You are on page 1of 10

በኢትዮጵያ፡ ኦርቶዶከስ፡ ተዋህዶ፡ ቤተክርስቲን፡

አዲስ፡አበባ ሀ/ስብከት ን/ላ/ክፍለ ከተማ በፉሪ መካነ


ቅዱሳን ደ/ምህረት ቅ/ሚካኤል
አጥቢያ ቤተክርስቲያን

ሰንበቴ ማህበር፡ መተዳደሪያ፡ ደንብ


መስከረም፡ 2015 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

1
መግቢያ፡
ሰንበቴ ማህበር በፉሪ መካነ-ዱሳን ደብረ ምህረት ቅ.ሚካኤል
አባቶቻችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚተርኩት ማህበር የሚለው ቃል ሲተረጎም አንድነት፣ጉባኤ ወይንም ሸንጎ
ሲሆን በአንድነት፡ በመተባበር፡ መኖር፡ ማለት፡ ነው፡፡ ቃሉም የግዕዝ፡ ቃል፡ መሆኑን፡ ይነግሩናል። ብዙዎች ተሰብስበው
በአንድነት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው ብዙዎች ስለ አንድ አንድ ስለብዙ የሚሆኑበት
ብልሃት ነው፡፡ በማያያዝም፡ በምድራዊው፡ ዓለም፡ በማህበር፡ ወይም፡ በመተባበር፡ መኖር፡ የተጀመረው፡ ከቀዳሚዎቹ፡
ፍጥረታት፡ ከአባታችን፡ ከአዳምና፡ ከእናታችን፡ ከሔዋን፡ ጊዜ፡ ጀምሮ፡ እንደሆነ፡ እና፡ ከዚያም፡ በኋላ፡ ልጆቻቸውና፡
የልጅ፡ ልጆቻቸው፡ አሁን፡ እኛ፡ እስካለንበት፡ ዘመን፡ ድረስ፡ በተለያየ፡ መልኩ፡ ሲጠቀሙበት፡ እንደቆዩ፡ እና፡አሁንም፡
እየተጠቀሙበት፡ መሆኑን፡ ሊቃውንተ፡ ቤተክርስቲያን፡ በሰፊው፡ ያስረዳሉ። እንዲሁም፡ ማህበር፡ ከምድራዊ፡ ሰዎች፡
ብቻ፡ ሣይሆን፡ በሠማያዊያን፡ መላዕክት፡ ዘንድም፡ በዓለመ፡ መላዕክት፡ ማህበር፡ መኖሩን፡ ይህም፡ ማህበር፡ በዘጠና፡
ዘጠኝ፡ ነገደ፡ መላዕክትና፡ በዘጠና፡ ዘጠኝ፡ የነገድ፡ አለቆች፡ የተከፋፈለና፡ የተመደበ፡ መሆኑን፡ መምህራንና፡ መጻህፍት፡
ይነግሩናል።
ማህበር ቤተክርስትያን የሚልም ትርጉምም ሊኖረው ይችላል የማህበርም መሥራች እርሱ ራሱ ጌታችንና መድሐኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስም ነው አስፈላጊነቱንም ለማጠየቅ 120 ቤተሰብ ማህበር መስርቶም ነበር፡፡ በሐዋርያት ሥራም
እንደምናውቀው ሐዋርያትም ማህበር ነበራቸው፡፡ በሀገራችንም አንድነት ገዳማት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
መጠንከር መስፋፋት ዓይነተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ይታመናል፡፡

ማህበር፡ በማህበርተኞቹ፡ ከሚያከናዉኑት፡ ተግባራት፡ አንጻር፡ እንዲሁም፡ ይዘት፡ ከተነሳው፡ ዓላማ፡ አኳያ፡ ሲመዘን፡
ዓለማዊ፡ ወይም፡ መንፈሳዊ፡ማህበር፡ ሊባል፡ ይችላል። ዓለማዊ፡ ማህበር፡ በአንድ፡ ነገር፡ ላይ፡ አንድ፡ ዓይነት፡ ፍላጎት፡
ያላቸው፡ ሠዎች፡ ፍላጎታቸውን፡ ወይንም፡ ዓላማቸውን፡ ለማሳካት፡ በጋራ፡ የሚያከናውኑት፡ ተግባር፡ ነው። መንፈሳዊ፡
ማህበር፡ ብለን፡ የምንጠራው፡ ማህበር፡ ግን፡ በዓለም፡ ውስጥ፡ እየኖሩ፡ የዓለሙን፡ አታላይነት፡ እና፡ ሀላፊነት፡
ተገንዝቦ፡ በልክ፡ እየኖሩ፡ ነገረ፡ እግዚአብሔርን፡ በማሠብ፡ ትዕዛዛቱን፡ በመጠበቅ፡ ምዕመናንና፡ ቤተክርስቲያንን፡
በማገልገል፡ ተስፋ፡ የምናደርጋትን፡ መንግስተ፡ ሠማያት፡ በጋራ፡ መውረስ፡ ነው።
በኢትዮጵያ፡ ኦርቶዶክስ፡ ተዋህዶ፡ ቤተክርስቲያን፡ ውስጥ፡ መንፈሳዊ፡ ማህበራት፡ ተብለው፡ ከሚታወቁት፡ ወይም፡
ከሚጠሩት፡ አንዱ፡ እና፡ ዋነኛው፡ የሰንበቴ፡ ማህበር፡ ነው። የሰንበቴ፡ ማህበር፡ አበው፡ለቃውንት፡ እንደሚሉት፡ ከሆነ፡
ረጅም፡ ዕድሜና፡ ከቤተክርስቲያኒቱ፡ ታሪክ፡ ጋር፡ የሚጋራ፡ ዕድሜ፡ ያለው፡ ነው፡ ይሉታል።
የሰንበቴ፡ ማህበር፡ ሲቋቋም፡ ወይም፡ ሲመሠረት፡ መጠሪያ፡ ስም፡ በአጥቢያው አካባቢና በቤተክረሰቲያኑ መነሻነት
ሊሰየም ይችላል፡፡

