You are on page 1of 17

የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት

ማስተግበሪያ ማ ኑዋል

ነሐሴ/2009 ዓ.ም

1
ማውጫ ገፅ
ክፍልአንድ.........................................................................................................................................................3

1. መግቢያ.........................................................................................................................................................3

2.የሰነዱአስፈላጊነት...........................................................................................................................................5

3. የሰነዱዓላማ..................................................................................................................................................5

3.1. ዋናዓላማ..................................................................................................................................................5

3.2 ዝርዝርአላማ..............................................................................................................................................6

4. ወሰን.............................................................................................................................................................6

5.የቴክኖሎጂኤክስቴንሽንመርሆች.......................................................................................................................6

ክፍልሁለት........................................................................................................................................................8

2. የቴክኖሎጂኤክስቴንሽንአገልግሎትፅንሰ-ሀሳብ....................................................................................................8

2.1. የቴክኖሎጂኤክስቴንሽንአምዶችናማስተግበሪያስልቶች.....................................................……………………………9

2.1.1. የቴክኖሎጂኤክስቴንሽንአምዶች.........................................................................................................9

2.1.2 የቴክኖሎጂኤክስቴንሽንማስተግበሪያስልቶች.......................................................................................10

2.2. የቴክኖሎጂኤክስቴንሽንአምዶችየስራፍሰት/ሂደቶች.....................................................................................11

2.2.1. የአቅምግንባታሥራ.........................................................................................................................11

2.2. የቴክኖሎጂመቶፐርሰንትቅጂ፣ክምችትናሽግግር...........................................................................................11

2.2.1 የቴክኖሎጂክፍሎች..........................................................................................................................11

2.2.2 የመቶፐርሰንትየቴክኖሎጂቅጂሂደቶች................................................................................................12

2.3. የምርጥተሞክሮቅመራናማስፋት................................................................................................................16

ክፍልሶስት.......................................................................................................................................................18

3.1. የቴክኖሎጂኤክስቴንሽንባለድርሻናአጋርአካላትተግባርናኃላፊነት.....................................................................18

3.1.1. ባለድርሻአካላት፡-............................................................................................................................18

3.1.2. አጋርአካላት....................................................................................................................................18

2
ክፍልአንድ

1. መግቢያ
ሀገራችንን ለረጅም ዓመታት ሲጫናት ከቆየዉ ድህነትና ኋላቀርነት በማላቀቅ፣ ታሪካችንን ለማደስና የህዝባችንን
የዘመናት የለውጥ ፍላጎትና ጥማት ለማርካት ለተያያዝነው የህዳሴ ጉዞ የቀረፅናቸውን ልማታዊ
አቅጣጫዎች፣ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መሰረት በማድረግ በኢንተርፕራይዝ የዳበረችና ዜጎቿም መካከለኛ ገቢ
ያላቸው እንዲሆኑና እስከ ሁለተኛው የዕትዕመጨረሻ የዕድገት ምዕራፍ ውስጥ ከድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ
ያላቸውን አገራት መቀላቀል የሚያስችል አገራዊ ራዕይ ተቀርፆ እየተተገበረ ይገኛል፡፡ በመሆኑም እስከ 2017 ባሉት
አመታት ውስጥ ኤክስፖርት መር የሆኑና ጉልበት በሰፊው የሚጠቀሙ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን
በማስፋፋት ከከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች ጋር ጠንካራ ትስስር እንዲፈጥሩ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ስለሆነም አነስተኛና
መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለሀገር እንድገት መሰረት እንደመሆናቸው እና እድገታቸውንና በገበያ ተወዳዳሪነታቸውን
ለማሳደግ በተለይም በምርት ጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ዙሪያ ቁልፍ ማነቆዎችን በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫ
ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡ በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የተለዩ ማነቆዎች በዋናነት የተፈላጊ ቴክኖሎጂ
አጠቃቀም ዝቅተኛ መሆኑ እና የሰው ሀይል እንዲሁም ቴክኖሎጂ የመጠቀም አቅም ውስን መሆኑ፡፡

በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ማነቆዎች መነሻ በማድረግ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ለማሳደግ
፣የሚያመርቱትን ምርት ጥራት ለማሻሻልና በአለም አቀፍ ገበያ ምርታቸውን በመላክ የውጪ ምንዛሬ ለማስገኘት የቴክኖሎጂ
ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ መስጠት አስፈላጊ ይሆናል ።

የአንድ ኢንተርፕራይዝ የተወዳዳሪነት አቅም በባለሙያዎች የስራ አመራር ብቃትና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም
ላይ የተመሰረተ ነው፡፡በመሆኑም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በየጊዜው ስራው የሚፈልገውን ቴክኖሎጂ
በመጠቀም ምርታማነታቸው እንዲጨምርና አገልግሎታቸው እንዲሻሻል ማድረግ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን በገበያ
ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ የመቆየትና ያለመቆየት ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የአነስተኛና
መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ የሚያደርጓቸውን የቴክኖሎጂ ክፍተትነቅሶ በመለየት
እነዚህን ክፍተቶች ሊያስወግድ ወይም ሊሞላ የሚያስችል የቴክኖሎጂ አቅም መፍጠር የሚያስችል አገልግሎት
ነው።

ስለሆነም በስራ ላይ ያሉ እና አዲስ የሚቀላቀሉ የአነስተኛና መካከለኛ የኢነተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ


