You are on page 1of 34

Wolaita sodo university

ottona campus evangelical Christian


students’ fellowship
Rehobot choir
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የኦቶና ካምፓስ

ወንጌላዊያን ክርስቲያን

ተማሪዎች ህብረት

የርኆቦት ኳይር የመዝሙር ደብተር

ከ 2005 ዓ.ም ጀምሮ…

ማውጫ/CONTENTS/

1- አንተ እንዴት ያለ ፍቅር አለህ ጌታ


2- ብዙ ብዙ ምህረትህን ሳይ
3- አላፈርክም በእኔ ባንተ አላፍርም
4- አቤቱ ጌታችን ሆይ፡ መንገድህን አሳየን
5- በድካሜ የራራህልኝ
6- ሠላሜ በዛ
7- ጌታ ኢየሱስ
8- ኢየሱስ ኢየሱስ ወዳጄ ኢየሱስ
9- የአምላኬን ውለታ ሳስበው ሳስበው
10- መክሊትህን ነግድነት
11- አቤቱ መልሰን ወደ ቀድሞ ፍቅርህ
12- እግዚአብሔር መታመኛዬ ነው
13- አምላኬ የዘላለም አባት
14- ድካሜን (3x) አንሳው ከላዬ
15- በማዳንህ እጅግ ደስ ይለኛል (2x)
16- ክበር ብዬ የማልጠግበው --- አሃሃሃ
17- የሚረባኝን ነገር የሚያስተምርኝ
18- ታማኝ ሰው አድርገህ በፊትህ አቁመኝ
19- የምለው አለኝ ጌታዬን የምለው
20- በተከበበ ከተማ የሚያስደንቅ ምህረቱን በእኔ የገለጠ
21- የዘላለም መኖሪያዬ ጌታ ኢየሱስ ነህ /2x/
22- እግዚአብሔር እግዚአብሔር እግዚአብሔር /2x/
23- የተደረገለት ውለታው ያለበት
24- ሃዘኔን ከእኔ አስወግዶ በደስታ ዘይት ቀባኝ
25- ሌላ ነገር ለምን አያለሁ ምህረቱን እንዴት እረሳለሁ
26- እኔ ነኝ እኔ ነኝ እንዳመሰግነው የሚገባኝ…አሃሃሃሃ
27- በልቤ ዙፋን ላይ ሾሜሃለሁ/3x/
28- ምስጋና ነው ያለኝ
29- አድስ ምስጋና/3x/
30- ሁሌ ነዉ ሁሌ
31- ክርስቶስን ከሙታን ያስነሳው

01

አንተ እንዴት ያለ ፍቅር አለህ ጌታ /2x/

እንዲሁ ወደኸኝ ራስህን ሰጥተኸኛል


ነፍስህን ሰውተህ እኔን አድነሃል

እወድሃለሁ ጌታ እወድሃለሁ

እወድሃለሁ ኢየሱስ እወድሃለሁ

ስለ ወደድከኝ፤ ስለ መረጥከኝ እወድሃለሁ

ስላከበርከኝ … አመልክሃለሁ

1. እኔ ሳልወድህ እንዲሁ ወደኸኝ

አስቀድመህ አውቀህ በፍቅር አስጠጋኸኝ

ወገን አስተዋሽ መጠጊያ ለሌለው

አባት ሆንክልኝ ክበር እልሃለሁ…….እወድሃለሁ

2. በኃጥአት ወድቄ ቅድስና አጥቼ

ትዕዛዝህን ጥሼ ከፊትህ ሸሽቼ

ሞትን ሲጠባበቅ ተስፋ ሁሉ ጨልሞ

ዛሬ ብርሃን አየሁ በአንተ ተፈፅሞ

በዚያ በቀራንዮ በከፈልከው ዋጋ

ምህረትን አግኝቼ ተጠጋው አንተጋ…….እወድሃለሁ

3. በእርሱ የሚያምን ማንም እንዳይጠፋ

እግዚአብሔር አብ ወዶ የሰጠው ስለ እኛ

እውነትና መንገድ ሕይወትም የሆነው

እርሱም ያድነናል በመስቀል የሞተው……እወድሃለሁ

02
ብዙ ብዙ ምህረትህን ሳይ
ብዙ ብዙ ፍቅርህን ሳይ
ብዙ ብዙ ማዳንህን ሳይ
ብዙ ብዙ ደግነትህን ሳይ
መገረም ይሞላዋል ውስጤን
መደነቅ ይሞላዋል ውስጤን