1 ለምሳሌ፡ በጌታ፡ በራሱ፡ ዕለተ፡ ሰንበትን፡ ምክንያት፡ በማድረግ፡ ሰንበቴ፡ ተብሎ፡የጽዋ፡ ማህበር፡ ሊጠጣ፡
ይችላል። እንዲሁም፡ መድሃሊዓለም፤ በዓለወልድ፡ እና፡ ሌሎችንም፡ ሊጨምር፡ ይችላል።
2 በእመቤታችን፡ በቅድስት፡ ድንግል፡ማርያም፡ ሥም
3 በቅዱሳኑ፡ እና፡ በሠማዕታቱ፡ ሥም፡ እንዲሁም
4 በቅዱሳን፡ መላዕክቱ፡ ሥም፡ ማህበሩ፡ ሊሠየም፡ ይችላል።

ማህበር እንግዲህ የስምምነት ውጤት እና የፍቅር መሠረት በመሆኑ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ እና የተቀደሰ ተግባር
ነው፡፡ ሁለቱ በምድር በማናቸውም ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማዩ ካለው አባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል፡፡ ሁለት ወይም ሶስት
በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና፡፡ መንፈሳዊ ማህበር እና የጸበል ጸዲቅ ዝግጅት ዋና ዓላማው እና መነሻው
“ በጻድቅ ሥም ንጹህ ውሃ ያጠጣ የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል” የሚለው፡ አምላካዊ ቃል ነው። ጌታችን አምላካችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን መረቡን ሲያሰፋ እና የሠው ልጆች በተለያዬ መልኩ መዳን እንዲችሉ ከላይ
በገለጽነው መልኩ ጸበል ጸዲቅ በሥማቸው ለሚዘከርላቸዉ ወዳጆቹ የማዳን፡ወይም የማማለድ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል።

2
የሰንበቴ ማህበር በዕለተ ሰንበት ብቻ ክርስቲያኖች በየሳምንቱ ዕሁድ እሁድ እየተሰበሰቡ ነዳያንን እየመገቡ
ስለኃይማኖታቸው እየተወያዩ የሚያሳልፉበት አሠራር ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርሰቲያን እንደሚገልፁት ሰንበቴ ማህበር
ዕብራውያን በየሳምንቱ ቀዳሚት ሰንበትን ከሚያከብሩበት ባህል የተወሰደ ይመስላል፡፡ ዕብራውያን በአሪት ዘመን
በቤተመቅደስ በየሳምንቱ እየተገናኙ ቃለ እግዚአብሄርን ይማሩ ነበርና በአዲስ ኪዳንም ከላይ በትንሹ እንዳነሳነው
ሐዋርየትም በተለይ በመጀመርያው ክፍለ ዘመን በዕለተ ሰንበት በየአጥቢያው ቤተክርስቲያን እየተሰበሰቡ በፀሎት፣በቅዳሴና
በውይይት ያሳልፉ እነደነበር ተጽፏል፡፡

በሀገራችንም በጥንት ጊዜ በዕለተ ሰንበት ክርስቲያኖች አብዛኛውን ጊዚያቸውን የሚያሳልፉት ቤተክርሰቲያን ነበር፡፡ ወደ
ቤተክርስቲያን የሚሄዱ እናቶች በሰንበት ዕለት የተቻላቸውን ሁሉ ለምሳሌ ዳቦ፣አነባበሮ፣ቂጣ፣አምባሻ፣ቆሎ፣ንፍሮ፣ወዘተ
ይዘው ይሄዱ እንደነበር የቤተክርሰቲያን የታሪክ መመጻሃፍት ያስረዳሉ አሁንም ይኸው ቀጥሎ እናቶች በቤተክርሰቲያናችን
እንደምናየው እንጀራም ጭምር ይዘው ይመጣሉ፡፡ በመቀጠልም ከቅዳሴ በኃላ ሁሉም ስጋ ወደሙ የሚቀበሉ በመሆኑ
መክፈልት ይቀምሳሉ፡፡ ቀጥሎም በዕለቱ የተመደቡ መምህራን ትምህርተወንጌል ያስተምራሉ ከዚያም ስለ መንፈሳዊና
ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች ያኪያሄዱ ነበር፡፡ የተከሰቱ ችግሮች ካሉ ለምሳሌ የተጣላ ካለ፣በኑሮ የተጎዳ/ድህነት
የተጠቃ ካለ፣ የታመመ፣ ቤት የፈረሰበት ወዘተ ተለይቶ ድጋፍ ይደረግ ነበር፡፡

