You are on page 1of 5

በሪል-ፕሮፐርቲ ግብይት ግመታና ፈቃድ መሪ ሥራ አስፈጸሚ እንዲከናወኑ በሲቨል

ሰርቪስ ኮምሽን የጸደቁ ዝርዝር ስራዎች፡-

1) በሀገር አቀፍ ደረጃ በወቅታዊነት የሪል ፕሮፐርቲ ግመታ፣ግብይት እና የፈቃድ አሰጣጥ


ጥናት እንዲከናወን ማድረግ፤
 የሪል ፕሮፐርቲ ግመታ የህግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ጥናት ማድረግ፣ የፀደቁ የህግ ማዕቀፎች

አተገባበር ጥናት በማድረግ ማሻሻያዎችን ማድረግ፡፡

 የሪል ፕሮፐርቲ ገበያ አቅርቦት እና ፍላጎት፣ የግብይት ፕላትፎርም አፈጻጸም፣ የባለድርሻዎች

ግንኙነት፣ጉድለቶች እና ጥንካሬዎች፣ የገበያ ዋጋዎች ለውጥ፣ የገበያ ጉድለት የሚያቃኑ የህግ

ማዕቀፍ ዝግጅት፣የገበያ የህግ ማዕቀፍ አተገባበር ጥናት ማድረግ፡፡

 የሪል ፕሮፐርቲ ግመታ ባለሙያዎች፣ የእርግጥ ንብረት ግብይት ባለሙያዎች እና ለሪልስቴት

አልሚዎች የሙያ ብቃት ማሳደጊያ ማረጋገጫ ስርዓት ጥናት ማድረግ፡፡

 የሪል ፕሮፐርቲ ግብይት ባለሙያዎች፣ የእርግጥ ንብረት ግመታ ባለሙያዎች እና የሪልስቴት

አልሚዎች ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ የሚሰጥበት አሰራር ጥናት ማድረግ፡፡

 የሪል ፕሮፐርቲ ገማቾች፣የእርግጥ ንብረት ግብይት አገበያዮች፣ ደላላዎች፣ ኤጀንቶች እና

የሪልስቴት አልሚዎች ደረጃ የሚወሰንበት አሰራር ጥናት ማድረግ፡፡

 በሪል ፕሮፐርቲ ግመታ ላይ የተሰማሩ ገማቾች፣ በእርግጥ ንብረት ገበያ ላይ የተሰማሩ

አገበያዮች፣ ደላላዎች፣ አስተላላፊዎች እና የሪልስቴት አልሚዎች ደረጃ ከፍ የሚሉበት፣ ከደረጃ

ዝቅ የሚሉበት እና የሚሰረዙበት አሰራር ጥናት ማድረግ፡፡

 የሪል ፕሮፐርቲ ግመታ ገማቾች፣ የእርግጥ ንብረት ግብይት አገናኞችና አስተላላፊዎች እና

የሪልስቴት አልሚዎች የስነምግባር ደንብ አተገባባር ጥናት ማካሄድ፡፡


2) የሪል ፕሮፐርቲ ግብይት፤ ግመታ እና የባለሙያዎች ፈቃድ አሰጣጥ ሚመራበት የህግ
ማዕቀፍ ማዘጋጀት፤
 የሪል ፕሮፐርቲ ግመታ አሰራር፣የእርግጥ ንብረት ገበያ ጉድለት የሚያቃኑ፣የእርግጥ ንብረት

ገበያ አቅርቦትና ፍላጎት የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት፡፡

 የሪል ፕሮፐርቲ ግመታ ባለሙያዎች፣የእርግጥ ንብረት ግብይት ባለሙያዎች እና ለሪልስቴት

አልሚዎች የሙያ ብቃት ማሳደጊያ ማረጋገጫ የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት፡፡


 የሪል ፕሮፐርቲ ግብይት አገበያዮችና አስተላላፊዎች፣የእርግጥ ንብረት ግመታ ገማቾች እና

የሪልስቴት አልሚዎች የሙያ ፈቃድ የሚሰጥበት የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት፡፡

 የሪል ፕሮፐርቲ ገማቾች፣የእርግጥ ንብረት ግብይት አገበያዮች፣ደላላዎች፣ኤጀንቶች እና

የሪልስቴት አልሚዎች ደረጃ የሚወሰንበት የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት፡፡

 በሪል ፕሮፐርቲ ግመታ ላይ የተሰማሩ ገማቾች፣በእርግጥ ንብረት ገበያ ላይ የተሰማሩ

አገበያዮች፣ደላላዎች፣ አስተላላፊዎች እና የሪልስቴት አልሚዎች ደረጃ ከፍ የሚሉበት፣ ከደረጃ

ዝቅ የሚሉበት እና የሚሰረዙበት የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት፡፡

 የሪል ፕሮፐርቲ ግመታ ገማቾች፣የእርግጥ ንብረት ግብይት አገናኞችና አስተላላፊዎች እና

የሪልስቴት አልሚዎች የስነምግባር ደንብ ማዘጋጀት፡፡

 ሀገር አቀፍ የካሳ ቀመርና የልማት አካታችነት የሚመራበት የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት፡፡

