You are on page 1of 5

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ፖሊሲ ምርምር ኢንስቲትዩት

ኮቪድ-19 በኢኮኖሚና በማህበራዊ ኑሮ ላይ የሚስከትለውን ተጽዕኖና መወሰድ ያለባቸውን


እርምጃዎች ጠቋሚ ምልከታ11

ድርሞ ( በአጭሩ የቀረበ)

ደግየ ጎሹ2፣ታደለ ፈረደ3፣ ጌታቸው ድሪባ4 ፣ መንግሥቱ ከተማ5

ሚያዝያ 2012

ISBN 978-99944-54-74-7

ድርሞ

1
የሰነዱን ወቅታዊነት ለመጠበቅ እንዲሁም በአፋጣኝ እንዲደርስ ታሰቦ በተጓዳኝ አጥኚ ቡድን አልተገመገመም።
2
ከፍተኛ ተመራማሪ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ፖሊሲ ምርምር ኢስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን
(degyeabgos@gmail.com)
3
አሶሴት ፕሮፌሰር፣ ኢኮኖሚክስ ዲፓርትመንት፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ (tadele.ferede@aau.edu.et)
4
ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የጽ/ቤት ኃላፊ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ፖሊሲ ምርምር ኢስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ
አሶሴሽን (gdiriba@yahoo.com)
5
ከፍተኛ ተመራማሪ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ፖሊሲ ምርምር ኢስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን
(mengistuket@gmail.com)
ኮቪድ-19 ተያያዥነት ያላቸውን የጤና መታወክና ህይወት ማጣትን፣ የምርት አቅርቦትና የፍላጎት አለመጣጣምን እንዲሁም
የፋናንስ ቀውሶችን ብሎም የአጠቃላይ ኢኮኖሚ መቀዛቀዝን ያስከተለ የዘመናችን አስከፊ ክስተት ነው፡፡ ድንበር ተሻጋሪው
ወረርሽኝ ከጤና ወደ ኢኮኖሚ ብሎም ማህበራዊ ቀውሶችን ከመፍጠሩም በላይ ተጽዕኖውን ለማርገብ የሚያስችል አቅምን
ተፈታታኝ ነው፡፡ ይህ ጥናት ወረርሽኙ ሊቆይ የሚችልበትን የጊዜ ርዝማኔና የቫይረሱን ሥርጭት ፍጥነት እንዲሁም ወረርሽኙን
ለመግታት የሚወሰዱ እርምጃዎች የይሆናል (የቢሆን) አማራጮች ላይ ተመስርቶ በአገራችን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ደህንነት ላይ
ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ስፋትና ጥልቀት እንዲሁም ችግሩን ለማርገብ መወሰድ ያለባቸውን አፋጣኝ እርምጃዎች
ይጠቁማል፡፡

ጥናቱ ወረርሽኙ ሊቆይ የሚችልበት የጊዜ ርዝማኔና የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት የሚወሰዱ እርምጃዎች የሚያስከትሉት
ውጤት የጉዳቱን ስፋትና ጥልቀት የሚወስኑት ቢሆንም ወረርሽኙ የአገራችንን የኢኮኖሚ እድገትን በመግታት ድህነትን ሊያባብስ
እንሚችል ያስገነዝባል፡፡ በዚህ መሠረት የወረርሽኙ የቆይታ ጊዜ እየተራዘመ በሄደ ቁጥር ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት ቅነሳ
ሊያስከትል እንደሚችል ተገምቷል፡፡ በዚህም የተነሳ ወረርሽኙ በስራተኛ ቅነሳና መፈናቀል ላይ በሚያስከትለዉ ተፅዕኖ
በኢኮኖሚዉ ላይ እስከ 200 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ሊያስከትል ይችላል። የወረርሽኙ ስርጭት መራዘምና መስፋፋት
የሚያስከትለው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መቀዛቀዝ በከተማና በገጠር ድህነትን ማሰከተሉ ግልጽ ሆኗል፡፡ በመሆኑም በአገር ዓቀፍ
ደረጃ ከድህነት ወለል በታች የሚኖረው ዜጋ እስከ 38.4 በመቶ ሊያሻቅብ እንደሚችልና ይህም በገጠር፣ በአነስተኛ ከተሞችና
በከተሞች ሲተነተን የሚኖረው ድህነት መጠን በቅደም ተከተል የ42.1፣ 29.1 እና 20 በመቶ ደርሻ እንደሚኖረው
ተመልክቷል6፡፡ በመሆኑም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚያስችሉ አፋጣኝና የተቀናጁ የመከላከል እርምጃዎችን መውሰድ
ካልተቻለ ዘርፈ-ብዙ የሶሽዮ-ኢኮኖሚ መዛባትን በመፍጠር መወጫ ወደሌለው የቀውስ አዙሪት መግባት አይቀሬ ነው፡፡
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰርቶ አደሮች ከእጅ ወደ አፍ በሆነ የኑሮ ሁኔታ የሚገኙበት የአገራችን ኢኮኖሚ ወረርሽኙ በተጨማሪ
የሚፈጥረው ጫና ከሥራ መፈናቀልን ከአስከተለ በእነዚህም ሆነ በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ የሚከትለውን አስከፊ ጉዳት
መገመት አያዳግትም፡፡