ሰንበቴ እንደ ቦታው ርቀት እንደ ምዕመናን ብዛት በሳምንት ወይንም በወር ይከናወን ነበር፡፡ ከዚሁ ጋር የቀደምት የሰንበቴ
ማህበራት በዋናነት የሚቀርበውን ዕህል ውሃ አብዛኛውን እና ቅድሚያ ለነዳያን በመስጠት ይከናውን ነበር፡፡
ሰንበቴ ቀደም ባሉ ግዚያት በሁለት ቦታዎች ይከናወን ነበር አንደኛው በቅፀረ ቤተክርስቲያን ውስጥ በስተምዕራብ አቅጣጫ
በደጀሰላም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአውራጎዳና በዋርካ ሥር የታላቁን የእግዚአብሔር ወዳጅ የአብርሐምን ልምድ ታሳቢ
ያደረገ ነበር፡፡ የሰንበቴ መክፈልት በካህናት ተባርኮ የሚበላና የሚጠጣ በመሆኑ ከስጋ ወደሙ ቀጥሎ በረከተ ነፍስ ወስጋ
ፍቅርን አንድነትን አሰገኚ ተደርጎ ስለሚወሰድ ሰንበቴ መሳተፍ ግዴታ ማህበር ግን ውዴታ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ሰንበቴ
የሚመራው በሙሴ የነበረ ሲሆን እያደር ግን ከሰው ብዛትና ተጨማሪ መንፈሳዊ ተግባራትን ለማካተት ሲባል ከሙሴ እና
ከግልገል ሙሴ(ረዳት) ተጨማሪ ሰዎችን (ደርገ ሙሴዎች) በማካተት መመራት ቀጥሏል፡፡
ሰንበቴ በተራ በሚፈፀምበት ሁኔታ ሙሴው ቀጣዩን ተረኛ ዘካሪ/አቅራቢ፣ሁለተኛውን እና ሶስተኛውን አንዲሁም
አራተኛውን አንዲህ በማለት ያስተናስላል፡፡ ማነህ ባለ ሳምንት፡ ባለሁለት፣ ባለ ሶስት ካለ በኋላ ባለ አራት ተወሳወስ ብሎ
ያጠቃልላል፡፡
ተረኞችም ተነስተው እኔ ነኝ በማለት ቢያድረሰን በያደርሳችሁ እያሉ ቄጤማውን ጎዝጉዤ ድግሱንም ደግሼ እቆያችኋለሁ
በማለት ተራ በተራ በጎ ፈቃደኝነታቸውን ይናገራሉ፡፡ በሊቀስልጣናት ሀብተማርያም ወርቅነህ፣ በኋላ አቡነ መለከጸዴቅ
በቅረቡ ህይወታቸው ያለፈው አባት ማህበራዊ ኑሮ በኢትዮጵያ በሚለው 1959 በታተመው መጽሀፋቸው እንደተገለጸው፡፡

ከዚህ፡ አንጻር፡ እኛም፡ በፉሪ መካነ-ቅዱሳን የደብረ ምህረት ሊቀ መላዕክት ቅ/ሚካኤል ሰንበቴ ማህበርን፡ ትውፊቱን
በጠበቀና በተከተለ አበው በከወኑበት መንገድ እንድንፈፅም አምለካችን አማኑኤል ይርዳን ብለን ስንወጥን እንዲህ ያሉ
ተግባራትን መፈፀም ከፈጣሪ፡ ቃል፡የተገባልን፡ መሆናችንን፡ እንረዳለን። በሰንበቴ ማህበራችን፡ ዙሪያ፡ ተሰባስበን
የምናደርገው፡ሁሉን አቀፍ አገልግሎት፡ የምናቀርበው፡ ጸበል፡ ጸዲቅ፡ በምጽአት፡ ቀን፡ በፍርድ፡ አደባባይ፡ ብራብ፡
አብልታችሁኛልና፡ ብጠማ፡ አጠጥታችሁኛልና፡ እናንተ፡ የአባቴ፡ ቡሩካን፡ ወደ፡ እኔ፡ ኑ፡ የሚል፡ የተስፋ፡ ድምጽ፡ የሠነቀ፡
ነው። በዚህም፡ መሰረት፡ እኛም፡ ይህንኑ፡ ፈለግ፡ በመከተል፡ የሰነበቴ ማህበራችንን፡ አቋቁመናል።

ከእግዚአብሔር፡ በተገነዘብነው እና በአቅማችን ልክ በአማኑኤል ረዳትነት በቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ልመና ሴንበቴ


ማህበራችንን፡ ያስፋልን። በጎ ሐሳባችንን ሁሉ ያሳካልን አሜን!!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል፡፡

3
በኢትዮጵያ፡ ኦርቶዶከስ፡ ተዋህዶ፡ ቤተክርስቲን፡ አዲስ፡አበባ ሀ/ስብከት

ን/ላ/ክፍለ ከተማ በፉሪ መካነ ቅዱሳን የደ/ምህረት ቅ/ሚካኤል ሰንበቴ፡


ማህበር መተዳደሪያ፡ ደንብ
አዲስ አበባ

አንቀጽ፡1. ስያሜና፡ አድራሻ

1.1 የማኀበሩ፡ ስም “የቅዱስ ሚካኤል ሰንበቴ፡ማህበር“(ከዚህ፡ በኋላ፡ “ሰንበቴው”) እየተባለ፡ ይጠራል።


1.2 የሰንበቴው፡ አድራሻ፡
በአዲሰ አበባ ን/ላ/ክ ወረዳ 15 ልዩ ስሙ ፉሪ አካባቢ ነው፡፡

አንቀጽ፡ 2. ዓላማ

2.1 ከአምላካችን፡ ባገኘነው፡ ጸጋና፡ በረከት፡ በአንድነት፡ በመሆን፡ በጸበል፡ ጸዲቅ፡ በመሳተፍ ምስጋና፡
ማቅረብ፤መንፈሳዊ ፀጋና ትጋት የሚገኙባቸውን ተግበራት ማከናወን

2.2 አቅም፡ በፈቀደ፡ ምግባረ፡ ሠናይ፡ ተግባሮችን፡ ለነዳያን፤ ለተቸገሩ፡ አብያተ ቤተክርስቲያናት፤ እንዲሁም፡
በቀጥታም ይሁን በትሩፋት፡ ድርጅቶች፡ በኩል ድጋፍ፡ ማድረግ፤

