You are on page 1of 13

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል

ንብረት ክፍፍል
ማስፈፀሚያ

አጭር የሥራ ዕቅድ፡፡

ጥቅምት 01/ 2016


ወላይታ ሶዶ

መግቢያ፡-
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላችን ከነባሩ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ራሱን ችሎ የኢትዮጵያ አስራ ሁለተኛ የኢትዮጵያ
ፌዴራል ክልል ሆኖ ከተመሠረተ የአንድ ወር ዕድሜ ያለው ቢሆንም እንኳ ያለውን ሰው ኃይልና ከፈረሰው
ነባሩ ክልል በቀመር መሠረት የደረሰውን ውስን ሀብት ይዞ ያለውን ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት በመጠቀም ክልሉን
ከሌሎች ክልሎች ጋር ተወዳዳሪና ውጤታማ ለማድረግ በፍጥነት ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ የተጀማመሩትን
ሥራዎች በሙሉ አቅም በመፈፀም ውጤታማ ማድረግ ይቻል ዘንድ የሥራ ማሳለጫ መሳሪያ የሆኑት የቢሮ
ቁሳቁስ ለተቋማት ማድረስ እገብጋቢ ጉዳይ መሆኑ ይታመናል፡፡

ለዚህም በድልድል ለክልላችን የደረሱት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ፋርኒቸር /ቁሳቁስ/ የተጠቀሰው ተቋም
ንብረት ብቻ ሳይሆን የክልሉ የሁሉም ተቋማት የጋራ ንብረት በመሆናቸው ምንም ንብረት ላልደረሳቸው እና
አንድ ዓይነት ንብረት ብቻ ለደረሳቸው ተቋማት በማጋራት ለህዝባችን ፈጣን፤ ፍትሃዊና ተደራሽ አገልግሎት
መስጠት ይቻል ዘንድ የክልላችን የውስጥ ንብረት ክፍፍል ሥራ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ አጭር የሥራ
የማስፈፀሚያ ሥራ ዕቅድ ወጥቷል፡፡

ክፍል አንድ፡

የኮሚቴ መቋቋም አስፈላጊነትና ዓላማ፡-

የንብረት ክፍፍሉን በበላይነት የሚመራ የሚያግዝና የሚስፈፅም ኮሚቴ መሰየም እንድሁም የሚመራበት
ግልፅ አሠራር ሥርዓት አስፈላጊ በመሆኑ በሚከተለው ሁኔታ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡

1. የኮሚቴዉ መቋቋም ዓላማ፡-


ኮሚቴውን ማቋቋም ያስፈለገበት ዋና ዓላማ በቀመር መሰረት በክልላችን ስም ለተወሰኑ ተቋማት
የደረሰዉን የቢሮ ፋርኒቸር /ቁሳቁስ/ ሆነ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ምንም ቁሳቁስ ላልደረሳቸዉ እና
አንድ ዓይነት ዕቃ ለደረሳቸው ተቋማት ካላቸው የሰው ኃይል፤ የሥራ ሁኔታ፤የሥራ ሥፋትና ክብደት
አኳያ በማየት ኃላፊነት በተሞላ ሁኔታ በማከፋፈል ሥራ ለማስጀመር ማስቻል ነዉ፡፡
2. የኮሚቴው ሁኔታ፡-
የኮሚቴዉ አደረጃጀት ለስራ አመችነትና ቅልጥፍና ሲባል አቢይ ኮሚቴና ንዑሳን ኮሚቴዎች በመሆን
ተደራጅቷል፡፡
2.1 አቢይ ኮሚቴ፡-
የአቢይ ኮሚቴ አባላት ለስራዉ ቅልጥፍናና ፍትሃዊነት ታስቦ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አማካሪዎች
ስራዉን በበላይነትና በባለቤትነት እንዲመሩ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፡-
1. ዶ/ር ብርሃኑ ጌቦ የርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ ሰብሳቢ
2. አቶ ኩታዬ ኩሲያ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ ም/ሰብሳቢ
3. አቶ ምህረቱ አሰፋ የፋይናንስ ቢሮ ም/ኃላፊ ፀሐፊ
4. አቶ ሳሙኤል ቀቀቦ ኢኮኖሚ ዘርፍ አማካሪ አባል
5. አቶ ለማ ገዙሜ የህግ ጉዳዮች ዘርፍ አማካሪ አባል
6. አቶ ይልማ ሱንታ የመሰረተ ልማት ጉዳዮች ዘርፍ አማካሪ አባል
7. አቶ ሀልገዮ ጅሎ የማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ አማካሪ አባል
8. አቶ ሎሬ ካኩታ የመሰረተ ልማት ጉዳዮች ዘርፍ አማካሪ አባል
9. አቶ ካሣሁን ፍልፍሉ የመልካም አስተዳደር እና አከባቢ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አባል በመሆን
አቢይ ኮሚቴ ሆነዉ ተሰይመዋል፡፡

