You are on page 1of 3

1.

ወዳንተ እሰግዳለሁ ሳልሁ

ወዳንተ እሰግዳለሁ ሳልሁ በሕይወቴ


ላንተም እገዛለሁ እስከ ዕለተ ሞቴ

አንተ ነህና መድኃኒቴ የዘላለም ቤቴ(2)

ሳይመሽብኝ ቀኑ ሳይጨልም ድንገት


በፅድቅ ጎዳና ልጓዝ ወደ ፊት

ምራኝ መንገዱን አሳየኝ እንዳልሳሳት(2)

የነፍስ የስጋዬ የህይወቴ ቤዛ


አትበለኝ ችላ በደሌ ቢበዛ

አንተን አምኜ እኖራለሁ ወዴት እሄዳለሁ(2)

አንተን አምኜ እኖራለሁ ወዴት እደርሳለሁ፡፡


ወዳንተ እሰግዳለሁ ሳልሁ በሕይወቴ
ላንተም እገዛለሁ እስከ ዕለተ ሞቴ

አንተ ነህና መድኃኒቴ የዘላለም ቤቴ(2)

እንደ ኒቆዲሞስ
እንደ ኒቆዲሞስ የሌሊት ተማሪ(2)

በእምነት ጎዳና መልካሙን ዘር ዝሪ(2)

መልካም ህይወት ስጠኝ ቅን ታዛዥ አርገኝ(2)

የዛሬዋን ደስታ ሁሌ አትንፈገኝ(2)፡፡

አይሁድ እንዳያዩት ተደብቆ መጣ

ያዉም በሌሊቱ ፀሐይዋ ሳትወጣ

የጌታዬን ማዳን ታምር ስለሰማ

ሊወጣበት መጣ የህይወትን ማማ፡፡

እንደ ኒቆዲሞስ የሌሊት ተማሪ(2)

በእምነት ጎዳና መልካሙን ዘር ዝሪ(2)

መልካም ህይወት ስጠኝ ቅን ታዛዥ አርገኝ(2)

የዛሬዋን ደስታ ሁሌ አትንፈገኝ(2)፡፡

እኔንም ተመልከት ችላ አትበለኝ ጌታ

ፍቃድህም ይሁን ከቤትህ እንድመጣ

ከእግርህ ስር ቁጭ ብዬ ልማር ወንጌልን

እንደ ኒቆዲሞስ አርገኝ እኔንም፡፡

እንደ ኒቆዲሞስ የሌሊት ተማሪ(2)

በእምነት ጎዳና መልካሙን ዘር ዝሪ(2)

መልካም ህይወት ስጠኝ ቅን ታዛዥ አርገኝ(2)

የዛሬዋን ደስታ ሁሌ አትንፈገኝ(2)፡፡

ለመኖር እያልኩኝ ካለም ስተባበር

ፍረድ አደባባይ ላይ ስቆም ለምስክር

ይቅር በለኝ ጌታ መንገድህን ምራኝ

እንደ ኒቆዲሞስ ልቤን ስበርልኝ፡፡

እንደ ኒቆዲሞስ የሌሊት ተማሪ(2)

በእምነት ጎዳና መልካሙን ዘር ዝሪ(2)

መልካም ህይወት ስጠኝ ቅን ታዛዥ አርገኝ(2)

የዛሬዋን ደስታ ሁሌ አትንፈገኝ(2)፡፡

You might also like