You are on page 1of 6

የግንባታ ፕሮጀክቶችን በሶፍትዌር ታግዞ የመምራትና የማስተዳደር ትሩፋቶች

/በሲቪል መሀንዲስ ዮሐንስ ብዙነህ ከሀዋሳ (ክፍል ፩)


እጅግ በሰለጠኑትና ባደጉት አገራት በተለያዩ ዓይነት የግንባታ ፕሮጀክቶቻቸው ላይ ስራዎችን ለማቀላጠፍ
ዳታቸው የተሻለ ትክክለኛነት ላይ እንዲደርስ፣ ሥኬት እንዲያገኝም ሆነ ፈጣን የሆነ ሪፖርት ለማምረት
ጭምር የተለያዩ ዓይነት ሶፍትዌሮችን መጠቀም ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል፡፡ አሁን አሁን በእኛም አገር
ተሞክሮ ያለ ቢመስልም በሁሉም ደረጃቸው ከፍ ባለ የኮንስትራክሽን ግንባታ ስራዎች ተቋራጮች ዘንድ ሙሉ
በሙሉ ጥቅም ላይ ውሏል ለማለት ግን አያስደፍርም ፡፡የግንባታ ፕሮጀክቶች ቴክኒካልም ሆነ አስተዳደራዊ -
ኮንትራቱንና የሰው ኃይልን ጨምሮ ማለት ነው መምራት ቲም ማቀናጀትና የተዋጣ ስራ እንዲሰራ እርስ
በእርስ እንዲግባባና የሚሰራቸውን እንዲናበብ ማድረግ ቀላል ሸክም አይደለም፡፡

ዋናው የግንባታ ካምፓኒዎች ተግባር የሚዘውሩትን ገንዘብ አጠቃቀሙን በጥብቅ መፈተሸ ከመሆኑ አንፃር
እንዳንዱ ፈራሚ የሚፈርመውን ሰነድ በሚገባ የመመርመር ሲጠናቀቅም ማለትም ሲወራረድም
እንደዚያው የመፈተሸና የማረጋገጥ ስራን ሊሰራ እንደሚገባ ግልፅ ሲሆን እነዚህን ሁሉ ግን በምን ጥራትና
ፍጥነት እንዲሁም ቁልጭ ባለ ሪፖርት ክሽን ለማድረግ አድካሚነቱን በእነዚህ ሶፍትዌሮች በመታገዝ ቀለል
አድርጎ ስራን መተግበር የሚቻልበት ዘመን ላይ ተደርሷል፡፡

ታብሌት ለሚጠቀሙ የፕሮጀክት ማናጀሮች እንዲያግዝ በሚል በጁሊ ጋብርዬል “አምስቱ ዋና የሆኑ
የግንባታ ፕሮጀክቶች /construction project/ አመራር ምዕራፎች /phases/ ሶፍትዌር እንዴት አድርጎ
ፕሮጀክት አመራርን እንደሚያግዝ /እንደሚደግፍ” በሚል ርዕስ በአፕሪል 8 እኤአ በ 2021 ከተጻፈ ብሎገር ላይ
መረዳት እንደሚቻለው እያንዳንዱ ፕሮጀክት መጠናቸውን ትተን እየተመሩ ማለፍ ያለባቸውን ሂደት ስናይ
የተፈላጊ ውጤታቸው መገኛ መንስዔ ከግንባታ ፕሮጀክት ጋር ዝምድና ያለው የፕሮጀክት ማናጀር ጥጥርና
ጥብቅ የሆነ እቅድ ጥቅም የተነሳ የሚገኝ ነው፡፡

ለአንድ የግንባታ ፕሮጀክት ትክክለኛና ተገቢ የሆነ እቅድን ማዘጋጀት የግንባታ ሂደቱን /process ለማጤን እጅግ
ጠቃሚ ነው፡፡ የግንባታ ፕሮጀክት ሂደት አንድን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ የሚረዱ ዝርዝር ደረጃዎችን /steps
ማካሄድ ይፈልጋል፡፡ እነዚህ ሂደቶች በ 5 ምዕራፎች እቅድ ወይም ዲዛይን የሚካተተና ሲዘረዘሩም፡- ቅድመ
ግንባታ /pre-construction፤ ግዥ /procurement ፤ ግንባታ /construction/ እና ድህረ-ግንባታ /post-
construction እየተባሉ ሊሸነሸኑ ይችላል፡፡ የግንባታ ፕሮጀክትን መጠንና ዓላማን ተንተርሶ እያንዳንዱ
ምዕራፍ /phases የራሳቸው የሆነ ተግዳሮት አላቸው፡፡ ይህ እንግዲህ እያንዳንዱን ምዕራፍ በሚፈለገው መጠን
ማስኬድ ለማስቻል ነው፡፡