2.2 ንዑሳን ኮሚቴ አደረጃጀት በተመለከተ፡-


ኮሚቴዉ ከአንድ በላይ የሆኑ ንዑሳን ኮሚቴዎች የሚኖሩት ሲሆን ይህም ንብረቱን እንድጋሩት
ከተለዩት ከክልሉ ተቋማት የተውጣጡ የንብረት ክፍል ኃላፊ ወይም የንብረት ኦፊሰር እና የአይሲቲ
/ICT/ ባለሙያዎች እንድሁም እንደየተቋሙ የሥራ ባህሪይ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች የንዑሳን
ኮሚቴው አባላት ይሆናሉ፡፡ የየተቋማቱ አመራርም በቅርበት ሥራውን ይከታተላሉ ይደግፋሉ፡፡

3. የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 በድልድሉ መሰረት ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደረሱ የቢሮ ፋርኒቸር /ቁሳቁስ/ ስራ


ለማስጀመር ይረዳ ዘንድ ድልድሉ ከደረሳቸዉ ቢሮዎች ምንም ዓይነት ዕቃ ላልደረሳቸዉ
እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብቻ ለደረሳቸው ቢሮዎች ከተቋማቱ የሰው ኃይል፤ የሥራ
ስፋትና ክብደት እንድሁም ከተቋማቱ ልዩ የሥራ ባህሪይ አንፃር የማከፋፈል ሥራ
መሥራት፤
 በድልድሉ መሰረት ለክልላችን የደረሱ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ከደረሳቸው ቢሮዎች ምንም
ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ላልደረሳቸዉ እና የቢሮ ፋርኒቸር /ቁሳቁድ/ ብቻ ለደረሳቸው
ተቋማት ካላቸው የሰው ኃይል፤ ሥራ ስፋትና ከተቋሙ ልዩ የሥራ ባህሪይ አንፃር ንብረቱን
አመጣጥኖ ማከፋፈል፤
 ቁሳቁሱ በተቻለ መጠን የአገልግሎት ጊዜያቸውና በየዓይነታቸው በጥንቃቄ እና ኃላፊነት
በተሞላ እንዲሁም በቅንነት፤ ከእኔነት በፀዳ የእኛነት መንፈስ በተላበሰ ሁኔታ ማከፋፈል ሥራ
የመሥራት፤
 የቢሮ ፋርኒቸርና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የምሰሩና የማይሰሩትን በጥንቃቄ የመለየት ሥራ
ይሠራል፡፡
3.1 የአቢይ ኮሚቴ ተግባራት በተመለከተ
አቢይ ኮሚቴው በዋናነት ክልሉ ባለፉት ጊዜያት በተለያዩ ምክንያት የባከነበትን የሥራ ጊዜ
ለማካካስና በጊዜ የለንም እሳቤ የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት አቅምን አሟጦ
