You are on page 1of 9

የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

I. አጠቃላይ መግለጫ

የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት

ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተማ አረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሠረተ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት
ልማት ስታንዳርድ ዝግጅት ባለሙያ III ስታንዳዳይዜሽን ዴስክ

የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ

የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ


ልማት ስታንዳዳይዜሽን ዴስክ ኃላፊ

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት

2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-

የአረንጓዴና የአካባቢ ጥበቃ መሠረተ ልማት ዘርፍ የሚመራባቸውን ስታንዳርዶችን እንዲሁም የማስፈጸሚያ ሰነዶች በጥናት
በማዘጋጀት፣ በማሻሻል፣ ተግባራዊነታቸውን በመከታተል፣ ድጋፍ በማድረግ እና ሰነዶችን በማስተዋወቅ፣ በማስፋፋትና ስልጠናዎች
በመስጠት ዘላቂነት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ የከተማ መሠረተ ልማት አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ነው፡፡

2.2.ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት

ውጤት 1፡ በአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማትና ስታንዳርድ ጥናቶች ላይ ትንተና ማድረግ፣

 የአካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች አስመልክቶ ለሚዘጋጁ የፖሊሲና የስትራቴጂ ሰነዶች መረጃዎች ያሰባስባል፣ ይተነትናል፣ መነሻ

1
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ሃሳብ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣


 ለስታንዳርዶች ዝግጅት የሚያስፈልጉ የተለያዩ መረጃዎችና ማስረጃዎች ያሰባስባል፣ ያደራጃል፣ ይተነትናል፤ ያቀርባል፣

 የተዘጋጁ የአረንጓዴና የአካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ስታንዳርድ ክፍተተት ለማጥናት የሚያስችል ዝርዝር የጥናት ማስፈጸሚያ
ሰነድ ያዘጋጃል፣
 አዳዲስ ስታንዳርድ የሚዘጋጅላቸውን መሰረተ ልማቶች በጥናት ይለያል፣ ለዝግጅት የሚረዳ መነሻ ጽሑፍ ያዘጋጃል፣
 የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሠረተ ልማቶች የጥገና/እንክብካቤና የአጠቃቀም ትግበራ ሁኔታ ያጠናል፣ ለስታንዳድ ዝግጅት
በግብዓትነት ይጠቀማል፣
 በከተሞች አረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ላይ አዳዲስ የአሰራር ስልቶችንና የሀገራት ተሞክሮዎችን በከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ
የሚያስችል ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ ጥናቶችን ያካሂዳል
 በአፈፃፀም ሂደት ላይ ያሉትን በስታንዳርድ ሰነዶች አተገባበር በመስክ ከተሰባሰቡ እና ከክልሎች የቀረቡ የአፈጻጸም ሪፖርቶችን
በመተንተን ያስገኙትን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ይተነትናል፤
 የተዘጋጁ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ስታንዳዶች ትግበራ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ጥናት ላይ ይሳተፋል፣ ተለይተው
በሚሰጡት ስራዎችን ያካውናል፣
 ለአረንጓዴ መሰረተ ልማት ስራ የሚስፈልጉ ግብዓቶችና አጠቃቀማቸውን በጥናት በዝርዘር ይለያል፣ ጥቅም ላይ እንዲውሉ
ለከተሞች ያስተላልፋል፣
 የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች የልማት አተገባበር ሂደትን በማጥናት የአሰራር ማሻሻያ እንዲደረግ ሀሳብ ያቀርባል፣ ያጸድቃል፣
እንዲተገበሩም ይሰራል፡፡

ውጤት 2፡- የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ስታንዳርድ ዝግጅት የሚያስፈልጉ ሰነዶች ማዘጋጀት፣ስታንዳርድ ዝግጅት ላይ መሳተፍ፣