2.3 የኢትዮጵያ፡ ኦርቶዶክስ፡ ተዋህዶ፡ ሃይማኖትን፡ መጠበቅ፤ ማጠንከር፤ ለእድገትዋም፡ ያልተቆጠበ፡ ጥረት፡
ማድረግ፤

2.4 የኢትዮጵያ፡ ኦርቶዶክስ፡ ተዋህዶ፡ ሃይማኖት፡ ከትውልድ፡ ወደ፡ ትውልድ፡ እንዲሸጋገር፡ ማናቸውንም
አስፈላጊ፡ አስተዋጽኦ፡ ማድረግ፤

2.5 “ብራብ፡ አብልታችሁኛል፤ ብጠማ፡ አጠጥታችሁኛል፤ ብታመም፡ ጠይቃችሁኛል፤ ብታሰር፡

ጎብኝታችሁኛል፣ ብታረዝ፡ አልብሳችሁኛል? “ የሚለውን፡ አምላካዊ፡ ቃል፡ ምርኩዝ፡ በማድረግ፡በአባል፡

/አባል፡ ቤተሰብ፡ ላይ፡ በሚደርሱ፡ ማህበራዊ፡ ችግሮች፡ ላይ፡ ንቁ፡ ተሳትፎ ፡ (መጠየቅ፤ ማጽናናት፤

እንዲሁም፡ እንደ፡ አስፈላጊነቱ፡ ድጋፍና፡ ልግስና)፡ ማድረግ፤

አንቀጽ፡ 3. የአባልነት፡ መስፈርት

3.1 ማንኛውም፡ ዕድሜው፡ ከ 18 አመት፡ በላይ፡ የሆነ፡ የኢትዮጵያ፡ ኦርቶዶክስ፡ ተዋህዶ፡ ኃይማኖት፡ ዕምነት፡
ተከታይና፡ በፉሪ መካነ ቅዱሳን የደብረምህረት፡ ሊቀ መላዕከት ቅ/ሚካኤል፡ አጥቢያ ቤተክርስቲያን፡ ወቅታዊ፡ ሙሉ፡ አባል፡
የሆነ፤

4
3.2 በፉሪ መካነ ቅዱሳን የደብረ ምህረት፡ ሊቀ መላዕከት ቅ/ሚካኤል፡ ቤተክርስቲያን ፡የሰንበቴ ማህበርን፡ ደንብና፡
መመሪያ፡ አክብሮ፡ በማስከበር፡ ለተግባራዊነቱም፡ የሚተጋ፤
3.3 የሰንበቴ፡ ማህበሩ፡ የስራ፡ አመራር፡ በደንቡ፡ መሰረት፡ የሚሰጠውን፡ ትዕዛዝና፡ መመሪያ፡ ለመፈጸም፡
ሙሉ፡ ፈቃደኛ፡ የሆነ፤

3.4 የሰንበቴ፡ ማህበሩ፡ በማንኛውም፡ የስራ፡ ዘርፍ፡ ለማገልገል፡ ፈቃደኛ፡ የሆነ፡ ሁሉ፡ የማህበሩ፡ አባል፡
መሆን፡ ይችላል
አንቀጽ፡ 4. መብትና፡ግዴታ
4.1 መብት

ሀ. ማንኛውም፡ የሰንበቴው፡ አባል፡ በአመራርና፡ ልዩ፡ ልዩ፡ የስራ፡ ዘርፎች፡ ራሱንም፡ ሆነ፡ ሌሎችን፡
የመምረጥ፡ መብት፡ አለው።

ለ. ማንኛውም፡ አባል፡ ሰንበቴው፡ በሚያዘጋጀው፡ ጉባኤና፡ የጸበል፡ ጸዲቅ፡ ዝክር፡ ላይ፡ የመሳተፍ፡ መብት፡
አለው።

ሐ. ባልና፡ ሚስት፡ የሆኑ፡ አባላት፡ ከላይ፡ በአንቀጽ 3፡ ንዑስ፡ አንቀጽ 3.1፡ የተጠቀሱትን፡ መስፈርቶች፡ ያሟሉ፡
ሆነው፡ ከተገኙ፡ ለወርኃዊ፡ ክፍያና፡ ለሌሎችም፡ መዋጮዎች፡ እንደ፡ አንድ፡ አባል፡ ሆነው፡ የሚቆጠሩ፡
ሲሆን፡ ሌሎች፡ መብቶቻቸው፡ ግን፡ እንደግል፡ የተጠበቁ፡ ይሆናሉ።

4.2 ግዴታ

ሀ. እያንዳንዱ፡ አባል፡/የአባል፡ ቤተሰብ(ባል/ሚስት)፡ የሰንበቴው፡ ደንብ፡ የማክበርና፡ የማስከበር፡ ግዴታ፡


አለበት።

ለ. እያንዳንዱ፡ አባል፡ እንዲሁም፡ የአባል፡ ቤተሰብ(ባል/ሚስት)፡ ሰንበቴው፡ የመደበውን፡ ወርኃዊ፡ መዋጮ፡


በወቅቱ፡ መክፈል፡ ይጠበቅበታል።

ሐ. እያንዳንዱ፡ አባል/ አባል፡ ቤተሰብ(ባል/ሚሰት)፡ የሰንበቴው፡ አመራር፡ በሚያወጣው፡መርሃ፡ ግብር፡


መሰረት፡ የጸበል፡ ጸዲቅ፡ ዝክር፡ ማዘጋጀት፡ ይጠበቅበታል።

መ. በመርሃ፡ ግብሩ፡ መሰረት፡ አዘጋጅ፡ ቤተሰብ፡ የሰንበቴውን፡ አባላትና፡እንግዶቹን፡በሚጠበቀውና በሚገባው


አግባብ ማስተናገድ፡ ይጠበቅበታል።

ሠ. ወርኃዊ፡ መዋጮም፡ ሆነ፡ የጸበል፡ ጸዲቅ፡ዝክር፡ በወቅቱ፡ ያልከፈለ፡ ሌሎች ተግባራትንም ባግባቡ ካልተወጣ

በመጀመሪያ፡ በአመራሩ፡ ማስጠንቀቂያ፡ ከተሰጠው፡ በኋላ፡ ካልታረመ፡ በምክረ፡ ካህን፡ እንዲመከር፡ ሆኖ፡
ለውጥ፡ ካላሳየ፡ ከማህበሩ፡ እንዲሰናበት፡ ይደረጋል።

