You are on page 1of 9

የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ


I. አጠቃላይ መግለጫ
የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት የከተማ አረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ባለሙያ III መሰረተ ልማት ስታንዳርዳይዜሽን
ዴስክ

የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ብቻ የሚሞላ


የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ
የከተማ አረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት
ስታንዳርዳይዜሽን ዴስክ ኃላፊ

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት

1
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

2.1 የሥራ መደቡ ዓላማ፡-


በሥራ መደቡ የተሰጠውን ሥራ በማቀድ፣ አፈጻጸሙን በመከታተልና በመደገፍ፣ ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ በመገምገም፣
በከተሞች የሚገነቡ አረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች የአካባቢማ ማህባረዊ ደህንነት ሥራዎች ግንባታ ከመጀመሩ
በፊት በአከባቢና በሰው ልጆች ላይ የሚሳደር ተፅዕኖ ካላ ማስተካካያ እርምጃዎች በስታንዳርድ ዲዛይን እና በኮንትራት የውል
ሰነድ መሠረት መሆኑን ለማረጋገጥ የአሠራር ሥርዓት በማዘጋጀትና እንዲፈጸም ድጋፍና ክትትል በማድረግ ፕሮጀክቶች
በተያዘላቸው ጊዜ፣ በሚፈለገው የጥራት ደረጃና በተመደበላቸው በጀት ተገንብተው ለአገልግልት እንዲበቁ የግንባታ ቁጥጥርና
ኮንትራት አስተዳደር ስርዓት በመፍጠር፣ የኢኮኖሚ መሰረተ ልማቶች የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ባረጋገጠ መልኩ ድጋፍና
ክትትል በማድረግ፣ በከተሞች የሚገነቡ ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማቶች ደረጃውን በጠበቀ ስታንዳርድ እንዲገነቡ በማድረግ
የመሠረተ ልማት ግንባታ ቀጥጥርና አስተዳደር በሥርዓት እንዲመራ ማድረግ ነው፡፡

2.2.ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት


ውጤት 1፡ የሥራ መደቡን ሥራ ማቀድ፣ ማስተባበርና መገምገም
 የሥራ መደቡን ዓመታዊ የበጀትና የስራ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ በዕቅዱ ላይ ተመስርቶ ሥራዎችን ማከናወን፣
 የአካባቢ ጥበቃና ማህበራዊ ደህንነት ሥራዎችን ያሰተባበራል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣ ውሳኔ ለሚያስፈልጋቸው
ጉዳዮች ወቅታዊ ምላሽ ይሰጣል፣
 የአካባቢ ጥበቃና ማህበራዊ ደህንነት አያያዝ ዕቀድ (ESMP) አፈጻጸምን ተከታትሎ ችግሮች ከተከሰቱ ተገቢ የእርምት
እርምጃ ለመውሰድ ወይም እንዲወስድ ማድረግ፣
 የአካባቢና ማህበራዊ ጉዳይ በተመለከተ በግንባታ የውል ሰነድ ላይ የሚፈሪሙበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣ መከታተልና መደገፍ፣
የሥራ ተቋራጮችን ማሰገደድ የሚቺሉበት አሠራር ሥርዐት በመዘርጋት እንዲፈጻም ማድረግ፣
 የግንባታ ፕሮጀክቶች የሚከናወንበት ቦታ ከሶስተኛ ወገን ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ፣ የሁሉም ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን
የአካባቢ እና ማህበራዊ ተጽዕኖ ጥናት ግምገማ መሠራቱን ማረጋገጥ እንዲቻል ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣
 ሀገራችን በምትከተለው የአካባቢያዊና ማህበራዊ ደህንነት ማእቀፍ ማንዋል እና በተቀመጠው ቼክ ሊስት መሰረት የአካባቢና
ማህበራዊ ችግሮቹን ዳስሰው የጠበቀ የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ልየታ(Screening) ሪፖርት እንዲዘጋጅና እንዲጸድቅ
ይከታተላል፣ ገምግሞ ግብረ መልሰ ይሰጣል፣
 የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ልየታ(Screening) ሪፓርት ሳይዘጋጅ ፤ የፕሮጀክቶች የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ
ጥናት ሳይሰራ እና የተፈናቀሉ ግለሰቦች የካሳ ክፍያ ሳይሰጥ የፕሮጀክት የግንባታ ስራ እንዳይጀመር ያደርጋል፤
 የአካባቢና ማህበረዊ ደህንነት ሥራዎች አፈጻጻም በየወቅቱ ይገመግማል፣ ለሚመለከተው አካል ወቅታዊና ጥራቱን የጠበቀ
ሪፓርት ያቀርባል፣ ግብረ መልስ በሪፖርቱ ላይ ሲሰጥም አስፈላጊ ማስተካከያዎችን ያደርጋል፣
 በአካባቢና ማህበረዊ ደህንነት ሥራዎች ላይ ለሚሳተፉ ባለሙያዎችን የስልጠና ፍላጎት ይለያል፣ ስልጠናዎችን ያመቻቻል፣
በተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል፣ የሥክጠና ሪፖርት ያዘጋጃል፣

