You are on page 1of 3

By Yayesew Shimelis

---

‹‹ትግራይ አኩርፋለች›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

----------------------------------------------------

ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ ባሳለፍነው ቅዳሜ በሸራተን አዲስ ‹‹ትግራይ እንዳኮረፈች›› ተናግረዋል፡፡ በርግጥ አኩርፋ
ስለመሆኗ ከእርሳቸው የበለጠ መረጃ የለኝም፡፡ በርግጥ ምልክቶቹ ታይተዋል፡፡ Forget TPLF, focus on elites in
general. (ሕወሓትማ ዛሬም ከዐቢይ ጋር ስትዶልት ነው የምትውለው)፡፡ የትግራይ ፖለቲካ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ
በተሻለ መልኩ የሚናበብ ነው፡፡ ለድጋፍም ለተቃውሞ አይቸኩልም፡፡ ሰከን ማለት ይችላል፡፡ ለዚያም ነው በመላ ሀገሪቱ
‹‹የተደምረናል›› ሰልፎች ሲቀጣጠሉ ትግራይ በአርምሞ ዝም ያለችው፡ ፡አብዲ ኢሌ እንኳን እኮ ተደምሬያለሁ ብሎ
ሰልፍ ጠርቶ በጅግጅጋ ስታድየም አዘፍኗል፡፡ ትግራይ ግን ያ ያልሆነው የሚናበብና የሰከነ ፖለቲካል ማኅበረሰብ
ስለተፈጠረ ይመስለኛል፡፡ ወደድንም ጠላንም ይህንን መቀበል አለብን፡፡ ለምሳሌ በፊት በፊት ሕወሓት መራሹን
ኢሕአዴግ የሚቃወሙ ፖለቲከኞች ሕዝቡንም መሪዎቹንም ነበር የሚሳደቡት፡፡ ‹‹ትግሬ ወደ መቀሌ›› የሚለውንና
‹‹አሳውን ለማጥመድ ውሃውን ማድረቅ›› የተባለውን ዘመቻ ማስታወስ ይቻላል፡፡

አሁን ያለውን ኦሕዴድ መራሽ ኢሕአዴግ የሚቃወሙ የትግራይ ፖለቲካል ሶሳይቲስ ግን ትኩረታቸው ጠቅላይሚኒስትር
ዐቢይ ላይ ነው፡፡ እርሳቸውን በተለያዩ ጸያፍ ቅጽሎች ማንጓጠጥ ተገቢ አለመሆኑን ባምንም ጠቅላይሚኒስትሩ
የበቀሉበትን ማኅበረሰብ አለመሳደባቸውን ማድነቅ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ከስክነትና ስትራቴጂክ አጋርን ከማወቅ እንዲሁም
ፖለቲካን ከመረዳት ይመነጫል፡፡

ግን ትግራይ ለምን እንዳኮረፈች መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡

እንደሚታወቀው የትግራይ ሕዝብ በዓቢይ መምጣት መደሰቱን ቀድሞ ገልጾ ነበር፡፡ ኋላ ላይ ግን መቃቃር መጣ፡፡ለምን?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ወደ መቐለ የተጓዙት ከጅግጅጋው የመጀመሪያ ጉዟቸው በኋላ ነበር፡፡ በወቅቱ በትግራይ ክልል
ከፍተኛ ድጋፍ እንዳላቸው ያረጋገጡበት ነበር፡፡ ሰማዕታት አዳራሽ በተካሄደው ውይይት ላይም ከክልሉ ሰዎች ጋር ጥሩ
መግባባት እንደነበራቸው ታይቷል፡፡ ይህ የተለያየ ምክንያት ይኖረዋል፡፡ በአንድ በኩል ሕወሓት በማዕከላዊ መንግሥት ላይ
ያለውን ጉልበት ስቦ ወደ ትግራይ እንዲያተኩር በፈለግ በለሌላ በኩል ደግሞ በሕወሓት ሥልጣን ምክንያት በትንሽ ትልቁ
የሚከሰሰውን፣የሚፈናቀለውን ትግራዋይ ስቃዩ እንዲቀንስለት በመሻት ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ እና ትግራይ የተኳረፉት በአሜሪካ ጉዟቸው ወቅት እንደሆነ የሚያምኑ ብዙ ናቸው፡፡ በአሜሪካ
የተለያዩ ግዛቶች ከዳያስፖራዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት የተናገሯቸው ንግግሮች ብዙዎችን እንዳስከፋ ይገመታል፡፡
በወቅቱ ዳያስፖራዎቹ ጥያቄ ሲጠይቁ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አካባቢያቸውን እየጠቀሱ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የትግራይ
ሰዎች መሆናቸውን የገለጹ ሰዎች የጠየቋቸውን ጥያቄዎች ሲያጣጥሉ ከመታየታቸውም በዘለለ የመለሱበት መንገድ
ትግራይንና ሕዝቡ ጀግናዬ ብሎ የሚያስባቸውን ሰዎች አንኳስሷል ብሎ የሚያስብ ሰው ጥቂት አይደለም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ አሜሪካ የሄዱት ከሰኔ 16 ቱ የግድያ ሙከራ በኋላ ስለነበር ፣‹‹ያንን ጥቃት ያደረሱት ሰዎች ለምን
በስም አይገለጹም›› ተብለው ከአንዲት ትግራዋይ ጥያቄ ሲቀርብላቸው ‹‹ከደሙ ንጹህ ነን ልትሉ ከሆነ አይደላችሁም፤
ገና ማን ፋይናንስ እንዳደረገ፣ እንዳሰለጠነና እንዳሰማራ እየተጣራ ነው›› ብለው ተናገሩ፡፡ የዚህን ንግግር አሽሙር
‹‹ከጥቃቱ ጀርባ የትግራይ ሰዎችም አሉበት›› የሚል ነው ብለው የተረጎሙት ብዙዎች ናቸው፡፡ እስካሁንም ፍርድቤትም
ሆነ አቃቤሕግ በዚህ ጉዳይ ላይ የወነጀለው ትግራዋይ ግን አልተገኘም፡፡