 ተሞክሮ ለመቀመር የሚያስችሉ የተለያዩ መረጃዎች ያሰባስባል፣ ይዘታቸውን ይተነትናል፣ ቀምሮ ያቀርባል፣

 የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ስታንዳድር ዝግጅት ለማካሄድ የሚያስችል አሰራር ያዘጋጃል፣
 በአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች አያያዝና አስተዳደር ላይ የተለያዩ የፖሊሲዎች ህጎችና ደንቦች ስታንዳርዶችና መመሪያዎች፣ ማዘጋጀት፣

 የአረንጓና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶችን የልማት ግብዓቶችን ይለያል፣ ያደረጃል፣ የአጠቃቀም ደረጃ ያወጣል፣

 ለተመረጡ የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች/የከተሞች ፈርጅ መሰረት በማድረግ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት (ደረጃ
ዘመናዊ ቄራ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ዘላቂ ማረፊያ፣ የተሸከርካሪ ማቆሚያ፣ ጋራዥ፣ መናኸሪያ፣ የገበያ
ቦታዎች፣ፓርኮች፣መናፈሻዎች፣የመንገድ ዳርቻ፣ አካፋይና አደባባዮች፣ ተፋሰሶችና ሌሎች አረንጓዴ መሠረተ ልማቶች፣የቆሻሻ
ማሰባሰቢያ፣መለያ፣ማቀነባበሪያ እና ማስወገጃ ቦታዎች…) የስታንዳርድ ዝግጅት ረቂቅ መነሻ ጽሑፍ ያዘጋጃል፣
 በአማካሪ ተጠንተው የሚዘጋጁ ስታንዳርዶች ይገመግማል፣ የግምገማ ውጤቱን ግብረ መልስ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣

 የተዘጋጁ ሰነዶችን በባለድርሻና አስፈጻሚ አካላት ቀርበው ውይይት ሲካሄድ የሚሰጡ አስተያየቶች ይመዘግባል፣ ተንትኖ በማደራጀት እንደ
አስፈላጊነቱ በሰነዱ እንዲካተቱ ያቀርባል፤
 የአረንጓዴ መሰረተ ልማት አቅርቦት፤ ጥገናና አስተዳዳር የግልና የህዝቡ ተሳትፎ በተከታታይነት የሚያድገብት ስርዓት ያዘጋጃል፣ ተግባረዊነቱን
ይከታታላል፡፡

2
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

 የአረንጓዴና የአካባቢ መሰረተ ልማት ጥናቶች ለዲዛይን ዝግጅት ግብዓት የሚሆኑበትን አሰራር ያዘጋጃል፣
 በውጭ አቅም የተዘጋጁና የተሻሻሉ ስታንዳርዳርዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሰነዶቹን የሚያዳብሩ ግብዓቶች በተለያዩ ደረጃዎች
ያሰባሰብባል፣ ያደረጃል፣ ለስታንዳርድ ዝግጅት ጥቅም ላይ ያውላል፣
 የሚገነቡ የአረንጓዴና የአካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ከጥራት አኳያ ያላቸውን አዋጭነት/value for Money/ናሙና በመውሰድ ያጠናል፣
ውጤቱን መነሻ በማድረግ ይደግፋል፣
 በስታንዳርድ ዝግጅት ሂደት ይሳተፋል፣

 ለስታንዳርድ ዝግጅት የሚያስፈልጉ ግብዓችንና መረጃዎች ያሰባስባል፣


ውጤት 3፡ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሠረተ ልማት የስታንዳዶች አሠራርና አገልግሎት ደረጃዎች መከታተልና መደገፍ፣

 በውስጥ አቅም ለሚዘጋጁ ስታንዳርዶች ስራው የሚከናወንበትን ሂደት በግልጽ የሚያመላክት ቢጋር ያዘጋጃል፣

 በአረንጓዴና በአካባቢያዊ ጥበቃ መሠረተ ልማት ተሞክሮ ለመቀመር የሚስችል መረጃ ያሰባስል፣ ይቀምራል፣

 በአፈጻጸም ወቅት የሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችና የስታንዳርዶችን ጥሰቶችን ይለያል፣ የመፍትሔ ሀሳቡን አደራጅቶ ያቀርባል፣
 የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች አያያዝና አጠቃቀም አሰራር ለመፍጠር የሚያችል መረጃ ያሰባስባል፣

