You are on page 1of 15

የ 2014 ዓ.

ም በጀት ዓመት የኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ዘርፍ የ 1 ኛ


ሩብት አመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

ስትራቴጂካዊ ግብ 1:- የሀገራዊ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ስፓሻል ማስተር ፕላንን መሰረት ባደረገ መልኩ
የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ልማት ማፋጠን፤
1.1 በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያልተጠናቀቁ ግንባታዎችን ማጠናቀቅ

በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ላይ በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የማስተካከያ ስራዎችን
ለማከናወን በዝርዝር ተግባር ታቅዶ የነበረ ሲሆን አፈጻጸማቸው እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የውሃና ፍሳሽ ማጣሪያ ሲቪል ስራዎች የተጠናቀቁ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሮ
ሜካኒካል ገጠማ ስራ ለማከናወን የሚያስችል እቃዎች ጅቡቲ ወደብ ደርሰው ከቀረጥ ነጻ ጋር በተያያዘ ያሉ መፈታት
ያለባቸው ጉዳዮች በመኖራቸው እቃዎቹን ወደ ፕሮጀክቱ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በአሁን
ወቅት አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም 96.61% ላይ ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በክረምት ወራት ውስጥ ነሐሴ 24
በነበረው ከባድ የሆነ አውሎ ንፋስ ምክንያት የተወሠኑ ሥራዎች የተጐዱ ስለሆነ ሥራተቋራጩ እንዲያስተካከል
በአማካሪው በኩል ትዕዛዝ እንዲደርሰው ተደርጓል፡፡

በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የፍሳሽና ውሃ ማጣሪያዎች የእርማትና ማስተካከያ እንዲሁም የአጠቃላይ የፓርኩን
ደህንነት በተሟላ ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል የ CCTV እና ተያያዥ ስራዎች በዚህ በጀት አመት መከናወን ሚገባቸው
ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት የ CCTV ና ተያያዥ የማስተካከያ ስራዎች ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው የርክክብ ሂደቱ
ተፈጻሚ ሆኗል፡፡ የፍሳሽ ማጣሪያ (ZLD) ማስተካከያ ስራዎችን በተመለከተ አማካሪውንና ስራ ተቋራጩን ያካተተ
የፍሳሽ ማጣሪያ ውጤታማነት እንዲከታተል በተቋቋመው ቡድን አማካኝነት ቀደም ሲል የተያዙ ስራዎች ኮንትራቱ
በሚፈቅደው አግባብ መሰረት የማስተካከያ ስራዎቹ ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል፡፡ ይሁንና ከቀረጥ ነጻ የሚገቡ
እቃዎች ጋር በተያያዘ የማስተካከያ ስራዎች ላይ ተጽኖ አሳድሯል፡፡ የውሃ ማጣሪያውን በተመለከተ የኦፕሬሽንና ጥገና
ሥራዎችንና የመጨረሻ ርክክብ ለማድረግ እንዲቻል ከኮርፖሬሽኑ ባለሙያዎች የተውጣጣ የቴክኒክ ኮሚቴ በማዋቀር
የግምገማ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርከ ከፍሳሽ ማጣሪያ ፣ Electric Fence & CCTV ካሜራ ገጠማ፣ የጎርፍ መከላከያ እና ተያያዥ
በአጭር ጊዜ ውስጥ መጠናቀቅ የሚገባቸው እንዲሁም የማስተካከያ እና የእርማት ስራ የሚያስፈልጋቸው ስራዎች
በስራ ተቋራጩ ደካማ አፈፃፀም የተጓተቱበት ሁኔታ በመኖሩ ይህንን በተመለከተ የኮርፖሬሽኑ በላይ አመራር
በተገኘበት በፕሮጀክቱ የመስክ ጉብኝት እና የፕሮጀክቱ ስራዎች የደረሱበት ደረጃ ጥልቅ ግምገማና አቅጣጫ
ተቀምጧል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከአማካሪው ጋር በጥልቀት በተደረገ ውይይት ቀሪ ስራዎቹን ከማጠናቀቅ አንፃር
በሥራ ተቋራጩ የሚጠናቀቁና በሌላ ተቋራጭም ሊሠሩ ይችላሉ ተብለው በተለዩት ስራዎች ላይ የጋራ ውይይት
በማድረግ መግባባት ላይ ተደርሶ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ በመሆኑም በአማካሪው በኩል መጠናቀቅ የሚገባቸው ስራዎችን
በተመለከተ ውስን የሆነ የጊዜ ገደብ ተሰቶት እንዲጠናቀቅ በአማካሪው በኩል ማሳሰቢያ እንዲሰጥ ውሳኔ ተላልፏል፡፡
በአጠቃላይ በሩብ ዓመቱ ከማስተካከያ ሥራዎች ውስጥ 29% ለማከናወን ታቅዶ 20% ተከናውኗል፡፡ አፈፃፀሙ ሲታይ
69% ይሆናል፡፡

የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተመለከተ የ CCTV ገጠማና የአስፋልት መንገድ ማስተካከያ እንዲሁም የጊዜያዊ ውሃ
አቅርቦት ግንባታ ስራዎች በፕሮጀክቱ በበጀት አመቱ ትኩረት ተሰጥቶ ክትትል ከሚደረግባቸው ስራዎች በዋናነት

1
የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት ከፕሮጀክቱ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ የኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራር በፕሮጀክቱ
በመገኘት አፈጻጸሙ የተገመገመ ሲሆን ከጉብኝቱ ለመረዳት እንደተቻለው ስራ ተቋራጩ የተጠቀሱትን ስራዎች
ለማከናወን የሚያስችል የቅንጅት ማነስ በከፍተኛ ሁኔታ መኖሩ ታይቷል፡፡ ከአስፓልት የማስተካከያ ስራውና የዘላቂ
ውሃ አቅርቦት ግንባታ ጋር ተያይዞ ስራዎቹ እጅግ በጣም የዘገዩ በመሆኑ እነዚህ ሁኔታዎች ተስተካክለው ስራው
መፋጠን እንዲችል አጠቃላይ የፕሮጀክት ማኔጅመንቱ ስራ ተቋራጩና የአማካሪ ድርጅቱ ተወካዮች የማስተካከያ
እርምጃ እንዲወስዱ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ በቀጣይም ስራው የሚፋጠንበት ሁኔታ እንዳስፈላጊነቱ መሻሻል የማያሳይ
ከሆነ ውል እስከማቋረጥ የሚደርስ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ በፕሮጀክቱ የማስተካከያ ሥራዎችን በተመለከተ በሩብ
ዓመቱ 8% ታቅዶ የነበረ ሲሆን በዕቅዱ መሰረት ተከናውኗል፡፡

የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ የጎርፍ መከላከያ ስራን በተመለከተ ዘላቂ መፍትሄ ለማስቀመጥ በስራ ተቋራጩ፤
አማካሪ ድርጅቱ እንዲሁም የኢትዮጵያ የመንገዶች ባለስልጣን አማካሪ ከሆነው ኤቢኤም አማካሪ ድርጅት ጋር
በደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ ሰፊ ውይይትና የሳይት ጉብኝት የተደረገ ሲሆን በውይይቱ መሰረት ስራ ተቋራጩ
የቁፋሮ ስራውን ያጠናቀቁ ቢሆንም የጐርፍ መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ የማስተካከያ ሥራዎችንና ሌሎች ተጨማሪ
ግንባታ የሚያስፈልጋቸውን ዲዛይን እንዲያዘጋጅ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

በባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ አብዛኛው የግንባታ ሥራዎች በስራ በዕቅዱ መሠረት የተከናወኑና የተሻለ አፈፃፀም
ያለው ፓርክ ሲሆን በሩብ ዓመቱ የአንድ ማዕከል አገለግሎት ህንፃ በአጥር እንዲከለል በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት
የአጥር ግንባው ተጠናቋል፡፡ እንዲሁም ከ CCTV እና የዋና መንገዶች ግንባታ ጋር የተያያዙ መጠነኛ የእርማትና
የማስተካከያ ሥራዎች ተጠናቅቀዋል፡፡

በቦሌ ለሚ ምዕራፍ ሁለት እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በተመለከተ በፓርኮቹ ያልተጠናቀቁ የግንባታና
ከመሰረተ ልማት ጋር የተያያዙ ስራዎች በጋራ ተለይተው ክትትል እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡ በዚህም የመንገድና
ተያያዥ የማስተካከያ ስራዎች እንዲሁም የምድረ ግቢና የጥበቃ ቤቶች፤ የፍሳሽ መስመሮች ማስተካከል ስራዎችን
በተመለከተ ከሲቪል ስራዎች ማስተካከያ አንፃር በሩብ አመቱ መጠናቀቅ የነበረባቸው ሲሆን በቦሌ ለሚ 53.3%
እንዲሁም በቂሊንጦ 83.3% ተከናውኗል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በሁለቱ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የፍሣሽ ማጣሪያን
በተመለከተ ምንም አይነት የማዘጋጃ ቤታዊና የኢንዱስትሪ ፍሣሽ ባለመኖሩ ምክንያት የፍተሻና ሙከራ ስራው
የሚዘገይ ይሆናል፡፡ ይህንን ለመፍታት እንዲቻል ከአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ጋር የተጀመረውን የጋራ
መግባቢያ ስምምነት ማጠናቀቅ ትኩረት የሚፈልግ ስራ ሆኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኤሌክትሪክ መስመርና ዕቃዎች
እንዲሁም የውሃ መስመርና ፓምፕ ስቴሽኖችን በተመለከተ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ዘላቂ ኤሌክትሪክ ሃይል ያልተገናኘ
በመሆኑ የርክክብ ሂደቱ በአሁኑ ወቅት ማከናወን የማይቻል በመሆኑ በቀጣይ የሚታይ ይሆናል፡፡

በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ቀደም ሲል የተጀመሩ የግንባታ ሥራዎችን ማጠናቀቅን በተመለከተ
በአጠቃላይ በሩብ ዓመቱ 5% ለማከናወን ታቅዶ 2.87% ተፈጽሟል፡፡ አጠቃላይ አፈፃፀሙ ሲታይ በአማካይ 57.4%
ነው፡፡ ከተያዙት የግንባታ ዕቅዶች መካከል የፓርኩን ወሰን ለማስከበር የሚያስችል አጥር ለመገንባት ከይገባኛል ነፃ
በሆኑ ቦታዎች ላይ 2.7 ኪ.ሜ አጥር እና 20 የሚደርሱ ጥበቃ ማማዎች እንዲገነቡ በተደርጓል፡፡ በፓርኩ ውስጥ
በተለያዩ ሥራተቋራጮች የተገነቡ የተገጣጣሚ ህንፃ፣ የቀድሞ MCIT ህንፃ እንዲሁም የኢንኩቤሽን ህንፃዎች
በአብዛኛው የተጠናቀቁ በመሆኑ የኮንትራት አስተዳደር ሂደታቸውን በመመልከትና የኮርፖሬሽኑን ጥቅም በማስከበር
ታይቶ ርክክብ ለመፈፀም የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ ሌሎች ግንባታዎች በተመለከተ

