You are on page 1of 8

የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ


I. አጠቃላይ መግለጫ
የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
የከተማ አረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሠረተ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት
ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር
ልማት ስታንዳርድ ዝግጅት መሀንዲስ III ስታንዳዳይዜሽን ዴስክ

የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ


የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ
ልማት ስታንዳዳይዜሽን ዴስክ ኃላፊ

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት


2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-
በከተሞች ለሚገነቡ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች የዲዛይን፣ ግንባታ፣ የግብዓት አጠቃቀም ስታንዳርድ በማዘጋጀት፣
የመሰረተ ልማት ግንባታ ስታንዳርድ ትግበራ ሥርዓት በመዘርጋት፣ የአረንጓዴና የአካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች የአካባቢና
ማህበራዊ ደህንነት ባረጋገጠ መልኩ እንዲገነቡ ድጋፍና ክትትል በማድረግ፣ በከተሞች የሚገነቡ አረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ
ልማቶች ስታንዳርዱን ጠብቀው እንዲገነቡ በመከታተልና በመደገፍ የመሠረተ ልማት አቅርቦቱ በሥርዓት እንዲመራ ማድረግ
ነው፡፡

2.2. ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት


ውጤት 1፡ ለአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ የግንባታ መሰረተ ልማቶች ቅድመ ዲዛይን ዝግጅት ሥራዎች ይሰራል፣ ዲዛይን ያዘጋጃል፣
 ለዲዛይን ቅድመ ዝግጅት የሚስፈልጉ የዲዛይን ፍላጎትና የመሠረተ ልማት ዓይነቶች ይለያል፣
 የመሰረተ ልማቶች ዲዛይን ለማዘጋጀት የሚያስችል ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል የጥናት ማስፈጸሚ ሰነድ ያዘጋጃል፣ ያቀርባል፣
 የግንባታ ዲዛይን ደረጃዎችን ከከተሞች ደረጃ/ፈርጅ በመለየት ፕሮፖዛል ያቀርባል፣ ግበረመልስ ሲሰጥ ያስተካክላል፣
 አረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ የግንባታ መሰረተ ልማቶች የመሰረተ ልማቶች ስታንዳርድ ድራፍት ዲዛይን ያዘጋጃል፣ ያቀርባል፣
ግበረመልስ ሲሰጥ በተሰጠው አስተያየት መሰረት ያካትታል፣

1
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

 ለሚዘጋጁ ዲዛይኖች ግብዓት ለማሰባሰብ የሚስችል መድረክ ያመቻቻል፣ ግብዓቶችን ይመዘግብል፣ አደራጅቶ ያቀርባል፣
 በጥናትና ዲዛይን ሥራዎች ላይ አስተያየት ይሰጣል፣ ይከታተላል፣ በወቅቱ እንዲቀርቡና የተዘጋጁ ዲዛይኖችንና የሥራ ዝርዝሮችን
ትክክለኝነት በመመርመር ማረጋገጫ ይሰጣል፣ ርክክብ እዲፈጽሙ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣
 በአማካሪ ለሚዘጋጁ ዲዛይኖች ለአማካሪ ግዥ የሚሆን TOR መነሻ ጽሁፍ ያዘጋጃል፤
 ለአማካሪ ግዢ የሚያገለግሉ መነሻ RFP ያዘጋጃል፤ ያቀርባል፣
 በዲዛይን አማካሪዎችና በውስጥ ባለሙያዎች በተዘጋጁ የጨረታ ሰነዶች የምዘና መስፈርቶች ያዘጋጃል ያቀርባል፣
 ከአማካሪ ድርጅቶች ጋር ኮንትራት ከመፈራረሙ በፊት የአማካሪዎች አጠቃላይ አቅምና ድርጅቶች ቀደም ሲል ያከናወናቸውን
ሥራዎች ጥራት እንዲሁም ሌሎች ሁኔታዎች አጥንቶ ያቀርባል፣ አስተያት ሲሰጥ ግብዓት ያካትታል፣
 የህዝብና የባላድርሻ አካላት በማሳተፍ የኢኮኖሚ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ የአካባቢውን ግብዓት እንዲጠቀሙ
በሚያደርግና የውጪ ምንዛሪ በሚቆጥብ መልኩ የዲዛይን አማራጭ ያዘጋጃል፣ አስተያየት ሲሰጥ ያካትታል፣
 በአካባቢና ማህበራዊ ጥናት የተመለከቱ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያደርሱ ጉዳዮች በዲዛይን እንዲካተቱ አደራጅቶ ያቀርባል፣
ግብረመልስ ሲሰጥ ያካትታል፣
 ከክልሎችና ከተሞች እንዲሁም ከፌደራል መ/ቤቶች ለሚቀርቡ የስታናዳርድ እና ዲዛይን ዝግጅት ለሚቀርቡ የድጋፍ ጥያቄዎች እንደ
አግባብነታቸው ምላሽ እንዲሰጣቸው ያደርጋል፤
 በአረንጓዴና አካባቢ መሰረተ ልማቶች ውስጥ የሚሰሩ ግንባታዎች የሚያፈልጋቸውን የግንባታ ግብዓትና ተስማሚነት ያጠናል፣
ግብዓቶችን በዓይነት ለይቶ ያቀርባል፣
 ቅድመ ዲዛይን ዝግጅት በከተሞች ለሚገነቡ መሰረተ ልማቶች ለዲዛይን ግብዓት የሚሆን ጥናት ያደርጋል፣
 ለአፈፃጸም ክትትል ስራ የሚያገለግሉ ረቂቅ የአፈጻጸም ግምገማ መረጃ ማሰባሰቢያና መገምገሚያ ቅጾችና ቼክሊስቶችን
ያዘጋጃል፣

