዎ የገዛልዎት ሰው ዋና


ቢሯችን መጥቶ ለቦርዱ በማቅረብ ማዞር ይቻላል፤ በእርስዎ መሞላት የሚያስፈልገውን ሰነዶች በድረ ገጻችን
ላይ ባለው የኦላይን መመዝገቢያ ወይም በእጅ ሞልተው መላክ ይችላሉ።

26. አክሲዮን ለማዛወር ክፍያ አለው?


በመቅረዝ የጤና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር በኩል የሚጠየቁት ምንም አይነት ክፍያ አይኖረውም ፤
አይኖረውበመንግሥትበመንግሥት በኩል ግን አክሲዮን ለማዛወር ክፍያ ሊኖረው ይችላል።
27.የአክሲዮን ድርሻዬን መሸጥ ብፈልግ መሸጥ እችላለሁ?
በተለያዩ ወቅቶች በጠቅላላ ጉባኤው ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተገዢ ለመሆን ዝግጁ የሆነ መሆን
ይኖርበታል
28. መቅረዝ ሥራ መቼ ይጀምራል ?
መቅረዝ የተቋቋመ ድርጅት ስለሆነ ከታቀዱት አምስት ፕሮጀክቶች ውስጥ በመጀመሪያ
የዲያግኖስቲክ ማእከሉን የሚያስጀምር ገንዘብ እንደተሰበሰበ ሥራውን ጀምሮ ጎን ለጎን ሌሎቹን
ሥራዎችንም በፍጥነት ለመጀመር አክሲዮኖች እየሸጠ ይቀጥላል። ይኸም ገንዘባችን ብዙ ጊዜ ያለ
ሥራ ባንክ ላይ እንዳይቀመጥ እና የተሻለ ትርፍን ለባለአክሲዮኖች እንዲያመጣ ያስችላል። ስለዚህ
አክሲዮኑን በቶሎ በመግዛት ወደ ሥራ እንድንገባ የድርሻዎትን ይወጡ።
29. የመቅረዝ ትርፋማነቱስ እንዴት ነው?
ባደረግነው የአዋጭነት ጥናት በሀገራችን ውስጥ እየተካሄዱ ካሉ የቢዝነስ ዘርፎች የጤናው ዘርፍ
በጣም አዋጪ እና ዝቅተኛ የመክሰር አደጋ ያለው መሆኑን ያሳያል። በዚህም መሠረት መቅረዝ የጤና
አገልግሎት ባደረገው የአምስት አመት የአዋጭነት ጥናት በመጀመሪያው ዓመት 13 በመቶ
በሁለተኛው ዓመት 26 በመቶ በሦስተኛው ዓመት 42 በመቶ በአራተኛው ዓመት 61 በመቶ እና
በአምስተኛው ዓመት 90 በመቶ ትርፍ እንደሚያመጣ ያመላክታል። የወጣበትንም የኢንቨስትመንት
ወጪ ከ ሁለት አመት ባነሰ ጊዜ እንደሚመልስ ያሳያል። በመሆኑን ከሌሎች ዘርፎች በተሻለ ትርፋማና
አዋጪ ተቋም መሆኑን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።
30. የትርፍ ክፍፍሉ በየዓመቱ ነው? ያገኘሁትን ትርፍ አክሲዮን ማሳደግ ብፈልግ እችላለሁ?
አዎ! የትርፍ ክፍፍሉ በየዓመቱ ባለዎት የአክሲዮን መጠን ልክ ሆኖ መጋቢት 30 2013 ዓ.ም አክሲዮን
ከገዙ ደግሞ በተጨማሪ የመሥራችነት ጥቅም 10 በመቶ በገዙት የአክሲዮን መጠን ልክ ለተከታታይ
ሦስት አመታት ይደርስዎታል። በአክሲዮን ማኅበሩ የወጣ የአክሲዮን ሽያጭ ካለ የትርፍ ክፍፍል
ድርሻዎን አክሲዮን ማኅበሩ ላይ አክሲዮኖችን ለማሳደግ ሊያውሉት ይችላሉ። አክሲዮን ማኅበሩን
ከተቀላቀሉ በኋላ ለያንዳንዱ ባለአክሲዮን በግሉ በሚከፈትለት መለያ ስም እና የይለፍ ቁጥር ወይንም
በቴሌግራም በቀላሉ በመግባት የገዙትን የአክሲዮን መጠን፣ የቀረብዎት የአክሲዮን ክፍያ ካለ፣ በትርፍ
ክፍፍሉ የደረሰዎትን ድርሻ፣ አዲስ ተጨማሪ የወጡ አክሲዮኖች ብዛት፣ በአክሲዮን ማኅበሩ የሚላኩ
መልእክቶችን በድረ ገጻችን ላይ ለባለአክሲዮን በሚለው ክፍል ( እየተዘጋጀ ያለ) ላይ በመግባት
መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ።
31. የአክሲዮን ሽያጭ የሚያበቃው መቼ ነው?
ይፍጠኑ!
የመሥራች አባል የመሆን እድል መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ይጠናቀቃል
ሙሉ በሙሉ የአክሲዮን ሽያጩ ለ ዘጠኝ ወራት የሚቆይ ሲሆን በ ሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም
ይጠናቀቃል
32. የጽ/ቤቱ አድራሻ የት ነው?
ዋና ጽ/ቤት በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ
ዩኒቨርሲቲ 2 ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-17 ለ
33. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉስ?
ስልክ ቁጥር +251-991-737373
ኢሜል: MeQrezHS2020@gmail.com,info@meqrezhealth.com,
shares@meqrezhealth.com
ድረ ገጽ፡ www.meqrezhealth.com
ቴሌግራም:@MeQrezHealth
facebook: fb.me/meqrezhealth
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

You might also like