ውጤት 2፡ በአካባቢና ማህበረዊ ደህንነት ሥራዎች የግንባታ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣

2
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

 በቅርበትና በቅንጅት ከተሞችንና ክልሎችን በመደገፍ በከተሞች በቀጣይነትም የመፈጸም አቅምን በማጎልበት የአካባቢና
ማህበራዊ ደህንነት ሥራ አፈጻጸም እንዲሻሻል ድጋፍ ያደርጋል፣
 በፕሮጅክቶች ግንባታ ምክንያት ይዞታቸው ወይም ንብረታቸው ለሚነካባቸው ባለይዞታዎች በአግባቡ ካሳ መክፈል እንዲቻል
የካሳ ክፍ የአሠራር ሥርዓትን ተከትሎ ከተሞች በቂ ገንዘብ በዓመታዊ በጀታቸው ውስጥ ማካተታቸውን ለማረጋጋጥ ክትትልና
ድጋፍ ያደርጋል፣
 በአካባቢና ማህበረዊ ደህንነት ሥራዎች ይገመግማል፣ ቸግሮች እንዲሻሻሉ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል
 ፕሮጀክቶች(Environmental and Social screening) አከባቢና ማህበራዊ ደህንነት ልየታ እንዲሰራላቸው ከትትልና ድጋፍ
ይደረጋል፡፡
 በከተሞች ለሚገነቡ ፕሮጀክቶች ከፊል እና ሙሉ EIA እንዲሁም ARAP እና RAP ለሚያሰፈልጋቸዉ ፕሮጀክቶች
ጥናታቸው እንዲዘጋጅና በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እንዲጸድቁ እና እንዲተገበር ድጋፍና ክትትል ይድረጋል፣
 በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የጸደቁና የአካባቢያዊ ደህንነት ልየታ ሪፖርት መስረት እየተተገበሩ መሆናቸውን በመስክ በመገኘት
አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ይደረጋል፣ መረጃዎችን በመሰብሰብና በመተንተን፣በማጠናቀር ሪፖርቶችን ያዘጋጃል፣
 ዓመታዊ የአካባቢ እና ማህበራዊ ስራዎች ኦዲት በሚመለከተው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን መደረጉን ይከታተላል፣
ስለአፈጻጸሙም ሪፖርት ያዘጋጃል፣
 በከተሞች ለአደጋ ስጋት ይጋለጣሉ ተብለው ለተለዩት ቦታዎች አደጋ ስጋት ካርታ እንዲያዘጋጁ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣

ውጤት 3፡ የአካባቢና ማህበረዊ ደህንነት ስርዓት እንደዘረጋ ማድረግ፣

 ለኢኮኖሚያዊ መሠረተ ልማት የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ስርዓት የአሠራር ስርዐት እንዲዘረጋ ያደረጋል፣ በአፈጻጸም
ወቅትም ከትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣
 ከከተማ መሰረተ ልማት ወሰን ማስከበር አኳያ የህብረተሰቡንና የሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ሚና የአሠራር ሥርአት
እንዲዘረጋ ያደርጋል፣አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
 የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ እና የመልሶ ማስፈር የሚያስፈልጋቸው ፕሮጀክቶቸ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ተለይተው የአካባውን
ማህበረሰብ በማሳተፍ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ እና የመልሶ ማስፈር የተዘጋጀላቸው ፕሮጀክቶቸ ፕሮጀክቱ ከመጀመሩ በፊት
ተግባራዊ አንዶሆኑ እንዲረጋገጥ ያደርጋል፣ ግብረ መልስም ተከታትሎ ይሰጣል፣
 በአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ሥራዎች የሚያጋጥሙ ችግሮችን፣ መንስኤውንና መፍትሔውን በጥናት ይለያል፣ በአሠራር ስር\
ዐቱ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ይደርጋል፣ ከፍተቶችን በመለየት የአቅም ግንባታ ሥራ ያከናውናል፣