2
የአስተዳደር ህንፃ፣ ዳታ ሴንተር፣ ላንድስኬፒንግ፣ የመንገድ ግንባታ ወዘተ… ሥራዎችን በተመለከተ ሥራ ተቋራጮች
ያላጠናቀቋቸውን በመለየትና በራስ ኃይል የሚሠሩትን ተመጣጣኝ ገንዘብ በመቀነስ የርክክብ ሥራዎች እንዲከናወኑ
አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ በአጠቃላይ በፓርኩ ውስጥ የተጀመሩ ግንባታዎች ቀደም ሲል ፓርኩ ወደ ኮርፖሬሽኑ
ከመቀላቀሉ በፊት የተጀመሩ ስራዎች በመሆናቸውና የኮንትራት ሂደታቸው ውስብስብ በመሆኑ ይህንኑ አጣርቶ
ፕሮጀክቶቻቸን የመዝጋት ሥራ እንዲከናወን ለማድረግ በአማካሪዎች በኩል የማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎች ለሥራ
ተቋራጮች እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡

1.5 የኢንዱስትሪ ፓርኮች መሬት ዝግጅትና ካሣ ክፍያ


ከመሬት ዝግጅትና ማስጠበቅ ጋር በተያያዘ የ 6 ኢንዱስትሪ ፓርኮች የጊዜያዊ አጥር ግንባታ ማከናወን አስፈላጊ ሆኖ
በመገኘቱ የሥራ ተቋራጭ ግዥ እንዲፈፀም የፍላጎት መግለጫ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡ በተጨማሪም የቦሌ ለሚ ምዕራፍ
አንድ አጥር ግንባታ ስራ በይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ያልታጠረ ቦታ ሳይት በመሄድ X, Y Coordinate መረጃ ተሰብስቦ
በፕላን የማመላከት ስራ ተሰርቷል፡፡ በዚህ መሰረት የአጥር ስራ ለማስቀጠል ካሳ ክፍያ የተፈፀመበትን መረጃ ተጣርቶ
እንዲቀርብ ለለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ተጠይቆ ክትትል እየተደረገ ነው፡፡

ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተለዋጭ 7.5 ሄ.ር መሬት ላይ የልማት ተነሺዎች መረጃ
እንዲሰበሰብ ተደርጓል፡፡ የመሰረተ ልማት መስመር ዝርጋታ የሚያልፍባቸው ቦታዎችን ወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ
ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የኤሌክትሪክ ሀይል ማሰራጫ ጣቢያ ይዞታ ውስጥ ያሉ ቤቶች ካሳ ክፍያ በተመለከተ
በድጋሚ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት ከክፍለ ከተማው ጋር ተነጋግረው ክፍያ እንዲፈፅሙ በደብዳቤ
ባሳወቅናቸው መሰረት ክትትል ቢደረግም እስከ አሁን ድረስ ክፍያ ባለመፈፀሙ ምክንያት የአካባቢ ነዋሪዎች
ተደጋጋሚ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

የመሰረተ ልማት መስመር ዝርጋታ የሚያልፍባቸው ቦታዎችን ወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ ቦሌ ለሚ ኢ /ፓርክ
የኤሌክትሪክ ሀይል ማሰራጫ ጣቢያ ይዞታ ውስጥ ያሉ ቤቶች ካሳ ክፍያ በተመለከተ ጉዳዩ በድጋሚ በመነሳቱ
ምክንያት ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በክፍለ ከተማው ጋር ተነጋግረው ክፍያ እንዲፈፅሙ በደብዳቤ በበላይ
ሀላፊዎች በኩል እንዲታይ እና ውሳኔ ሀሳብ እንዲሰጥበት ክትትል እየተደረገ ነው፡፡ የቦሌ ለሚ ምዕራፍ አንድ የውሀ
መስመር ዝርጋታ ውስጥ እስከ 600 ሜትር ካሳ ክፍያ እንዲፈጸም ለገንዘብ ሚኒስቴር በተጠየቀው መሰረት ብር
17,562,030.00 ተፈቅዶ ክፍያው ለቦሌ ክፍለ ከተማ በአካውንታቸው ገቢ የተደረገ ቢሆንም በከተማው አስተዳደር
ውሳኔ ለጊዜው መሬት ነክ አገልግሎት ስራ የተቋረጠ በመሆኑ ገቢ የተደረገው የካሳ ክፍያ ገንዘብ ለተነሺዎች መፈፀም
እንደማይቻል አሣውቀዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተቋረጠው አገልግሎት ተጀምሮ ለተነሺዎች የካሳ ክፍያው እስኪከፈላቸው
ድረስ የመስመር ዝርጋታውን ስራ ጎን ለጎን ለማከናወን እንድንችል ተነሺዎችን የማሳመን ስራ በትብብር እንዲሰራ
በተጠየቀው መሰረት ተነሺዎችን የማሳመን ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በተጨማሪ ከቦሌ ለሚ ዘላቂ የኤሌክትሪክ
መስመር ዝርጋታ በጥናት ከተለየው 1.5 ኪ.ሜ ውስጥ ከይዞታችን ውጪ የሚገኘው ይገባኛል ጥያቄ ያለበት 500
ሜትር የሚሆን ቦታን በተመለከተ መስመሩ ይዞታቸውን የሚነካባቸው አርሶ አደሮች ሙሉ በሙሉ ይዞታቸው
እንዲለካላቸው እና ካሳ እንዲከፈላቸው በሚል ጥያቄ ባቀረቡት መሰረት ከመስመሩ ውጭ ያለውን መከፈል ያለበትን
የሚል ጥያቄ ቀርቦ ክፍለ ከተማው በድጋሚ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ለማድረግና የማሳመን ስራ ለመስራት በሂደት
ላይ ይገኛል፡፡

1.6 .1 በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለግል ኢንዱስትሪ ፓርክ አልሚና ኢንተርፕራይዞች ቦታ በማጥናት ርክክብ መፈፀም፤

3
ኮርፖሬሽኑ ባለማቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በማስተር ፕላኑና ሽንሻኖ ጥናቱ መሰረት የለማ መሬት ለባለሀብቶች ለመመደብ
እንዲቻል በሩብ ዓመቱ ለ 3 ባለሀብቶች ቦታ ለመመደብ በዕቅድ ተይዞ በአይ ሲ ቲ ፓርክ ለ 1 ባለሀብት ቦታ የመመደብ ስራ ተከናወነ
ሲሆን ይህም 33.33% አፈፃፀም አሳይቷል፡፡ በተጨማሪም ለፓርኩ በዘላቂነት የሚያገለግል 230 KV ሀይል ማከፋፈያ ጣቢያ የሚሆን
6 ሄክታር ቦታ በጥናት በመለየት በፕላን ፎርማት ተዘጋጅቶ ወደ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በደብዳቤ ተልኳል፡፡ የቦታ ዝግጅቱ አፈፃፀም
አነስተኛ የሆነበት ምክንያት በሚፈለገው ደረጃ ቦታ የተፈቀደላቸው ባለሀብቶች ባለመምጣታቸው ነው፡፡

16.2 በኢንዱስትሪ ፓርኮች ቦታ ርክክብ ለተደረገላቸው ባለሐብቶች የግንባታ ፈቃድ መሥጠት፤

በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተጠኑ ቦታዎች ላይ ቦታ የተመደበላቸውና ርክክብ የፈፀሙ ባለሐብቶችን በተመለከተ በሩብ ዓመቱ ለ 2
ባለሐብቶች ግንባታ ፈቃድ ለመስጠት በታቀደው መሠረት ለ 3 ባለሐብቶች የግንባታ ፈቃድ ተሠጥቷል፡፡ ለግንባታ ፈቃድ የቀረቡ
ባለሐብቶች ብዛት ከእቅዱ አንፃር ሲታይ የበለጠ የሆነበት ምክንያት ባለፈው በጀት ዓመት ቦታ የወሰዱ ባለሐብቶች ዲዛይን አዘጋጅተው
ያቀረቡት በያዝነው በጀት ዓመት ውስጥ በመሆኑ ነው፡፡

1.8 በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ መሠረት ልማት ማሟላት


1.8.1 ጊዜያዊ የኤሌክትሪክ ሀይል ማቅረብ

በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የገባው ካርቪኮ የተባለው የግል አልሚ ተጨማሪ 16 ሜጋዋት ጊዜያዊ
የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ በባለፈው የበጀት ዓመት 40% የኃይል አቅርቦት ስራው የተከናወነ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ
የኮንክሪት ፖል ሳይት ደርሷል፡፡ በባለሃበቱ በኩል ከውጭ አገር ግዥ ተፈፅሞ የሚቀርቡ የ top pole accessories ሳይት
ላይ ደርሰው ርክክብ ለማከናወን ባለሃበቱ ለኢትዮጵያ ኤልክትሪክ አገልግሎት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ አዲስ ስራ ተቋራጭ
ተቀጥሮ ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ የ Check survey፣ 274 የኮንክሪት ፖል ጉድጓድ ቁፋሮ እና 144 የኮንክሪት ፖል
ተከላ ተከናውኗል፡፡ በመጀመሪያው ሩብ በጀት ዓመት 25% ክንውን እንዲኖረው ታቅዶ 22% ተከናውኗል፡፡
አፈፃፀሙም 88% ነው፡፡ ለአፈፃፀሙ ማነስ ዋነኛ ምክንያት የኮንክሪት ፖል ተከላ ለመከናወን የሲሚንቶ አቅርቦት
ዕጥረት መኖሩ ነው፡፡

በቦሌ ለሚ II ኢንዱስትሪ ፓርክ ዘላቂ የኤሌክትሪክ ኃይል እስኪሟላ ድረስ ሻንግቴክስ ለተባለ የግል ባለሀብት 1.2
ሜጋዋት ጊዜያዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 927,749.36 የዋጋ ግምት ቀርቦ
ክፍያው ተከናውኗል፤በባለሀብቱ የቀረበው ትራንስፎርመር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል ፍተሻ ስራ
ተከናውኖ መስመሩ ኢነርጃይዝ ሆኗል፡፡ ለባለሀብቱም በጥቅምት ወር የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቀርብ የታቀደ ቢሆንም
ከታቀደበት ጊዜ አስቀድሞ የተጠየቀው የኤሌክትሪክ ኃይል ቀርቧል፡፡ የሩብ ዓመቱ አፈፃፀም 100% ነው፡፡ ከዕቅዱ
በፊት ስራው ሊከናወን የቻለበት ዋነኛው ምክንያት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይትና
ጥብቅ ክትትል በማድረግ ለባለሀብቱ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቀርብ በመደረጉ ነው፡፡

