Professional Documents
Culture Documents
0 Com
0 Com
መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ
1
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች አስመልክቶ በሚዘጋጁ የፖሊሲና የስትራቴጂ ሰነዶች ሲቀረጹ ይሳተፋል፣
ይገመግማል፣ ለውሳኔ ያቀርባል፣
የከተማ መሰረተ ልማት በተመለከተ የፖሊሲ ግብአትና የፖሊሲ አፈጻጸም ግምገማ ጥናትና ምርምሮች እንዲካሄድ ያደርጋል፣ ይገመግማል፣
ያስጸድቃል፣
የከተማ መሰረተ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጅና መተግበሪያ አማራጮች ይቀይሳል ለተግባራዊነታቸውም ለክልሎች፤ ከተሞችና ለግሉ ዘርፍ ድጋፍ
ያደርጋል፡፡
ለለአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች የዲዛይን ዝግጅት የሚስፈልጉ ጥናቶች ያስደርጋል፣ ለዲዛይን ዝግጅት
በግብዓትነት ይጠቀማል፣
በግንባታ ሂደት በዲዛይን ምክንያት የሚያጋጥሙ ችግሮችን፣ መንስኤውንና መፍትሔውን በጥናት ይለያል፣
የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ስታንዳድር ዝግጅት ለማካሄድ የሚያስችል የዲዛይን አዘገጃጃት አሰራር
እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣
የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሠረተ ልማቶች የጥገና አፈጻጸም ነባራዊ ሁኔታ ያጠናል፣ ለስታንዳድ ዝግጅት በግብዓትነት
ይጠቀማል፣
የከተሞች የመሰረተ ልማት ስራዎች ግንባታ ዲዛይኖች፤ ግብአቶች፤ የግንባታ ውህዶች፤ የግንባታ ሂደትና ውጤት ደረጃ
ለማውጣት የሚያስችል ጥናት ያስደርጋል፣ የጥናት ውጤት ይገመግማል፣ ያስጸድል፡፡
በከተሞች የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት እያረጋገጡ የሚተገበሩ መሆኑን በጥናት እንዲረጋገጥ ያደርጋል፣
ይገመግማል፣ ውጤቱን ያስፈጽማል፣
የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች የግንባታ አተገባበር ሂደትን በማጥናት የአሰራር ማሻሻያ እንዲደረግ ሀሳብ ያቀርባል፣ ያጸድቃል፣
እንዲተገበሩም ይሰራል፡፡
ውጤት 3፡- የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት አቅርቦት ሊከተላቸው የሚገባ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት
የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች በከተሞች ደረጃ መተግባር የሚችሉበትን ሁኔታ ከከተሞች ያልተማከለ
አስተዳደር ስርዓት ጋር በማስተሳሰር መሰረተ ልማቶቹና የከተሞች ደረጃ የተጣጣመ እንዲሆን በጥናት ይለያል፣ በዚሁ
መሰረትም ስራዎችን እንዲሰሩ ያደርጋል፣
በስራ ላይ ያሉ የከተማ መሰረተ ልማት የግንባታ ዲዛይኖችን በመፈተሽ ሞዴል ዲዛይኖችን እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣
ዲዛይኖቹ በከተሞች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያስተባበራል፣ ይመራል፣
ከተቋሙ አቅም በላይ የሆኑ የዲዛይን ሥራዎች ሲኖሩ በክልሎች ወይም በከተሞች ውክልና በውጭ አማካሪ መሃንዲሶች እንዲሰሩ
2
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
በክልሎችና ከተሞች የሚተገበሩ አረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶችን በመስክና በመድረክ በመገኘት አተገባበራቸውን ይከታተላል
ይገመግማል፣
የተዘጋጁ ዲዛይኖችና ስታንዳርዶች በከተሞች ተግባር ላይ ሲውሉ ያስገኙትን ፋይዳ ይገመግማል፣ ይደግፋል፣ ማሻሻያ ሲያስፈልግ ያስፈጽማል፣
በክልሎችና ከተሞች የሚቀርቡ የዲዛይን ዝግጅት ድጋፍ ጥያቄዎች አጥንቶ ድጋፍ ያደርጋል፣
