You are on page 1of 2

++++++++++++++++++++++++++

የማህበረ አቡነ ሰላማ አጭር ታሪክ

+++++++++++++++++++++++++++

ማኅበራችን አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መረዳጃ ግብረ ሰናይ ማህበር /Abune Selama Kesate Birhan Self Help
Association / በሚል ስያሜ የሚታወቅ ሲሆን ማህበሩ በሰኔ 2 ቀን 1994 ዓ/ም በአባ ሳሙኤል ወልደሰላማ እና
በመምህር አባ ገብረመድህን በርሄ የተቋቋመ ግብረ ሰናይ ማህበር ነው። ማህበሩ ሲመሰረት የነበሩት ጥቂት ሰዎች
በአሁኑ ሰዓት በርካታ አባላትና ደጋፊዎች በማፍራት በተለያዩ ቦታዎች ቅርንጫፍ ማህበራት በመክፈት በጎ ስራ እየሰራ
ይገኛል፡፡ ማህበሩ ህግጋተ እግዚአብሔር የሆንቱን አስርቱ ትእዛዛትና ስድስቱ ቃላተ ወንጌል በመተግበር እንዲሁም
በቅዱሳን ስም ፀበል ፀዲቅ በመዘከር የአባላቱን ገንዘብ ፣ጉልበትና እውቀት በማስተባበር የተቸገሩ ወገኖቻችንና ገዳማት
(አብያተ ክርስትያናት) በመርዳት ላይ ይገኛል::

ማኅበራችን የያዘውን ዓላማና ራእይ ለማስፈፀም የራሱ የሆነ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ቦርድና የስራ አመራር መዋቅር
በማውጣት በተለያዩ የስራ ክፍሎች የተደራጀ ነው። እያንዳንዳቸው የስራ ክፍሎች የማህበሩን ዓላማና ራእይ አንግበው
ለሚያከናውኑት ስራ የራሳቸው የሆነ የሰው ሃይልና የገንዘብ ዓቅም /በጀት/ ይዘው የማህበሩ በጎ ስራዎች እንዲሰፋ ትልቅ
አስተዋፅኦ ያላቸውና አሁንም በተጠናከረ መልኩ በመስራት ላይ የሚገኙ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ማህበሩ
በሚያካሂዳቸው መንፈሳዊ የበጎ ስራ አገልግሎቶች አማካይነት የተመሰረቱ የቅርንጫፍ ማህበራት ብዛት በየጊዜው
እየጨመረ ነው። በአሁኑ ሰዓት ማህበሩ በተለያዩ ቦታዎች ቅርንጫፍ ማበራት ሲኖሩት ዋና ማእከሉ በሚሰጣቸው
መመርያ መሰረት በማድረግ የጎላ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ።

የማህበሩ ዓላማ

============

ማህበሩ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ኣሁን እየሰራባቸው የሚገኘው ዝርዝር ዓላማዎች፡-

ሀ/. በአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃንና በቅዱሳን ስም በመሰባሰብ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በመላው ኢትዮጵያ ማዳረስና
ከኤች.አይ.ቪ ኤድስ ሕብረተሰቡ እራሱን እንዲጠብቅ ማድረግ፤

ለ/. አድሎና ማግለል እንዳይኖር ታላላቅ መንፈሳዊ ክብረ በዓላት በሚውሉበት ቀን ህዝቡን በማስተባበርና የምሳ
ግብዣበማዘጋጀት ፍቅርንና መተሳሰብን ማስተማር፤

ሐ/. በሆስፒታልና በየቤታቸው ሆነው የሚሰቃዩ የአልጋ ቁራኛ በሽተኞችን በመጎብኘት አቅም በፈቀደው በመርዳትና
በመንከባከብ የማጽናኛ ትምህርት መስጠት፤

መ/. በኢትዮጵያ የሚገኙ አድባር ገዳማትና ቤተክርስቲያናት በየበዓላቸው ቀን ጉዞ በማዘጋጀት


ማስጎብኘትና፤የተቸገሩገዳማትን በንዋየ ቅዱሳት በመርዳት ቅርሳቸው እንዲጠበቅ መርዳት፤

ሠ/. ዘወትር እሁድ እና በየክብረ በዓላት ልዩ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ለምዕመናኑ በማዘጋጀት እንዲማሩና
እንዲዘምሩ ማድረግ፤
ረ/. ምእመናን በብልሹ ስነምግባር ተበላሽተው አላስፈላጊ ቦታ እንዳይውሉና ለተለያዩ ጎጂ ሱሶች እንዳይጋለጡ የባህሪ
ለውጥ የሚያመጣ ትምህርት በመስጠት በመልካም ስነምግባር የታነጸ ዜጋ መፍጠር፤

የማህበሩ ተልእኮ

============

እግዚአብሄርንና ባለእንጀራህን በመውደድ እውነተኛ አምልኮተ እግዚአብሄር መፈፀምና ፃድቁ ህሩይ ማር ኣቡነ ሰላማ
ከሳቴ ብርሃን በሁሉም ቦታ በማስተዋወቅ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ የሁሉም ቅዱሳን በረከት ረድኤት
ለመላው ዓለም ማዳረስ ::

የማኅበሩ ራእይ

============

ስርአተ እግዚአብሄር የጠበቀች ንፅህና ቅድሰና ያላት መተሳሰብና መደጋገፍ የሰፈነባት ምግባረ ትሩፋት የሚሰራባት
ሃገራችንና ዓለማችንን ማየት::

You might also like