You are on page 1of 7

በቆላማ አካባቢዎች ለግብርና ኢንቨስትመንት የሚዉሉና በህጋዊ መንገድ ያልተያዙ ነጻ

መሬቶችን ለመለየት የተዘጋጀ ቼክ ሊስት

ነሐሴ 2014

መሬት ቢሮ

መግቢያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በገጠር መሬት ግብርና ኢንቨስትመንት ለመሰማራት የሚፈልገው ባለሀብት
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል:: በመሆኑም የመሬት ቢሮ በገጠር ግብርና ኢንቨስመንት የተሰማሩ ባለሃብቶችን

1
የማልማት እንቅስቃሴ በተጨባጭ ሁኔታ በማረጋገጥ ድጋፍና እውቅና በመስጠት ፣ባለሃብቶች የተረከቡት መሬት
ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን በማረጋገጥ ሰፊ የአፈፃፀም ጉድለት ያለባቸውን ባለሃብቶች በወቅቱ የማስተካከያ
እርምጃ በመውሰድ፣
የክልሉን የገጠር ግብርና ኢንቨስመንት መሬት ለሚፈለገው ልማት እንዲውልና ለክልሉ ብሎም ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ
እድገት የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያስገኝ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የአማራ ብሔራዊ ክልል የመሬት ቢሮ ተሻሽሎ በወጣው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 60 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የፕሮፋይል መመሪያ
ቁጥር 12/20012 ዓ.ም አውጥቶ መመሪያውን በማስፈፀም ላይ ይገኛል:: በዚህም መሰረት ባለሀብቱ በአፈፃጸም
ግምገማ ሁለት ጊዜ ዝቅተኛ ውጤት ያመጡ ባለሀብቶችን መሬት ለዉድድር እያወጣ ለአልሚ ባለሀብቶች
እያስተላለፈ ይገኛል፡፡ ቢሮው ይህን ሥራ በንቃት እየሰራ ቢገኝም በህገ-ወጥ መልኩ የተያዙ እና ወደ መሬት ባንክ
ያልገቡ ነፃ መሬቶችን አጣርቶ ለባለሀብቶች በህጉ መሰረት በዉድድር ማስተላለፍ እንደሚገባ ያመነበት በመሆኑ
በቆላማ አካባቢዎች ማለትም በአዊ ዞን (ዚገም ፣ ጃዊ እና አየሁ ገጓጉሣ ወረዳዎች)፤በምዕራብ ጎጃም ዞን (ደቡብ
አቸፈር እና ወንበርማ ወረዳዎች)፣ምዕራብ ጎንደር ዞን (መተማ፣ም/አርማጭሆ እና ቋራ ወረዳዎች) እና
ማዕ/ጎንደር ዞን (ጠገዴ ወረዳ) ያለውን የነፃ መሬት ሀብት ለማወቅ እና ለባለሀብቱ ለማስተላለፍ ይህ ቸክሊስት
ተዘጋጂቷል፡፡

1. የመስክ ስምሪቱ አላማ

ከዞን፣ ከወረዳ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ከቀበሌ አመራርና ባለሙያ ጋር የጋራ ግንዛቤ በመያዝ የነፃ
መሬት ሀብቶችን በመለየት ወደ መሬት ባንክ ማስገባት እና ለባለሀብት እንዲተላለፍ ማዘጋጀት፡፡

2. ለመሥክ ስምሪቱ የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች

በክልል በዞን እና በወረዳ ደረጃ

 በቢሮው ማኔጂመንት የስራውን አስፈላጊነት በተመለከተ ዉይይት ማድረግ

2
 ማዕከላዊ ቦታ በመምረጥ ለሚመለከታቸው ዞንና ወረዳ አመራርና ባለሙያ የግንዛቤ
መፍጠር እና ሥምሪት መስጠት
 ወረዳዎች ለየቀበሌው የመሬት ኮሚቴዎች ፣ የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎች፣ለቀበሌ
የጸጥታ ሀይሎች የግንዛቤ ፈጠራ እና የስምሪት ሥራ መስጠት፡፡
 ለስራው አስፈላጊ የሆነ የሰው ሀይል ፣ በጀት እና ቁሳቁስ ማመቻቸት
 በግንዛቤ ፈጠራው የሚሣተፉ አካላትን መምረጥ

