You are on page 1of 17

🛐ሴት በወር አበባ ጊዜ መጸለይ

ትችላለች⁉

➦በወር አበባ ጊዜ የሚከለከልስ ጸሎት አለ?

➦ተወዳጆች ሆይ ሴት ልጅ በሱባኤ ወቅት የወር አበባ/ደመ ፅጌ/ ቢታያት ከሱባኤ


የመውጣትና የመቆየቷ ነገር እንደ ገዳሙ ሥርዓት ይወሰናል፡፡ ከሱባኤ ትወጣለች ማለት
ሱባኤን (አርምሞን) ትፈታለች፣ተአቅቦዋን ትተዋለች ማለት ሳይሆን እስከምትነፃ ድረስ ገዳሙ
ባዘጋጀው ቦታ ቆይታ መጨረስ ትችላለች፡፡ በሱባኤው ላይ ወይንም መውጫው ሲቃረብ
የወር አበባ ቢታያት ሱባኤውን ማቋረጥ ሳይሆን በጊዜያዊ ቦታ መጨረስ ይገባታል፡፡

ብዙዎች እህቶቻችን ሱባኤ የምንይዙት በድንገት ነው፡፡

➦ይህ ችግር እንዳይገጥማችሁ ሱባኤ ከመግባታችሁ በፊት ቀናችሁን ቆጥራችሁ


አስተካክላችሁ ብትይዙ የበለጠ ትጠቀማላችሁ፡፡ ሰይጣን ያለጊዜው በወር አበባ ሊፈትናችሁ
ስለሚችል ቀናችሁን እንደጨረሳችሁ ሱባኤ ብትይዙ ይመረጣል፡፡ በተለይ ዓይነ ጥላ ከዓይነ
ጥላም ገርግር ዓይነ ጥላ ያለባቸውና መተት እና ድግምት የተደገመባቸው እህቶቻችን ያለ
ጊዜና ያለ ቀኑ በሚመጣ የወር አበባ በሱባኤ ወቅት ይፈተናሉ፡፡ ምስጋና ለእመቤታችን
ይሁንና እመቤታችን ንፁህ አይደላችሁም በማለት ጸሎታችሁን ቸል ስለመትል የያዛችሁትን
ሱባኤ ቀጥሉ፡፡ ምክንያቱም የእኛ ርኩሰት የእመቤታችንን ንፅህና ስለማያሳድፍ ጸሎታችንን
ትሰማናለች፡፡

➦ጸሎት ከፈጣሪ የምንገናኝበት መንገድ ስለሆነ እግዚአብሔር ጊዜን እየጠበቀ በዚህ ጊዜ


እሰማችኋለሁ በዚህን ጊዜ አልሰማችሁም አይልም፡፡ በወር አበባ ጊዜ አይጸልይም ማለት
የቤተ-ክርስትያን አስተምህሮ ሳይሆን የሰነፉ ሰይጣን የተንኮል እና የእንቅፋት ስብከት ነው፡፡
የሰይጣንን እንኳን ጸሎት ትተን ቀርቶ እየጸለይን ፈተናችንን እኛና እግዚአብሔር ነው
የምናውቀው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በዘመኑ እንደ እኛ ግራ ለተጋቡት የተሰሎንቄ ምእመናን
"ሳታቋርጡ ፀልዩ" በማለት ፀሎት በየትኛውም ሁኔታ እና አጋጣሚ ማቋረጥ እንደሌለባቸው
ፅፎላቸዋል።
➦ሴት በወር አበባዋ ጊዜ እስከ መንጻቷ ቤተ-ክርስትያን ነው መግባት የማትችለው እንጂ፣
ጸሎት ማቋረጥ የለባትም፡፡ ጊዜን ተብቆ አለመጸለይ ለሰይጣን በር መክፈት ነውና ትንሿን
ጸሎታችንን ማቋረጥ የለብንም፡፡

➦እኛ በወር አበባ ጊዜ ንፁህ አይደለንም ብለን ሥጋዊ ምግብ እንደማንተው ሁሉ ጸሎት
የነፍስ ምግብ ነውና ነፍሳችን ለ7 /ሰባት/ ቀን ከውዳሴ ማርያም ፣ ከሰኔ ጎለጎታ
፣ከአርጋኖን፣ከሰይፈ ሥላሴ፣ከሰይፈ መለኮት እና ከተለያዩ የጸሎት ማዕድ እየከለከልን
ሕያዊት ነፍሳችንን ማስራብ የለብንም፡፡ ይልቁንም ዘወትር በመጸለይ ነፍሳችንን መመገብ
ይገባናል፡፡

ተወዳጆች ሆይ ጌታችን ደመኛን እንጂ ደምን አይጠየፍም አይጠላም፡፡ ቢጠየፍማ ለአሥራ


ሁለት ዓመት ሰውነቷ በደም ሲጨቀይባት የነበረችውን ምስኪን ሴት መለኮት ጋ ጠጋ ብላ
ልብሱን ነክታ ልትድን ቀርቶ መርገምንና ሌላ በሽታን ሸምታ በተቀሰፈች ነበር፡፡ ጌታችን ግን
መልካም አመጣጧን ፣ የዓመታት ጭንቀቷን ተመልክቶ ከነደሟ ተቀብሎ በልቧ የነበረውን
አውቆ ፣ የደሟን ምንጭ አድርቆ፣ እምነቷን አድንቆ፣ ከጤናዋ ጋር በሰላም ወደ ቤቷ
መልሷታል፡፡ /ማቴ. 9፣18-26, ማር. 5፣21-43, ሉቃ. 8፤41 ይመልከቱ/

ወለላይቱ የእመብርሃን ልጆች የእመቤታችንን ባህርይ አላወቅንም እንጂ፤ እርሷ ጥዩፍነት ከቶ


በባህሪዋ የለም፡፡

➦የዛሬውን አያድርገውና ሁላችንም ስንወለድ እናቶቻችን በምጥ ሰዓት ከነደማቸው በጸሎትና


በጭንቀት ጠርተዋት አወዋልዳቸዋለች፤ አሁንም ታዋልዳቸዋለች፡፡ በአራስራቸው ጊዜ ከእነሱ
አትለይም፣ እስከ ስሙም ‹የማርያም አራስ› ተብለው በስም ይጠራሉ፡፡

አንዳንዶቹ እንኳን ሊጸለይ ቀርቶ የጸሎት መፅሐፍ አይነካም እያሉ እህቶቻችንን የሚያሳቅቁ
አሉ፡፡ እባካችሁ ሰው ከምታሳቅቁ እወቁ፣ ጠይቁ፣ ጠንቅቁ፣ ያለበለዚያ ለእህቶቻችን ፈተና
አትሁኑ፡፡ ባይሆን ጥሩ ስሜትና መንፈስ ካልተሰማችሁ ሰውነታችሁን መታጠብ፣አንቀጸ
👉
ሥጋችሁን/የከበረውን ቦታ/ ብቻ በመታጠብ ጸሎታችሁን መቀጠል ትችላላችሁ፡፡ ምናልባት
የስንፍና ምክር ሰምታችሁ ካልሆነ በስተቀር ከወር ወር ጸሎት፣የምትተዉበት ምክንያት የለም፡