 የተዘጋጁ ሰነዶችን በባለድርሻና አስፈጻሚ አካላት ቀርበው ውይይት ሲካሄድ የሚሰጡ አስተያየቶች ይመዘግባል፣ ተንትኖ በማደራጀት እንደ
አስፈላጊነቱ በሰነዱ እንዲካተቱ ያቀርባል፤

 ለዘርፉ ተዋንያንና ባለድርሻ አካላት ስታንዳርዶች ጥናቶችና አውደ ጥናቶችን በማዘጋጀት የምክክር መድረኩን ያመቻቻል፣
 በክልሎችና ከተሞች የሚተገበሩ አረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶችን በመስክና በመድረክ በመገኘት አተገባበራቸውን ይከታተላል
ይገመግማል፣
 ከተገኙ ተሞክሮች እና ከተለዩ ክፍተቶች መነሻ በማድረግ የስታንዳርድ ዝግጅት፣ የክትትልና ድጋፍ ለማሻሻል የሚስችል አሰራር ያዘጋጃል፣

 አስቀድመው የተዘጋጁ የዘርፉን የስታንዳርድ ሰነዶች በማሰባሰብ ለጥናት በሚያመቹ አግባብ ያደራጃል፣ ያዘጋጃል፤ እንደአስፈላጊነቱ ያጠናል፤

ውጤት 4 ፡- የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ስታንዳርዶችን ማስተዋወቅ፣ስልጠና ማመቻቸት ስልጠና መስጠት፣

 በርዘፉ ለተሰማሩ አስፈጻሚና ፈጻሚ አካላት ስልጠና ለመስጠትና ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል ቢጋር ያዘጋጃል፣
 የአረንጓዴና አካቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ለማስተዋወቅ የሚያችሉ መድረኮችን ይፈጥራል፣ ያመቻቻል፣
 ስታንዳዶችን ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ የተለያዩ አማራጮችን ይዘይዳል፣ በጽሑፍ ዘአጋጅቶ ያቀርባል፣
 በተመረጡ መሰረተ ልማቶች ላይ ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል የስልጠና ሰነድ ያዘጋጃል፣
 እንደ አስፈላጊነቱ በተመረጡ የአረንጓዴ የአካባቢ መሰረተ ልማት ስታንዳዶች ላይ ስልጠና ይሰጣል፣
 ስልጠናዎችን በአግባቡ መስጠት ያስችል ዘንድ በየወቅቱ የተለዩትን የስታንዳርድ አፈጻጸም ችግሮችና መልካም ተሞክሮዎችን

3
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

አጭር መግለጫ ጹሑፍ ያዘጋጃል፣ ያቀርባል፣


 የስታንዳርዶችን ሰነዶች በባለድርሻ አካላትና የዘርፉ ተዋንያን ለማስረጽ የሚያስችሉ ትምህርታዊ ብሮሸሮችና በራሪ ፅሑፎች
ያዘጋጃል፣ ለሚመለከታቸው እንዲዳረሱ ያደርጋል፤
 የነዋሪው ህበረተሰብ የስታንዳርድ ትግበራዎችን ፋይዳ መገንዘብ ይችል ዘንድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልት ይነድፋል፣

