You are on page 1of 32

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት የስልጣን

ውክልና

ግንቦት፣ 2014
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት የስልጣን ውክልና [Publish Date]

ይዝት
የስልጣን ውክልና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊዎችመግቢያ .................................................................................................. 1
የስልጣን ውክልናው ዓላማ እና ታሳቢ የተደረጉ መርሆች (Basic Principles) ..................................................................... 3
የስልጣን ውክልና መሰረታዊ ደረጃዎች ................................................................................................................... 3
የስልጣን ውክልና ዓላማ..................................................................................................................................... 3
የዚህ የውክልና አሰጣጥ ሂደት የሚያመጣቸው ጥቅሞች .............................................................................................. 6
ታሳቢ የተደረጉ መርሆች (Basic Principles) ....................................................................................................... 7
በትግበራ ላይ ያለው የስልጣን ውክልና ለመከለስ ያስፈለጉ ምክንያቶች ............................................................................ 8
ከሌሎች ሀገራትና ተቋማት የተወሰዱ ተሞክሮዎች ..................................................................................................... 9
1. የታንዛንያ መንገድ ኤጀንሲ ተሞክሮ ........................................................................................................... 9
2. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ተሞክሮ ....................................................................................... 10
መደምደሚያ .................................................................................................................................................... 11
የተከለሰው የስልጣን ውክልና ................................................................................................................................ 14

1|Page
የስልጣን ውክልና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊዎች መግቢያ
የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የአንድን ሀገር ሁለንተናዊ የእድገት አቅጣጫ የሚወስኑ እና አመላካች እሴቶች ሲሆኑ
የመንገድ መሰረት ልማትም ከሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ ግዝፈት አንፃር ከግንባር ቀደም
የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ውስጥ የሚመደብና ቀዳሚ ፖሊሲያዊ እይታን የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡

ይህንን ነባራዊ ሀኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ባለፉት ሶስት አስርት አመታት የመንገድ ልማት ዘርፉ ከመንግስት የተለየ
ትኩረት የተሰጠው ሲሆን ከሀገሪቱ አመታዊ በጀት ውስጥም ከፍተኛውን ድርሻ በመያዝ በሰፊ የትግበራ ሂደት ውስጥ
ሲጓዝ ቆይቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው የባለድርሻ አካላት በተለይም የማህበረሰቡ የመንገድ
መሰረ ልማት ፍላጎት መናር ከተመዘገበው ኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር ተዳምሮ ለመንገድ መሰረተ ልማት ዘርፉ ለተሰጠው
ልዩ ትኩረትና እድገት የራሱን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት አስችሎታል፡፡

በነዚህና ሌሎች ተዛማጅ ምክንያቶች መነሻነት የመንገድ አውታር ሽፋኑ በአንፃራዊነት ከፍተኛ እድገትን እያመጣ ያለ
ሲሆን አሃዛዊ መረጃዎችን በዋቢነት ለመመልከት ያህል በአሁኑ ወቅት ያለው የሀገሪቱ የመንገድ ሽፋን መስፋፋቱን አና
በቀጣይም ተጠናክሮ እንሚቀጥል የተቀመጡት ተቋማዊና ሃገራዊ ፖሊሲዎችና እቅዶች አመላካች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በመንገድ መሰረት ልማት ዘርፉ ላይ የአስፈጻሚነት ሚናን እንዲይዝ ተደርጎ በአዋጅ
ከተቋቋመበትና እንዳዲስ እንዲደራጅ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ የተቋሙንና የመንገድ ዘርፍ ፖሊሲዎችን በመቅረፅ፣
የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅዶችን በማውጣት፣ አዳዲስ መንገዶችን በመሥራት፣ የነባር መንገዶችን ደረጃ ከፍ በማድረግ
እንዲሁም የመንገድ ሀብቱን በመንከባከብና እንዳጠቃላይም የመንገድ አውታሩ በተቀናጀ መልኩ የሚያድግበትን አመች
ሁኔታን በመፍጠር ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ተደራሽና ጥራት ያለው የመንገድ አገልግሎት የመስጠት ሀገራዊ ኃላፊነት
ተጥሎበት ከሞላ ጎደል ሃላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል፡፡

ከተሰጠው የሃላፊነት ክብደት አንፃር የአስፈፃሚነት ብቃቱን በመገምገም በበጎ የሚወሰዱ ተሞክሮዎችን ይበልጥ
በማሳደግና የሚስተዋሉ ክፍተቶች በመሙላት በጥሩ የአፈፃፀም ቁመና ላይ መገኘት ይችል ዘንድና የተሰጠውን ሀገራዊ
ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣት እንዲያችለው በብቃትና በጥራት የተደራጀ የሰው ኃይል፣ የማስፈጸም አቅሙን ሊያግዝ
የሚችል ቴክኖሎጂ እና ዘመናዊ የአሰራር ሂደት፣ አደረጃጀት እንዲሁም የፋይናንስ እና የማቴሪያል ግብአቶች አስፈላጊነት
ጉልህ ስፍራ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

ስለሆነም የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የአፈጻጸም ደረጃውን በማሳደግ የተጣለበትን ከፍተኛ ሃላፊነት በሚፈለገው
መልኩ ለመወጣት በተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ ተመርኩዞ በየጊዜው ማሻሻያ ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች መካከል
የመስሪያ ቤቱን መዋቅር መፈተሸና ማሻሻል አንደኛውና ዋነኛው ሲሆን ከተቋቋመለት አላማ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ
አካሄድን መቅረፅና መተግበር አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በመሰረታዊነት የአንድ የመንገድ አስተዳደር መለኪያ ሊሆኑ
ከሚችሉ ዋና ዋና መስፈርቶች መካከል ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው የጊዜ፣ የገንዘብና የጥራት ደረጃ አጠናቆ
የሚጠበቅባቸውን ግልጋሎት እዲሰጡ ለማድረግ የመስሪያቤቱ የአስተዳራዊ መዋቅር መስተካካል የራሱን ከፍተኛ

1|Page
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት የስልጣን ውክልና [Publish Date]

አስተዋፆ ያበረክታል፡፡ በዚህ ረገድ የተቋም አስተዳደራዊ መዋቅር ስኬታማ ነው ሊባል የሚችለው በተለያየ የእርከን ደረጃ
የሚገኙ የስራ ክፍሎችና በስራቸው ያሉ ባለሙያዎችን የሚኖራቸው የስራ ድርሻና ሃላፊነት ከድርጅቱ አጠቃላይ ሲስተምና
ራዕይ ጋር ሲጣጣምና እቅዱ በተፈለገው መልኩ ተፈፃሚ ሆኖ ፕሮጀክቶች ለተፈለገው አላማ እንዲውሉ ማድረግ ሲቻል
ነው፡፡

እንደተቋም የተያዘውን የመንገድ አውታር ሽፋኑ ጥራትን መሰረት ባደረገ መልኩ የማስፋፋት እንዲሁም የመልማት አቅም
ያላቸውን ሁሉም የሀገሪቱን አካባቢዎች በማስተሳሰር ፈጣን የሆነ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትን እንዲያመጣ ታሳቢ
ተደርጎ የወጣውን የተቋሙን ራዕይ ሊሳካ የሚችለው ይህንን ራዕይ ሊያስተገብር የሚችል ተቋማዊ አደረጃጃትና ትግበራ
ሲኖር ብቻ እንደሚሆን አጠያያቂ አይደለም፡፡

ከዚህ አኳያ እስካሁን በነበረው የተቋሙ ታሪክ ውስጥ ተደጋጋሚ የመዋቅር ለውጦች የተደረጉ ሲሆን አሁንም ላይ መሬት
ላይ ያሉ እውነታዎችን በአንክሮ በመመልከት፣ የበፊት ተሞክሮዎች ላይ በመመርኮዝ፣ ለአዳዲስ ለውጦችን በበጎ
የሚያካትትና የሚመጥን ሲስተምን ለመተግበር፣ ተስፋ ሰጭ የወደፊት መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀም፣ ወዘተ
የነበረውን የተቋሙን አደረጃጃትና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ተጨማሪ ማሻሻያ ማድረግን አስፈላጊ እንዲሆን
አድርጎታል፡፡

ስለሆነም እስካሁን በነበረው የተቋሙ መዋቀርና የስልጣን የውክልና ሂደት ላይ መጠነኛ ማሻሻያ የተደረገ ሲሆን በዚህ
መዋቅር መሰረትም ስልጣንና ሃላፊነትን በውክልና እንዲተላለፍ በማድረግ ያልተማከለ የአስተዳደር ሂደት ይበልጥ
እንዲጠናከር በማድረግ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ላይ ፈጣንና ትክክለኛ ውሳኔ እንዲተላለፍባቸውና ለፕሮጀክቶቹ
እንደተግዳሮት በመሆን የትግበራ ሂደታቸውንና አፈፃፀማቸውን የሚያስተጓጉሉ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ ፈጣን የእርምት
እርምጃን ለመውሰድ እንዲያግዝ የሚል እሳቤን የያዘ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ከዚህ ቀደም በዋና መስሪያቤት ደረጃ እየተፈተሹ
ውሳኔ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ እዛው በፕሮጀክቶቹ ሳይት የቅርብ ክትትል በሚያደርጉ የስራ ክፍሎችና ባለሙያዎች
የሚፈለገውን ትክክለኛና ፈጣን ውሳኔ የሚሰጥበት አካሄድ የተቀረፀ ሲሆን በፕሮጀክት ሳይቶች ላይ ወይም አቅራቢያ
በመቀመጥ የስራ ክትትልና ውሳኔ እንዲተላለፍ የተወሰነበት መንገድ የፕሮጀክቶቹን የትግበራ አካሄድ በቅርበት
በመከታተል፣ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በሚፈለገው መልኩና ፍጥነት በመፍታት፣ መልካም አጋጣሚወችን በአግባቡ
በመጠቀም፣ ወዘተ የተቀመጠውን ግብ ለመምታት እንደዋና መሳሪያ በመሆን ያለግላል የሚል አመኔታ ተጥሎበታል፡፡

እዚህ ላይ በፕሮጀክት ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት መካከል ማለትም የአሰሪ መስሪያቤቱ፣ የአማካሪ መሃዲሱና የስራ
ተቋራጩ መካከል ሚዛናዊ የሆነ የስልጣንና የውሳኔ ሰጭነት ሚና እንዲኖር እንዲሁም በተገባው የኮንትራት ማዕቀፍ
መሰረት ውሉ በሚገባ ይተገበር ዘንድ የሃላፊነት፣ የስልጣንና የተጠያቂነት ልክ ግልፅ በሆነ መልኩ መቀመጥ
ስለሚያስፈልገው በዚህ ታሳቢነት የተቀረፀ ሲሆን አዳዲስ እንዲካተቱ የተደረጉ፣ እንዲታጠፉ የተፈለጉና በነበራቸው
አካሄድ እንዲቀጥሉ የተደረጉ የሃላፊነት ቦታዎች ወይም የስራ ክፍሎች የሚኖራቸው ሚናና ሃላፊነት ግልፅ በሆነ መንገድ
የተለየና የተቀረፀ ነው፡፡

2|Page
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት የስልጣን ውክልና [Publish Date]

የስልጣን ውክልናው ዓላማ እና ታሳቢ የተደረጉ መርሆች (Basic Principles)


የስልጣን ውክልና ማለት ስልጣን እና ሃላፊነትን በየደረጃው ለሚገኙ የሙያ ክፍሎች አልያም የሙያ መደቦች ወደታች
ከፋፍሎ የመስጠት ሂደት ሲሆን የመከፋፈሉና ተፈፃሚነት ያለው ስልጣንን መስጠቱ ስኬታማትን በሚያረጋግጥ መልኩ
መሆን ይጠበቅበታል፡፡

የስልጣን ውክልና መሰረታዊ ደረጃዎች

1. ሃላፊነትን መስጠት

ውክልናው ለሚሰጠው አካል የሚኖረውን የስራ ድርሻና ሀላፊነት በሚገባ ለይቶ ማስቀመጡ ምን ምን አይነት ውጤቶች
እንደሚጠበቁ ግልፅ የሆነ እይታን ይፈጥራል፡፡ ስለሆነም ሃላፊነቶችና ተፈላጊ ውጤቶች በሚገባና ግልፅነት ባለው መልኩ
መቀረፃቸው የመጀመሪያው ደረጃ ነው፡፡ በዚህም መሰረት እነዚህ ሃላፊነቶችን ይወጣ ዘንድ ውክልናው ለሚሰጠው
የሙያ ክፍል ወይም ባለሙያ ግልፅ በሆነና በማያሻማ መልኩ መተላለፍ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም የሃላፊነትና የተጠያቂነት
አካሄዱ ከታች ወደላይ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

2. ስልጣንን መስጠት

በደረጃው የሚገኙ የሙያ ክፍሎችና ባለሙያዎች ባላቸው የስራ ድርሻ ልክ የተሰጣቸውን ሃላፊነት ለመፈፀምና
ለማስፈፀም እንዲረዳ የውሳኔ ሰጭነት መብቱ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ይህም የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት መሰረታዊ
ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን የክፍሉ ወይም የባለሙያው የስልጣን ልክ በሚገባ መወሰንና የውሳኔ ሰጭነቱ አልያም የተሰጠው
ስልጣን እስከምን ድረስ እንደሆነ እያንዳንዱ የስራ ክፍልና ባለሙያ ማወቅ ይኖርበታል፡፡

3. ተጠያቂነት

የስልጣን ውክልና በየደረጃው ለሚገኙ የበታች አካላት ሀላፊነትን የመስጠትና ስልጣንን የማጋራት ሂደት ብቻ ሳይሆን
ለተሰጣቸው ሀላፊነት ተገቢውን ውጤት እያመጡ እንደሆነና እንዳልሆነ ክትትልን በማድረግ ተጠያቂነትን ሊያመጣ
የሚችል መሆን አለበት፡፡ እዚህ ላይ ትልቅ ግንዛቤን የሚፈልገው ጉዳይ ሃላፊነት ማለት አንድ ባለሙያ የተሰጠው
አቅጣጫን መሰረት አድርጎ የተጣለበትን ተግባራት በሚገባ መወጣት ሲሆን ተጠያቂነት ማለት ደግሞ አንድ ባለሙያ
በሚጠበቀው የአፈፃፀም ደረጃ ስራውን የመወጣት ግዴታ ነው፡፡