ሌሎች በወር አበባ ጊዜ አይጾምም ይላሉ፣ ከየት እንዳገኙት ባይገባኝም ይህች በወር አበባ
አመካኝቶ፣ለመብላት አንኩቶ ይመስለኛል፡፡ በወር አበባ ጊዜ አንዳንድ እህቶቻችን ከፍተኛ
የሕመምና የስቃይ ስሜት የሚሰማቸው ብሎም እስከ ሕክምና የሚያደርሳቸው ከሆነ
ምናልባት መድሃኒት ሊወስዱ ስለሚችሉ እነርሱን አይመለከትም፡፡

➦እኛ የምንረክሰው በወር አበባ ጊዜ ሳይሆን ኃጢአት በመሥራት ሥጋችንንም ነፍሳችንንም


ስናደማ ነው፡፡ ያኔ በሁሉም እንረክሳለን፡፡ ጸሎታችን በእግዚአብሔር እና በእመቤታችን ፊት
ስለማረጉ መመዘኛው የወር አበባ ሳይሆን የልባችን
ንጽህና፣መልካምነታችን፣ቅንነታችን፣ታማኝነታችን፣እምነታችን፣መታዘዛችን ነው፡፡ በተለይ አዲስ
መንፈሳዊ ሕይወት ጀማሪዎች፣ ቤተክርስትያን ሳሚዎችና አስቀዳሾች ፣ ገዳማት ተመላላሾች
ስንሆን የቤተክርስትያን ሥርዓት ያወቅን፣ ያስጠበቅን እየመሰለን በወር አበባ ጊዜ
እንደማይጸለይ እንደማስተማር እያደረገን ለመንፈሳዊ እህቶቻችን ማሰናከያ በመሆን የጸሎት
ሥርዓት እናፋልሳለን፡፡ በዚህም የሰይጣን ስፓንሰር እንሆናለን፡፡

ተወዳጆች ሆይ ለአብነት በአዲስ አበባ ያሉትን እንጦጦ ማርያምና አራዳ ጊዮርጊስን


ብንመለከት ሁለት ግቢ አላቸው፡፡ ለምን እንደዚያ የተሠሩ ይመስላችኋል?

➦ባለ ሁለት ግቢ የሆነበት ምክንያት ሴተችና ወንዶች ንፁህ በማይሆኑበት ፣ የሥጋ ድቀት
በሚያገኛቸው ጊዜና በጋብቻ ተወስነው ሕጋዊ ሩካቤ ሲፈጽሙ በእነዚህ ምክንያት ከቤተ-
ክርስትያን ደጅ እንዳይርቁና ኪዳን፣ቅዳሴ ጸሎት እንዲያደርሱበት ነው፡፡ ይህም የሚከናወነው
በመጀመሪያው  ግቢ በመሆን ነው፡፡

አንደኛው ጊቢ የመንጻት ጊዜያቸው እስከሚያልፍ ድረስ እንዲጸልዮበትና እንዲያስቀድሱበት፣


እንዲማሩባቸው ከዚያም ግዳጃቸውን ሲጨርሱ ወደ ሁለተኛው ወይም ወደ ቤተክርስትያኑ
ግቢ መግባት እንዲችሉ እንጂ ለሌላ የተሠሩ አይደሉም፡፡

➦አባቶቻችን ለተፈጥሮ ግዳጅ እንደዚህ ተጨንቀው ምዕመናን ከቤተክርስትያን ሳይርቁ


እንዲገለግሉ ሥርዓት ሲሠሩ እኛ አዋቂዎች ትልቅ እንቅፋት እንሆናለን፡፡

ወዳጆቼ ቤተ-ክርስትያናችን ከሠራችልንና ከደነገገችልን የግል ጸሎቶች ውስጥ በወር አበባ


ጊዜ ይሄ አይጸለይም ይህ የተከለከለ ብላ አላስተማረችንም፡፡

➦ስለዚህ ያስለመድናቸውን ጸሎቶች ሁሉ መጸለይ እንችላለን፡፡ እራሳችሁን ከኃጢአት እንጂ


ከጸሎት አታርቁ፡፡ አንደበታችሁን ከሐሜት እንጂ ከጸሎት አታርቁ፡፡ ሥራችሁን ከወር አበባ
አንጽታችሁ፣በልባችሁ ማህደር ቂም እና ክፋት ቋጥራችሁ ብትጸልዩ ምን ዋጋ አለው? ከአንድ
ሳምንት ከመርገም ጨርቅ ይልቅ በኃጢአት፣በክፋት ከሚጨማለቅ ሰውነት የሚቀርብ ጸሎት
ከደመና በታች ነው፡፡ የወር አበባ በአንድ ሳምንት ይነጻል፡፡

ግን ከሰውነታችን አልነጻ ያሉን ስንት ኃጢአቶች አሉ፡፡

ስለዚህ ንጹህም ሆንን አልሆንን በርትተን ተግተን ልንጸልይ ይገባል፡፡

ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው በተክሊል ማግባት ይችላልን?

 በወጣትነት ወራት ስለ አባል ዘር ሥራና ውጤት ለማወቅ ካለ ጉጉትና ለተቃራኒ ፆታ የሚኖር


ዝንባሌ ከመጨመሩ የተነሣ ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች የመራብያ አካላቸውን በመነካካት ጾታዊ
ስሜት እንዲሰማቸውና የስሜት እርካታ እንዲያገኙ  ሆን ተብሎ የሚፈጸም ተግባር ሴጋ
ወይም ማስተርቤሽን በመባል ይታወቃል።

   የዚህ ጽሁፍ አላማ ስለ ግለ ወሲብ በዝርዝር ማብራራት ሳይሆን ማስተርቤሽን የተባለውን


የዝሙት ኃጢአት የፈጸመ ሰው ተክሊል መፈጸም ይችላል ወይስ አይችልም የሚለውን ጥያቄ
ለመመለስ ነው ተወዳጆች ሆይ እያወራን ያለነው ከወንድ ጋር በአካል ዝሙት ፈጽማ
የማታውቅ ነገር ግን የዝሙትን ጣዕም ለማጣጣም ራሷን በራሷ ለማርካት ማስተርቤሽን
ስለፈጸመች ሴት ወይም የዝሙትን ጣዕም ለማጣጣም ራሱን በራሱ ለማርካት ማስተርቤሽን
ስለፈጸመ ወንድ ነው።

እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ከተቃራኒ ጾታ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሳያደርጉ ለእንደዚህ


አይነት የዝሙት ተግባር በመጋለጣቸው ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ ከወንዱ ጋር
በምንጣፍ አንድ አልሆንኩም ነገር ግን ማስተርቤሽን ፈጽሜለሁኝ ድንግል ልባል እችላለሁ?

እና ለድንግላን የሚፈጸመውን ሥርዓተ ተክሊልስ ለእኔ ሊፈጸምልኝ ይችላልን?

 የሚለው ዋነኛ ጥያቄ ነው።

ይሄ ጥያቄ በራሱ ተገቢነት የሌለው ትሕትና በማጣት ዲያብሎስ እየፈተነን መሆኑ ማስረጃ
ነው። አንድ ኦርቶዶክስ ከማንኛውም የዝሙት ተግባር እርቆ ከኖረ በኋላ ተክሊል ሊፈጸምለት
ሲል አረኸ አይገባኝም በማለት ራሱን ዝቅ ያደርጋል።

 ከዚህ በተቃራኒው ራስን በራስ የማርካት የዝሙት ኃጢአት የኖረ ሰው ተክሊል ይገባሃል
ቢባል እንኳን አረኸ እኔ አይገባኝም ብሎ በተሰበረ ልብ ሊርቅ ሲገባው በማስተርቤሽን
ኃጢአት የዝሙትን ተግባር ሲፈጽም ከኖረ በኋላ ተክሊል ይገኛል ብሎ መጠየቅ ልባችን
በፈጸምነው ኃጢአት አለመሰበሩን ማረጋገጫ ነው።

አንዲት ሴት ራሷን የዝሙትን የኃጢአት እርካታ የመራቢያ አካሏን በመነካካት አያረካች ከኖረች
በኋላ እንዴት ባለ ድፍረት ነው ተክሊል ይገባኛል ብላ የምትጠይቀው?