1. መሪርን ለቅሶ ሳለቅስ አይተህ

አፅናንተኸኛል ዕንባዬን ጠርገህ

ማቄን ከላዬ ቀዳደህ ጥለህ

ሳቅ አረክልኝ ደስታዬ ሆነህ /2x/

2. ከሰዎች ተራ የማልውለውን

በህግ የተገለልኩ ርቄ ያለሁትን

በፍቅር ቀርበህ ዳስሰህ ፈወስከኝ

ኦ! ጌታዬ ሆይ ተባረክልኝ /2x/

3. ሕመሜን ታመህ እኔ ድኛለሁ

ለኃጥአት በደሌ ይቅርታ አገኘሁ

ደምህን አፍስሰህ ነፍሴን ተበዣሃት

ክበር ልበልህ መድኃኒቴ ነህ /2x/

4. ከአእምሮ ያልፋል በጣሙም ምጡቅ

የአንተ ፍቅር ለኔ ያለህ መውደድ

ዘርዝሬ አልጨርስ ሳወራው ብውል

ከፍ በል እንጂ ሌላ ምን ልበል /2x/

5. ትዕግስትህ ብዙ እጅጉንም ቸር

ለሚታመኑህ ፅኑ አስተማማኝ

አይሰጋብህ መለወጥ አታውቅ

እንደ አንተ የለም ለኔ ውድ ድንቅ /2x/


03

አላፈርክም በእኔ ባንተ አላፍርም

ጌታዬ ባንተ አላፍርም

አላፈርክም በእኔ ባንተ አላፍርም

ኢየሱስ ባንተ አላፍርም

1. ጎልጎታ ስትወጣ

አቤት ያየኸው ጣጣ

እራቁትህን መገረፍህ

ለእኔ ነው መንገላታትህ

2. ና ውረድ ብለው

ጌታ ሲዘባበቱብህ

አምላክ እያለህ ዝም ማለትህ

ለእኔ ነው መዋረድህ

3. ሁሉን ስትችል

ኢየሱስ ዝም ማለትህ

እስከ ሞት ድረስ መታገስህ

ለእኔ ነው መሞትህ

4. እኔን መውደድህ

ጌታ እጅግ ይገርማል

በሕይወት እንድኖር አደረከኝ

ጌታዬ ሞቴን ሞትክልኝ


04

አቤቱ ጌታችን ሆይ፡ መንገድህን አሳየን

በእውነትህም ሁልጊዜ ምራን

የልብህን ሐሳብ ፈቃድህን

ግለጠው በእኛ ላይ ደስታህን

1. ታይቶ የሚጠፋው የዓለም ክብር

በልባችን ነግሶ ብልጭልጩ ነገር

ተውጠን እንዳንቀር በከንቱ ምኞት

መኖር ይሁንልን ዓላማህ ባለበት

2. የእምነት አባቶች ብዙ ዋጋ ከፍለው

ፈቃድህን ለመኖር ሥጋቸውን ነክሰው

የዓለምን ነገር እንደ ከንቱ ቆጥረው

ምሳሌ ሆኑልን አንተን አስከብረው

3. አቤቱ አምላኬ አንድን ነገር እሻለሁ

እርስዋንም ለማየት እጅግ እፈልጋለሁ

በሕይወቴ ዘመን በቤትህ እንድኖር

አንተን ደስ እያሰኘሁ ክብርህን እንድናገር

4. መድኃኒታችን ሆይ እንጠራሃለን

ፀጋን እንድትሰጠን እንለምንሃለን

በሕይወት ጎዳና ቀሪው ዘመናችን

በቤትህ እንድያልቅልን አደራ እንላለን


05 በድካሜ የራራህልኝ

ከፊትህም ፍፁምያ ልተውከኝ

የመድኃኒቴ አምላክ እወድሃለሁ

የልጅነቴ አምላክ እወድሃለሁ

1. ኃጥአቴ ተሽሮ ምህረት በዝቶልኛል

ውርደቴም በክብር ተቀይሮልኛል

በጨለማ ሳለሁ ብርሃን ወጥቶልኛል

የዘላለም ሕይወት ተበርክቶልኛል

ስለዚህ እላለሁ ተመስገንልኝ

ስለዚህ እላለሁ ከፍ በልልኝ

ስለዚህ እላለሁ ተባረክልኝ

ስለዚህ እላለሁ ከፍ በልልኝ

2. ዘመድ ርቆኝ ሳለ አንተ ተጠግተህ

ደዌዬንና እድፌን ከእኔ አስወግደህ

ሙሉ ሰው አረከኝ ይኸው አውጃለሁ

ተመስገን ተመስገን ከፍ በል እላለሁ

ስለዚህ እላለሁ ተመስገንልኝ…..

3. ምህረትህ በዝቶልኝ ፊትህን አይቻለሁ

በማዳንህም ደስ ተሰኝቻለሁ

ተመስገን ከማለት ምን እከፍልሃለሁ

ኢየሱስ አምላኬ አዜምልሃለሁ

ስለዚህ እላለሁ ተመስገንልኝ……

4. ምስኪኑን ከትቢያ ከአመድ አንስተሃል

ከህዝብ አለቆች ጋር በአንድ አስቀምጠሃል


የተናቀውንም ሞገስ ሰጥተኸዋል

ዕንባን ከዓይኑ አብሰህ ፅዋውን ሞልተሃል

ስለዚህ እላለሁ ተመስገንልኝ……

06

ሠላሜ በዛ /3x/

ካንተ የተነሣ

ተድላዬ በዛ /3x/

ካንተ የተነሣ

1. እንደ ወንዝ ይፈሳል ሠላሜ በውስጤ

እጅግ ደስተኛ ነኝ ምንም ሳይኖር በእጄ

በምድረ በዳ ላይ በማይመች ሥፍራ

ደስታዬን አበዛህ ሆነህ ከእኔ ጋራ

2. በብርና በወርቅ እጅግ በበዛ ሃብት

ማይለካ ከቶ ፍጹም ማይገመት

ዕረፍትና ሠላም ባንተ ሆኖልኛል

ክበር ለዘላለም ቀንበሬን ሰብረሃል

3. ሃዜን መከራዬን ከድንኳኔ አርቀህ

ዓይኖቼንም ከዕንባ ፈጽሞ ከልክለህ

ሀሩሩን አብርደህ ነፍሴን አሳረፍካት

ቤዛ ሆነህላት ከሞት አተረፍካት


07 ጌታ ኢየሱስ….. ጌታ ኢየሱስ …..