III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች

3.1. የሥራ ውስብስብነት


 ሥራው ለሚዘጋጁ የፖሊሲና የስትራቴጂ ሰነዶች መረጃዎች ማሰባሰብ፣ መተንተን፣ መነሻ ሃሳብ አዘጋጅቶ ማቅረብ፣
የአረንጓዴና የአካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ስታንዳርድ ክፍተተት ለማጥናት የሚያስችል ዝርዝር የጥናት ማስፈጸሚ ሰነድ
ማዘጋጀት፣ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሠረተ ልማቶች የጥገና/እንከብካቤና የአጠቃቀም ትግበራ ሁኔታ ማጥናት፣ በከተሞች
አረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ላይ አዳዲስ የአሰራር ስልቶችንና የሀገራት ተሞክሮዎችን በከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል
ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ ጥናቶችን ማካሄድ፣ በስታንዳርድ ሰነዶች አተገባበር በመስክ ከተሰባሰቡ እና ከክልሎች በቀረቡ
የአፈጻጸም ሪፖርቶችን በመጠቀም ያስገኙትን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በጥልቀት መተንተን፤ ተሞክሮ ለመቀመር
የሚያስችሉ የተለያዩ መረጃዎች ማሰባሰብ፣ ይዘታቸውን መትተን ሃሰቡን አደራጅቶ ማቅረብ፣ በአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች አያያዝና
አስተዳደር ላይ የተለያዩ አሰራሮችን ለማሻሻል መቅረጽ፣ ለተመረጡ የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች /የከተሞች ፈርጅ መሰረት በማድረግ
የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት (ደረጃ ዘመናዊ ቄራ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ዘላቂ ማረፊያ፣ የተሸከርካሪ
ማቆሚያ፣ ጋራዥ፣ መናኸሪያ፣ የገበያ ቦታዎች፣ፓርኮች፣መናፈሻዎች፣የመንገድ ዳርቻ፣ አካፋይና አደባባዮች፣ ተፋሰሶችና ሌሎች
አረንጓዴ መሠረተ ልማቶች፣የቆሻሻ ማሰባሰቢያ፣መለያ፣ማቀነባበሪያ እና ማስወገጃ ቦታዎች…) የስታንዳርድ ዝግጅት ረቂቅ መነሻ
ጽሑፍ ማዘጋጀት፣ በአማካሪ ተጠንተው የሚዘጋጁ ስታንዳርዶችን ይዘት መገምገም፣ የአረንጓዴና የአካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ከጥራት
አኳያ ያላቸውን አዋጭነት/value for Money/ናሙና በመውሰድ ማጥናት፣ ለዘርፉ ተዋንያንና ባለድርሻ አካላት ስታንዳርዶች ጥናቶችና አውደ
ጥናቶችን በማዘጋጀት የምክክር መድረኩን ማመቻቸት፣ ስታንዳዶችን ለማስተዋወቅ አሰራሩን ለማስረጽ የሚያስችሉ የተለያዩ
አማራጮችን ይዘይዳል፣ በጽሑፍ ዘአጋጅቶ ማቅረብ የሚጠይቅ ነው፡፡

 ሥራው በሚከናወንበት ወቅት የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ስታንዳድ ዝግጅት አዲስ ከመሆኑ አንጻር
የሚፈለገውን ስታንዳርድና አንዳንድ ሰነዶች ለማዘጋጀትና ጥናት ለማድረግ በቂ መነሻ መረጃዎች የማይገኝ መሆኑ፣
ስታንዳርዶች ያስገኙትን የማህበራዊ፣ አካባቢዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ለመገምገም የሚያስችል ሪፖርት አለሟሟላት፣ የሌሎች
ሀገሮች ሊገኙ የሚችሉም ተሞክሮዎች ከተጨባጭ ሁኔታ ጋር ያለመጣጣም፣ በአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት

4
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ስታንዳዶችን ክፍተቶች ላይ የሚደረጉ ጥናቶች ዘርፈ ብዙ ክህሎት ያላቸውን ባለሙያዎች ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆን፣
የሚዘጋጁ (ደረጃ ዘመናዊ ቄራ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ዘላቂ ማረፊያ፣ የተሸከርካሪ ማቆሚያ፣ ጋራዥ፣ መናኸሪያ፣
የገበያ ቦታዎች፣ ፓርኮች፣ መናፈሻዎች፣የመንገድ ዳርቻ፣ አካፋይና አደባባዮች፣ ተፋሰሶችና ሌሎች አረንጓዴ መሠረተ
ልማቶች፣ የቆሻሻ ማሰባሰቢያ፣ መለያ፣ ማቀነባበሪያ እና ማስወገጃ ቦታዎች…) ስታንዳዶች ጥልቅ ትንተናና ትኩረት
የሚጠይቅ መሆኑ፣ በአማካሪዎች የሚዘጋጁ ስታንዳርዶች የውል ጊዜ ማስጠበቅና ግብረ መልሶችን ተከታትሎ እንዲካተቱ
ማድረግ የሚጠይቅ መሆኑ፣ የአረንጓዴና የአካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ከጥራትና ኢኮኖሚ አኳያ ያላቸውን
አዋጭነት/value for Money/ናሙና ማጥናት የሌሎች አካላትን ከፍተኛ ትብብር የሚጠይቅ መሆኑ፣ የተዘጋጁ ስታንዳርዶች
ላይ ከባለድርሻ አካላት በቂ ግብረመልስ አለማግኘት፣ የሚሰጡ ስልጠናዎችና የግንዛቤ መፍጠሪያዎች እኩል ግንዛቤ አለመፈጠር
በሥራው ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ናቸው፡፡

 እነዚህን ችግሮች ለስታንዳድ ዝግጅት የሚያስፈልጉ መረጃዎችን የተለያዩ ባለድርሻ አካትን ዩንቨርሲቶችን፣ ተቋትን ወዘተ በሰፊው
እንዲሳተፉ በማድረግ፣ ማሰባሰብና አደራጅቶ በመጠቀም፣ በአረንጓዴና አካባቢ መሰረተ ልማት ስንታንዳርድ ዝግጅት ወቅት
ባለድርሻ አካላትን አጥርቶ በመለየት በመድረኮች፣ በሰነድ ዝግጅት ወዘተ እንዲሳተፉና ግብዓት እንዲሰጡ በማድረግ፣ የተለያዩ
ሀገራትን ተሞክሮን የሚመለከቱ ወቅታዊ ጽሁፎችን በማፈላለግ ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዲጣጣም ጥናት በማድረግና
በመቀመር፤ በስታንዳድ ዝግጅ ወቅት ለተለያዩ መሰረተ ልማቶች የሚስፈልጉ ባለሙያዎች ከተለያ አካባቢዎች ለይቶ በማሰባሰብ
በንቃት እንዲሳተፉ በማድረግ፣ በአማካሪ የሚዘጋጁ ስታንዳርዶችን በጥልቀት በመፈተሸና በውላቸው ይዘት መሰረት
መስራታቸውን በመገምገም፣ የሚሰጡ ስጠናዎችና የግንዛቤ ማስጨበጫዎችን ብዛትና ጥራት በማሳደግ፣ በመስክ በመገኘት
ተግባራዊ ስልጠና በመስጠትና ልምድ በማካፈል የሚፈጠረው ግንዛቤ ተቀራራቢ እንዲሆን በማስቻል፣ ስታንዳዶችን
ለማስተዋወቅ የሚስፈልጉ የተለያዩ የማስተዋወቂያ ስልቶችን በመቀየስ የሚያጋጥሙ ችግሮችን መፍታት ይጠይቃል፡፡

3.2. ራስን ችሎ መስራት


3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ሥራው ሀገር አቀፍ ግቦችን፣ ተልእኮዎችን፣ አጠቃላይ ፖሊሲዎችን ስትራቴጂዎችን፤ ፕሮግራሞችን፣
ልዩ ልዩ አዋጆችን፣ የማስፈጸሚያ ደንቦችንና መመሪያዎችን፣ በሌሎች ዘርፎች የተዘጋጁ
ስታንዳርዶችን መነሻ በማድረግና የተለያዩ ሀገራት ልዶችን መሠረት በማድረግ ይከናወናል፡፡

3.2.2 ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ


 ሥራው ከአጠቃላይ ከሀገሪቱ ፖሊሲ፣ ከዘርፉ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች የተቋሙ ስትራቴጂያዊ
ዕቅድ እና የአሰራር ስርአቶች ግቦች ከማሳካት አንጻር ይገመገማል፡፡