የ ICT ፓርክ 10 ሜጋዋት ጊዚያዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማሟላት በተያዘው እቅድ መሰረት በአምራች ኩባንያ ኮንክሪት
ፖሎች ተመርተው ፍተሻና ሙከራ ተከናውኗል፤ 34 ኮንክሪት ፖሎች ወደ ሳይት ተጓጉዘዋል፤ ከእነዚህ ውስጥ 23
ኮንክሪት ፖሎች ተተክለዋል፡፡ አስፈላጊ የኮንክሪት ፖል ዕቃዎች ቀርበዋል፡፡ በሁሉም የተተከሉ ኮንክሪት ፖሎች ላይ
Insulators ለመግጠም እና Coductor ለመዘርጋት የሚረዱ Cros-arms ተገጥመዋል፡፡ 11 ኮንክሪት ፖሎች በሚተከሉበት
ቦታ ላይ ያጋጠመውን የይገባኛል ጥያቄ ለመፍታት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ስራ ተቋራጩ ጋር የሳይት
ምልከታ በማድረግ፣ የ GPS ኮኦርዲኔት በመውሰድና በካርታ ላይ ተመላክቷል፡፡ ይህ እደተጠበቀ ሆኖ ኮንክሪት ፖሎቹ
በሚተከሉበት መሬት ላይ ሰብል የተዘራበትና ቤቶች የተሰሩበት በመሆኑ ይህንን ችግር መፍታት ስለሚቻልበት ሁኔታ
ከለሚ ኩራ ክ/ከተማ አመራሮች በተደረገው ውይይት ከዚህ ቀደም በቦሌ ለሚ ሰብስቴሽን ውስጥ የሚገኘው መሬት

4
ባለይዞታዎች ካሳ ሳይከፈላቸው በመነሳታቸው ምክንያት ፖሎች እንደማያስተክሉን ጠቅሰው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ
ኃይል የካሳ ክፍያውን ቅድሚያ መክፈል እንዳለበት ተገልጿል፡፡ መስመር ዝርጋታው በሩብ ዓመቱ 12% አፈፃፀም
እንዲኖረው ታቅዶ 9% ተከናውኗል፡፡ አጠቃላይ አፈፃፀሙ 75% ሲሆን ለአፈፃፀሙ ማነስ ዋነኛ ምክንያቶቸ የኮንክሪት
ፖሎችና ተያያዥ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አቅርቦት መዘግየት፣ በ EEU በኩል የኤሌክትሪክ መስመሩ የሚዘረጋበት
አቅጣጫ በተደጋጋሚ ጊዜ ለውጥ ማድረግና፣ 11 ኮንክሪት ፖሎች በሚተከሉበት ቦታ ከይገባኛል ጥያቄ ጋር የተያያዙ
መሆናቸው ናቸው፡፡

ለሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ 10 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል ለማቅረብ በባለፈው የበጀት ዓመት 70% የኃይል አቅርበት
ስራው ተጠናቋል፡፡ የመካከለኛ ቮለቴጅ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ፣ ፍተሻና ሙከራ ስራ ተከናውኗል :: በፓርኩ
ውስጥ የ 33 ኪ.ቮ ኬብል ዝርጋታ እስከ ሼዶቹ የተከናወነ ሲሆን የሰብስቴሽን ወጪ ላይ Dedicated Breaker እና Panel
ገጠማ፣ ፍተሻና ሙከራ ተከናውኗል፡፡ የመካከለኛ ቮልቴጅ ዕቃ RMU በአሁኑ ጊዜ ሳይት ላይ ደርሷል፡፡ በመጀመሪያው
ሩብ በጀት ዓመት 11% ክንውን እንዲኖረው ታቅዶ 9% ተከናውኗል፡፡ አፈፃፀሙም 82% ነው፡፡ ለአፈፃፀሙ ማነስ ዋነኛ
ምክንያት ስራ ተቋራጩ የመካከለኛ ቮልቴጅ ዕቃዎች (RMU እና ትራንስፎርመር) ወደ ሀገር ውስጥ በሚፈለገው
ፍጥነት አለማስገባቱ ነው፡፡

1.8.2 ዘላቂ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፤

በቦሌ ለሚ II ኢንዱስትሪ ፓርክ ዘላቂ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች
ተሰርቷል፤ከቅድመ ዝግጅት ስራዎች አንዱ የመካከለኛ ቮልቴጅ ተሸካሚ መስመር የሲቪል ስራ ለማከናወን እንዲረዳ
ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በጋራ የልኬት ስራ ተከናውኗል፡፡ መስመሩ በሚያልፍበት ኮሪደር ላይ
የይገባኛል ጥያቄዎች ተለይተው ከክፍለ ከተማ አስተዳደሩ የዋጋ ግምት ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ይህ የዋጋ ግምትም
የመካከለኛ ቮልቴጅ መስመሩ የሚልፍበትን ቦታ ተለይቶ የዋጋ ግምቱ ያልቀረበ መሆኑን በማመላከት ምላሽ
ለሚመለከተው አካል ተሰጥቷል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የሲቪል ስራውን ለማከናወንና ስራ ተቋራጭ ለመምረጥ
የጨረታ ሰነድ በአየር ላይ ይገኛል፡፡ በመጀመሪያው ሩብ በጀት ዓመት 5% ክንውን እንዲኖረው ታቅዶ 2.5%
ተከናውኗል፡፡ አፈፃፀሙም 50% ነው፡፡ ለአፈፃፀሙ ማነስ ዋነኛ ምክንያት ከይገባኛል ጥያቄ ጋር የተያያዙ የክፍያ
ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ከባለድርሻአካላት አለመገኘቱ እና ስራ ተቋራጭ አለመለየት ነው፡፡

የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዘላቂ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች
ተሰርቷል፤ከቅድመ ዝግጅት ስራዎች አንዱ ከሰብስቴሽን እስከ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ድረስ ያለው የኬብል ትሬንች
ዲዛይን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በጋራ በመሆን ዲዛይን የመከለስ ስራ በመከናወን ላይ ነው፡፡ ለኢንዱስትሪ
ፓርኩ የኬብል ትሬንች መስሪያ በቂ ቦታ ለመስጠት መንገዱን ከሚያሰሩ አማካሪዎች ዝርዝር መረጃ ለኢትዮጵያ
ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የሲቪል ስራውን ለማከናወንና ስራ
ተቋራጭ ለመምረጥ የጨረታ ሰነድ በአየር ላይ ይገኛል፡፡ በመጀመሪያው ሩብ በጀት ዓመት 5% ክንውን እንዲኖረው
ታቅዶ 2.5% ተከናውኗል፡፡ አፈፃፀሙም 50% ነው፡፡ ለአፈፃፀሙ ማነስ ዋነኛ ምክንያት የኬብል ትሬንች ዲዛይን
የመከለስ ስራ በባለድርሻ አካላት በኩል በፍጥነት አለመጠናቀቁ እና ስራ ተቋራጭ አለመለየት ነው፡፡

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር 407 ኪ.ሜ ዝርጋታ እና የሰብስቴሽን
ግንባታ 60 ሜጋዋት ዘላቂ የኤሌክትሪክ ኃይል ለኢዱስትሪ ፓርኩ ማቅረብ የሚችል በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን
በባለፈው የበጀት ዓመት 60% የግንባታው ስራው ተጠናቋል፡፡ የከፍተኛ ቮልቴጅ ተሸካሚ መስመር ዝርጋታ ስራዎች

5
807 የታዎር ፋውንዴሽን ተዘጋጅቷል፤ 616 ታዎሮች ተተክለዋል፤የዕቃዎች ምርት ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ
ተከናውኗል፡፡ የ Insulator fixing ስራዎች 33 ኪ.ሜ ተከናውኗል፤ የ Conductor stringing ስራዎች 25 ኪ.ሜ ተጠናቋል፡፡
በሰብስቴሽን ግንባታ የሲቪል ስራ፤ የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች ምርት፤ የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች አቅርቦት
እንዲሁም የኤሌክትሮ መካኒካል steel structure ስራዎች ተከናውኗል፡፡ ጠቅላላ ስራው በመጀመሪያው ሩብ በጀት
ዓመት 9% ክንውን እንዲኖረው ታቅዶ 6% ተከናውኗል፡፡ አፈፃፀሙም 67% ነው፡፡ ለአፈፃፀሙ ማነስ ዋነኛ ምክንያት
በሀገሪቱ ባለው ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ስራውን ለመፈፀም አስቸጋሪ መሆን ነው፡፡

ለ ICT ፓርክ 200 ሜጋ ዋት ዘላቂ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማሟላትና ወደ ቀጣይ የትግበራ ምዕራፍ ለመሸጋገር
እንዲያስችል የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ በአዋጭነት ጥናቱ ላይ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና በኮርፖሬሽኑ
በኩል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ይህንን መሰረት በማድረግ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ለኢንዱስትሪ
ፓርኩ ዘላቂ ኤሌክትሪክ ኃይል ለማሟላት በቅድሚያ ዝርዝር ዲዛይን እና የዋጋ ግምት ተዘጋጅቶ ለኮርፖሬሽኑ
ቀርቧል፡፡ ይህንን የቅድመ ዝግጅት ስራ ለማከናወን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር የማመከር ስራ ውል ተፈፅሟል፡፡
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የፕሮጀክቱን አጠቃላይ ወጪ የሚያመላክት የፋይናንሺያል የዋጋ ግምት በኢትዮጵያ
ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ቀርቧል፡፡ ነገርግን ይህ የዋጋ ግምት በአዋጭነት ጥናቱ ከቀረበው ጋር የዋጋ ልዩነት መኖሩና
በፊዚቢሊቲ ጥናቱ ወቅት ያልታዩ ወጪዎችን በመጠባበቂያነት የተያዘ የገንዘብ ልዩነት መሆኑን በማመላከት ለውሳኔ
የሚረዳ አስተያየት ቀርቧል፡፡ በቀረበው አስተያየት ላይ ውሳኔ እንዲሰጥበት ክትትል እየተደረገ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ለኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ሊገነባ ለታቀደው የ 230 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ
ጣቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ዲዛይን ዝግጅት እየተጠናቀቀ ሲሆን ለሰብስቴሽን ግንባታ የሚሆን አማራጭ ቦታዎችን
ለመለየት፣ አካባቢያዊ እና ማህበረሰባዊ ተፅዕኖዎችን ለመቀነስ እንዲረዳ የሳይት ምልከታ በተደጋጋሚ በማድረግ
ለኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው የሚሆን የቦታ መረጣ ተከናውኗል፡፡

የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከዋናው ሰብስቴሽን ጋር በ 33 ኪቮ ፊደር ለማገናኘትና መስመሩ
የሚያልፍበትን ኮሪደር ለመምረጥ ፊደሮቹ የሚወጡበት የሰብሰቴሽን መነሻ፣ መስመሩ የሚያልፍበት ኮሪደር፣ ወደ
ሀዋሳ ኢ/ፓርክ የሚገባበት ቦታ (interface point)፣ የልኬት እና የ GPS ኮርዲኔት ኮርፖሬሽኑ እና የኢትዮጵያ
ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጋራ የመስክ ምልከታ ስራ ተከናውኗል እንዲሁም bill of quantity ቀርቧል፣ ስራውን
ለማከናወን እንዲቻል የሚስፈልገውን የኬብል ትሬንች ግንባታ ስራ ግዥው በታቀደው ጊዜ እንዲፈፀም የፍላጎት
መግለጫ ሰነድ ለሚመለከተው የስራ ክፍል ቀርቧል፡፡ የኬብል ትሬንች ዲዛይን እና ለትሬንች ሲቪል ስራ ግንባታ
የተያዘውን ዋጋ ግምት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለኮርፖሬሽኑ ያሳወቀ ሲሆን የዋጋ ግምቱን በተመለከተ
አሁን ካለው አጠቃላይ የግንባታ ዋጋ መረጃ ጋር በማገናዘብ በኮርፖሬሽኑ በኩል የዋጋ ግምት የቀረበ ሲሆን በኢትዮጵያ
ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቀረበው የዋጋ ግምት ልዩነት ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ሙያዊ አስተያየት እንዲቀርብ
ጥያቄ ለተቋሙ ቀርቧል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የኤሌክትሪክ ኬብል በአምራች ኩባንያው በመመረት ላይ ይገኛሉ፡፡