እባክህ ምህረት አድርግልኝ /2x/

እንደገና /3x/ በእግሮቼ አቁመኝ

እንደገና ፊትህን መልስልኝ ምህረት አድርግልኝ

1. በሐሳብ ተግባሬ አንተን አሳዘንኩኝ

ባልተገባኝ ሥፍራ ሆኜ ተገኘሁኝ

ትዕዛዝህን ጥሼ በድዬሃለሁኝ

ዛሬ ግን ጌታ ሆይ ምህረት አድርግልኝ.……ማረኝ /8x/

2. ፀንቼ በመቆም አንተን መጠበቅን

ዘንግቼ ፈቀቅ አልኩ ፈቃዴን ልፈጽም

መሄዴ ጎድቶኛል ከሃሳብህ ርቄ

ጎስቋላ ሆኛለሁ ራራልኝ ጌታዬ…………….ማረኝ /8x/

3. አቅም ጨምርልኝ መፍገምገሜ አይብዛ

መውደቅ መነሳቴ መዛሌ ይቅርና

ድካሜን አርቀህ በጸጋህ ደግፈኝ

እንደ ፍቅርህ ብዛት በደሌን ሻርልኝ………..ማረኝ /8x/

4. ማጥፋቴ ገብቶኛል አንተን መበደሌ

ስምህን ያስነቀፍኩ ያሰደብኩ መሆኔ

ደግመህ ማረኝና ወደ ቤትህ ልግባ

ሃሩሩ ጎድቶኛል እባክህ አባባ………………ማረኝ /8x/


5. ምህረትህ የበዛህ ይቅር ባይ እንደሆንክ

ጠንቅቄ አውቃለሁ ማረኝ ብሎ ላለህ

ወደ ፀጋህ ዙፋን በምህረትህ አቅርበኝ

ይቅር በለኝና በሕይወት አኑረኝ ………….ማረኝ /8x/

6. ልለይህ አልሻም ካንተ ርቄ ልኖር

ፈፅሞ አይረባኝም የኃጥአት መዝገብ

በደምህ እርጨኝና ጉድፌን አንፃልኝ

ተጠልዬ ልኑር በፍቅርህ ጥላ ሥር..…….ማረኝ /8x/

08

ኢየሱስ ኢየሱስ ወዳጄ ኢየሱስ

አባቴ ኢየሱስ

ረዳቴ ኢየሱስ ኢየሱስ

ለድሃው መጠጊያ

በጭንቅ ጊዜ ለችግረኛው መጠለያ

ከማዕበልም መሸሸጊያ

ከፀሐይ ትኩሳት ሆነሃል ጥላ (3x)

1. ቀንበሬ ከብዶኝ ልገለኝ ቢሞክር

ተስፋ ቢያስቆርጥ በዝቶብኝ ችግር

ዘመን የማይሽረው ኤልሻዳዩ እግዚአብሔር

ነፃ አወጣኝ ከመከራዬ ቀንበር

2. ሳለቅስ ሳነባ መሄጃ አጥቼ

አይዞህ የምለኝ ጠፍቶ ብቻዬን ቀርቼ

ውድቀቴን የማይወድ አባት ደረሰና


በፊቱ አቆመኝ እንባዬን አበሰና

3. ዘመድ አዝማድ ብተወኝ ብርቀኝ

የያዝኩት ሁሉ ከእጄ ብጠፋብኝ

ከወንድም አብልጦ የሚጠጋጋኝን

ወዳጅን አገኘሁ የሚያረጋጋኝን

4. መጠጊያ አጥቶ ለሚንከራተተው

በሰው ሁሉ ዘንድ ከቶ ለተረሳው

የሚያዝንለት አንዱ ወዳጅ

ኢየሱስ ብቻ ነው እውነተኛው ፈራጅ

09

የአምላኬን ውለታ ሳስበው ሳስበው (2x)

አምልከው ይለኛል

አክብረው ይለኛል

ከፍ አርገው ይለኛል

በእርሱ ደስ ብሎኛል

1. ጨለማዬን አብርቶ በብርሃን መራኝ

ጌታ ለመንገዴ መብራት ሆነልኝ

እስራቴን ፈቶ ነፃ ሂድ አለኝ

ነፍሱን ለእኔ ሰጥቶ ልጁ አደረገኝ

2. ጌታዬን ስጠራው መቼ ዝም አለኝ

የውስጤን የልቤን ለእርሱ ነገርኩኝ

ዘላለም እንዳልወድቅ በእርሱ ተደገፍኩኝ


ከመከራ ሥጋት በእርሱ አረፍኩኝ

3. የጠላት ፉከራ እጅግ ሲያስፈራራኝ

እኔም ጌታዬ ሆይ ጠፋሁኝ አልኩኝ

ከመከራው ብዛት እጅግ ተጨነኩኝ

ጌታ ቀኜን ይዞ በድል አሻገረኝ

4. ተመስገን ከማለት የሚለው የለኝም

ብቆጥረው ባወራው ብጽፍም አያልቅም

ሁልጊዜ ባከብረው ለእርሱ ብዘምር

አይበቃውም ጌታ ከፍ ላለው በክብር

10 መክሊትህን ነግድነት

አትቅበረው እንዳትከስርበት

ወንድሜ ሆይ ይህ ነው ዛሬ

ያለኝ መልዕክት በዝማሬ

1. ባለ አምስቱ አምስት አትርፎ

ባለ ሁለቱም ሁለት አትርፎ

ተሹመዋል በጌታቸው

ተመስግነው በስራቸው

2. መክሊት ወስዶ የቀበረው

በጌታው ላይ የዘበተው

ተብሎ ቀረ ሐኬተኛ

ትምህርት ሆነ ዛሬ ለእኛ
3. የሚሰብከው በስብከቱ

እየተጋ በእምነቱ

ዘማሪውም ባለው ጸጋ

ለሽልማት ካሁኑ ይትጋ

4. አንተ መሪ አትዘንጋ

ከመረጠህ ልታገኝ ዋጋ

በርታ በእርሱ እንደ ትናንቱ

የመነገድ ነውና ወቅቱ

5. በተሰጠው የሚነግድ

እየሄደ በእውነት መንገድ

ተመስጋኝ ነው መጨረሻ

ከጌታ ዘንድ አለው ድርሻ

11

አቤቱ መልሰን ወደ ቀድሞ ፍቅርህ

አቤቱ መልሰን ወደ ፈቃድህ

ምህረትህ ናፍቆናል እንመለሳለን (2x)