የስልጣን ውክልና ዓላማ

ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተሰጠው ሃላፊነት ከፖሊሲ ቀረፃና እቅድ መንድፍ አንስቶ የመንገድ
ሃብትን እንክብካቤና ጥገና እስከማድረግ ድረስ ቢሆንም ዋነኛ ግቡ የሆነው የፕሮጀክቶችን የማስፈፀም ሚና የሚከተሉትን
አንኳር ግቦችን ይይዛል፡፡

3|Page
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት የስልጣን ውክልና [Publish Date]

ሀ. በጀት (Cost): ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የበጀት እቅድ ውስጥ እንዲጠናቀቁ ማድረግ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ
ሲሆን በዚህም የፕሮጀክቶች ዋነኛ መገለጫ የሆነው ተጨማሪ ወጭ (Cost Overrun) ማስወገድ የግድ የሚል ነው፡፡

ለ. ጊዜ (Time): ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የበጀት እቅድ እንዲጠናቀቁ ማድረግ ሌላኛው አንገብጋ ጉዳይ ሲሆን በዚህም
የፕሮጀክቶች ዋነኛ መገለጫ የሆነው የተራዘመ ጊዜ (Time Overrun) ማስወገድ የግድ የሚል ነው፡፡

ሐ. ጥራት (Quality): ፕሮጀክቶች የሚጠበቅባቸውን ግልጋሎት በሚፈለገው የጥራትና የአገልግሎት ዘመን ልክ መስጠት
ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህም የፕሮጀክቶች ዋነኛ መገለጫ የሆነው አጭር የአገልግሎት እድሜና ዝቅተኛ የአገልግሎት ጥራት
(Unsatsfactory Serviceability and Performance) መወገድ ይኖርበታል፡፡

መ. የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ (Stakeholders Management) ፡ በሁሉም የፕሮጀክት ትግበራ ሂደቶች ላይ


ከሚኖራቸው ቀጥተኛ ወይም ቀጥተኛ ያልሆነ ሚናና ተሳትፎ አንፃር እንዲሁም በአይነትና በብዛት እንደመገኘታቸው
ሁሉም የባለድርሻ አካላት ተገቢውን ተሳትፎ እያደረጉና እነሱን የተመለከቱ ጉዳዮችን በተመለከተ አስፈላጊውን አቅጣጫ
በተፈለገው ጊዜ እያስቀመጡ ማስኬድ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም ከባለድርሻ አካላት አዘውትሮ የሚነሳውን ቅሬታ ማስወገድ
ከማስሻሉም ባሻገር በፕሮጀክቶች ላይ የባለቤትነት ስሜትን በመፍጠር አጋዥ ሃይል እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡

ነገር ግን እስካሁን በነበረው የቁጥጥርና የክትትል አካሄድና ልምድ መሰረት በኢ.መ.ኣ በኩል ፕሮጀክቶችን ለማስተዳደር
እንደመገልገያነት ጥቅም ላይ ሲውሉ ከነበሩ መሳሪያዎች መካከል ወቅታዊ የሳይት ጉብኝት፣ ከስራ ተቋራጭና አማካሪ መሃንዲስ
የሚመጡ ወርሃዊ ሪፖርቶች፣ ከስራ ተቋራጭና አማካሪ መሃንዲስ እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚመጡ ደብዳቤዎች
በዋናነት ተጠቃሽ ሲሆኑ እነዚህም በዋናው መስሪያቤት በኩል ተደራሽ ሆነው በሚመለከተው ክፍልና የስልጣን ተዋረድ
የሚታዩ፣ አቅጣጫና ግብረ መልስ የሚሰጥባቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ መልኩ የሚደረግ የቁጥጥርና የክትትል አካሄድ
በይበልጥ ግብረመልስ ላይ ያዘነበለ (reactive) ሲሆን የጉዳዮቹን ስር መሰረት በመረዳቱና አስፈላጊውን ውሳኔ ከፍጥነት ጋር
በመመለስ ረገድ እንዲሁም ችግሮች እንዳይፈጠሩ በማድረግ (Prevention Mechanism) ረገድ ጉልህ ክፍተትን ይፈጥራል፡

ስለሆነም የተለዩ ጉዳዮች/ችግሮች ላይ መፍትሄ ለማበጀት አለፍ ሲልም አስድሞ መከላከልን መርህ ለማድረግ በዛው
በፕሮጀክቶች ሳይት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በሚገባ መፈተሸና መረዳት አስፈላጊ ከመሆኑ አኳያ የፕሮጀክቶች የቀን ተቀን
እንቅስቃሴ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆን በእጅጉ እንዲሚያፈልግ እሙን ነው፡፡ በተጨማሪም በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ
የፕሮጀክቶች መብዛት ከዚህ አኳያ ያለውን ክፍተት የሚያጎላው ሲሆን ይህ በራሱ አስቸኳያ የማስተካከያ እርምጃን የሚፈልግና
የቁጥጥርና የክትትል ሂደቱን ይበልጥ በሳይት ደረጃ አውርዶ መከወንን አስፈላጊ ከመሆንም አልፎ አስገዳጅ ሁኔታን ፈጥሯል

ስለሆነም የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ፕሮጀክቶችን በኮንትራ ውሉ አግባብ በማስተዳደር ረገድ ሲስተዋሉ የቆዩትን
እነዚህንና ሌሎች ጉዳዮችን በአንክሮ በመመልከትና የፕሮጀክቶች መልካም አካሄድና አጨራረስ ላይ የሚያደርሱትንም አሉታዊ
ተፅዕኖ ታሳቢ በማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንዲኖርበት አስገዳጅ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

ለዚህም እንደ ዋና መፍትሄ ሊወሰድ የታሰበው እዛው በፕሮጀክት ሳይቱና በአቅራቢያው በሚቀመጡ የመስሪያቤቱ የስራ
ክፍሎችና ሰራተኞች የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ሲስተዋሉና የፕሮጀክቶች አካሄድ ላይ ጎታች ሚናን ሲጫወቱ በነበሩ
አያሌ ችግሮችን ከማወገድ በተጨማሪ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት የቅድመ መከላከል ስራን መስራት ዋነኛው ግቡ እንዲሆን

4|Page
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት የስልጣን ውክልና [Publish Date]

ነው፡፡ በዚህ ረገድ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ በፕሮጀክት ደረጃ እልባት ሊሰጣቸው የሚችሉ ጉዳዮችን በመለየት እዛው
በሚቀመጥ የስራ ክፍል ወይም ሰራተኞች ተገቢውን የስልጣን ውክልናና ሃላፊነት በመስጠት እዛው እልባት እንዲያገኙ ማድረግ
ያለውን ቢሮክራሲያዊ አካሄድ በማስቀረትና የፕሮጀክቶችን መልካም አካሄድ አጋዥ ይሆናል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

እንዳጠቃላይ በዚህ አግባብ ሊደረግ የተፈለገው ለውጥ በሚከተለው መልኩ ለፕሮጀክቶች የሚፈለገውን ውጤት ያስገኛል
ተብሎ አመኔታ ተጥሎበታል፡፡

1. የኢ.መ.አን የኮንትራት ሃላፊነቶች አጥጋቢ በሆነ መልኩ ለመወጣት

እንደ አንድ ዋነኛ የባለድርሻ አካልነቱ እንዲሁም የስራው ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በሁሉም የፕሮጀክቶች
የትግበራ ሂደት ወቅት መሰረታዊ የሆኑ ኮንትራታዊ ሃላፊነቶች አሉበት፡፡ ስለሆነም እነዚህን ሀላፊነቶች በሚፈለገው መልኩና
ፍጥነት መወጣት አለመቻል ለፕሮጀክቱ የታሰበውን ግብ አለመምታት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የራሱን አሉታዊ ድርሻ
ይወስዳል፡፡ ስለሆነም የአሰሪ መስሪያቤቱ ያሉበትን የኮንትራት ሃላፊነቶች የሚወጣበት መንገድና ጊዜ የፕሮጀክቶቹ አካሄድና
አፈጻፀም ላይ ጉልህ ተፅዕኖን ስለሚፈጥር ፕሮጀክች በሚፈለገው ልክ ተግባራዊ እንዲሆኑ ከተፈለጊ እነዚህ ወሳኝ ሃላፊነቶች
በሚገባ ተፈፃሚ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ይህም በዋናነት የወሰን ማስከበር ስራዎችን ላይ ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚኖሩ ጉዳዮችን በመፍታ ረገድ፣ የአሰሪ
መስሪያቤቱን ተሳትፎና ርምጃ በሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ፣ በክፍያ ሰነዶች ዝግጅታና አፈፃፀም ላይ፣ ወዘተ ፈጣንና ትክክለኛ
ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ወይም ድርጊቶችን ለመከወን ያግዛል፡፡

ፕሮጀክት ማለት የሁሉም ባላድርሻ አካላት ጥርቅም ውጤት እንደመሆኑ መጠን ሁሉም አካላት በተሰጣቸው የሃላፊነት ሚዛን
ልክ ፈፃሚ ሆነው ሊገኙ ስለሚገባ አሰሪ መስሪያቤቱም በዚህ ረገድ ያሉበትን የትኛውንም ሃላፊነት አጥጋቢ በሆነ መልኩ
ሊወጣ ይገባል፡፡

ስለሆነም እነዚህ ሃላፊነቶች በዚህ መልኩ ተፈፃሚ እንዲሆኑ የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎችና ባለሙያዎች በፕሮጀክት
ሳይቶች ላይ ተቀማጭ ሆነው የቅርብ ክትትልና ርምጃ የመውሰዱ አስፈላጊነት አሻሚ ያልሆነ አውነታ ነው፡፡

2. ሌሎች የባለድርሻ አካላት በተለይም አማካሪ መሃንዲሶችና የስራ ተቋጮች ድርሻቸውን በሚፈለገው መልኩ
እየተወጡ እንደሚገኙ ማረጋገጥ

በኮንትራት ማዕቀፉ ወይ ውሉ ላይ የያንዳንዱ የስራ ባለድርሻ ሃላፊነት በጊዜ፣ ይዘት፣ አይነትና ጥራት ምን እንደሆነ በሚገባ
የተቀመጠና የፕሮጀክቱ ክንውንም ይህንን መሰረት ያደረገ እንደመሆኑ ሁሉም የውል አካላት ያለባቸው ሃላፊነት በሚፈለገው
መልኩ ሊወጡ ይገባል፡፡

ነገር ግን ለፕሮጀክቶች ደካማ አፈፃፀምና ውድቀት እንደዋነኛ ምክንያት ከሚጠቀሱ ችግሮች ውስጥ የእነዚህ ወሳኝ ባለድርሻ
አካላት ሚና በሚፈለገው መልኩ አለመፈፀም አንዱ ሲሆን የሚኖረውም አሉታዊ ተፅዕኖ ትልቅ ነው፡፡ የማማከርና የቁጥጥር
ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ያልቻለ አማካሪ መሃንዲስና ስራውን በውሉ አግባብ ማስኬድ የተሳነው የስራ ተቋራጭ
የፕሮጀክቱ ህልውና ላይ የሚኖራቸው አሉታዊ ተፅዕኖ የገዘፈ ነው፡፡ ስለዚህ የመንገድ ፕሮጀክቱን ህልውና ከማስጠበቅ አንፃር
እነዚህ ወሳኝ የባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ተግባር በሚፈለገው መልኩ እየተገበሩ እንደሚገኙ ክትትልና ቁጥጥር

5|Page
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት የስልጣን ውክልና [Publish Date]

በማድረግ ማረጋጋጥ አስፈላጊ ሲሆን ክፍተቶች የሚስተዋሉ ከሆነም የፕሮጀክቱን ቁመና በሚያተካክል መልኩ አስፈላጊው
የማስተካከያ እርምጃ በቶሎ ሊወሰድ ይገባል፡፡

ስለሆነም የአሰሪ መስሪያቤቱ የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎችና ባለሙያዎች የፕሮጀክት ሳይቶቹ ላይ ወይም አቅራቢያ ሆነው
የፕሮጀክቱን የቀን ተቀን ክንውንና የነዚህን ወሳኝ የባለድርሻ አካላት ተግባር መቆጣጠሩና አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ
መውሰዱ የሚያበረክተው አወንታዊ አስተዋፆ ትልቅ ነው፡፡

ይህ ከላይ በሰፊው የተብራራው የፕሮጀክቶችን የትግበራ ሂደት ማሳለጥና የሚፈለገውን ግብ እንዲመቱ የማድረጉ አስፈላነት
በዋናነት ለዚህ የስልጣን ውክልና ወይም መዋቅር መሻሻል ትልቁን ድርሻ ይውሰድ እንጅ ከዚህ በተጓዳኝ የሚከተሉት ዋና ዋና
ጉዳዮችም የውክልና አሰጣጡ ላይ ለውጥ እንዲመጣ ገፋፊ ምክንያቶች ናቸው፡፡

• የመንገድ ሀብት እንክብካቤ እና ጥገና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ የተጠቃሚውን ፍላጎት ማርካት፣
ኢኮኖሚያዊ ልማትን መደገፍ፤
• ሥራዎችንና የሥራ ክፍሎችን እንደገና በማደራጀት ቀልጣፋ ፣ወጪ ቆጣቢ እና ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ
• በየጊዜው ቁጥሩና ሥርጭቱ እየጨመረ እና እየሰፋ የመጣውን የግንባታ ፕሮጄክቶች በቅርበት በመገኘት
ክትትልና ድጋፍ በመሥጠት የፕሮጄክቶችን አፈጻጸም ማሻሻል የሚያስችል አደረጃጀት ማስፈለጉ፣ ለዚህም
ሲባል ስልጣንን እና ሃላፊነትን እሰከ ታችኛው የስራ ክፍል ማውረድ ቁለፍ ሆኖ በመገኘቱ
• በሂደት በኢ.መ.አ ተግባርና ኃላፊነት ላይ የተጨማሩ ተግባሮችና ኃላፊነቶችን በአግባቡ መሸከም የሚችል
አደረጃጀት ማስፈለጉ ( የራስ ኃይል መንገድ ጥገና፣መንገድ ፈንድ)፣
• የመንገድ ሀብትን በአግባቡ ለመንከባከብ እና ወቅታዊ የጥገና አገልግሎት ለመስጠት ያጋጠመውን የተደራሽነት
ችግር ለማቃለል ተገቢ አደረጃጀት መፍጥር ማሰፈለጉ
• መቀናጀት ሲገባቸው ተበታትነው የተደራጁ፣ በሥራ ክብደታቸውና መጠናቸው ልክ አደረጃጀት
ያልተፈጠራላቸውን ሥራዎችና የሥራ ክፍሎች እንደገና በማየት ቀልጣፋ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ
ማደራጀትን በማስፈለጉ፣
• በአጠቃላይ ቀጣዩን የመንገድ ዘርፍ የ10 ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ትግበራን ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ግልጽ
እና ተጠያቂነት ባለው አሰራር መፈጸም የሚያስችል ድርጅታዊ መዋቅር ማስፈለጉ፡፡
የዚህ የውክልና አሰጣጥ ሂደት የሚያመጣቸው ጥቅሞች