1.8.3 በኢንዱስትሪ ፓርኮች የቴሌኮም መሰረተ ልማትን ማሟላት

ለባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ከኢትዮ ቴሌኮም ስቴሽን እስከ ፓርኩ የፋይበር ኬብል ዝርጋታ የሚከናወንበት መስመር
በአሁኑ ጊዜ የአዋጪነት ጥናት እና ዲዛይን ስራዎች በኢትዮ ቴሌኮም በኩል ተከናውኗል፡፡ ዝርጋታውን ለማከናወን

6
የሳይት ርክክብ ተከናውኖ የፋይበር ኬብል ሳይት ላይ ደርሷል፡፡ የሲቪል ስራ ተጀምሮ 3 የቴሌኮም ማንሆሎች
ተሰርቷል፡፡ በመጀመሪያው ሩብ በጀት ዓመት 3% ክንውን እንዲኖረው ታቅዶ 1.5% ተከናውኗል፡፡ አፈፃፀሙም 50%
ነው፡፡ ለአፈፃፀሙ ማነስ ዋነኛ ምክንያት በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የፋይበር ኬብል ዝርጋታ በፍጥነት አለመከናወኑ ነው፡፡

ለሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የቴሌኮም መሰረተ ልማት ለማሟላት በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የየ offsite ፋይበር እና
የውስጥ ኮፐር ኬብል ዝርጋታ በመከናወን ላይ ሲሆን በባለፈው የበጀት ዓመት 30% የቴሌኮም መሰረተ ልማት
አቅርቦት ስራ ተጠናቅቋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ 150 የቴሌኮም ፖሎች ተከላ እና 7 ኪ.ሜ የፋይበር ኬብል ዝርጋታ
ተከናውኗል፡፡ በፓርኩ ውስጥ የፋይበር ኬብል ዝርጋታ ስራዎች ሙሉ በሙሉ ተከናውኗል፡፡ አንዳንድ ሰነዶች በኢትዮ
ቴሌኮም በኩል ፀድቀዋል ሌሎች በሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡ በመጀመሪያው ሩብ በጀት ዓመት 20% ክንውን እንዲኖረው
ታቅዶ 16% ተከናውኗል፡፡ አፈፃፀሙም 80% ነው፡፡ ለአፈፃፀሙ ማነስ ዋነኛ ምክንያት ስራ ተቋራጩ በዲዛይን ማፀደቅ
ሂደት ላይ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የቀረቡ አስተያየቶችን ተቀብሎ ማስተካከያ በሚፈለገው ፍጥነት ባለማቅረቡ ነው፡፡

1.8.4 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉሃ አቅርቦት


የቦሌ ለሚ ምዕራፍ አንድ ውኃ አርቅቦትን በተመለከተ በ 1 ኛ ሩብ ዓመት በሲቪል ስራ ተካተው 0.84% ዕቅድ ተይዞ 0.2 የተከናወነ ሲሆን
አፈፃፀሙም 23.8% ነዉ፡፡ ለአፈፃፀም ማነስ ዋና ምክንያት የወሰን ማስከበር ችግር አለመፈታት ሲሆን ለዚህም በኮርፖሬሽኑ ስራ አመራር
በኩል ኮርፖሬሽኑ ክፍያውን እንዲከፍል ተወስኖ ከ IDF በጀት ብሩ ወደ ክፍለ ከተማ ባንክ ሂሳብ ገቢ የተደረገ ቢሆንም መሬት ነክ ስራዎች
ለጊዜዉ በመንግስት አቅጣጫ እየተከናወነ ባለመሆኑ ምክንያት ክፍያዉ ለባይዞታዎች መፈፀም አልታቸለም። ሆኖም ክፍለ ከተማዉ አርሶ
አዳሮቹን እና ወረዳውን እንዲያስተባብር እና ስራዉን እንድናከናዉን ክ/ከተማውን ጥያቄ በቀረበው መሠረት ክትትል በመደረግ ላይ ነው፡፡
የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራውን በሩብ ዓመቱ 5% ለማከናወን ታቅዶ 3% ተፈፅሟል፡፡ አፈፃፀሙ በመቶኛ ሲታይ 60% ይሆናል፡፡ ለአፈፃፀሙ
ማነስ የተወሠነ የሥራ ተቋራጩ ችግሮች ቢኖሩበትም በዋናነት ግን ከቦታ ይገባኛል ጋር የተያያዙ ችግሮች ባለመፈታታቸው ነው፡፡

በዚሁ በቦሌ-ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጉድጓድ ቁ. 5 በብልሽት ምክንያት አገልግሎት ላይ ባለመሆኑ ችግሩን ለመፍታት ከስራ
ተቋራጭ፣ አማካሪ እና የጉድጓድ ቁፋሮውን ካከናወነው (ሲጂሲኦሲ) ጋር በመሆን ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠትና አገልግሎት ላይ
ለማዋል ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ ቀድሞ የጉድጓድ ቁፋሮውን ያከናወነው አካል ስራ ተቋራጭ በኩል ያላቸዉን አስተያየት
በሪፖርት ያሳወቁን ሲሆን አማካሪዉ ከዚህ በኋላ ችግሩን ለመፍታት የሚደረግ ስራ ዉጤታማ እንደማይሆን እና ስለጉድጓድ ቁ. 5
ምትክ እዚያው ግቢ ዉስጥ አዲስ ጉድጓድ መቆፈር መፍትሔ ይሆናል የሚል ውሣኔ አሣርፏል፡፡ በተመሣሣይ በሌሎች ጉድጓድ ላይ
የመልሶ ማሻሻያ (Rehabilitation) ሥራ እንዲከናወን ትዕዛዝ ባሣለፈው መሠረት የሚከናወን ይሆናል፡፡

በድሬደዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለዘላቂ ዉሃ አቅርቦት በአንደኛው ሩብ ዓመት ስራ ተቋራጩ የአንድ ጉድጓድ አጠናቋል። የዉሃ
ማጠራቀሚያ (service reservoir) እና የ high voltage room ሲቪል ስራዎች እየተከናወኑ ነዉ፡፡ የዉሃ መስመር ቁፋሮ ከዉሃ
ማጠራቀሚያ እስከ ፓርክ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም በይገባኛል ጥያቄ ምክንያት በአካባቢው የሚገኙ ስራዉን ማስቀጠል ባለመቻሉ

7
ችግሩን ለመፍታት ከከተማው የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በተደረገው ውይይት ሥራው እንዲጀመር ተደርጓል፡፡ እንዲሁም
ከጉድጓድ ቁ.2 ወደ ጉድጓድ ቁ.3 ዉሃ ማጠራቀሚያ የሚሄድ መስመር ቁፋሮዉን ለማከናወን በይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ጉድጓዱን
ማከናወን አልተቻለም። በአጠቃላይ በአንደኛ ሩብ ዓመት ለዘላቂ ዉሃ 15% ለመከናወን ታቅዶ የነበረ ቢሆንም 6.11 ተከናውኖ
የሩብ ዓመቱ አፈፃፀም 40% ነዉ። ለድሬ ዳዋ ኢ/ፓ ዘላቂ ዉሃ አቅርቦት አፈፃፀም ማነስ ዋናኛ ምክንያት የስራ ተቋራጩ
አፈፃፀም ማነስ ሲሆን በተደጋጋሚ በቦታይገባኛል ጥያቄ ምክንያት የሚቋረጠውም የሥራሱ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሯል። ሥራ
ተቋራጩ ከውጭ ሀገር የሚያስገባቸው ዕቃዎችን በተመለከተ የሚዘገይ ከሆነ በጊዜያዊነት መፍትሔ ለመስጠት እንዲቻል ተጨማሪ
አማራጭ (Plan B) ረቂቅ ሰነድ ለውይይት ተዘጋጅቷል። ይህ ረቂቅ ሰነድ ሙሉ የስራ ሂደት፣ ዋጋ ግምት እና የስራ መርሐ ግብር
ተዘጋጅቷል።

አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተለያየ ጊዜ በተደረጉ የውሃ ጉዳጓድ ቁፋሮዎች የውሃ አቅርቦት ማሟላ ባለመቻሉ በኢንዱስትሪ ፓርኩ
የገቡ ባለሐብቶች የራሣቸውን ውሃ ጉድጓድ በመቆፈር ውሃ ለማቅረብ ጥረት ያደረጉ መሆናቸው የሚታቅ ነው፡፡ በሥራ ተቋራጩ
በኩል ዘላቂ የውሃ አቅረቦት እንዲያማላ በተገባው ውል መሠረት በአማካሪው በኩል ቀጣይ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ለማድረግ
የሚያስችል ውሣኔ ተሏልፏ፡፡ ሥራ ተቋራጩ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሲደርሰው አንድ የውሃ ጉድጓድ መቆፈሪያ ማሽን
አስገብቷል፡፡ ከውሉ አንፃር አጠቃላይ ሂደቱንና የተወሠዱ እርምጃዎችን ተመልክቶ የመጨረሻ የውሣኔ ሃሣብ እንዲያቀረብ
ለአማካሪው ተገልፆለታል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢንዱስትሪ ፓርኩን ዘላቂ ውሃ አቅርቦት ለሟሟላት ሌላ አማራጭ መታየት
ያለበት በመሆኑ በኮርፖሬሽኑ በኩል በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከኦሮሚያ ውሃ ሥራዎች ድርጅት ጋር በጥናትና ግንባታ ዙሪያ
የመጀመሪያ ደረጃ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በተደረገው የጋራ ውይይት መሰመሰረት በኢንዱስትሪ ፓርኩ ከከርሰ ምድር በጉድጓድ ውሃ፣
ከአካባቢው ገፀምድር ከሚገኝ ውሃ ወይም የተወሠነ መጠን ያለው ውሃ ከአዋሽ ወንዝ እንዲሁም ውሃን መልሶ መጠቅም
እንዲያስችሉ ከተገጠመው ፍሣሽ ማጣሪያ በማቀናጀት በመቀላቀል የውሃን ጥራት በአካባቢው የሚታየው የስምጥት ሸለቆ የውሃ
ሙቀት ለመቀነስ የሚያስችል በመሆኑ በዚሁ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት እንዲቻል በጋራ ለጥናቱ የሚረዳ ዝርዝር ተግባር
በመዘጋጀት ላይ ነው፡፡ ይህ ሠነድ ሲጠናቀቅ ለቀጣይ ውጤት የኮፖሬሽኑና የኦሮሚያ ውሃ ሥራዎች ድርጅት የበላይ አመራሮች
በጋራ ውይይት ተደርጐበት አቅጣጫ የሚቀመጥበት ይሆናል፡፡