አንቀጽ 5. ክፍያ

5.1 መደበኛ፡ መዋጮ

ከላይ፡ በአንቀጽ፡ 2፡ የተዘረዘሩትን፡ ምግባረ፡ ሠናይ፡ ተግባሮች፡ ለማከናወን፡ የገንዘብ፡ መዋጮ፡ አስፈላጊ፡
ስለሆነ፡ አባላት፡ በየወሩ፡ የብር-------(---------------------------------) ወቅታዊ፡ መዋጮ፡ ማድረግ፡
ይጠበቅባቸዋል። ይህንኑም፡ እንደአመችነቱ፡ የ 3 ወር፤ የ 6 ወር፤ ወይም፡ የአመቱን፡ ባንድ፡ ጊዜ፡ መክፈል፡

5
ለማህበሩ፡ ሥራ፡ ቅልጥፍና፡ ከፍተኛ፡ አስተዋጽኦ፡ ስለሚኖረው፡ የተጠቃለለ/ በከፊል፡ የተጠቃለለ፡ ክፍያ፡
እንዲኖር፡ ማህበሩ፡ ያበረታታል።

5.2 ልዩ፡ መዋጮ

ሰንበቴው፡ አጣዳፊና፡አስቸኳይ፡ተግባሮችን፡ ለማከናወን፡ ከመደበኛው፡ክፍያ፡በተጨማሪ፡ ገንዘብ፡


ሲያስፈልገው፡ በአባላት፡ ፈቃድ፡ የሚወሰንና፡ በተመደበለት፡ የጊዜ፡ ሠሌዳ፡ የሚከፈል፡ መዋጮ፡ ሊጠይቅ፡
ይችላል። ልዩ፡ መዋጮ፡ ለመወሰን፡ የአባላት፡ ብዛት፡ ከጠቅላላው፡ አባላት፡ ከግማሽ፡ በላይ፡ መሆን፡ አለበት።
በዚህም፡ የአብላጫ፡ ድምጽ፡ የተሰጠበት፡ ውሳኔ፡ የጸና፡ ይሆናል።

5.3 አስራት፡ በኩራት፡

በቤተክራስቲያን፡ ሥርዓት፡ መሰረት፡ እያንዳንዱ፡ የእምነት፡ ተከታይ፡ ከሚያገኘው፡ ማንኛውም፡ ገቢ፡ ላይ፡
አስራት፡ በኩራት፡ ማውጣት፡ ግዴታውና የሚጠበቅበት ነው። በሚልኪያስ፡ ም 3 ቁ 10 እንደተጻፈው፡ “
በቤቴ፡ ውስጥ፡ መብል፡ እንዲሆን፡ አስራቱን፡ ሁሉ፡ ወደ፡ ጎተራ፡ አግቡ፤ የሰማይንም፡ መስኮት፡
ባልከፍትላችሁ፤ በረከትንም፡ አትረፍርፌ፡ ባላፈስስላችሁ፡ በዚሁ፡ ፈትኑኝ፡ ይላል፡ የሰራዊት፡ ጌታ፡ እግዚአብሔር”፡
በሚለው፡ አምላካዊ፡ መርህ፡ መሰረት፡ እያንዳንዱ፡ አባል፡ ለቤተክርስቲያን እነዲያስገባ ሰንበቴው ያበረታታል።
ማንኛውም የሰንበቴ ማህበሩ መዋጮ ለተሩፋት በመሆኑ ከአሥራት ውጪ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡

አንቀጽ፡ 6. ከአባልነት፡ ስለመወገድ

6.1.አንድ፡ አባል፡/ አባል፡ ቤተሰብ (ባለትዳር) ፡ የሰንበቴውን፡ ሕገ፡ ደንብ፡የተላለፈ፤ ያላከበረ፤ እንዲሁም፡ ግዴታውን፡
ለመወጣት፡ ያልቻለ፡ ከሆነ፡ በቅድሚያ፡ በአመራር፡ አካላት፡ የእርምት፡ ማስጠንቀቂያ፡ ተሰጥቶት፡ በተሰጠው፡ ጊዜ፡
ገደብ፡ ውስጥ፡ ካልተሻሻለ፡ እንዲሁም፡ በምክረ-ካህን፡ ምክር፡ ተሰጥቶት፡ ካልተለወጠ፡ ከማህበሩ፡ በይፋ፡ ይለያል።

6.2. አንድ፡ አባል/ አባል፡ቤተሰብ፡ በራሱ፡ ፈቃድ፡ ወይም፡ በጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ ወይም፡ በሥራ፡ አመራሩና፡ በዝክረ፡ ካህኑ፡ ውሳኔ፡
ከአባልነት፡ ከተለየ፡ እስከዚያን፡ ጊዜ፡ ድረስ፡ ያዋጣው፡ መዋጮ፡ ወይንም፡ በማህበሩ፡ ስም፡ ከተቀመጠው፡ ገንዘብ፡
ምንም፡ ዓይነት፡ ክፍያ፡ መጠየቅ፡ አይችልም።