ይህን መሰል የመዋቅር ለውጥና አደረጃጀት መፈጠሩ ከሚያስገኛቸው አያሌ ጥቅሞች መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ
ናቸው፡፡

➢ የስራዎችን የክንውን አፈፃፀም ለማሳደግ በትክክለኛው የውክልና ሂደት ሃላፊነቶችን ማከፋፈል (delegation)
በተለይም በበላይ የማኔጅንት አካላት ላይ የሚኖረውን ከፍተኛ የስራ ጫና በመቀነስ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ
እንዲያተኩሩ በቂ ጊዜና ነፃነትን ይሰጣል፡፡

6|Page
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት የስልጣን ውክልና [Publish Date]

➢ ፈጣን የውሳኔ አሰጣጥ ሂደትን ስለሚፈጥር ለጉዳዮች ወቅታዊና ፈጣን ምላሽን እንዲያገኙ ያስችላል፡፡ የውሳኔ
አሰጣጥ ሂደቱም የነገሩን ነባራዊ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ለጉዳዩ ያለው ቅርበት አጋዥ ስለሚሆን
የውሳኔውን ትክክለኛነትና ፍጥነት ይጨምራል፡፡
➢ አዳዲስ ለውጦችን ወይም ማስተካካያዎችን ማድረግ በሚያስፈልግበት ወቅት በቀላሉ ለማካተት ምቹ ሁኔታን
ይፈጥራል፡፡
➢ በየደረጃው ለሚገኙ የእርከን ደረጃዎችና ባለሙያዎች በራሳቸው የሚወስኑበትና የሚጠየቁበትን የአሰራር ሂደት
ስለሚፈጥር የስራ ትጋትንና አፈጻጸምን ለማሳደግ ትልቅ ጠቀሜታ ይሰጣል፡፡
ታሳቢ የተደረጉ መርሆች (Basic Principles)

• ተፈጥሯዊ የስራ ፍሰት (Natural Works Flow) መከተል

የመንገድ ስራ ፕሮጀክቶች በባህሪያቸው ብዙ ባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፉ እንደመሆናቸው፣ ተለዋዋጭና አብዛኛውን ጊዜ


በትክክል ሊገመት በማይችል ሁኔታ ላይ የሚተገበሩ በመሆኑ ፣ ለትግበራው ረዘም ያለ ጊዜን የሚወስዱ መሆኑ፣ ብዙ አይነትና
ቁጥር ያላቸውን ንዑስ ስራዎችን ማካተታቸው፣ ወዘተ የፕሮጀክቶቹን የትግበራ ሂደት ውስብስብና ከፍተኛ ጥንቃቄን
እንደያስፈልገው ያስገድዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የስራዎቹ ሂደት ወይም ንዑስ የስራ ውጤቶች የራሳቸውን ሂደት ተከትለው
የመጨረሻውን ውጤት ከመወሰናቸው አኳያ እያንድንዱን የስራውን ሂደት የቅርብ ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ
ነው፡፡

ከዚህ አኳያ በየንዑስ የስራ ሂደቶች ላይ የሚጠበቀውን ውጤት በማምጣት ፕሮጀክቱ በታቀደው ልክ እንዲጠናቀቅና
የሚጠበቅበትን ግልጋሎት ይሰጥ ዘንድ ሁሉም የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላት ያሉባቸውን ሃላፊነቶች አጥጋቢ በሆነ መልኩ
ሊወጡ የሚገባ ሲሆን ይህም መሬት ላይ ያለ እውነታ እንደሆነ የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ መረጋጥ ይኖርበታል፡፡
ስለሆነም የስልጣን ውክልና መኖሩ በዚህ ረገድ የስራውን የክንውን ሂደት በደንብ የተረዳ የክትትልና የቁጥጥር ስርዓትን
ለመዘርጋት ያስችላል፡፡

• የስራ ጫና ፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነትን ማመጣጠን (Balancing Work Load, Duties & Responsibilities)

የስራ ሂደቶች እንደሚይዙት የውሳኔ ክብደት፣ እንደሚፈልጉት የቴክኒክ እውቀት፣ የግብረመልስ ጊዜና ሌሎች አስፈላጊ
የሆኑ ጉዳዮች አንጻር ተመዝነው ለሚመለከተው የስራ ክፍልና ባለሙያ ቢመደቡ አስፈላጊውን የቅርብ ክትትልና የውሳኔ
አሰጣጥ ሂደትን ይፈጥራል፡፡ ይህም ሁሉም ባለሙያ መሸከም በሚችለው ልክ ሃላፊነቱና ተጠያቂነቱን ስለሚሰጠው
ስራዎች በሚፈለገው የፍጥነትና የአፈጻጸም መለኪያ እንዲከወኑ ይረዳል፡፡ ስለሆነም አግባብ የሆነ የስልጣን ውክልና
ስራዎች በሚፈለጉበት የአፈፃፀም ደረጃ እንዲከወኑ ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥር የሰራተኛውን እርካታና የስራውን ባህሪ
ያማከለ እንዲሆን ያርገዋል፡፡

• የሥራ ተግባር እና ኃላፊነትን እንዲሁም የመወሰን ሥልጣን እንዳስፈላጊነቱ ወደታች በማውረድ ቀልጣፋ
የአመራር ፣የአሠራር እና አፈጻጸም ውጤት እንዲኖር ማድረግ (Decentralization)

7|Page
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት የስልጣን ውክልና [Publish Date]

ያልተማከለ አደረጃጀት (Decentralization) ማለት ስልጣንን በሁሉም የማኔጅንት እርከን ላሉ አካላት ስልታዊ በሆነ
መንገድ የመወከል ወይም የመስጠት ሂደት ነው፡፡ እዚህ ላይ ትልልቅ ውሳኔዎችና የፖሊሲ ጊዳዮችን የተመለከቱ ሃፊነቶች
ለበላይ የማኔጅንት አካላት የሚተው ሲሆን ሌሎች ጉዳዮች ደግሞ እንደክብደታቸውና ደረጃቸው በመካከለኛውና
በታችኛው መደብ ላይ ለተቀመጡ የማኔጅመት የአስፈጻሚ አካላት የሚሰጥ ነው፡፡ ስለሆነም ይህ አደረጃጀት በሁሉም
እርከን ያሉ ክፍሎችን በተሰጣቸው የስልጣን ደረጃ በነፃነት ተግባራቸውን እንዲከውኑና የሚጠበቀውን ተቋማዊ ራዕይና
ግብ በተባበረ መልኩ እንዲያሳኩት የሚያግዝ ስልት ነው፡፡

በትግበራ ላይ ያለው የስልጣን ውክልና ለመከለስ ያስፈለጉ ምክንያቶች

ባጠቃላይ አስካሁን በትግበራ ላይ የቆየውን የስልጣን ውክልና ለመከለስ ምክንያች የነበሩ ጉዳዮችን ከያንዳንዱ የስራ
ክፍል አንፃር እንደሚከተለው በሰንጠረዥ ተዳሰዋል፡፡

• በየጊዜው ቁጥሩና ሥርጭቱ እየጨመረ እና እየሰፋ የመጣውን የግንባታ ፕሮጄክቶች በቅርበት በመገኘት
ክትትልና ድጋፍ በመሥጠት የፕሮጄክቶችን አፈጻጸም ማሻሻል የሚያስችል አደረጃጀት ማስፈለጉ፣ ለዚህም
ሲባል ስልጣንን እና ሃላፊነትን እሰከ ታችኛው የስራ ክፍል ማውረድ ቁለፍ ሆኖ በመገኘቱ

• በሂደት በአመአ ተግባርና ኃላፊነት ላይ የተጨማሩ ተግባሮችና ኃላፊነቶችን በአግባቡ መሸከም የሚችል
አደረጃጀት ማስፈለጉ (የራስ ኃይል መንገድ ጥገና፣መንገድ ፈንድ)፣

• የመንገድ ሀብትን በአግባቡ ለመንከባከብ እና ወቅታዊ የጥገና አገልግሎት ለመስጠት ያጋጠመውን የተደራሽነት
ችግር ለማቃለል ተገቢ አደረጃጀት መፍጥር ማሰፈለጉ

• መቀናጀት ሲገባቸው ተበታትነው የተደራጁ፣ በሥራ ክብደታቸውና መጠናቸው ልክ አደረጃጀት


ያልተፈጠራላቸውን ሥራዎችና ነሥራ ክፍሎች እንደገና በማየት ቀልጣፋ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ
ማደራጀት ማስፈለጉ፣

• በአጠቃላይ ቀጣዩን የመንገድ ዘርፍ የ10 ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ትግበራን ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ግልጽ
እና ተጠያቂነት ባለው አሰራር መፈጸም የሚያስችል ድርጅታዊ መዋቅር ማስፈለጉ፡፡

8|Page
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት የስልጣን ውክልና [Publish Date]

ዳይሬክቶሬት በትግበራ ላይ የነበረው የስልጣን ውክልና ክፍተቶች

የዳይሬክቶሬቶች የስራ ሀላፊነት በግልፅ አለመቀመጡ (10 RNSMBDs )


• ትግበራ (Implementation)
• የክትትል እና ግምገማ (Monitoring and Evaluation)
የመንገድ ሀብት ማኔጅመንት ም/ወና ከዚህ ቀደም የነበረው የስልጣን ውክልና ለ RAMCD፣ RNSMBDs ከፍተኛ የስራ ጫና የሚሰጥ እና
ዳይሬክተር፣ Coordination Directorate የመወሰን አቅምን ያላማከለ ነበር
and RNSMBD • EOT
• Variation
• ROW compensation
የመንገድ ሀብት አስተዳደር

• RE, ARE and Team Leader


የcoordination ዳይሬክቶሬት እና ሲስተም ማኔጅመንት መካከል ያለው የስራ ክፍፍል በግለፅ
አልተቀመጠም
RAM, DDG ,RAM, ሲስተም ማኔጅመንት • Planning
and RNSMBD • Programming
• Preparation
• Implementation
• Monitoring and Evaluation
የመንገድ ጥገና ክፍል ከዚህ ቀደም በነበረው የስልጣን ውክልና ላይ የተብብር ሰጪ ሚና ብቻ እንጂ ውሳኔ
RAM, DDG ,የመንገድ ጥገና ዳይሬክቶሬት
የመስጠት ስልጣን አልነበረውም
RAM, DDG, Goods Procurement and
Supplies Management Directorate
በአዲስ የተዋቀሩ ክፍሎች አንደመሆናቸው በተከለሰው የስልጣን ውክልና ላይ እንዲካተቱ ሆኗል
RAM, DDG ,Bridge construction and
maintenance Directorate

** በተከለሰው መዋቅር መሰረት ስልጣንን እንዲሁም አጠቃላይ ስራዎችን ወደ መስክ የማውረድ እና የdecentralization
አለማ ስላለው በትግበራ ላይ ይገኝ የነበረው የስልጣን ውክልናን መከለስ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ከሌሎች ሀገራትና ተቋማት የተወሰዱ ተሞክሮዎች

1. የታንዛንያ መንገድ ኤጀንሲ ተሞክሮ

ይህንን ሲስተም ትግበራ ላይ በማዋል የተገኙ ተሞክሮዎችን በመቅሰም ረገድ የሌሎች ሀገራትን ልምድ ለመቃኘት
የተሞከረ ሲሆን የታንዛንያ መንገድ ኤጀንሲ (TANROADS) ተመሳሳይ አካሄድን የሚከተል ሲሆን ፕሮጀክቶችን
እንዲያስፈፅም ሃላፊነት የተሰጠው አካል (Directorate of Projects) የስልጣን ክፍፍልና የሃላፊነት መደብን በዋና
መስሪያቤትና በፕሮጀክቶች ላይ በሚቀመጡ መሃንዲሶች መካከል በመከፋፈል ፕሮጀክቶቹን ያስተዳድራል፡፡
የትግበራውን ውጤታማነትም ለማረጋገጥ ያስችል ዘንድ ተከታታይ የኦዲት ስራዎች እንደ ትልቅ መሳሪያነት ግልጋሎት
ላይ ይውላሉ፡፡

ይህም የታንዛንያ ልምድ በኢ.መ.አ ሊተገበር ከታሰበው አካሄድ ጋር ተመሳሳይ ይዘትና አንድምታ ያለው ቢሆንም በዋና
መስሪያቤትና በፕሮጀክት ሳይት ደረጃ ባሉ የአሰሪ መስሪያቤቱ የስልጣን እርከኖችና የሙያ ደረጃዎች መካከል ያለው
9|Page
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት የስልጣን ውክልና [Publish Date]

የሃላፊነት አይነት፣ ልክ፣ አተገባበርና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ግልፅ በሆነ መልኩ የተዋቀረ ባለመሆኑ የተፈለገውን ውጤት
እንዳላመጣ የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ከዚህ አንፃር በዋና መስሪያቤትና በፕሮጀክት ሳይቶች ላይ በሚሰየሙ
ባለሙያዎች የሚኖረው የስልጣን ተዋረድ፣ የሃላፊነት ልክ፣ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች፣ ወዘተ ላይ በሚገባ፣ ግልፅና ተፈጻሚ
በሆነ መልኩ መቅረፅና ተፈፃሚነቱን ማረጋገጥ ካልተቻለ የተፈለገውን ውጤት እንደማያስገኝ የታንዛንያ ተሞክሮ በግልፅ
አመላካች ነው፡፡

2. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ተሞክሮ

በመቀጠል ልምድን ለመውሰድ የሚያስችል ተመሳሳይ አደረጃጀትን የያዘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት
ሲሆን የተቋሙም መዋቅር እንደሚከተለው በዋና መስሪያቤትና በሪጅን የስራ ክፍሎች የተዋቀረና የስራ ክፍሎቹም
ተግባርና ስልጣን ተለይቶ የተቀመጠ ነው፡፡

▪ በዋና መስሪያቤት ደረጃ ያሉ የስራ ሀላፊነቶች

▪ የተቋሙን የአጭርና ረጅም ጊዜ አቅድ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂ ትግበራን ማረጋገጥ


▪ የተገልጋዩን ማህበረሰብና የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ጥያቄዎችን ባማከለ መልኩ በአገልግሎት ደረጃና ተደራሽነት በኩል
ማሻሻያዎችን ማድረግ
▪ ስታንዳርዱን የጸበቀና ወቅቱን ያማከለ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ሲስተምን መዘርጋት
▪ በሪጅናል እና ሌሎች ዘርፎች የሚገኙ ተግባራትን ለዳይሬክተሮች ቦርድ ማቅረብ
▪ በአጠቃላይ የአስተዳደር ስራዎችን መከታተልና ተፈፃሚ ማድረግ

▪ በዲስትሪክት ደረጃ ያሉ የስራ ሀላፊነቶች

▪ በየዲስትሪክቱ እና ሪጅኖች የሚገኙ ፕሮጀክቶችን መምራት፣ መቆጣጠር፣ ማስተዳደር ፣ መገምገም


▪ በዲስትሪክት ደረጃ የሚቀርቡ የሀይል ፍላጎቶችንና ሌሎች የአገልግሎት ጥያቄዎች ላይ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት
▪ በዲስትሪክት የማይቆራረጥ የሀይል አቅርቦትን እና የደንበኞች መስተንግዶን ማረጋገጥ
▪ የኦዲት፣ የኮምኒኬሽን፣ፕላኒንግ፣ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና፣ የህግ ክፍል፣ የቅሬታ ሰሚ፣ ወዘተ በዲስትሪክት ደረጃ
የተቋቋሙ ሲሆን የተሰጣቸውን ልዩ ልዩ ሀላፊነቶችንና ተግባራት በመወጣት ላይ ይገኛሉ፡፡

10 | P a g e
መደምደሚያ
ከላይ በሚገባ እንደተብራራው አስካሁን ሲተገበር የቆየው የመስሪያቤቱ የተማከለ ተቋማዊ አደረጃጀትና የስልጣን ውክልና
ውስንነት ለፕሮጀክቶች ደካማ አፈፃፀምና ግብ ያለመምታት ብቻውን ምክንያት ባይሆንም የራሱን አሉታዊ ድርሻ
እንደተወጣ ግን አሙን ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ይህንን ችግር በመቅረፍ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው የገንዘብና የጊዜ ገደብ
እንዲሁም በአጥጋቢ የጥራት ደረጃ ተሰርተው ለተፈለገው አላማ ይዉሉ ዘንድ አስፈላጊውን የክትትልና የቁጥጥር ሂደት
መፍጠር አስፈላጊ ሁኖ ተገኝቷል፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ የተቋሙን አደረጃጀትና የስልጣን ውክልና በማሻሻል አስፈላጊ
የሆኑ የስራ ክፍሎችን ወይም ባለሙያዎችን በፕሮጀክቶቹ ሳይት ላይ ወይም አቅራቢያ በማስቀመጥ እንዲሁም
አስፈላጊውን የስልጣን ውክልና በመስጠት ለችግሮቹ እልባት እየሰጡና የሚያስፈልገውን አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስዱ
ይህ ውሳኔ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ባጠቃላይ ይህንን የለውጥ ሂደት በተመለከተ፡-
▪ በተከለሰው መዋቅር መሰረት የሚቋቋሙ የሥራ ክፍሎች እና አዳዲስ የስራ መደቦችን የስልጣን ውክልናን ውስጥ
እንዲካተቱ ተደርጓል
▪ በተደረገው ክለሳ ውስጥ የስራ መጓጓት ከዚህ ቀደም እንዲኖር ምክንያት የሆኑ የሀላፊነት አደላደሎች ላይ ለውጥ
ተደርጓል
▪ በተከለሰው መዋቅር መሰረት ስልጣንን እንዲሁም አጠቃላይ ስራዎችን ወደ መስክ የማውረድ እና
የdecentralization/የስልጣን ክፍፍል አለማ ስላለው በትግበራ ላይ ይገኝ የነበረው የስልጣን ውክልናን ይህን ባማከለ
መልኩ እንዲከለስ ሆኗል፡፡
▪ አዲሱ ድርጅታዊ መዋቅር ስኬታማነቱ እንዲረጋገጥ በተከለሰው የስልጣን ውክልና መሰረት አስፈላጊውን አካሄድ
ከግምት ውስጥ በማስገባት ተዘጋጅቷል፡፡

11 | ገ ፅ
የኢ.መ.አ የተከለሰው መዋቅር (ORGANAIZATIONAL STRUCTURE)

MUDI
MoF
ERA Board

ERA –Director General


Ethics &Anti corruption Commission

Internal Audit service


Advisors
Ethics Directorate
Pool

Off. Of Director PD DDG CPM DDG RAM DDG CS DDG


General DDG
Advisors Advisors Advisors Advisors

PPMD EW&CSP Directo CPM-DDGO Proc.& Supply Financial Alemgena Train.

Legal Regions (5) Cent. Equip. Ginchi Train


DM Directorate HRMD

PQSM
የስራ RoWM Direc. ESOHS Bridge &Stru. Change & ID
WYAD
RRC Directorate Mega &Special RAM Coo. ICT
Road Fund
Branches. (11) Property &facil.

Own force RM

1 Director General 5 7 52
Deputy DG Executive & Senior Directorate Branches. (11)

12 | ገ ፅ
የኮንስትራክሽን ፕጀክቶች ማኔጅንት የተከለሰው መዋቅር (CPM Structure)

ዋና ዳይሬክተር

CPM ም/ዋና
ዳይሬክተር

Special CPM Advisors


ምስራቅ ምዕራብ ደቡብ ሰሜን ማዕከላዊ Pro.M EsOHs • Chief Engineer
O • Senior Advisors
• Senior Engineers

•PM
PMU PMO •DPM
P
Stakeholder M RoW Experts
•Stak.&
& RoW Mgt •Unit Team Leader •PM O
•EsOHs Experts
• Lead Engineers •DPM •QA & QC Experts
• Admin Assistant •Senior Engineers •Stak.& RoW Experts •Design Experts
• Finance officer •Engineers •EsOHs Experts •Project Engineers
• Lead RoW AG. •Junior Engineers •QA & QC Experts •Admin Assistant
• RoW Agents •Office Assistant •Project Engineers
•Drivers
•IT Experts
•Admin ast

13 | ገ ፅ
የተከለሰው የስልጣን ውክልና

ለግንባታ ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ም/ዋና ዳይሬክተር ፣ በቀጥታ ተጠሪ ለሆኑ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮችና በስራቸው
ለሚገኙ ቡድን መሪዎች የተሰጠ የሥልጣን ውክልና

14 | ገ ፅ
የስልጣን ውክልና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊዎች
ፕሮጀክት የአካባቢ ፣
የአካባቢ ፣ ማህበራዊ
የስልጣን ውክልና ማኔጅመንት ቢሮ ማህበራዊ እና
የተሰጠበት ጉዳይ ሪጅናል ፕሮግራም ማናጀር እና እና የሥራ ላይ
የኮንስትክሽን ፕሮጀክቶች የአማካሪ ፑል ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮጀክት ማኔጅመንት የወሰን ማስከበር፣ የሥራ ላይ ደህንነት
የልዩ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት ደህንነት
ማኔጅመንት ም/ዋና ዳይሬክተር ቺፍ/ዋና ኢንጅነር ቢሮ ፕሮጀክት ማናጀር ዩኒት ቡድን መሪ አስተዳደርና ዳይሬክቶሬት ስር
ማናጀር ዳይሬክቶሬት
ፋይናንስ ቡድን የሚገኙ ቡድን
ዳይሬክተር
መሪዎች መሪዎች
ለተቋራጮችና
የአካባቢ፣ ማህበራዊ
አማካሪዎች ወደ
እና የሥራ ቦታ
ኘሮጀክት ሳይት
ደህንነትን
የሥራ ትዕዛዝ ወይም - ለመግባት ያልተገደበ
የሥራ ማስጀመሪያ ትዕዛዝ አስመልክቶ ለሚሰሩ
ፈቃድ (Work - ፈቃድ መስጠት፡፡ - - -
መስጠት፡፡ የማማከር
Order) መስጠት (Unrestricted site
አገልግሎቶች የስራ
Access Permit to
ማስጀመር ትዕዛዝ
contractors and
መስጠት፡፡
consultants)
1. የጊዜ ማራዘሚያ
(EOT) ጥያቄ
ለውሳኔ
በሚላክበት ወቅት
1. የጊዜ ማራዘሚያ (EOT) 1. የጊዜ ማራዘሚያ (EOT)
ጥያቄውን
ጥያቄ በመጀመሪያው የውለታ ጥያቄ በመጀመሪያው የውለታ የጊዜ ማራዘሚያ
መርምሮ 1. የጊዜ ማራዘሚያ (EOT)
ጊዜ ውስጥ (Original contract ጊዜ ውስጥ (Original (EOT)
ተገቢውን በሚመለከት የሚቀርቡ
period) እስከ 180(አንድ መቶ contract period) እስከ 60 የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄዎችን እና
የማማከር ጥያቄዎችን መርምሮ
ሰማኒያ) ቀናት መፍቀድ፣ ሆኖም (ስልሳ) ቀናት መፍቀድ፣ (EOT) ጥያቄዎችን ተያይዘው
የኮንትራት የጊዜ አገልግልት ለፕሮግራም ማናጀር
አጠቃላይ የጊዜ ማራዘሚያው ሆኖም አጠቃላይ የጊዜ እና ተያይዘው የሚመጡ
ማራዘሚያ ፈቃድ ለም/ዋና ያቀርባል፡፡
ከመጀመሪያው የውለታ ጊዜ ማራዘሚያው ከመጀመሪያው የሚመጡ የይገባኛል የይገባኛል
(Extension of Time ዳይሬክተሩ
ከ15% መብለጥ የለበትም፡፡ የውለታ ጊዜ ከ10% መብለጥ (Claim) ጥያቄዎችን (Claim) - -
– EOT) ፡- የይገባኛል ይሰጣል፡፡ 2. የፕሮጀክት ግንባታ
የለበትም፡፡ ለሚመረምረው ዪኑት ጥያቄዎችን
ጥያቄዎች 2. የፕሮጀክት አፈፃፀም በማስመልከት
2. የፕሮጀክት ግንባታ አፈፃፀም አስፈላጊውን መረጃ ለሚመረምው
ስለመፍቀድ ግንባታ አፈፃፀም የሚቀርቡ የይገባኛል
በማስመልከት የሚቀርቡ 2. የፕሮጀክት ግንባታ አፈፃፀም በመስጠት ይተባበራል፡ ዪኑት
በማስመልከት (Claim) ጥያቄዎችን
የይገባኛል (Claims) ጥያቄዎችን በማስመልከት የሚቀርቡ ፡ አስፈላጊውን
የሚቀርቡ መርምሮ ለፕግራም ማናጀር
በማረጋገጥ ውሳኔና አቅጣጫ የይገባኛል (Claim) መረጃ በመስጠት
የይገባኛል ያቀርባል፡፡
እንዲሰጥበት ለዋናው ጥያቄዎችን መርምሮ ይተባበራል፡፡
(Claim)
ዳይሬክተር ያቀርባል፡፡ ለም/ዋ/ዳይሬክተር ያቀርባል፡፡
ጥያቄዎችን
መርምሮ
ለም/ዋ/ዳይሬክተር
ለውሳኔ ያማክራል