መሥራት የሚቻልበት ላይ ተቋማትን በመደገፍ በፍጥነት ወደ ሥራ ማስገባት ነው፡፡ ምንም እንኳ
የንብረት ክፍፍሉ በተወሰኑ ተቋማት ስም የተከፋፈለ ቢሆንም በአጠቃላይ የክልሉ የጋራ ንብረት
በመሆኑ በመተሳሰብ በሁሉም ተቋማት ለክልሉ ሕዝብ ሚዛናዊ አገልግሎት መስጠት የሚቻልበት
ላይ በንብረት ክፍፍል ሥራው ንዑሳን ኮሚቴዎችን በበላይነትና በቅርበት ይመራል ይከታተላል፡፡
ለዚህም፡-
 ለንዑሳን ኮሚቴዎች የስራ ኦሬንቴሽን በመስጠት በአስቸኳይ ወደ ስራ ያስገባል፤
 የተደራጁ ንዑሳን ኮሚቴዎችን በመከፋፈል ስራዉን በቅርበት ይመራል ይከታተላል ክፍተት
ሲፈጠር ያርማል፤
 በንዑሳን ኮሚቴዉ ተሰርቶ የሚቀርበዉን ንብረት ክፍፍል አስተያየት ሰጥቶና ስህተት ካለም
በማረም ተግባራዊ እንድደረግ ያደርጋል ያስፈፅማል፤
 ንብረት ክፍፍሉ የደረሳቸው ተቋማት ንብረቱን በፍጥነት እንድያነሱ ያሳውቃል
አስፈላግውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
 ተቋማት የቢሮ ፋርኒቸርም ሆነ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የማጓጓዣ መኪና በማዘጋጀት
ሳያቆራርጡ አንድ ጊዜ አንድ ላይ እንድያነሱ ያደርጋል፤
 ክልሉ ያለበትን የበጀት ችግር ከግምት ባስገባ ሁኔታ ወጪ ቆጣቢ በሆነ ብቻል የመንግስት
ተሸከርካሪዎች በማፈላለግ በአማራጭ እንድጠቀሙ ያደርጋል፡፡
3.2 የንዑሳን ኮሚቴዎች ተግባራትን በተመለከተ
 ንዑሳን ኮሚቴዎች ኦሬንተሸን ከተቀበሉ በኃላ በዚሁ የማስፈፀምያ ጠቋሚ ዕቅድ መሠረት
በፍጥነት ወደ ሥራ ይገባሉ፤
 በየተቋማቱ ያሉ የንብረት ትክክለኛ መረጃ በመያዝና የጋራ በማድረግ በግልፀኝነት፤
በመተማመንና በመተሳሰብ መርህ ላይ ተመስርቶ ይሰራሉ፤
 የቢሮ ፋርኒቸርም ሆነ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አገልግሎት ጊዜያቸውን ማለትም ያረጁና
አዳድስ የሆኑት ብዛት ጭምር በመለየት ይመዘግባሉ፤
 የተመዘገቡ ንብረቶችን ከየተቋማቱ የሰው ኃይል /ብዛት/ እና የተቋሙ የሥራ ክብደት
እንድሁም ስፋት አንጻር በዐቢይ ኮሚቴ ተለይቶ በተዘጋጀው ንብረት ክፍፍል መሠረት
በማየት ያከፋፍላል፤
 ለአፈፃፀም የሚያስቸግር ሁኔታ ሰያጋጥመው በቅርበት ለሚከታተለው አቢይ ኮሚቴ አካል
ያቀርባል በምሰጠውም ምላሽ ወደ ሥራ ይገባል፡፡