ይህ የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ማስተግበሪያ ሰነድ ተዘጋጅቷል።

3
2.የሰነዱአስፈላጊነት
ከአሁን በፊት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ይሰጥ የነበረውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ
ሽግግር አገልግሎት በአራቱም የድጋፍ ማዕቀፎች (ካይዘን፣ ስራ ፈጠራ፣ቴክኒካል ክህሎትና ቴክኖሎጂ) ድጋፍ
በማድረግ ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ ጥረት የተደረገ ቢሆንም የቴክኖሎጂ ድጋፉ በትግበራ ወቅት በሌሎቹ
የድጋፍ ማዕቀፎች የተሸፈነበመሆኑ እና በጥቃቅንደረጃ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችምበቁጥር ሰፊ
በመሆናቸው የቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎቱ ውጤታማነት በሚፈለገው ልክመሆን አልቻለም፡፡ ስለዚህ ይህ
የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ማስተግበሪያ ሰነድ በሚከተሉት ነጥቦች ምክንያት አስፈላጊ ሆኖ
ተገኝቷል፡፡

 በአንስተኛና መካከለኛ ደረጃ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጠውን ድጋፍ ውጤታማ


ለማድረግ፣
 የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላትባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ የተቀናጀ ድጋፍ ለመስጠት፣
 የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችበቴክኖሎጂ አቅም እና አጠቃቀም ላይ ችግሮችን
ሊፈታ የሚያስችል ጥራት ያለው ድጋፍ ለመስጠት፣
 ብቃት ያለው፣ተነሳሽነትን የተላበሰ፣ለምርታማነት የተዘጋጀና ከቴክኖሎጂ ለውጥ ጋር ራሱን
ማስተሳሰር የሚችል የሰው ሀይል አቅም ለማሳደግ፣
 በመሪ ክላስተር ተቋማት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን
አገልግሎት የሚሰጥበትንና የሚዳረስበትን መንገድ ለመፍጠር፣
 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አደረጃጀት ለመፍጠርና
ለማጠናከር፣

3. የሰነዱዓላማ

3.1.ዋናዓላማ
የሰነዱ ዓላማ ለአዲስና ለነባር አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችየተሟላ የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት
በመስጠት በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪየሆነምርት በማምረትናአገልግሎት በመስጠት ጥራትና ምርታማነትን
በማሳደግ የውጭ ምርትን መተካትነው፡፡

3.2 ዝርዝርአላማ
 ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጠውን የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት
የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት ባለቤት በማድረግና በማቀናጀት ውጤታማ ማድረግ፣

4
 ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ውስጥ የሚገኙትን የቴክኖሎጂ አቅምና አጠቃቀም
ችግሮችን ሊፈታ የሚያስችል ጥራት ያለው የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን ድጋፍ መስጠት፣
 ብቃት ያለው፣ተነሳሽነት የተላበሰ፣ለምርታማነት የተዘጋጀና ከቴክኖሎጂ ለውጥ ጋር ራሱን
ማስተካከል የሚችል የሰው ሀይል አቅም ማሳደግ፣
 በመሪ ክላስተር ተቋማት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን
ድጋፍ የሚሰጥበትንና የሚዳረስበትን መንገድ መፍጠር፣
 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አደረጃጀት መፍጠርና ማጠናከር፣
 የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን የውጭ ምርት መተካት የሚያስችል አቅም መፍጠር፣

4. ወሰን
ይህ የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተግባራዊ ሲሆን አገልግሎቱም
የእሴት ሠንሠለት ትንተና በማከናወን ክፍተት መለየት፣ የተሟላ መረጃ በማደራጀት የአቅም ግንባታ ሥራ
ማከናወን፣ ክፍተቶቹን ሊሞሉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን በመምረጥ መቶ ፐርሰንት ቅጂ በማከናወን የተቀዳውን
ቴክኖሎጂ ማሸጋገርን እና ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ተሞክሮዎችን ቀምሮ ማስፋትን ያካትታል፡፡

5.የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን መርሆች


የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን የሚከተሉትን መሠረታዊ መርሆች አሉት

 በትኩረት ዘርፍ ለተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ቅድሚያ ይሠጣል፤


 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎቱ የእሴት ሠንሠለት ትንተናን መነሻ ያደርጋል፣
 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎትበቴ/ሙ/ት/ስልጠና ክላስተር መሪ ተቋማት ተግባራዊ ይሆናል፣
 ከባለድርሸ አካላት እና ከአጋር አካላት ጋር በጋራ በመሆን አገልግሎቱ የሚደገፍ ይሆናል፣
 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት
በማረጋገጥ ላይ ያተኮረ ይሆናል፤
 የቴክኖለጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በአለም አቀፍ ደረጃ የተዋጣላቸውን የአሰራር ሂደቶችና
ተሞክሮዎች የሚከተል ይሆናል፣
 የቴክኖለጂ ኤክስቴንሽን ድጋፉ ወቅቱ በሚፈልገው የቴክኖሎጂ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ
ይሆናል፣
 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ውጤታማነት በየደረጃውመረጋገጥ፤ሪፖርት መደረግ እና መረጃው