15 | ገ ፅ
የስልጣን ውክልና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊዎች
ፕሮጀክት የአካባቢ ፣
የአካባቢ ፣ ማህበራዊ
የስልጣን ውክልና ማኔጅመንት ቢሮ ማህበራዊ እና
የተሰጠበት ጉዳይ ሪጅናል ፕሮግራም ማናጀር እና እና የሥራ ላይ
የኮንስትክሽን ፕሮጀክቶች የአማካሪ ፑል ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮጀክት ማኔጅመንት የወሰን ማስከበር፣ የሥራ ላይ ደህንነት
የልዩ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት ደህንነት
ማኔጅመንት ም/ዋና ዳይሬክተር ቺፍ/ዋና ኢንጅነር ቢሮ ፕሮጀክት ማናጀር ዩኒት ቡድን መሪ አስተዳደርና ዳይሬክቶሬት ስር
ማናጀር ዳይሬክቶሬት
ፋይናንስ ቡድን የሚገኙ ቡድን
ዳይሬክተር
መሪዎች መሪዎች
የግንባታ የለውጥ
ሥራ (Variation
ከተቆጣጣሪ መሃንዲሱ ስልጣን ከተቆጣጣሪ መሃንዲሱ
Order) ትዕዛዝ
በላይ የሆኑ የግንባታ የለውጥ ከተቆጣጣሪ መሃንዲሱ ስልጣን ስልጣን በላይ የሆኑ
የለውጥሥራ መርምሮ
ሥራ ትዕዛዝ (Variation በላይ የሆኑ የግንባታ የለውጥ የግንባታ የለውጥ ሥራ
(Variation Order) በሚቀርብበት -
Order) በመጀመሪያው የውለታ ሥራ (Variation Order) (Variation Order) - - -
ጥያቄዎች ወቅት በጥልቅ
መጠን እስከ 10,000,000 ብር ትዕዛዝ መርምሮ ትዕዛዝ መርምሮ
ስለመፍቀድ በመመርመር
(አምስት ሚሊዮን ብር) ለም/ዋ/ዳይሬክተር ያቀርባል፡፡ ለፕሮግራም ማናጀሩ
ቴክኒካል እገዛ
መፍቀድ፡፡ ያቀርባል፡፡
ለም/ዋ/ዳይሬክተር
ያደርጋል፡፡
የይገባኛል ጥያቄ
(Claim) (የገንዘብ
ይገባኛል Cost የይገባኛል ጥያቄ
የይገባኛል ጥያቄ (Claim) Claim ጨምሮ) የይገባኛል ጥያቄ (Claim) (Claim) (የገንዘብ የይገባኛል ጥያቄ (Claim)
የይገባኛል ጥያቄ
(የገንዘብ ይገባኛል Cost Claim እና ክርክር (የገንዘብ ይገባኛል Cost ይገባኛል Cost Claim (የገንዘብ ይገባኛል Cost
(Claim) (የገንዘብ
ጨምሮ) እና ክርክር (Dispute) (Dispute) Claim ጨምሮ) እና ክርክር ጨምሮ) እና ክርክር Claim ጨምሮ) እና ክርክር
ይገባኛል Cost Claim - - -
ጉዳዮችን ገምግሞ ለዋና ጉዳዮች ላይ (Dispute) ጉዳዮችን ገምግሞ (Dispute) ጉዳዮችን (Dispute) ጉዳዮችን
ጨምሮ) እና ክርክር
ዳይሬክተር እንዲፀድቅ በጥለቅት ለም/ዋና ዳይሬክተር ያቀርባል፡ ጋር በተያያዘ ገምግሞ ለፕሮግራም
(Dispute)
ያቀርባል፡፡ በመሳተፍ ሙያዊ ፡ ለፕሮጀክቱ ዩኒቱ ማናጀሩ ያቀርባል፡፡
አስታየቶችን እና መረጃዎችን ያቀብላል፡፡
ምክረሀሳቦችን
ይሰጣል፡፡
የመዘግየት ጉዳት ካሣ
(Liquidated
Damage) በውሉ መሠረት ለኢ.መ.አ በውሉ መሠረት ለኢ.መ.አ
ማስጠንቀቂያ መስጠት የሚገባው የመዘግየት ጉዳት ካሣ የሚገባውን የመዘግየት ጉዳት
ወይም ተግባራዊ (Liquidated Damage) ላይ - ካሣ (Liquidated damage) - - - -
ማድረግ (Notice to ለዋናው ዳይሬክተር የውሣኔ ገምግሞ ለም/ዋ/ዳይሬክተር
/Order to recover ሐሣብ ማቅረብ፡፡ አስተያየት ማቅረብ፡፡
Delay/Liquidated
damages)

16 | ገ ፅ
የስልጣን ውክልና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊዎች
ፕሮጀክት የአካባቢ ፣
የአካባቢ ፣ ማህበራዊ
የስልጣን ውክልና ማኔጅመንት ቢሮ ማህበራዊ እና
የተሰጠበት ጉዳይ ሪጅናል ፕሮግራም ማናጀር እና እና የሥራ ላይ
የኮንስትክሽን ፕሮጀክቶች የአማካሪ ፑል ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮጀክት ማኔጅመንት የወሰን ማስከበር፣ የሥራ ላይ ደህንነት
የልዩ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት ደህንነት
ማኔጅመንት ም/ዋና ዳይሬክተር ቺፍ/ዋና ኢንጅነር ቢሮ ፕሮጀክት ማናጀር ዩኒት ቡድን መሪ አስተዳደርና ዳይሬክቶሬት ስር
ማናጀር ዳይሬክቶሬት
ፋይናንስ ቡድን የሚገኙ ቡድን
ዳይሬክተር
መሪዎች መሪዎች
1. ቅድመ ክፍያ ዋስትና፤
የተያዥ ገንዘብ ዋስትና፣ ስራ
1. ቅድመ ክፍያ ዋስትና፤
ተቋራጮች ስጋት ዋስትና
የተያዥ ገንዘብ ዋስትና፣ ስራ
(Performance Bond,
ተቋራጮች ስጋት ዋስትና
Advance Guarantee,
(Performance Bond,
Retention Guarantee፣
Advance Guarantee,
CAR Policy)) እና ሌሎች
Retention Guarantee፣
የኢንሹራንስ እና ተያያዝ
CAR Policy) እና ሌሎች
ዶክመንቶችን በገምገም
የቅድመ ክፍያ የኢንሹራንስ እና ተያያዝ
ለፕሮግራም ማናጀሩ
ዋስትና፤ የተያዥ መያዣዎችን ገምግሞ
ያቀርባል፡፡
ገንዘብ ዋስትና፣ ስራ ዶክመንቶቹን በአግባቡ
ተቋራጮች ስጋት በኢ.መ.አ እጅ የሚገኙ ለሚያስቀምጠው አካል
2. በኢ.መ.አ እጅ የሚገኙ
ዋስትና ዋስትናዎች ቀነ ገደባቸው ማስተላለፍ፡፡
ዋስትናዎች ቀነ ገደባቸው
(Performance እንዳያልፉ እንዲታደሱ፣ ሊያልፉ
እንዳያልፉ እንዲታደሱ፣
Bond, Advance ያሉትንም ከሌሎች የአፈፃፀም 2. በኢ.መ.አ እጅ የሚገኙ
- - ሊያልፉ ያሉትንም ከሌሎች - - -
Guarantee, መጓደል ጋር ተያይዞ በሚወሰዱ ዋስትናዎች ቀነ ገደባቸው
የአፈፃፀም መጓደል ጋር
Retention እርመጃዎች ጋር ተያይዞ እንዳያልፉ እንዲታደሱ፣
ተያይዞ ከሚወሰዱ
Guarantee፣ CAR ዋስትናው ለኢ.መ.አ ተገቢውን ሊያልፉ ያሉትንም ከሌሎች
እርመጃዎች ጋር ተያይዞ
Policy) እና ሌሎች ክፍያ እንዲፈፅም ደብደዳቤውን የአፈፃፀም መጓደል ጋር ተያይዞ
ዋስትናው ለኢ.መ.አ
የኢንሹራንስ እና ያፀድቃል፡፡ በሚወሰዱ እርመጃዎች ጋር
ተገቢውን ክፍያ እንዲፈፅም
ተያያዝ መያዣዎችን ተያይዞ ዋስትናው ለኢ.መ.አ
ለማድረግ በመከታተል
ማፅደቅ ተገቢውን ክፍያ እንዲፈፅም
ለፕሮግራም ማናጀሩ
ለማድረግ በመከታተል
ያቀርባል፡፡
ለም/ዋና ዳይሬክተሮ ያቀርባል፡

3. የዋስትና ዶክመንቶች
የውል ጊዚያቸው
3.የዋስትና ዶክመንቶች የውል
ከመጠናቀቁ በፊት
ጊዚያቸው ከመጠናቀቁ በፊት
የማራዘሚያ ጥያቄ
የማራዘሚያ ጥያቄ ያቀርባል
በፕሮግራም ማናጀሩ በኩል
ያቀርባል፡፡

17 | ገ ፅ
የስልጣን ውክልና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊዎች
ፕሮጀክት የአካባቢ ፣
የአካባቢ ፣ ማህበራዊ
የስልጣን ውክልና ማኔጅመንት ቢሮ ማህበራዊ እና
የተሰጠበት ጉዳይ ሪጅናል ፕሮግራም ማናጀር እና እና የሥራ ላይ
የኮንስትክሽን ፕሮጀክቶች የአማካሪ ፑል ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮጀክት ማኔጅመንት የወሰን ማስከበር፣ የሥራ ላይ ደህንነት
የልዩ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት ደህንነት
ማኔጅመንት ም/ዋና ዳይሬክተር ቺፍ/ዋና ኢንጅነር ቢሮ ፕሮጀክት ማናጀር ዩኒት ቡድን መሪ አስተዳደርና ዳይሬክቶሬት ስር
ማናጀር ዳይሬክቶሬት
ፋይናንስ ቡድን የሚገኙ ቡድን
ዳይሬክተር
መሪዎች መሪዎች
ከአካባቢያዊ፣
1. ከአካባቢያዊ፣ ማህበራዊ እና
ማህበራዊ እና ደህንነት ጉደዮች
ድህንነት ጉደዮች ጋር ጋር በተያያዙ
በተያያዙ የሚሰጡ የሚሰጡ ሥራዎችን
ሥራዎችን እና የ እና የ ከሥራ
ከሥራ ተቋራጮች ተቋራጮች
ከሥራ ተቋራጮች ለንዑስ ሥራ ሚሰጣቸውን ንዑስ ሚሰጣቸውን ንዑስ
ተቋራጮች (sub-contractors) ከሥራ ተቋራጮች ለንዑስ ሥራ ተቋራጮች ሥራ ተቋራጮች
ከሥራ ተቋራጮች ለንዑስ
በሥራ ተቋራጮች የሚሰጡ ሥራዎች በኮንትራት ሥራ ተቋራጮች (sub- (sub-contractors) (sub-
ሥራ ተቋራጮች (sub-
ለንዑስ ሥራ ውሉ መሠረት የኢመአን contractors) የሚሰጡ በኮንትራት ውሉ፣ contractors)
- contractors) የሚሰጡ - -
ተቋራጮች የሚሰጥ ይሁንታ ብቻ የሚጠይቀውን ሥራዎች ገምግሞ ሌሎች አለም አቀፋዊ በኮንትራት ውሉ፣
ሥራዎች ገምግሞ ለምክትል
የሥራ መጠን ማጽደቅ (Needs only ERA Consent ለፕሮግራም ማናጀር እና ሀገር አቀፍ ሌሎች አለም
ዋና ዳይሬከተሩ ያቀርባል፡፡
not Approval) ገምግሞ ያቀርባል፡፡ ድንጋጌዎች መሰረት አቀፋዊ እና ሀገር
ይሁንታ ይሰጣል፡፡ ገምግሞ ለፕሮግራም አቀፍ ድንጋጌዎች
ማናጀሩ ያቀርባል፡፡ መሰረት ገምግሞ
2. የSTD & የአካባቢ ፣
HIV/AIDS ንዑስ ማህበራዊ እና
ሥራ ተቋራጮች የሥራ ላይ ደህንነት
(sub-contractors) ዳይሬክቶሬት
ያፀድቃል፡፡ ዳይሬክተሩ
ያቀርባል፡፡
ለፌደራል ሚንስትር ቢሮዎች፣ ከዞን እና ከክልል ወረዳ እና የቀበሌ
ከባለድረሻ አካላት፣ የተወካዮች ምክር ቤት እና መስተዳድሮች ጋር የሚደረጉ መስተዳድሮች ጋር
ሌሎች ቢሮዎች እና ሌሎች የበላይ መስሪያቤቶች ጋር ደብዳቤዎችን የሚያፀድቅ የሚደረጉ ከወሰን
ወረዳ እና የቀበሌ
መስተዳድሮች ጋር የሚደረጉ ልውውጦችን መርምሮ ይሆናል፡፡ ማስከበር ጉዳዮች
መስተዳድሮች ጋር
በግንባታ ፕሮጀክቶች ለዋና ዳይሬክተሩ የሚያቀርብ - lክልል መስተዳድሮችና ከክልል - ጋር በተያያዘ - -
የሚደረጉ ደብዳቤዎችን
ዙሪያ የሚደረጉ ይሆናል፡፡ለፌድራል አና ቢሮዎች የሚመጡ ጉዳዮች የደብዳቤ
የሚያፀድቅ ይሆናል፡፡
የደብዳቤ ኮንሰትራክሽን ቢሮዎች፣ lክልል ገምግሞ ምላሽ አንዲሰጥበት ልውውጦችን
ልውውጦች፡፡ መስተዳድሮችና ልክልል ቢሮዎች ለምክትል ዋና ዳይሬከተሩ የሚያደርግ
ምላሽ ይሰጣል፡፡ ያቀርባል፡፡ ይሆናል፡፡

18 | ገ ፅ
የስልጣን ውክልና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊዎች
ፕሮጀክት የአካባቢ ፣
የአካባቢ ፣ ማህበራዊ
የስልጣን ውክልና ማኔጅመንት ቢሮ ማህበራዊ እና
የተሰጠበት ጉዳይ ሪጅናል ፕሮግራም ማናጀር እና እና የሥራ ላይ
የኮንስትክሽን ፕሮጀክቶች የአማካሪ ፑል ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮጀክት ማኔጅመንት የወሰን ማስከበር፣ የሥራ ላይ ደህንነት
የልዩ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት ደህንነት
ማኔጅመንት ም/ዋና ዳይሬክተር ቺፍ/ዋና ኢንጅነር ቢሮ ፕሮጀክት ማናጀር ዩኒት ቡድን መሪ አስተዳደርና ዳይሬክቶሬት ስር
ማናጀር ዳይሬክቶሬት
ፋይናንስ ቡድን የሚገኙ ቡድን
ዳይሬክተር
መሪዎች መሪዎች
በግንባታ ፕሮጀክቶች
ትግበራ ወቅት የጥራት
ማኔጀመነትን
በተመለከተ ከጥራት
ክትትል እና ግምገማ
ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ
የጥራት መጓደል
በግንባታ ፕሮጀክቶች ሲያጋጥም ለአማካሪ
በጥራት መጓደል ሳቢያ አማካሪ
ትግበራ ወቅት የጥራት በጥራት መጓደል ሳቢያ አማካሪ መሀንዲሱ በግንባታም
ድርጅቶች እና ስራ ተቋራጮች
ማኔጀመነትን ድርጅቶች እና ስራ ተቋራጮች ሆነ በክትትል ላይ
ላይ እንደድርጅት እርምጃ
በተመለከተ ከጥራት ላይ እንደድርጅት እርምጃ - የእርምት እርምጃ - - - -
እንዲወሰድ ሲታመንበት
ክትትል እና ግምገማ እንዲወሰድ ሲታመንበት ዋና እንዲወሰድ ትዕዛዝ
ለም/ዋና ዳይሬክተሩ ያቀርባል፡
ጋር ተያያዥ የሆኑ ዳይሬክተሩ ያቀርባል፡፡ ይሰጣል፡፡ ከዚህ