 ይቺ ሴት ከወንድ የምታገኘውን የሩካቤ ሥጋ ግንኘነት ከራሷ እያገኘች ከሆነ ከጋብቻ ውጭ


ከወንድ ጋር ዝሙት ከሰሩት ሴቶች በምን ትለያለች?

 ምንም ከወንድ ጋር በምንጣፍ አንድ ባትሆንም በኅሊና ወንድ በማሰብ አልፋ በፍቃዷ አፈ
ማኅፀኗን እየነካካች የዝሙትን ተግባር ስለፈጸመች ድንግል ተብላም አትጠራም።
በሉቃስ ወንጌል ላይ የሚገኝ አንድ ታሪክ አለ።

 ይህ ሕያው ታሪክ ከአባቱ ተለይቶ የኮበለለው ልጅ ሕይወትን ያሳስበናል።  ይህ ልጅ ከአባቱ


ለመለየት መወሰኑ ስህተት መሆኑ ገብቶታል።

 ስለዚህም የሰራውን ስህተት ለማረም ሲነሳ ወደ አባቱ ለመመለስም ሲወስን እንዲህ ብሎ


ነው ያሰበው "ተነስቼ ወደ አባቴ እሄዳለሁና አባቴ ሆይ በሰማይና በፊትህ በደልሁ ወደ ፊትም
ልጅህ ልባል አይገባኝም ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ።" የሉቃስ ወንጌል
15፥18-19

ይሄ ልጅ በአባቱ ላይ ማመጹ ኃጢአት መስራቱ ፈጽሞ እንደጸጸተው የምንረዳው "ወደፊትም


ልጅህ ልባል አአይገባኝም" በሚለው ንግግሩ ነው።

 ወደ አባቱ ቤት ሲመለስ ስለመብቱ እያሰበ አልነበረም በልጅነት ክብር ለመጠራት


እንደማይገባው ወደ አባቱ ቤት የተመለሰው በአባቱ ቤት ከሚሰሩት ሙያተኞች መካከል እንደ
አንዱ ሆኖ በባርነት ለማገልገል ነበር።

ማስተርቤሽን ሲፈጽም የኖረም ሰው ኃጢአቱን አምኖ ሲመለስ ድንግል ልባል የድንግልና


ሥርዓትም ሊፈጸምልኝ አይገባም በሚል በተሰበረ መንፈስ ነው እንጂ በይገባኛል የሚል
የትዕቢት ሐሳበ በልቡ የያዘ መንፈሳዊ ኪሳራ ውስጥ መሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ማስተርቤሽን ቪድዮ ሴክስ ፎን ከፈጸሙ በኋላ

 "በአካል ተቃራኒ ጾታ ጋር ግንኙነት አላደረኩም ተክሊል መፈጸም ይፈቀድልኛል?"

የሚል ጥያቄ በአእምሯቸው የሚፈጠረው ፍቅር እግዚአብሔር ሲጎድልብንና ራስ ወዳድ


ስንሆን ነው።

ምክንያቱም ማስተርቤሽን ቪድዮ ሴክስ ፎን ሴክስ የመሰለ ብዙ ኅቡረ ዝሙት እየፈጸምን


ያሳስበን በደልነቱ ሳይሆን ተክሊል መፈጸም አለመፈጸም መሆኑ ነው።

እንዲህ አይነት አስተሳሰብ "የቤተ ፈት" አስተሳሰብ ይባላል።

ቤተ ፈት የምትባለው ባል አግብታ እየኖረች ከጊዜ በኋላ ባሏን ፈታ የኮበለለች ሴት ናት።

ከሄደችም ችግር ሲያጋጥማት የሚታያት ባሏን መበደሏ ሳይሆን ከባሏ ጋር በምትኖርበት ጊዜ


የነበራት ምቾት እና ክብር ነው።

አባታችን አዳምን ግን የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም ማለትም ኃጢአት ሰርቶ ከገነት በተባረሩ
ጊዜ ፈጣሪዬን አስቀየምኩት ስለ በደሉ ያለቅስ ነበር።

እንደዚህ ሁሉ ሰው በልዩ ልዩ የዝሙት ኃጢአት በተሰነካከለ ጊዜ "ድንግል ነኝን?"


"ተክሊል ይገባኛል?" እያለ ያወጣውና ያገኘውን እያሰበ ከመተከዝ" አንተን ብቻ በድልሁ
በፊትህም ክፋትን አደረኩ መዝ 51፥4

 ማለት ኃጥአቱን እያሰበ ቢያለቅስ በንስሐ አዳምን  መስሎታልና የቤተ ፈት ፍቃድ ልማድ
አላገኘውም ይባላል።

በመጨረሻ ከማስተርቤሽን እና ይህንን ከመሰሉ የዝሙት ርኩሰት መንገዶች የምታመልጠው


በተቀደሰው ጋብቻ አማካኝነት ነው። ይህንን በተመለከተ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል ፦
ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱም ደግሞ ለራሷ
ባል ይኑራት። 1ኛ ወደ ቆሮንጦስ 7፥2 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ዝሙትን ጠንቅ ብሎ ነው
የጠራው በወጣትነት ወራታችን ከዲያብሎስ ከሚወረወሩ ፈላጻ ለመመከት ጋሻ መሆኑን
ከገጸ ንባቡ እንረዳለን። በእውነት ከሴጋ የኃጢአት ዓለም ወጥተን በተቀደሰ ጋብቻ ለመኖር
ማሰባችን የሚመሰገን መንፈሳዊ ውሳኔ ቢሆንም ጋብቻችንን ግን በትህትና በተሰበረ ልብ
ልንፈጽም መዘጋጀት ይኖርብናል።

 አንዳንድ ሰዎች ማስተርቤሽን ሲፈጽሙ ከኖሩ በኋላ የንስሐ አባቴ ፈቅደውልኛል በማለት
ተክሊል ለመፈጸም ሲዳፈሩ ይታያል።

እነዚህ ሰዎች ስለ ማስተርቤሽን በጥልቀት ለንስሐ አባታቸው ሳይናገሩ በሥጋ ብቻ ድንግል


መሆናቸውን ብቻ አጉልተው በማምታታት በማድበስበስ ኑዛዜ ፈጽመው ወደ ተክሊል
ለመምጣት የሚያደርጉት ጥረት ለምዓት ካልሆነ የበረከት መንገድ አለመሆኑ ግልጽ ጉዳይ
ነውና መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

ተወዳጆች ሆይ ከድፍረት የሚገኝ ምንም አይነት መንፈሳዊ በረከት የለም። ድፍረት መንፈሳዊ
ኪሳራን ለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊት እንደዚህ ያለው "የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባርያህን
ጠብቀኝ ያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ" መዝሙር 19፥13

 ምን አልባት አንዳንድ ካህናት ስለዚህ አይነት ኃጢአት ግንዛቤ ሳይኖራቸው ቀርቶ ተክሊል
😔
ፈጽሚ ተክሊል ፈጽም ቢሉን እንኳን ራሳችንን ዝቅ አድርገን አይገባኝም ልንል ያስፈልጋል።

ሕልመ ሌሊት ምንድነው ?