3.3 ተጠያቂነት

5
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

3.3.1 ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /Responsibility for Impact/፣


 ሥራው የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሠረተ ልማቶች የጥገና/እንከብካቤና የአጠቃቀም ትግበራ ሁኔታ ማጥናት፣ በከተሞች
አረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ላይ አዳዲስ የአሰራር ስልቶችንና የሀገራት ተሞክሮዎችን በከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል
ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ ጥናቶችን ማካሄድ፣ በስታንዳርድ ሰነዶች አተገባበር በመስክ ከተሰባሰቡ እና ከክልሎች በቀረቡ
የአፈጻጸም ሪፖርቶችን በመጠቀም ያስገኙትን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በጥልቀት መተንተን፤ ተሞክሮ ለመቀመር
የሚያስችሉ የተለያዩ መረጃዎች ማሰባሰብ፣ ይዘታቸውን መትተን ሃሰቡን አደራጅቶ ማቅረብ፣ በአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች አያያዝና
አስተዳደር ላይ የተለያዩ አሰራሮችን ለማሻሻል መቅረጽ፣ ለተመረጡ የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች /የከተሞች ፈርጅ መሰረት በማድረግ
የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት (ደረጃ ዘመናዊ ቄራ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ዘላቂ ማረፊያ፣ የተሸከርካሪ
ማቆሚያ፣ ጋራዥ፣ መናኸሪያ፣ የገበያ ቦታዎች፣ፓርኮች፣መናፈሻዎች፣የመንገድ ዳርቻ፣ አካፋይና አደባባዮች፣ ተፋሰሶችና ሌሎች
አረንጓዴ መሠረተ ልማቶች፣የቆሻሻ ማሰባሰቢያ፣መለያ፣ማቀነባበሪያ እና ማስወገጃ ቦታዎች…) የስታንዳርድ ዝግጅት ረቂቅ መነሻ
ጽሑፍ ማዘጋጀት፣ በአማካሪ ተጠንተው የሚዘጋጁ ስታንዳርዶችን ይዘት መገምገም፣ የአረንጓዴና የአካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ከጥራት
አኳያ ያላቸውን አዋጭነት/value for Money/ናሙና በመውሰድ ማጥናት የሚጠይቅ ነው፡፡

 እነዚህ ተግባሮች በአግባቡ ባይከናወኑ የከተማ መሰረተ ልማት አቅርቦቱ ወጥ በሆነ ስታንዳርድ ስርዓት
እንዳይመራ ያደርጋል፣ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ሀብት ብክነት ያከትላል፣ የከተሞች ለአየር ብክለት
እንዲጋለጡ ያደርጋል፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት እጥረትን ያስከትላል እና የተቋሙ ግብ እንዳይሳካ
ያደርጋል፡፡

3.3.2 ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣

 ያልጸደቁና በረቂቅ ሂደት የሚገኙ የደረጃና ስታንዳርድ ዝግጅት በሚስጥር መያዝ ወይም መጠበቅ
ያለባቸው ሲሆን እነዚህን ሰነዶች በማይመለከታቸው እጅ ቢገቡ በተቋሙ ላይ ተአማኒነትን ያሳጣል፡፡

3.4 ፈጠራ
 ሥራው በዘርፉ ለሚዘጋጁ አዋጅና ደንቦች ዝግጅት የሚያስፈልጉ ሀሳቦችን ማመንጨት፣ የሚዘጋጁ
ስታንዳርዶች ሀገራዊ ተጨባጭን ያገናዘቡ እንዲሆኑ ማሰላሰልንና ሲተገበሩ በማህበረሰብ ላይ
የሚያሳድሩን ተጽዕኖ አሰላለስሎ ማሰራት፣ ተሞክሮዎችን በመቀመር እና ክፍተቶች ላይ ጥናት
በማድረግ አዳዲስ ወይም የተሻሻሉ የስታንዳርዶች የአሰራር ስርአትን ማዘጋጀትና ማሻሻል ይጠይቃል፣