ጉዳዮችን ይመለከታል በተጨማሪም በጥራት
መጓደል ሳቢያ አማካሪ
ድርጅቶች እና ስራ
ተቋራጮች ላይ
እንደድርጅት እርምጃ
እንዲወሰድ
ሲታመንበት ለፕግራም
ማናጀሩ ያቀርባል፡፡
የአማካሪ መሀንዲስ ተጠሪ 1. የአማካሪ መሀንዲስ
በስራ ግድፈቶች ወቅት በተገባው
መሀንዲስ (Resident ተጠሪ መሀንዲስ
የአማካሪ መሀንዲስ ውል መሰረት የአማካሪ
Engineer)፣ ምክትል ተጠሪ (Resident
እና የስራ ተቋራጭ መሀንዲስ ተጠሪ መሀንዲስ
መሀንዲስ (Assistant Engineer)፣ ምክትል
ሰራተኞች CV ማፅደቅ (Resident Engineer) ከስራው
Resident Engineer) እና ተጠሪ መሀንዲስ
የዲስፕሊን እና ማሰናበት እና የስራ ተቋራጭ - - - - -
የስራ ተቋራጭ ፕሮጀክት (Assistant Resident
የአፈፃፀም ችግር ፕሮጀክት ማናጀር (Project
ማናጀር (Project Manager) Engineer) እና የስራ
ያለባቸውንም Manager) በተመሳሳይ ከሰራው
ቦታዎች የሚቀርቡ ሰራተኞችን ተቋራጭ ፕሮጀክት
ከስራቸው ማንሳት እንዲሰናበት የትዕዛዝ ደብዳቤ
ማፅደቅ የዲስፕሊን እና ማናጀር (Project
ለአማካሪ መሀንዲሱ ይሰጣል
የአፈፃፀም ችግር ያለባቸውንም Manager) ቦታዎች

19 | ገ ፅ
የስልጣን ውክልና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊዎች
ፕሮጀክት የአካባቢ ፣
የአካባቢ ፣ ማህበራዊ
የስልጣን ውክልና ማኔጅመንት ቢሮ ማህበራዊ እና
የተሰጠበት ጉዳይ ሪጅናል ፕሮግራም ማናጀር እና እና የሥራ ላይ
የኮንስትክሽን ፕሮጀክቶች የአማካሪ ፑል ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮጀክት ማኔጅመንት የወሰን ማስከበር፣ የሥራ ላይ ደህንነት
የልዩ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት ደህንነት
ማኔጅመንት ም/ዋና ዳይሬክተር ቺፍ/ዋና ኢንጅነር ቢሮ ፕሮጀክት ማናጀር ዩኒት ቡድን መሪ አስተዳደርና ዳይሬክቶሬት ስር
ማናጀር ዳይሬክቶሬት
ፋይናንስ ቡድን የሚገኙ ቡድን
ዳይሬክተር
መሪዎች መሪዎች
ከስራቸው ለማንሳት መርምሮ የሚቀርቡ ሰራተኞች
ለም/ዋና ዳይሬክተር CV ገምግሞ ለፕሮግም
ማስተላለፍ ማናጀር ማቅረብ
እንዲሁም የዲስፕሊን
እና የአፈፃፀም ችግር
ያለባቸውንም ገምግሞ
ማቅረብ

2. የአማካሪ መሀንዲስ
ተጠሪ መሀንዲስ
(Resident
Engineer)፣ ምክትል
ተጠሪ መሀንዲስ
(Assistant Resident
Engineer) እና የስራ
ተቋራጭ ፕሮጀክት
ማናጀር (Project
Manager) ውጪ ላሉ
የስራ ቦታዎች
የሚቀርቡ ሰራተኞች
CV ገምግሞ ማፅደቅ
እንዲሁም የዲስፕሊን
እና የአፈፃፀም ችግር
ያለባቸውንም
ከስራቸው ማንሳት ፡፡
ደካማ አፈፃፀም 1. ደካማ አፈፃፀም
የስራ ተቋራጮች እና ደካማ አፈፃፀም የተስተዋለበቸው
የተስተዋለበቸው ስራ የተስተዋለበቸው ስራ
አማካሪ መሀንዲሶች ስራ ተቋራጮች እና አማካሪ
ተቋራጮች እና አማካሪ ተቋራጮች እና አማካሪ
አፈፃፀምን በመገምገም ድርጅቶች ተገምግመው
- ድርጅቶች በመገምገም ለቀጣይ ድርጅቶች ተገምግመው - - - -
ደካማ አፈፃፀሞችን የፕሮጀክት ውል ማቋረጥ
እርምጃ ለምክትል ዋና እንደየሁኔታው ታይቶ
ተከትሎ የሚሰጡ የተወሰነባቸው ከሆኑ ለዋናው
ዳይሬክተሩ የሚያቀርብ የፕሮጀክት
ማስጠንቀቂያዎች እና ዳይሬክተር ያቀርባል፡፡
ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የስራ ማስጠንቀቂያ

20 | ገ ፅ
የስልጣን ውክልና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊዎች
ፕሮጀክት የአካባቢ ፣
የአካባቢ ፣ ማህበራዊ
የስልጣን ውክልና ማኔጅመንት ቢሮ ማህበራዊ እና
የተሰጠበት ጉዳይ ሪጅናል ፕሮግራም ማናጀር እና እና የሥራ ላይ
የኮንስትክሽን ፕሮጀክቶች የአማካሪ ፑል ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮጀክት ማኔጅመንት የወሰን ማስከበር፣ የሥራ ላይ ደህንነት
የልዩ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት ደህንነት
ማኔጅመንት ም/ዋና ዳይሬክተር ቺፍ/ዋና ኢንጅነር ቢሮ ፕሮጀክት ማናጀር ዩኒት ቡድን መሪ አስተዳደርና ዳይሬክቶሬት ስር
ማናጀር ዳይሬክቶሬት
ፋይናንስ ቡድን የሚገኙ ቡድን
ዳይሬክተር
መሪዎች መሪዎች
ውል ማቋረጥ አፈፃፀማቸው ተገምግሞ (Dissatsfaction)
ትዕዛዞችን መስጠት ለውጥ ላላመጡ ፕሮጀክቶች የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ውል የማቋረጥ ማስጠንቀቂያ
ይሰጣል፡፡ 2. ደካማ አፈፃፀም
የተስተዋለበቸው ስራ
ተቋራጮች እና አማካሪ
ድርጅቶች በመገምገም
ቀጣይ ለቅጣት እርምጃ
ሀሳብ ለፕግራም
ማናጀሩ የሚያቀርብ
ይሆናል፡፡
በጸድቀው ዲዛይን
መሰረት የወሰን
የመንገድ ወሰን
የመንገድ ወሰን ማስከበር ጥያቄዎች
ማስከበር ክፍያ
ማስከበር ካሳ ክፍያ የመንገድ ወሰን ማስከበር በአማካሪ መሃንዲሱ
ገምግሞ
ማስተላለፍ (ROW -- - ክፍያ አረጋግጦ ለክፍያ በኩል እንዲቀርቡ - - -
ለፕሮግራም
compensation ማስተላለፍ፡፡ በማድርግ ያነሳሳል
ማናጀሩ
payment) ወደቅጣዩ
ያስተላልፋል፡፡
የሚመለከተው ክፍል
ያስተላልፋል፡፡
1. ለስራ ተቋራጭ እና 1. ለስራ ተቋራጭ እና 1. ለስራ ተቋራጭ እና
1. ለስራ ተቋራጭ እና
ለአማካሪ ድርጅት ሰራተኞች ለአማካሪ ድርጅት ለአማካሪ ድርጅት
ለአማካሪ ድርጅት
የቪዛ(VISA) የስራ ሰራተኞች የቪዛ(VISA) ሰራተኞች የቪዛ(VISA)
ሰራተኞች
ፍቃድ(Work Permit)፣ የስራ ፍቃድ(Work የስራ ፍቃድ(Work
የቪዛ(VISA) የስራ
የመኖሪያ ፈቃድ (Residence Permit)፣ የመኖሪያ Permit)፣ የመኖሪያ ፈቃድ
ፍቃድ(Work
- - ID) እና ሌሎች ተያያዥ ፈቃድ (Residence (Residence ID) እና - - -
Permit)፣ የመኖሪያ
ጉዳዮች ተመርምሮ በፕሮጀክት ID) እና ሌሎች ተያያዥ ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች
ፈቃድ (Residence
ዩኒቱ የቀረቡለትን ማፅደቅ፡፡ ጉዳዮች ጥያቄ በውሉ መሰረት
ID) እና ሌሎች
የቀረበባቸው ሰራተኞች መቅረባቸውን መመርመር
ተያያዥ ጉዳዮች
2. ለግንባታ እና በውል የመስክ ስራ ላይ እንዲሁም የሰራተኞቹን
ለሚለከተው አካል
መሰርት ለሚስተናገዱ ሌሎች በቀጥታ ተሰታፊ አስፈላጊነት እነደአስፈላጊነቱ

21 | ገ ፅ
የስልጣን ውክልና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊዎች
ፕሮጀክት የአካባቢ ፣
የአካባቢ ፣ ማህበራዊ
የስልጣን ውክልና ማኔጅመንት ቢሮ ማህበራዊ እና
የተሰጠበት ጉዳይ ሪጅናል ፕሮግራም ማናጀር እና እና የሥራ ላይ
የኮንስትክሽን ፕሮጀክቶች የአማካሪ ፑል ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮጀክት ማኔጅመንት የወሰን ማስከበር፣ የሥራ ላይ ደህንነት
የልዩ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት ደህንነት
ማኔጅመንት ም/ዋና ዳይሬክተር ቺፍ/ዋና ኢንጅነር ቢሮ ፕሮጀክት ማናጀር ዩኒት ቡድን መሪ አስተዳደርና ዳይሬክቶሬት ስር
ማናጀር ዳይሬክቶሬት
ፋይናንስ ቡድን የሚገኙ ቡድን
ዳይሬክተር
መሪዎች መሪዎች
በማሳወቅ ትብብር ጉዳዩች ከውጪ ሀገራት ገቢ የሚሆኑት ላይ ከፕሮጀክት ማናጀሩ ጋር
ማድረግ የሚደረጉ ግብዓት እና ለፕሮጀክት ዩኒቱ ሀሳብ በመወያየት ለፕግራም
ንብረቶች (Importation ማቅረብ፡፡ ማናጀሩ ያቀርባል፡፡
2. ለግንባታ እና Order) በፕሮጀክት ዩኒቱ
በውል መሰርት ተመርምሮ የቀረቡለትን 2. ለግንባታ እና በውል 2. ለግንባታ እና በውል
ለሚስተናገዱ ሌሎች ማፅደቅ፡፡ መሰርት ለሚስተናገዱ መሰርት ለሚስተናገዱ
ጉዳዩች ከውጪ ሌሎች ጉዳዩች ከውጪ ሌሎች ጉዳዩች ከውጪ
ሀገራት ገቢ የሚደረጉ ሀገራት ገቢ የሚደረጉ ሀገራት ገቢ የሚደረጉ
ግብዓት እና ንብረቶች ግብዓት እና ንብረቶች ግብዓት እና ንብረቶች
(Importation (Importation Order) (Importation Order)
Order) የትብብር የመስክ ስራ ላይ በውሉ መሰረት
ጥያቄዎችን ማፅደቅ በቀጥታ ግንኙነት መቅረባቸውን መመርመር
እና ለሚመለከተው የሚሆኑት ላይ እንዲሁም የሰራተኞቹን
አካል ተገቢው ህጋዊ ለፕሮጀክት ዩኒቱ ሀሳብ አስፈላጊነት እነደአስፈላጊነቱ
ትብብር እንዲደረግ ማቅረብ፡፡ ከፕሮጀክት ማናጀሩ ጋር
ማሳወቅ በመወያየት ለፕግራም
ማናጀሩ ያቀርባል፡፡
1. በም/ዋ/ዳይሬክተሩ ሥር 1. የክፍያ ጥያቄ 1. የአካባቢ ጥበቃ፣፣ 1. የክፍያ ጥያቄ
1. የግንባታ ፕሮጀክቶች እና
በሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች በማስመልከት ከአማካሪ ማህበራዊ በማስመልከት
ለግንባታ ፕሮጀክቶችና የማማከር አገልግሎት
የሚተዳደሩ የግንባታ ድርጅቶች የሚፈለጉ አገልግሎት፣ የሥራ ከአማካሪ ድርጅቶች
ለምህንድስና የምክር ድርጅቶች የሥራ አፈፃፀም
ፕሮጀክቶች እና የማማከር ተጨማሪ መረጃዎች/ ቦታ ጤናና ደህንነትን የሚፈለጉ ተጨማሪ
አገልግሎት ክፍያ (Invoice & IPC)
አገልግሎቶችን በየወሩ ሪፖርት ማብራሪያዎች ማግኘት አስመልክቶ ለሚሰሩ መረጃዎች/
ኮንትራቶች (Works እንዲሁም ሌሎች የፕሮጀክቶች ዝርዘር
አዘጋጅቶ ለበላይ አመራሩ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የማማከር ማብራሪያዎች
& Engineering የባለሙያዎች (Experts) እና አፈፃፀም በየወሩ
(Executive council) ሪፖርት ደብዳቤ መፃፃፍ፡፡ አገልግሎት ማግኘት አስፈላጊ
Consultancy የቅድመ ክፍያ ጥያቄ ሲያቀርቡ ከአጠቃላይ የስራ አፈጻጸም
ያቀርባል፡፡ - - ድርጅቶች የሥራ ሆኖ ሲገኝ ደብዳቤ
Service) የሚቀርቡ አረጋግጦና አፅድቆ ለፋይናንስ ሪፖርት በሪጅን ደረጃ
2. የአማካሪ ድርጅቶች አፈፃፀም ክፍያ መፃፃፍ፡፡
ክፍያ ጥያቄዎች (IPC) ለክፍያ ያስተላልፋል፡፡ አጠናቅሮ ለፕሮግራም
2. በአማካሪ መሐንዲሱ የክፍያ ክፍያ (Invoice) የስራ (IPC) እንዲሁም
እንዲሁም ሌሎች ማናጀሩ ማቅረብ፡፡
መጠየቂያ ተዘጋጅቶ ሲቀርብ ተቋራጮች ክፍያ ሌሎች የባለሙያዎች 2. የአካባቢ ጥበቃ፣
የባለሙያዎች 2. ዝርዘር አፈጻጸሙን በየወሩ
የስራ ተቋራጭ “Statement at (IPC) ክፍያ እንዲሁም (Experts) እና ፣ ማህበራዊ
(Experts) ላይ ከአጠቃላይ የስራ አፈጻጸም
completion“ እና የመጨረሻ ሌሎች የባለሙያዎች የቅድመ ክፍያ ጥያቄ አገልግሎት፣ የሥራ
ስለመወሰን ሪፖርት ጋር ለም/ዋ/ዳ
ክፍያ (Final Payment) ጥያቄ (Experts) ማመልከቻ ሲያቀርቡ አረጋግጦና ቦታ ጤናና
ዳይሬክተሩ ማቅረብ፡፡
ውሉን በሚያስተዳድረው በውል አግባብ አፅድቆ ለክፍያ ደህንነትን