በዐፍላ የጉልምስና ወቅት አባለ ዘርዕ ወደ ሙሉ የዕድገት ደረጃ መድረስ ብቻ ሳይሆን


መስራትም ይጀምራል ። በዚህ ጊዜ ከኀፍረተ አካል ዘርዐ ብእሲ (የወንድ ዘር ) ይወጣል ።
ወንድና ሴት ግንኙነት በሚያደርጉበት ጊዜ ወደ ሴቲቱ ማኀፀን በመግባት ፅንስ እንዲፈጠር
የሚያደርገው ይህ ፈሳሽ ንጥረ ነገር ነው ። ለዘር የበቁ ወጣቶች ዘር የሚወጣቸው በተለያየ
መንገድ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ግን ተኝተው ሳለ በጠለቀ እንቅልፍ ሆነው ሕልም
በሚያልሙበት ወቅት ነው ። ይህ ሲሆን በሳይንስ እንደ ጤናማ የተፈጥሮ ሂደት ይቆጠራል ።
የዚህ አይነቱን ሕልም መፅሐፈ መነኮሳት በአንድ ስፍራ #ሕልመ_ጽምረት በሌላ ቦታ ደግሞ
#መስቆርርተ_ሕልም ሲለው ይገኛል።  ሕልሙን ያየው ሰው ደግሞ #ዝንየት መታኝ ወይም
#ሕልመ_ሌሊት አገኘኝ ይላል

ሕልመ ሌሊት ኃጢአት ነውን?

በጠለቀ እንቅልፍ ላይ ሳሉ የሚከሰት ሕልመ ሌሊትን እንደ ኀጢአት እንዲቆጠርና


እንዳይቆጠር የሚያደርጉ የተለያዩ ሁኔታዎች አሉ ።ስለዚህ ሕልመ ለሊትን በጥቅሉ ኃጢአት
ነው ወይም አይደለም ማለት አይቻልም ። እንደ ኃጢአት እንዲቆጠር የሚያደርጉ ሁኔታዎችን
በጥቂቱ ለማየት ያህል

ሀ. አጋንንት የሰው ልጆችን በልዩ ልዩ መንገድ ክፋኛ ይዋጓቸዋል ። የሰው ልጆች ሲያንቀላፉ
አጋንንት ግን ለቅጽበት እንኳን አያሸልቡም ። ያንቀላፋው ሰው እስኪነቃ ድረስ እንኳን
አይጠብቁም ። አጋንንት የሰውን ልጅ በተኛበት ክፋ ክፋ ሕልም በማሳየት ይፈትኑታል ። አንድ
ጊዜ የተራቆተ የሴት ገላ ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ወንድና ሴት ግንኙነት ሲያደርጉ በምትሐት
ያሳዩታል። በዚህ ጊዜ እርሱም በዝሙት ሐሳብ ይሳብና በሕልሙ ዝሙት ሲፈፅም ያድራል ።
መፅሐፈ መነኮሳት "ሰይጣናት የሰውን ልጅ ቀን ቀን ክፋ ሐሳብ በማሳሰብና በማሰራት
በሌሊት ደግሞ ዝሙት የሞላበት አስጸያፊ ሕልም በማሳየት ይዋጉታል " ይላል። በዚህ ጊዜ
ሰይጣናት ያቀረቡለትን ረቂቅ ፈተና ከመቃወም ፣ ከመፀፀትና ከመቆጨት ይልቅ ደስ እያለው
የሚያጣጥም ከሆነ ፤ በደስታ ስለ ዝሙት የሚያሰላስል ፣ የሚዳራ ፣ የሚዛለል ፣ ወደ ዝሙት
ከሚያመሩ ማናቸውም ነገሮች የማይሸሽ ሰው እነዚህን ነገሮች ነቅቶ ሳለ ያልተቃወማቸውን
ተግባራት በሕልሙ በፈፀማቸው ጊዜ በተግባር እንደ ፈፀማቸው ይቆጠራል ።ሌላው ከሥራ
ብዛት ሕልም እንዲታይ ጠቢቡ ሰሎሞን[ " ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል " በማለት የተናገረው
ያስረዳል (መክ5:3) እንደዚሁም ሁሉ ከምኞት ብዛትም ሕልም ሊከሰት ይችላል። ክፋ ምኞት
በሕልምም ማርከሱ አይቀርም ። ሐዋርያው ይሁዳ " እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ "  ያለው
ለዚህ ይጠቀሳል ። (ይሁዳ 1:8) እንደሚታወቀው ነፍስ አትተኛም ።  ስለዚህ ነፍስ በእንቅልፍ
ልቤ ነው ብላ ማመካኘት አትችልም ። ነፍስ በረከሰ ሕልም ምክንያት ከተጠያቂነት ነጻ መሆን
የምትችለው ሥጋ ከእንቅልፍ ውጭ በሚሆንበት ጊዜ ተግባረ ዝሙትን በመቃወምና
በመጥላት ከእግዚአብሔር ጋር መሆኗን ስታስመሰክር ብቻ ነው ። ሌላው ሕልመ ለሊትን
እንደ ኀጢአት የሚያስቆጥረው ሁኔታ አብዝቶ መመገብ ነው ። ጾም ለፅድቅ ስራ ሁሉ መሰረት
እንደሆነው እንደዚሁም አብዝቶ መመገብ የኀጢአት ሁሉ መሰረት ነው ። "እህል ጉልበትን
ያጠነክራል ተብሏልና ።ሰው ሁሉ ለቁመተ ስጋ ያህል ብቻ መመገብ ያሻዋል ። ከዛ ውጭ ግን
አብዝቶ መመገብ "ሆዳቸው አምላካቸው " እንደ ተባለው ለህልመ ለሊት ያጋልጠናል ።

🏠በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት(ዝንየት) ቢመታን ምን


እናደርጋለን?
 

በሱባኤ የአጋንንት ውጊያ የሚበረታበት፣ሕልመ ሌሊት ደግሞ በተደጋጋሚ የሚከሰትበት


ነው። የበጎ ነገር ጠላት አጋንንት እኛን ከመንፈሳዊ አገልግሎት እና ተገልጎሎት ለማሰናከል እኛ
ላይ ዓይኑን ፈጠጥ፣ጥርሱን ገጠጥ የሚያደርግበት ጊዜ በአጽዋማት ወቅት ነው ሕልመ
ሌሊት (ዝንየት) የሚባለው አንድ ሰው ተኝቶ በሕልሙ ወንድን በሴት፣ ሴትን በወንድ አምሳል
እንደ ገሐዱ በሚመስል ሩካቤ ሥጋ የሚታየንና ከሰውነታችን ፈሳሽ የሚወጣበት ሂደት
ነው።ዝንየት የሚባለው ደግሞ በሕልመ ሌሊት የሚፈታተነን አጋንንት ነው፡፡ ሕልመ ሌሊት 
ወንድና ሴት ሳይል በማንኛውም ሰው ላይ በተለያየ ምክንያት ሊከሰት ይችላል።

