You are on page 1of 3

ኪነ ጥበባት ክፍል ዘ ቀሃ ጎንደር

 ሁለት ሰዎች ከተለያየ ቦታ ሲመጡ መድረክ ላይ ይታያሉ የሁለቱም ሰዎች ማለፊያ መንገድ አንድ በመሆኑ መንገዱ አጠገብ ያለው
ድልድይ ደግሞ የሚያሳልፈው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ በዚያ አገር ባህል እና ወግ ደግሞ ሁለትሰዎች እዚያ ድልድይ ላይ ከተገናኙ በልሃ ልበልሃ
ተባብለው ያሸነፈው ሰው በቅሚያ ያልፋል፡፡ ይሕም ነገር አሁን ተከሰተ፡፡

1. እንግዲህ ወንድሜ ባገሩ ወግና ባህል


በልሃ ልበልሃ እንባባል ቀዳሚው እንዲለይ

2. ምን ገዶኝ ወንድም ጃል
የቀየው ባህልና ወግ አይደል
ታዲያ ቀዳሚው እንዲለይ
በዕጣ መጣጣል ብንለያይ
እኔ ግን በእድሜም ከፍ ስለምትለኝ
አንተ ብትቀድም ነው የሚበጀኝ

1) ስላከበርከኝ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው
እንግዲህ በልሃ ልበልሃ ልጀምረው
በልሃ ልበልሃ
ካልመለስክ ልቅጣሃ

2) በላሃ በለኛ
ካልመለስኩ ቅጣኛ

1. ከሲና በርሃ ተነስቶ


ሃመልማል ሳይቃጠል አይቶ
ምንም አፉ ጎልዳፋ ቢሆን
እግዚአብሔር ለክብሩ መገለጫ ያሳየን
በዘጠኝ ተአምራት በአስረኛ ሞተ በኩር
የአምላክን ሕዝብ ከፈርዖን አገዛዝ ያስጣለ በተአምር
የስራኤልን ሕዝብ የመራ
ማነው ስሙን ጥራ?

2. እሱንማ መች አጥቼው
እናቱ ሸሽጋ በሳጥን ያኖረችው
የፈርዖን ልጅ አግኝታ በፍቅር ያቀፈችው
ያ መልከ መልካም እንቦቀቅላ
ፍትፍቱን ትቶ እሳቱን የበላ
የአምስት መፅሐፍ ፀሐፊ የተባለው
ሊቁ ታላቁ አባት ሊቀ ነቢያት ሙሴ ነው፡፡

1. ትክክል ብልሃል መልሱንም አውቀሃል


በል ተራው ያንተ ነው ጥያቄህ የታል

2. በልሃ ልበልሃ
ካላወክ ልቅጣሃ
1. በልሃ በለኛ
ካላወኩ ቅጣኛ

1. አርጢሞስ አምላክ ሳትሆን ተቀራፂ ምስል


ባንዴ የምትፈርስ በእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል
ብሎ ባመሰስተማር ለእስር የበቃሁ
በፈላም ውሃ ውስጥ የተቀቀለም ነው
ይሔም አልበቃውም ንጉሱም ጨካኝ ነው
በፍጥሞ ደሴት ውስጥ በግዞት ያለ ነው
በዛ ውስጥ እያለ አንድ ነገር ሰርቷል
የሰራሁስ ስራ? ስሙስ ማን ይባላል?

2. ይህንን ካላወኩ ምኑን አወኩ ሊባል


ባጭሩ ልንገርህ ኤሊያስም አይደል

1. ፍፁም ስህተት ነው መልሱም ይህ አይደል


ቅጣትህን ተቀበል

2. ይሔው ለቅጣቴ ጎንበስ ቀና ብዬ


ባለማወቄማ ልቀጣ ጌታዬ

1. አቡነ ዘበሰማያት ይደገም ግዕዙ


እሱን ካላወቁ ሌላ ይታዘዙ

2. ይሔው ልጀምረው ያደኩበትን


ከየኔታ እግር ስር የተማርኩትን
አቡነ ሰበሰማያት …….

1. በትክክል ነው ግዕዙንም ያልከው


የጥያቄዬን መልስ ስማኝ ልናገር ነው
በፍጥሞ ደሴት ውስጥ በግዞት ተቀምጦ
ራዕዩንም ፃፈው ብራናውን ገልጦ
የዚህ ታላቅ አባት ስሙም ክብር ያለው
ቅዱስ ዮሐንስ ነው ደቀ መዝሙሩም ነው
እንግዲህ አሁንም ጠያቂው እኜ ነኝ
በልሃ ልበልሃ
ካላወክ ልቅጣሃ

2. በልሃ በለኛ
ካላወኩ ቅጣኛ

1. በጎጃም ሃገር በዳማ ሥላሴ


አንድ ፀሐይ ወጥታ ታዛዥ ለሥላሴ
በ 7 አመቱ ብርሃኑን አጥቶ
ለአምስት አመት ቆየ በጸሎት በርትቶ
ጌታ አምላካችን በአካል ተገልፃል
አዳኝ በመሆንህ ዓይንህ ይስራ ተመልሶ
ይሔንንም ሰጠው 12 አክናፍ
ዓለምን ይዞራል በመፍጠን
ታዲያ ይህ አባት ስሙን በል ጥራልኝ
እውቀትህን ገልጸህ ለይተህ አሳየኝ
2. ማንም አይረሳቸው አባ ዘርዐብሩክ
ሐይን ያቆሙ ታላቅ አባት ናቸው
ለወንዝ መፅሐፍን ባደራ የሰጡ
በጸሎት በስግደት የኖሩ ሳይወጡ
የዞንዶ ጥርስ ሳይቀር አስታርቀው ሲቆጥሩ
እንዴት ይረሳሉ እኝህ ታላቅ አባት
ይደርብን ዘውትር የእሳቸው በረከት

1. በእውነት ልክ ነው ፍፁም የለው ስህተት


እንዴት ይረሳሉ እኝህ ታላቅ አባት

2. በል እንግዲህ ያሸነፍኩ እኔ ነኝ
ድልድዩን ልቀቅ በሰላም አሻግረኝ

1. ይሔው ለቀኩልህ በሰላም ተሸገር


ካሸነፍከኝማ ላንተ ይሁን ክብር
ወጉ ማዕረጉን አልጥስ
አንተ እኮ ነህ ንጉስ

2. ወጉን ማዕረጉን የሚቀድመው አለ


ማክበር መከባበር የኢትዮጵያውያን ወጋቸው አይደለ
አንተም እኮመ እኔን በእድሜዬ ሰትበልጠኝ
በጥያቄው ሳይሆን በእድሜዬ አሸነፍከኝ

ሁለቱም ሰዎች ተሳስመው ተመራርቀው በእድሜ የሚበልጠው ሰውዬ ቀድሞ ይሻገራል ቀጥሎ ተሸግሮ ወጥቶ ይሔዳል

የደ/ስ/ቀሃ ኢየሱስ ሰ/ት/ቤት ኪነ ጥበባት ክፍል ጎንደር

You might also like