You are on page 1of 2

ክ/ከተማ ------------------------------------ ቦሌ ከ/ክተማ

ወረዳ ------------------------------------ 17

ቀበሌ ------------------------------------- 24

ጥናቱ የሚያካትታቸው ቤቶች ---------------የፍሳሽ መስመራቸው ከቤት ቁጥር 1314 እና 1323 የተገናኘ

መግቢያ
ከላይ የተጠቀሱት ከቤት ቁጥር 1314 ጀምሮ እስከ ቤት ቁጥር 1323 ያሉ የኮርፖሬሽናችን ይዞታ የሆኑ ቤቶች የፍሳሽ
መስመር ከብዙ ቤቶች የተናኘ ከመሆኑም በላይ ካሉበት ቦታ አቀማመጥ የተነሳ የሁሉም ቤቶች የፍሳሽ ቆሻሻ ተሰባስቦ
ከነዚህ ቤቶች ጀርባ ባሉ ሴፕቲክ ታንከሮች ይሰባሰባል፡፡ ከነዚህ ቤቶች ጀርባ ካሉ ሴፕቲክ ታንከሮች መካከል ሁለቱ
የፈረሱ ከመሆናቸውም በላይ ቀሪዎቹም ሴፕቲክ ታንከሮች ከአገልግሎት ዘመን ብዛት የተነሳ ተጨማሪ የፍሳሽ ጫና
ተቀብለው አገልግሎት የማይሰጡ እና ሁልግዜም የጽዳት እና ክትትል ስራ የሚፈልጉ ናቸው፡፡

ነባራዊ ሁኔታ
ከላይ የተገለጹት መኖሪያ ቤቶች የፍሳሽ መስመር ሴፕቲክ ታንከሮች አሁን ባለው እና ቤቶቹ ካሉበት የመሬት
አቀማመጥ የተነሳ ከሌሎች ቤቶች የሚመነጭ የፍሳሽ ቆሻሻ መሸከም የማይችሉበት ሁኔታ የደረሱ ሲሆን በተጨማሪም
ሁለት የፈረሱ ሴፕቲክ ታንከሮች መፍትሄ የሚፈልጉ ናቸው፡፡
በዚህ ስራ ላይ የተካተቱ መኖሪ ቤቶች ዝርዝር (የቤት ቁጥር)

1. ከቤት ቁጥር 1314 እስከ ቤት ቁጥር 1323 የ 10 ቤቶች

የቀረቡ ምፍትሄዎች
መፍትሄዎቹን በሁለት ከፍለን ማለትም የአጭር ግዜና እና ዘላቂ መፍትሄ ብለን ከፋፍለን እናያለን፡፡
1. የአጭር ግዜ መፍትሄ፡- ከላይ እንደተገለጸው በዚህ ደብዳቤ ላይ የተጠቀሱት ቤቶችን የፍሳሽ መስመር ቀድሞ
የተገናኙበትን የፍሳሽ መስመር ሙሉ በሙሉ በማቋረጥ በዚሁ አመት ከሰራነው የፍሳሽ መስመር ጋር ማገናኘት
እና የፈረሱትን ሴፕቲክ ታንከሮች የፍሳሽ ቆሻሻ በሙሉ በማስወገድ ሴፕቲክ ታንከሮቹን በአፈር መሙላት፡፡
2. ዘላቂ መፍትሄ፡- ከጊዜያዊው መፍትሄ ጎን ለጎን ከአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር በመነጋገር
የአካባቢውን ቤቶች የፍሳሽ መስመር ለአካባቢው በቅርበት ከሚገኝ የከተማው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ጋር
ማገናኘት፡፡ የዚህንም ጉዳይ ተፈጻሚነት ባለው አሰራር መሰረት የቅ/ጽቤታችን በሃላፊነት ክትትል ማድረግ
ይኖርበታል፡፡

ማጠቃለያ፡-
 ከጽቤታችን የሚጠበቅ
 ከላይ ለተገለጹት ስራዎች የሚያስፈልገውን ዲዛይን ፣ሰራ ዝርዝር እና የበጀት ግምት እና የስራ እቅድ
አዘጋጅቶ ማቅረብ
 በመጸዳጃ ፍሳሽ መስመር ስራ ላይ ከላይ በዝርዝር የተገለጹት የኮርፖሬሽናችን ቤት ነዋሪዎች ተሳታፊ
እንዲሆኑ ማስተባበር፡፡
 ከወረዳ 05 ጋር በመሆን የመንገድ ፍሳሽ ማስወገጃ መስመር እና ሴፕቲክ ታነክ ግንባታ ስራ ላይ
በወጪ መጋራት አሰራር ላይ የወረዳ 05 አስተዳደር እና የአካባቢው ነዋሪ ተሳተፊ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
 በዘላቂነት የአካባቢው አጠቃላይ የፍሳሽ ችግር ሊፈታ የሚችለው የየቤቶቹን ፍሳሽ መስመር
ከከተማው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ጋር እንዲገናኝ ክፍተኛ ትኩረት በመስጠት መስራት፡፡
 ከወረዳ 05 አስተዳደር የሚጠበቀው
 የቅ/ ጽቤታችንን ጥረት በበጎ በመረዳት በራስ አቅምም ሆነ ነዋሪው ህብረተሰብን በማስተባበር
የመፍትሄው አካል መሆን፡፡

1
 በመጸዳጃ ፍሳሽ መስመር ስራ ላይ የሚመለከታቸው ካላይ የተጠቀሱት ነዋሪዎች በወጪ መጋራቱ
አነዲሳተፉ ማስተባበር
 የተከራይ ደንበኞቻችን ድርሻ ፡-
 አሁን በቅ/ጽቤታችን የታቀደው በዋናነት ደንበኞቻችንን በተገቢው ለማገልገል እና አካባቢያቸውንም
የበለጠ ለመኖሪያነት ምቹ ለማድረግ ከመሆኑ እንጻር ከማንም በላይ በሃላፊነት በመነሳት ሌሎች
የአካባቢዎቻቸው መሰል ተከራየች እንደሚያደርጉት ለስራው የሚያስፈልገውን በጀት በማዋጣት
መደገፍ ይኖርባቸውል፡፡
 ተያያዥ መረጃዎች
-በዝርዝረ የተገለጹት ቤቶች ጂ.አይ.ኤስ ማፕ እና ከማንሆል እስከ ነባሩ ሴፕቲክ ታንክ ያለው ማፕ
-ለስራው የሚያስፈልግ የስራ ዝርዝር እና ዲዛይን
የስራ ዝርዝሩየሚጠቃልላቸው ስራዎች፡-

 የሳይት ክሊሪንግ ስራዎች


 የፈረሱት ሴፕቲንክ ታንከሮች ውስጥ የሚገኝ ፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገድ
 የፈረሱትን ሴፐፕቲክ ታንከሮች በአፈር መሙላት
 የማንሆል ስራዎች
 40 ሜትር የባለ 40 ቱቦ ቀበራ

You might also like