3.5 የሥራ ግንኙነት /Work Communication/


3.5.1 የግንኙነት ደረጃ

6
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

 ሥራው ከውስጥ ከቅርብ ኃላፊውና ከክፍሉ ባለሙያዎች፣ ከሌሎች ሥራ ክፍሎች ባለሙያዎችና


ዴስኮች፣ ከተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች፣ ከውጭ ደግሞ ከአማካሪዎች፣ ከሥራ ተቋራጮች ከሙያ
ማሕበራት፣ ከክልሎች፣ ከግሉ ዘርፍ፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላትና ተቋማት
ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡

3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ


 ሥራው መመሪያ ለመቀበል፣ ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን ለማማከርና ለመወያየት፤ በጋራ የሚሰሩ
ሥራዎችን ለመወሰን፣ የታቀዱ ስራዎችን በተያዘላቸዉ ጊዜ መፈጸማቸዉን ለመከታተል
ለመገምገም፣ በአሰራር ችግሮች ዙሪያ ለመወያየት፣ ለተዘጋጁ ረቂቅ ሰነዶች ግብዓት ለማሰባሰብና
ለማፀደቅ፣ በስራ ላይ በዋሉ ሰነዶች አፈጻጸም ዙሪያ ማብራሪያ ለመስጠትና ለማስረዳት፣ ስልጠናዎች
ለመስጠት ነው፡፡

3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ


 ሥራው ከሥራ ጊዜው 35 በመቶ የሥራ ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡

3.6. ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
3.6.1.1. በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
 የለበትም፡፡

3.6.1.2. የኃላፊነት አይነትና ደረጃ


 የለበትም፡፡
3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ
 የለበትም፡፡

3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት


 ሥራውን ለማከናወን ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ኮምፒዩተር(ዴስክ ቶፕና ላፕቶፕ)፣ ፕሪንተር፣ ፋክስ፣ የፋይል ካቢኔት እስከ ብር
150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) የሚገመት ንብረት የመረከብ ኃላፊነት አለበት፡፡

3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 ሥራው ለሚዘጋጁ የፖሊሲና የስትራቴጂ ሰነዶች መረጃዎች ማሰባሰብ፣ መተንተን፣ መነሻ ሃሳብ አዘጋጅቶ ማቅረብ፣

7
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሠረተ ልማቶች የጥገና/እንከብካቤና የአጠቃቀም ትግበራ ሁኔታ ማጥናት፣ በከተሞች አረንጓዴ
መሰረተ ልማቶች ላይ አዳዲስ የአሰራር ስልቶችንና የሀገራት ተሞክሮዎችን በከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል
ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ ጥናቶችን ማካሄድ፣ በስታንዳርድ ሰነዶች አተገባበር በመስክ ከተሰባሰቡ እና ከክልሎች በቀረቡ
የአፈጻጸም ሪፖርቶችን በመጠቀም ያስገኙትን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በጥልቀት መተንተን፤ ተሞክሮ ለመቀመር
የሚያስችሉ የተለያዩ መረጃዎች ማሰባሰብ፣ ይዘታቸውን መትተን ሃሰቡን አደራጅቶ ማቅረብ፣ በአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች አያያዝና
አስተዳደር ላይ የተለያዩ አሰራሮችን ለማሻሻል መቅረጽ፣ ለተመረጡ የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች /የከተሞች ፈርጅ መሰረት
በማድረግ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት (ደረጃ ዘመናዊ ቄራ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ዘላቂ ማረፊያ፣
የተሸከርካሪ ማቆሚያ፣ ጋራዥ፣ መናኸሪያ፣ የገበያ ቦታዎች፣ፓርኮች፣መናፈሻዎች፣የመንገድ ዳርቻ፣ አካፋይና አደባባዮች፣
ተፋሰሶችና ሌሎች አረንጓዴ መሠረተ ልማቶች፣የቆሻሻ ማሰባሰቢያ፣መለያ፣ማቀነባበሪያ እና ማስወገጃ ቦታዎች…)
የስታንዳርድ ዝግጅት ረቂቅ መነሻ ጽሑፍ ማዘጋጀት፣ በአማካሪ ተጠንተው የሚዘጋጁ ስታንዳርዶችን ይዘት መገምገም፣ የአረንጓዴና
የአካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ከጥራት አኳያ ያላቸውን አዋጭነት/value for Money/ናሙና በመውሰድ ማጥናትና የአሰራር ማሻሻያ
ማድረግ አዕምሮ የሚያደክሙ ሲሆኑ፣ ይህም ከቀን የሥራ ጊዜው 75 በመቶ ይወስዳል፡፡