ውጤት 2፡ የግንባታ ክትትልና ኮንትራት አስተዳደር ሥራዎች ሰታንዳርድ ጠብቀው እንዲሰሩ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
 በአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ውስጥ ለሚገነቡ ግንባታዎች ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ሰነድ ያዘጋጃል፣
የዲዛይን ትግበራን ለመገምገም የሚያገለግሉ ቼክሊስት በማዘጋጀት በመስክ ይገመግማል፡፡
 በአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ውስጥ የሚገነቡ ግንባታዎች በዲዛይናቸው መሰረት መሆኑን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣
የማሻሻ ሀሳብ ያቀርባል፣
 ፕሮጀክቶች በፀደቀዉ የሥራ ዝርዝር እና የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መፈፀማቸዉን ይከታተላል፣ ሪፖርት ያቀርባል፣
 ግንባታዎች በጨረታ ሰነዶችና በኮንትራት ውል ውስጥ መሟላት ያለባቸው ሰነዶች በትክክል መሟላታቸው ክትትል ያድርጋል፣
 የግንባታ ስራዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ወጪና ጥራት መሰረት መከናወናቸውን ይገመግማል ሪፖርት ያቀርባል፣
 የኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች ከፕላንና ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለይቶ ያቀርባል፣
 ሁሉም ግንባታዎች ጥራታቸውን የጠበቁና በተያዘው ዕቅድ መሠረት መከናወናቸውን ርክክብ ከመፈፀሙና ለኅብረተሰቡ
ከመተላለፋቸው በፊት ያሉበትን ሁኔታ ገምግሞ ያቀርባል፣
 የአረንጓዴና የአካካቢ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶት ተግባረዊ በሚደረጉበት አካባቢ የሚገኘው ማህበረሰብ በግንባታ ዕቅድ፣ ትግበራና
ርክክብ ወቅት የሚሳተፍበትን አሰራር ማዘጋጀት፣

2
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

 የአካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ከፕሮጀክት መጠናቀቅ በኋላ ያሉበትን ደረጃ ይከታታል፣ ችግሮች የሚፈቱበትን አማራጭ
ገምግሞ ያቀርባል፣
 የግንባታና የኮንትራት አስተዳደር ሥራዎች የአፈጻጻም ሪፖርት ያዘጋጃል፣
 ከክልሎችና ከተሞች እንዲሁም ከተለያዩ አካላት ለሚቀርቡ የግንባታ ክትትልና ኮንትራት አስተዳደር የድጋፍ ጥያቄዎች እንደ አግባብነታቸው
ምላሽ እንዲሰጣቸው ያደርጋል፤
 የሥራ መደቡን ዓመታዊ የበጀትና የስራ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ በዕቅዱ ላይ ተመስርቶ ሥራዎችን ያከናውናል፣ በስትራቴጅክ ዕቅድ ዝግጅት
ላይ ይሳተፋል፣

