You are on page 1of 12

በደቡብ ኢፓልኮ የፕሮጀክቶች ሪፖርት

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የፕሮጀክቶች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት

ሚያዝያ 2012 ዓ/ም


ሀዋሣ

ሚያዝያ 2012 ዓ.ም ሀዋሳ Page 1


በደቡብ ኢፓልኮ የፕሮጀክቶች ሪፖርት

 የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓረክ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ስራ በተመለከተ፡-

በይርጋዓለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ስራን በዚህ ግማሽ ዓመት ሙሉ

ለሙሉ ለማጠናቀቅ ታቅዶ ከግንባታዎቹ ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ (የአስተዳደር ህንጻ፣ የስልጠና ማዕከል፣

ሪቴል ስፔስ፣ ክሪች፣ ኢንፎርሜሽን ኪዮስክ፣ ሁለት የትራንስፎርመር ማስቀመጫ፣ አራት ጊዜያዊ የትራንስፎርመር

ማስቀመጫ እና የፓርኩ ዙሪያ አጥር) ግንባታዎች ሙሉ በሙሉ ተጠናቆና ጊዜያዊ ርክክብ ተደርጎ ለአገልግሎት ዝግጁ

ሆነዋል፡፡

ጊዜያዊ ርክክብ የተደረገ ሪቴል ስፔስ ጊዜያዊ ርክክብ የተደረገ የአስተዳደር ህንጻ

ጊዜያዊ ርክክብ የተደረገ የስልጠና ማዕከል ጊዜያዊ የኢንፎርሜሽን ኪዮስክ ግንባታ ሂደት በከፊል

የሼድ ግንባታ ስራ በተመለከተ

አራት የማምረቻ ሼዶች (የአቮካዶ፣ የቡና፣ የማር እና አትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ) አለማቀፍ ደረጃቸውን ጠብቀው

የግንባታ ሥራቸው በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የአቮካዶ ማቀነባበሪያ ሼድ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ
SUNVADO ORGANIC AVOCCADO OIL MANUFACTURING PLC የሙከራ የምርት ስራውን ባለፈው
ክረምት አጠናቆ ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት ሥራ ገብቶ በአራት ዙር የአቮካዶ ዘይት በማምረት የውጪ ምንዛሪ እያስገኘ
ይገኛል፡፡

ሚያዝያ 2012 ዓ.ም ሀዋሳ Page 2


በደቡብ ኢፓልኮ የፕሮጀክቶች ሪፖርት

ጊዜያዊ ርክክብ የተደረገ የአቮካዶ ዘይት ማቀነባበሪያ ሼድ ግንባታ በከፊል

የፓርኩ የውሃ አቅርቦት ሥራ በተመለከተ

ለይርጋዓለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የውሃ አቅርቦት ግንባታ ስራ 100% ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን ውል
ከተገባው 9 ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ስድስቱ ጉድጓዶች ተቆፍረው የ 24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡
በተጨማሪም የፓርኩን የውሃ አቅርቦት ከፍ ለማድረግ ከፓርኩ ውጪ አምስት ጉድጓዶችን ለማስቆፈር በታቀደው መሰረት ማቴሪያል
ሳይት ገብቶ ስራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር ግንባታ በከፊል

 የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን በተመለከተ

የፓርኩ የመንገድ ዳር መብራትን በሚመለከት ለፓርኩ የሚስፈልገው 2 አይነት ፖል በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የመንገድ ዳር
መብራት 20 ሜትር ርዝመት እና ባለ 7 ሜትር ሙሉ በሙሉ ዕቃዎቹ ሳይት ገብተው በአሁኑ ጊዜ እየተገጠሙ ይገኛሉ፡፡
በመሆኑም ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በተጠናቀቁ መንገዶች አብዛኛው የመንገድ ዳር መብራት አገልግሎት መስጠት
ይጀምራል፡፡

