You are on page 1of 1

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን

የፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና ቅ ሚካኤል ሰበካ


መንፈሳዊ ጉባኤ
የንብረት በጨረታ ክንውን ሂደት
በፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
የንብረት በጨረታ የመሽጥ ሂደት እንዴት መከናወን እንዳለበት የሚያሰይ ጥናት ለማደረግ
በተሰጠን ኃላፊነት መሠረት ከሰበካ ጽ/ቤቱ ዋና ጸኃፊ፣ ንብረት ክፍል፣ ሂሳብ ክፍል እና
ኦዲት ክፍል መረጃዎችን ለማጠናቀር ጥረት ተደርጓል። በዚህም መሠረት ከዚህ በፊት
የተከናወኑ ጨረታዎች ሂደት ምን ይመስል እንደነበር፣ የተሸጡ ንብረቶች እና የተሸጡበት
ዋጋ የሚገልጹ መረጃዎችን ለማየት ተችሏል። ይህንን መሠረት በማድረግ የንብረት ጨረታ
አሻሻጥ ሂደቱ የሚከነወንበት ለውይይት የሚሆን መነሻ ሀሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል፤

1. የሚሽጠው ንብረት አይነት እና ብዛት ተለይቶና ተዘርዝሮ፤ ንብረቱ የሚገኝበት


አጥቢያና ጨረታው ዕለት ተገልጾ የጨረታ ሰነድ በቁጥር ተወስኖ ይዘጋጃል።
2. በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የጨረታ ሰነድ ተከታታይ ቁጥር ተሰጥቶት የጨረታ
ኮሚቴ አባላት ይፈርሙበታል የሰበካ ጽ/ቤቱ ማህተም ይደረግበታል።
3. የሚሽጠው ንብረት የሚገኝበት አጥቢያና ጨረታው የዕለት ተገልጾ የጨረታ
ማስታወቂያ ይወጣ እና አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች ይለጠፋል።
4. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በሚቀመጥለት ጊዜ ገደብ ውስጥ እና በተተመነለት ዋጋ
ይሸጣል።
5. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በዝርዝር የተቀመጡትን ንብረቶች የሚገዙበትን
ዋጋ ሞልተው እና ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝ ቅጅ አየዘይዘው ከአንድ ቀን በፊት
ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ።
6. በዚሁ ዕለት የጨረታ ኮሚቴው ሳጥኑን በመክፈት እና በተጫራቾት ተሞልቶ
የቀረበውን ሰነድ በመከለስ ለጨረታ ለቀረቡት እቃዎች በተለያዩ ተጫራቾች
የተሰጠውን ከፍተኛ ዋጋ በመልቀም የመነሻ ዋጋ በማድረግ ዝርዝር አዘጋጅቶ
ጨረታው በሚከናወንበት ለእይታ በሚያመች ቦታ ላይ እንዲለጠፍ ያደርጋል።
7. በጨረታው ዕለት የሚሽጠው ንብረት አይነት ናሙናዎች ለተጫራቾች እይታ
በሚያመች ቦታላይ ተጫራቾች እንዲያዩአቸው ይደረጋል።
8. የቀረበውን የጨረታ መነሻ ዋጋ በመንተራስ የሚሽጠው ንብረት ላይ ግልጽ ጨረታ
ይከናወናል።
9. ለቀረበው ጨረታ ከ1 እስከ ሶስት ከፍተኛ ዋጋ የሰጡ ተጫራቾች ስም ዝርዝር
እና የሰጡትየጨረታ ማሸነፊያ ዋጋ ተመዝግቦ ይያዛል።
10. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች ወዲያውኑ በዕለቱ ጨረታው ሳይበተን ጠቅላላ
ከፍሎ ንብረቱን ያነሳል፤ ጨረታው ሳይበተን ጠቅላላ ዋጋውን መክፈል የማይ
ችልበት ሁኔታ ከተፈጠረ ቀጣዮ ከፍተኛ ዋጋ የቀረበው ተጫራች የመግዛት ዕድሉ
ይሰጠዋል፤ ሁለተኛው ካልቻለ ለሶስተኛ የመግዛት ዕድሉ ይተላለፋል፤ ሶስኛው
ካልቻለ ጨረታው እንዲተላለፍ ይደረጋል።
11. በመጨረሻ የጨረታ ቃለ ጉባኤ በሶስት ቅጅ ተዘጋጅቶ እና በኮሚቴው አባላት
ተፈርሞ በንብረት ክፍል በመዝገብ ቤት እና ከጨረታው ገቢ ሰነድ ጋር ተያይዞ
እንዲቀመጥ ይደረጋል።

You might also like