ውጤት 3፡- የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት የግንባታ ስታንዳርድና ሌሎች ሰነዶች ያዘጋጃል፣

 የአረንጓዴና አካባቢያዊ መሰረተ ልማት ግንባታ በተመለከተ የግንባታዎች ይዘት፣ መካተት ያለባቸውን ስራዎች፣ የቦታ አቀማመጥ
ተስማሚነትን ታሳቢ አድርጎ ስታንዳርድ ለማዘጋጀት የሚያስችል መረጃ ያደረጃል፣
 የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ስታንዳርድ ዝግጅት ለማካሄድ የሚያስችል የስታንዳርድ አዘገጃጃት አሰራር ይቀርጻል፣
ያዘጋጃል፣
 የሀገርና የዓለም አቀፍ የስታንዳርድ ስርዓትን ለመቀመር የሚስችል ሰነዶች ያሰባስባል፣ የሰነዶችን ይዘት ገምግሞ በአጭሩ አዘጋጅቶ
ያቀርባል፣
 የከተሞች ፈርጅ መሰረት በማድረግ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት መለስተኛ ስታንዳዶች ያዘጋጃል፣ ያቀርባል፣
 በተዘጋጁ የአረንጓዴና የአካባቢ መሰረተ ልማቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት እና ከፈጻሚና አስፈጻሚ አካላት ጋር በሚኖር ምክክር
ይሰተፋል፣ ግብዓቶችን አደራጅቶ ይመዘግባል፣ ያቀርባል፣
 በውጭ አቅም ለሚዘጋጁ የስታንዳርድ ቴክኒካል ሰነዶች ዝግጅት አማካሪ ለመቅጠር የሚያስችል ቢጋር ያዘጋጃል፣
 በአማካሪ ተዘጋጅተው የሚቀርቡ የስታንዳርድ ሰነዶችን ይገመግማል፣ ውጤቱን አደራጅቶ ያቀርባል፣
 የተዘጋጁና ትግበራ ላይ ያሉ የተለያዩ የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ስታንዳዶች ይሰበስባል፣ ክፍተቶችን ለይቶ ያቀርባል፣
 በሴክተሩ የተሻሉ ናቸው የሚባሉ የስታንዳርዶችን ሰነዶች ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የሚሄዱበት አግባብ በማጥናት
በአዳዲስ ወይም ማሻሻያ ስታንዳርዶች የሚካተቱበትን አማራጭ ሀሳብ ይሰጣል፣በሚመለከተው አካል ሲደገፍም
እንደየአስፈላጊነታቸው ያካትታል፤
 የከተሞች ፈርጅ መሰረት በማድረግ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ስታንዳዶች ዝግጅት ላይ ይሳተፋል፣

ውጤት 4፡- የአረንጓዴና የአካባቢ ጥበቃ መሠረተ ልማት ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ላይ ስልጠናዎች መስጠት
 ለስልጠና የሚስፈልጉ የተለያዩ የስታንዳድ ትግበራ ልምዶችን ተንትንኖ ያቀርባል፣
 ለሚሰጡ ስጠናዎች የሚሆኑ በዲዛይን ዝግጅትና ግንባታ ትግበራ ሂደት የሚያሳዩ ሰነዶች ያሰባስል፣
 መለስተኛ ስልጠናዎችን በዲዛይንና ግንባታ ትግበራ ላይ ይሰጣል፣
 የስታንዳርዶችን ሰነዶች በባለድርሻ አካላትና የዘርፉ ተዋንያን ለማስረጽ የሚያስችሉ ትምህርታዊ ብሮሸሮችና በራሪ ፅሑፎች
ያዘጋጃል፣ለሚመለከታቸው እንዲዳረሱ ያደርጋል፤