ተ.ቁ የሚከናወኑ ተግባራት ፈፃሚ አካል የሚፈጸምበት ምርመራ


ጊዜ
1 ለንዑሳን ኮሚቴዎች ኦሬንተሸን ዐቢይ ኮሚቴ በ 05/02/16 ዓ/ም
መስጠት አባላት
2 በዐቢይ ኮሚቴ በተዘጋጀው ንዑሳን ኮሚተዎች በ 06/02/16 ዓ/ም
ንብረት ክፍፍል መረጃ መሠረት
ሥራ መጀመር
3 በየምድባቸው ንብረቶችን ንዑሳን ኮሚቴዎች ከ 07/02/16-
የመለየትና ማከፋፈል ሥራ 08/02/16 ዓ/ም
መሥራት ድረስ
4 ተቋማት ንብረቶቹን የማጓጓዝ የክልሉ ተቋማት 09/02/2016 ዐቢይ ኮሚቴና ንዑሳን
/ማንሳት/ ተግባር ይፈፅማሉ ኮሚቴዎች ያስፈፅማሉ

ክፍል ሁለት፡-

የፈርኒቸር ዕቃዎች ክፍፍል መረጃን በተመለከተ፡-


ከቀድሞ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል በቀመር መሠረት ለአድሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላችን የደረሰው ንብረት
ስታይ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የ 15 /አሥራ አምስት/ መሥሪያ ቤቶች፤ የቢሮ ፈርኒቸር /ቁሳቁስ/ ደግሞ የ 15
/አስራ አምስት/ እንድሁም ሁለቱንም ማለትም የኤሌክትሮኒክስና የቢሮ ፈርኒቸር /ቁሳቁስ/ የደረሳቸው
መሥሪያ ቤቶች 6 /ስድስት ተቋማት/ ብቻ ሲሆኑ እነዚህም 1 ኛ/ ገቢዎች ቢሮ፤ 2 ኛ/ ፍትህ ቢሮ፤ 3 ኛ/ ሥነ
ምግባርና ፀረ ሙ/ኮሚሽን፤ 4 ኛ/ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ፤ 5 ኛ/ ሰቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቢሮ እና 6 ኛ/ ወሳኝ
ኩኔቶች ኤጀንሲ ናቸው፡፡

ከዚህ አኳያ አንድ ዓይነት ዕቃ ብቻ የደረሳቸው፤ ከሁለቱም ዓይነት ዕቃ የደረሳቸው እንድሁም ምንም ዓይነት
ዕቃ ላልደረሳቸው በተቻለ መጤን በጥንቃቄ የመለየት ሥራ ለመሥራት ጥረት ተደርጓል፡፡ ንብረቶቹን
የማከፋፈል ሥራው ከላይ መግቢያና በክፍል አንድ ላይ በተመላከተው ሁኔታ የተከፋፈለ በመሆኑ ከሥራው
አጣዳፊነት የተነሳ ሁሉም አካል በመተሳሰብ መርህ ጉድለት ባለበትም ላይ ዓይቶ በመሙላት የመፍተሔ አካል
መሆን እንዳለበትም ይጠበቃል፡፡ ንብረቶቹን የትኛው መሥሪያ ቤት ለየትኛው መሥሪያ ቤት እንደምሰጥ፤
የትኛው መሥሪያ ቤት ከየትኛው መሥሪያ ቤት እንደምቀበል ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሠንጠረዥ የተመላከተ
ሲሆን የንረቱን ዓይነትና መጤን /ብዛት/ ሙሉ መረጃ የያዘው ለብቻው በኤክስል ላይ ይገኛል፡፡

1 ኛ- የቢሮ ፈርኒቸር /ቁሳቁስ/ በሚመለከት፡

1.1 ወላይታ ሶዶ ማዕከል፡-

ተ.ቁ ሰጪ ተቀባይ ምርመራ


ፈርኒቸር (ቁሳቁስ) አካፋይ ቢሮ ፈርኒቸር (ቁሳቁስ) ተካፋይ ቢሮ
1 ርዕሰ መስተዳድር 1. ለራሱ ለርዕሰ መስተዳድር
2. ለፖሊስ ኮሚሽን
3. ለፖሊሲ ጥ/ ምርምር ኢንስቲትዩት
2 ፋይናንስ ቢሮ 1. ለራሱ ለፋይናንስ ቢሮ
2. ለፐብልክ ሰርቭስ ቢሮ
3. ለሚሊሻ ጽ/ቤት
4. ለፕላንና ልማት ቢሮ
5. ለቴ/ሙ/ት/ሥ/ቢሮ
3 ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ከራሱ ለራሱ ብቻ
1.2 አርባምንጭ ማዕከል፡-