ምንም እንኳን የግንባታ ፕሮጀክቶች በመጠንና ዓይነታቸው የተነሳ የማስረከቢያ ቀናቸው፤ የባለድርሻ አካላት
ቁጥርና በጀት፣ወዘተ ምክንያት የተነሳ የተለያዩ ቢሆንም እንኳን በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሊኮን ይገባል ያም

1
የግንባታ ፕሮጀክቶች ሁልጊዜም ረዥም ሂደትን ከተለያዩ ተንቀሳቃሽ ክፍሎች ጋር ማካሄድን የሚጠይቁ
መሆናቸው ናቸው፡፡ መልካም ዜና ግን አለ ይኧውም ለግንባታ ፕሮጀክቶች የተለየ የፕሮጀክት ግንባታ ስራዎች
መሳለጥ አጋዥ የሆነ የፕሮጀክት አመራር ሶፍትዌርን ማግኘትና መጠቀም መቻሉን መገንዘብና ማወቁ ላይ
ነው፡፡ በዚህ ሶፍትዌር አማካኝነት የተለያዩ ፕሮጀክቶች ምዕራፍ / phases ተገቢ በሆነ መልኩ በቀላሉ
ሊተገበሩ ይችላሉ፡፡

የፕሮጀክትን ሂደት ለመተገበርና ለመከታተል የሚያግዙትን እነዚህን ሶፍትዌር መጠቀም የሚቻል እንደመሆኑ
መጠን የሚከተሉትን የፕሮጀክት ሂደት ደረጃዎችን በዝርዝር በማየት እንዴት የፕሮጀክት አመራር ቴክኖሎጂ
በእያንዳንዱ ምዕራፍ /each phases ላይ አቅምን እንዲጎለብት አድርጎ ጥቅምን እንደሚሰጥ ማየት ይችላል፡፡

ምዕራፍ I የመነሳሻ /ጥንስስ ምዕራፍ / Initiation phases

ፕሮጀክትን ለመስራት የማቀድ ወይም የመነሳሻ /ጥንስስ /Initiation phases ጊዜ ወይም ወቅት የፕሮጀክት
ሀሳብ ውሳኔ ማግኘት ለፕሮጀክት አመራር በጣም አሰፈላጊ የሆነ ባህርይ /እይታ /Aspects ያለው ነው፡፡ አንድ
ፕሮጀክት ከመፅደቁና ፕላን ከመጀመሩ በፊት የግድ ሁሉንም ደረጀዎች /steps/ አካቶ /አቅፎ/ encompasses
all of the steps የሚይዝ ምዕራፍ ያለው ነው፡፡ ይህ ምዕራፍ ሳይከናወን ወይም እውን ሳይሆን ሌሎች
ተግባራት የሚጀምሩ ስላልሆነ ይህንን ሂደት ቀድሞ ማሳለጥ ያስፈልጋል፡፡ በተለምዶ በዚህ ምዕራፍ በውስጡ
3 የተለያዩ የማስጀመሪያ ዲዛይን ስቴጆች ይካተታሉ፡፡ እነዚህም በዝርዝር ሲታዩ፡፡