ውጤት 4፡ ከአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ጋር የተያየዙ ጥናቶች እንዲካሄዱ ማድረግ፣ መገምገምና ማረጋገጥ፣

 በአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ሥራዎች አፈጻጸም ዙሪያ የሚታዩ ቸእግሮች እንዲሻሸሉ የተለያዩ የፖሊሲ ሀሳቦችን ያመነጫል፣
 በአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ማረጋገጥ ሥራ ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመለየት ችግር ፈቺ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ ተግባራዊ

3
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

እንዲሆን ይሰራል፣
 በከተሞች የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት እያረጋገጡ የሚተገበሩ መሆኑን በጥናት እንዲረጋገጥ
ያደርጋል፣ ይገመግማል፣ ውጤቱን ያስፈጽማል፣
 በከተማ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ዙሪያ የሚያጋጥሙ የወሰን ማስከበር ችግሮችንና ክፍተቶችን ለመለየት የሚያስችል
ጥናት ያጠናል፤ሀሳብ ያመነጫል፣ተሳታፊ ይሆናል፡፡
 የከተማ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በወሰን አለማስከበር ምክንያት በሚፈጠር መጓተት የሚወጣውን ወጪ ጥናት እንዲዘጋጅ
በማድረግ ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጠው ያደርጋል፤
 ሊሰሩ የታሰቡ የግንባታ ሥራዎች በአካባቢ ላይ የሚፈጥሩት ተፅዕኖ እንዲጠና በማደረግ በጥናቱ ውጤት መሠረት አፈፃፀሙን
ይከታተላል፣
 በጥናት ላይ በመመስረት፤ የመከታተያ ቅፆችን፤ የአሰራር ሥርዓቶችን እና ስታንዳርዶችን በየወቅቱ እንዲሻሻሉ ያደርጋል፣
ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፡፡
 የግንባታ ሥራዎች በአከባቢ ላይ የሚፈጥሩት ተፅዕኖ ከግንባታ በፊት መሠራቱ አንዲረጋገጥ ያደርጋል፣ በጥናቱ ውጤት መሠረት
አፈፃፀሙን ይከታተላል፣

III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች

3.1. የሥራ ውስብስብነት

 የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ልየታ(Screening) ሪፓርት ሳይዘጋጅ ፤ የፕሮጀክቶች የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ
ጥናት ሳይሰራ እና የተፈናቀሉ ግለሰቦች የካሳ ክፍያ ሳይሰጥ የፕሮጀክት የግንባታ ሥራ እንዳይጀመር ማስደረግ፣ የአካባቢና
ማህበራዊ ደህንነት ልየታ(Screening) ሪፖርት እንዲዘጋጅና እንዲጸድቅ መደገፍና መከታተል፣ ፕሮጀክቶች ከፊል እና ሙሉ
EIA እንዲሁም ARAP እና RAP ለሚያሰፈልጋቸዉ ፕሮጀክቶች ጥናታቸው እንዲዘጋጅና በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
እንዲጸድቁ እና እንዲተገበር ድጋፍና ክትትል ማደረግ፣ የፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን የአካባቢ እና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ
ማካተቱንና ከግንባታ በፊት መሠራቱን ማረጋገጥ፣ በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የጸደቁና የአካባቢያዊ ደህንነት ልየታ ሪፖርት
መስረት እየተተገበሩ መሆናቸውንና ዓመታዊ የአካባቢ እና ማህበራዊ ስራዎች ኦዲት መደረጉን መከታተል፣ መረጃዎችን
በመሰብሰብና በመተንተን፣በማጠናቀር ሪፖርት ማዘጋጀት፣ የከተሞች አደጋ ስጋት ካርታ እንዲያዘጋጁ መደገፍ፣ በአካባቢና
ማህበራዊ ደህንነት ሥራዎች የሚያጋጥሙ ችግሮችን፣ መንስኤውንና መፍትሔውን በጥናት መለየት፣ የአቅም ግንባታ ሥራ
ማከናወን፣