ተደራጅቶ መቀመጥ ይኖርበታል፣

5
ክፍልሁለት

2.የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ፅንሰ-ሀሳብ


ያደጉ አገሮች የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎትን ተግባራዊ በማድረጋቸው ለእድገታቸው እና ለልማታቸው
እንደዋነኛ መሳሪያ በመሆን አገልግሏቸዋል፡፡ የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የቴክኖሎጂ አቅም የማከማቸት
ሂደት ሲሆን ይህ ተግባርና ሂደት እጅግ መሠረታዊ የገበያ ጉድለት ከሚታይባቸው የገበያ መስኮች ውስጥ በዋነኛነት
የሚጠቀስ ነው፡፡ የቴክኖሎጂ አቅምን ለመገንባት የሚፈጠሩት ተቋሞች በተራዘመ የታሪክ ሂደት የሚፈጠሩና
ከህብረተሰቡ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ባህርይ የሚመነጩ በመሆናቸው በተለያዩ ሃገሮች የተለያዩ ናቸው፡፡

የኢንዱስትሪ አብዮት ከተጀመረ ወዲህ ፈጣን እድገት ያስመዘገቡ አገሮች የየራሳቸው የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን
አገልግሎት አቅጣጫዎችን የተከተሉ ቢሆንም በሂደት ውጤማ መሆን ከቻሉት አገሮች ውስጥ በይበልጥ ጀርመን፣
አሜሪካ፣ ጃፓን እና ካናዳ ተጠቃሾች ናቸው ፡፡

አገራችን ልምድ ካላቸው ሀገሮች የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን ተሞክሮዎችን በመውሰድ የአነስተኛና መካከለኛ
ኢንተርፕራይዞችን በምርትና አገልግሎት አሰጣጥ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ በሁሉም ክልሎችና የከተማ
መስተዳደሮች አደረጃጀት በመዘርጋት የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎትን መተግበር አስፈላጊ ሁኖ ተገኝቷል፡፡

በመሆኑም በኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂያችን ላይ በተቀመጠው መሠረት የአነስተኛና መካከለኛ


ኢንተርፕራይዞችን በቅደም ተከተል በመለየትና በእያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ ላይ ከትኩረት ዘርፎች በመነሳት
የእሴት ሠንሠለት ትንተና በማካሄድ፣ የቴክኖሎጂ ክፍተት በመለየት መቶ ፐርሰንት መቅዳትና ማሸጋገር፣ በተለየው
ክፍተት መሰረት የአቅም ግንባታ ሥራ መስራትና ተሞክሮዎችን ቀምሮ የማስፋት ሥራ በማከናወን በአለም አቀፍ
ገበያ ተወዳዳሪ ማድረግ ይቻላል፡፡

ይህ ማንዋል በየደረጃው ላሉ በቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ሥራ ላይ ለተሠማሩ ተቋማትና ባለሙያዎች


በተለይ በመሪ ክላስተር ቴ/ሙ/ት/ሥ/ ተቋማት በቴክኖሎጂ ቅጅና ሽግግር፣ የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታና ተሞክሮ
ቅመራና ማስፋት ተገቢ እውቀትና መረጃ ኖሯቸው ሥራቸውን እንዲያከናውኑ በማሰብ የተዘጋጀ ነው፡፡

6
2.1. የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አምዶችና ማስተግበሪያ ስልቶች

2.1.1. የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አምዶች


አገራችን በማደግ ላይ ያለች አገር በመሆኗ የሌሎች አገሮችን ተሞክሮ በመከተል አነስተኛና መካከለኛ
ኢንተርፕራይዞችን በአለም አቅፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ የተለያዩ አሰራሮችንና ስልቶችን በመዘርት
የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎትን ለመተግበር በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች፡፡ ስለሆነም የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን
አገልግሎትን በተሟላ መንገድ ለመተግበር የማስተግበሪያ ሰነዱ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን አምዶች ያካትታል፡-
ሀ/ የአቅም ግንባታ ሥራ
ለ/ የቴክኖሎጂ መቶ ፐርሰንት ቅጂ፣ ክምችትና ሽግግር
ሐ/ የተሞክሮ ቅመራና ማስፋት
ሀ/ የአቅም ግንባታ ሥራ
የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ የፈፃሚዎችን አቅም
በክህሎት፣ በዕውቀትና በአመለካከት ላይ ያለውን ክፍተት በጥናት በመለየት በሚፈለገው ደረጃ እና የሙያ አይነት
የአቅም ግንባታ ሥራ ለማካሄድ የንድፍ ሀሳብና የተግባር ስልጠና ማከናወን አስፈላጊ ነው፡፡ ስለሆነም በ A እና B
ደረጃ ያሉ የቴ/ሙ/ትም/ስልጠና አሰልጣኞችንና አመራሮችን ከአለም አቅፍ ተሞክሮ በመነሳት የአነስተኛና
መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የቴክኖሎጂ አቅም ፍላጎት በሚጠይቀው ደረጃ ልክ ለማድረስ ከዘርፍ መሪ መ/ቤቶች
ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር ተግባራዊ ማደረግ አስፈላጊ ነው፡፡
ለ/ የቴክኖሎጂ መቶ ፐርሰንት ቅጂ፣ ክምችትና ሽግግር