ከክልል

 የመሬት አስተዳደር ባለሙያ


 .የመሬት አጠቃቀም ባለሙያ
 የኢንቨስትመንት ባለሙያ
 የቅየሣ ባለሙያ

ከዞን

 የዞን አስተዳደሮች
 የመሬት መምሪያ ሀላፊዎች
 የሠላምና ደህንነት መምሪያ ሀላፊዎች
 የገጠር መሬት አስተዳደር ቡድን
 የመሬት አጠቃቀም ቡድን
 የኢንበስትመንት ቡድን
 የኢንበስትመንት ቡድን መሪ በሌለበት አንድ ባለሙያ
 የቅየሳ ባለሙያ

ከወረዳ
 የወረዳ አስተዳደሮች
 የመሬት ጽ/ቤት ሀላፊዎች
 የሠላምና ደህንነት ጽ/ቤት ሀላፊዎች
 የገጠር መሬት አስተዳደር ቡድን
 የመሬት አጠቃቀም ቡድን
 የኢንቨስትመንት ቡድን
 የኢንቨስትመንት ቡድን በሌለበት ባለሙያ
 የቅየሳ ባለሙያ

3. የመሥክ ሥምሪቱ ተሣታፊዎች


የመስክ ስምሪቱ በሁለት ቡድን የሚሰራ ሁኖ ፡-
1. ቡድን 1

3
ምዕ/ጎጃም ዞን --ደ/አቸፈር እና ወንበርማ ወረዳዎች በቆላማ አካባቢዎች ያሉትን ነፃ መሬቶች
አዊ ዞን ---ጃዊ እና አየሁ ጓጉሣ ወረዳዎች ሲሆኑ፡-
2. ቡድን 2
ማዕ/ጎንደር ዞን-- የጠገዴ ወረዳ
ምዕ/ጎንደር ዞን ---ሲሆኑ፡-ምዕ/አርማጭሆ እና ቋራ ወረዳ በቆላማ አካባቢዎች ያሉትን ነፃ መሬቶች፡፡

ከክልል የሚደራጀው ቡድን

ቡድን 1 ብዛት ቡድን 2 ብዛት

 ከመሬት አስተዳደር 1 ከመሬት አስተዳደር 1


 ከመሬት አጠቃቀም 1 ከመሬት አጠቃቀም 1
 ከኢን ቨስትመንት 1 ከኢንቨስት መንት 1
 ከቅየሣ ባለሙያ 2 ከቅየሣ ባለሙያ 2
 ሹፌር 1 ሹፌር 1

ከዞን የሚደራጀው ቡድን

 ከመሬት አጠቃቀም 1 ከመሬት አጠቃቀም 1


 ከኢንቨስትመንት 1 ከኢንቨስትመንት 1
 ከቅየሳ ባለሙያ 1 ከቅየሳ ባለሙያ 1

ከወረዳ
 ከኢንቨስትመንት 1 ከኢንቨስትመንት 1
 ከቅየሳ ባለሙያ 1 ከቅየሣ ባለሙያ 1

ከቀበሌ
 የቀበሌው አስተዳዳሪ የቀበሌ አስተዳዳሪ
 የመሬት ባለሙያ የመሬት ባለሙያ
 የመሬት ኮሚቴዎች የመሬት ኮሚቴዎች
 የቀበሌው የፀጥታ ሀይል የቀበሌ የፀጥታ ሀይል

የመሥክ ሥምሪቱ የሚደረግባቸው ቦታዎች

በአዊ ብሄረሰብ ዞን ዞን፣ ዚገም ፣ ጃዊ፣አየሁ ገጓጉሣ ወረዳዎች ፣በምዕራብ ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር
፣ወንበርማ ወረዳዎች፣ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ፣አርማጭሆ፣ቋራ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ
ወረዳ
4. በመስክ ስምሪቱ ወቅት የሚከናወኑ ዋናዋና ተግባራት

4
 ለዞንና ወረዳ መሬት ተቋማት አመራርና ባለሙያ ግንዛቤ መፍጠር
 ወረዳዎች ከቸክ ሊስቱ በመነሳት የሚመለከታቸዉን የቀበሌ አመራርና ባለሙያ ከወረዳ ባለሙያ ጋር
በማቀናጀት ነጻ መሬት የመለየት ሥራ መሥራት
 ወረዳዎች ነጻ መሬት በሚለይበት ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ የሚመለከታቸዉን
የጸጥታ አካላት ከባለሙያዉ ጋር በቅንጅት ስምሪት መስጠት
 ነጻ መሬቱ ከተለየ በኋላ ቀያሾች የኮኦርድኔት ለቀማ ማካሄድ
 የወረዳዎች የነጻ መሬት ልየታዉ እና መረጃ አያያዝ ሥራ ላይ በየቀኑ እየገመገሙ፣ለሚፈጠሩ ችግሮች
አስቸኳይ መፍትሄ መስጠት
 ወረዳዎች የእየ ቀኑን የሥራ ሁኔታ ለዞን ሪፖርት ማድረግ
 ዞኖች ይህን ተግባር የሚከታተል ኮሚቴ በማዋቀር የነጻ መሬት ልየታዉን ሥራ መከታተል፣ መደገፍ
 ዞኖች የእየወረዳዉን የሥራ እንቅስቃሴ ለክልል በየቀኑ በስልክ ሪፖርት ማድረግ፣ በሦስት ቀን ዉስጥ የተሰሩ
እና የተገኙ ዉጤቶችን በጽሑፍ ለክልል ሪፖርት ማድረግ