1.8.5 የኢንዱስትሪ ፓርኮች መዳረሻና ተለዋጭ መንገድ


የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመንገድ ተደራሽ ለማድረግና ውጤታማና ፈጣን የሆነ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር ለማድረግ
እንዲቻል ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጋር በመሆን የመዳረሻ መንገድ ግንባታዎች እየተከናወኑ ነዉ፡፡ በዚህ ሩብ ዓመት
ለመዳረሻና ተለዋጭ መንገዶች በዕቅድ ደረጃ የተያዘ የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቀሪ ግንባታ 1% ለማከናወን ዕቅድ ተይዞ 0.75%
የተከናወነ ሲሆን አፈፃፀሙም 75% ነዉ፡፡ ሌላዉ የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ አጎራባች ለሚኖሩ ነዋሪዎች ከተለዋጭ መንገድ ግንባታ ጋር
ተያያዥ ቀሪ ስራዎች እንዲጠናቀቁ ክትትል ተደርጓል፡፡ በዚህም ለቀሪ ስራዎች መከናወን የ Box culvert structure እና Slope
protection ስራዎች ለማከናወን ከተያዘዉ 3% የሩብ ዓመት ዕቅድ ዉስጥ ሙሉ በሙሉ ተከናዉኗል፡፡ የቦሌ ለሚ ምዕራፍ አንዱ ኢንዱስትሪ
ፓርክ አጎራባች ለሚኖሩ ነዋሪዎች የተለዋጭ መንገድ ግንባታ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩል እንዲከናወን በተደረሰዉ መግባባት
መሰረት በበጀት ዓመቱ የመንገዱን ዲዛይን ለማከናወን የኮርፖሬሽኑ፣ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣንና የመንገዱን ዲዛይን አማካሪ
ጋር በጋራ በመሆን የመስክ ምልከታ በማድረግ የመንገዱ የሚያልፍበት መስመር የመናበብና በመንገዱ ላይ ስላሉ ሁኔታዎች መግባባት ላይ
በተደረሰው መሠረት የዲዛይን ቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጀምሯል፡፡

በሌላ በኩል የደብረ ብርሀን ኢ/ፓርክ የ 6 ኪ.ሜ መዳረሻ መንገድና የመኪና ማቆሚያ ግንባታ እንዲከናወን በታቀደው መሠረት
በግንባታ ወሰን ዉስጥ ያሉ ንብረቶች በከተማ አስተዳደሩ እንዲነሱና የመንገዶች ባለስልጣን የካሳ ክፍያ እንዲፈፅም ለማድረግ ክትትልና
ድጋፍ እየተደረገ ነዉ፡፡ ከዋናው መንገዱ ጋር ተያይዞ የፓርኩን ተሽከርካሪ ማቆሚያ ግንባታ በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን
አመራሮች ጋር በተደረገው መግባባት መሠረት የመንገድ ግንባታዉን በሚያከናዉነዉ ስራ ተቋራጭ በኩል እንዲከናወን የስራ ትእዛዝ
እንዲሰጠው መግባባት ላይ ተደርሶ የዲዛይን ስራ ተጠናቋል፡፡ በተጨማሪም ከመዳረሻ መንገዱ ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚመጣዉን ጎርፍ
ፍሳሽ ለመከላከል የተፋሰስ ዲዛይንና ሃይድሮሎጂ ጥናት በተመለከተ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የመንገድ ግንባታውን የሚያማክረው
አማካሪ ድርጅት እና የኮርፖሬሽኑ ተወካዮች በተገኙበት የጋራ የመስክ ዳሰሳ እና የውይይት መድረክ ተካሂዶ ስለ ቀጣይ አፈፃፀም መግባባት
ላይ ተደርሷል፡፡

8
እንደሚታወቀው ሁሉ የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ በሚወስደው ዋና መንገድ ዳርቻ የሚገኝ በመሆኑና
ይኸው መንገድ express way በመሆኑ ምክንያት በቀጣይ ሊኖረው ከሚችለው የትራፊክ ፍሰት አንፃር እንዲሁም በቀጥታ ከወደብ
የሚመጣውን ጥሬ ዕቃ ወይም ከፓርኩ የሚወጣውን ምርት በቀላሉ ወደ ዋና መንገዱ መግባት የሚያስችል መዳረሻ መንገድ እና ራሱን የቻለ
ማሳለጫ ድልድይ (Interchange Bridge) ዲዛይኑ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡ ይህንኑ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚሆን ድልድይ እና 3 ኪ.ሜትር
የሚሆን የመዳረሻ መንገድ ግንባታ ለማከናወን በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በኩል የስራ ተቋራጭ ግዢ ለማድረግ በተደጋጋሚ
ጨረታ የወጣ ቢሆንም የጅቡቲ ዋና መንገድ ሣይዘጋ ሊገነባ የሚችለውን ድልድይ ለመሥራት አቅም ያለዉ ስራ ተቋራጭ ባለመገኘቱ
እንዲሁም በዋጋ መጋነን ምክንያት የተቋራጭ ግዥ አልተፈፀመም፡፡ አሁንም ለ 3 ኛ ጊዜ የሥራ ተቋራጭ ግዥ ጨረታ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

1.9 የኤሌክትሪክ ኃይልና ቴሌኮም የርክክብ ስራዎች


የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኤሌክትሪክ እና ቴሌኮም መስመሮችና ተያያዥ ዕቃዎች ማስተካከያ ስራዎች ለማጠናቀቅ
እንዲረዳ ቀሪ ስራዎች ተለይተው በሩብ ዓመቱ ማጠናቀቅ ስለሚቻልበት ሁኔታ ሳይት ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
በተመሳሳይ ቀሪ ስራዎቹ በተያዘው ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ ከአማካሪው ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን
አማካሪው ስራዎቹን ተከታትሎ በሩብ ዓመቱ እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት
ስራ ተቋራጩ በፓምፕ ስቴሽን እና ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ያልተጠናቀቁ የፋይበርና ኮፐር ኬብሎች ዝርጋታ ስራዎችን
አጠናቋል፡፡ የፍሳሽ ማጣሪያው መስመር ዝርጋታ ተጠናቋል፤ እስከ 75% የሚደርሰው የፋይበር እና ኮፐር ኬብሎች
ዝርጋታ ስራ ተከናውኗል፡፡ 360 ሜትር የመካከለኛ ቮልቴጅ ኬብል ትሬንች የማፅዳት ስራ የተከናወነ ሲሆን በ 13
ማንሆሎች ላይ የማስተካከያ ስራ ተሰርቷል፡፡ የፋይበር ኬብል እና ቴሌኮም ዕቃዎች ማስተካከያ ስራዎች ለማከናወን
የሚያስፈልጉ ዕቃዎች ከድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለማጓዝ እና ከውጭ ሀገር
ተገዝተው በመጡ ዕቃዎች ላይ የካስተምስ ድጋፍ እንዲደረግለት ስራ ተቋራጩ በጠየቀው መሰረት ድጋፍ
ተደርጎለታል፡፡ የፍሳሽ ማጣሪያ ETP ኤሌክትሪክ ኃይል ለማገናኘት EEU ባቀረበው የዋጋ ስፔሲፊኬሽን መሰረት
የ Dropout Fuses እና Lightning Arresters በኮርፖሬሽኑ በኩል ግዥ ተፈፅሞ ርክክብ ተደርጓል፡፡ በሩብ ዓመቱ
የኤሌክትሪክና ቴሌኮምና መስመሮችና ተያያዥ ዕቃዎች ርክክብ 8.5% አፈፃፀም እንዲኖረው ታቅዶ አፈፃፀሙ 6.5%
ነው፡፡ አፈፃፀሙም 76% ነው፡፡ ለአፈፃፀሙ ማነስ ዋነኛ ምክንያት የቴሌኮም ዕቃዎች ዝውውር መዘግየትና ስራ
ተቋራጩ የማስተካከያ ስራዎቹን በሚፈለገው ፍጥነት ባለማከናወኑ ምክንያት የርክክብ ስራው በተቀመጠው
መርሀግብር መሰረት አለመጠናቁ ነው፡፡

የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኤሌክትሪክ እና ቴሌኮም መስመሮችና ተያያዥ ዕቃዎች ማስተካከያ ስራዎች ለማፋጠን
እንዲረዳ ቀሪ ስራዎች ተለይተው ማጠናቀቅ ስለሚቻልበት ሁኔታ ተከታታይ ውይይቶች ተደርጓል፡፡ በዚህ መሰረት
የኤሌክትሪክ እና ቴሌኮም መስመሮችና ተያያዥ ዕቃዎች ማስተካከያ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡ በዳታ ሴንተር
ውስጥ የኮርስዊች ኮንፊገሬሽን ስራዎች እና የሼዶች ራውተር ኮንፊገሬሽን ተከናውነዋል፡፡ እንዲሁም የፋይበር እና
ኮፐር ኬብሎች ፍተሻና ሙከራ ስራ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል ተጠናቋል፡፡ በፍተሻና ሙከራ ጊዜ የተስተዋሉ የተወሰኑ
የኮፐር ኬብል ችግሮች እንዲስተካከሉ ለስራ ተቋራጩ በአማካሪ ድርጅቱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ በሩብ ዓመቱ
የኤሌክትሪክና ቴሌኮም መስመሮችና ተያያዥ ዕቃዎች ርክክብ 9% አፈፃፀም እንዲኖረው ታቅዶ አፈፃፀሙ 7% ነው፡፡

9
አፈፃፀሙም 78% ነው፡፡ ለአፈፃፀሙ ማነስ ዋነኛ ምክንያቶች የቴሌኮም ዕቃዎች ዝውውር መዘግየትና ስራ ተቋራጩ
በኤሌክትሪክ መስመሮችና ተያያዥ ዕቃዎች ማስተካከያ ስራ ላይ በሚፈለገው ፍጥነት አለማከናወኑ ነው፡፡

ለደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ የኤሌክትሪክ እና ቴሌኮም ስራዎች ርክክብ ለማከናወን የመካከለኛ ቮልቴጅ የኤሌክትሪክ ሲስተም
ማስተካከያ ስራ እንዲሁም የቴሌኮም Weak current System ፍተሻና ሙከራ ስራዎች ተከናውኗል፤ በአማካሪው በኩል ለስራ
ተቋራጩ አስተያየቶች ቀርቧል፡፡ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 4% አፈፃፀም እንዲኖረው ታቅዶ 3% ተከናውኗል፡፡ አፈፃፀሙም 75%
ሲሆን ለአፈፃፀሙ ማነስ ዋነኛ ምክንያት ስራ ተቋራጩ በወቅቱ ባለሙያ አለመመደብና የጊዜ ሰለዳ በሚፈለገው ፍጥነት አለማሳወቁ
ነው፡፡

የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ የመካከለኛ ቮልቴጅ ማስተላለፊያ ዕቃዎችና መስመር ዝርጋታ በመጀመሪያ ደረጃ ርክክብ
ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች በስራ ተቋራጩ በኩል የማስተካከያ ስራዎች ተከናውኗል፡፡ ስራ ተቋራጩ የቴሌኮም
የርክክብ ሰነድ በኢትዮ ቴሌኮም የተሰጡት አስተያየቶች በማጠናቀቁ ሰነዱ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል እየተገመገመ
ይገኛል፡፡ በመጀመሪያው ሩብ በጀት ዓመት 20% ክንውን እንዲኖረው ታቅዶ 10% ተከናውኗል፡፡ አፈፃፀሙም 50%
ነው፡፡ ለአፈፃፀሙ ማነስ ዋነኛ ምክንያት ስራ ተቋራጩ የርክክብ ሰነድ በኢትዮ ቴሌኮም የተሰጠው አስተያየት መሰረት
አስተካክሎ በሚፈለገው ፍጥነት ባለማቅረቡ ነው፡፡

ስትራቴጂካዊ ግብ 2:- የኢንዱስትሪ ፓርኮች የስራ ዕድል ፈጠራ ውጤታማነትን ማሳደግ


2.1 በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ማሣደግ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ ባለሐብቶች ለሠራተኞቻቸው ቤት እንዲገነቡ ለማድረግ እስከ 1 ዐ ለሚደርሱ
ባለሐብቶች ቦታ ተፈቅዷል፡፡ ቦታ ከተፈቀደላቸው ባለሐብቶች መካከል በሩብ ዓመቱ በቦሌ ለሚ ሲንትስ የተባለው
ኩባንያ የጀመራቸውን የሠራተኞች ቤት ግንባታ ለማፋጠን የማያስችለው የሲሚንቶና የፋይናንስ እጥረት ለመፍታት
የማያስችሉ ድጋፎችና የተለያዩ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡ በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ Funali የተባለወ ኩባንያ ግዜያዊ
የሆነ የመኖሪያ ቤት ለመገንባት የቅድመ ዝግጅት አድርጐ የነበረ ቢሆንም ለዘላቂ የመኖሪያ ቤት ለመገንባት የሚያስችል
መሬት በኢትዮጵያ ኢቨስትመንት ኮሚሽን በኩል ቦታ የተፈቀደለት በመሆኑ ለዚሁ ቋሚ የሆነ የቤት ግንባታ የሚሆን
ዲዛይን እንዲያቀርብ ተጠይቋል፡፡ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሠራተኞች ቤት ግንባታ በቀረበው ዲዛይን መሠረት
ቁፋሮ ተጀምሮ የተቋረጠውና Antex በተባለው ኩባንያ የተያዘው የግንባታ ዕቃ በተመለከተ በቦታው ላይ የካሣ ይገባኛል
ጥያቄ በመቅረቡ ምክንያት ይህንኑ ለመፍታት ከአዳማ ከተማ አስተዳደር ጋር ክትትል ሲደረግ የቆየ ቢሆንም ችግሩ
ሊፈታ ባለመቻሉ የቤቶቹ ግንባታ ሥራው ሊቀጥል አልቻለም፡፡

በሃዋሣ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ለሚሠሩ ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ለሟሟላት እንዲቻል ኮርነርስቶን
ከተባለ የግል ባለሐብት ጋር ውል ተፈፅም 2.08 ሄክታር መሬት ርክክብ ተፈፅሟል፡፡ ይህ መሬት በኢንዱስትሪ ፓርኩ
ቅጥር ግቢ ውስጥ ቀደም ሲል ከተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ጐን ላይ የሚገኘ ቦታ ነው፡፡ በባለሐብቱ በኩል የሚገነቡ ቤቴች
ለ 6500 ሠራተኞች የሚሆኑ ከመኖሪያ ቤት በተጨማሪ ሌሎች አገልግሎት መስጫዎችም የተካተቱበት ነው፡፡ የቤቶች
ግንባታ በፓርኩ ውስጥ ከተዘረጉ ነባር የመሠረተ ልማት የተለያዩ አገግሎቶችን የሚጠቀም በመሆኑ በዲዛይን ዝግጅት
ወቅት መታየት ያለባቸው የቅንጅት ስራዎችን በተመለከተ በተለያዩ ሙያዎች ላይ ያተኮረ የዲዛይን ቡድኖችን
በማቋቋም የዲዛይን ማጣጣም ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጐን ለጐን በባለሐብቱ በኩል የግንባታ ቢሮና የዕቃ
ማስቀመጫ ሥራዎች፣ የአፈር ጠረጋ እና ዝርዝር ዲዛይኖች የማዘጋጅት ሥራ በማከናወን ላይ ነው፡፡

10
ስትራቴጂካዊ ግብ 3፡ የወጪ ንግድ ገቢን ማሳደግ

3.2 በኢንዱስትሪ ፓርኮች የመሰረተ ልማት ችግር የታዩባቸውን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን መፍታት፤

የኤሌክትሪክ ኃል አቅርቦት መቆራረጥ ችግር ያለበት ድሬዳዋ ኢንዱትሪ ፓርክ ችግሩን ለመፍታት የኢትዮጵያ
ኤሌክትሪክ ኃይል በሰብስቴሽኑ ውስጥ ትራንስፎርመሩን ከስዊችጊር የሚያገናኘውን ኬብል ለመቀየር የሚያስፈልጉ
ዕቃዎች ሰብስቴሽኑ ውስጥ ደርሷል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሰብስቴሽኑ ውስጥ Wuxi #1 ለተባለው ባለሀብት
ኤሌክትሪክ በሚያቀርበው ፓኔል የሚገኘው Current Transformer ምክንያት የሚፈጠረውን የኤሌክትሪክ መቆራረጥ
ችግር እንዲቀረፍ በኮርፖሬሽናችንና በኢትየዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል ጥያቄ ቀርቦ ከሁርሶ ሰብስቴሽን
የሚመጣው የኤሌክትሪክ ኃይል በሁለት መስመር ሲሆን አንዱ ለዚሁ ባለሀብት ተገናኝቷል፡፡ ሁለተኛው መስመር
ደግሞ ለኢንዱስትሪ ፓርኩ ተገናኝቷል፡፡ በዚሁ መሰረት በሁለቱ መስመሮች ተነስቶ የነበረውን ችግር ለመፍታት
በታቀደው መሰረት ሙሉ በሙሉ ተከናውኗል፡፡
በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር የሚስተዋልበት ሲሆን ይህንን ችግር
ለመፍታት በአዋሽ መልካሳ ሰብስቴሽን ውስጥ የሚገኘውን Earthing Transformer በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
በኩል በመቀየር እንዲሁም የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፋያ ፌደሮቹ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል ለየብቻ
እንዲገናኙ በማድረግ ችግሩ በጊዚያዊነት እንዲፈታ ተደርጓል፡፡ ነገርግን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር
በዘለቄታዊ ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግና የችግሩ መንስኤ በኢትዮጵያ
ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል እንዲጠና በማስድረግ ችግሩ በዘለቄታዊ እንዲፈታ
ክትትል የሚደረግ ይሆናል፡፡

ስትራቴጂካዊ ግብ 5:- በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ድርጅቶችን እና የሀገር ውስጥ አማራጮች መሃል
ያለውን ተስስር ማሳደግ፤
5.1 የሳተላይት ፓርኮች መለየትና ከክልል ከተሞች ጋር ስምምነት ላይ መድረስ፤

የአገራዊ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ስፓሻል ፕላን ጥናትን በተመለከተ በየክልሉ ላሉ 84 አመራሮች ግንዛቤ ማስጨበጫ
መድረክ ለመፍጠር እንዲቻል ዝርዝር ፕሮፖዛል ተዘጋጅቶ በመስከረም ወር ለ 42 የክልልና ከተማ አስተዳደር
አመራሮች የግንዛቤ መድረክ ለመፍጠር ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በመስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም በሚደረገው አዲስ
የመንግስት አደረጃጀት ምክንያት የአመራር መለዋወጥ ሊገጥም የሚችል መሆኑን ታሳቢ በማድረግ የፕሮግራም
ሽግሽግ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም የሳተላይት ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በፕላን ከመለየት ስራ ጋር ተያይዞ ቀድመው
የተመረጡት ቦታዎች በሳይት ፕላን በማመላከት እንዲልኩ ለሚመለከታቸው ከተማ አስተዳደሮች በደብዳቤ
ጥያቄ የቀረበ ሲሆን በተጨማሪም የአገራዊ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ስፓሻል ፕላን ጥናቱን መነሻ በማድረግ ለጅማና
አዳማ እንዲሁም ለባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሶስት የሳተላይት ፓርኮች (ቦንጋ፣ ዴራ እና መራዊ) የሚባሉ
ከተሞች የተለዩ ሲሆን አፈፃፀሙ 100% ነው፡፡

ስትራቴጂካዊ ግብ 6:- የኢኮ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ልማት ዘላቂነትን ማረጋገጥ

11
የደብረ ብርሃን እና ባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርኮች ፍሳሽ ማጣሪያ ግንባታን በተመለከተ ስራው ከሚጠበቀው አንጻር በሚፈለገው
ፍጥነት እየሄደ ባለመሆኑ ይህንኑ ለማስተካከልና ስራ ተቋራጩ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ ለማስቻል ከአማካሪውና ስራ
ተቋራጩ ጋር ውይይት ተደርጎ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ስራ ተቋራጩ በባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ Buffer Tank
የቁፋሮ ስራ ተጠናቆ የብረት እና የኮንትራት ስራ እየተሰራ ሲሆን ለኮንክሪት ስራ ዝግጁ ሆኗል፡፡ በደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ
የቁፋሮ ስራ ተጠናቆ የመሠረት ስራ እተሰራ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በአማካሪውም በኩል ዲዛይኖች በቶሎ እንዲጸድቁና ስራ
ተቋራጩም በኮንትራቱ መሰረት በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ ከውልና ዲዛይን ጋር በተያያዘ የተነሡ ጥያቄዎችን
ለመፍታት እንዲቻል ከተለያ ሥራ ክፍሎች የተውጣጡ ባለሙያዎች ኮሚቴ ተዋቅሮ በመታየት ላይ ነው፡፡ በሁለቱም
ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን አጠቃላይ የግንባታ ሂደት በተመለከተ አፈፃፀሙ ሲታይ በደብረ ብርሃን በሩብ ዓመቱ የተያዘው
ዕቅድ 7% ሲሆን የተፈፀመው 1.5% ነው፡፡ ይህ አፈፃፀሙ በመቶኛ ሲታይ 10.5% ነው፡፡ እንዲሁም በባህርዳር ኢንዱስትሪ
ፓርክበሩብ ዓመቱ የተያዘው ዕቅድ 7% ሲሆን የተፈፀመው 3% ሲሆን አፈፃፀሙ በመቶኛ ሲታይ 42.8% ነው፡፡ አፈፃፀሙ ማነስ
ዋነኛ ምክንያት ከዲዛይንና ውል ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በወቅቱ አለመፈታትና የሥራ ተቋራጩ የሞባይላይዜሽን ጊዜ መዘግየት
ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ከዚሁ በተጨማሪ በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቀደም ሲል የተገነባው የማዘጋጃ ቤታዊ ፍሣሽ ማጣሪያን በተመለከተ ወደ
የተቀናጀ የኢንዱስትሪና ማዘጋጃ ቤታዊ ፍሣሽ ማጣሪያ እንዲሆንና ማሻሻል እንዲቻል ከሥራ ተቋራጭ ጋር ውል በተገባው
መሠረት ዲዛይን በመዘጋጀት ላይ ሲሆን በቦታው ላይ የአፈር ምርመራ ስራ ተከናውኗል፡፡ በሩብ ዓመቱ 5% የሚሆን ፊዚካል ሥራ
ለማከናወን ዕቅድ የተያዘ ቢሆንም የግንባታ ሥራው አልተጀመረም፡፡ ለዚህ አፈፃፀም ማነስ በዋነኛነት የዲዛይን ዝግጅት
በሚፈለገው ደረጃ አለመከናወኑ ነው፡፡