‹‹ብንሞትም አረቄ ቤት አንሞትም›› የሚለው መልሳቸውንም አሽሙር አድርገው የወሰዱት ከጥቂት በላይ
ናቸው፡፡‹‹ሐየሎም አርዐያን ሰደበብን›› ብለው የተቆጡ የትግራይ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡

‹‹በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሰው ዝመት እና ተዋጋ ሲሉኝ እኔ ዘምቻለሁ፤ አሁንም ቢሆን ከኤርትራ ጋር
ስላለው ጉዳይ ሕዝቡ አያገባውም እኔ ያልኩትን ተቀብሎ መፈጸም አለበት›› ብለው የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ
በአብዛኛው የትግራይ ኤሊት ዘንድ ንግግራቸው አልተወደደላቸውም፡፡ በአንድ በኩል ጦርነቱን መዋጋት የለብንም ይሉ
የነበሩትን መለስ ዜናዊን ጦረኛ አድርገዋቸዋል የሚል ቅሬታ ሲሰማ፣ በሌላ በኩል በራሳችን ጉዳይ እንዴት አያገባችሁም
እንባላለን የሚል ጥያቄም ያለው ትግራዋይ እንዲበዛ ሰበብ ሆኗል፡፡

‹‹ያለፉት 27 ዓመታት ቆሻሻ ናቸው›› የሚለው ንግግራቸውም፣ በሕወሓት ዙሪያ ያለውን የፖለቲካ ኃይል ይጎረብጣል፤
በሕወሓት የበላይነት ተመርቷል የሚል ትርክት ላለው ፖለቲካ ይህ የእርሳቸው ንግግር በሕወሓት ዙሪያ ላለው ትግራዋይ
ምቾት አልሰጠም፡፡ጥፋቱም ልማቱም በልክ መቅረብ አለበት ብለው የተከራከሩ ሰዎች ብዙ ነበሩ-በወቅቱ፡፡

የትግራይን የፖለቲካ ማኅበረሰብ የበለጠ ጥርስ የነከሰባቸው ግን ከዶክመንተሪው በኋላ ነው፡፡መጀመሪያ ‹‹ትግርኛ
ተናጋሪዎች ›› ዘረፉን፣ ኋላ ላይ ‹‹ትግርኛ ተናጋሪዎች ገረፉን›› ተብሎ የተሰራው ዘጋቢ ፊልም መላ ትግራይን ጸጉር
ያስነጨ ይመስለኛል፡፡ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ የፃፉት ወይም ኤዲት ያደረጉት የሚመስለው ሁለቱም ዘጋቢ ፊልም
ከአሳውን መያዝና ውሃውን ማድረቅ ዘመቻ ተለይቶ መታየት አልቻለም፡፡

የጠቅላይሚኒስትሩን አካሄድ ከትግራይ ጋር ያኳረፈውም እነዚህ ይመስሉኛል፡፡

አቶ መለስን የርዕዮተዓለምና የፖለቲካ ሊቅ፣ ሐየሎም አርዐያን የጀግንነት ቁንጮ አድርጎ ለሚያምነው ለእያንዳንዱ
ትግራዋይ ይህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ የአሜሪካ ንግግር ምቾት የሚሰጥ አይደለም፡፡ ስለ ቲም ለማ
ሲያወሩም፣‹‹ቲም ለማ ማለት ደመቀ ነው፤ ሙፍሪያት ናት፣…››እያሉ ሲዘረዝሩ፣‹‹አምባቸው ሰላም ብሏችኋል፣ገዱ
ሰላም ብሏችኋል…›› እያሉም የባለሥልጣናትን ሥም ከየብሔሩ ሲጠሩ፣ ከትግራይ አንድም ሰው አልጠቀሱም፡፡ ይህ
ደግሞ የትግራይ ልሂቃን ‹‹ከጠራኋቸው ውጭ ያሉት እንደ እኛ አይደሉም›› አሉ ብሎ ትርጉም እንዲሰጠው አድርጓል፡፡
በዚህና በመሰል ጉዳዮች በፌደራሉ መንግሥትና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያኮረፈ ይመስለኛል፡፡ ለዚያም ነው በአማራ
ክልል እና በኦሮሚያ በከፊል እንደታየው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግሮችና ፎቶዎች በትግራይ ሰልፎች ላይ ያልታዩት፡፡
ሆኖም ግን አንድም ጊዜ በየትኛውም ሰልፍ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶዎች ሲቃጠሉ አልተስተዋለም፤ እርሳቸውን
የሚቃወሙ መፈክሮችም አልታዩም፡፡ please share and like.

You might also like