5. ሥራውን ለመሥራት ያሉ ምቹ ሁኔታዎች


ክልሉ ለስራው የበጀት ፣ የተሸከርካሪ እና የቁሳቁስ አቅርቦት ያመቻቻል ተብሎ መታሰቡ፡፡
6. ሥራውን ለመስራት የሚያጋጥሙ ችግሮች
 ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ነፃ መሬቶች በህገ-ወጥ አራሾች በሰብል ተሸፍነው ስለሚሆን ከመሬቴ
አላስገባም አዝመራየ ይጠቀጠቅብኛል በሚል ችግር ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡
 ወረዳዎች ክረምት ከመሆኑ አንፃር ነፃ መሬቱ በደን ስለተሸፈነ የጠራ መረጃ ለመያዝ እና
ትክክለኛ የመሬት ሀብታችንን ለማግኘት ሊያስቸግር ይችላል፡፡
 ከወረዳ እስከ ቀበሌ ያሉ የሚመለከታቸው አካላት ተናበው ያለመስራት ችግር ይፈጠራል የሚል
ስጋት
 የፀጥታ ችግር ሊገጥም ይችላል
 ክረምት በመሆኑ የቅየሣ መሣሪያው ትክክለኛ መረጃ ላናገኝ እንችላለን
 ክረምት በመሆኑ ከቦታ ቦታ ተንቀሣቅሶ ለመስራት ጭቃውና ወንዞች ሊያስቸግሩ ይችላሉ
መፍትሄ
 ወረዳዎችና የቀበሌ አመራሩ እና ባለሙያው በትኩረት ይዞ በታማኝነት በወረዳው ውስጥ ያለ
ነፃ የኢንቨስትመንት መሬት ተለይቶ እንዲያዝ እና በአመለካከት አንድ አቋም ይዘው
ወደተግባር እንዲገቡ ማድረግ፡፡

5
 የፀጥታ ችግርን ለመፍታት ስራው በሚሰራባቸው ወረዳዎች ያሉትን የፀጥታ ሀይሎች የቡድኑ
አካል አድርጎ መድቦ ወደስምሪት ማስገባት

የስምሪት ቆይታ እና ጊዜ ሰሌዳ


ከ 10/12/2014 ዓ.ም እስከ 30/12/2014 ዓ.ም

ተ.ቁ ዞን/ወረዳ/ቀበሌ ቆይታ ከ - እስከ መድረክ አወያይ ምርመራ

1 የቢሮው ማናጂመንት የጋራ በቢሮው ሀላፊዎች


ውይይት ማካሄድ 6/12/2014 ዓ.ም
2 የዞንና የወረዳ የግንዛቤ ፈጠራ
መድረክ ማዘጋጀትነ ማካሄድ 8/12/2014 ዓ.ም በቢሮው ሀላፊዎች

3 የዞንና የወረዳ
ሀላፊዎች፣ለቀበሌ አመራሮች
እና ባለሙያዎች የግንዛቤ 12/12/2014 ዓ.ም በቢሮ ሀላፊዎች
ፈጠራ ማካሄድ

6
4 ለዞንና ወረዳው ሀላፊነቱን
ወስዶ ስምሪት ይሰጣል 13/12/2014 ዓ.ም በቢሮ ሀላፊዎች

5 ሥራውን በበላይነት
የሚገመግም እና የሚሰራ 14/12/2014 ዓ.ም በቢሮ ሀላፊዎች
አመራር መመደብ
6 የመስክ ባለሙያ የሥራ
ግምገማ እና ሪፖርት ዝግጂት ከ 15/12/ 2014 እስከ በአስተባባሪዎች እና በመስክ ባለሙያዎች
30/12/2014 በጋራ

You might also like