በሱባኤ ጊዜ ሕልመ ሌሊት ከመታን እለቱን ቤተ-ክርስትያን በተለይም ቤተ-መቅደስ


መግባት፣ቅዱስ ቁርባን መቀበል፣ጸበል መጠመቅና መጠጣት፣ አንችልም።በማግስቱ ግን
ሰውነታችንን ታጥበን፣ልብሳችንን ቀይረን ቤተ-ክርስትያን መግባት፣ቅዱስ ቁርባን
መቀበል፣ጸበል መጠመቅና መጠጣት እንችላለን። እንደዚህ የምናደርገው አንደኛ መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ትእዛዝ ስለሆነ ነው።ሁለተኛ ቅድስት ለሆነችው እናት ቤተክርስትያን ክብር
ከመስጠት አንጻር ነው። እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን በዘሌዋውያን ምዕራፍ 15÷2 ላይ
‹‹ማንም ሰው ከሥጋው ፈሳሽ ነገር ቢወጣ፣ስለሚወጣው ነገር ርኩስ ነው›› ይልና ቁ 16 ላይ
‹‹ማንም ሰው ዘር ከእርሱ ቢወጣ፣ገላውን ሁሉ በውኃ ይታጠባል፣እስከ ማታም ድረስ ርኩስ
ነው›› ይላል።/ዘሌ 15÷16/

ተወዳጆች ሆይ ልብ በሉ ‹‹ማንም ሰው›› ነው እንጂ ወንድ ሴት፣ወጣት አዛውንት


አይልም።ይህ የሚያሳየው ኦርቶዶክስ የሆነ በየትኛው ጾታ እና የእድሜ ክልል ያለ ሁሉ ሕልመ
ሌሊት ከመታው እለቱን ሳይሆን ማግስቱን ነው ቤተ-ክርስትያን መግባት የሚችለው። ‹‹እስከ
ማታ›› የሚለው ሕልመ ሌሊት ሲመታን ለአንድ ቀን ብቻ የተከለከልን መሆናችን
ያስረዳል።መቼም ሕልመ ሌሊት የሚመታን ማታ ወይም ሌሊት ነው።ስለዚህ አንድ ሰው ማታ
ወይም ሌሊት ሕልመ ሌሊት ከመታው ቀኑን ውሎ እስከ ማታ ነው የሚረክሰው። ከማታ በኃላ
ንፁህ ይሆናል።

ወዳጆቼ አንዳንዶች ‹‹ሕልመ ሌሊት ከተመታችሁ እስከ ሦስት ቀን ቤተ-ክርስትያን መግባት


አይቻልም›› ይላሉ።ይህንም ‹‹ማነው ያለው›› ስትሉ የፈረደባቸው ‹‹አባቶች›› ናቸው ይላሉ።
ቅዱስ መጽሐፍም አባቶቻችንም የሚነግሩን እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቤተ-ክርስትያን
የማንገበው ሩካቤ ሥጋ ስንፈጽም ብቻ ነው።

ሕልመ ሌሊት መታን ማለት በቤት እና በቅጽረ ቤተ-ክርስትያን ሆኖ መጸለይ አይቻልም ማለት
አይደለም።በሱባኤም ሆነን ሕልመ ሌሊት ቢመታን ሰውነታችን ታጥበት ሱባኤው መቀጠል
እንጂ ማፍረስ የለብንም።

ወዳጆቼ ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት አይደለም። ግን ኃጢአት የሚሆንበት ሂደት


አለው።አንድ ሰው በሕልሙ ሕልመ ሌሊት ቢመታው በዚህም ከሰውነቱ አባለ ዘር
ይፈሳል።የአባለ ዘር መፍሰስ ኃጢአት የሚሆነው በራስ ፍቃድ ሲሆን ነው። ለምሳሌ ወዶ እና
ፈቅዶ ግለ ወሲብ ሲፈጽም፣የወሲብ ፊልም በማየት ከሚመጣ የሰውነት ሙቀት ጋር ዘር
ሲፈስ፣ከተቃራኒ ጾና ጋር በሚደረግ አልባል ንክኪና መሳሳም ነው።ሕልመ ሌሊት እላፊ በልቶ
እና ጠጥቶ ከሚመጣ የሥጋ ፈተና ከሆነ ኃጢአት ይሆንበታል።ቅድስናን የሚያጎድል በመሆኑ
የኃጢአተኝነት ስሜት እንዲጫነን ያደርገናል።ግን አንድ ሰውን ሕልመ ሌሊት ቢመታው
ኃጢአት የሚሆንበት ሂደት አለ። ይህም አንድን ሰው ሕልመ ሌሊት ሲመታው ማለትም
አጋንንቱ በሚያውቃት ሴት ተመስሎ በተኛበት ተገናኝቶት ዘሩን ቢያስፈስሰው የዚህ ችግር
ሰለባ የሆነው ሰው በተፈጠረው ነገር ለምሳሌ ሴቷን እያሰበ፣በሕልሙ ያየውን እያሰበ
የሚደሰት፣በሕልሙ የተፈጠረውን ግንኙነት በምልሰት እያየ ደስታን ካጣጣመ ኃጢአት ነው።
ምክንያቱም ይሁዳ በመልእክቱ ‹‹እያለሙ ሥጋቸውን ያስደስታሉ›› ብሏልና። /ይሁ 1÷8/
በሕልማችን የተፈጠረውን ሕልመ ሌሊት በምልሰት በማየት እና በማሰብ መደሰት ሳይሆን
መጸጸት መቆጨት ካልተሰማን ኃጢአት ነው የሚሆንብን።

ወዳጆቼ የአጋንንት የረከሰ ሐሳብ በሕልማችን እየተከሰተ ሕልመ ሌሊት ሲያጋጥመን


የተፈጠረውን ክስተት በጸጸት አጋንንቱንልናሳፍረው ይገባል እንጂ የሆነውን እንደ በጎ ነገር
ልንቀበለው አይገባም።ይህ እሳቤያችን ከፈጣሪ መለኮታዊ እርዳታ እንድናገኝ ይረዳናል።
የማንቆጭ፣የማንጸጸት ከሆነ የዝንየት አጋንንት ይለምድና የሌሊት ደንበኛው ያደርገናል።

እዚህ ላይ አንድ መረሳት የሌለበት ነገር አለ። አንዳንዴ ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) በሰይጣን
ፈተና ብቻ ላይከሰት ይችላል።ምናልባት ከምንጠቀማቸው ምግብና መጠጥ እንዲሁም
ከሥጋ ባህርያችን ሊከሰት ይችላል።ምክንያቱም ሰውነታችን ሲስማማው በራሱ ጊዜ ፈሳሽ
ሊወጣ ይችላል።ይህ ደግሞ ተፈጥሮ ነው፤ ምንም ማድረግ አይቻልም በጸጋ መቀበል
ነው።ለምሳሌ ማታ ትኩስ ነገር ሙቅ፣ሻይ አብዝተን የምንጠጣ ከሆነ በዘር ከረጢጣችን
ያለው አባለ ዘር በራሱ ጊዜ ሊፈስ ይችላል።

ተወዳጆች ሆይ በተአምረ ማርያም ላይ እንደሰማችሁት በሕልመ ሌሊት የተፈተነው ወጣት


መነኩሴ ሕልመ ሌሊት ሳይሆን በሥጋው ምክንያት ሞት የመጣበት ስለመሰለው
‹‹የፍትወትን ጣዕም ዛሬ ቀምሰሻልና ወዮልሽ›› በማለት አምርሮ እራሱን ጠልቶ ወደ
እመቤታችን አንብቶ ቢማጸናት እመቤታችን ተገልጣ ፈተናውን አርቃለት፣በእጆችዋም ምልክት
አድርጋለታለች

ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል ⁉


ተወዳጆች ሆይ ሕልመ ሌሊት ከሚከሰትብን ምክንያቶች ዋና ዋናዎችን ከዚህ በታች
እናያለን።

1ኛ/ በአጋንንት ይከሰታል

በጣም የሚገርመው በሕልመ ሌሊት (ዝንየት) የተፈተናችሁ እስቲ ልብ በሉ።ወደ መንፈሳዊ


ሕይወት ውስጥ ሳትገቡ በዓለም ሳላችሁ ብዙም አይከሰትም።ቢከሰትም ለአቅመ-አዳምና
ለአቅመ ሔዋን በደረስንበት ወቅት በሥጋ ባህሪያችን ይከሰታል።ወደ መንፈሳዊ ሕይወት
ውስጥ ገብተን በተግባር መኖር ስንጀምር ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) በተደጋጋሚ
ይመታናል።በተለይ ወንዶችን ቋሚ ደንበኞች ያደርገናል።

ወዳጆቼ አጋንንት ጸበል እንዳንጠመቅ፣ ቤተ ክርስትያን ገብተን ጸሎት እንዳናደርስ፣


ከመለኮታዊው ማዕድ እንዳንቋደስ/ቅዱስ ቁርባን እንዳንቀበል/ ከሱባኤ ዋሻ ለማስወጣት
ከሚጠቀምበት ዋንኛ ማሰናከያ መፈተኛው ሕልመ ሌሊት ዝንየት ነው። አባቶቻችን ‹‹ተጻቦዖ››
ይሉታል ‹‹ተጻብዖ›› ማለት ቃሉ የግዕዝ ሲሆን መጣላትን ያመለክታል። እኛ ሀገር ሰላም ብለን
በተኛንበት ሰይጣን በማናየው መልኩ በሕልመ ሌሊት ስለሚጣባንና እኛ የማንፈልገውን
ፈቃደ ሥጋ በማሳየት ፈትኖን ከሰውነታችን ፈሳሽ እንዲወጣ ስለሚያደርግ ‹‹ተጻብዖ››
ብለውታል።በእውነት ከዚህ በላይ ምን ጸብ አለ? ሰው የማይገላግለን፣ሰው
የማይደርስልን፣ጮኸን የማናመልጠው ጠብ።

ተወዳጆች ሆይ በሱባኤ ላይ ሆነን አጋንንት በሕልመ ሌሊት ቢፈትነን ሱባኤያችን አይፋረስም።


ሕልመ ሌሊት ስለመታን ሱባኤያችን አይቋረጥም።

ሕልመ ሌሊት መፍትሄ አለው ?

ብዙ ሰዎች ተግቶ ለመፀለይ ፣ ለማስቀደስና ለመቁረብ በወሰኑ ጊዜ ሕልመ ለሊት እንቅፋት


እየሆነ ይፈተኑበታል። በእርግጥ መብላትና መጠጣት ሳያቆሙ ሙሉ ለሙሉ ከሕልመ ለሊት
መለየት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ የሚቻል ነገር አይደለም ። ስለዚህ መፍትሄዎችን እናያለን 

#ሀ በመፅሐፈ መነኮሳት ላይ"በሌሊት በሕልም ከሴት ጋር የተገናኘህ መስሎህ ዘር


ቢወርድህ በመዓልት አታስባት " ይላል ። ሕልምህን ደስ እያለህ ብታስባት ግን በተግባር
ዝሙትን ወደ መፈፀም ያደርስሃል። ስለዚህ ከሕልመ ለሊት ፈተና ለመዳን አንዱ መፍትሔ
ሕልምን በውን ደስ እየተሰኙ መላልሶ አለማሰብ ነው 

#ለ ሕልመ ለሊት በምታይበት ጊዜ ከነቃህ ቸል ብለህ ተመልሰህ አትተኛ ። ፈጥነህ ተነሳና


ተጣጥበህ ጸሎት አድርስ ። ከተቻለህ ስገድ ባይቻልህ ግን የባሕሪህን ድካም ፈጣሪ
ያውቀዋልና ይቅር በለኝ ፣ አድነኝ ፣ እያልህ ወደ እግዚአብሔር ለምን 

#ሐ ሌላው ከሕልመ ለሊት ለመዳን ዋነኛው መፍትሔ ውኀ በብዛት አለመጠጣት ነው ።


መፅሐፈ መነኮሳትም ይሄን ሲመሰክር " እንደ ውኀ ጥም አካልን የሚያደርቅ ፣ከሕልመ
ሌሊትና ከዘር መፍሰስ ፣ በቀን  ሐጢአት ማሰብን የሚያጠፋ የለም " ይላል ። አንድ ሰው
ምንም በጾም አመጋገቡን ቢቀንስ አብዝቶ ውኃ የሚጠጣ ከሆነ አይጠቀምም። ለምን ቢባል
ሰውነቱ ስለሚለመልምና ሰይጣን እርሱን ለማሳት መንገድ ስለሚያገኝ ነው ። ስለዚህ
ከሕልመ ሌሊት እፎይ ለማለት ከፈለክ "ውኃን ከልክለህ ሰውነትህን አስጨንቀው "
ተብለሀል። ወንጌልም ይህን ሲያጠነክር እንዲህ ይለናል ፦ "ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ
ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውሃ በሌለበት ቦታ ያልፋል ፤ አያገኝምም ። በዚያን ጊዜ ወደ ወጣሁበት
ቤቴ እመለሳለሁ ይላል ፣ ቢመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎ አጊጦ ያገኘዋል " (ማቴ 12-43) ይህ
ጥቅስ ብዙ ትርጉሞች ቢኖሩትም ከያዝነው ሃሳብ ጋር የሚዛመደውን ብቻ እንይ ፡" ርኩስ
መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውሃ በሌለበት ቦታ ያልፋል ። ማለት ሰይጣን
መግቢያ ካገኘው ብሎ ሰውነቱን በረሃብና በጥም ወደሚያስጨንቅ ሰው ይሄዳል ማለት ነው
። ይልቁንም "ውሃ በሌለበት" ማለቱን መዘንጋት የለብንም ።"አያገኝምም "የሚለው ቃል ደሞ
ሰይጣን ሰውነቱን በውሃ ጥም (በፆም) በሚያስጨንቅ ሰው ላይ ለማደር አለመቻሉን ያሳያል ።

#መ በሕልመ ለሊት በተደጋጋሚ እንዳትጠቃ ወደ ዝሙት ከሚያመራ ማናቸውም ነገር ሽሽ።


በመሸ ጊዜ የምታያቸውን ፊልሞች ፣ ንባቦች ፣ ሌሎችንም ነገሮች በጥንቃቄ መርምረህ
ለፍትወት የሚያጋልጡትን ሽሽ።ከዚያ ይልቅ ደጋግ መንፈሳዊ መፅሐፍትን ለማንበብ ትጋ ።

#ሠ ሌላው መፍትሄ ደግሞ ከመንፈሳዊ መምህራንና ከአበው ካህናት ጋር እየተመካከሩ


በሚያቀርቡት የመፍትሄ ሀሳብ መጓዝ ነው ። እዚህ ላይ ልንጠነቀቅ የሚገባን የምናማክረው
ሰው ምስጢራችንን ለመጠበቅ የታመነና በምንነግረውም ነገር ራሱ ወደ ፈተና ሊገባ
የማይችል በሕይወቱ ብዙ ተሞክሮ ያለው መሆን አለበት ። እንዲሁም ጥሩ መፍትሄ አለን ፡
ልፋፈ ፅድቅ እንደግማለን እያሉ ከሚያጭበረብሩ ተኩላ ባህታውያንም መጠንቀቅ

 አለብን 

ግብረ አውናን (Masterbation) #ምንድነው ?

