You are on page 1of 5

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ 1 ዱ አምላክ አሜን

ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ 121፡1

በኢ.ኦ.ተ.ቤተ ክርስቲያን በጎዶሊያንስ መንፈሳዊ ጉዞ ማህበር ወደ አድባራትና ገዳማት ለሚሄዱ ምዕመናን/ናት


የተዘጋጀ መጠይቅ

ውድ ምዕመናን/ናት በቅድሚያ ምህረቱን ያበዛልን ሥላሴን እያመሰገንሁ፤ የከበረ ሠላምታዬን በልዑል እግዚአብሔር
ስም አቀርባለሁ፡፡
ክቡራን የጎዶሊያስ መንፈሳዊ ጉዞ ማህበር ተሳታፊዎች እኔ ደቀ መዝሙር ተናኘ እባላለሁ፡፡ በኢ.ኦ.ተ.ቤተ ክርስቲያን
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ዕጩ ተመራቂ ደቀ መዝሙር ነኝ፡፡ ትምህርቴን ለማጠናቀቅ በመንፈሳዊ ጉዞ ማህበራት
የሚከናወኑ መንፈሳዊ ጉዞዎች በምዕመናን ሕይወት ላይ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በማጥናት ላይ ነኝ፡፡ ይህ ጥናት ለኔ
መመረቂያ ሆኖ እንዲያገልግል ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ማህበሩም በቀጣይ ጥንካሬና ጉድለቱን ለይቶ በላቀ ሁኔታ
ተግባሩን እንዲያከናውን ያስችለዋል፡፡ከእናንተ የማገኘው መረጃ ለጥናት ዓላማ ብቻ እንጂ ለሌላ ለምንም አገልግሎት
አይውልም፡፡ መጠይቁ በጣም አጭርና ግልጽ፤ ለሙሙላት 20 ደቂቃ ብቻ የሚወስድ ነው፡፡
ስለሆነም ትክክለኛ እና ውጤታማ ጥናት ማጥናት የሚያስችለኝ መረጃ እንድትሰጡኝ በአክብሮት እየጠየቅሁ
ጊዜያችሁን ሰውታችሁ ለምታደርጉልኝ ትብብር ቅድመ ምስጋናዬ የላቀ ነው፡፡
ከሰላምታ ጋር
ለበለጠ መረጃ
melakuawg2008@gmail.com & Mobile: 0928823499