አንቀጽ 7. የማህበሩ፡ የአሰራር አደረጀጀት፡

7.1 የሥራ አደረጃጀት፡ መዋቅር

ሀ. መንፈሳዊ ሰበካ ጉባኤ

ለ. የሰንበቴው፡ ጠቅላላ፡ ጉባኤ /ሁሉም የሰንበቴው አባላት /

ሐ. የሰንበቴው ፡ሥራ፡ አመራር፡ ኮሚቴ

6
7.2. ሰንበቴው ተጠሪነቱ ለመንፈሳዊ ሰበካ ጉበኤ ይሆናል

7.3 የሰንበቴው፡ ጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ ተግባርና፡ ኃላፊነት

ሀ. የሰንበቴው፡ 50% + 1፡ አባላት፡ የተገኙበትና፡ ዓቢይ፡ ጉዳዮችን፡ ለመወሰን፡የሥራ፡ አመራሩ፡የጠራው፡ስብሰባ፡ የጠቅላላ፡


ጉባኤ፡ ሥብሰባ፡ ይሆናል።

ለ. የሰንበቴው ጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ የሥራ፡ አመራር፡ ኮሚቴ፡ አባላትን፡ ይሾማል፤ ይሽራል።

ሐ. የሰንበቴው፡ ጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ የሥራ፡ አመራር፡ ኮሚቴውን፡ ዓመታዊ/ ወቅታዊ፡ ሪፖርት፡ ያዳምጣል፤
ያጸድቃል፤ እንደአስፈላጊነቱም፡ ውሳኔ፡ ይሰጥበታል።

መ. የሰንበቴው፡ መደበኛ፡ የጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ ስብሰባ፡ በአመቱ፡ መጨረሻ፡ በአመት፡ አንድ፡ ጊዜ፡ ይደረጋል።

አስፈላጊ፡ ሆኖ፡ ሲገኝም፡ የሰንበቴው፡ ሥራ፡ አመራር፡ ወቅታዊና፡ አጣዳፊ፡ ጉዳዮች፡ ሲያጋጥሙት፡ ልዩ፡
የጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ ስብሰባ፡ ሊጠራ፡ ይችላል።

ሠ. ለመደበኛም፡ ሆነ፡ ለልዩ፡ የሰንበቴው ጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ ስብሰባ፡ ግዴታቸውን፡ ካሟሉ፡ አባላት፡

መካከል፡50% + 1፡ በላይ፡ የሆኑት፡ ከተገኙ፡ ምልዓተ፡ ጉባኤ፡ ይሆናል።

ረ. ይህን፡ የሰንበቴውን፡ መተዳደሪያ፡ ደንብ፡ አንቀጾች፡ ለማሻሻል፡ ሲያስፈልግ፡ በምልዓተ፡ ጉባኤው፡ ከተገኙት፡

መካከል፡ 66% እና ከዚያ፡ በላይ፡ ድምጽ፡በመስጠት፡ ከደገፉት፡አንቀጹ/ አንቀጾቹ፡ ሊሻሻሉ፡ወይም፡

ሊሰረዙ፡ ይችላሉ።

ሸ. ሰንበቴውን፡ ለማፍረስ፡ በሚፈለግበት፡ ጊዜ፡ ግዴታቸውን፡ላጠናቀቁትና፡ ለዚሁ፡ ተብሎ፡ በተጠራው፡ ምልዓተ፡

ጉባኤ፡ በተገኙበት፡ የጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ አባላት፡ ከ 75% እና፡ በላይ፡ ሲደግፉ፡ብቻ፡ ሰንበቴው፡ ሊፈርስ፡

ይችላል። በዚህን፡ ወቅት፡ በእጅ፡ ያለ፡ንብረትና፡ገንዘብ፡ በመካነ-ቅዱሳን ለፉሪ፡ ደብረ፡ ምህረት፡ ቅዱስ

ሚካኤል አጥቢያ ቤተክርስቲያን፡ ገቢ፡ የሚደረግ፡ ሲሆን፡ ለአባላት፡ የሚከፋፈል፡ ወይም፡ የሚመለስ፡
ንብረትም፡ ሆነ፡ ገንዘብ፡ አይኖርም።

7.3 የሥራ፡ አመራር፡ ኮሚቴ


1. ሙሴ( ሊቀመንበር)

2. ም/ል ሙሴ (ጸሐፊ)

3. ገንዘብ፡ ያዥ

7
ሀ. ጠቅላላ

1. የሰንበቴው፡ ሥራ፡ አመራር፡ ኮሚቴ፡ በጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ የተመረጡ፡ ከ 3-5፡ አባላት፡ ይኖሩታል።

2. የሰንበቴው፡ ሥራ፡ አመራር፡ የሥራ፡ ዘመን፡ 2 አመት፡ ይሆናል። ሆኖም፡ የስራ፡ አመራሩ፡

በአገልግሎቱ፡ እንዲቀጥል፡ ከተጠየቀና፡ የጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ ድጋፍ፡ ካገኘ፡ ለሁለተኛ፡ የሥራ፡ ዘመን፡
ብቻ አገልግሎት፡ ሊሰጥ፡ ይችላል። ነገር፡ ግን፡ በአገልግሎቱ፡ ለመቀጠል፡ ፈቃደኛ፡ ያልሆነ፡ የሥራ፡
አመራር፡ አባል፡ ካለ፡ እንዲቀጥል፡አይገደድም። በምትኩ፡ ሌላ፡ አባል፡ ሊመረጥ፡ ይችላል።

3. የሰንበቴው፡ ሥራ፡ አመራር፡ የሥራ፡ ድልድል፡ በጠቅላላ፡ ጉባኤው፡ ይወሰናል።

4. የሰንበቴው፡ ሥራ፡ አመራር፡ መደበኛ፡ ወይም፡ ልዩ፡ ጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ እንዲጠራ፡ በድምጽ፡ ብልጫ፡
ሲወሰን፡የጉባኤውን፡ ቀን፤ ቦታና፤ ሠዓት፡ ወስኖ፡ ለአባላት፡ ቢያንስ፡ ከአንድ፡ ወር፡ በፊት፡ ያስታውቃል።