ሚያዝያ 2012 ዓ.ም ሀዋሳ Page 3


በደቡብ ኢፓልኮ የፕሮጀክቶች ሪፖርት

የመንገድ ዳር መብራት ፖሎች

ፓርኩ በአሁኑ ጊዜ 2 ሜጋ ዋት ሃይል ቀርቦለት ቀድሞ የገባው እንዱስትሪ ስራ ላይ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ለሌሎች ኢንዱሰትሪዎች
(ለማር፣ ለወተትና ለቡና ማቀነባበሪያዎች እና ለሌሎች የአስተዳደር ህንጻዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ
በግንባታ ላይ ለሚገኙ 7 ሼዶች የ 8 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እና ትራንስፎርመር ጥያቄ ለደቡብ ክልል ኤሌክትሪክ
ኃይል አገልግሎት ጥያቄ ቀርቦ አዎንታዊ ምላሽ ተገኝቶ በአገልግሎቱ የ 8 ሜጋ ዋት ኃይል አቅርቦት ስራ በሂደት ላይ
ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ የፓርኩን የኤሌክትሪክ አቅርቦት በዘላቂነት ለማሟላት ከፌደራል ኤሌክትሪክ ሃይል ጋር በመተባበር
የሳብስቴሽን ግንባታ ስራ ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

 የፓርኩ የሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ስራ በተመለከተ፡-

የይርጋዓለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ 2 ኛ ምዕራፍ የግንባታ ሥራ በዚህ በጀት ዓመት 100% ለማጠናቀቅ ታቅዶ ግንባታው
እየተከናወነ ሲሆን ከግንባታ ሥራዎቹ ማለትም የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ፣ የሳይት ወርክ ሥራ፣ የውስጥ
ኤሌክትሪክ፣ ውሃና ሳኒቴሪ፣ የአፈር መደገፊያ (Retaining Wall)፣ የሳይት ማስተካከያ ሥራዎችና ሌሎች ግንባታዎች
ያሉት ሲሆኑ ከእነዚህም ስራዎች ውስጥ የሳኒቴሪና የውሃ መስመር ዝርጋታ ስራ ቅድሚያ ለተሰጣቸው ለአቮካዶ፣ ለማር

ሚያዝያ 2012 ዓ.ም ሀዋሳ Page 4


በደቡብ ኢፓልኮ የፕሮጀክቶች ሪፖርት

እና ለ 5 ቱ ህንጻዎች የተጠናቀቀ ሲሆን 3 ኪ.ሜ በላይ የአስፓልት ማንጠፍ ስራ ተከናውኗል፡፡ የሳይት ማስተካከልና የአፈር
መደገፊያ ግንብ ሥራ በተቀመጠው ማስተር ፕላን መሰረት ከሌሎች ስራዎች ጋር በተጓዳኝ እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡
በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ 2 ኛ ምዕራፍ ፊዚካል አፈጻጸም በአማካይ 80 በመቶ ደርሷል፡፡

የመንገድ ግንባታ ስራ ሂደት በከፊል

የሪቴኒንግና ሳይት ማስተካከል ስራ በከፊል

 የፓርኩ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ግንባታ ስራን በተመለከተ

የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የ 2 ኛ ምዕራፍ ግንባታ ስራ ዋናው ኮንትራትን እና አስፈላጊ የሆነ
የተጨማሪ ስራ ውለታን ያካተተ ነው፡፡

እስከዚህ ወር ከዋናው ኮንትራት የውስጥ ለውስጥ መንገድ 3 ኪ.ሜ የአስፋልት ንጣፍ ከመሰራቱም በተጨማሪ የውስጥ
ለውስጥ መንገድ አካል የሆነው የሰብ ቤዝ፣ ቤዝ ኮርዝ የማንጠፍ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ የአስፓልት መንገድ ንጣፍ
ፕሮጀክትን ለማጠናቀቅ ለአስፓልት ንጣፍ ግብዓት የሆነው ጥሬ ዕቃ ሬንጅ (ቢትመን) ችግር እንዳይገጥም ስራ ተቋራጩ
ቀደም ብሎ እንዲያቀርብ ተደርጓል፡፡ በቀጣይም የሚያስፈልገውን ቢትመን እንዲያቀርብ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