1. መሰዊያችን ፈርሷል የጸሎት

ርቀን ሄደናል ካንተ መገኘት

ጓዳችን ተሞልቷል በእርም ነገር

እባክህ መልሰን ወደ አንተ ፍቅር

2. ቀንበር ከብዶናል የባርነት

ጀርባችን ተልጧል በግርፋት


እባክህ ጌታ ሆይ እራራልን

ከጨካኙ አውሬ አስመልጠን

3. በልተን አልጠገብንም ለብሰን አልሞቀንም

ለነገው ስናስብ ለዛሬ አልበቃንም

እባክህ ጌታ ሆይ ተመልከተን

በቀድሞ በረከት ዳግም አስበን

4. አልበቃ ብሎናል የተፈቀደልን

ካንተ የተሰጠን የራሳችን

በረከት አጥተናል የአንተን ሰርቀን

ቃልህን ተላልፈን ኃጥአት ሰርተን

12

እግዚአብሔር መታመኛዬ ነው

በሕያዋን ምድር ዕድል ፈንታዬ

ባንተ ታምኜ አፍሬ አላውቅም

ስምህን ጠርቼ ከስሬ አላውቅም

1. ለምታመንህ አንተ ነህ መታመኛ

ስምህን ለምጠሩ ከጠላት ማምለጫ

ተሰብረህ የማታውቅ ጽኑ መመኪያ

እታመንሃለሁ የእኔ ማረፊያ

2. በልዑል መጠጊያ ታምኖ የሚኖር

ሁሉን በምችል አምላክ ጥላ ሥር የሚያድር

ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስፈራው ነገር


እርሱ ያመልጣል ሁሉን በእግዚአብሔር

3. ሥሙ የጸና ግንብ የሁሉ ጥላ

ጻድቅም ሮጦ የማያፍር ከለላ

ባንተ ለምታመን ሁሌም ታማኝ ነህ

ጊዜ የማይሽርህ አንተ ብቻ ነህ

4. ኪዳንን የሚያከብር ተስፋን የሚያድስ

ታሪክ ለውጦ እንባን የሚያብስ

ከአመድ አንስቶ ማዕረግን የሚያሳይ

ለምታመኑህ ታማኝ ነው ኤልሻዳይ

13

አምላኬ የዘላለም አባት

ኢየሱስ የነፍሴ መድኃኒት

ላንተ ሰጥቻለሁ የእኔን ነገር

እባክህ ኑሮዬን አሳምር

አቁመኝ በፊትህ ሕይወቴን ለውጠህ

ዘመኔን በክብር በምስጋና ሞልተህ

ሥራኝ እንደገና ሥራኝ እንደገና

በእጅህ ያለሁ ሸክላ ነኝና

1. ሕመሜን ደብቄ ሳልነግረው ለጌታ

ፈውሴ ዘገየብኝ ነፍሴ ተንገላታ

አቤቱ ለቃልህ ልቤን ክፈትኝ

ለሞት እንዳልተኛ ዓይኖቼን አብራልኝ

2. የአምልኮን መልክ ይዤ ዘመን አስቆጥሬ


የክብርህን ውበት ሳላይ እስከ ዛሬ

እባክህ አምላኬ ፊትህን መልስልኝ

አብልጬ እንዳመልክህ ፀጋህን አብዛልኝ

3. መኖር አቅቶኛል መታዘዝ ቃልህን

አንተን መስሎ መኖር ማድረግ ፈቃድህን

የቆሸሸው ልቤን ቀድስ በመንፈስህ

አድርገው ጌታዬ ማደሪያ ሥፍራህ

4. እኔ ዝቅ ልበል ልዋረድ በፊትህ

በኑሮዬ ይታይ ኢየሱስ ጌትነትህ

ላንግስህ ኢየሱሴ በልቤ ዙፋን ላይ

ቆርጫለሁ እኔ ካንተ ሌላ ላላይ

14

ድካሜን (3x) አንሳው ከላዬ

ዓይኖቼን (3x) አብራው ጌታዬ

ጌታ ክብርህ በዘመኔ ኢየሱስ አይጓደል በሕይወቴ

ክንድህ ይገለጥ በእኔ ላይ ዛሬም ይታደስ ጉልበቴ

1. በቃል ብቻ አይሁን ይለወጥ ሕይወቴ

በኑሮዬ ይክበር ኢየሱስ መድኃኒቴ

ይብራ በጨለማ ይታይ ብርሃኔ

ክርስቲያን ነኝ ካልኩኝ ክርስቶስም በእኔ

2. ባለፉት ዘመናት ብዙ ባክኛለሁ

ከፈቃድህ ዉጭ ተመላልሻለሁ
አሁን ተቀበለኝ አጥግበኝ ፍቅርህን

ወዜን መልስልኝ ስጠኝ መንፈስን

3. በምድር እስካለሁ ልኑር ለፈቃድህ

በመንገዴ ሁሉ ምራኝ እንደ ቃልህ

በመቅደስህ ውስጥ ሁሌ ላገልግልህ

ማደሪያዬ ይሁን ቅዱስ ተራራህ

4. አጥርቼ ሳላየው የመጥራቱን ተስፋ

በድንግዝግዝ ጉዞ መንገዱ እንዳይጠፋ

አይኖቼን አንስቼ ከምድራዊ ነገር

አብዝቼ እሮጣለሁ ለማይጠፋው ክብር

5. ለሚያልፈው ነገር መጨነቄን ትቼ

በጽድቅ ለመኖር ልፀልይ ተግቼ

ጌታ ሆይ እጄን ያዝ ዘመኑን እንድሻገር

ከለላ ሁንልኝ ከዓለም ውሽንፍር

15

በማዳንህ እጅግ ደስ ይለኛል (2x)

ቤዛ ሆነህ ሕይወት ሰጥተኸኛል

ከጠላት እጅ ነፍሴን አድነሃታል

እዘምራለሁ ለጌታ እዘምራለሁ

እዘምራለሁ ለኢየሱስ እዘምራለሁ

ደስ እያለኝ ሁሌ አመልካለሁ

ዝቅ ብዬ በፊቱ እሰግድለታለሁ
1. ከአእምሮዬ በላይ ጌታ ያደረገልኝ

ተቆጥሮ አያልቅም ለእኔ የሆነልኝ

መቼ ይረሳኛል ከየት እንዳነሳኝ

በጎነቱን ላውራ ለዚህ ስላበቃኝ

2. ጌታዬ ሆነልኝ የዘላለም መኖሪያ

ከክፉ ማምለጫ ጥላና መጠጊያ

እንደ እርሱ አላየሁም በሕይወት ዘመኔ

ምስጋና ልጨምር ልቀኝለት ቅኔ

3. ጨለማዬ በራ ሠመረ ሕይወቴ

ኢየሱሴን ይዤ ሠላም ሆነ ቤቴ

ምንም አያሠጋኝ በእርሱ ተደግፌ

እሄዳለሁ ገና ሁሉን በእርሱ አልፌ

4. እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው

የሚያስደነግጠኝ የሚያስፈራኝ ማነው

በክንፎቹ በታች እተማመናለሁ

ከጠላቶቼ ቀስት በእርሱ እድናለሁ

16 ክበር ብዬ የማልጠግበው --- አሃሃሃ

ንገሥ ብዬ የማልረካው --- ኦሆሆሆ

አመስግኜ የማልጠግበው --- አሃሃሃ

ዘምሬ የማልረካው --- ኦሆሆሆ

ምክንያቱ ኢየሱስ ነው (4x)


ምስጢሩ ኢየሱስ ነው (4x)

