You are on page 1of 17

ነፍስ ፡ እስከመስጠት ፡ ድረስ

በዘላለም ፡ መውደድ ፡ ወዶኛል (፪x) 


ፍቅሩ ፡ ይቀንሳል ፡ ብዬ
አልሰጋም ፡ በዚህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
አልሰጋም ፡ በዚህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (፪x)
አዝ፦ ለዘላለም ፡ ነዉ (፬x)
ሲወድ ፡ ጌታ ፡ እስከመስቀል ፡ ነዉ (፪x)
ሲወድ ፡ ጌታ ፡ ላይጠላ ፡ ነዉ (፪x)
እስከመጨረሻ ፡ ወዶኛል ፡ ወዶኛል 
በማይለቀው ፡ እጁ ፡ ይዞኛል ፡ ይዞኛል
ከትከሻው ፡ መሃል ፡ አድራለሁ ፡ አድራለሁ
ፍቅሩ ፡ እያባበለኝ ፡ ኖራለሁ ፡ ኖራለሁ
ዛሬ ፡ ይዞ ፡ ነገ ፡ አይለቀኝም ፡ ሂጂ ፡ ብሎ ፡ አያባርረኝም
ተመችቶኝ ፡ ኖራለሁ ፡ በቤቱ ፡ ተሸክሞኝ ፡ በሰፊ ፡ ትዕግስቱ
ዛሬ ፡ ይዞ ፡ ነገ ፡ አይለቀኝም ፡ ሂጂ ፡ ብሎ ፡ አያባርረኝም
ያለፍርሃት፡ ኖራለሁ ፡ በቤቱ ፡ ተሸክሞኝ ፡ በሰፊ ፡ ትዕግስቱ
ነፍስ ፡ እስከመስጠት ፡ ድረስ
በዘላለም ፡ መውደድ ፡ ወዶኛል (፪x) 
ፍቅሩ ፡ ይቀንሳል ፡ ብዬ
አልሰጋም ፡ በዚህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
አልሰጋም ፡ በዚህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (፪x)
አዝ፦ ለዘላለም ፡ ነዉ (፬x)
ሲወድ ፡ ጌታ ፡ እስከመስቀል ፡ ነዉ (፪x)
ሲወድ ፡ ጌታ ፡ ላይጠላ ፡ ነዉ (፪x)
አይጓደልም ፡ ልማዴ
እሰዋለሁኝ፡ ለውዴ
ሆነ ፡ አል ፡ ነገሩ
አባቴ ፡ አለ ፡ በመንበሩ
አይቋረጥም ፡ ልማዴ
እሰግዳለሁኝ ፡ ለውዴ
ሞላ ፡ አልሞላ ፡ ነገሩ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በመንበሩ
አዝ፦ በማደሪያው ፡ ላይ
በዙፋኑ ፡ ላይ
በመንበሩ ፡ ላይ
በከፍታው ፡ ላይ
አለ ፡ የሚሰማ ፡ የሚያይ
አለ ፡ የሚረዳ ፡ የሚያይ
አለ ፡ የሚፈውስ ፡ የሚያይ
አለ ፡ የሚረዳ ፡ የሚያይ
የልቤ ፡ ደስታ ፡ ጌታ
የልቤ ፡ ደስታ ፡ የሱስ
በገናዬን ፡ ልያዝ ፡ ልቀኝልህ
ነፍሴ ፡ ውላ ፡ ታድራለች ፡ በስምህ (፪x)
ምንም ፡ በሌለበት ፡ ማይነጥፍ ፡ ደስታ
ብር ፡ ያልደጋገፈው ፡ የዚህ ፡ አለም ፡ ስጦታ
ፊትን ፡ የሚያበራ ፡ ከላይ ፡ የሆነው
ዘላቂው ፡ ደስታዬ ፡ ጌታ ፡ ባንተ ፡ እኮ ፡ ነው
እንዴት ፡ ተደርጐ ፡ ይወራል
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ ፡ ጌታዬ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ ፡ አባባ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ (፪x)

አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ኖሮ


ወድቄ ፡ ነበረ ፡ ድሮ
አባብዬ ፡ አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ኖሮ
ጠፍቼ ፡ ነበረ ፡ ድሮ (፪x)
ምሥጋና ፡ የሚገባውን
እግዚአብሔርን ፡ እጠራለሁ
ከጠላቶቼም ፡ እድናለሁ (፪x)

የአመጽ ፡ ፈሳሽ ፡ ሲያስፈራራኝ ፡ የሲዖል ፡ ጣርም ፡ ሲከበኝ


አምላክህ ፡ የታለ ፡ ሲለኝ ፡ ባላንጣዬ ፡ ሲያፌዝብኝ
ከመሠረቴ ፡ ሊነቅለኝ ፡ ቆይ ፡ ብቻ ፡ ሲል ፡ ሲዝትብኝ
የጌታን ፡ ሥም ፡ እጠራለሁ ፡ ከጠላቴም ፡ እድናለሁ

ምሥጋና ፡ የሚገባውን
እግዚአብሔርን ፡ እጠራለሁ
ከጠላቶቼም ፡ እድናለሁ (፪x)

የጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ለእኔ ፡ የፀና ፡ ግንብ ፡ ነውና


እስከዛሬም ፡ እርሱን ፡ ጠርቶ ፡ ማንም ፡ አላፈረምና
በኪሩቤል ፡ የሚኖረው ፡ ሙሉ ፡ ተስፋ ፡ ስለሰጠኝ
ታምኜ ፡ ሥሙን ፡ እጠራለሁ ፡ ከጠላቴም ፡ እድናለሁ

ምሥጋና ፡ የሚገባውን
እግዚአብሔርን ፡ እጠራለሁ
ከጠላቶቼም ፡ እድናለሁ (፪x)
በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ ሁሉ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ጠራሁት
ስቅስቅ ፡ እያልኩኝ ፡ በእንባ ፡ የሆዴን ፡ ብሶት ፡ ነገርኩት
ከዚያም ፡ በበቀል ፡ ወረደ ፡ ከሰማይ ፡ አንጐደጐደ
በመብረቁ ፡ አወካቸው ፡ በፍላጻው ፡ በተናቸው

ምሥጋና ፡ የሚገባውን
እግዚአብሔርን ፡ እጠራለሁ
ከጠላቶቼም ፡ እድናለሁ (፪x)

ለጥርሶቻቸው ፡ ንክሻ ፡ አላደረገኝምና


ከተዘረጋብኝ ፡ ወጥመድ ፡ ሁሌ ፡ አድኖኛልና
አርነቴን ፡ ከሚቀማ ፡ ከሰይጣን ፡ ጋርዶኛልና
ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ሃሌሉያ ፡ እያልኩኝ ፡ ልኑር ፡ በእርሱ ፡ ጉያ

ምሥጋና ፡ የሚገባውን
እግዚአብሔርን ፡ እጠራለሁ
ከጠላቶቼም ፡ እድናለሁ (፪x)
ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል
ከሞትም ያድናል ኢየሱስ (2x)
አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ኖሮ
ወድቄ ፡ ነበረ ፡ ድሮ
አባብዬ ፡ አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ኖሮ
ጠፍቼ ፡ ነበረ ፡ ድሮ (፪x)

አዝ፦ የልቤ ፡ ደስታ ፡ ጌታ


የልቤ ፡ ደስታ ፡ የሱስ
በገናዬን ፡ ልያዝ ፡ ልቀኝልህ
ነፍሴ ፡ ውላ ፡ ታድራለች ፡ በስምህ (፪x)

ምንም ፡ በሌለበት ፡ ማይነጥፍ ፡ ደስታ


ብር ፡ ያልደጋገፈው ፡ የዚህ ፡ አለም ፡ ስጦታ
ፊትን ፡ የሚያበራ ፡ ከላይ ፡ የሆነው
ዘላቂው ፡ ደስታዬ ፡ ጌታ ፡ ባንተ ፡ እኮ ፡ ነው
አዝ፦ ተራራ ፡ የሚናድለት ፡ ጨለማ ፡ ሚገፈፍለት
ነፋሳት ፡ የሚገዙለት ፡ ወጀቡ ፡ ሚታዘዝለት
ቃሉ ፡ ሲያስተምረን ፡ መንፈሱ ፡ ሲያጽናናን ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይሁን
ካቻምናን ፡ አለፍን ፡ ተሻገርን ፡ አምናን  ጉንድሹ ቢመጣ ፡ አካሉ ፡ ተሟልቶ
ጠላት ፡ ቢቃወመን ፡ እጅግ ፡ ተገዳድሮ እውሩ ፡ ቢመጣ ፡ ሄደ ፡ ዓይኑ ፡ ተከፍቶ
ጌታ ፡ ተዋግቶልን ፡ ደረስን ፡ ዘንድሮ (፪x) ሙታን ፡ ተነስተዋል ፡ የተራቡም ፡ በሉ
እጁን ፡ ከዘረጋ ፡ ይደርሳል ፡ ለሁሉ (፪x)
አዝ፦ ተራራ ፡ የሚናድለት ፡ ጨለማ ፡
ሚገፈፍለት አዝ፦ ተራራ ፡ የሚናድለት ፡ ጨለማ ፡ ሚገፈፍለት
ነፋሳት ፡ የሚገዙለት ፡ ወጀቡ ፡ ሚታዘዝለት ነፋሳት ፡ የሚገዙለት ፡ ወጀቡ ፡ ሚታዘዝለት
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት

መጻተኞች ፡ ብንሆን ፡ ምድር ፡ ያልተገባን ሕዝቡ ፡ እንደሆነ ፡ አይቀር ፡ ተስፋውን ፡ መውረሱ


ምንም ፡ አልጐደለን ፡ ለእኛ ፡ ከሚረባን ፈርዖን ፡ ለምን ፡ ነው ፡ ኃይሉን ፡ መጨረሱ
ወላጅ ፡ እንደሌለው ፡ ልጅ ፡ አላደረገን ባሕር ፡ ተከፈለ ፡ በድል ፡ ተሻገሩ
የሁላችን ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር ፡ አንዴ ፡ እስከዘለዓለም ፡ ተሰብሯል ፡ ቀንበሩ (፪x)
ይመስገን (፪x)
አዝ፦ ተራራ ፡ የሚናድለት ፡ ጨለማ ፡ ሚገፈፍለት
ነፋሳት ፡ የሚገዙለት ፡ ወጀቡ ፡ ሚታዘዝለት
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት

You might also like