You are on page 1of 2

ምክር

አሥሩ የሕይወት መርሆዎች/ለደስተኛ ህይወት/

ሳሙኤል በለጤ (የፍሬ ነኝ)

1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን

ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን

ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር

ነው።

2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ ይሁን፡-

ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ

ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው።

ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል

እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን

ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን

ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡

4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ

እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር

ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።

5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ

መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ

በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ

ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና

ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና

መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡

6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦


ሰዎችን አትናቅ፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች

ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡

7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ

በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ

የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው።

8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤

የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ

እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን ሲያጠፋ ይቅር

በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት

ተንከባከበው፡፡

9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው

ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት

ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ

አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ

አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን

ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን

ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው?

መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡፡

ምንጭ ዶ/ር እርህመት ሰኢድ

Join

@xibeb

@xibeb

@xibeb

You might also like