1. ነፍሴ ታከብራለች የረዳኝን ጌታ

ሁልጊዜ እያሰበች የእርሱን ውለታ

አምልጣለች በእርሱ ከሲኦል ጨለማ

ከጌታ ጋር ልትኖር በአዲሱ ከተማ

2. ጌታ የሆነልኝ መቼ ዝም ያሰኛል

አላወራም ብል እንኳ እንዴት ያስችለኛል

ውለታው በሕይወቴ የበዛው ምህረቱ

ከቁጥር ይበልጣል አቤት ቸርነቱ

3. ሰውን አይቼ አይደለም የማመሰግነው

እንዳልተደረገልኝ አልሆንም ሳመልክው

ለእኔ ያደረገው ከቃላት በላይ ነው

ምላሽ ባይሆነውም ያለኝ ምስጋና ነው

4. ከዛ ከጨለማ ጌታ ጠራኝና

አቃናው መንገዴን የሕይወቴን ጎዳና

በደሙ አጠበው ኃጥአቴን በሙሉ

ነገሬን ፈፀመው ኢየሱስ በመስቀሉ

5. ቃላት ከየት አግኝቼ ጌታን ላመስግነው

በምን ቋንቋ ውዴን ሥሙን ላሞጋግሰው

በማይለዋወጠው ፍቅሩ ለወደደኝ

ለመንግስቱ ካህን አድርጎ ለሾመኝ


17

የሚረባኝን ነገር የሚያስተምርኝ

በሚሄድበት መንገድ የሚመራኝ

ከማንም በላይ ለእኔ የሚያስብልኝ

ከመልካምነቱ ሁሉ የሚያጠግበኝ

አባት አለኝ (3x) ጌታ አለኝ

አምላክ አለኝ (3x) ኢየሱስ አለኝ

1. በመንገዴ ሁሉ ሬድኤት የሆነኝ

ስለ ሥሙ በጽድቅ መንገድ የመራኝ

እረኛዬ ሆኖ ምንም ያላሳጣኝ

እስከዚህ ያደረሰኝ é ረ እኔ ማነኝ

2. በምድር ጠቢባን ኃያላን እያሉ

ደካማውን መረጠኝ ሊያቆመኝ በቃሉ

ጸጋው ሲደግፈኝ እግሮቼም ጸኑልኝ

ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ

3. ከማይጠፋው ዘር በክርስቶስ ወለደኝ

በትንሳኤው መንፈስ ሕያው አደረገኝ

የክብር ተስፋዬ ኢየሱስ ሆነልኝ

ጊዜያዊ ነው ምድር ሌላ ርስት አለኝ

4. ከግንዱ ተጣበኩ ከሩቅ ተጠርቼ

ከመሃል ገባሁኝ ከበረሃ መጥቼ

በፍጥረቴ ሳልሆን መልካም የወይራ ዘር

በኢየሱስ ቸርነት አገኘሁ ይህን ክብር


18

ታማኝ ሰው አድርገህ በፊትህ አቁመኝ …

ፈቃድህን ማድረግ ጌታ አስተምረኝ …

በሕይወቴ ሁሉ አንተው ክበርብኝ …

ቅዱስ መንፈስህን አትውሰድብኝ …

1. ጠዋት ቢሆን ማታ ቀንም ሆነ ሌሊት

በማንኛውም ሥፍራ በየትኛውም ሰዓት

ከመገኘትህ ውጭ እንዳልሆን ከሃሳብህ

ህልውናህ ጌታ ያኑረኝ በቤትህ

2. ማንነቴ ስታይ ሲፈተሽ በቃልህ

አንዳች ምክንያት የለም የሚያቆመኝ በፊትህ

ከጸጋህ በስተቀር የለኝም መመኪያ

አጽናንተኸኛል ጌታ ሆነኸኝ መጠጊያ

3. ባለማወቅ ብዙ ዘመናት አልፈዋል

ተምችና ኩብኩባ ሕይወቴን በልተዋል

የቀረው ዘመኔን አድርገው የበረከት

ሃሳብህን አውቄ ይለቅ በአገልግሎት

4. በቅድስና ሕይወት አንተን በማሳየት

በዚህ ክፉ ዘመን ልኑር በቃልህ እውነት

ለገንዘብ ለዝና ለታይታ አልሮጥም

ክብርህ ይበቃኛል አልፈልግም ምንም


19 የምለው አለኝ ጌታዬን የምለው

የምለው አለኝ ኢየሱሴን የምለው

ለእርሱ የምሰጠው ምስጋና ይህ ነው

ለእርሱ የምሰጠው አምልኮ ይህ ነው

ለእርሱ የምሰጠው ዝማሬ ይህ ነው

ለእርሱ የምሰጠው እልልታ ይህ ነው

ለእርሱ የምሰጠው ሽብሸባ ይህ ነው

ለእርሱ የምሰጠው ጭብጨባ ይህ ነው

1. ከእናት ከአባት በላይ ጌታ በልጦብኛል

በእጄ ነህ ከቶ አትወድቅም ብሎኛል

በጥፋት ጎዳና ሳለሁ ደረሰልኝ

እንዲሁ ወዶኝ በሕይወት ኑር አለኝ

2. ያልሆነውን ሳይሆን የሆነውን ቆጥሬ

ጌታን ለማመስገን ምክንያት ፈጥሬ

ብገባኝ ነው እንጂ እንደዚህ መሆኔ

ቢያልቅ ምን አለበት በቤቱ ዘመኔ

3. ክብሩን አይቻለሁ በእርሱ ተመርጬ

በወደደኝ በእርሱ ከሲኦል አምልጬ

ታድያ ለዚህ ጌታ ምላሽ ምኔን ልስጠው

ያንስበታል ለእርሱ ዘመኔን ብሰጠው

4. ገመዴ ባማረ ሥፍራ ወደቀች


ርስቴ በጌታ በእርሱ ተዋበች

ቀድሞ መርጦኝ ኢየሱስ ወራሽ አድርጎኛል

ስለዚህ በአምላኬ እጅግ ደስ ይለኛል

20 በተከበበ ከተማ የሚያስደንቅ ምህረቱን በእኔ የገለጠ

የዘላለም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን ጠላት ተረገጠ

ባፈርኩባት ምድር ለክብር ሾመኝ

በጠላቶቼ ፊት ቀና አደረገኝ

የትናንቱን ሃዘን በደስታ ለወጠው

አፌን በምስጋና በዝማሬ ሞላው

ምስጋና አለኝ /3x/ እልልታ አለኝ (2x)