የቴክኖሎጂ መቶ ፐርሰንት ቅጂ፣ ክምችትና ሽግግር ሲባል ከእሴት ሰንሰለት ትንተና በመነሳት የአካባቢውን የልማት
ቀጠና በመለየት ወቅቱ የሚፈልገውንና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርግ አዋጭና ተፈላጊ የሆነን ቴክኖሎጂ
በመለየት፣ የአዋጭነት ትንተና በማድረግ መቶ ፐርሰንት በመቅዳትና በማከማቸት ፈትሾ ኢንተርፕራይዞች ማሸጋገር
ነው፡፡

ሐ/ የተሞክሮ ቅመራና ማስፋት


በቴክኖሎጂ አክስቴንሽን አገልግሎት ብቁ የሰው ሀይል ለማፍራት እና የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን
በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ አገር አቀፍና አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን (አሰራሮችን እና

7
ቴክኖሎጂዎችን) በመለየት፣ መረጃዎችን በመተንተን እና በማደራጀት ተሞክሮዎችን የመቀመርና የማስፋት ሥራ
መስራት፡፡

2.1.2 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን ማስተግበሪያ ስልቶች


የቴክኖሎጂ አክስቴንሽን ድጋፍ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ወቅቱ ከሚፈልገው የ ቴክኖሎጂ አቅምና ለውጥ ጋር
እራሱን የሚያላምድ የሰው ሀይል በመፍጠርና በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሚያደርግ አዋጭና ተፈላጊ
ቴክኖሎጂን መቶ ፐርሰንት ቀድቶ በማሸጋገር ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪ ማድረግ እና ምርጥ ተሞክሮዎችን
የመቀመርና የማስፋት ሥራ ዋና ዋና የማስተግበሪያ ስልቶች ሲሆኑ ዝርዝር የማስተግበሪያ ዘዴዎችም የሚከተሉት
ናቸው፡-

 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎትን የሚተገብሩ አሰልጣኞችንና አመራሮችን ከአለም አቀፍ ተሞክሮ በመነሳት የአቅም
ግንባታ ስራ ማከናወን፣
 አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና አሰራሮችን ተቀብለው እንዲተገብሩና ጠያቂ
እንዲሆኑ የሚያስችል የግንዛቤ ሥራ መስራት፣
 የልማት ቀጠናዎችን መሰረት ያደረገ የእሴት ሰንሰለት ትንተናን በማከናወን አነስተኛና መካከለኛ
ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ቴክኖሎጂዎችን መለየት፣
 የተለዩ ቴክኖሎጂዎችን የአዋጭነት ትንተና በማከናወን ቅድሚያ ለሚሰጠው ቴክኖሎጂ ሙሉ ሰነድ
በማዘጋጀት የናሙና ምርት ማምረትና ፈትሾ ለኢንተርፕራይዞች ማሸጋገር፣
 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎቱን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል አደረጃጀት በየደረጃው መዘርጋት፣
 በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ደረጃ በቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አተገባበር ላይ ምርጥ ተሞክሮዎችን
የመቀመርና የማስፋት ሥራ መስራት፣
 ሌሎች የቴክኖሎጂ አማራጮች ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች
አሰራር በሚፈቅደው መሰረት እንዲሰራ ማድረግ፣

2.2. የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አምዶች የስራ ፍሰት/ሂደቶች


የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን ትግበራን ለመረዳት ከሚያስችሉት መንገዶች መካከል ግንዛቤን በሚገባ ተረድቶ የመፈፀም
አቅምን በማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ ቅጂ፣ ክምችት ሽግግር እና ተሞክሮዎችን በመቀመርና በማስፋት ሂደት ውስጥ
የሚያልፍ ይሆናል፡፡

2.2.1. የአቅም ግንባታ ሥራ


የሌሎች ሀገሮችን ተሞክሮ መነሻ በማድረግ የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎትን በአነስተኛና መካከለኛ
ኢንተርፕራይዞች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ የፈፃሚዎችን አቅም ማሳደግ አስፈላጊ ሲሆን ሂደቶችም፡-

8
 ፈፃሚዎች ቴክኖሎጂን ተረድቶ ከሙሉ ሰነድ ዝግጅት ጀምሮ እስከ መቶ ፐርሰንት የመቅዳት አቅምን፣
በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪነትን ጥናት የማድረግ እና ተሞክሮ በመቀመር የማስፋት አቅም ክፍተትን
በጥናት ላይ ተመስርቶ የመለየት ሥራ ማከናወን፣
 የፈፃሚዎችን አቅም ለማጎልበት የዘርፍ መሪ መ/ቤቶችን፣ የከፍተኛ ኢንዱስትሪዎችን፣ የኢንስቲትዩቶች፣
የዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርመር እና የፖሊ ቴክኒክ ተቋማትን አቅም በመጠቀም የአቅም ግንባታ ሥራውን
ማከናወን፣
 በእሴት ሰንሰለት ትንተና መሰረት የተለየውን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ያለባቸውን ክፍተት
በመለየት የአቅም ግንባታ ስራ ማከናወን፣
 በአዳዲስ የአመራረት ዘዴዎችና የመሳሪያ አጠቃቀም ላይ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የውጭ ባለሙያዎችን
በመጠቀም በኢንተርፕራይዙ የስራ ቦታ ላይ የተሟላ የክህሎት ስልጠና ይከናወናል፣