3.7.2 ስነልቦናዊ ጥረት

 ሥራው ከባለድርሻ እና አስፈጻሚ አካላት ጋር በመሰረተ ልማት ስታንዳርድ ዝግጅትና አፈጻጸም ስራዎች በምክክር መድረክ
በሚፈጠሩ ክርክሮች እና የሀሳብ አለመግባባቶች ስነልቦናን የሚፈታተኑ ሲሆኑ እነዚህን በትዕግስትና በተረጋጋ ስሜት ተቋቁሞ
ሥራዎችን ውጤታማ ማድረግ ይጠይቃል፡፡

3.7.3 የዕይታ ጥረት፣


 ሥራው የተለያዩ ጥናት ለማድረግ የሚስፈልጉ ግብዓቶችን ማንበብ እንዲሁም በዳሰሳ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ሀሳብ
ማመንጨት፣ የጥናት ሰነዶችን አንብቦ ማረምና ማስተካከል፣ የመሰረተ ልማት ስታንዳርድ ሰነዶች በጥናት ላይ ተመስርቶ
የተለያ ሰነዶችን በማንብብና በማገናዘብ ማዘጋጀት፣ የተለያዩ ሰነዶችን በማንበብና በማገናዘብ የሀገራትን የስታንዳንድር
ዝግጅት ተሞክሮ መቀመር፣ የስልጠና ማንዋሎችን ዝግጅት፣ የክትትልና ድጋፍ ሪፖርቶች እና ሌሎች ሥራዎችን ኮምፕዩተር
ላይ ማዘጋጀት፣ የተለያዩ ማጣቀሻዎችን ማገናዘብ፣ የዋና ስራ አስፈጻሚውን የተጠቃለለ ሪፖርት ማዘጋጀትና በኮምፒዩተር
መጻፍ እይታን የሚያደክም ሲሆን ይህም ከሥራ ጊዜው 45 በመቶ ይሆናል፡፡

3.7.4 የአካል ጥረት


 ሥራው 70 % በመቀመጥ፣ 30 % በመንቀሳቀስ የሚከናወን ይሆናል፡፡

3.8 የሥራ ሁኔታ


3.8.1 ሥጋትና አደጋ
 የለበትም፡፡

3.8.2 የሥራ አካባቢ ሁኔታ

8
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

 የለበትም፡፡

3.9 እውቀትና ክህሎት፣

3.9.1 ትምህርት

የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት


ከተማ ልማትና ኢንቫይሮንመንት፣ በተፈጥሮ ሀብት አያያዝና አስተዳድር፤ አግሪካልቸራል
የመጀመሪያ ዲግሪ ኢንጀር፣አካባቢ ሳይንስ፣ ኢንቫሮመንታል ኢንጂነር ወይም ስነ-ህይዎት ወይም ኢኮሎጅካል
ሳይንስ ወይም ደን ሳይንስ፣ በአርባን ፎርስትሪ ወይም በዕጽዋት ሳይንስ ወይም በከተማ ውበትና
አረንጓዴ ልማት፣

3.1.1. ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ

የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት

4 ዓመት ቀጥታ አግበብነት ያለው የሥራ ልምድ

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like