ላረገልኝ ውለታ ስለሆነኝ አለኝታ (4x)

1. የታሰርኩበትን ገመዱን በጣጥሶ

የጭንቀት ኑሮዬን በክብር ለውጦ

ጌታ ሊከርብኝ ዘመን ደረሰና

እኔም በዕጣዬ ቆምኩኝ ለምስጋና

2. ውርደቴን የሚሻ ጠላት እያየኝ

ጌታዬ ራሴን በዘይት ቀባኝ

እንኳን ይባስ ብሎ ከፍታ ሰጠኝ

በጠላቶቼ ላይ አረማመደኝ

3. አምላኬ የዘላለም መኖሪያ ሆኖኝ

በክንዶቹ በታች በሰላም ኖርኩኝ


እርሱ ነው ጌታዬ የረድኤቴ ጋሻ

በክፉ ቀን ለእኔ ጥላና መሸሻ

4. አሁን መች ጀመርኩኝ ገና አመልከዋለሁ

የጌታዬን ማዳን ኃይሉን አወራለሁ

በሚሞት ስጋዬ ጌታ ይክበርበት

አልቆጥብም ድምጼን ለእርሱ ይዘመርለት

21 የዘላለም መኖሪያዬ ጌታ ኢየሱስ ነህ /2x/

በክንፎችህ ጥላ አርፋለሁ /2x/

ባንተ ተማምኜ እኖራለሁ /2x/

ታስመካለህ ለሚታመኑህ ጋሻ ነህ /4x/

አዳንከኝ ከውድቀት ሆነኸኝ ረድኤቴ

ፈጥነህ ደረስክልኝ ስደክም ጉልበቴ

የሕይወቴ ዋስትና የሾምኩህ በራሴ

ኢየሱስ ዓለቴ ማምለጫ ለነፍሴ

ማረፊያዬ ጌታዬ አንተ ነህ

መመኪያዬ ጌታዬ አንተ ነህ

ከለላዬ ጌታዬ አንተ ነህ

ከማንም ከምንም ትበልጥብኛለህ

አከብርሃለሁ አመልክሃለሁ /2x/

በሕይወት ዘመኔ እገዛልሃለሁ

1. አልፈራም በፍጹም አልሰጋምም እኔ

አምላኬ እያለኝ ሳይርቅ ሆኖ ጎኔ

የሚያስጨንቀኝን በጌታ ላይ ጥዬ

በደስታ እኖራለሁ በእርሱ እፎይ ብዬ


2. ማይጠፋ ርስት ካለን በሰማይ አገር

በዚህች አጭር ዘመን እንኑር በፍቅር

በሚጠፋው ነገር አንጣላ ከሰው

በፀጋው እንደገፍ ሁሉን በሚያስችለው

3. ተስፋችን ምድራዊ ጊዜያዊ አይደለም

እንግዳ ነን እንጂ በዚህ ዓለም አንቀርም

እኛ ከኢየሱስ ነን መገኛችን ከላይ

ዘላለም መኖሪያ ቤት አለን በሰማይ

22

እግዚአብሔር እግዚአብሔር እግዚአብሔር /2x/


ትኖራለህ ለዘላለም በልዕልና…
ፍጥረታት ያመልኩሃል በምስጋና
መች ያንስሃል አምልኮ በማደሪያህ …
አሁንም ይወደስ ቅዱስ ስምህ
ያለኝ ቃላት አንተን ባይገልዑህም
ያለኝ ቋንቋ ባይመጥንህም
ሳላመልክህ እንዴት እኖራለሁ
ዝም ብዬ እንዴት እችላለሁ
ትልቅ ነህ ጌታዬ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ አምላኬ ትልቅ ነህ
የሚመስልህ አቻ የሌለህ
ለዘላለም አንተ ትልቅ ነህ

1. ፍርድህም ትክክል ልዩ ነው አገዛዝህ


ድንቅ ነው አሠራርህ እንከን አይገኝብህ
ማስተዋልህ በሰው አይመረመርም
እውቀትህ ጥልቅ ነው ከቶ አትታወቅም

2. የጌቶች ጌታ ነህ ግዛትህ ዘላለም


ፊትህን ሊያይ ችሎ የሚቆም የለም
በብርሃን ውስጥ ያለህ ብርሃን ነው ውበትህ
ሁሉም በመገረም ዘውትር የሚያመልክህ

3. ጥበብን ለጠቢብ አንተው ትሰጣለህ


እውቀትን ለአስተዋይ እንዲያው ታድላለህ
የወደድከውን ነገር ጌታ ታደርጋለህ
በኃይልህ በግርማህ ትደነቃለህ

4. ነገሥታትን በምድር አንተው ትሾማለህ


አንዱን ታስነሳለህ ሌላውን ታፈልሳለህ
መሾምና መሻር ማንስ ያግድሃል
ሥልጣንህ ሙሉ ነው ማን ይቃወምሃል

23

የተደረገለት ውለታው ያለበት


እስቲ ይነሳና ለእርሱ ይዘምርለት
ጌታ የጠራው ከዚያ ከጨለማ
ያጎናጸፈው የመንፈሱን ሸማ

1. በቀራንዮ መስቀል ኢየሱስ የሞተለት


የኃጥአቱ ዕዳ የተከፈለለት
ፍቅሩን የቀመሰ ምህረቱ የገባው
እስራቱን ፈትቶ ነጻ ሂድ ያለው
2. ሥፍራውን የተረዳ ከየት እንደ ተጠራ
ኃያላን ሳይጠሩ የደረሰው ተራ
የመዳኑን ተስፋ ዕድሉን ያገኘ
አዋጅ ተገልብጦ እዚህ የተገኘ
ከእኔ ጋራ ሆኖ አምላኬን ያክብረው
በምስጋና ሽታ ዙፋኑን ያውደው

3. ጌታ ያከበረው ከትቢያ አንስቶ


ከተረሳ ሥፍራ የመጣ ተጠርቶ
ንግስናን ያገኘ ታሪክ ተገልብጦ
አምላክ የጎበኘው ሁኔታን ለውጦ
እንዴት አያመልክም ከዙፋኑ ወርዶ
ለምን አይዘምርም እራሱን አዋርዶ
ሚልኮልን እያየ ሽብሸባውን ጨምሮ
ላከበረው ጌታ ብልቃጡ ተሰብሮ