3
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች


3.1. የሥራ ውስብስብነት
 ሥራው ለተለያዩ መሰረተ ልማቶች (ለዘመናዊ ቄራ፣ ለእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ ለዘላቂ ማረፍያ፣ ለፍሳሽ ማስወገጃና
ማከሚያ፣ ፓርኮች ውስጥ ለሚሰሩ ግንባታዎች፣ አካፋይና አደባባዮች፣ ለተፋሰሶች ልማት የሚሰሩ ግንባዎች ወዘተ)
ድራፍት/መለስተኛ ስታንዳድ ዲዛይን ማዘጋጀት፣ ለቅድመ ዲዛይን ዝግጅት የሚያስፈልጉ ጥናቶች ማድረግና ማቅረብ፣
ለግንባታዎች የሚያስፈልጋቸውን የግንባታ ግብዓትና አስፈላጊነትና የግብዓቶችን ዓይነት ጥናት ማድረግ፣ በውጭ አማካሪ ወይም
በራስ ሀይል የተዘጋጁ ረቂቅ ሰነዶችን በየደረጃው መገምገምና ግብረመልስ መስጠት፣ የስታንዳርዶችን ክፍተት በጥናት መለየትና
ስታንዳርዶችን ለማሻሻል የሚያስችል አማራጭ አዘጋጅቶ ማቅረብ፣ ከባለድርሻ አካላት እና ከፈጻሚና አስፈጻሚ አካላት ጋር

በሚኖር ምክክር ይሰተፋል፣ ግብዓቶችን አደራጅቶ ይመዘግባል፣ ማቅረብ፣ በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች የሀገር ውስጥና የውጭ
ሀገር ተሞክሮዎችን ለመቀመር የሚስችል ሰነዶች ያሰባስባል፣ የሰነዶችን ይዘት ገምግሞ በአጭሩ አዘጋጅቶ ማቅረብ፣ የመሠረተ
ልማት ፕሮጀክቶች የዲዛይን፣ የግንባታና ርክክብ ሂደቶችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ወጪና ጥራት መሰረት መከናወናቸውን
በመስክ መከታተልና ግብረመልስ ማዘጋጀት ይጠይቃል፡፡

 በሥራው ክንውን ወቅት የተሟላ መረጃ አለማግኘት፣ ዲዛይንና ስታንዳድ የሚዘጋጅላቸው መሰረተ ልማቶች ዘርፈ ብዙና ሁለገብ
ክህሎት የሚፈልጉ መሆን፣ የከተማ መሠረተ ልማት የቴክኖሎጂ ፍላጎት ከፍተኛና ተለዋዋጭ መሆኑ፣ በዘርፉ የሚገኘውን የተለያየ
ተሞክሮ ወደ ከአገራዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት የሚጠይቅና አስቸጋሪ መሆን፣ በውጭ በአማካሪ
ድርጅቶችንና ዩኒቨርስቲዎች እና ሌሎች የወጭ አካላት የሚዘጋጁ ሰነዶች ደረጃውን የጠበቀ አለመሆን፤ የአፈጻጸም ሪፖርቶች
ከአስፈጻሚ አካላት ወቅቱን ጠብቆና በተሟላና በሚፈለገው ጥራት ያለመቅረብ፣የአፈጻጸም መረጃዎች ተሟልተውና