 በሥራው ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች/ችግሮች ፡- የአካባቢያዊና ማህበራዊ ደህንነት ማእቀፍ መሰሪያ ማንዋልና
በተቀመጠው ቼክ ሊስት መሰረት የአካባቢና ማህበራዊ ችግሮቹን ዳስሰው የጠበቀ የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት
ልየታ(Screening) ሪፖርት በአግባቡ ያለማዘጋጀት ፣ የፕሮጀክቶች የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት ሳይሰራ እና
የተፈናቀሉ ግለሰቦች የካሳ ክፍያ ሳይሰጥ የፕሮጀክት የግንባታ ስራ መጀመር፤ ፕሮጀክት ከመጀመሩ በፊት የወሰን ማስከበር ስራ

4
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ማጠናቀቅ ሲገባቸው ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ቡኋላ የወሰን ማስከበር ስራ ለማከናወን መሞከር፣ የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት
ልየታ(Screening) ሪፖርት ዝግጅት ለፕሮጀክቶቹ መስሪያ ቦታ የተመረጡትን ሳይት ያላገናዘበና ተመሳሳይ ሆኖ መገኘት፣
የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ልየታ(Screening) ሪፓርት ለማዘጋጀት ፤ የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት
ለማካሄድ፣ ተመጣጣኝ የካሳ ክፍያ ለመፈጸም በቂ ተሟላ መረጃ ያለመገንት፣ ከፊል እና ሙሉ EIA እንዲሁም ARAP እና
RAP ለሚያሰፈልጋቸዉ ፕሮጀክቶች በሚሠራው ሥራ የህብረተሰብ ተሳትፎ አነስተኛ መሆን፣ለዓመታዊ የአካባቢ እና
ማህበራዊ ኦዲት ስራዎች እና ለአደጋ ስጋት ካርታ ለማዘጋጀትና ለመተንተን በቂ መረጃ ያለማግኘት፣ በአካባቢና ማህበራዊ
ደህንነት ሠረራዎች አስፈላጊነት በህብረተሰቡና አስፈጸሸሚ አከላት የግንዛቤ ማነስ፣

 እነዚህን ችግሮች ፡- የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ልየታ(Screening) ሪፓርት ለማዘጋጀት ፤ የፕሮጀክቶች የአካባቢና ማህበራዊ
ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት ሳይሰራ እና የተፈናቀሉ ግለሰቦች የካሳ ክፍያ ሳይሰጥ የፕሮጀክት የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት
ልየታ(Screening) ሪፖርት እንዲዘጋጅና እንዲጸድቅ በመደገፍና በመከታተል፣ ፕሮጀክቶች ከፊል እና ሙሉ EIA እንዲሁም
ARAP እና RAP ለሚያሰፈልጋቸዉ ፕሮጀክቶች ጥናታቸው እንዲዘጋጅና በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እንዲጸድቁ እና
እንዲተገበር ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ የፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን የአካባቢ እና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ማካተቱንና
ከግንባታ በፊት መሠራቱን በማረጋገጥ፣ በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የጸደቁና የአካባቢያዊ ደህንነት ልየታ ሪፖርት መስረት
እየተተገበሩ መሆናቸውንና ዓመታዊ የአካባቢ እና ማህበራዊ ስራዎች ኦዲት መደረጉን መከታተል፣ መረጃዎችን በመሰብሰብና
በመተንተን፣በማጠናቀር ሪፖርት በማዘጋጀት፣ የከተሞች አደጋ ስጋት ካርታ እንዲያዘጋጁ በመደገፍ፣ በአካባቢና ማህበራዊ
ደህንነት ሥራዎች የሚያጋጥሙ ችግሮችን፣ መንስኤውንና መፍትሔውን በጥናት በመለየት፣ የአካባቢያዊና ማህበራዊ ደህንነት
ማእቀፍ ማኑዋልተጠቅ ለመሥራጥ የሚያችል አቅም በመፍጠር፣ ለባለድርሻ አካላት የህንዛቤ ማስጨበጫና የአቅም ግንባታ
ሥራዎችን በማከናወን፣ የሙያ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም የራስን የፈጠራ ክህሎት እና ጥረት በመጠቀም ይፈታሉ፡፡

3.2. ራስን ችሎ መስራት


3.2.1. ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 የከተማና መሠረተ ልማት እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲ፣ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያዊች እና እንዲሁም ሀገራችን
በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ሰምምነቶች እና ዓለም አቀፍ ግቦችን፣ የተለያዩ እቅዶችን መሠረት በማድረግ ይከናወናል፡፡