አዲስ ለሚሰሩና በመሰራት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች በውሉ መሠረት ጥራታቸውንና ደረጃቸውን ጠብቀው በተያዘላቸው ጊዜ መሠራታቸውን
3
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
ያረጋግጣል፣
ውጤት 5 ፡- የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ስታንዳርዶች ማስተዋወቅ፣ ማስፋፋትና የማስረጽ ስልጠናዎች እንዲከናወኑ ማድረግ፣
አዲስ የወጡና የተሻሻሉ የጸደቁ ስታንዳርዶች ለዘርፉ ተዋንያንና ባለድርሻ አካላት መዳረሳቸውንና መተዋወቃቸውን
ያረጋግጣል፤
በስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ መሰረት በስታንዳርዶች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚያስችሉ ስልጠናዎች እንዲሰጡ ውሳኔ
በመስጠት አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
አዲስ የወጡና የተሻሻሉ ስታንዳርዶች በባለድርሻ አካላትና የዘርፉ ተዋንያን ለማስረጽ የሚያስችል ሥልጠና እንዲዘጋጅ
ያደርጋል የስልጠናውን ዝክረ ተግባር ያፀድቃል፤
ስልጠና እንዲሰጥባቸው በተመረጡ ስታንዳርዶች ላይ አስፈላጊ የሆኑ የስልጠና ሰነዶችና ግብዓቶች መዘጋጀታቸውን
ያረጋግጣል፣
በአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች በተዘጋጁ ደረጃዎችና ስታንደርዶች ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ የስልጠና
ፅሑፎች እንዲዘጋጁና አንዲሰጡ በማድረግ የስልጠና ሂደቱን ያስፈፅማል ይመራል፣
ሥራው የዴስኩን ሥራ ማቀድ፣ መምራት፣ ማስተባበርን፣ በዴስኩ የሚዘጋጁ የተለያዩ የአረንጓዴና አካባቢ
4
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
ጥበቃ መሠረተ ልማት ኮዶችና ስታንዳርዶች ጥናቶችና የሚዘጋጁ ስትራቴጂዎች በመገምገም ማስወሰን፣ ለሚዘጋጁ
ዲዛይኖች ቅድመ ዲዛይን የሚሰሩ የአዋጭነት ጥናቶችን መገምገምና ማስጽደቅ፣ የሚዘጋጁ የመሠረተ ልማት
የግንባታ ዲዛይኖችን ከመሰረተ ልማት ዓይነትና ከከተሞች ደረጃ አንጻር አግባብነቱን መርምሮ ማስወሰን፣ በከተሞች
ለሚገነቡ መሰረተ ልማቶች የስራና የአገልግሎት የጥራት ደረጃ ለመወሰን የሚዘጋጁ ሰነዶችን መርምሮ ማስጽደቅን፣
የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ስታንዳርዶች እንዲዘጋጁ ማድረግ፣ መገምገምና ማስጸደቅ፤ ከሌሎች
አካላት የሚቀርቡ የዲዛይን ዝግጅትና የግንባታ አፈጻጸም ድጋፍ ጥያቄዎች መርምሮ መደገፍን፣ የስታንዳርድ ዓለም
አቀፍ ተሞክሮ መቀመርና ከሀራዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ እንዲተገበሩ ማድረግ፣ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ
መሠረተ ልማቶች የግብዓት ዓይነቶችን መለየትና የጥራት ደረጃ እንዲዘጋጅ ማድረግ፣ መገምገምና ማጸደቅ፣
የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሠረተ ልማቶች የግንባታ አተገባበር ስርዓት መፍጠር መደገፍና መከታተል፣ በዴስኩ
የሚሰሩ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውን ስራዎችን መወሰን፣ የዴስኩ የአፈጻጸም ስርዓት አዳዲስ የአሰራር ዘዴዎችን
የተከተለና የተገልጋዮች እርካታና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የአሰራር ስልት በመቀየስ ተግባራዊ
እንዲሆን ማድረግ የሚጠይቅ ነው፡፡
የሚዘጋጁ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ጥናቶች ውስብስብነት የአካበቢና ማህበራዊ
5