1.1. ዕቅድና እውንነት /programming & feasibility/

የእቅድ ቲም የፕሮጀክቱን ጭብጥንና ግቡን /objectives & goals/ በንግድ ዓይን እይታ ሁኔታ ውስጥ ከቶ
የፕሮጀክቱን የእውንነት ጥናት /Feasibility study አሻግሮ የሚያይበት ሂደት የሚተገበርበት ስቴጅ ነው፡፡
የህንፃውን ግዙፍነት ጨምሮ ምን ያህል ቦታን ይሸፍናል /ይወስናል ከሚለው ጀምሮ ምን ያህል ክፍሎች
ያስፈልጉታል የሚለውን አካቶ መደምደሚያ የሚሰጥበትን ሀሳብ ይዞ ውሳኔ የሚሰጥበት ክፍል /stage/ ነው፡፡
እነዚህ ሁሉ ታይተው፤ ተፈትሸው፤ ተገናዝበው ተንሰላስለው አንድ ጊዜ ውሳኔዎች ላይ ከተደረሰ በኋላ
የፕሮጀክት መነሻ አሳብ ዶክመንት ፒ አይ ዲ /project initiation document (PID) ተዘጋጅቶ/ተቀርፆ
/created/ ለቀጣይ የፕሮጀክቶች ሂደቶች ዝግጁ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

2
1.2. ንድፍ ዲዛይን /schematic design

በዚህ ክፍለ ጊዜ /step/ ቲሙ ክፍሎችን፤ የግንባታ ማቴሪያሎችን፤ ቀለማትንና ቴክስቸሮችን አካተው የስኬች
/sketch/ ስራን ይሰራሉ፡፡ ለሥራው አስፈላጊ የሆኑትን ኢኪውፕመንትንና የግንባታ ማቴሪያሎችን ጨምሮ
በዲዛይን ማጎልበት /design development /ወቅት ጥናቶችን በማካሄድና መረጃዎችን በመጠቀም /using
information/ ይህ ሥራ ይሰራል፡፡

1.3. የኮንትራት ዶክመንት

ይህ የኮንትራት ዶክመንት ያለቀለትን የመጨረሻውን ድሮዊንግና የሥራ መዘርዘሮችን /drawings &


specifications/ አንድ ላይ አቅፎና አቆራኝቶ የሚይዝ ነው፡፡ እነዚህ ዶክመንቶችም የጨረታ ውድድሩን
አሸንፎ /placing bids to work on the project የፕሮጀክቱን የግንባታ ሥራ ጀምሮ ለማጠናቀቅ በሚደረግ
ሂደት ውስጥ የሚጠቀሙበት ዶክመንት ነው፡፡

1.3.1. በፕላኒንግ ወይም ዲዛይን ምዕራፍ ውስጥ የተለመዱ ተግዳሮቶች/ common


challenges in the planning, design stage /

ፕሮጀክት ጅማሬው ላይ በሁለት እግሩ ቀጥ ብሎ በትክክል መቆም ካልቻለና ካልተራመደ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡
ይህ እንዳይሆን ከሚያደርጉት ትልቁ አስቸጋሪ ሁኔታዎች /biggest hindrance አንዱ የሆነው የተግባቦሽ ችግር
/miss-communication / ነው፡፡ ቲሙ ውስጥ ያሉ በተለያዩ የሙያ ሥርዓት /multi professional disciplines
/ ውስጥ የተካተቱት አባላቱ እርሰ በርሳቸው በመከባበርና በመቀባበል ሁኔታ መግባባትና መደማመጥ ሳይችሉ
ሲቀር የሚያጋጥም /የሚፈጠር/ ችግር ነው፡፡

ያልተብራሩ ግቦች /Undefined goals / ሌላው ትልቁ በፕሮጀክት ጅማሬ ላይ የሚከሰት ተግዳሮት
/challenges/ ከመሆኑ አንፃር መጀመሪያውኑ የፕሮጀክቱ ግቦች ሊብራሩና ሊታወቁ ይገባል፡፡ አንዳንዴ
የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላት /stakeholders/ ምን እንደሚፈልጉ በትክክል ካለማወቅ የተነሳ ፕሮጀክቶች
ተግዳሮቶች ይገጥሙታል፡፡ የፕሮጀክት ግቡ ግልጽ ሆኖ ካልተቀመጠ ፕሮጀክትን መምራት አስቸጋሪ
ያደርገዋል፡፡ ስለሆነም ይህን ሁሉ አውቆ የፕሮጀክትን ግብ አስቀድሞ ማብራራት የተሻለ የፕሮጀክት አመራር
እንዲገኝ ትልቅ አቅም ይሆናል፡፡