ሚያዝያ 2012 ዓ.ም ሀዋሳ Page 5


በደቡብ ኢፓልኮ የፕሮጀክቶች ሪፖርት

የፓርኩ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ግንባታ በከፊል

የሳይት ማስተካከልና የአፈር መደገፊያ ግንብ ሥራ በተቀመጠው ማስተር ፕላን መሰረት ከሌሎች ስራዎች ጋር በተጓዳኝ
እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ 2 ኛ ምዕራፍ የዋናው ኮንትራት ሥራዎች ፊዚካል አፈጻጸም በአማካይ 76
መቶ ደርሷል፡፡

 የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ 7 ተጨማሪ የማምረቻ ሼዶች ግንባታ ስራ


በተመለከተ

የተጨማሪ ሰባት ሼዶች ግንባታ ስራዎች በተመለከተ (የወተት፣ የቡናና የፓኬጂንግ) ግንባታ ስራዎች 80% ለማጠናቀቅ

ታቅዶ የሁሉም ብሎኮች የመሰረት ስራ ተጠናቆ የስቲል ስትራክቸሩን ምርት ከአገር ውጪ ተመርቶ ወደ ሃገር ውስጥ

ለማስገባት የውጭ ምንዛሪ ችግር ያጋጠመ ቢሆንም በክልሉ መንግስት እና በጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ከፍተኛ አስተዋጽኦ

የውጪ ምንዛሪ ችግር ተቀርፎ በአሁኑ ጊዜ የስቲል ስትራክቸር ምርት ስራ እየተጠናቀቀ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ወር

መጨረሻ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ ወደ አገር ውስጥ ይገባል፡፡ አጠቃላይ የግንባታ ስራው 55 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡ ይህ ዕቅድ

አፈጻጸም አነስተኛ የሆነው የውጭ ምንዛሪ ዘግይቶ በመፈቀዱ ምክንያት ነው፡፡

በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ሼዶች ግንባታ ስራ በከፊል

 የመኖሪያ ህንጻዎች ግንባታ ስራዎችን በተመለከተ

ሚያዝያ 2012 ዓ.ም ሀዋሳ Page 6


በደቡብ ኢፓልኮ የፕሮጀክቶች ሪፖርት

በፓርኩ ውስጥ በፋይናንስ እጥረት ምክንያት ዘግይቶ የተጀመረው ለ 80 የፓርኩ ሰራተኞች አገልግሎት እንዲሰጥ እየተሰራ የሚገኘው 5
ቪላ፤ 3 ባለ ሁለት መኝታ እና 3 ባለ አንድ መኝታ፣ የፖሊስ ስቴሽን፣ የእሳት አደጋ ጣቢያ እና ክሊኒክ ግንባታ ሥራው የተጀመረ
ሲሆን በዚህ ሩብ ዓመት የግንባታው አፈጻጸም 15 በመቶ ደርሷል፡፡

የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ በከፊል

 የፓርኩ የመዳረሻ መንገድና የዋና መግቢያ በር ግንባታ ስራ በተመለከተ፡-

የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ 1.5 ኪ/ሜ የመዳረሻ መንገድና የዋና መግቢያ በር ግንባታ ሥራ 70%
ለማድረስ ታቅዶ የመንገድ ስራው የአፈር ቆረጣ፣ የአፈር ሙሌት፣ የውሃ መውረጃ ቦይ ግንባታና የቦክስ ካልቨርት ግንባታ
ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን የፓርኩ ዋና መግቢያ በር ግንባታ ሥራ የመሰረት ሥራው ተጠናቆ የስትራክቸር ሥራ የኢልቬሽን
ኮለን፣ ቢም፣ የኮንክሪት ግድግዳ ግንባታ ሥራ በመሰራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በአጠቃላይ የግንባታ ስራው እስከ መጋቢት
30/2012 ዓ.ም ድረስ አፈጻጸሙ 65 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