5. ከአባላት፡ መካከል፡ 20% የሚሆኑ፡ አባላት፡ልዩ፡ የጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ እንዲጠራላቸው፡ ፔቲሽን፡

ሲያቀርቡ፡ ፔቲሽኑ፡ በቀረበ፡ በ 30፡ ቀናት፡ ውስጥ፡ አመራሩ፡ ልዩ፡ የጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ መጥራት፡

አለበት። የ 30 ቀኑ፡

የጊዜ፡ ገደብ፡ ካለፈ፡ ፔቲሽን፡ የፈረሙት፡ ስብሰባውን፡ የመጥራት፡ መብትና፡ በዚያ፡ ስብሰባ፡
ምልዓተ፡ ጉባኤ፡ መሙላቱ፡ ከተረጋገጠ፡ በጉባኤው፡ የሚወሰኑትን፡ ውሳኔዎች፡ አመራሩ፡
ተግባራዊ፡ የማድረግ፡ ግዴታ፡ አለበት።

6. ባልና፡ ሚስት፡ በአመራር፡ ውስጥ፡ በአንድነት፡ ሊያገለግሉ፡


አይችሉም።
ለ. የሰንበቴው፡ ሥራ፡ አመራር፡ ኮሚቴ፡ ግባርና፡ኃላፊነት

1. ለሰንበቴው ማንኛውንም ሥራ ማከናወኛ ከአባላት የሚሰብሰብ ገንዘብ ማስቀመጫ በሰንበቴው


ስም/ወይንም በሶስቱ ሥራ አስፈጻሚ አባለት ማለትም ዋና ሙሴ፣ምክትል ሙሴ እና ፀሐፊ ስም
ይከፍታል፡፡
2. ለሰንበቴው ወርሃዊ/ሳምነታው የጸበል፡ ጸዲቅ፡ ዝክር፡ መርሃ፡ ግብር፡እንዲሁም ለሌሎች አገልገሎቶች
ማከናወኛ ወጪዎች የሚሆን ከአባላት መዋጮ ይሰበስባል ለሰንበተው በተከፈተው አካውንት በሦስት ቀን
ውስጥ ገቢ ያደርጋል፡፡
3. ከሰበካጉባኤ ጋር በመተባበር ሰንበቴው ዝክር የሚያከናውንበትን ቦታ ይወስናል ለአባላት ያሳውቃል፡፡
4. የሰንበቴውን፡ ወርሃዊ/ሳምንታዊ፡ የጸበል፡ ጸዲቅ፡ ዝክር፡ መርሃ፡ ግብር፡ ያወጣል። ያሳውቃል። በወቅቱ፡
መፈጸሙንም፡ ያረጋግጣል።

5. ስብሰባዎችን፡ በመንፈሳዊ፡ የስብሰባ፡ ደንብ፡ መሰረት፡ ይመራል።

8
3. የጸበል፡ ጸዲቅ፡ ዝግጅትና፡ መስተንግዶ፡ በሥርአት፡ መካሄዱን፡ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል።

4. የስብከተ፡ ወንጌል፡ የመዝሙር፡ አገልግሎት፡ በዝክሩ፡ ወቅት፡ እንዲከናወን፡ ይከታተላል። ያስተባብራል።

5. መንፈሳዊ፡ ጉዞ፡ ያቅዳል፤ያስተባብራል፣ ያደራጃል፡፡

6. ሰንቤተው የተመሠረተበትን ዓመታዊ በዓል በተለየ ሁኔታ አንዲከበር ያስተባብራል ያደራጃል ይመራል

7. የማህበሩ፡ አባላት፡ በየዝክሩ፡ ቀን፡ መገኘታቸውን፡ ይቆጣጠራል። ባልተገኙት፡ላይ፡ በሰንበቴ፡ ማህበሩ፡ ሕገ፡
ደንብ፡ መሰረት፡ ተገቢውን፡ እርምጃ፡ ይወስዳል።

ሐ የሰንበቴው፡ ሥራ፡ አመራር፡ ኃላፊዎች፡ ተግባርና፡ ኃላፊነት፡

1 ዋና ሙሴ (ሊቀመንበር)

1.1 የዝክር፡ ቀን፡ ፕሮግራሞችና፡ ስብሰባዎችን፡ በስርአት፡ ይመራል።


1. 2 በተለያዩ፡ ስብሰባዎች፡ የሥራ፡ ግብዣዎችና፡ ማህበራዊ፡ ግንኙነቶች፡ ላይ፡ሰንበቴውን
በመወከል፡ ይገኛል፡ ወይም፡ ሌሎች፡ እንዲወክሉት፡ ያደርጋል።
1.3 በጠቅላላ ጉባኤ የፀደቁ ተግባራትን ለማከናወን ከገንዘብ፡ ያዢው፡ ጋር፡ በመሆን፡ የማህበሩን፡ ሂሳብ/ ገንዘብ፡
ያንቀሳቅሳል።
1.4 ከማህበሩ፡ ወጪ፡ የሚሆኑ፡ ደብዳቤዎችና፡ ማስታወቂያዎች፡ ላይ፡ ፈርሞ፡ እንዲሰራጭ፡ ያደርጋል።