3.2.2. ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ


 ሥራው የተቋሙን ዕቅድ ከማሳካት አኳያ በጥራትና በአግባቡ ስለመከናወኑ በወቅቱ ባለማድረግ በወቅቱ ሪፖርትና ግምገማ
በማድረግና የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ ይደረግበታል፡፡

3.3. ተጠያቂነት
3.3.1. ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /Responsibility for Impact/፣
 ሥራው ማቀድ፣ ጥናት ማካሄድ፣ ተሞክሮ መቀመር፣ በፌደራል፣ክልሎችና በከተሞች የሚካሄዱ የተለያዩ ጥናቶችና የሚዘጋጁ

5
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ስትራቴጂዎች በመገምገም ማስወሰን፣ መልካም ተሞክሮ እንዲቀመርና ከሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዲጣጣም ማስደረግና
እንዲተገበር ማድረግ፣ ሲተገበሩ ከትትልና ድጋፍ ማድረግ፣ የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ልየታ(Screening) ሪፓርት
በማዘጋጀት ፤ የፕሮጀክቶች የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት እንዲሠራ ማድረግንና እና ለተፈናቀሉ ግለሰቦች
ተመጠጠኝ የካሳ ክፍያ እንደፈጸም ክትትል ማድረግን፣ ፕሮጀክቶቸ በአካባቢና በሰው ላይ የሚያሳድሩትን ተፅእኖ እንዲቀነስ
በማድረግ፣ የፕሮጀክት የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ልየታ(Screening) ሪፖርት እንዲዘጋጅና እንዲጸድቅ መደገፍና
መከታተል፣ ፕሮጀክቶች ከፊል እና ሙሉ EIA እንዲሁም ARAP እና RAP ለሚያሰፈልጋቸዉ ፕሮጀክቶች ጥናታቸው
እንዲዘጋጅና በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እንዲጸድቁ እና እንዲተገበር ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ የፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን
የአካባቢ እና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ማካተቱንና ከግንባታ በፊት መሠራቱን ማረጋገጥ፣ በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የጸደቁና
የአካባቢያዊ ደህንነት ልየታ ሪፖርት መስረት እየተተገበሩ መሆናቸውንና ዓመታዊ የአካባቢ እና ማህበራዊ ስራዎች ኦዲት
መደረጉን መከታተል፣ በቂ መረጃዎችን መሰብሰብና መተንተን፣የተጠናከረ ሪፖርት ማዘጋጀትና ግብረ መልስ መስጠት፣ የአደጋ
ስጋት ካርታ እንዲያዘጋጅ መደገፍ፣ በአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ሥራዎች የሚያጋጥሙ ችግሮችን፣ መንስኤውንና
መፍትሔውን በጥናት መለየትን፣ የአካባቢያዊና ማህበራዊ ደህንነት ማእቀፍ ማኑዋል ተጠቅሞ ለመሥራት የሚያችል አቅም
መፍጠርን፣ ለባለድርሻ አካላት ለማህበረሰቡ በሥፋት ግንዛቤ ማስጨበጫና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ማከናወን፣ የሙያ
ስልጠናዎችን መስጠትን እንዲሁም የራስን የፈጠራ ክህሎት እና ጥረት የሚጠይቅ ሲሆን
 ሥራው በአግባቡ ባይከናወን ህበረተሱ ተሳትፎ የተመረጡ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም አንዲዘገይ ምክያት ይሆናል፣ በዘህም
ምክንያት የመሠረተ ልማት ፍላጎትና አቅርቦት በሚፈለገው ሁኔታ ባለመሟላቱ የመልካ አስተዳደር ጥያቄ ያስነሳል፣ ለሀብትና
ለጊዜ ብክነት ይዳርጋል፣ በአካባቢ ለይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ያደርሳል፣ በከመታው ነዋሪ ዘንድ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ
ቀወስ ይፈጥራል፣ የአካባቢና ማህበረዊ ደህንነት ሥራዎች በሚፈለገው ደረጃ ያለመክናወን በአካባቢና በነዋሪዎች ላይ
የሚሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ በዚህ ምክንያት ፕሮጀክቶች በመዘግየታቸው ለከፍተኛ ወጪ ይዳርጋል፣