እግዚአብሔር ለምህረትና ለመቅሰፍት ያዘጋጃቸው ልዩ ልዩ ግዳጆችን የሚፈፅሙ መላእክት


እንዳሉት ሁሉ ሰይጣንም ሰውን በልዩ ልዩ መንገድ እንዲፈትኑ ድርሻ ሰጥቶ ያዘጋጃቸው
አጋንንት አሉት ። ከእነርሱም ውስጥ አንዱ #ሰይጣነ_ዝሙት ነው ። ሰይጣነ ዝሙት የሰው
ልጆችን የሚፈትንበት መንገድ የተለያየ ነው ። እንደውም አንዳንዶቹ ፈተናዎቹ የዝሙት
አይመስሉም 

 #ፆር_የለመዱ (የሰይጣንን የፈተና ስልት በደንብ ለይተው ያወቁ ) አበው ቅዱሳን ግን ሽንገላ
የሞላበትን የሰይጣንን ፈተና አሸንክላ ምን እንደሚመስል መጪ ትውልድ እንዲያውቀው
በሕይወታቸው ያዪትንና መንፈስ ቅዱስ ያቀበላቸውን ፅፈው አስቀምጠዋል ። ለምሳሌ
ሰይጣነ ዝሙት የሰውን ልጅ ወደ ዝሙት ተግባር ከሚስብባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው
ገሢሥ ነው ። #ገሢሥ ማለት ማሻሸት፣ መነካካት ፣ መዳበስ ማለት ነው ። ነብዩ ሕዝቅኤል
"ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር " (ሕዝ 23:3) በማለት እንደተናገረው ለዘር የደረሱ
ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲላፋና ሲዳሩ ሩካቤ ሳይፈፅሙ ዘራቸው የሚፈስበት ጊዜ አለ ። ይህን
ድርጊት እንደ ተድላ በመቁጠር ብዙ ወጣቶች ሆን ብለው ያደርጉታል 
 በቅዱስ መፅሐፍ "የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር " እንደተባለው ቦታ ሳይመርጡና
ሰው ሳይለዩ የሴት ልጅን ገላ በመዳበስ "ግልሙትናን ማፍሰስ " ያሳፍራል ። ይህ መጥፎ
ልማድ የተጠናወታቸው ሰዎች ግርግርና በሰው ብዛት የተጨናነቀ ስፍራ የሴቶችን ገላ እንደ
ሐሳባቸው ለመነካካት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል። ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ሰው
ስራቸውን አይቶ እንዳይነቅፋቸው የተለያዪ ዘዴዎችን ይፈጥራሉ። ለምሳሌ አንዳንዶቹ ምንም
ሳያውቁና በእንቅልፍ ልባቸው ያደረጉት ለማስመሰል እንደ ተኛ ሰው እየተገላበጡና እያንኮራፋ
በልዩ አጋጣሚ አጠገባቸው የተኛችውን ሴት ገላ ሲዳብሱ ያድራሉ 

 ይህ ድርጊት ያለ ሩካቤ የወንድ ዘር ከሚፈስባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ነው ። ሌሎች


ደግሞ በአድካሚ የጉዞ ወቅት ደጋፊ ፣ በሕመም ጊዜ ደግሞ አስታማሚ ... እየመሰሉ
ከወሊድ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን አካላት ለመደባበስ የሚሞክሩ ናቸው ። አንዳንዶች ደሞ
እነርሱ ፈፅሞ ለመንካት እንዳላሰቡ ነገር ግን የተፈጠረው ሁኔታ እንዲጋፋ ወይም እንዲነካኩ
እንዳደረጋቸው ለማስመሰል ይሞክራሉ ። በብዛት እንደዚ የሚያደርጉት ሕዝባዊ ስብሰባዎች
በሚደረግባቸው እለታትና መጨናነቅ በሚኖርባቸው ስፍራዎች ነው ። ለምሳሌ እንደ
ጥምቀት ፣ መስቀል ፣ ኤግዚብሽኖች ፣ የሞሉ ሚኒባሶች ሀይገሮች ባሶችና ባቡሮች መጥቀስ
ይቻላል

 ሌሎች ደግሞ ውጫዊ ይዘታቸው ሲታይ በዚህ ዓይነት ዘርን በማፍሰስ የመርካት ተግባር
የማይጠረጠሩ አይነት ናቸው ። ለምሳሌ እድሜያቸው በጣም የገፋ ፣ በአስተሳሰብ የበሰሉ ፣
በአለባበስና በምጣኔ ሀብት የተከበሩ የሚመስሉ ወይም አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ አቋምና
መልካም ስም የያዙ ናቸው ። እንደዚ ያሉት ሰዎች የሌሎችን ህዋሳት ለመነካካት
የሚያደርጉት ጥረት "ይህን አስበው አይደለም " እየተባለ ብዙ ጊዜ በበጎ ይተረጎምላቸዋል

ሌላው ዝንባሌያቸው ደግሞ ታዳጊ ህፃናትን ማባለግ ነው ። በቅጡ ጡት ያላጎጠጎጡ


ሕፃናትም እንኳን የእነዚህ ሰዎች የጥቃት ሰለባዎች ናቸው ። ህፃናቱ እነዚህ ሰዎች ምን
እያደረጉ እንደሆነ አያስተውሉም ፣ አያውቁም ፣ ቢያውቁም አይቃወሟቸውም አይከሷቸውም
። ወይም በትንሽ ነገር ሊባበሉና ሊታለሉ ይችላሉ ።ሕፃናቱን ያጫወቱና ያሳሳቁ በመምሰል
ሲታገሉና ሲላፋ በፍትወት እየተቃጠሉ ልብሳቸውን በዘር ጭቃ የሚለውሱትን ወንዶች ቁጥር
ቤት ይቁጠረው

ግብረ_አውናን(Masterbation)#ተገቢ_ነውን_?
#ግብአውናን የተባለበት ምክንያት  አውናን የተባለው ሰው ከሚስቱ ጋር ግንኙነት እየፈፀመ
ሳለ ዘሩን ከማህፀን ውጪ ያፈሰው ስለነበር ነው ። ግብረ አውናን/Masterbation (ሴጋ)
በመፅሐፍ ቅዱስ ስንመዝነው ተገቢ ነገር አለመሆኑን እንረዳለን ። አንድ ገበሬ ለዘር
የሚያስቀረው ዘር ራሱ ከሚመገበው እንኳን የተሻለውን ምርጥ ዘር ነው ። ስለሆነም ከዘር
ወቅት በፊት ተጠንቅቆ በጎተራ ያስቀምጠዋል።  በዘር ወቅት ደሞ አውጥቶ በመልካም ማሳ
ላይ ይዘራዋል እንጂ ያለ ቦታው አይበትነውም ። እንደዚሁም የሰው ዘር ከእህል ዘር
ይከብራልና በመልካም ጎተራ ማለትም በሰውነት ተጠብቆ መቆየት አለበት ። ከጋብቻ ቡሃላ
ባልና ሚስት ሩካቤ ሲፈፅሙ ደግሞ በመልካምዋ ማሳ በሚስት ማኀፀን መዝራት እንጂ ሆን
ብሎ እራስን በራስ በማርካት  በየቦታው ማፍሰስ ተገቢ አይደለም ። እራስን በራስ ማርካት /
ሴጋ መፈፀም ተገቢ አለመሆኑን የሚያስረዱ በልዩ ልዩ አገባብ የተጠቀሱ ጥቅሶች አሉ 