የፌዴራልና የክልል መስተዳድሮች፤ ህብረተሰቡ፣ የንግዱ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ፣ እና ሌሎችም ወረርሽኙ በጤና ላይ
የሚያስከትለውን ችግር ለመከላከል በሚያደርጉት እርብርብ በኢኮኖሚ ዘርፉም ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ጫና ባገናዘበና
ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ መሆን እንዳለበት ግንዛቤ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ በአገራችን ወረርሽኙን በመከላከል ረገድ የሚደረገው
ጥረት በህብረተሰቡ ላይ ሊከሰት በሚችለው የሞት አደጋና ርሀብ መካከል ምርጫ ሊኖር አይገባም። በመሆኑም ፈጣንና ሁሉን
አቀፍ የመከላከልና የማገገሚያ መርሀ-ግብር በመዘርጋትና በመተግበር ጊዚያዊ የሆነው የጤና መታወክ ዘላቂና የከፋ የኢኮኖሚና
ማህበራዊ ቀውስ እንዳያስከትል ማድረግ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው፡፡

6
የዚህን ዝርዝር በሚከተለው መረጃ መመልከት ይቻላል ፡፡
http://eeaecon.org/sites/default/files/publications/Economic%20Impacts%20of%20Coronavirus%20and%
20%20Responses%20in%20Ethiopia__08042020.pdf
ወረርሽኙን የመከላከል አማራጮች

ጤናና ማህበራዊ ደህንነት

• የቫይረሱን ስርጭት ፍጥነት በመቀነስ ወረርሽኙ በኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን
ተጽዕኖ ማርገብ፣ ለቫይረሱ ተጋላጭ በሆኑ ላይ ምርመራ ማካሄድ፣ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ጋር ግንኙነት ያላቸውን
መለየት፣ የማህበራዊ ቅርርብ የሚጎላባቸውን የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን ማስቆምና የመሳሰሉትን
በመተግበር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚያስችል ፈጣንና የተቀናጀ እርምጃ መውሰድ፣
• በመላው አገሪቱ የሚከናወኑ የገበያ ቦታዎች፣ የግብርና ምርቶችና የጉልት ገበያን፣ አነስተኛ ሱቆች፣ የጎዳና ላይ ግብይትን
ጨምሮ በሚካሄዱ የሸቀጥ ልውውጦች ህብረተሰቡ የማህበራዊ ርቀትን በመጠበቅ እና ራስን ለመከላከል የሚያስችል
መሳሪያን በመጠቀም የቫይረሱን ስርጭት መግታት፣
• ውጤታማ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ከየካቲት ወር ጀምሮ በመካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የመረጃ
ተደራሽነት አናሳ በሆነባቸው የገጠሩና ከማዕከል ርቀት ባላቸው አካባቢ ተመሳሳይ ዘመቻ ማካሄድ፣፡