3.3.2. ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣


 የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ሪፖርቶችና መረጃዎች በሚስጥርና በአግባቡ መያዝ ወይም መጠበቅ ያለባቸው ሲሆን
እነዚህን መረጃዎችና ተያያዥ ሰነዶች በማይፈለግ ጊዜ በማይመለከታቸው እጅ ቢገቡ በተቋሙ ላይ ቅሬታ ያስነሳል፣
3.4. ፈጠራ
 በሌሎች ባለሙያዎች የተዘጋጁትን ጥናቶችና ስትራቴጂዎችን አዳዲስ ሀሳቦችን ማመንጨትና ማሻሻል፣ በዘርፉ ለሚዘጋጁ
አዋጅና ደንቦች ዝግጅት የሚያስፈልጉ ሀሳቦችን ማመንጨት፣ ተሞክሮዎችን መቀመር የአካባቢና ማህባራዊ ደህንነት ልየት
ሥራዎች፣ የኦዲት ሪፖርቶችን መገምገምና ወቅታዊ ግብረ መልስ መስጠት እንዲሁም የሥልጠና ፍላጊት ዳሰሳ ጥናትና
ማካሄድና የሥልጠና ሰነድ ማዘጋጃትና ሥልጠና መስጠት፣ የአካባባና ማህበራዊ ደህምንነት ሥራው በአግባቡ እነዲሥራ
መደገፍና አሰራር ስርዓት ማሻሻል፣ የሚሻሻልበትን ስልት መቀየስ የፈጠራ ክህሎትን ይጠይቃል፡፡

3.5. የሥራ ግንኙነት /Work Communication/


3.5.1. የግንኙነት ደረጃ
 ሥራው ከውስጥ ከዴስክ ኃላፊውና ከዴስኩ ባለሙያዎች፣ ከሌሎች የዴስክ ኃላዎችና ባለሙያዎች ከተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች

6
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ጋር ግንኙነት ያደርጋል፡፡
 ሥራው ከውጭ ከውጭ መንግስታዊ( በየረደራጀው ካሉ የመንግስት መ/ቤቶች) እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ፣ የልማት
አጋሮች ፣ ጋር ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡
3.5.2. የግንኙነቱ ዓላማ
 ሥራው መመሪያ ለመቀበልና ሪፖርት ለማቅረብ፣ የስራ መመሪያ ለመስጠት፣ ድጋፍና ከትትል ለማድረግ፣ የዴስኩን ዕቅድ
በተቀናጀ መልኩ ለመፈጸም፣ በጀትና የሚያስፈልገውን የሰው ሃይል እንዲሟላ ለማድረግ፣ በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ውይይት
ለማድረግና የስራ አቅጣጫ ለመቀበል፣ ተሞክሮዎችን ለማግኘትና ለማስፋት፣ ችግሮችን ለመፍታትና ቀጣይነት ያለው አቅም
ለመፍጠር ነው፡፡
3.5.3. የግንኙነቱ ድግግሞሽ
 ሥራው ከሥራ ጊዜው 50 በመቶ የሥራ ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡
3.6. ኃላፊነት
3.6.1. ኃላፊነት ለሰው ሀብት
3.6.1.1. በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
 የለም፡፡
3.6.1.2. የኃላፊነት አይነትና ደረጃ
 የማስተባበር፣ የመከታተል፣የመደገፍ እና የመገምገም ኃላፊነት አለበት፡፡
3.6.2. ኃላፊነት ለንዋይ
 የለበትም፡፡
3.6.3. ኃላፊነት ለንብረት
 ሥራውን ለማከናወን ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ኮምፒዩተር(ዴስክ ቶፕና ላፕቶፕ)፣ ፕሪንተር፣ ፋክስ፣ የፋይል ካቢኔት እና እስከ ብር
150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) የሚገመት ንብረት የመረከብ ኃላፊነት አለበት፡፡