2.2. የቴክኖሎጂ መቶ ፐርሰንት ቅጂ፣ ክምችትና ሽግግር


የቴከኖሎጂ መቶ ፐርሰንት ቅጂን ይበልጥ ለመረዳት ቴክኖሎጂዎችን በክፍሎቻቸው ለይቶ ማስቀመጥ አስፈላጊ
ነው፡፡

2.2.1 የቴክኖሎጂክፍሎች
 ቁሳዊ ቴክኖሎጂ (Technoware) ይህ ቁስን ያካተቱ መሳሪያዎችን የያዘ የቴክኖሎጂ ክፍል
ነው፡፡ ለምሳሌ ኮምፒተር፣ ትራክተር፣ አይሮፕላን ወዘተ…
 ዕውቀታዊ ቴክኖሎጂ (Humanware) በሰው ልጅ ዕውቀት፣ ችሎታ፣ ልምድና ተሞክሮን
የሚያካትት የቴክኖሎጂ ክፍል ነው፡፡ ለምሳሌ የጥገና ችሎታ፣ የአመራር ልምድ ወዘተ...
ያካተተ ነዉ፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ በሀብት አጠቃቀም፣ በአሰራር ቅልጥፍና ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል፡፡
 ሰነዳዊ ቴክኖሎጂ (Inforware) ይህ በአግባቡ የተደራጁ ሰነዳዊ ማስረጃዎች፣ የአሰራር
ሂደቶችን፣ የንድፍ ዝርዝሮችና ማኑዋሎችን የሚያካትት የቴክኖሎጂ ክፍል ነው፡፡ ምሳሌ
የጥገና ማኑዋል፣ የቤት ዲዛይን ወዘተ… ይህ ቴክኖሎጂ መረጃዎች ደረጃቸውን ጠብቀው
እንዲተላለፍና ተቋማዊ አቅም ለመፍጠር ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል፡፡
 ድርጅታዊ ቴክኖሎጂ (Orgawere) ይህ ቴክኖሎጂ የአደረጃጀት ማዕቀፎችን የአሰራር
ዘዴዎችን ቅንጅታዊ ግንኙነት ወዘተ... ያካተተ ክፍል ነው፡፡

9
2.2.2 የመቶ ፐርሰንት የቴክኖሎጂቅጂ ሂደቶች

የተመረጡ አዋጭ ቴክኖሎጂዎችን በተሳካ ሁኔታ ለማሸጋገር ከገበያ ፍላጎት እስከ ሽግግር ድረስ ያለውን ሂደት
በቅደም ተከተል ማከናወንን ይጠይቃል፡፡ በዚህም መሰረት መቶ ፐርሰንት ቴክኖሎጂ የመቅዳትን ሂደት በቴክኖሎጂ
ኤክስቴንሽን ስርዓቱ ውስጥ አንድ ዓብይ ስራ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

በዚህ ሂደት ውሰጥ ከትኩረት ዘርፎች በእሴት ሰንሰለት ትንተና የተለዩ ቴክኖሎጂዎችን አዋጭነታቸውን በማረጋገጥ፣
ናሙና አምርቶ እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ አሰራሮችን ፈትሾ እስከ ሽግግር ያሉትን ሂደቶች እና የቅደም ተከተሎች
ተግባራት በዝርዝር የሚታዩበት ክፍል ነው፡፡ ይህንን ሂደት በትክክል በመተግበር የዘርፉን የአነስተኛና መካከለኛ
ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጡ ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳት ማቅረብ/ማሸጋገር ያስፈልጋል፡፡

ሀ/ ቴክኖሎጂን መቶ ፐርሰንት በመቅዳት የማሸጋገር ሂደቶች

የቴክኖሎጂ መቶ ፐርሰንት ቅጂ መሰረታዊ ሂደቶች ማለፍ ይጠበቅበታል፡፡ እነዚህም ቴክኖሎጂውን በእሴት ሰንሰለት
መለየት፣ የቴክኖሎጂውን አዋጭነት መተንተን፣ አዋጪ የሆነውን ቴክኖሎጂ ሙሉ ሰነድ ማዘጋጀት፣ በተዘጋጀው
ሰነድ መሰረት ናሙና ማምረትና የተመረተውን ናሙና ፈትሾ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን አብቅቶ
ማሸጋገር ያካተተ ሲሆን እያንዳንዱ ሂደትም እየተረጋገጠ መሄድ ይኖርበታል፡፡

1- ከእሴት ሰንሰለት በመነሳትና በቴክኖሎጂ ዓይነቶች ( Humanware, Technoware, Infoware And

Orgaware) ተለይቶ የተቀመጠ መሆኑን ማረጋገጥ፣


2- የተለየውን ቴክኖሎጂ በጥልቀት በመረዳትና በመተንተን የአዋጭነት ትንተና ማከናወን፣
3- የቴክኖሎጂ ንድፍ (የአሠራር ድሮዊንግ) እንደ ሙያ ዘርፉ ማዘጋጀት፣
4- የቴክኖሎጂ የማምረቻ ዋጋ አወጣጥ ግመታን ማከናወን፣
5- በተዘጋጀው ንድፍ መሰረት የምርት/የአገልግሎት ቴክኖሎጂ ናሙና ማዘጋጀት፣
6- የተቀዳውን ቴክኖሎጂ በተቋም ውስጥና በስራ ቦታ በተጠቃሚዎች ደረጃ የናሙና ፍተሻ ማከናወን፣
7- በናሙና ፍተሻ የሚፈለግበትን አገልግሎት መስጠቱ በተረጋገጠው ቴክኖሎጂ ላይ አብዢዎችን በመምረጥ
የአቅም ግንባታ ሥራ በመስራት ብሎም የማሸጋገር ተግባር ማከናወን፣