24
ሃዘኔን ከእኔ አስወግዶ በደስታ ዘይት ቀባኝ
የእኔን ሞት ጌታዬ ሞቶ ፍፃሜዬን ውብ አረገልኝ
ነገሬ ተቀየረልኝ ኑሮዬ በእርሱ አማረልኝ
ኢየሱስ ቤቴ ስገባ ለውስጤ ሠላም ሆነልኝ

1. ሳልወደው ጌታዬ ወዶኝ


ስሸሸው ይልቅ ቀረበኝ
አጣሁት መሳይ እኩያ
በሠማይ በምድር አምሳያ
በፍቅሩ ተማርክያለሁ
ጌታዬን እወደዋለሁ
ዘመኔን ለእርሱ እሰጣለሁ
በቤቱ ሁሌም እኖራለሁ

2. ከምድር አፈር አንስቶኝ


የክብር ሥፍራ ሰጠኝ
ፍቅር ነው ከማንም በላይ
ያዳነኝ ወርዶ ከሰማይ
በምን ቃል በምን አንደበት
ልግለጸው የእርሱን በጎነት
ልስጠው ብል ምን አለኝና
ይብዛለት ክብር ምስጋና
3. ለጊዜው ጌታ ዝም ቢል
የተወኝ የረሳኝ ቢመስል
ዲያብሎስ ብዙ ፎከረ
ላያገኘኝ እየጨፈረ
በኢየሱስ ሥራው ፈረሰ
ከሳሼ እፍረት ለበሰ
አለሁኝ እያማረብኝ
መንፈሱ እየጨመረብኝ

25
ሌላ ነገር ለምን አያለሁ ምህረቱን እንዴት እረሳለሁ
ሌላ ነገር ለምን አያለሁ ውለታውን እንዴት እረሳለሁ
ከእኔ በላይ ጌታ የራራለት መቃብሩን የከፈተለት
ከእኔ በላይ ጌታ የወደደው ነፍሱን አሳልፎ የሰጠው
ማነው ኧረ ማነው ማነው
ማነው እስቲ ማነው ማነው
እኔ ነኝ እኔ ነኝ ጌታ ያዳነኝ /3x/
ያለ ምክንያት እንዲሁ የተወደድኩኝ

1. አልታይ አለኝ እንጂ ቀድሞ መነሻዬ


ወደ ሞት ሳዘግም ደርሶልኝ ጌታዬ
እንዴት እንዳዳነኝ እኔ እገረማለሁ
ዛሬ ፊቱ ቆሜ ይኸው እዘምራለሁ

2. ሥራዬን በሙሉ ኢየሱስ ሠርቶልኝ


ከእኔ ምንም ሳይኖር ሁሉን ፈጽሞልኝ
በምህረቱ ብዛት በፍቅሩ ወዶኛል
ከመዳኔ በላይ ምን ያዘምረኛል

3. ወደ ፊት እሄዳለሁ አላይም የኋላ


መኖር ከኢየሱስ ውጭ አያሰኘኝ ሌላ
ዓይኖቼን አንስቼ ከነገሮች በላይ
መዝገቤ ያለበትን አያለሁ ሰማይ
4. የዚህ ዓለም ነገር የከንቱ ከንቱ ነው
ውበቱ ድምቀቱ አላፊ ጠፊ ነው
ኢየሱስን ትቼ ወዴት እሄዳለሁ
ያለ አፉ ቃል ታዲያ እንዴት እኖራለሁ

26
እኔ ነኝ እኔ ነኝ እንዳመሰግነው የሚገባኝ…አሃሃሃሃ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ እንድዘምርለት የሚገባኝ…አሃሃሃሃ
ከስንቱ ጣጣ ጌታ አወጣኝ
ቀንበሬን ሰብሮ ቀና አደረገኝ
እዳዬን ሁሉ እርሱ ከፍሎልኝ
አሁን ኢየሱስ አሳረፈኝ /4x/

1. ለእኔ ያደረገው ከማንም በላይ


ስሜ ተጻፈ በህይወት መዝገብ ላይ…….አሃሃሃሃ
አዘጋጅቶልኛል የዘላለም ቤት
ወራሽ አድርጎኛል የሰማዩን ርስት…….አሃሃሃሃ
ከዚህ ሌላ ለእኔ ምን ክብር አለኝ
ከእስራት ፈቶ ነፃ ነህ ካለኝ
ሁሉን አውረቼ አልጨርሰውም
ይክበርልኝ ሥሙ የመድሃንዓለም

2. በኃጢአቴ ምክንያት ሙት የነበርኩኝ


የሰይጣን ፈቃድ ሳደርግ የኖርኩኝ………….አሃሃሃሃ
ተስፋ ሳይኖረኝ እንዲሁ ተጥዬ
የዘላለም ሞት ነበር ዕጣዬ………..አሃሃሃሃ
ጌታ በፍቅሩ ወደደኝና
በደሌን ሻረው ሕይወት ሰጠና
በደሙ ገዝቶ ልጁ አደረገኝ
በምህረቱ ቤቱ ገባሁኝ

3. ጌታን አግኝቼ ታድያለሁኝ


ከጥፋት ጉድጓድ ወጥቻለሁኝ……..አሃሃሃሃ
በቀራንዮ ፍቅሩን አሳይቶኛል
ለሚበልጥ ክብር አዘጋጅቶኛል…….ሃሃሃሃ
ጌታ ነው ራርቶ ሕይወት የሰጠኝ
የውስጤን ሕመም በቃሉ ያከመኝ
አላለቅስም አባት እንደሌለው ሰው
አለኝ ጩኸቴን ሰምቶ የሚመልሰው
27