ስትራቴጂካዊ ግብ 8:- የኮርፖሬሽኑን ትርፋማነት ዘላቂ እንዲሆን ማድረግ፤

8.1 ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ሕንፃ ጐን የሚገነባ አዲስ የቢዝነስ ህንፃ

በኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ግቢ ውስጥ የሚገነባው ባለ 2 ዐ ፎቅ ህንፃ ግንባታን በተመለከተ የተለያዩ አይነት
ዲዛይኖች ቀደም ሲል ተጠናቀዋል፡፡ ሆኖም በስትራክቸራል ዲዛይን ውስጥ የመሠረት ዓይነት ለመወሰን እንዲቻ የአፈር
ምርመራ ሥራውን ለማከናወን የአፈር ቁፋሮ ምርመራ ድርጅት እንዲቀጠር ተደርጓል፡፡ በዚሁ መሰረት ከኮንሰትራክሽን
ዲዛይን ድርጅት ጋር ውል ተፈፅሟል፡፡ ነገር ግን በቦታው ላይ የሚቆፈሩ ሦስት ጉድጓዶችን በተመለከተ በግቢው ውስጥ
ቀደም ሲል በተሠሩ ሰርቪስ መደዳ ቤቶች ላይ በማረፉ ምክንያት እና እነዚህ ቤቶች እያሉ የአፈር መቆፈሪያ ማሽኖች
በሚፈለገው ደረጃ መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ምክንያት ቤቶች እንዱፈርሱ ከተደረገ በኋላ የአፈር ቆፎሮ ሥራው
እንዲከናወን ለማድረግ የቀፋሮ ጊዜው እንዲሸጋሸግ ሆኗል፡፡ በሩብ ዓመቱ ዲዛይኑን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ዕቅድ
የተያዘ ቢሆንም አምስት ዲዛይኖች የተዘጋጁ ቢሆንም የአፈር ቁፋሮ ስራ በመዘግየቱ የስትራክቸራል ዲዛይኑ
አልተጠናቀቀም፡፡

8.2 የኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ

የኮርፖሬሽኑ ዋና መሰሪያ ቤት ለመገንባታ እንዲቻል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ክልል ውስጥ 3
ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ርክክብ በተፈፀመው መሰረት የአፈር ጠረጋ ሥራ ተናከውኗል፡፡ በቦታ ላይ የከተማው ማስተር ፕላን
በሚፈቅደው መሠረት ባለ 2 ዐ ፎቅ ህንፃ ለመገንባት እንዲቻል ዮሐንስ አባይ ከተባለ አገር በቀል አማካሪ ኩባንያ ጋር
ውል ተፈፅሞ የመጀመሪያ ደረጀ ዲዛይን ተዘጋጅቷል፡፡ በዚሁ ዲዛይን ዝግጅት ላይ እንደታየው አጠቃላይ በህንፃው

12
ውስጥ ከዲዛይን ጀምሮ መካተት ስላለባቸው አገልግሎቶች ማለትም በህንፃው ውስጥ መካተት ስላለባቸው የቢዝነስ
ቦታዎች ስፋት፣ ስለ ህንፃው ዘመናዊነት፣ የአካባቢ ጥበቃ መስፈርት ስለማሟላቱ፣ አዳዲስ ቴክኖለጂዎች ለመጠቀም
የሚያስችል ስለመሆኑ፣ ስለ ኪነ-ሕንፃው አጠቃላይ እይታ፣ የኮንስትራክሽን ሂደቱንና በአጭር ጊዜ እንዴት ተገንብቶ
ሊያልቅ የሚቻል ስለመሆኑ፤ በአጠቃላይ በዲዛይን ወቅት መካተት ያለባቸውን ሃሣቦች ተገልፆ የዲዛይን የማሻሻያ ሥራ
በመከናወን ላይ ነው፡፡ ይህም ሆኖ በቀጣይ የመጀመሪያ ደረጃ ዲዛይን ለማጠናቀቅ የሚያስችል የባለድርሻ አካላትና
የኮርፖሬሽኑ የተለያዩ ስራ ክፍሎች በተገኙበት የጋራ ወይይት የሚካሄድበት ይሆናል፡፡

ስትራቴጂካዊ ግብ 10:- በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መሰል ተቋማት እና የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር
ቅንጅታዊ አስራር ማሳደግ፤
10.1 የኮርፖሬሽኑ ልማት አጋር ድርጅቶች የሚያስፈልገውን የቴክኒክና ገንዘብ ድጋፍ ዳሠሣ ማድረግና ቅንጅት መፍጠር

በኮርፖሬሽኑ በኩል ግኑሽነት ካላቸው መካከል Fc ከተባለው የልማት አጋር ድርጅት ጋር በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ
ለሚሠሩ ሠራተኞች ቤት አቅርቦት በተመለከተ የተጠቃለለ የስትራቴጂ ጥናት ለማከናወን እንዲቻል የጋራ መግባቢያ
ስምምነት ተፈፅሞና የመጀመሪያ ደረጃ ጥናቱ ተጠናቆ በአገር አቀፍ ደረጃ በቤት ልማት ረገድ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ
ተብለው የተለዩ መስሪያ ቤቶችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሣተፋበት አውደ ጥናት ተካሒዷል፡፡ በዚሁ አውደ
ጥናት የቀረበው ቀደም ሲል ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ሠራኞች ተከናውነው የነበሩ ልዩ ልዩ ጥናቶች፣ እስከ አሁን ድስር
ከባንኮች ጋር የተደረጉ ሙከራዎች፣በኢንዱስትሪ ፖርኮች ውስጥ የገቡ ባለሐብቶች የተከናወኑ ሥራዎችና ያጋጠሟቸው
ችግሮች እንዲሁም የሌሎች አገሮች የተገኙ ተሞክሮዎችን መሰረት በማድረግ ከሕግ ማዕቀፍ፣ የድጐማ ማዕቀፍ፣
መሬትና መሰረተ ልማት አቅርቦት የቤቶች ዲዛይንና ቴክኒካዊ ጉዳዮች፣ የፋይናንሲንግ ሁኔታ ፣ የፓሊሲ ጉዳዮች እና
በመሳሰሉት ላይ ከአውደ ጥናቱ የተገኙ ግብዓቶችን መሰረት በማድረግ ጥናቱ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

IFC ከተባለ የፋይናንስ አበዳሪ ተቋም ጋር በተደረገው የጋራ መግባቢያ ስምምነት መሠረት ለኢንዱስትሪ ፓርክ
ሠራተኞች ቤት ለማቅረብ የሚያስችሉ አማካሪዎች በጥናት ሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡ በጥናቱ መሠረት ከተገነቡ ፓርኮች
መካከል በቅድሚያ መታየት ያለባቸው የቦሌ ለሚ እና የሃዋሣ ኢንዱስትሪ ፓርኮተ መሆናቸውን ታይቷል፡፡ ለነዚሁ
ፓርኮች የቤት አቅርቦቱ አጠቃልይ ማዕቀፍን በተመለከተ ጥናቱ ሲጠቃለል ለሞዴል ግንባታው የፋይናንስ አቅርቦቱ
የሚመቻችበት ሁኔታ የሚካተት ይሆናል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች አማራጭ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በተመለከተ በፋብሪካ ሼዶች ጣሪያ ላይ ከፀሐይ ብርሃን የኤሌክትሪክ
ኃይል ለማመንጨትና ለማቅረብ የሚያስችል Frontier Energy ከተባለው አጋር የልማት ድርጅት ጋር በተመረጡ ኢንዱስትሪ
ፓርኮች ከፀሐይ ብርሃን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ከኮርፖሬሽኑ ጋር በተደረገው ስምምነት መሰረት በአዳማ እና ድሬዳዋ
ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሳይት ምልከታውን መነሻ በማድረግ ረቂቅ የአዋጭነት ጥናት ተከናውኗል፡፡ ጥናቱን መነሻ በማድረግ
በቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ትራንስፎርመሮች እና ኢነርጂ
አጠቃቀም መረጃ እንዲሁም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል በአዳማ ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘው ሰብስቴሽን
መረጃዎች ተደራጅቶ ቀርቧል፤ አስተያየቶችም ለ Frontier Energy እና አማካሪ ድርጅቱ ምላሽ እንዲሰጥበትና ጥናቱ የበለጠ
እንዲዳብር በፅሑፍ ቀርቧል፤

10.2 ከከተማ አስተዳደሮችና መሠረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሠራርን መፍጠር
በአገር አቀፍ ደረጃ የተለያዩ መሰረተ ልማት ተቋማትን በወቅቱና በጥራት ማቅረብ ብሎም ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ዉጤታማነትን ለማረጋገጥ
መቻል አንዱ የትኩረት አቅጣጫችን በመሆኑ በዘርፉ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር የተናበበ ዕቅድ እንዲኖረንና በአግባቡ የተጠናከረና ቅንጅቱ
የተረጋገጠ አሰራር እንዲኖር ለማስቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር ለሚከናወኑ ተግባራት የጋራ ዕቅድ እንዲኖር ከተቀናጀ መሰረተ ልማቶች

13
ማስተባበሪያ ኤጀንሲ ጋር 2014 በጀት ዓመት የጋራ ዕቅድ ተይዟል፡፡ እንዲሁም በጋራ ዕቅዱ ላይ በጥናትና ዲዛይን ደረጃ
በመገምገም የጋራ መናበብና ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በሩብ ዓመቱ የተያዘዉ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ተከናዉኗል፡፡

11. ተቋማዊ አቅም ግንባታ ስራዎች፤


በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ዘርፍ ከተቋም አቅም ግንባታ አንፃር ዕቅድ የተያዘባቸው የአደረጃጀት ማሻሻያ፣ የተለያዩ
ጥናቶችን ማከናወን፣ የአሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችሉ የአሠራር ማኑዋሎችና መመሪያዎች ዝግጅት፣ ሥልጠናዎች፣
የዶክመንቴሽን ማዕከል እንዲሁም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመኖሪየ ቤት ግንባታ ለማከናወን የሚያስችሉ
ዝግጅቶች የተያያዙ ሥራዎች ያካትታል፡፡