22 | ገ ፅ
የስልጣን ውክልና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊዎች
ፕሮጀክት የአካባቢ ፣
የአካባቢ ፣ ማህበራዊ
የስልጣን ውክልና ማኔጅመንት ቢሮ ማህበራዊ እና
የተሰጠበት ጉዳይ ሪጅናል ፕሮግራም ማናጀር እና እና የሥራ ላይ
የኮንስትክሽን ፕሮጀክቶች የአማካሪ ፑል ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮጀክት ማኔጅመንት የወሰን ማስከበር፣ የሥራ ላይ ደህንነት
የልዩ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት ደህንነት
ማኔጅመንት ም/ዋና ዳይሬክተር ቺፍ/ዋና ኢንጅነር ቢሮ ፕሮጀክት ማናጀር ዩኒት ቡድን መሪ አስተዳደርና ዳይሬክቶሬት ስር
ማናጀር ዳይሬክቶሬት
ፋይናንስ ቡድን የሚገኙ ቡድን
ዳይሬክተር
መሪዎች መሪዎች
ፕሮግራም ማናጀር ታይቶና ተዘጋጅቶ ሲቀርብ ያስተላልፋል፡፡ አስመልክቶ
አስፈላጊው ሁሉ መሟላቱ በማረጋገጥ ለፕሮግራም ለሚሰሩ የማማከር
ተረጋግጦ ሲቀርብ በማጽደቅ ማናጀሩ ማስተላለፍ፡፡ 2. ዝርዝር አገልግሎት
ለፋይናንስ ለክፍያ ማስተላለፍ፡፡ አፈጻጸሙን በየወሩ ድርጅቶች የሥራ
3. የፕሮጀክቶች ዝርዘር ከአጠቃላይ የስራ አፈፃፀም ክፍያ
አፈፃፀም በየወሩ አፈጻጸም ሪፖርት (IPC) እንዲሁም
ከአጠቃላይ የስራ ጋር ለም/ዋ/ዳ ሌሎች
አፈጻጸም ሪፖርት ጋር ዳይሬክተሩ ማቅረብ፡ የባለሙያዎች
ፕሮግራም ማናጀሩ ፡ (Experts) እና
ማቅረብ፡፡ የቅድመ ክፍያ ጥያቄ
በማረጋገጥ
ለዳይሬክተር
ማስተላለፍ፡፡
የስራ ተቋራጮችና የስራ ተቋራጮችና የምክር
የስራ ተቋራጮችና የምክር የምክር አገልግሎት አገልግሎት ሰጭ /ስራ
በERAMS ሪፖረቶች ውጤት አገልግሎት ሰጭ /ስራ አማካሪ/ ሰጭ /ስራ አማካሪ/ አማካሪ/ ድርጅቶችን
የፕሮጀክት አፈፃፀም
መሰረት ውሳኔዎችን ማሳለፍ ድርጅቶችን አፈፃፀም ድርጅቶችን አፈፃፀም አፈፃፀም ለመለካት
ግምገማ መረጃዎችን - - - -
አስፈላጊ የሆኑትንም ወደ ዋናው ለመለካት የሚያግዝ መረጃ ለመለካት የሚያግዝ የሚያግዝ መረጃ /data for
ማስተላለፍ
ዳይሬክተር ማስተላለፍ፡፡ /data for performance መረጃ /data for performance rating/
rating/ OPR ማፅደቅ:: performance rating/ ትክክለኛነቱን አረጋግጦ
Monitoring ማፅደቅ:: ERAMS ላይ ማስገባት፡፡
የአማካሪው ድርጅትና
የፕሮጀክቶች ሥራ የአማካሪው ድርጅትና የፕሮጀክት ግንባታ ውል የፕሮጀክቶች ሥራ ወይም
ወይም የምክር የፕሮጀክት ግንባታ ውል ከተቋረጠ በኋላ ምትክ የምክር አገልግሎት ግዢ
አገልግሎት ግዢ ከተቋረጠ በኋላ በምትኩ አማካሪ ወይም የሥራ የኮንትራት ውል ሲቋረጥ
የኮንትራት ውል አማካሪ ወይም የሥራ ተቋራጭ ተቋራጭ ግዥ እንዲከናወን በምትኩ የግዢ ጥያቄ
ሲቋረጥ በምትኩ ግዥ እንዲከናወን ገምግሞ አስፈላጊ መረጃዎችን ሰብስቦና እንዲቀርብ ለፕሮግራም
የግዢ ጥያቄ ማቅረብ ለዋናው ዳይሬክተር ማቅረብ፡፡ ገምግሞ ለም/ዋ ዳይሬክተር ማናጀሩ ማቅረብ
ማቅረብ፡፡

23 | ገ ፅ
የስልጣን ውክልና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊዎች
ፕሮጀክት የአካባቢ ፣
የአካባቢ ፣ ማህበራዊ
የስልጣን ውክልና ማኔጅመንት ቢሮ ማህበራዊ እና
የተሰጠበት ጉዳይ ሪጅናል ፕሮግራም ማናጀር እና እና የሥራ ላይ
የኮንስትክሽን ፕሮጀክቶች የአማካሪ ፑል ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮጀክት ማኔጅመንት የወሰን ማስከበር፣ የሥራ ላይ ደህንነት
የልዩ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት ደህንነት
ማኔጅመንት ም/ዋና ዳይሬክተር ቺፍ/ዋና ኢንጅነር ቢሮ ፕሮጀክት ማናጀር ዩኒት ቡድን መሪ አስተዳደርና ዳይሬክቶሬት ስር
ማናጀር ዳይሬክቶሬት
ፋይናንስ ቡድን የሚገኙ ቡድን
ዳይሬክተር
መሪዎች መሪዎች
1. በመንገድ 1. ስትራክቸር እና
መስመር (Route ኮምኘሊሽን ሪፖርቶችን
Selection) በመገምገም ማፅደቅ፡፡
መረጣን
መመርመር፣ 2. የስራ ተቋራጩንና
ምክረሀሳብ እና የአማካሪ መሐንዲሱን
አስተያየት የሞብላይዘሽን ዕቅድ
1. በዲዛይን ክለሳ እና በመንገድ
መስጠት በመገምገም አስተያየት
1. በመንገድ መስመር (Route መስመር (Route Selection)
በጽሑፍ ለአማካሪ በፕሮጀክቶች ውል
Selection) መረጣ ላይ መረጣ ላይ አስተያየት
2. በዲዛይን ክለሳ መሐንዲሱ መስጠት፡፡ መሰረት የሚጠበቁ
አስተያየት መስጠት እና ለዋና መስጠት እና ለም/ዋና
ላይ አስተያየት እና ከአካባቢያዊ፣
ዳይሬክተር እንዲፀድቅ ዳይሬክተር ማስተላለፍ፡፡
ምከረሀሳብ 3.የግንባታ ፕሮጀክቶች ማህበራዊ እና የስራ
ማስተላለፍ፡፡
መስጠት የጥራት መከታተያ እና ላይ ደህንነት ጋር
2. የዲዛይን እና ግንባታ
መቆጣጠሪያ ማኑዋል፣ ተያያዥ ዶክመንችን
2. በዲዛይን ክለሳ ላይ አስተያየት ፕሮጀክቶች ላይ የሚገቡ
3. የዲዛይን እና የስራ ተቋራጩን የስራ እንደ ESIA,
ሪፖርቶችን መስጠት እና ማፅደቅ ጂኦሜትሪክ ዲዛይን
ግንባታ ዕቅድ እና የትራፊክ SSEMP, ESMP
መገምገምና አስተያየት ዶክመንቶችን መገምገም እና
ፕሮጀክቶች ላይ ፍሰት መቆጣጠሪያ እንዲሁም ልሌችን
መስጠት/ ማፅደቅ 3. የዲዛይን እና ግንባታ በም/ዋና ዳይሬክተር
የሚገቡ ዕቅድ በመገምገም መገምገም እና
ፕሮጀክቶች ላይ የሚገቡ እንዲፀድቅ ማስተላለፍ፡፡
ጂኦሜትሪክ አስተያየት በጽሑፍ አስተያየት
ጂኦሜትሪክ ዲዛይን ዶክመንቶች
ዲዛይን ለአማካሪ መሐንዲሱ በመስጠት
መገምገም ማፅደቅ፡፡ 3. የልዩ ፕሮጀክቶች በተለየ
ዶክመንቶች ላይ መስጠት፡፡ ፕሮጀክቱ
ሁኔታ ላይ በውሉ መሰረት
ምከረሀሳብ እና ለሚገኝበት
4. የልዩ ፕሮጀክቶች ላይ በውሉ መፅደቅ የሚገባቸውን የዲዛይን
አስተያየት 4. በዲዛይን ክለሳ እና ፕሮግራም ማናጀር
መሰረት መፅደቅ የሚገባቸውን ስራዎች በዝርዝር በመገምገም
መስጠት በመንገድ መስመር መላክ፡፡
የዲዛይን ስራዎች ማፅደቅ ለም/ዋና ዳይሬክተር
(Route Selection)
ማስተላለፍ፡፡
3. የልዩ መረጣ ላይ አስተያየት
ፕሮጀክቶች ላይ መስጠት፡፡
በልዩነት በውሉ
መሰረት መፅደቅ 5. እነዳንድ የዲዛይን
የሚገባቸውን እና ግንባታ ፕሮጀክቶች
የዲዛይን ስራዎች ላይ የሚገቡ
በዝርዝር ጂኦሜትሪክ ዲዛይን

24 | ገ ፅ
የስልጣን ውክልና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊዎች
ፕሮጀክት የአካባቢ ፣
የአካባቢ ፣ ማህበራዊ
የስልጣን ውክልና ማኔጅመንት ቢሮ ማህበራዊ እና
የተሰጠበት ጉዳይ ሪጅናል ፕሮግራም ማናጀር እና እና የሥራ ላይ
የኮንስትክሽን ፕሮጀክቶች የአማካሪ ፑል ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮጀክት ማኔጅመንት የወሰን ማስከበር፣ የሥራ ላይ ደህንነት
የልዩ ፕሮጀክቶች ፕሮጀክት ደህንነት
ማኔጅመንት ም/ዋና ዳይሬክተር ቺፍ/ዋና ኢንጅነር ቢሮ ፕሮጀክት ማናጀር ዩኒት ቡድን መሪ አስተዳደርና ዳይሬክቶሬት ስር
ማናጀር ዳይሬክቶሬት
ፋይናንስ ቡድን የሚገኙ ቡድን
ዳይሬክተር
መሪዎች መሪዎች
በመገምገም ምክረ መገምገም እና
ሀሳብ መስጠት ለፕሮግራም ማናጀር
ማስተላለፍ፡፡

6. ዲዛይን እና ግንባታ
ፕሮጀክች (DB
Projects) ላይ
የተቋራጮች
Payement Schedule
ላይ አስተያየት መስጠት
እና ማፅደቅ፡፡

7. የአማካሪ
መሐንዲሱን inception
report በመገምገም
አስተያየት በጽሑፍ
ለአማካሪ መሐንድሱ
መስጠት፡፡
ያለቁ የመንገድ ግንባታ በኮንትራት ውሉና በዲዛይን
የጋራ ምርመራዎችን
ፕሮጀክቶች በፕሮጀክት ርክክብ ስታንዳርዱ መሰረት የመንገድ
ማስተባበር፣ ማካሄድ
የግንባታ ሥራዎች ማንዋል (project handover ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን
እና የድጋፍ ሀሳቦችን
ርክክብ guidelines) መሰረት መሆኑን በማረጋገጥ ለርክክብ ዝግጁ
ለፕሮግራም ማነጀሩ
አረጋግጦ እና ደግፎ እንዲፀድቅ በማድረግ ለም/ዋ/ዳይሬክተር
ማቅረብ፡፡
ለዋናው ዳይሬክተር ማቅረብ፡፡ ማቅረብ፡፡

25 | ገ ፅ
የስልጣን ውክልና ፕሮጀክት ማኔጅመንት የአካባቢ ፣ ማህበራዊ እና
የኮንስትክሽን ፕሮጀክቶች ለሪጅናል እና ሜጋ እና ልዩ የአካባቢ ፣ ማህበራዊ እና
ፕሮጀክት ማኔጅመንት ቢሮ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ቢሮ የወሰን ማስከበር፣ የሥራ ላይ ደህንነት
የተሰጠበት ጉዳይ ማኔጅመንት ም/ዋና ፕሮጀክቶች ፕሮግራም የሥራ ላይ ደህንነት
ፕሮጀክት ማናጀር ዩኒት ቡድን መሪ አስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ስር የሚገኙ
ዳይሬክተር ማናጀር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
ቡድን መሪዎች ቡድን መሪዎች