ተደራጅተው አለመገኘት፣ የከተማ መሠረተ ልማት ዓይነቶች የተለያዩ በመሆናቸው የተለያየ የአሰራር ስርዓትን የሚከተሉ መሆን፣
በፈጸሚዎች መካከል በሕግ ማዕቀፍና ማስፈጸሚያ ሰነድ የግንዛቤና የእውቀት ክፍተት መኖር፣ በሰነዶች ላይ ያልተካተቱ ቴክኒካል
ጉዳዮች መከሰት የሚያጋጥሙ ችግሮች ሲሆኑ፣
 እነዚህ ችግሮች ለዲዛይንና ለስታንዳድ ዝግጀት የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በጥልቅ በመተንተን፣ ዲዛይንና ስታንዳድ የሚዘጋጅላቸው
መሰረተ ልማቶች የተለያዩ ቢሆኑም ባድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማሳደግና ሚናቸውን በማጎልበት፣ የከተማ መሠረተ ልማት
የቴክኖሎጂ ፍላጎት በማጥናትና ወቅቱን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ፣፣ በዘርፉ የሚገኘውን የተለያየ ተሞክሮ ወደ ከአገራዊ
ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ እንዲሆን የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም፣ በውጭ በአማካሪ ድርጅቶችንና ዩኒቨርስቲዎች እና
ሌሎች የወጭ አካላት የሚዘጋጁ ሰነዶች ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በየደራጃው በመገምገምና ግብረመልስ በመስጠትና
እንዲስተካከል በማድረግ፤ የአፈጻጸም ሪፖርቶች ከአስፈጻሚ አካላት ወቅቱን ጠብቆና በተሟላና በሚፈለገው ጥራት እንዲቀርብ
ለማድረግ የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ፣ የአፈጻጸም መረጃዎች የከተማ መሠረተ ልማት ዓይነቶች የተለያዩ በመሆናቸው
የተለያየ የአሰራር ስርዓትን እነደአመቺነቱ አጥንቶ በመዘርጋት፣ በፈጸሚዎች መካከል በሕግ ማዕቀፍና ማስፈጸሚያ ሰነድ የግንዛቤና
የእውቀት ክፍተት በተካታተይ በዴስክና በተግባር ግንዛቤ በማሳደግ፣ በሰነዶች ላይ ያልተካተቱ ቴክኒካል ጉዳዮች እንዳይከሰጡ

4
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ክትትል በማጠንከር፣ አስቀድሞ በማረም ይፈታሉ፡፡.

3.2. ራስን ችሎ መስራት


3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ሥራው በደንብና መመሪያ፣የወጡ የስታንዳርዶች ሰነዶች፣የአሰራር ሥርአቶችን እና ከቅርብ ኃላፊ የሚሰጥ መመሪያን መሠረት
በማድረግ የሚከናወን ነው፡፡

3.2.2. ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ


 ሥራው በደንብና መመሪያ፣የወጡ የስታንዳርዶችን ሰነዶችን፣የአሰራር ሥርአቶችን እና ከቅርብ ኃላፊ የሚሰጥ መመሪያን
መሠረት አድረጎ በአግባቡ ስለመከናወኑ በመጨረሻ በቅርብ ኃላፊው ይገመገማል፣ይታያል፡፡
3.3. ተጠያቂነት
3.3.1 ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /Responsibility for Impact/፣
 ሥራው ለተለያዩ መሰረተ ልማቶች (ለዘመናዊ ቄራ፣ ለእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ ለዘላቂ ማረፍያ፣ ለፍሳሽ ማስወገጃና
ማከሚያ፣ ፓርኮች ውስጥ ለሚሰሩ ግንባታዎች፣ አካፋይና አደባባዮች፣ ለተፋሰሶች ልማት የሚሰሩ ግንባዎች ወዘተ)
ድራፍት/መለስተኛ ስታንዳድ ዲዛይን ማዘጋጀት፣ ለቅድመ ዲዛይን ዝግጅት የሚያስፈልጉ ጥናቶች ማድረግና ማቅረብ፣
ለግንባታዎች የሚያስፈልጋቸውን የግንባታ ግብዓትና አስፈላጊነትና የግብዓቶችን ዓይነት ጥናት ማድረግ፣ በውጭ አማካሪ ወይም
በራስ ሀይል የተዘጋጁ ረቂቅ ሰነዶችን በየደረጃው መገምገምና ግብረመልስ መስጠት፣ የስታንዳርዶችን ክፍተት በጥናት መለየትና
ስታንዳርዶችን ለማሻሻል የሚያስችል አማራጭ አዘጋጅቶ ማቅረብ፣ ከባለድርሻ አካላት እና ከፈጻሚና አስፈጻሚ አካላት ጋር