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
3.3. ተጠያቂነት
3.3.1 ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /Responsibility for Impact/፣
ሥራው ለከተማ መሰረተ ልማቶች የከተሞችን ደረጃ በሚመጥን መልኩ ጥራት ያለው ዲዛይን
እንዲዘጋጅ ማድረግ፣ አዳዲስ የመሰረተ ልማት የስታንዳርዶች እንዲዘጋጁ ማድረግ፣ በውጭ አቅም
ለሚዘጋጁ ሰነዶች/ስታንዳርዶች/ የአማካሪ ግዥ ሰነዶች ማዘጋጀትና ሰነዶችን መገምገምና
ግብረመልስ መስጠት፣ የግንባታ ደረጃውን ጥራት ለማስጠበቅ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ ጥራት ያለው ደረጃ
ማውጣትን፣ የከተማ መሰረተ ልማቶች የጥራት ስታንዳርድ በተመለከተ ጥናት ማድረግና እንዲሻሻሉ
ያልጸደቁና በረቂቅ ሂደት የሚገኙ የደረጃና ስታንዳርድ ዝግጅት በሚስጥር መያዝ ወይም መጠበቅ
ያለባቸው ሲሆን እነዚህን ሰነዶች በማይመለከታቸው እጅ ቢገቡ በተቋሙ ላይ ተአማኒነትን ያሳጣል፡፡
3.4. ፈጠራ
ሥራው በዘርፉ ለሚዘጋጁ አዋጅና ደንቦች ዝግጅት የሚያስፈልጉ ሀሳቦችን ማመንጨት፣ የሚዘጋጁ
ስታንዳርዶች ሀገራዊ ተጨባጭን ያገናዘቡ እንዲሆኑ ማሰላሰልንና ሲተገበሩ በማህበረሰብ ላይ
የሚያሳድሩን ተጽዕኖ አሰላለስሎ ማሰራት፣ የዲዛይን ዝግጅቶች አዳዲስ አሰራር እንዲያካትቱ
ማድረግና አንደምታቸውን ማጤን የሚፈልግ መሆኑ፣ የሚደረጉ ጥናቶች አዳዲስ ዕይታዎችን
እንዲካትቱ ማድረግና በማሰላሰል ገምግሞ ግብረመልስ መስጠትን፣ ተሞክሮዎችን በመቀመር እና
ክፍተቶች ላይ ጥናት በማድረግ አዳዲስ ወይም የተሻሻሉ የስታንዳርዶች የአሰራር ስርአትን
ማዘጋጀትና ማሻሻል ይጠይቃል፣
3.5. የሥራ ግንኙነት /Work Communication/
3.5.1. የግንኙነት ደረጃ
7
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
ሥራው መመሪያ ለመቀበል፣ ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን ለማማከርና ለመወያየት፤ በጋራ የሚሰሩ
ሥራዎችን ለመወሰን፣ የታቀዱ ስራዎችን በተያዘላቸዉ ጊዜ መፈጸማቸዉን ለመከታተል
ለመገምገም፣ በአሰራር ችግሮች ዙሪያ ለመወያየት፣ ለተዘጋጁ ረቂቅ ሰነዶች ግብዓት ለማሰባሰብና
ለማፀደቅ፣ በስራ ላይ በዋሉ ሰነዶች አፈጻጸም ዙሪያ ማብራሪያ ለመስጠትና ለማስረዳት፣ የግሉ
ሴክተር በግልና በመንግስት አጋርነት እንዲሳተፍ ለማመቻቸት፣ የስልጠና ሂደቶችን ለመከታተልና
አፈጻፀሙን ለመገምገም ነው፡፡
3.7. ጥረት
3.7.1. የአዕምሮ ጥረት
ሥራው ለከተማ መሰረተ ልማቶች የከተሞችን ደረጃ በሚመጥን መልኩ ጥራት ያለው ዲዛይን እንዲዘጋጅ ማድረግን፣
አዳዲስ የመሰረተ ልማት የስታንዳርዶች እንዲዘጋጁ ማድረግ፣ የግንባታ ደረጃውን ጥራት ለማስጠበቅ ጥናት
እንዲካሄድ በማድረግ ጥራት ያለው ደረጃ ማውጣትን፣ የከተማ መሰረተ ልማቶች ስታንዳርድ በተመለከተ ጥናት
ማስደረግና እንዲሻሻሉ ማድረግ፤ ጥናቱን በበላይነት መምራት መከታተልና መገምገምን፣ የተዘጋጁና የተሻሻሉ
የስታንዳርድ ሰነዶች ከአገራዊና ከዘርፉ ፖሊሲና ስትራቴጂ ጋር የተገናዘበና የተጣጣመ መሆኑን መገምገምና
ማረጋገጥን፣ ከአፈጻጸም ክትትል ቡድኑና ከአስፈጻሚ አካላት የቀረቡ የአፈጻጸም ሪፖርቶችን መገምገምንና ለታዩ
የአፈጻጸም ክፍተቶች ግብረመልስ መስጠት፣ የወጡ የመሰረተ ልማት ፖሊሲዎች፣ ሕጐች፣ ደንቦችና መመሪያዎች
በተግባር ያስከተሉትን ለውጥ መገምገም፣ የተለያዩ ሀገራትን ተሞክሮ ከተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ተግባራዊ ሊሆኑ
8
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
የሚችሉትን መንገድ መቀየስ አዕምሮ የሚያደክሙ ሲሆኑ፣ ይህም ከቀን የሥራ ጊዜው 75 በመቶ ይወስዳል፡፡
9
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
10