በልቤ ዙፋን ላይ ሾሜሃለሁ/3x/

በዘመኔ ጌታ አድርጌሃለሁ/3x/
ዋናዬ ሁን ኢየሱስ ዋናዬ ሁን
ዋናዬ ሁን በሕይወቴ መጀመሪያ ሁን

ሌላ ሌላውን ዓይኔ አያይም /3x/

ከኢየሱስ የሚሻል ወዳጅ አላውቅም/3x/


ያሳደገኝ እሱ ሰው ያደረገኝ
በክብር ጌጥ ልብሱ የሸላለመኝ

1. በመንገዴ ሁሉ አንተን አስቀድሜ


የልብህን ሃሳብ መሻትህን ፈጽሜ
በቀረኝ ዘመኔ ልኑር በቤትህ
ፈቃድህን ላገልግል ልጣል በደጅህ

2. በሰጠኸኝ ዕድሜ በዚህ ጉብዝናዬ


ላምልክህ ጌታዬ በሁለንተናዬ
አያምረኝም ሌላ አንተ የሌለህበት
ቤትህ ይሻለኛል ሠላምህ ያለበት

3. በዘመኔ ካንተ ሌላ ባለ ዝና
የማወራው የለኝ አምላኬ ገናና
በኑሮዬ ከብረህ ታይልኝ በህይወቴ
ፍጹም እርካታዬ ይህ ነው ፍላጎቴ

4. ዛሬ ታይቶ ነገ በሚጠፋው ነገር


አላደርግም ልቤን በዚህ ዓለም ክብር
የማይናወጥ መንግስት ሰማይ ነው ርስቴ
መኖር እናፍቃለሁ በላይ በዘላለም ቤቴ
28
ምስጋና ነው ያለኝ/3x/
ሌላ ምኔን ልስጠው ያለኝ ምስጋና ነው/2x/
ተቆጥሮ አያልቅም ውለታው ብዙ ነው የተደረገልኝ
ምህረቱን ፍቅሩን ሁልጊዜ አውርቼ መች እጨርሳለሁኝ
ስለ እኔ በመስቀል መሞቱ ማዳኑ ከሲኦል ጨለማ
ያዘምረኛል ሁልጊዜ አልችልም ዝም ሊል ለጌታ/5x/

1. የማይገባኝ ነበር የተሰጠኝ ህይወት


ባልሠራሁት ሥራ አገኘሁኝ ምህረት
እስካሁን በፀጋው አለሁኝ በቤቱ
ከፊቱ እንዳልጠፋ ያዘኝ ቸርነቱ/3x/

2. የቁጣ ልጅ ነበርኩ ኃጢአት የገዛኝ


ከእግዚአብሔር ፍቅር እጅጉን የራቅኩኝ
የሞት መውጊያ ሰብሮ ከሞት የተነሳው
ታደገኝ ኢየሱስ የይሁዳ አንበሳው/3x/

3. በልዑል መጠጊያ በጥላው አርፌ


ከአውሬ ተርፍያለሁ በእርሱ ተደግፌ
ሥጋት አይገባኝም በጊዜው ሁኔታ
አባት አለኝ ጌታ በኃይል የበረታ/3x/

4. በኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው ጉልበት


የማይጠፋ ርስት የዘላለም ሕይወት
አግኝቻለሁ መዳን የእግዚአብሔር ሥጦታ
ተካፋይ ሆኛለሁ የዘላለም ደስታ/3x/

29.አድስ ምስጋና(2x)
አቀርብለታለው ለ ጌታ
ስላደረገልኝ መልካም ስራ
1.ጠላቶቼ ልያጠፉኝ ስማማሉ
ወድቀቴን ፈልገዉ ነፍሰን ሲሹ
አምላኬ ቀደመ እኔን ልያስመልጠኝ
ወጥመድ ተሰበሬ እኔም አመለጥኩኝ
2.ያደረገልኝን ሳስበው
ከ አዕምሮ በላይ ነዉ ለኔ ያረገዉ
በ ምህረቱ ብዛት ቤቱ እገባለው
ምስጋናን ዝማሬ አቀርብለታለው
3.አቤቱ ስራ ሁሉ ግሩም ነው
ስለዝህ ምስጋናን ነዉ ምሰዋዉ
ተባረክ ተወደስ ትልሀለች ነፍሰ
ዘወትር ይገባሀል አምልኮ ዉዳሰ

30. ሁሌ ነዉ ሁሌ የምትጠነቀቅልኝ
እንደ አይን ብሌን እኔን የምትጠብቀኝ X2
ምህረት ገኗል እጅግ በእኔ
የሆነ የለም አንዳች ከእኔ
እግዚአብሔር እረኛዬ/2x
እግዚአብሔር መልካም ወዳጀ/2x

1.እረኝነትህ አስገርሞኛል
በለመለመ መስክ እኔን መምራት/2
እንዳልራብ ትመግበኛል
እንዳልጠማ ከምንጭ ታረከኛል/2
እግ/ር እሬኛዬ.......

2.ከልጅነት ተሸክመሄኛል
እንደ አባትም መክሬ አሳድገሄኛል
ሰው ስላሌ አይደለም መልካም ነው የምለው
ምስክር ነኝ እኔ በግለ አውቅሀለው

3.ትላንተን ሳስበው ዛሬን ያየሁት ባንተ ነው


አንተ ባትረዳኝ ኖሮ ከጠላቴ የምያስጥለኝ ማን ነዉ
ዉግያዬን ተዋግቴ ድልን ሰተሄኛል
ላንቴ ለ እሬኛዬ ክብር ይገባሀል

31.ክርስቶስን ከሙታን ያስነሳዉ


ያ ያንተ መንፈስ ሙሉ ነዉ ሚያደርገዉ
ስለዝህ ይስራ በዉስጤ
ለመንፈስ ይገዛ መላዉ ማንነቴ
1.ያንተ ስለመሆኔ መስካሪዉ
ስጋን አሸናፍዉ ያ ያንተ መንፈስ ነዉ
በልቤ ዙፋን ላይ ሃጢያት እንዳይነግስ
አስተዋይ ያደርገኛል የክርስቶስ መንፈስ
ስለዝህ ይስራ....
2.ለሟቹ ስጋዬ ህወትን ይዘራል
ከጽድቅ የተነሳ መንፈሰን ህያዉ ያደርጋል
እላይ ያለዉን ክብር ያሳየኛል
ጸንቼ እንድቆም ሀይልን ይሰጠኛል
ስለዝህ ይስራ...
3.ክፉ የሆነዉን የስጋን ስራ ያሸንፋል
ቆሜ እንዳልወድቅ አይኖቸን ይከፍታል
ሙሉ የሚያደርገዉ የክርስቶስ መንፈስ
ዘመኔን በሙሉ ለራሱ ይቀድስ

You might also like