በመካሄድ ላይ ያለውን የገጠርና የከተማ የማህበራዊ ዋስትና (ሴፍቲ ኔት) ፕሮግራም ማሳደግ

• በኢትዮጵያ የተጠናከረና የተቀናጀ የገጠርና የከተማ የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት አደረጃጀት፣ ፕሮግራም፣ እንዲሁም
የጥሬ ገንዘብና የቫውቸር ስርጭት መኖሩ የብዙዎችን ምስክርነት ያገኘ ተግባር ነው፡፡ ፕሮግራሙ በአሁኑ ጊዜ ለአደጋ
ተጋላጮችን የሚደግፍ በቂና ውጤታማ የእህል ክምችትና የስርጭት ስትራተጂና ቁመና ያለው መሆኑ የሚፈተሸበት
ወቅት ነው።፡
• ወረርሽኙ ምናልባት የተባባሰ ቢሆን የማህበራዊ ዋስትና ፕሮግራሙ በአጭር ግዜ በተለይም በከተሞች ከፍተኛ ጫና
የሚኖርበት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም የህብረት ሥራ ማህበራትን፣ የቀበሌ አስተዳደር የስርጭት መረብን፣
እንዲሁም አነስተኛ የችርቻሮ ንግድ ድርጅቶችን በቫውቸር ላይ የተመሰረተ አማራጭ ስልት በመጠቀም በወረርሽኙ
ሊጠቁ የሚችሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ ዝግጅት ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ የጥሬ ገንዘብና የቫውቸር አሰራር
በአሁኑ ወቅት የብሄራዊ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ከዓለም አቀፍና አሁጉራዊ ድርጅቶች እንዲሁም
መንግሥታት ጋር በመተባበር መተግበር።
• ህብረተሰቡ ችግሩን የሚጋራበትና ማህበራዊ ትስስሩን የሚገልጽባቸው አደረጃጀቶች ለምሳሌም እድርና ማህበርን
ከመደበኛ መዋቅር ጋር በማስተሳሰር በወረርሽኙ በቀላሉ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን እገዛ ማድረግ
ተገቢ ነው፡፡

መሰረታዊ የሆኑ ሸቀጦችን ስርጭት ማጎልበት

• የምግብ እህሎችን፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የንጽህና እቃዎች እና ቅመማ ቅመሞችን የመሳሰሉ መሰረታዊ ሸቀጦች
አቅርቦት ሳይቆራረጥ በመደበኛነት በመላው ሀገሪቱ ስርጭታቸው ቀጣይነት እንዲኖረዉ ማድረግ፡፡ ከክልል ክልል
የሚደረግ ሽግግርን የሚያግደው አሰራር የሸቀጦችን ዝውውር የሚያውክ መሆን አይኖርበትም፡፡ የሸቀጦች ዝውውርን
መገደብ የሚያስከትለው ተጽዕኖ የህብረተሰቡን ኑሮ ከማቃወስ አልፎ የብሄራዊ ህልውናን ስጋት ላይ የሚጥል ነው፡፡
• የግብርና ምርቶች ልውውጥ መሰናክል አለመኖሩን ማረጋገጥ፣ በገበሬዎች መካከል የሚደረጉ የእርስ በርስ
ልውውጦችን፣ ከግብርና አምራቾች ወደ ጅምላና ችርቻሮ ነጋዴዎች የሚደረጉ ግብይይቶችንና ስርጭትን የተሳለጠ
እንዲሆን ማድረግ፣፡፡
• የምግብ ሸቀጦችን ከውጭ ማስገባት በአገር ውስጥ ያለውን የምግብ እጥረት ችግር ለመቅረፍ ያለው ጠቀሜታ የጎላ
ነው፡፡ በወረርሽኙ ዓለም ዓቀፋዊ ባህሪ የተነሳ ሸቀጦችን ከውጭ ማስመጣት እንደቀድሞው ቀላል ላይሆን ይችላል፡፡
ይህ ደግሞ ከውጭ በሚገቡ የምግብ ሸቀጦች ላይ መዘግየትን ሊያስከትል ስለሚችል፣ የዓለም ዓቀፍ የሸቀጦች ንግድ
ልውውጥ አሰራርን ተከትሎ የምግብ ሸቀጦችን ከውጭ ለማስገባት የወደፊት ግዥ ኮንትራትን ስልት በተቻለ መጠን
መተግበር ጠቃሚ ነው፡፡