ተ.ቁ ሰጪ ተቀባይ ምርመራ


ፈርኒቸር (ቁሳቁስ) አካፋይ ቢሮ ፈርኒቸር (ቁሳቁስ) ተካፋይ ቢሮ
1 ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ 1. ለራሱ ለሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ
2. ለዋና ኦዲተር
2 ስነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን 1. ለራሱ ለስነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን

2. ለከተማ ልማት ቢሮ
3 ገቢዎች ቢሮ 1. ለራሱ ለገቢዎች ቢሮ
2. ለሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተር/ ልማት ቢሮ
3. ለንግድና ገበያ ልማት ቢሮ
4 የኮንስትራክሽን ባለስልጣን 1. ለራሱ ለኮንስትራክሽን ባለስልጣን
2. ለክልል ምክር ቤት
3. ለኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

1.3 ሳውላ ማዕከል፡-

ተ.ቁ ሰጪ ተቀባይ ምርመራ


ፈርኒቸር (ቁሳቁስ) አካፋይ ቢሮ ፈርኒቸር (ቁሳቁስ) ተካፋይ ቢሮ
1 የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ 1. ለራሱ ለሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ
2. ለፍትህ አካላት ሥልጠና ማዕከል
3. ለማረሚያ ኮሚሽን
1.4 ዲላ ማዕከል፡-

ተ.ቁ ሰጪ ተቀባይ
ፈርኒቸር (ቁሳቁስ) አካፋይ ቢሮ ፈርኒቸር (ቁሳቁስ) ተካፋይ ቢሮ ምርመራ
1 ህብረት ስራ ልማት ኤጀንሲ 1. ለራሱ ለህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ
2. ለቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን
2 መንግሥት ኮምንኬሽን ቢሮ (ወንበር 1. ለራሱ ለመንግስት ኮምንኬሽን ቢሮ ከወንበር በቀር
ብቻ) 2. ለትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የጎደላቸዉን
3. ለውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ
ከፋይናንስና ከርዕሰ

መስተዳደር ያገኛሉ፡፡
3 ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1. ለራሱ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት
2. ለክልሉ መንገዶች ባለስልጣን
3. ለግብርና ቢሮ

1.5 ጂንካ ማዕከል፡

ተ.ቁ ሰጪ ተቀባይ ምርመራ


ፈርኒቸር (ቁሳቁስ) አካፋይ ቢሮ ፈርኒቸር (ቁሳቁስ) ተካፋይ ቢሮ
1 ፍትህ ቢሮ 1. ለራሱ ለፍትህ ቢሮ
2. ለጤና ቢሮ
2 ትምህርት ቢሮ 1. ለራሱ ለትምህርት ቢሮ
2. ለወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
3. ለሠራተኛና ማህበራዊ ጉ/ቢሮ
3 ኢንቨስትመንትና ኢንድስትሪ ልማት 1. ለራሱ ለኢንቨስትመንትና ኢ/ሪ ልማት ቢሮ
ቢሮ 2. ለመስኖ ተቋማት ልማትና አስ/ ኤጀንሲ
3. ለአርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ
1.6 ካራት ማዕከል፡

ተ.ቁ ሰጪ ተቀባይ ምርመራ


ፈርኒቸር (ቁሳቁስ) አካፋይ ቢሮ ፈርኒቸር (ቁሳቁስ) ተካፋይ ቢሮ
1 የወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ 1. ለራሱ ለወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ የጎደላቸዉን
2. ለሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ፈርኒቸር
3. ለብሔረሰቦች ም/ቤት ከፋይናንስ
4. ለባህልና ቱሪዝም ቢሮ ቢሮ ይቀበላሉ