የእግረኛ መንገድ ንጣፍ ግንባታ ስራ እና 400 ሜትር በላይ የአስፓልት ንጣፍ ስራ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት ያለቀ ሲሆን
የሶላር የመንገድ ዳር መብራት ፖል ሙሉ በሙሉ ተመርቶ ወደ ሳይት ለመግባት በዝግጅት ላይ ነው፡፡

ሚያዝያ 2012 ዓ.ም ሀዋሳ Page 7


በደቡብ ኢፓልኮ የፕሮጀክቶች ሪፖርት

ከዚህ በላይ እንዳይሰራ በሳይት ላይ ያጋጠመው ችግር በዞኑ በኩል በፍጥነት ባለመፈታቱ መዳረሻ መንገድ አካል የሆነው
400 ሜትር የሚደርስ መንገድ በዞኑ የወሰን ማካለል ችግር በተፈጠረ ቅሬታ ሙሉ በሙሉ የቆመ በመሆኑ ከዚህ በተሻለ
መስራት አልተቻለም፡፡

የመዳረሻ መንገድ አስፓልት እና የዋና መግቢያ በር ግንባታ በከፊል

 የፓርኩን የአረንጓዴ ልማትና የማስዋብ ስራ በተመለከተ፡-


የይርጋለም የተቀናጀ ግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የአረንጓዴ ልማትና የማስዋብ ሥራ በ 67 ማህበራት እየተሰራ የሚገኝ
ሲሆን ይህም ስራ ለበርካታ የአካባቢ ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረ ስራ ነው፡፡ በዚህ ወር 4 ሄክታር የአረንጓዴ ልማት
ሥራዎች ለመስራት ታቅዶ በዚህ ሩብ ዓመት ብቻ 6 ሄክታር የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ሙሉ በሙሉ ተከናውኗል፡፡ይህ
ስራም በአሁኑ ጊዜ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ሚያዝያ 2012 ዓ.ም ሀዋሳ Page 8


በደቡብ ኢፓልኮ የፕሮጀክቶች ሪፖርት

የአረንጓዴ ልማት ሥራ በከፊል

 ለህብረተሰቡ የሚያገለግል የጠጠር መንገድ ግንባታ ስራ በተመለከተ፡-

የይርጋለም የተቀናጀ ግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የዙሪያ አጥር በመታጠሩ ምክንያት ቀደም ሲል ፓርኩን አቋርጦ
የሚያልፈው የአካባቢው ህብረተሰብ የመተላለፊያ መንገድ መዘጋት ስላለበት ለአካባቢው ህብረተሰብ አገልግሎት
የሚውል ከ 5 ኪሜ በላይ ጥርጊያ የጠጠር መንገድ በመገንባት ለአገልግሎት እንዲውል ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም በሌላ
በኩል ያለውን ቀሪ የህብረተሰብ መተላለፊያ መንገድ ለመስራት የቅየሳ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የገጠር ለውጥ ማዕከላት (RTC) ግንባታ ስራን በተመለከተ፡-

 የዲላ ጪጩ የገጠር ለውጥ ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ስራ፡-

ሚያዝያ 2012 ዓ.ም ሀዋሳ Page 9


በደቡብ ኢፓልኮ የፕሮጀክቶች ሪፖርት

የዲላ ጪጩ የገጠር ለውጥ ማዕከል (RTC) የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ስራን 100% ለማጠናቀቅ ታቅዶ የ Combined PEB