10
8- የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት ማድረግና በውጤቱ መሰረት አስፈላጊውን ማሻሻያ ማድረግ ናቸው፡፡

ለ/ የትኩረት ዘርፎችን መሰረት ያደረገ እሴት ሰንሰለት ማዘጋጀት


የትኩረት ዘርፎችን ተወዳደሪ ለማድረግ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን በዘርፎች መሪነት የእሴት ሰንሰለት ትንተና
በየዘርፉ በማዘጋጀት (ነባራዊ አሰራር፣ የእሴት ሰንሰለት በሚገባ በማስቀመጥና ምርጥ አሰራር በመምረጥ)
በመቀጠልም በሁለቱ መካከል ያለው ክፍተት በሚገባ በመተንተን የተለዩትን ቴክኖሎጂዎች በአራቱም የቴክኖሎጂ
ክፍሎች ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡

የእሴት ሰንሰለት ትንተና ማከናወን ያስፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ከተሰጡት
የበቃ የሰው ሃይል ማቅረብ ተልዕኮ ባሻገር ኢንተርፕራይዞችን በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ አዋጭና ችግር
ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን የማቅረብ ተልዕኮ በሚገባ ለመለየት ነው፡፡

ሐ/ ከእሴት ሰንሰለት ትንተና በመነሳት ምርጥ ቴክኖሎጂዎችን መለየትና መምረጥ


ቴክኖሎጂን መቶ ፐርሰንት ቀድቶ ለማሸጋገር ከዘርፍ ጋር በጋራ በተዘጋጀ እሴት ሰንሰለት ትንተና የተመረኮዘ መሆን
ይኖርበታል፡፡ የተለየውን ቴክኖሎጂ ሊፈታው በሚችለው የችግር መጠን መሰረት ተንትኖ በቅደም ተከተል
በማስቀመጥ መምረጥና ለአዋጭነት ትንተና ዝግጁ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መልኩ የተመረጠው ምርጡ ቴክኖሎጂ
የአዋጭነት ትንተና ተከናውኖለት በቀጣይ በአሰልጣኞች ሲረጋገጥ ተመርቶ የሚሸጋገር ይሆናል፡፡

መ/ የአዋጭነት ትንተና ማከናወን

ከትኩረት ዘርፎች በመነሳት በእሴት ሰንሰለት የተለዩ ቴክኖሎጂዎችን በተፈላጊ ቅደም ተከተላቸው ከተለዩ በኋላ
አዋጭነት ትንተና ማከናወን አስፈላጊ ነው፡፡

አዋጭነት በብዙ መንገድ የሚታይ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ፡ - ኢኮኖሚያዊ፣ ቴክኒካል እና አካባቢ ደህንነት አዋጪነት
ናቸው፡፡

 ኢኮኖሚክ አዋጭነት
 የጥገና ጊዜያቸው በምን ያህል ጊዜ መከናወን እንዳለበትና ምን ያህል ወጪ ሊያስወጣ እንደሚችል በመዳሰስ
አንድ አይነት አመራረት ካላቸው ቴክኖሎጂዎች ጋር ማነፃፀር፤
 የመለዋወጫ እቃዎችን አቅርቦት በአነስተኛ ዋጋ በሀገራችን ለመስራት የሚቻልበትን መንገድ መቃኘት፣

 የተመረጠው ቴክኖሎጂ ብዙ የሰው ሃይል አሰማርቶ የስራ እድልን መፍጠር የሚችል መሆኑን፣

 የምርት/አገልግሎት ጥራትና ምርታማነትን መጨመሩን ማረጋገጥ፣

 የህብረተሰቡ/ የደንበኞች የመግዛት አቅምን ያገናዘበ መሆኑን ማረጋገጥ፣

11
 ቴክኒካል አዋጪነት
 የተለየውን ቴክኖሎጂ መቀዳት ስለመቻሉ እያንዳንዱን አካላት በጥልቀት መረዳትና መተንተን መቻሉን
ማረጋገጥ፣
 የተለየው ቴክኖሎጂ በዲዛይኑ ከበፊቱ አንድ አይነት መሆኑንና ሀገር ውስጥ መቅዳት እና ማላመድ መቻሉን
መፈተሽ፣
 ቴክኒካዊ የሆኑ አሰራሮችን በዘርፉ እውቀትና ክህሎት ባላቸው ባለሙያዎች መገምገም እና የአሰራር
ዘዴያቸውንና ሊያመጡ የሚችሉትን ለውጥ መዳሰስ፤
 ከዚህ ቀደም የገቡ ቴክኖሎጂዎችን በመዳሰስ የሚቀዳው ቴክኖሎጂ በአወቃቀሩ፣ በአሰራር ዘይቤውና
በጥራቱ ተወዳዳሪ መሆኑን ማረጋገጥ፣
 ለቴክኖሎጂው የሚያስፈልጉትን ማንኛውንም ጥሬ ዕቃዎች፣ መለዋወጫዎች፣ የምርት ጥራት
መለኪያዎች ወዘተ በበቂና በቀላሉ የሚገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣
 የተለየው ቴክኖሎጂ በቀላሉ መጠገን መቻሉ፣