1.3.2. ሶፍት ዌር እንዴት በፕላኒንግ ወይም ዲዛይን ጊዜ ሊረዳ እንደሚችል፤

ቴክኖሎጂ ምስጋና ይግባውና የግንባታ ፕላኒንግ /construction planning/ ትልቅ እፎይታን ባስገኘ ሁኔታ
እመርታን በማሳየቱ የተነሳ ትልቅ አብዮት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ላይ አምጥቷል፡፡ የተቀናጀ የግንባታ
አስተዳደር ሶፍትዌር /integrated construction management software/ የግንባታ ፕሮጀክቶች

3
ከመጀመራቸው በፊት የፕሮጀክት ማናጀሮችና ባለድርሻ አካላት ሊከሰቱ ይቻላሉ የሚባሉ እንቅፋቶችን
/obstacles/ ተለይተውና ታውቀው መፍትሔያቸው አስቀድሞ እንዲበጁ በማድረጉ ረገድ ከሚሰጡት ጥቅም
አንጻር እነዚህ ሶፍት ዌሮች ትልቅ መፍትሔን ይዘው በመቅረባቸው የተነሳ ለኢንዱስትሪው እፎይታን
ይሰጣሉ፡፡ እነዚህ የግንባታ መርሀ-ግብር በፕላኒንግ ምዕራፍ ስቴጅ ላይ ስምምነት የተደረገባቸውን ሶፍትዌሮች
ዳታዎችን በመመዝገብ /record/ ቀላልና ምቹ የሆኑ ዳታዎችን በማድረስ ይበልጥ ወደ እውነታ የተጠጋጋና
ዳታዎቹም የእስካሁን ድረስ እንዲሆኑ ለማድረግና ለማሰራጨትም ሆነ እስከዚያ ጥግ ለማድረስ /makes data
sharing more accurate & up-to-date ጭምር ይረዳሉ፡፡

ይህም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ሁሉም ዳታዎች ማዕከላዊ ሲሆኑ የሰውኛ ስህተት ጉዳትን /the risk of
human errors/ በመቀነስ ሁሉም ቲም በተመሳሳይ ገፅ ላይ /whole team stays on the same page/
ቆይታችው እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችልም ጭምር ነው፡፡

ከዶክመንቶች መዘባረቅ፤ መበታተንና በተለያዩ ቦታዎች ላይ መከማቸት የተነሳ ስኬማቲኮችን ወደ ዋና


ድሮዊንጎች መቀየር በተለምዶ ውስብስብ ሂደትን የሚያልፉ ናቸው፡፡ ነገር ግን ሁሉንም ተፈላጊ የሆኑ
ዶክመንቴሽኖችን አንድ ላይ መሰብሰብ ሲቻል ግን ሁኔታዎች ሁሉ ቀላል ይሆናሉ፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ
መረጃዎች ወዲያው ወዲያው ሲታደሱ /ሲጎለብቱ updated/ የፕላኒንግ ቲሙ ሥራው እንዴት መራመድና
ማደግ እንደሚችል ትክክለኛ የሆነ /the planning team can create an accurate picture of how the job
will progress/ ምሥልን ማግኘት የሚቻልበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡

እንግዲህ እነዚህ ሶፍትዌሮች በፕላኒንግ ወይም ዲዛይን ደረጃ ላይ ላለ ፕሮጀክት ፍትሁን መድኃኒት አምጪ
ሆነው ከተገኙ ምንጫቸው፤ አጠቃቀማቸውንና ውስንነት የሚታይባቸው ሁኔታም ካለ እነዚህን ለመለየትና
ለማጣራትም የሚቻልበትን ስራ እየሰሩ የትኛው ሶፍትዌር ከየትኛው ሶፍትዌር የተሻለ እንደሆነ ለማወቅ
የሚያስችል በቂ መረዳትን በማግኘት መጠቀም መቻል ተገቢነት ይኖረዋል ማለት ነው፡፡