2 ኛ/ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በተመለከተ፡-

2.1 አርባምንጭ ማዕከል፡

ተ.ቀ ሰጪ (አካፋይ) ተቀባይ (ተካፋይ) ምርመራ


1 ከተማ ልማት ቢሮ 1. ለራሱ ለከተማ ልማት
ቢሮ
2. ለሥራ ዕድል ፈጠራና
ኢን/ ልማት ቢሮ
3. ለሙያ ብቃት ማረጋገጫ
ኤጀንሲ
4. ለኢንዱስትሪ ልማት
5. ለክልል ምክር ቤት
2 ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ 1. ሠራተኛና ማህበራዊ
ጉ/ቢሮ ለራሱ ብቻ
2. ፕላንና ልማት ቢሮ
3 ገቢዎች ቢሮ 1. ለራሱ ለገቢዎች ቢሮ
2. ለዋና ኦዲተር
3. ለም/ርዕሰ መስተደድር
ጽ/ቤት
2.2 ካራት ማዕከል፡

ተ.ቀ ሰጪ (አካፋይ) ተቀባይ (ተካፋይ) ምርመራ


1 ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ 1. ለራሱ ለሳይንስና
ቢሮ ኢንፎርሜሽን ቴክ/ ቢሮ
2. ለባህልና ቱሪዝም ቢሮ
3. ለብሔረሰቦች ም/ቤት

2.3 ሳዉላ ማዕከል፡

ተ.ቀ ሰጪ (አካፋይ) ተቀባይ (ተካፋይ) ምርመራ


1 ፍትህ ቢሮ 1. ለራሱ ለፍትህ ቢሮ
2. ለማረሚያ ኮሚሽን
3. ለፍትህ አካላት ሥ/ ማዕከል
4. ለጠቅላይ ፍ/ቤት

2.4 ወላይታ ሶዶ ማዕከል፡

ተ.ቀ ሰጪ (አካፋይ) ተቀባይ (ተካፋይ) ምርመራ


1 ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ 1. ለራሱ ለወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ
2. ለመንግስት ኮምንኬሽን ቢሮ
3. ለፖሊሲ ጥናትና ምርምር
ኢንስቲትዩት
2 ሰላምና ፀጥታ 1. ለራሱ ለሰላምና ፀጥታ ቢሮ
2. ለፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ
3. ለፖሊስ ኮሚሽን
3 ቴክኒክና ሙ/ሥ/ቢሮ 1. ለራሱ ለቴክኒክና ሙያ ሥ/ቢሮ
2. ለርዕሰ መስ/ጽ/ቤት
3. ለሚሊሻ ጽ/ቤት
4. ለኢንቨስትመንት ቢሮ
4 ሥነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና 1. ለራሱ ለሥ/ፀ/ ሙስና ኮሚሽን
ኮሚሽን 2. ለፋይናንስ ቢሮ

2.5 ዲላ ማዕከል፡

ተ.ቀ ሰጪ (አካፋይ) ተቀባይ (ተካፋይ) ምርመራ


1 የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ 1. ለራሱ ለሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ
2. ለትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
3. ለክልሉ መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት
2 ከቡና ቅ/ቅ/ባለስልጣን 1. ለራሱ ለቡናና ቅመማ ቅ/ባለስልጣን
2. ለህብረት ስራ ልማት ኤጀንሲ
3 የውሃ መስኖና ማዕድን ልማት 1. ለራሱ ለውሃና ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ
ቢሮ 2. ለግብርና ቢሮ
3. ለደንና አካባቢ ጥበቃ

2.6 ጂንካ ማዕከል፡

ተ.ቀ ሰጪ (አካፋይ) ተቀባይ (ተካፋይ) ምርመራ


1 አርብቶ አደር ጉዳዮች 1. ለራሱ ለአርብቶ አደር ጉዳዮች
ማስተባበሪያ ቢሮ ማስተባበሪያ ቢሮ
2. ለትምህርት ቢሮ
2 ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ 1. ለራሱ ለንግድና ገ/ ልማት ቢሮ
2. ለጤና ቢሮ
3 የመስኖ ተቋማት ልማትና 1. ለራሱ ለመስኖ ተቋማት ልማትና
አስተዳደር ኤጀንሲ አስተዳደር ኤጀንሲ
2. ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች፡-