ስምዎን መጻፍ የግድ አይደለም፡፡ ከፈለጉ ግን ይችላሉ ……………………………………

ክፍል 1 አጠቃላይ መረጃ


 ዕድሜ ጾታ የትምህርት ደረጃ
ከዚህ ቀደም መንፈሳዊ ጉዞ ስንት ጊዜ (ለምን ያህል ጊዜ) ተጉዘዋል
 በዚህ ማኅበር
 በሌሎች ማኅበር
በአብዛኛው መንፈሳዊ ጉዞ የሚያደርጉት መች ነው
 በሰንበት 
 በአዘቦት 
 ዓመታዊ ክብረ በዓላት (ወርሃዊ እና ዓመታዊ) 
ክፍል 2 የመንፈሳዊ ሕይወት እድገት ጥያቄዎች
ከዚህ በታች ምዕመናን መንፈሳዊ ጉዞዎች ላይ በመሳተፍ ያገኙትን የመንፈሳዊ ዕድገት ለውጥ መለካት የሚያስችሉ
መጠይቆች ተዘርዝረዋል፡፡ ስለሆነም በእያንዳንዱ ሃሳብ ላይ ያመጡትን ለውጥ የሚለኩ የአፈጻጸም ደረጃ ከ 1-5
በተገለጹ መግለጫዎች መረሰት የ‘X’ ምልክት በማድረግ ስምምነቶች ይግለጹ፡፡
1 በጣም ልስማማም 2 አልስማማም 3. በከፊል እስማማለሁ 4 እስማማለሁ 5 በጣም እስማማለሁ
ተ/ ዋና ዋና መመዘኛዎች የስምምነት ደረጃ
1 ሥርዓተ ጾምን በተመለከተ 1 2 3 4 5
1.1 መንፈሳዊ ጉዞ ላይ መሳተፍ ከጀመርኩ ጀምሮ አርብ እና ረቡዕን ብቻ ሳይሆን ሌሎች
የሕግ አጽዋማትን በሥርዓቱ መሠረት ሰዓቱን አክብሬ መጾም ጀምሬአለሁ
1.2 ቤተሰቦቼ በሙሉ የጾምን ጥቅም፣ ዓይነትና ሥርዓት እንዲረዱና እንዲተገብሩ
አድርጌአለሁ፡፡
2 ሥርዓተ ጸሎትን በተመለከተ
2.1 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ጸሎትን አውቄአለሁ፡፡
2.2 የግልና የማኅበር ጸሎት ለአንድ ምእመን መንፈሳዊ ዕድገት አስፈላጊ መሆናቸውን
ተረድቻለሁ፡፡
2.3 ጠዋትና ማታ በአቅሜ አምላኬን በጸሎት ማመስገን ጀምሬያለሁ
2.4 በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚካሄዱ የጸሎት መርሃ ግብራት ሁሉ መሳተፍ
ጀምሬያለሁ፡፡
3 የምሥጢራት ተሳትፎን በተመለከተ
3.1 መንፈሳዊ ጉዞ መጓዝ ከጀመርሁ በኋላ በየዕለቱ ኪዳን ማድረስ ጀምሬአለሁ
3.2 መንፈሳዊ ጉዞ መጓዝ ከጀመርሁ በኋላ ቤተሰቦቼ በየዕለቱ ኪዳን እንዲያደርሱ
አድርጌአለሁ
3.3 መንፈሳዊ ጉዞ መጓዝ ከጀመርሁ በኋላ በእለተ ሰንበት በደብሬ ማስቀደስ
ጀምሬያለሁ፡፡
3.4 መንፈሳዊ ጉዞ መጓዝ ከጀመርሁ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል
ጀምሬያለሁ (ተቀብያለሁ)
3.5 መንፈሳዊ ጉዞ መጓዝ ከጀመርሁ ቤተሰቦቼ በእለተ ሰንበት በደብሬ ማስቀደስ
እንዲጀምሩ አስችሎናል
3.6 መንፈሳዊ ጉዞ መጓዝ ከጀመርሁ ቤተሰቦቼ በእለተ ሰንበት ቅዱስ ስጋ እና ክቡር
ደሙን መቀበል ጀምረዋል
3.7 መንፈሳዊ ጉዞ መጓዝ ከጀመርሁ በኋላ እኔም ሆንኩ መላው ቤተሰቦቼ የንስሃ አባት
ይዘናል
3.8 መንፈሳዊ ጉዞ መጓዝ ከጀመርሁ በኋላ እኔም ሆንኩ ቤተሰቦቼ የሰበካ ጉባኤ ክፍያ
መክፈል ጀምረናል
3.9 መንፈሳዊ ጉዞ መጓዝ ከጀመርሁ በኋላ እኔም ሆንኩ ቤተሰቦቼ አስራታችንን
በአግባቡ ማውጣት ጀምረናል
4 ክርስቲያናዊ ግዴታ መወጣትን በተመለከተ
ቤተክርስቲያኔ የእኔ መሆኗን በመረዳት በተለያዩ የቤተክርስቲያን ይልማተ ሥራዎች
መሳተፍ ጀምሬያለሁ፡፡
የቤተክርስቲያን ጠላቶች በተለያየ መንገድ እያደረሱ ያሉትን ጫና በመገንዘብ
በተለያየ መንገድ ቤተ ክርስቲያን በምታዘው መሠረት የመከላከል ሥራ መሥራት
ጀምሬያለሁ፡፡
እኔም ቤተሰቦቼም የሰንበት ት/ቤት አባል በመሆን የቤተ ክርስቲያናችንን ሥርዓተ
አምልኮ ለማወቅ ጥረት ማድረግ ጀምረናል፡፡

ክፍል 3 ማብራሪያ የሚሹ ኃሳቦችን በተመለከተ


3.1. በመንፈሳዊ ጉዞ ወቅት የሚገኟቸውን መንፈሳዊ እና ምሥጢራዊ አገልግሎቶችን ቢያብራሩ፡፡
3.2. መንፈሳዊ ጉዞ ላይ መሳተፍ ለምእመናን ክርስቲያናዊ ሕይወት እድገት ምን ተጨማሪ አስተዋጽኦ (ጥቅም) አለው
ይላሉ ያብራሩ፡፡

3.3. መንፈሳዊ ጉዞዎችን የሚያስተባብሩ አካላት በቀጣይ ምን ምን ጉዳዮችን ማስተካከል አለባቸው ይላሉ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ 1 ዱ አምላክ አሜን

ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ 121፡1

በኢ.ኦ.ተ.ቤተ ክርስቲያን በጎዶሊያንስ መንፈሳዊ ጉዞ ማህበር አመራሮች /ባለቤት/ የተዘጋጀ መጠይቅ


ውድ የመንፈሳዊ ማህበሩ አስተዳዳሪዎችና ባለቤቶች በቅድሚያ ምህረቱን ያበዛልን ሥላሴን እያመሰገንሁ፤ የከበረ
ሠላምታዬን በልዑል እግዚአብሔር ስም አቀርባለሁ፡፡
እኔ ደቀ መዝሙር ተናኘ እባላለሁ፡፡ በኢ.ኦ.ተ.ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ዕጩ ተመራቂ ደቀ መዝሙር
ነኝ፡፡ ትምህርቴን ለማጠናቀቅ በመንፈሳዊ ጉዞ ማህበራት የሚከናወኑ መንፈሳዊ ጉዞዎች በምዕመናን ሕይወት ላይ
ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በማጥናት ላይ እገኛለሁ፡፡ ለዚህ ጥናት መንፈሳዊ ጉዞ ከሚያከናውኑ ማህበራት መካከል የእንናተ
ማህበር በሚያደርገው መንፈሳዊ እንቅስቃሴ የተሻለ በመሆኑ ለጥናቴ መርጨዋለሁ፡፡ ይህ ጥናት ለኔ መመረቂያ ሆኖ
እንዲያገልግል ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ማህበሩም በቀጣይ ጥንካሬና ጉድለቱን ለይቶ በላቀ ሁኔታ ተግባሩን እንዲያከናውን
ያስችለዋል፡፡ ከእናንተ የማገኘው መረጃ ለጥናት ዓላማ ብቻ እንጂ ለሌላ ለምንም አገልግሎት አይውልም፡፡ መጠይቁ
በጣም አጭርና ግልጽ፤ ለሙሙላት 20 ደቂቃ ብቻ የሚወስድ ነው፡፡
ስለሆነም ትክክለኛ እና ውጤታማ ጥናት ማጥናት የሚያስችለኝ መረጃ እንድትሰጡኝ በአክብሮት እየጠየቅሁ
ጊዜያችሁን ሰውታችሁ ለምታደርጉልኝ ትብብር ቅድመ ምስጋናዬ የላቀ ነው፡፡
ከሰላምታ ጋር
ለበለጠ መረጃ
melakuawg2008@gmail.com & Mobile: 0928823499

1. የመንፈሳዊ ጉዞ ማኅበሩ ስም
2. የተቋቋመበት ዓመት
የጉዞ ማኅበሩ ዋና ዓላማ ያብራሩ ( ይህን መንፈሳዊ ማህበር ለምን መሰረቱት)

3. የማኅበሩ ቋሚ አባላት ወንድ ሴት ድምር


4. ጉዞው የሚመቻችበት ወቅት መች መች ነው? በየሳምንቱ ፣ በየወሩ
በወርሃዊና ዓመታዊ በዓላት
ምዕመናን መንፈሳዊ ጉዞ የሚያደርጉት ለምንድን ነው?

5. ማህበሩ መንፈሳዊ ጉዞ ላይ በመሰማራቱ ጉዞው ላይ በሚሳተፉ ምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት ዕድገት ላይ


ያበረተውን አስተዋጽኦ ያብራሩ

6. ማህበሩ መንፈሳዊ ጉዞ ላይ በመሰማራቱ ለቤተ ክርስቲያን ሐዋሪያዊ ተልዕኮ ስኬትና ለወንጌል ትምህርት
መስፋፋት እና ሌሎች ተዛመዘጅ ጉዳዮች ያበረተውን አስተዋጽኦ ያብራሩ
7.

8. በመንፈሳዊ ጉዞ ወቅት ማኅበሩ ለምእመናን የሚሰጣቸው መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ይዘርዝሩ፡፡

9. በመንፈሳዊ ጉዞ ወቅት ለምእመናን የሚሰጡ (የሚፈጸሙ) ምሥጢራት ካሉ ቢብራራ፡፡

10. ይህን መርሃ ግብር ሲያስተባብሩ የገጠማችሁ ዋና ዋና ችግሮችን ቢያብራሩ

11. በቀጣይ በምዕመናን መንፈሳዊ ሕይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት የሚችል መርሃ ግብር
ከማዘጋጀት አንጻር ከማን ምን አይነት ድጋፍ ይፈልጋሉ

እግዚአብሔር ይስጥልን

You might also like