 የተለየውን ቴክኖሎጂ ለማምረት አቅም (እውቀትና ክህሎት) መኖሩን ማረጋገጥ፣

 አካባቢያዊ የህብረተሰቡን ባህላዊ እሴትን የጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ፣

 አካባቢና ህብረተሰቡ ላይ ከሚያመጡት ተፅዕኖ አንፃር ተገቢ የሆነ መረጃ መያዛቸውን በግልፅ የመቆጣጠሪያ
ስልታቸውን ማስቀመጥ አለባቸው፡፡

 አካባቢ ደህንነት አዋጭነት


 ከጤናና አከባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ጋር ተያያዥ የሆኑ መረጃዎች ተቀድተው ለሚሸጋገሩ
የቴክኖሎጂ ዓይነቶች ከአቅራቢው ማረጋገጫ መቅረብ ይኖርበታል፣
 የተለያዩ ኬሚካሎች፣ ጨረሮችና ንጥረ ነገሮች የሚጠቀሙ ቴክኖሎጂዎች የሀገሪቷን
የመቆጣጠር ዓቅምና የሚያቀርቡትን የመከላከያ ዘዴ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካለት
በሚሰጡት ሙያዊ አስተያየት የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፣
 ሀገሪቱ ከፈረመቻቸው ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች ጋር የሚጣረስ የቴክኖሎጂ መረጣ መከናወን
የለበትም፣
 የሚመረጠው ቴክኖሎጂ ከአካላዊ፣ ሰነልቦናዊና ከስራ ቦታ ደህንነት አንጻር ጎጂ አለመሆኑ
መረጋገጥ ይኖርበታል፣
 የሚመረጠው ቴክኖሎጂ ከአካባቢ ብክለት የነጻ መሆኑን ማረጋገጥ፣

12
 የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅምና የደህንነት መረጃ ስርዓትን አደጋ ውስጥ የሚጥሉ ቴክኖሎጂዎች
ለመቶ ፐርሰንት ቅጂም ሆነ ለሽግግር መመረጥ የለባቸውም።
በአጠቃላይ የአዋጭነት ትንተና ከላይ ከተገለጹት ሶስቱም አንጻር በዝርዝር ሲከናወን መረጃዎች ተደራጅተው
መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ለምሳሌ አንድ ቴክኖሎጂ ከኢኮኖሚ አንጻር አዋጪ ነው ሲባል በአካባቢ ላይ የተከናወነ
የገበያ ጥናትና ቴክኖሎጂውን ለማምረት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የተከናወነ የዳሰሳ
ጥናት ውጤት መረጃ መኖር ይኖርበታል፡፡
ሠ/ የቴክኖሎጂን ክምችት (ማቀብ)
በኢኮኖሚ ቀጠና ውስጥ ያለ የትኩረት ኢንተርፕራይዝን የእሴት ሰንሰለት ትንተና ያገናዘበ ምርጥ ቴክኖሎጂን
ለማሸጋገር ሌሎች ደረጃውን ጠብቀው እንዲሰሩት ለማድረግ ቴክኖሎጂውን ማቀብ (ማከማቸት) ያስፈልጋል፡፡

ቴክኖሎጂ በማቀብ ሂደት ውስጥ የተመረጠውን ቴክኖሎጂ ንድፍ (Blue Print) ማዘጋጀትና ናሙና አምርቶ ተከታታይ
ፍተሻ ማካሄድ ዋና ዋና ሥራዎቹ ናቸው፡፡ የቴክኖሎጂ ተቋማት ቴክኖሎጂ ማቀብ ዋና ስራቸው በመሆኑ በሳይንሳዊ
ትንተናና መረጃ ተመስርተው የቴክኖሎጂ ንድፍ ማዘጋጀት ይጠበቃል፡፡ በተዘጋጀው ንድፍ መሠረት ብቃት ያለው
ናሙና ማዘጋጀት፣ የተዘጋጀውን ናሙና በተገቢው ቦታና በሚፈለገው ደረጃ የፍተሻ ሥራ ማካሄድ እና በፍተሻ በተገኙ
መረጃዎች ላይ ተመርኩዞ ማስተካከያ/ማሻሻያ በማድረግ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2.3. የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት


በቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዙሪያ በአገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተዋጣላቸውን ተሞክሮዎች
በመቀመርና በማስፋት ሂደት የሚከተሉት ተግባራት ይከናወናሉ፡-

 በቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ምርጥ አሰራር ያላቸውን ሀገሮች ተሞክሮ በመውሰድ መረጃ
የማደራጀት፣ የመተንተንና የመቀመር ስራ ይከናወናል፣

 የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ በማገናዘብ የተገኘውን ተሞክሮ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ግንዛቤ
በመፍጠር የማስፋት ስራ ማከናወን፣

 በትግበራ ወቅት ሰፊ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ መረጃ የማደራጀትና ግብረ መልስ መስጠት፣

 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎትን በመተግበር ውጤታማ የሆኑ አነስተኛና መካከለኛ


ኢንተርፕራይዞችን እውቅና በመስጠት ማበረታታት፣

 በቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የመጣውን ለውጥና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በፋይዳ ዳሰሳ ጥናት
ማካሄድ፣