በሚኖር ምክክር ይሰተፋል፣ ግብዓቶችን አደራጅቶ ይመዘግባል፣ ማቅረብ፣ በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች የሀገር ውስጥና የውጭ
ሀገር ተሞክሮዎችን ለመቀመር የሚስችል ሰነዶች ያሰባስባል፣ የሰነዶችን ይዘት ገምግሞ በአጭሩ አዘጋጅቶ ማቅረብ፣ የመሠረተ
ልማት ፕሮጀክቶች የዲዛይን፣ የግንባታና ርክክብ ሂደቶችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ወጪና ጥራት መሰረት መከናወናቸውን
በመስክ መከታተልና ግብረመልስ ማዘጋጀት የሚጠይቅ ሲሆን፣
 እነዚህ ተግባራት በአግባቡ ባይከናወኑ ህረተሰቡ ከመሰረተ ልማቶቹ የሚያገኘውን የጤና ጥበቃና የአኗኗር ዘይቤ መሻሻል ያስቀራል፣
የከተማ መሠረተ ልማቶች የሚጠበቅባቸውን አገልግልት እንዳይሰጡ ያደርጋል፣ በመሠረተ ልማት ዝርጋታ የሀብት ብክነትና
በከተማ ነዋሪ ዘንድ ቅሬታ ሊያስከትል ይችላል፣ በቀጣይ የስታንዳርዶችን ሥራዎች ላይ መሰተጓጎልን በመፍጠር በተቋሙ ዕቅድ
አፈፃፀም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡

3.3.2 ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣


 የለበትም፡፡

3.3.3. ፈጠራ
 ሥራው አዳዲስ ስታንዳርድ ዲዛይንና ሰነዶችን ለማዘጋጀትና ነባሩን ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦችን በማፍለቅ፣ በመተንተንና
በመቀመር፤የተገኙ ተሞክሮዎችን ወደ አገሪቷ ተጨባጭ ሁኔታ ለማጣጣም ማስላትን እና ክፍተቶች ላይ ጥናት በማድረግ አዳዲስ
ወይም የተሸሻሉ የአሰራር ስልቶችን መቀየስንና በየጊዜው ማሻሻል የፈጠራ ጥረትን ይጠይቃል፡፡

5
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

3.4. የሥራ ግንኙነት /Work Communication/


3.4.1 የግንኙነት ደረጃ
 ሥራው ከውስጥ ከቅርብ ኃላፊው፤ከክፍሉ ባለሞያዎችና ከሌሎች የስራ ክፍሎች ባለሙያዎች፣ ከውች ከክልልና ከተማ አስተዳደር
አስፈጻሚ አካላት ከአማካሪዎች፣ ከሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች ከሙያ ማሕበራት፣ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ባለሙያዎችና
ኃላፊዎች ጋር ግንኙነት ማድረግ ይጠይቃል፡

3.4.2 የግንኙነቱ ዓላማ


 የሥራ መመሪያ ለመቀበል፣ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን ለማማከር፤በጋራ የሚሰሩ ሥራዎችን ለማከናወን፣ ለመመካከርና
መረጃዎችን ለማሰባሰብ፣ ለመስጠት፣ በቅንጅት ለመስራት፣ የስታንዳርዶችን አፈጻጸምን ለመገምገምና ለመከታተል እንዲሁም
ድጋፍ ለማድረግ ነው፡፡

3.4.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ


 ከመደበኛ የሥራ ሠዓት ጊዜው 30 በመቶ ይወስዳል፡፡

3.5 ኃላፊነት
3.5.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
3.5.1.1 በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
 የለበትም፡፡