/warehouse/ ሼድ ግንባታ ጨምሮ 10 የተለያዩ ህንጻዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል፡፡ በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ
የመጀመሪያ ምዕራፍ ፊዚካል አፈጻጸም 97% ላይ ይገኛል፡፡
 የዲላ ገጠር ለውጥ ማዕከልሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ስራ በተመለከተ

የዲላ ጪጩ የገጠር ለውጥ ማዕከል (RTC) ሁለተኛ ምዕራፍ የመሰረተ ልማት ግንባታ ሥራ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን
በአካባቢው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሳቢያ የግንባታ ስራው በተቀመጠው የድርጊት መርሀ-ግብር መሰረት መጠናቀቅ
ባይችልም በአሁኑ ጊዜ የግንባታ ሥራዎቹ ማለትም የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ፣ የሳይት ሥራ፣ የውስጥ
ኤሌክትሪክና ሳኒቴሪ፣ የአፈር መደገፊያ(Retaining Wall), የፓምፕ ሀውስ/pump house/ ሥራዎችና ሌሎች ግንባታዎች
እየተከናወኑ ሲሆን አጠቃላይ አፈጻጸሙም በአማካይ 75 በመቶ ደርሷል፡፡
 የዋና እና ሁለተኛ መግቢያ በር ግንባታ ስራን በተመለከተ
የዲላ ገጠር ለውጥ ማዕከል የዋና መግቢያ በር ግንባታ የመሰረት ስራው ተጠናቆ ከመሬት በላይ ያለው የኮንክሪት ወለል ግንባታ ስራ

በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡ አፈጻጸሙ 35% ላይ ይገኛል፡፡

 የአረንጓዴ ልማትና የማስዋብ ስራ በተመለከተ፡-

የዲላ ገጠር ለውጥ ማዕከል የአረንጓዴ ልማትና የማስዋብ ሥራ 5 ማህበራት ውል በማስገባት ሳይት ርክክብ ተደርጎ
የአረንጓዴ ልማት ሥራው ተጀምሮ እየተሰራ ይገኛል፡፡

 የዲላ ገጠር ለውጥ ማዕከል የውሃ አቅርቦትን በተመለከተ

ለዲላ ጪጩ የገጠር ለውጥ ማዕከል አገልግሎት የሚውል አንድ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ለመቆፈር ታቅዶ የቁፋሮ ስራው
ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ 2 ኪሜ የመስመር ዝርጋታ፣ የጥበቃ ቤት፣ የትራንስፎርመር ማስቀመጫና የሴፕቲክ ታንክ ግንባታ
እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የግንባታው አፈጻጸም 80% ደርሷል፡፡

የይርጋጨፌ የገጠር ለውጥ ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ስራ

የይርጋጨፌ የገጠር ለውጥ ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ የ Combined PEB /warehouse/ ሼድ ግንባታ ጨምሮ 10 ዓይነት የግንባታ
ሥራዎችን 100% ለማጠናቀቅ ታቅዶ በሳይቱ ረግረጋማነት፣ ከዋናው መንገድ እስከ ሳይቱ ድረስ ያለው መጋቢ መንገድ ባለመሰራቱ እና
የዝናብ ወቅት መብዛት የተነሳ የስራው እንቅስቃሴ በዕቅዱ መሰረት እንዳይከናወን ያደረገ ቢሆንም የመግቢያ መንገዱ ተሰርቶ የሁሉም
ብሎኮች ግንባታ ሥራ በአግባቡ እየተሰራ ይገኛል ፡፡ በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ አማካይ አፈጻጸም 82% ላይ ደርሷል፡፡
 የይርጋጨፌ የገጠር ለውጥ ማዕከል የሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ በተመለከተ

የይርጋጨፌ የገጠር ለውጥ ማዕከል ሁለተኛ ምዕራፍ የመሰረተ ልማት ግንባታ ሥራዎችን ለመሰራት ታቅዶ የሳይቱ
ረግረጋማነት፣ ከዋናው መንገድ እስከ ሳይቱ ድረስ ያለው መጋቢ መንገድ ባለመሰራቱ እና የዝናብ ወቅት መራዘም የተነሳ የስራው