2. የድህረ-ግንባታ ምዕራፍ፤

የግንባታ ሥራን የሚያካሂድ ሥራ ተቋራጭ በጨረታ ውድድር የመለየትና የማወቅ ሥራ ተሰርቶ ከተከናወነ
በኋላ ቀጣይ የሚሆነው የግንባታውን ሥራ መጀመር እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ አንድ ምርትን የማምረቻ
ኢንዱስትሪ ግንባታው ከተጠናቀቁ በኋላ ወደ ስራ ለማስገባት ኢንዱስትሪው ከብዙ ማረጋገጥ፤ ፍተሻና
ለማምረት ዝግጁ መሆንን በማስመልከት እነዚህ ሁሉ ተረጋግጠው ሲያበቁ ማምረትህን ጀምር /ቀጥል/
እንደሚባለው ሁሉ የግንባታ ሥራን ጀምር/ ቀጥል/ ብሎ መሬትን ለመቆፈር ከመንደርደር በፊት የፕሮጀክት
ቲም በጋራ ተቀምጦ የግንባታ ሥራው መጀመር ስለመቻልና ስላለመቻሉ መሟላት የሚያስፈልጋቸው ነገሮች
ሁሉ ተሟልተው ያለቁ ስለመሆኑ እርግጠኛ ለመሆን አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ተፈላጊ የሆኑ በሙሉ
ስለመጠናቀቃቸው እርግጠኛ ለመሆን የፕሮጀክቱ ዝግጁነት ላይ ውይይት ሊያደረግበት ይገባል፡፡

4
አብዛኛወን ጊዜ ከተሞክሮ /ተለምዶ/ እንደሚታየው ቲም የሚያቅፋቸው ወይም የሚያካትታቸው አባላቱ፤

 ኮንትራት አስተዳደር
 ፕሮጀክት ማናጀር
 ሱፐር ኢንተንደንት
 የመስክ መሃንዲሶችንና
 የጤናና ጥንቃቄ መጠበቅ /health & safety manager ማናጀር ይሆናሉ፡፡

በዚህ ደረጃ ጊዜ ሥራ ከመጀመሩ በፊት የፕሮጀክት ቲሙ /project team/ የፕሮጀክቱን የግንባታ ሳይት ዝግጁ
የማድረግ ሥራን ይሰራሉ፡፡ ይህ ማለት ከአፈር መርመራ /soil Testing/ ጋር በተያያዘም ሆነ ከተፈጥሮ
ችግሮች ጋር በተያያዘ /Environmental Issue/ ፤ የይዞታ ባለቤትነት ጥያቄ /night-off way problem/ ፤
ወዘተ ጋራ በተያያዘ የነጻና የፀዳ ስለመሆኑ እርግጠኛ የማድረግ ሥራን ይሰራሉ ማለት ነው፡፡ ይህን መሰሎቹን
የሳይቱን የምርመራ ሥራን /site examination is completed/ ሰርተው ካጠናቀቁ በኋላ ሁሉም ፕላንና
ግኝቶች /all plan & findings/ ተጠቃለው ከሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ጋር ለውይይት ዝግጁ ይደረጋል፡፡

አንዴ የስትራቴጂክ እቅድ ከተዘጋጀ /ከታቀደ/once strategic plan has been created/ በኋላ በጀት፤ ዲዛይንና
የጊዜ ሰሌዳው /budget, design & timeline/ ይጠናቀቅና በአጠቃላይ መስመር ከያዘ በኋላ ለፕሮጀክቱ ግንባታ
ሥራዎች ክንውን አስፈላጊ የሆኑትን ሠራተኞችንና ሀብትን በማሰባሰብ ፕሮጀክት እንዲጀመር የማስደረግ
ሂደት ክንውን ያበቃና ፕሮጀክቱ ስራውን እንዲጀምር ይደረጋል፡፡

2.1. በድህረ-ግንባታ ምዕራፍ ዋና የሆኑ ተግዳሮቶች /common challenges in the construction


phases ምን እንደሚመሰሉ፤

ፕሮጀክት መች እንደሚጀምርና መች መጠናቀቅ እንዳለበት የሚያሳይ ግልፅ ምስል ከሌለ ያልታወቁና


ያልተገመቱ ብዙ ዓይነተኞች /variables/ የግንባታ ስራው እየተከናወነ እያለ ሊታዩ እንደሚችሉ መታወቅ
አለበት፡፡ ሁሉንም ምቹ ሲናሪዮ/ all possible scenarios/ ወደፊት በማምጣት መገምገም ካልተቻለ
የፕሮጀክቱ ባለቤት /clients or owner / ስለፕሮጀክቱ የሚኖረው ግምት ወይም መጠበቅ ጋር ተያዞ ካለው
ተነሳሽነቱ በተቆራኘ ፕሮጀክቱ ገና ግንባታ ላይ እያለ /client of owner can have unrealistic expectations/
ተዓማኒነት እንዲያጣ ሊያስገድደው የሚችል ነገር ሊከሰት ይችላል፡