 የመሬት የመጠቀም መብት በማጣቱ ምክነያት የሚያጋጥም የገቢ መቀነስ ካሳ ክፍያ ቀመር

የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት፡፡

 አገር አቀፍ የልማት ቦታ ነባር ተጠቃሚዎች የንብረት ግምት እና የህይዎት ለውጥ ድጋፍ ህግ

ማዕቀፍ ማዘጋጀት፡፡

 የተፈጠረዉን የግብይት ፕላትፎርም የሪል እስቴት ገዢ እና ሻጭ እንዲጠቀሙበት እና ወደ

ስርአቱ እንዲገቡ የሚያስችል መመሪያ ማዘጋጀት፡፡


3) የከተማ ቦታ ደረጃና እና የሪል ፕሮፐርቲ እሴት እርከኖች መወሰኛ መስፈርት እንዲዘጋጅ
ማድረግ፤

 የተዘጋጀዉን የከተሞች ፈርጅ መሰረት ያደረገ እሴት እርከኖች መወሰኛ መስፈርት

ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር የዉይይት ውይይት በማድረግ፣ በዉይይቱ የተገኙ

ግብአቶች እንዲካተት እና እንዲሻሻል ማድረግ፡፡

 በተዘጋጀዉ የከተሞ ፈርጅ መወሰኛ መስፈርት የተዘጋጀውን የሪል ፕሮፐርቲ እሴት

እርከኖች መወሰኛ መስፈርት ለክልሎች እንዲሰራጭ ማድረግ፡፡

 ክልሎች በሚያወጡት መስፈርት ከተሞች እንደተሰጣቸው ፈርጅ እና እያንዳንዱ አካባቢ

እንዳአለው የሪል ፕሮፐርቲ ዋጋ ልዩነት የከተማቸውን የቦታ ደረጃ እንዲያወጡ

ከሚመለከታቸዉ አመራሮች ጋር በቅርበት ማወያየት፣ ድጋፍ ማድረግ ፣ በአግባቡ


ተግባራዊ መደረጋቸውን በሚመለከታቸዉ ባለሙያዎች መገምገም፣ በቀረበዉ

የግብረመልስ ሪፖርት መሰረት ለባለድርሻ አካላት ማሳወቅ፡፡

 ለክልሎች የተዘጋጀዉን የቦታ ደረጃ ሰንጠረዥ እና ካርታ ለህዝብ ግልጽ የሚደረግበትን

የአሰራር ስልቶች በመንደፍ ፤ ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ፡፡

 የአዲስ አበባና ድሬድዋ ከተሞች ፍረጃና የቦታ ደረጃ መስፈርት በተለየ ሁኔታ

የሚዘጋጅበትን መስፈርት እንዲወጣ በማድረገ የከተማ መስተዳድር አካላት ማወየየት፣

በሚነስትሪዉ በበላይ አመራሮች በማስተቸት ፣ ይሁንታ እንዲያገኝ እና እንዲጸድቅ

ማድረግ፣ ለተግበራዉ አስፈላጊዉን ድጋፍና ክትትል ማድረግ፡፡

 በየስድስት ወሩ የተከለሱ የከተሞች መወሰኛ መስፈርቶች በክልሎች እና በከተሞች

ወቅታዊ እንዲደረግ ማድረግ፣ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፡


4) በሀገር አቀፍ ደረጃ ዘመናዊ የሪል ፕሮፐርቲ ግብይት ኦበዘረቫቶሪ ስርአት እንዲዘረጋ
ማድረግ፤

 በየስድስት ወሩ የገበያ ጥናት በማካሔድ ክልላዊ የገበያ ጠቋሚዎችን የሚያጠቃልልና

የሚተነትን የሪልስቴት ገበያ ጠቋሚ አማካኝ ግምት እንዲታተም ማድረግ፡፡

 ህገ-ወጥ(ኢ-መደበኛ) የሆነ የሪል ፕሮፐርቲ ግብይት ግልጽነት መጥፋት ለመፍታት

የእርግጥ ንብርት ተገበያዮች የሚገበያዩበት ወጥ ፕላትፎርም እንደገበያው ባህሪ(ለኪራይ

በከተማ ደረጃ፤ለሽያጭ በአገር አቀፍ ደረጃ) በቴክኖሎጅ የተደገፈ ሻጭ እና ገዥ፣ አከራይ

እና ተከራይ የሚገናኙበት በቨርቹዋል ገበያ እንዲደራጅ ማድረግ፡፡

 የሪል ፕሮፐርቲ የግብይት ዋጋ (የኪራይ እና የሽያጭ) ለህዝብ እና ለመንግስት ግልጽ

እንዲሆን የሚያስችል አሰራር እንዲዘረጋ ማድረግ፡፡

 በተገበያዮች መካከል የሚነሳ አለመግባባት የሚፈቱበት ስርዓት እንዲዘረጋ ማድረግ፡፡

 በሪልስቴት ህግ መሰረት የቤት ገዥዎች ማህበርን በማሳተፍ አልሚው ለግንባታ

እንዲጠቀምበት የተለቀቀለትን ገንዘብ በአግባቡ ስራ ላይ ማዋሉን ማረጋገጥ፡፡

 የሪል ስቴት ልማትና ግብይት ውስጥ ህጋዊነትን የተከተለ የገንዘብ ዝውውር እንዲኖር

አስቻይ ሁኔታዎች እንዲሟሉ ማድረግ፡፡


 የሪልስቴት አልሚ ቤቱን ሳይገነባ ለፈላጊዎች በቅድሚያ በሚሸጥበት ወቅት የአልሚውን

እና የቤት ገዥዉን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ እና የሚገጥሟቸዉን ስጋቶች ለመቀነስ