ሚያዝያ 2012 ዓ.ም ሀዋሳ Page 10


በደቡብ ኢፓልኮ የፕሮጀክቶች ሪፖርት

እንቅስቃሴ በዕቅዱ መሰረት እንዳይከናወን ተጽዕኖ የፈጠረ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ችግሩ ተቀርፎ የመንገድ ስራው በአግባቡ እየተሰራ
ሲሆን የመንገድ ስራ፣ የጎርፍ መውረጃ ፓይፕ፣ ከተራራው የሚመጣውን ከፍተኛ ውሃ መቀበያ ዲች፣ ማንሆልና የትራንስፎርመር ግንባታ
ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ አማካይ አፈጻጸም 70 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡
 የመግቢያ በር ግንባታን በተመለከተ
የይርጋጨፌ ገጠር ለውጥ ማዕከል የዋና መግቢያ በር ግንባታ የመሰረት ስራው ተጠናቆ ከመሬት በላይ ያለው የኮንክሪት ግድግዳ ግንባታ

በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡ አፈጻጸሙ 30% ላይ ይገኛል፡፡

 የይርጋጨፌ ገጠር ለውጥ ማዕከል የውሃ አቅርቦትን በተመለከተ

ለገጠር ለውጥ ማዕከሉ አገልግሎት የሚውል አንድ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ለመቆፈር ታቅዶ የቁፋሮ ስራው ሙሉ ለሙሉ
ተጠናቅቆ የመስመር ዝርጋታው እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የስራው አፈጻጸም 70% ደርሷል፡፡

 የበንሳ ዳዬ የገጠር ለውጥ ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ

የበንሳ ዳዬ የገጠር ለውጥ ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ የ Combined PEB /warehouse/ ሼድ ግንባታ ጨምሮ 10 የተለያዩ
አገልግሎት የሚሰጡ ህንጻዎችንና የዙሪያ አጥር ለመስራት ታቅዶ በአካባቢዊ ረግረጋማነትና ዝናባማነት በተያዘለት የጊዜ ገደብ
እንዳይጠናቀቅ ቢያደርገውም በአሁኑ ወቅት የሁሉም ብሎኮች የግንባታ ሥራው በአግባቡ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ
የፕሮጀክቱ አማካይ የግንባታ ስራ ፊዚካል አፈጻጸም 78% ላይ ይገኛል፡፡

 የበንሳ ዳዬ የገጠር ለውጥ ማዕከል የሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታን በተመለከተ


የበንሳ ዳዬ የገጠር ለውጥ ማዕከል (RTC) የሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ሥራዎች (Infrastructure works) ማለትም የውስጥ
ለውስጥ አስፋልት መንገድ፣ የሳይት ሥራ፣ የውስጥ ኤሌክትሪክና የሳኒቴሪ ሥራዎችን ለማከናወን ሳይት ርክክብ ተደርጎ
ስራው በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡ ነገር ግን በሳይቱ ረግራጋማነት የተነሳ ሥራው በሚፈለገው መጠን መስራት አልተቻለም፡፡
አጠቃላይ አፈጻጸም 40 በመቶ ብቻ ነው፡፡

 የመግቢያ በር ግንባታን በተመለከተ


የበንሳ ዳዬ ገጠር ለውጥ ማዕከል የዋና መግቢያ በር ግንባታ የመሰረት ስራው ተጠናቆ ከመሬት በላይ ያለው የኮንክሪት ግድግዳ ግንባታ

በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡ አፈጻጸሙ 30% ላይ ይገኛል፡፡

 የበንሳ ዳዬ ገጠር ለውጥ ማዕከል የውሃ አቅርቦትን በተመለከተ

ለገጠር ለውጥ ማዕከሉ አገልግሎት የሚውል አንድ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ለመቆፈር በታቀደው መሰረት የቁፋሮ ስራው
ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ የውሃ አገልግሎት ለማግኘት የመስመር ዝርጋታው እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የሥራው አፈጻጸም 70
በመቶ ደርሷል፡፡

 የዲላ፣ ይርጋጨፌና በንሳ ዳዬ የገጠር ለውጥ ማዕከላት የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦትን በተመለከተ

ሚያዝያ 2012 ዓ.ም ሀዋሳ Page 11


በደቡብ ኢፓልኮ የፕሮጀክቶች ሪፖርት

ለሶስቱም የገጠር ለውጥ ማዕከላት የኤሌክትሪክ ሀይል ለማሟላት ከኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን የትራንስፎርመርና
የመስመር ዝርጋታን ለማከናወን ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ ተፈጽሞ አገልግሎቱን ለማሟላት ሥራው እየተሰራ
ይገኛል፡፡ የሥራው አፈጻጸም በአማካይ 50% ደርሷል፡፡

 አዳዲስ የአለታ፣ የሞሮቾ እና የቡሌ የገጠር ለውጥ ማዕከላትን በተመለከተ

ኮርፖሬሽኑ በዝህ በጀት ዓመት ሶስት የገጠር ለውጥ ማዕከላት (የሞሮቾ፤ አለታወንዶ እና የቡሌ) የግንባታ ስራ
ለማከናወን በታቀደው መሰረት በዚህ ወር የአጥር ግንባታ ሥራ ለማስጀመር የሳይት ርክክብ ተደርጓል፡፡

ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች

ያጋጠሙ ችግሮች

 በውጭ ምንዛሪ (LC) አከፋፈት መዘግየት ምክንያት የፋበር ኦፕቲክ ኬብል፣ ሚዲየም ቮልቴጅ ኬብል፣ ለፓርኩ
ተጨማሪ የውሃ ሪዘርቫየር፣ የአርቲሲ የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መካኒካል ስራዎች የሚሆን የውጭ ምንዛሪ
አለማግኘት ችግር፣
 የሰብስቴቭን ስራ መዘግየት፣
 ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው የቅንጅት አነስተኛ መሆን፣
 የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በፕሮጀክቶቹ ግንባታ ስራ ላይ ተጽእኖ መፍጠሩ፣
የተቀመጡ የመፍትሔ ሃሳቦች
 የውጭ ምንዛሪ በሚመለከት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ከክልሉ መንግስት
ድጋፍ በማጻፍ ያለውን ችግር ለማስረዳት ጥረት ተደርጓል፡፡
 ሰብስቴሽንን በሚመለከት ከፌዴራል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትኩረት እንዲሰጥ ክትትል የማድረግ ስራ
ተሰርቷል፡፡
 የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማሰግ መድረክ በመፍጠር በችግሮቹ ዙሪያ ላይ በጋራ ለመስራት መስማማት ላይ
ተደርሷል፡፡ ለምሳሌ ሲዳማ ዞን፣ ጌዴኦ ዞን ፣ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ኢንቨስትመንት ኮሚችን. ምግብና መጠጥ
ቁጥጥር ና ክብካቤ ባለስልጣን፣ ኢንዱሰትሪ ሚኒስቴር ፣ UNIDO ወዘተ እና ሌሎች
 በቫይረሱ ምክንያት ስራው እንዳይቆም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅድመ ጥንቃቄ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር
የተቋረጠው ስራ እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡ይህንንም የሚከታተልና የሚደግፍ እንዱሁም የሚያጋጥሙ ችግሮችን
የሚቀርፍ የማኔጅመንት ቡድን ከባለሞያ ጋራ እየተጣመረ በየፕሮጀክቱ ተመድቦ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ
ይገኛል፡፡

ሚያዝያ 2012 ዓ.ም ሀዋሳ Page 12

You might also like