11.1 የተለያዩ ስልጠናዎችን እንዲሠጡ ማድረግ፤


የሠው ኃይል አቅም ግንባታ ሥልጠናን በተመለከተ ከፕሮጀክቶች ማጠቃለያ ጋር በተያያዘና ከባለድርሻ አካላት ጋር መከናወን
ሥላለባቸው ተግባራት፣ በፕሮጀክት ማጠቃለያ ወቅት መዘጋጀት ሥላለባቸው ሪፖርቶች በየፕሮጀክቶች ያልተከናወኑ ተግባራት
ስለሚፈጠሩብትና መቋርጥ ያለባቸውን ሥራዎች ከኮንትራት ጋር ያለውን ሁኔታ፣ ከፕሮጀክቶች ዋስትና ጋር የተያያዙ
ጉዳዮች፣ የማኑዋል ዝግጅቶች፣ የተገነቡ ፓርኮች ዲዛይን የማሠባሠብ፣ የቴስቲንግና ኮሚሽኒንግ ሥራዎች አካሄድ፣
የማጠቃለያ ሠርተፊኬት አሠጣጦችን በተመለከተ ለ 12 ባለሙያዎች በራስ ኃይልና ከአማካሪና ሥራ ተቋራጮች ጋር በመሆን
ስልጠና እንዲሠጥ ተደርጓል፡፡

11.2 የኮርፖሬሽኑ ስራዎች የሚያግዙ እና የሚያቀላጥፉ ማንዋሎችን ማዘጋጀት፤


የአሠራር ሥርዓትን በተመለከተ በዘርፉ ሥር የሚገኙ መምሪያዎች በሚከታተሏቸው ዋና ዋና ተግባራትን ያካተተ ይኸውም
ከዲዛይን፣ ኮንትራት አስተዳደርና ፕሮጀክቶች ክትትል ጋር የተያያዙ ሂደቶችን፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚከናወኑ የቅንጅት
ሥራዎች፣ የቴሌኮምና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትና ርክክብ ሥራዎች፣ የከርሰ ምድር ውሃ ጥናት፣ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮና
ውሃ አጠቃቀም አቅርቦት፣ የመሬት ዝግጅትና ማስተርፕላን ጥናቶች ጋር የተገናኙ የአሠራር ሥርዓቶችና ሂደቶችን
የሚያመላክቱ ዝርዝር አሠራሮችን የሚያሰቀምጡ አራት የተለያ ማኑዋሎች ዝግጅት በመከናወን ላይ ነው፡፡ ከአደረጃጀት ጋር
በተያያዘ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ዘርፍ በኩል ከሚታዩ ሥራዎች መካከል የኢነርጂ፣ ኦዲትና ጥገና ጋር የተያያዙ
ሥራዎች፣ የዲዛይን ማማከር ሥራ፣ ግንባታ ማከናወን የሚያስችል የሥራ ተቋራጭም ሽርክና አደረጃጀት፣ ከመኖሪያ ቤቶችና
ሪልስቴት ልማት ጋር የተያያዙ ሥራዎች፣ በሌሎች መስሪያ ቤቶችና ተቋማት አማካኝነት በጀት ተይዘው የሚገነቡ ህንፃዎችን
መሠረተ ልማት ግንባታ በተመለከተ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል አደረጃጀት መፍጠር
በተመለከተ ረቂቅ ሠነድ ተዘጋጅቶ የማሻሻያ ሥራ ተከናውኗል፡፡

በኮርፖሬሽኑ አማካኝነት የተገነቡ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተመለከተ ከግንባታ ቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በሂደት የተደረጉ ህጋዊ
የጽሑፍ ልውውጦችና መፍትሄዎች፣ ዲዛይኖች፣ ፎቶዎች፣ ጥናቶች የተለያዩ ጽሁት፣ ማኑዋሎች፣ ከተለያዩ አገራት የተደረጉ
ጉብኝቶች የተዘጋጁ ሪፖርቶች ወዘተ…. ያካተተ የዶከመንቴሽን ማዕከል ለማደራጀት ሠነዶች የማሰባሰብ ሥራ በመከናወን
ላይ ነው፡፡ ከዚሁ በተጨማሪ በተለያዩ አገሮች የተገነቡ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚያሣዩ ፅሁፎችና መፅሐፎች የማሣተምና
ማሠባሠብ ሥራ በመከናወን ላይ ነው፡፡ በዶክመንቴሽነ ማዕከል የሚገኙ ሠነዶችና ዲዛይኖችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ
ለማድረግ በሶፍት ኮፒ የማዘጋጀትና የማሰባሠብ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶች በመዘጋጀት ላይ ነው፡፡

11.3 የኮርፖሬሽኑ የመሠራር ስርዓት የሚያቀላጥፉ ጥናቶችን ማካሄድ፤


የመሬት ይዞታ ለማረጋገጥ እንዲቻልና በአግባቡ ለመከታተል እንዲሁም ዘመናዊ የሆነ የቅየሳ ስራዎችን መነሻ በማድረግ
የመሬት ዝግጅትና ርክክብ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡ በእነዚህ የቅየሳ መረጃዎች የቦታዎችን ይዞታ መለየት፣
ይህንንም ቦታ በተለየው መሰረት ለባለሀብቶች የማስረከብ በዚህም ፍትሀዊ በሆነ መንገድ የቦታ አጠቃቀምንም ጭምር
ያጠቃለለ ስራ ይከናወናል፡፡ በተጨማሪም መሬትን በህግ ስርዓት እውቅና የሚሰጥበት ዘመናዊ በሆነ አሰራር ተግባራዊ
የሚደረግበት ይህንንም ተከትሎ መሬትና መሬት ላይ የሰፈረ ንብረት የሚመዘገብበት የካዳስተር ስርዓት መዘርጋት

14
አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በካዳስተር ስርዓት የጂኦ-ካዳስተር ፕላኖች ማዘጋጀት፣ የፋብሪካ ህንፃዎች፣ የአገልግሎት መስጫ
ተቋማት እና የፊዚካል መሰረተ ልማቶች የሚመላከቱበት፣ የህጋዊ ይዞታ መብቶችን ለማረጋገጥ እንዲቻልና ዘመናዊ የሆነ
መረጃ ጭምር ለማደራጀት አማካሪ ተመርጦ በሁለቱም ወገን የውል ስምምነት ተፈርሞ የመነሻ ሪፖርት እና ሌሎች
ስራዎች በማቅረብ በኮርፖሬሽኑ ባለሙያዎች ግብአት መሰጠቱ በባለፈው በጀት ዓመት ሪፖርት መደረጉ ይታወሳል፡፡
በመሆኑም በሩብ ዓመት 30 በመቶ ለማከናወን ታቅዶ በፍላጎት ትንተና ጥናት ላይ (RAD) የተካተተው የሲስተም ጥናት
ላይ አስተያየት የተሰጠ ሲሆን ሲስተሙ ወቅታዊ ሪፖርት ማውጣት እንዲችል ግብአት የሚሆን ዝርዝር ጥናት ቀርቧል፡፡
በተጨማሪም ጥናቱ በፓይለት ተግባራዊ በሚደረግባቸው ሀዋሳና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የቅየሳ ስራ ተከናውኗል፡፡
አፈፃፀሙ 100% አሳይቷል፡፡

11.4 ለኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ቅድመ ዝግጅቶች ማከናወን፤


የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን በተመለከተ ቀደም ሲል ተዘጋጅቶ የነበረውን ዲዛይን በመመልከት ወቅታዊ
የሆነ የዋጋ ግምት የማዘጋጀት ሥራ ተከናውኗል፡፡ ለቤቶቹ ግንባታ የሚውለውን መሬት በተመለተ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ
ፓርክ ክልል ውስጥ ከተመረጡ ሶስት ቦታዎች መካከል ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር በመሆን አንዱ ተመርጦ ይህንኑ ታሣቢ ተደርጐ
ዲዛይኑ የከናወነ ነው፡፡ ሆኖም ይህ የተመረጠ ቦታ በአካባቢው ነዋሪዎች ካሣ ይገባኛል ጥያቄ በማንሣታቸው ከሚመለታቸው
ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ውይይት በመደረግ ላይ ነው፡፡ ለቤቶች ግንባታ የፋይናንስሲንግ ቀጠይ የግንባታ ሂደትን
በተመለከተ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችሉ ውይይቶች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡

በሩብ ዓመቱ ያጋጠመ ችግርና የመፍትሔ ኃሣብ

ያጋጠመ ችግር

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት መሰረታዊ ከሆኑ ችግሮች መካከል አንዱ የቦታ ይዞታ ይገባኛል ጥያቄ ነው፡፡ በዚህ ረገድ
በሁሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሚባል ደረጃ ወሠንን ለማስከበር የሚያስችሉ የአጥር ግንባታ ሥራ ለማከናወን፣ የውሃ
መስመር ዝርጋታ ሥራ፣ የኤሌክትሪክ መስመሮችን ለመዘርጋት፣ ለባለሐብት ርክክብ የሚፈፀምባቸው ቦታዎች፣ መዳረጃ
መንገድ ግንባታዎችና በአጠቃላይ ኮርፖሬሽኑ በሕጋዋ አግባብ በተረከባቸው ቦታዎች ከይዞታ ይገባኛል ጥያቄ ጋር
በተያያዘ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ በዚሁ መሠረት በዕቅድ የተያዙ ሥራዎችነ ለማከናወን አሉታዊ የሆኑ ተፅዕኖ
አሣድሯል፡፡

የመፍትሄ ኃሣብ

በሁሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ የአካባቢና የከተማ አስተዳደር አካላት ለውጥ በመደረግ
ላይ በመሆኑ አዲስ ከሚመደቡ የአመራር አካላት ጋር ውይይቶችን በማካሄድ የጋራ ዕቅዶችን በማዘጋጀት ማስፈፀም
ያስፈልጋል፡፡ በቀጣይ ነፃ በሚደረጉ መሬቶች ላይ በጊዜያዊም ቢሆን አጥር ግንባታዎችን ከየኢንዱስትሪ ፓርኮች
ኃላፊነት ተሠጥቶ እንዲታጠር ማድረግ፣ በአጠቃላይ ከይዞታና ወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ በሕግ መምሪያ፣ በመሬት
ባንክና ማስተርፕላን መምሪያ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የፀጥታና ደህንነት መምሪያ እንዲሁም በየኢንዱስትሪ ፓርኮች
የሚገኙ ሥራ አስኪያጆች በጋራና በተቀናጀ አግባብ ሊከታተሉና ሊያስፈጽሙበት የሚያስችሉበት የአሠራር ሥርዓት
መዘርጋት አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ከዚሁ በተጨማሪ ቀደም ሲል በኮርፖሬሽኑ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በኢንዱስትሪ
ፓርኮች አጠቃላይ ልማት ላይ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጡት አነስተኛ ወጪ የሚያስከትሉ የካሣ ጥያቄዎችን ምላሽ
በመስጠት ልማቱን ማስቀጠል የሚጠበቅ ይሆናል፡፡

15

You might also like