የአገር ውስጥ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴን መደገፍ

• ከውጭ የሚገቡ የምግብ ሸቀጦች መቀነስ ምክንያት የሚከሰት ጉድለትን ለመተካት የሚስችል አማራጭ መዘየድ ተገቢ
ነው፡፡ እነዚህም በአፋጣኝ የሚደርሱ የእህል ሰብሎችን ማምረት፣ የመስኖ ሥራዎችም ለተመረጡ የምግብ እህሎችና
አትከልቶች ለምሳሌም ድንች፣ በቆሎና ለመሳሰሉት የቅድሚያ ትኩረት መስጠት፣
• የልተቆራረጠና ፈጠን የሆነ የግብርና ግብዓቶችን ማለትም ማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘር፣ ፀረ-ተባይ እና የእንስሳት
መድሀኒቶችን አቅርቦትና ስርጭት የተፋጠነ በማድረግ፣ ወረርሽኙ በግብርና እንቅስቃሴ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን
ተጽዕኖ ለማርገብ ይረዳል፡፡
• በወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ ለተጎዱ የኢኮኖሚ ዘርፎች ወረርሽኙ እስከሚወገድ ድርስ የንግድ ባንኮች የብድር
ክፍያዎች ሽግሽግ እና የወለድ ክፍያ ስረዛ እንዲያደርጉ ውይይትና ምክክር ማድረግ፣
• የንግድ ባንኮችን የገንዘብ አቅርቦት ለማሳደግ የኢትዮጵያ በሄራዊ ባንክ አስገዳጅ የሆነውን የተቀማጭ መጠንን ዝቅ
እንዲያደርግ መጠየቅ፣
• የኢኮኖሚ መነቃቃት ለመፍጠር የወለድ መጣኔን ዝቅ ለማድረግ የሚያስችል ውይይትና ምክክር በኢትዮጵያ ብሄራዊ
ባንክ እና በንግድ ባንኮች መካከል ማካሄድ፣
• የንግድ ባንኮች በኤክስፖርት ተግባር ላይ ለተሰማሩ የውጭ ንግድ ብድር እንዲያቀርቡ፣ እንዲሁም ኤክስፖርተሮች
ያለባቸውን ብድር ክፍያ ላይ ሽግሽግ እንዲያደርጉ ምክክርና ውይይት ማድረግ፣

መሰረታዊ አገልግሎቶች ተጠናክረው እንዲቀርቡ ማድረግ

• ለመጠጥና ለንጽህና ጥበቃ አስፈላጊ የሆነው የውኃ አቅርቦት በተለይ በከተሞች ባልተቆራረጠ ሁኔታ እንዲቀርብ
ማድረግ፣
• የወረርሽኙን አስከፊነትና መከላከያውን በተመለከተ በአገር ዓቀፍ፣ በክልል፣ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ አስተማማኝና
ተቀባይነት ባላቸው የብዙሃን መገናኛ ዘዴዎች ትክክለኛ መረጃዎች ለህብረተሰቡ እንዲደርሱ ማድረግ፣ የመረጃ
ስርጭቱም በገጠርና ከተማ፣ ለአካል ጉዳተኞችና ላልተማረው የህብረተሰብ ክፍል ጭምር ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ
የተሳሳቱ መረጃዎችን ለመግታት የሚስችል መሆን ይኖርበታል፡፡
• የማህበራዊ ቀውስ ቢፈጥር ጸጥታን ለመቆጣጠር የሚያስችል በቂና የተጠናከረ የጸጥታና ጥበቃ ኃይል ማደራጀት።

ኃብት ማሰባሰብ

• ወረርሽኙን ለመከላከል፣ በቫይረሱ የተጠቁትን ለመለየትና አስፈላጊውን እንክብካቤና የማገገም ተግባር ለማከናወን
እንዲረዳ ታስቦ የተቋቋመውን የወረርሽኝ ፈንድ አሰባሰብ ማጠናከር፣ በዚህ ረገድ የፈንዱን አስተዳደር ግልጽነትና
ተጠያቂነት በማረጋገጥ፣ የዜጎችን ተነሳሽነትና አንድነት በማጎልበት ወረርሽኙን ለመከለከል የሚደረገውን ጥረት
ውጤታማ እንዲሆን ያስችላል፡፡
• የኮቪድ-19 ወረርሽኝን መከላከል ለሚከናወኑ ተግባራት የወጪ ሽግሽግ (ለምሳሌም የመንግሥት በጀት) ማድረግ፡፡
በዚህ ረገድ በወረርሽኙ ሳቢያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ትምህርት ቤቶች የተዘጉ በመሆኑ ለዚህ ተግባር የተመደበ
የወጪ በጀትን ወረርሽኙን ለመዋጋት ለሚደረጉ ጥረቶች ማዋል የሚመከር ይሆናል፡፡
• ይህን መሰሉ አገራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ቀውስ ሲያጋጥም አጋዥ ሆነ አገር ዓቀፍ ሉዓላዊ የመጠባበቂያ ፈንድ ማቋቋምና
ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑን ከኮቪድ-19 ወረርሽ መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡

You might also like