በድህረ-ግንባታ ምዕራፍ /post construction phase/ በርካታ /ብዙ/ አንድ ሁለት ሊባሉ የሚችሉ ተቆጣሪ
ይኖራሉ፡፡ እነዚህም፡- ህጋዊ ጭብጦች/ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮች /numerous legal issues/ ፤ ፍቃድ
የሚያስፈልጋቸው ወይም የሚያሻቸው / permits እና የህንፃ ኮዶች /building codes involved / ማለቅ

5
የሚገባቸው ሂደቶች ናቸው፡፡ በተጨማሪም እነዚህን መሰል ጭብጦች በግንባታ ሂደት ውስጥ የሚያልፉ
ስለሆኑ ለእነዚህ የሚሆን ሥራን መሥራት መቻል ግድ ይላል፡፡ ካለ ብቁና ተገቢ የወረቀት ሥራ አመራር፣
ዶክመንቴሽን ክምችት /documentation storage እና ቁጥጥር /control ሥራ የግንባታ ፕሮጀክታችን
መተውና ይህን መስራት አለመቻል ሌላ ተግዳሮት /con become another challenge/ ሆነው በመምጣት
ናላን የሚያዞሩና ጭንቅላትን የሚበጠብጡ ሆነው የግንባታ ፕሮጀክቱን አመራር አጣብቂኝ ውስጥ በመክተት
ወደ አዝቅት እንዲያመራ ያደርጉታል፡፡

2.2. በድህረ-ግንባታ ጊዜ ሶፍትዌር እንዴት አጋዥ ሊሆን እንደሚችል፤

በደህረ-ግንባታ ደረጃ /stage/ የፕሮጀክት የጊዜ ሰሌዳ መርሃ-ግብር በማደራጀት /build progress timeline
schedule በቲሙ አባላት ውስጥ ተዓማኒ የሆነ የሥራ ፍሰት /logical work flow/ እንዲኖር የማድረግ ስራን
ይሰራሉ፡፡ ተዓማኒ የሆነ የግንባታ መርሃ-ግብር ማዘጋጀት ሶፍትዌር /having reliable schedule software/
ማግኘት ፕሮጀክቱን መግለፅ የሚያስችል /project unfolds እና መርከብን ባህር ወይም ወቅያኖስ ላይ
በአስተማማኝ ሁኔታ መንሳፈፉን /smooth sailing / የማረጋገጥ የዓይነት ስራን እንደመተግበር ያስቆጥራል፡፡

የፕሮጀክት ቲም አወቃቀር /ውቅራታቸው እንዳለቀ የቲሙ አባላት በእያንዳንዱ መርሃ-ገብር ዙሪያ ያላቸውን
ኃላፊነት ወደ ማቀናጀት ሥራ ይገባሉ፡፡ የተለያዩ መርሃ-ግብሮች የተደራጁ፣ የሚመሩና በእጅ የተጨበጡ
/become handy / በመሰሉ ጊዜ ቲሙ ከጋንት ቻርት፤ ከካላንደርና ከጊዜ ሰሌዳ /team switch between Gantt
chart, calendar & timeline/ ጋር ማበሪያ ማጥፊያውን እያንቀሳቀሰ ትኩረቱን አድርጎ ቀጣዮች ሂደቶች
እንዲተገበሩ ያደረጋል፡፡

በዚህ ደረጃ ላይ የግንባታ ዶክመንት አመራር በጣም አስፈላጊ ይሆናል፡፡ እነዚህ አንዴ ይሁንታን አግኝተው
ከተረጋገጡ /once securing permits or entitlements / ሁሉም ፕሮጀክት ነክ ዶክመንቶች /all project
released documents location / ዳታን አንድ በማዕከላዊነት ማግኘት በሚቻልበት ስፍራ /stored in one
centralized ማንም ሰው ማለትም ዳታውን የሚፈልገው አግኝቶ ሊጠቀምባቸው /accessible by anyone /
በሚቻልበት ሁኔታ የማደራጀትና የማከማቸት ሥራ ይሰራል፡፡

You might also like