2 ምክትል ሙሴ
2.1. ዋና ሙሴ በሌለበት ጊዜ ዋና ሙሴውን ተክቶ ሁሉንም የዋና ሙሴውን ተግባራት ያከናውናል
2.2. የዝክር፡ ቀን፡ ፕሮግራሞችና፡ ስብሰባዎችን፡ በስርአት፡ ይመራል።
2.3. በተለያዩ፡ ስብሰባዎች፡ የሥራ፡ ግብዣዎችና፡ ማህበራዊ፡ ግንኙነቶች፡ ላይ፡ሰንበቴውን በመወከል፡ ይገኛል፡
ወይም፡ ሌሎች፡ እንዲወክሉት፡ ያደርጋል።
2.4. በጠቅላላ ጉባኤ የፀደቁ ተግባራትን ለማከናወን ከገንዘብ፡ ያዢው፡ ጋር፡ በመሆን፡ የማህበሩን፡ ሂሳብ/ ገንዘብ፡
ያንቀሳቅሳል።
2.5. ከማህበሩ፡ ወጪ፡ የሚሆኑ፡ ደብዳቤዎችና፡ ማስታወቂያዎች፡ ላይ፡ ፈርሞ፡ እንዲሰራጭ፡ ያደርጋል።

3 ግልገል ሙሴ( ጸሐፊ)


3.1 የስብሰባ፡ ቃለጉባኤዎችን፡ ይይዛል።
3.2 ከሙሴው፡ ጋር፡ በመነጋገርና፡ በሚሰጠው፡ መመሪያ፡ መሰረት፡ የስብሰባ፡ አጀንዳዎችን፡ ያዘጋጃል።
3.3 ሰንበቴ ማህበሩን፡ ፋይሎች፡ በሚገባ፡ ያደራጃል። የአባላትንም፡ ስምና፡ አድራሻ፡ በመዝገብ፡ ይይዛል።
3.4 ደብዳቤዎችን፡ አዘጋጅቶ፡ በሙሴው፡ ከተፈረመ፡ በኋላ፡ ወጪ፡ ያደርጋል።
3.5 በጸበል፡ ጸዲቅ፡ ዝክር፡ ቀን፡ ለዝግጅቱ፡ አስፈላጊ፡ የሆኑት፡ ቁሳቁስ፡ ጽዋ፤ድምጽ
ማጉያ፤ጠረጴዛና፡ ወንበር፤ ከበሮ፡ መሟላታቸውን፡ ያስተባብራል። ይመራል። ይቆጣጠራል።
3.6 ሙሴው፡ በሌለበት፡ ጊዜ፡ እሱን፡ ተክቶ፡ ይሰራል።
3. ገንዘብ፡ ያዥ

3.1 ከአባላት፡ የሚሰበሰቡ፡ ክፍያዎች/ መዋጮዎችን፡ ይሰበስባል። በማህበሩ፡ የባንክ፡ ሂሳብ፡


ውስጥ፡ በ 3 ቀናት፡ ጊዜ፡ ባንክ፡ ገቢ፡ ያደርጋል።

9
3.2 በሂሳብ፡ አያያዝ፡ ደንብ፡ መሰረት፡ የሂሳብ፡ መዛግብት፡ ያዘጋጃል፤ይመዘግባል፤ ባንክ፡ ካለው፡ ሂሳብ፡ ጋር፡
መመሳከሩንም፡ በየጊዜው፡ ይቆጣጠራል።

3.3 ማንኛውም፡ ወጪ/ ክፍያ፡ ተገቢው የክፍያ ሰነዶች መዘጋጀታቸውን እና እንደ አስፈላጊነቱም በቼክ፡
የሚፈፀሙትን ትክክለኝነት ያረጋግጣል።

3.4 ከሙሴው፡( ሙሴው፡ ከሌለ፡ ከም/ል፡ ሙሴው፡ ) ጋር፡ በመሆን፡ ገንዘብ፡ ወጪ፡ ያደርጋል።

3.5 ለጥቃቅን፡ ወጪዎች፡ የተመደበውን፡ እና በጠቅላላ ጉባኤ ተወሰነውን መጠን (petty cash) ጥሬ፡ ገንዘብ፡
ይይዛል። በሙሴው፡ ሲፈቀድም፡ ወጪ፡ ያደርጋል። የወጪ፡ ሰነዶችንም፡ በማሰባሰብ፡ ምትክ፡ ገንዘብ፡ ከባንክ፡
እንዲተካለት፡ ያደርጋል።
3.6 የገንዘብ፡ ገቢና፡ ወጪ፡ ሪፖርት፡ በየ 6 ወሩ፡ ለሰንበቴው ሥራ፡ አመራር፡ ኮሚቴ፤ በየአመቱ፡ ለጠቅላላ፡ ጉባኤ፡
ሪፖርት፡ ያቀርባል።
4. የቁጥጥር፡ ኮሚቴ
4.1 እንደአስፈላጊነቱ፡ ሶስት፡ አባላት፡ ያሉት፡ የቁጥጥር፡ ቡድን፡ (ደርገ ሙሴ) በጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ ይመረጣል።
ተጠሪነቱም፡ ለጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ ይሆናል።
4.2 የሰንበቴ፡ ማህበሩን፡ የአስተዳደርና፡ ፋይናንስ፡ አያያዝ፡ በሕግ፡ ደንቡ፡ መሰረት፡ ትክክለኛ፡
መሆኑን፡ ይመረምራል፤ይቆጣጠራል። በጠቅላላ፡ ጉባኤ፡ ስብሰባ፡ ላይም፡ ሪፖርት፡ ያቀርባል፡፡

አንቀጽ 8. መተዳደሪያ፡ ደንቡ፡ የሚጸናበት፡ ጊዜ

ይህ፡ መተዳደሪያ፡ ደንብ፡በአባላት፡ ሙሉ፡ፈቃድና፡ ፊርማ፡ተረጋግጦ፡ ለሰበካ ጉበኤ ቀርቦ ታይቶና ተመርምሮና
ፀድቆ ከጥቅምት 2015 ዓ.ም. ጀምሮ፡ በሕግ፡ የጸና፡ ይሆኗል።

10

You might also like