3.5.1.2 የኃላፊነት አይነትና ደረጃ


 የለበትም፡፡

3.6 ኃላፊነት ለንዋይ


 የለበትም፡፡

3.6.1 ኃላፊነት ለንብረት


 ሥራው ለቢሮ መገልገያነት የተሰጡትን ወንበር፣ጠረጴዛ፣መደርደርያ እና ኮሚፒዩተር፣ ግምታቸው ብር 150,000.00 (አንድ መቶ
ሃምሳ ሺህ) የሚሆኑ ንብረቶችን በአግባቡ የመያዝና የመጠቀም ኃላፊት አለበት፡፡
3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 አዳዲስ የግንባታ ዲዛይን ስታንዳርድ ሰነዶችን ለማዘጋጀትና ነባሩን ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦችን ማፍለቅና መተንተን፣ በተለያዩ
አካላት የሚቀርቡ ዲዛይኖችን የኮንትራት አስተዳደር ሰነዶችን መገምገምና ግበረ መልስ መስጠት፣ ለዲዛይን ዝግጅ የሚረዱ
ጥናቶችን ማንበብና ግብረመልስ መስጠት፣ በአፈጻጸም ወቅት የሚታዩ የአሰራር ክፍቶች ስታንዳርዶችን መለየትና ወቅታዊ ግብረ
መልስ መልስ መስጠት፣ የውጭና የሀገር ውስጥ ተሞክሮ መቀመርና ማስፋት አእምሮን የሚያደክሙ ተግባራት ሲሆኑ እነዚህም
ከሥራ ጊዜው 70% ይወስዳል፡፡

6
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

3.7.2. ስነልቦናዊ ጥረት


 የስታንዳርዶችን ዲዛይኖች ባለድርሻ አካላት አምነው እንዲተገብሩ ማድረግ፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካት በዲዛይን ዝግጅት፣ በግንባታ
ትግበራ ሂደት ግምገማ ለማሳተፍ በሚደረጉ ጥረቶች ከባለቤትነት ስሜት ማጣት እንዲሁም ስታንዳርዶችን ከሚተገብረው አካል
ጋር በሚፈጠሩ ክርክሮች እና የሀሳብ አለመግባባቶች ስነልቦናን የሚፈታተኑ ሲሆኑ እነዚህን በትዕግስትና በተረጋጋ ስሜት ተቋቁሞ
ሥራዎችን ውጤታማ ማድረግ ይጠይቃል፡፡

3.7.3 የዕይታ ጥረት፣


 ሥራው ለተለያዩ መሰረተ ልማቶች (ለዘመናዊ ቄራ፣ ለእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ ለዘላቂ ማረፍያ፣ ለፍሳሽ ማስወገጃና
ማከሚያ፣ ፓርኮች ውስጥ ለሚሰሩ ግንባታዎች፣ አካፋይና አደባባዮች፣ ለተፋሰሶች ልማት የሚሰሩ ግንባዎች ወዘተ) ስታንዳርድ
ዲዛይን በኮምፕዩተር ማዘጋጀት፣ የተዘጋጁ ስታንዳርዶችን በማንበብ መገምገምና ማረጋገጥ፣ የጥናት ሰነዶችን በማንበብ
መገምገምና ማረጋገጥ፣ ለግንባታዎች የሚያስፈልጋቸውን በውጭ አማካሪ ወይም በራስ ሀይል የተዘጋጁ ረቂቅ ሰነዶችን

በየደረጃው በማንበብ መገምገምና ግብረመልስ መስጠት፣ማረጋገጥ፣ በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር

ተሞክሮዎችን ለመቀመር የተለያ ሰነዶችን ማገናዘብ፣ ኮምፒዩተር በመጠቀም ሰነዶችን በጥንቃቄ ማዘጋጃት፣ ጽሁፎችን
ማንበብና መተንነተን እይታን የሚያደክሙ ተግባራት ሲሆኑ እነዚህም ተግባራት ከሥራ ሰዓቱ 40 በመቶ ይወስዳሉ፡፡

3.7.4 የአካል ጥረት


 ሥራው 70 በመቶ በመቀመጥ እና 30 በመቶ በመንቀሳቀስ የሚከናወን ነው፡፡

3.8. የሥራ ሁኔታ


3.8.1. ሥጋትና አደጋ
 የለበትም፡፡
3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ
ሥራው ምቹ በሆነ የሥራ አከባቢ ይከናወናል፡፡
3.9. እውቀትና ክህሎት፣
3.9.1 ትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት

በሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ በሳኒታሪ/ሃይድሮሊክስ/፣ በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ


የመጀመሪያ ዲግሪ
ማኔጅመነት፣ አግሪካልቸራል ኢንጀር፣ ስትራክቸራል ምህንድስና፤ አርባን ኢነጂነሪንግ

3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ


የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
4 ዓመት ቀጥታ አግበብነት ያለው የሥራ ልምድ

7
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like