 በጥናቱ የተገኙ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ማስቀጠልና የተገኙ ውስንነቶችን የማስተካከል ስራ ማከናወን፣

13
14
ክፍልሶስት

3.1. የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን ባለድርሻና አጋር አካላት ተግባርና ኃላፊነት

3.1.1. ባለድርሻ አካላት፡-


በቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስርአት ከመዘርጋት እስከ ትግበራ ባለው ሂደት ላይ የሚሳተፉ ናቸዉ፡፡

 የትኩረት ዘርፍ መሪ መ/ቤቶች፣


 የቴ/ሙ/ት/ስ አጄንሲዎች/ቢሮዎች/ተቋማት፤
 የምርምር እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፤
 የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኤጀንሲ/ቢሮ/መምሪያ/ኢንተርፕራይዞች፣
 የመንግስት የልማት ድርጅቶች፤
 የሙያ ማህበራት፤

3.1.2. አጋር አካላት


የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን ተግባርን ለማከናወን አጋር የሆኑ አካላት

 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች


 ለጋሾች

3.1.1.1 የትኩረት ዘርፍ መሪ መ/ቤቶች

 የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ የሚያስችል የዘርፋቸዉንና የንዑስ


ዘርፋቸዉን እሴት ሰንሰለት ይሰራሉ፣
 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ትግበራ ላይ በባለቤትነት ይተገብራሉ፣ ለትግበራው ውጤታማነት የመፍትሄ
ሃሳቦችን ያቀርባሉ፣ ትግበራውንም ይከታተላሉ፣
 በቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ትግበራ ላይ ግንዛቤ ይፈጥራሉ፤ አቅም ይገነባሉ
 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ ተግባራዊ እንዲሆን ስልትና ዕቅድ ያስቀምጣሉ፤
 ክትትልና ግምገማ ያካሄዳሉ፤

3.1.1.2.የምርምር እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት

 የቴክኖጂ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት ላይ የዲዛይን ስራዎችን ያከናውናሉ፣ ምርምር በማድረግ ድጋፉ ስኬታማ
እንዲሆን ያደርጋሉ፣
 በቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን ድጋፍ የሌሎች ሀገሮች ተሞክሮን በመቀመር ተግባራዊ እንዲሆን ያግዛሉ፤

15
 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት ላይ ግንዛቤ ይፈጥራሉ፤አቅም ይገነባሉ፤
 ክትትልና ግምገማ ያካሄዳሉ፤

3.1.1.3 ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናተ ቋማት

I.በፌደራል ደረጃ
 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ የአሰራር ስርአት ይዘረጋል፤

 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አደረጃጀትና ግልፅ የአሰራር ስርዓት የተዘረጋለት መሆኑን ያረጋግጣል፤

 በቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አተገባበር ላይ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ፈፃሚዎችን ያበቃል፤ ግንዛቤ ያስጨብጣል፤

 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍን በበላይነት ያስተባብራል፤

 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ላይ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤

 በቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ላይ የተገኙ ተሞክሮዎችን በመቀመር እንዲሰፋ ያደርጋል፤

II.በክልል ደረጃ
 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ የአሰራር ስርአት በክልል ደረጃ ይዘረጋል፤

 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አደረጃጀት ይፈጥራል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፤

 በቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አተገባበር ላይ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ፈፃሚዎችን ያበቃል፤ ግንዛቤ ያስጨብጣል፤

 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍን በክልል ደረጃ ያስተባብራል፤

 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ላይ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤

III. በመሪ ክላስተር ተቋማት


 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ የአሰራር ስርአትን መሰረት በማድረግ ይተገብራል፣

 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አደረጃጀት ይፈጥራል፣ ተግባራዊም ያደርጋል

 በቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አተገባበር ላይ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ፈፃሚዎችን ያበቃል፤ ግንዛቤ ያስጨብጣል፤

 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍን በተቋም ደረጃ ያስተባብራል፤

 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ላይ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤

3.1.1.4. የአንስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኤጀንሲ/ቢሮ/መምሪያ/ኢንተርፕራይዞች


 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተግባራዊ ማድረግ፣
 የኢንተርፕራይዞችን ደረጃ በመመሪያው መሰረት በመለየት ለቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን ድጋፉ ዝግጁ ማድረግ፣

16
 ለአንሰተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን ድጋፉ ላይ ግንዛቤ መፍጠር፣
 በፌደራልና በክልል ደረጃ የሌሎች ሀገሮችን ተሞክሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን መቀመርና ማስፋት፣
 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽንን ድጋፍ ከፌደራል እስከ ክልል ባለው አደረጃጀት በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ
ተግባራዊ እንዲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣

3.1.1.5 የመንግስት የልማት ድርጅቶች


 በቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ላይ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ችግር በመፍታት በአለም አቀፍ ገበያ
ተወዳዳሪ ማድረግ የሚችልና በሀገር ውስጥ የማይገኙ ቴክኖሎጂዎችን ለመቶ ፐርሰንት ቅጂ ማቅረብ ላይ እንዲተባበሩን
ማድረግ፣
 የቴክኖሎጂ ኤክስቴንሽን አተገባበር ላይ የፈጻሚዎችን አቅም ለመገንባት ትብብር እንዲያደርጉ ማድረግ፣

17

You might also like