3.7. ጥረት
3.7.1. የአዕምሮ ጥረት

 ሥራው ማቀድ፣ ጥናት ማካሄድ፣ ተሞክሮ መቀመር፣ በፌደራል፣ክልሎችና በከተሞች የሚካሄዱ የተለያዩ ጥናቶችና የሚዘጋጁ
ስትራቴጂዎች መገምገም፣ መልካም ተሞክሮ መቀመርና ፣ የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ልየታ(Screening) ሪፓርት ማዘጋጀት
፤ የፕሮጀክቶች የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት እንዲሠራ የካሳ ክፍያ ግመታ ሥራን ክትትል ማድረግን፣
ፕሮጀክቶቸ በአካባቢና በሰው ላይ የሚያሳድሩትን ተፅእኖ እንዲቀነስ በጥልቀት ጉዳዮችን ማየትን፣ የፕሮጀክት የአካባቢና
ማህበራዊ ደህንነት ልየታ(Screening) ሪፖርት እንዲዘጋጅና እንዲጸድቅ መደገፍና መከታተል፣ ፕሮጀክቶች ከፊል እና ሙሉ
EIA እንዲሁም ARAP እና RAP ለሚያሰፈልጋቸዉ ፕሮጀክቶች ጥናታቸውን መመርመርን፣ የፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን
የአካባቢ እና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ማካተቱንና ከግንባታ በፊት መሠራቱን ማረጋገጥ፣ ዓመታዊ የአካባቢ እና ማህበራዊ
ስራዎች ኦዲት መደረጉን መከታተል፣ በቂ መረጃዎችን መሰብሰብና መተንተን፣የተጠናከረ ሪፖርት ማዘጋጀትና ግብረ መልስ

7
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

መስጠት፣ የአደጋ ስጋት ካርታ እንዲያዘጋጅ መደገፍ፣ በአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ሥራዎች የሚያጋጥሙ ችግሮችን፣
መንስኤውንና መፍትሔውን በጥናት መለየትን፣ የአካባቢያዊና ማህበራዊ ደህንነት ማእቀፍ ማኑዋል ተጠቅሞ ለመሥራት
የሚያችል አቅም መፍጠርን፣ ለባለድርሻ አካላት ለማህበረሰቡ በሥፋት ግንዛቤ ማስጨበጫና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን
ማከናወን፣ የሙያ ስልጠናዎችን መስጠትን እንዲሁም
የአሰራር ስርዓት ማሻሻል አእምሮ የሚያደክም ሲሆን ይህም ከሥራ ጊዜው 80 በመቶ ሊወስድ ይችላል፡፡

3.7.2. ስነልቦናዊ ጥረት

 የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት እንዲሠራ የካሳ ክፍያ ግመታ ሥራን ክትትል ማድረግ፣ ከህብረተሰቡና ባለድርሻ
አካላት ጋር የሚገናኝ ሥራ በመሆኑ ከፍተኛ ውጥረት የሚፈጥር ሥራ ነው፣ ሰለሆነም ሥራውን በመምራት፣ በማስተባበር፣
በመከታተል፣ በመደገፍና አሰራሩን ዘመናዊ በማድረግ ሂደት የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችንና ክርክሮችን ተቋቁሞ በትዕግስት
መስራትን ይጠይቃል።

3.7.3. የዕይታ ጥረት፣


 ሥራው የዴስኩን ሥራ ማቀድ፣ በዴስኩ የሚካሄዱ የተለያዩ ጥናቶችና የልየታና የኦዲት ሪፖርቶች የሚዘጋጁ ስትራቴጂዎች
አንብቦ መገምገም ፣ ከፊል እና ሙሉ EIA እንዲሁም ARAP እና RAP ለሚያሰፈልጋቸዉ ፕሮጀክቶች ጥናታቸውን
መመርመርና ማረጋገጥ በጥንቃቄ በኮምፒዩተር መጻፍና እንዲጻፍ በማድረግ ተጽፎ የቀረበውን ማመሳከር እይታን የሚያደክም
ሲሆን ይህም ከሥራ ጊዜው 40 በመቶ ይሆናል፡፡

3.7.4. የአካል ጥረት


 ሥራው 70 % በመቀመጥ፣ 30 % በእግር በመጓዝ የሚከናወን ይሆናል፡፡
3.8. የሥራ ሁኔታ
3.8.1. ሥጋትና አደጋ
 የለበትም፡፡
3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ
 የለበትም፡፡
3.9. እውቀትና ክህሎት፣
3.9.1. ትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት
ከተማ ልማትና ኢንቫይሮንመንት፣ በተፈጥሮ ሀብት አያያዝና አስተዳድር፤
አግሪካልቸራል ኢንጀር አካባቢ ሳይንስ፣ ኢንቫሮመንታል ኢንጂነር ወይም
የመጀመሪያ ዲግሪ
ስነ-ህይዎት ወይም ኢኮሎጅካል ሳይንስ ወይም ደን ሳይንስ፣ በአርባን
ፎርስትሪ ወይም በዕጽዋት ሳይንስ ወይም በከተማ ውበትና አረንጓዴ
ልማት፣
3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ
የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት

8
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

4 ዓመት ቀጥታ አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like