Professional Documents
Culture Documents
1
1
የተቸገሩ ሰዎች የምላቸው በኑሮዋቸው ማለትም በገቢያቸው ዝቅተኛ ሆኖ መሰረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎት
የምንላቸውን (ምግብ፣መጠለያ፣ልብስ…) ማሟልት የማይችሉ፣
የተደላደለ ኑሮ ኖሯቸው በቤታቸው ደስታ እና ፍቅር የሌላቸው፣
በህይወታቸው ተስፋ የሌላቸው ፣
እውቀት የጎደላቸው ያላቸውን እና የተሰጣቸውን ነገር እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ የማያውቁ
ሃይማኖቴን በፍቅር ለመግለፅ እሞክራለው ነገር ግን ከእግዜአብሄር ምላሽ አገኛለው ብዬ ስለማስብ ነው፣
እንዴት?
ለተቸገረ ሰው በመስጠት
ሰው በማክበር
ሰው በመውደድ (በገደብ) ሰውን ያለ ምክንያት አልወደውም ያለምክንያት ግን ልጠላው እችላለው
የት
በእምነት ቦታ
በቤት ውስጥ
በአካባቤ
በስራ ቦታ ….
ለማን
ለቤተሰቦቼ
ለስራ ባልደረቦቼ
ለነድያን
3. እየቆረብሽ ነው ?ካልቆረብሽ ለምን?መቼ ታስበሻል?
እየቆረብሽ ነው ?
አልቆረብኩም
ካልቆረብሽ ለምን?
መቼ ታስቢያለሽ?
በስራ እየተረጎምኩት ነው ብለሽ የምታስቢው ሃይማኖታዊ ትእዛዝ የቱ ነው? ፍጹም አከብራቸዋለሁ ብዬ ባላስብም ግን በስራ
ለመተርጎም የምሞክራቸው
የማትፈጽሚውስ?
አትዋሽ
ባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር
የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ
የባልንጀራህን ቤት አትመኝ
አባትህንና እናትህን አክብር
ለምን?
በወቅቱ ልክ የሆንኩ ስለሚመስለኝ
ልክ እንዳልሆንኩ ባውቅም ባለማድረጌ የማገኘው ነገር በልጦ ስለሚታየኝ
ስተቶችን በተደጋጋሚ ከመፈጸሜ የተነሳ ልማድ ሆኖ በመቅረቱ
ምሳሌ ይሰጥበት?
በአካባቢዬ የእውነት የሚያመልኩ እና ትእዛቱንም የሚያከብሩ ሰዎች አውቃለው ሰውን የሚወዱ የማይዋሹ፣
አዛኝ፣ ለተራበ የሚያበሉ፣ ሰውን ማማት የሚጸየፉ,፣የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ በፍርሃትና በንጽህና
የሚፈጽሙ ፣በማንኛኛም ሁኔታ በሃዘንም በደስታም እግዚያብሄርን የሚያመሰግን ሰው አውቃለሁ፡፡
6. ስለገነት እና ሲኦል ፣መንግስተ ሰማያት እና ገሃነመ እሳት….ያለሽ ኅሊናዊ ስዕል ምንድነው›
ገነት
በምድር ላይ ሳሉ የእግዚአብሄርን ትእዛዝ ሲፈፅሙ የኖሩ ሰዎች ሲሞቱ የእግዚያብሄር ዳግም መምጫው
እስኪደርስ ድረስ በጊዜያዊነት ነብሳቸው የምትቆይበት ቦታ ፣
አረንጓዴና ለም ቦታ፣ መላክቶች እያሸበሸቡ ፍጠሪያቸውን የሚያመሰግኑበት ቦታ አድርጌ እስለዋለሁ፣
ችግር ረሃብ በሽታ የሚባል ነገር የሌለው እና ነብሳችን በጣም የምትደስትበት ቦታ ይመስለኛል፣
የመንግስተ ሰማያት ተምሳሌት
ሲኦል
በምድር ላይ ሳሉ የእግዛብሄርን ትእዛዝ ሳይፈጽሙ የኖሩ ሰዎች ሲሞቱ የእግዚያብሄር ዳግም መምጫው
እስኪደርስ ድረስ በጊዜያዊነት ነብሳቸው የምትቆይበት ቦታ
የሚያቃጥል እሳት፣ሰውነት የሚሰነጣጥቅ ብርድ አጋንንት ተሰብስበው የሰውን ነብስ የሚያሰቃዩበት ቦታ
አድርጌ እስለዋለሁ
ችግር ረሃብ በሽታ ያለበት እና ነብሳችን የምትሰቃይበት ቦታ ይመስለኛል፣
የገሃነም ተምሳሌት
መንግስተ ሰማያት
እግዚአብሄር ወደ ምድር ሲመጣ እና ሲፈርድ ገነት ያሉ ነብሶች ለዘላለም በደስታ የሚኖሩባት የእግዚአብሄር ከተማ
ትመስለኛለች
ገሃነም
እግዚአብሄር ወደ ምድር ሲመጣ እና ሲፈርድ ሲኦል ያሉ ነብሶች ሁላ በስቃይ ለዘላለም የሚኖሩባት ትመስለኛለች
7. ጽድቅና ኩነኔን እንዴት ታስቢያቸዋለሽ?
ጽድቅ
ኩነኔ
ለምን ?