1. የመረጃ አለመጣጣም
2. የቅንጅት ጉድለት
3. የተመዘገበዉ ንብረት በአካል ላይገኝ ይችላል
4. የንብረት ደህንነት
5. የተመደበላቸዉ ተቋማት በጊዜ አለማንሳት

መፍትሔዎች፡-

1. ከንብረት ክፍል ባለሙያዎች ጋር በቅርበት መሥራትና መረጃዎችን ማጥራት


2. ከፕሮጀክት ጽ/ቤት እና የአራቱም ክልል የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተቀራርቦ መሥራት
3. ንብረቶቹን በባለሙያ ማስፈተሽና የጸጥታ ጥበቃ ማጠናከር
4. ንብረቱን ለማንቀሳቀስ ከፕሮጀክት ጽ/ቤት ህጋዊ ደብዳቤ መያዝ

ማሳሰቢያ፡-

 በንብረት ክፍፍሉ ስማቸው ያተጠቀሱት መሥሪያ ቤቶች ተጠሪ ከሆኑበት እናት ቢሮ የምጋሩ ይሆናሉ፡፡
 ላብቶፕና ታብሌት ንብረቶች በግለሰቦች እጅ ያሉ በመሆኑ ሰብስቦ ለማከፋፈል አስቸጋሪ ሆኖ በመገኘቱ
ተቋማት በሠራተኞቻቸው እጅ ያሉትን በንብረትነት መዝግቦ ሥራ ላይ ያውላል፡፡

3 ኛ/ ዝርዝር የንብረት ክፍፍሉን በዓይነትና መጠን የያዘው መረጃ በተመለከተ በኤክሰል ላይ


መመልከት ይቻላል፡፡

ቁጥር…………………….

ቀን……………………….

ለ-----------------------ቢሮ /ኤጀንሲ /ኢንስቲትዩት /ባለስልጣን/ ኮሚሽን

በያሉበት፡-

ጉዳዩ፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የንብረት ድልድል ስለመላክ ይሆናል፡፡

የቀድሞ ደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት አካል የነበሩ አራቱ ክልሎች በጋራ ያፈሯቸውን ንብረቶች ከፌዴራልና ከአራቱም
ክልሎች በተወጣጣ የተቋቋመ ኮሚቴ የንብረት ድልድል ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
በዚህ መሰረት በተዋቀረው ኮሚቴ በተቋማቱ የስራ ስፋት፣ የተመደበ የሰው ኃይል ብዛት እና የስራ ክብደት እንድሁም
ያላቸው ልዩ የሥራ ባህሪ ታሳቢ በማድረግ ለክልላችን የደረሰውን ንብረት ማለትም ፈርኒቸርና የኢሌክትሮኒክስ እቃዎች
በክልላችን ለተዋቀሩ ሁሉም ቢሮዎች እንድሁም አንዳንድ ተጠሪ ተቋማት መልሶ በመደልደል በተቻለ መጠን ለሁሉም
የማዳረስ ሥራ ተሰርቷል፡፡

በመሆኑም የንብረት ድልድሉን የያዘ -------- ገጽ በዚህ ደብዳቤ ሸኚነት የላክን መሆኑን እየገለጽን ቢሮዎቹም በድልድሉ
ውስጥ ላልተካተቱና በሥራቸው ለተደራጁ ተጠሪ ተቋማት ከደረሳቸው ድርሻ ውስጣዊ የንብረት ድልድል እንዲያደርጉ
ጭምር እናሳስባለን፡፡

// ከሰላምታ ጋር//

ግልባጭ፡-

 ለክቡር ርዕሰ መስተዳድር


 ለርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ
 ለርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ
ወላይታ ሶዶ፡

You might also like