የኢ.መ.አ ህግና ደንቦች ለጣሱ


የኢ.መ.አ ህግና ደንቦች ለጣሱ
እና በአግባቡ የማይተገብሩ የኢ.መ.አ ህግና ደንቦች የኢ.መ.አ ህግና ደንቦች ለጣሱ የኢ.መ.አ ህግና ደንቦች የኢ.መ.አ ህግና ደንቦች የኢ.መ.አ ህግና ደንቦች
እና በአግባቡ የማይተገብሩ
በምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ለጣሱ እና በአግባቡ እና በአግባቡ የማይተገብሩ ለጣሱ እና በአግባቡ ለጣሱ እና በአግባቡ ለጣሱ እና በአግባቡ
በቡድኑ ወይም ሰራተኞችን ማስጠንቀቂያ
ስር ለሚገኙ የፕሮግረማ የማይተገብሩ ሰራተኞችን ሰራተኞችን ማስጠንቀቂያ የማይተገብሩ ሰራተኞችን የማይተገብሩ ሰራተኞችን የማይተገብሩ ሰራተኞችን
በማናጀሩ ስር የሰራተኞች መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ
ማናጀር ሰራተኞች ማስጠንቀቂያ መስጠት መስጠት እንዲሁም እርመጃ ማስጠንቀቂያ መስጠት ማስጠንቀቂያ መስጠት ማስጠንቀቂያ መስጠት
እርምት እርመጃ የአካባቢ ፣ ማህበራዊ እና
ማስጠንቀቂያ መስጠት እንዲሁም እርምጃ መውሰድ መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እርመጃ መውሰድ አስፈላጊ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እንዲሁም እርመጃ መውሰድ
(Dicipilinary የሥራ ላይ ደህንነት
እነዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለሰው ለፕሮግራም ማናጀሩ ሆኖ ሲገኝ ለፕሮግራም ለፕሮግራም ማናጀሩ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለሰው
measures) መውሰድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
ለሰው ሀብት አስተዳደር ሀብት መስተዳደር እርምጃው እርምጃው እንዲወሰድ ማናጀሩ እርምጃው እርምጃው እንዲወሰድ ሀብት አስተዳደር አርምጃው
እርምጃው እንዲወሰድ
እርምጃው እንዲወሰድ እንዲወሰድ ማስተላለፍ፡፡ ማስተላለፍ፡፡ እንዲወሰድ ማስተላለፍ፡፡ ማስተላለፍ፡፡ እንዲወሰድ ማስተላለፍ፡፡
ማስተላለፍ፡፡
ማስተላለፍ፡፡

በኢ.መ.አ ፕሮጀክት ቢሮው


የኢ.መ.አ ሰራተኞች በኢ.መ.አ ፕሮጀክት ቢሮው በኢ.መ.አ ፕሮጀክት ዩኒቱ
እና ፕሮጀክት ዩኒቱ በቢሮው ሰራተኞች ከስራ በቢሮው ሰራተኞች ከስራ በቢሮው ሰራተኞች ከስራ
ከስራ ሰዓት ውጪ ሰራተኞች ከስራ ሰዓት ውጪ ሰራተኞች ከስራ ሰዓት
ሰራተኞች ከስራ ሰዓት ውጪ ሰዓት ውጪ አስከ 60 ሰዓት ውጪ ከ60 ሰዓት ሰዓት ውጪ አስከ 60 ሰዓት
የትርፍ ሰዓት ስራዎችን አስከ 60 ሰዓት ለሚሆን ውጪ አስከ 60 ሰዓት
ከ60 ሰዓት በላይ ለሚሆን ሰዓት ለሚሆን የሚከናወኑ በላይ ለሚሆን የሚከናወኑ ለሚሆን የሚከናወኑ ስራዎች
ማፅደቅ እና ለክፍያ የሚከናወኑ ስራዎች ክፍያ ለሚሆን የሚከናወኑ
የሚከናወኑ ስራዎች ክፍያ ስራዎች ክፍያ ማፅደቅ እና ስራዎች ክፍያ ማፅደቅ እና ክፍያ ማፅደቅ እና ለክፍያ
መምራት (Overtime ማፅደቅ እና ለክፍያ ስራዎች ክፍያ ማፅደቅ እና
ማፅደቅ እና ለክፍያ ለክፍያ መምራት፡፡ ለክፍያ መምራት፡፡ መምራት፡፡
Payment) መምራት፡፡ ለክፍያ መምራት፡፡
መምራት፡፡

በምክትል ዋና ዳይሬክተሩ
የዕቃ ግዢ፣ የሰራተኞች በፕሮግራም ማናጀሩ ስር በፕሮጀክት ማናጀሩ ስር በቡድኑ ስር የዕቃ ግዢ፣ በቡድኑ ስር የዕቃ ግዢ፣ በዳይሬክተሩ ስር የዕቃ
ስር ለሚገኙ ክፍሎች የዕቃ በቡድኑ የዕቃ ግዢ፣
ክፍያ (የውሎ አበልን የዕቃ ግዢ፣ የሰራተኞች ክፍያ ለሚገኙ የዕቃ ግዢ፣ የሰራተኞች ክፍያ (የውሎ የሰራተኞች ክፍያ (የውሎ ግዢ፣ የሰራተኞች ክፍያ
ግዢ፣ የሰራተኞች ክፍያ የሰራተኞች ክፍያ (የውሎ
ጨምሮ)፣ የአመት ፈቃድ (የውሎ አበልን ጨምሮ)፣ የሰራተኞች ክፍያ (የውሎ አበልን ጨምሮ)፣ የአመት አበልን ጨምሮ)፣ የአመት (የውሎ አበልን ጨምሮ)፣
(የውሎ አበልን ጨምሮ)፣ አበልን ጨምሮ)፣ የአመት
(Annual Leave)፣ የአመት ፈቃድ (Annual አበልን ጨምሮ)፣ የአመት ፈቃድ (Annual Leave)፣ ፈቃድ (Annual Leave)፣ የአመት ፈቃድ (Annual
የአመት ፈቃድ (Annual ፈቃድ (Annual Leave)፣
የተለያዩ ስለጠናዎች፣ Leave)፣ የተለያዩ ፈቃድ (Annual Leave)፣ የተለያዩ ስለጠናዎች፣ የጉዞ የተለያዩ ስለጠናዎች፣ Leave)፣ የተለያዩ
Leave)፣ የተለያዩ የተለያዩ ስለጠናዎች፣ የጉዞ
የጉዞ ትኬት ጉዳዮችን ስለጠናዎች፣የጉዞ ትኬት የተለያዩ ስለጠናዎች፣የጉዞ ትኬት ጉዳዮችን ያፀድቃል፡ የጉዞ ትኬት ጉዳዮችን ስለጠናዎች፣ የጉዞ ትኬት
ስለጠናዎች፣የጉዞ ትኬት ትኬት ጉዳዮችን ያፀድቃል፡፡
ማፅደቅ ጉዳዮችን ያፀድቃል፡፡ ትኬት ጉዳዮችን ያፀድቃል፡፡ ፡ ያፀድቃል፡፡ ጉዳዮችን ያፀድቃል፡፡
ጉዳዮችን ያፀድቃል፡፡

26 | ገ ፅ
ለሁሉም ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፣ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች የተሰጠ የወል ወይም የጋራ የሥልጣን ውክልና

27 | ገ ፅ
ተ/ቁ የሥልጣን የሥልጣን ውክልና የተሰጣቸው የሥራ ኃላፊዎች
ውክልናው
የተሰጠበት ጉዳይ ለምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ለዳይሬክተሮች፣ ኤክስኪዩቲቭ እና ከፍተኛ አማካሪዎች ለቡድን መሪዎች

ለ10ሩ የራስ ኃይል የመንገድ ጥገና ዲስትሪክት ዳይሬክተሮች መብራት፣ ውሃ፣ የስልክ፣ የሞባይል
✓ የውስን ጨረታ ግዥዎችን ማፅደቅ፡፡ ክፍያዎችን፣ የቤት ኪራይና ሊፍት ጥገና
• የሲሚንቶ ግዥዎችን እስከ ብር 5,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን ብር) ክፍያዎች መጠየቅ ማፅደቅና ለፋይናንስ
• ሌሎች ዕቃዎችን እስከ ብር 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ብር) ማቅረብ፡፡ (ለአስተዳደርና ፋይናንስ
ለመንገድ ሃብት አስተዳደር ም/ዋ/ዳይሬክተር ብቻ እንዲሁም ለፋሲሊቲ ማኔጅመንት ቡድን
• የአገልግሎት ግዥዎችን እስከ ብር 1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን ብር)
የተሰጠ የሥልጣን ውክልና መሪዎች ብቻ)
• የፕሮፎርማ የግዥ ውሳኔዎችን ማፅደቅ
✓ የውስን ጨረታ ግዥዎችን ማፅደቅ፡፡
• ለእቃ ግዥ እስከ ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ ብር) ግዥ መፈፀምና ዝርዝር የሆነ ሪፖርት
• ሌሎች ዕቃዎችን እስከ ብር 3,750,000 ለየዘርፉ ም/ዋ/ዳይሬክተርና ለኮርፖሬት አገልግሎት ም/ዋ/ዳይሬክተር በየሩብ ዓመቱ ማቅረብ
(ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር)
• ለሌሎች አገልግሎት ግዥ እስከ ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ፡፡
• የአገልግሎት ግዥዎችን እስከ ብር
✓ የቀጥታ የዱቤ ግዥ ውሳኔዎችን ማፅደቅ
3,000,000 (ሶስት ሚሊየን ብር)
• ውል ከተገባላቸው ዋና ዋና አቅራቢዎች እስከ ብር 1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን ብር)
✓ የፕሮፎርማ የግዥ ውሳኔዎችን ማፅደቅ
የሚደርስ የመለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ ማፅደቅ፡፡
• ለእቃ ግዥ በአንድ ጊዜ እስከ ብር
• በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የተገቡ ውሎችን እስከ አንድ ወር ማራዘም፣
400,000 (አራት መቶ ሺህ ብር)፡፡
የዕቃ እና • ለምክር አገልግሎት በአንድ ጊዜ እስከ ብር
1
አገልግሎት ግዥ 240,000 (ሁለት መቶ አርባ ሺህ ብር)፡፡ ✓ በዋጋ ማቅረቢያ/ፕሮፎርማ ግዥ በጀትን መሠረት ባደረገ መልኩ
• ለሌሎች አገልግሎት ግዥ እስከ ብር ✓ እቃ ግዥ እና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬ/ዳይሬክተር፣ የመንገድ አውታር እና ሴፍቲ
300,000/ (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ማጽደቅ፡ ማኔጅመንት ቅርንጫፍ ዳይሬ/ዳይሬክተሮች፣ አለምገና ምህንድስና እና ማኔጅመንት ማሰልጠኛ
፡ ማዕከል ዳይሬ/ዳይሬክተር ፣ የማዕከላዊ መሳሪያዎች ጥገና ዳይሬ/ዳይሬክተር እንዲሁም ጊንጪ
✓ ከአንድ አቅርቢ ግዥ እንዲፈፀም በወጣው ሌበር ቤዝድ ቴክኖሎጂ ማሰልጠኛ ማዕከል ዳይሬ/ዳይሬክተር በዋጋ ማቅረቢያ የግዥ ዘዴ፡-
መመሪያ መሰረት የቀጥታ የግዥ ውሳኔዎች ✓ ለእቃ ግዥ እስከ ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ ብር) ግዥ መፈፀምና ዝርዝር የሆነ ሪፖርት
ማፅደቅ ለየዘርፉ ም/ዋ/ዳይሬክተርና ለኮርፖሬት አገልግሎት ም/ዋ/ዳይሬክተር በየሩብ ዓመቱ ማቅረብ
✓ የቀጥታ የዱቤ ግዥ ውሳኔዎችን ማፅደቅ ✓ ለሌሎች አገልግሎት ግዥ እስከ ብር 70,000 (ሰባ ሺህ ብር)፡፡
ከላይ በቀረቡ መንገዶች የተፈፀሙ ግዥዎችን ሪፖርት ✓ የመንገድ ምርምር ማዕከል እና ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች
ተንትኖ ለበላይ አመራሩ (Executive Council) ✓ ለእቃ ግዥ እና አገልግሎት እስከ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ግዥ መፈፀምና ዝርዘር የሆነ
ያቀርባል:: ሪፖርት ለየዘርፉ ም/ዋ/ዳይሬክተርና ለመንገድ ሃብት አስተዳደር ም/ዋ/ዳይሬክተር በየሩብ
ዓመቱ

28 | ገ ፅ
ተ/ቁ የሥልጣን የሥልጣን ውክልና የተሰጣቸው የሥራ ኃላፊዎች
ውክልናው
የተሰጠበት ጉዳይ ለምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ለዳይሬክተሮች፣ ኤክስኪዩቲቭ እና ከፍተኛ አማካሪዎች ለቡድን መሪዎች

በጉዞ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን


በጉዞ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ከመፍታት ጋር ከመፍታት ጋር በተያያዘ የአንድ የግዥ
በተያያዘ የአንድ የግዥ መጠየቂያ ዋጋቸው ከ 10,000 ✓ በጉዞ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ከመፍታት ጋር በተያያዘ የአንድ የግዥ መጠየቂያ ዋጋቸው መጠየቂያ ዋጋቸው ከብር 3,000 (ሶስት
(ከብር አስር ሺህ) ያልበለጡ እቃዎች /አገልግሎቶች ከ 4,000 (ከብር አራት ሺህ) ያልበለጡ እቃዎች /አገልግሎቶች ከማንኛውም ሻጭ /ድርጅት ሺህ ) ያልበለጡ እቃዎች /አገልግሎቶች
2. ድንገተኛ ግዥ/በጉዞ ከማንኛውም ሻጭ /ድርጅት የቀጥታ ግዥ መፈጸም፡፡ ከማንኛውም ሻጭ /ድርጅት የቀጥታ
ሆኖም በዚህ መንገድ የሚገዙ እቃዎች/ አገልግሎቶች የቀጥታ ግዥ መፈጸም፡፡ ሆኖም በዚህ መንገድ የሚገዙ እቃዎች/ አገልግሎቶች በአመት ውስጥ ግዥ መፈጸም፡፡ ሆኖም በዚህ መንገድ
በአመት ውስጥ ከ150,000 (ከአንድ መቶ ሀምሳ ሺ ከ 50,000 (ከሃምሳ ሺ ብር) መብለጥ የለበትም፡፡ የሚገዙ እቃዎች/ አገልግሎቶች በአመት
ብር) መብለጥ የለበትም፡፡ ውስጥ 30,000 ከሰላሳ ሺ መብለጥ
የለበትም፡፡

29 | ገ ፅ
30
ምርጥ መንገዶች ለኢትዮጵያ ብልጽግና Best Roads For Prosperous Ethiopia

You might also like