የሚያስችል የዋስትና ስርዓት እንዲዘረጋ ማድረግ፡፡

 ከባንኮች፤ ከዉል እና ማስረጃ ተቋማት ፤ ከመሬት እና ካዳስተር፣ ከቤቶች ልማት እና

ከሪል እስቴት አልሚዎች እና አስተላላፊዎች ወቅታዊ የእርግጥ ንብረት ግብይት መረጃ እና

የገንዘብ ዝዉዉር መረጃ ልዉዉጥ ሂደቱን የተሣለጠ እንዲሆን የመግባቢያ ሰነድ

መፈራርም፡፡
5) በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ የሪል ፕሮፐርቲ ግብይትና ግመታ መረጃ ቋት
እንዲመሰረት ማድረግ፤

 የወቅቱን ቴከኖሎጂ እና የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘገበ የሪል ፕሮፐርቲ ግብይትና

ግመታ መረጃ ቋት ስርአት ለመፍጠር ሚያስችል የዳሰሳ ጥናት እንዲከናወን ማድረግ፡፡

 የሪል ፕሮፐርቲ ፕላት ፎርም እና የግመታ መረጃ ዳታ ቤዝ ማዘጋጀት፡፡

 በለማዉ ሲስተም ላይ ሁሉ አቀፍ እና አካታች ይሆን ዘንድ ሁሉንም የባለድርሻ አካላት

ሃሳብና አስተያየት ለማሰባሰብ ሲስተሙ የሙከራ ትግበራ እንደካሄድ በማድረግ የተገኙ

ግብአቶች አካቶ የመረጃ ስርአቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ማድረግ፡፡


6) የሪል ፕሮፐርቲ ግመታ ስርዓት እንዲዘረጋ ማድረግ፤
 በወቅታዊ ጥናት የከተሞች እና አካባቢዎች የግመታ ወሳኝ ቫሪያብልስ በመለየት የእነዚህ

ወሳኝ ቫሪያብልስ ኮፊሸንት ለግመታ ያላቸው ድርሻ ወይም ሚዛን ቀመር ማዘጋጀት፡፡

 የሪል ፕሮፐርቲ ግመታ ፖሊሲዎች መተግበራቸው የሚያረጋግጡ አመላካቾችን ተግባራዊ

ማድረግ፡፡

 ሀገር አቀፍ የሪል ፕሮፐርቲ ግመታ መስፈርቶችን እንዲለዩ ያደርጋል፤ በመስፈርቶቹ

መሠረት የሪል ፕሮፐርቲ እሴት መተመኛ ቀመር ማዘጋጀት፡፡

 በግመታ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎች እና አለመግባባቶች የሚፈቱበት ሙያዊ አደረጃጀትና

አሰራር መዘርጋት፡፡

 ለሪል ፕሮፐርቲ ግብር አጣጣል የብዘሃ ግመታ (mass valuation) ስርዓት በመዘርጋት፣

ለሪል ፕሮፐርቲ ግብር አጣጣል የብዘሃ ግመታ ለመስራት የሚያስችል ሲስተም እንዲለማ

ማድረግ ፣ የለማውን ሲስተም ውጤታማነት መገምገም፡፡


 የግመታ ስርዓቱ በሙያዊ ገለልተኝነት ታማኝ ሆኖ መከናወኑን በጥናት እንዲለይ

ማድረግ፤ ጉድለቱን መፈተሽ፡፡


7) በ ሪል ፕሮፐርቲ ግብይትና ግመታ ሥራ አመራርና አስተዳደር መስኮች የአቅም ግንባታ
መርሀ-ግብሮች ማዘጋጀት፤
 የዘርፉን ችግር ሊፈታ የሚችል ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የሙያ ደረጃ ማዘጋጀት፡፡

 በዘርፉ ላይ የተለየውን ክፍተት መሰረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፡፡

 የዘርፉን ባለሙያ በምዘና ብቃቱ እንዲረጋገጥ ማድረግ፡፡

 በተዘጋጁ ጥናቶች፣ አማራጭ ፓሊሲዎችና ስትራቴጂዎች፣ የህግ ማዕቀፎች፣ የአሰራር

ማኑዋሎችና ስታንዳርዶች እና የአፈፃፀም ተሞክሮዎችና ለውጦች ዙርያ የግንዛቤ

ማስጨበጥ ስራ በየደረጃው መምራት፣ ማረጋገጥ፡፡

You might also like