"እንግዲህ በምድር ያሉትን ብልቶቻችሁን ግደሉ እነዚህም ዝሙትና ርኩሰት ፍትወትም ክፋ


ምኞትም ፣ ጣዖትን ማምለክ የሆነ መጎምዠት ነው " (ቆላ 3:5) እዚህ ላይ "ብልቶቻችሁን
ግደሉ" ሲል ቆርጣችሁ ጣሉ ማለት ሳይሆን አትቀስቅሱ ማለት ነው ።  "ደንዝዘውም
በመመኘት ርኩሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ " (ኤፌ 4:19)
ይህ ጥቅስ ለግብረ አውናንም ሊጠቀስ ይችላል። ምክንያቱም ሴጋ ዝሙትንና ርኩሰትን
የመመኘት ዝንባሌ ዋና መገለጫ ነውና ። ሐዋርያው ጳውሎስ በፍትወት ለተቃጠሉ መፍትሄ
ሲሰጥ " በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ፤ ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ "
ብሏል ። (1ቆሮ 6:9) ስለዚህ በዝሙት ለሚቃጠሉ መፍትሄው #ማግባት እንጂ #ሴጋ
መፈፀም አይደለም። ሐዋርያው ማግባትን እንጂ ግብረአውናንን እንደ መፍትሄ አልመከረምና 

ሌላው አምላካችን ሥጋ የፍትወቱን ያህል አግኝቶ እንዲረካ ጋብቻን ሲያሰናዳ ከጋብቻ ጋር


አብረው የሚሄዱትን ኃላፊነቶች ከመቀበልና ከመሸከም ጋር ነው ። ነገር ግን ሴጋ ምንም
አይነት ኃላፊነት ሳይሸከሙ ያንን እርካታ ለማግኘት እንደ መሞከር ይቆጠራል ።የምኞት
ቃጠሎን ዘርን በማፍሰስ ለማብረድ መሞከር ስሕተት ነው ። ምክንያቱም 1 ችግር ሲያጋጥም
ተቋቁሞ በማለፍ ፈንታ በተሳሳተ ጎዳና በመጓዝ ችግሩን ለማምለጥ መሞከር ሽንፈትንና
ደካማነትን የሚያመለክት በመሆኑ ነው ። በዚ ምክንያት ብዙ ወጣቶች ላለመማራቸውና
ለሥራ አጥነታቸው ወይም በሕይወታቸው ለገጠማቸው 1 ችግር ተገቢና ጤናማ መፍትሄ
ከመፈለግ ይልቅ ዱርዬነትን ፣ ሌብነትን ፣ ሰካራምነትን፣ ሲጋራ ማጨስንና ጫት መቃምን ፣
በየክለቡ መጨፈርን እንደ አማራጭ ይወስዳሉ 

 ታዲያ የሽንፈትና የደካማነት ምልክት አይደለምን ? አንዳንድ ሰዎች "1 ሰው ጋብቻ


ለመመስረት ዕድሜው ያልደረሰ ወይም ሁኔታዎች ያልፈቀዱለት ከሆነ የጋብቻ ጊዜውን
እየተጠባበቀ በዝሙትና በሰዶማዊ ተግባር ከሚሰነካከል ራሱን በራሱ በማርካት ተግባር
ቢቆይ አይሻልም ? እስከ ማለት ደርሰው ግብረአውናን/ሴጋ ተገቢ ነገር ለማስመሰል
ይጥራሉ። ሁሉም የዝሙት ልዩ ልዩ ገፅታዎች ናቸው ። ሰይጣንም ቢሆን ሐሳቡ
እንድንፈፅምለት ከግብረ ሰዶምና ከዝሙት ታንሳለች በማለት ያሳስበናል እንጂ በዚሁ ኃጢአት
የተያዙትን ደሞ ያልሰሩት ዝሙትና ግብረ ሰዶም እንዲፈፅሙለት "አንደኛውን ዝሙት ይሻላል
፡ ይህን የመሰለ ኃጢአት እየሰራህ ዝሙት አልሰራሁም ለማለት ነው ? እያለ ተስፋ
ለማስቆረጥ እንደሚያምታታቸው መዘንጋት የለብንም።

ከግብረ_አውናን (Masterbation)
#እንዴት_መላቀቅ_ይቻላል?

#ሀ. ግብረ አውናን እንደ ማር ጠብታ ነው ። የማር ጠብታ ልብስ ላይ የወደቀ እንደሆነ
በፍፁም የሚለቅ አይመስልም ፣ ነገር ግን ትንሽ ለቅለቅ ያደረጉት እንደሆነ ወዲያውኑ
ይለቃል። ይህ ክፋ ልማድም እንደማር በቀላሉ ባይሆንም ከልብ በመፀፀት በጠንካራ
መንፈስ ከተነሱ ሊያስወግዱት ይቻላል። በመጀመሪያ የሚያስፈልገው ከዚ ነገር
መቼም መላቀቅ አልችልም ብሎ ተስፋ አለመቁረጥ ነው ። ከፍተኛ ትግልና ጥረት
ይጠይቃል ። ስለዚህ ተስፋ መቁረጥ ፈፅሞ አይገባም 

#ለ. ሴጋ ልማድ ነው ። ልማድ ደሞ በሌላ ልማድ ይሸነፋል። ጠንክረህ ከተነሳህ ይህን


ተግባር በትዝታ ብቻ የምታስብበት ቀን ሩቅ አይሆንም ። ነገር ግን ከዚህ ልማድ ጋር
ለመዋጋት ከመነሳትህ በፊት "ይህን ክፋ ልማድ ምን ያህል ከልቤ ጠልቼዋለው ? "
በማለት ራስህን ጠይቅ ። መላልሰህ የምትሰናከለው ሳትፀፀት ወይም ሴጋን መተው
ስላልፈለክ ሳይሆን ጣዕሙ በልቡናህ ስላለና ጎጂነቱ ዘልቆ ወደልብህ  ስላልገባ ነው ።
ስለዚህ ይህን ነገር ከልብህ ልትጠላው ይገባል

#ሐ. ይህን ክፋ ልማድ እንደ እሳት የሚያያይዙት የራስህ ተግባርና በዙሪያህ ያሉ


ነገሮች ናቸው ። ከዚህ እኩይ ተግባር መላቀቅ ከፈለክ #ተዐቅቦ ያስፈልግሀል።
#ተዐቅቦ ማለት መከልከል መቆጠብ ማለት ነው ። የምትከለከለውም ወደዚህ
መጥፎ ሐሳብ ልቡናህን የሚስቡትን ነገሮች ከማየት ፣ ከመስማት፣ ከመንካትና ፣
ከመሳሰሉት ነው ። ስለዚህ የሴቶችን ገላ በፊልምም ፣ በአካልም ቢሆን በምንም
መልኩ ከማየት ተቆጠብ።  በመዋኛና በመጠመቂያ ቦታዎች ራስህን ጠብቅ የሴት
ልጅን መልክና ቅርፅ መርዘህና አተኩረህ አትመልከት ።  ስለ ዝሙት የሚያሳስቡ
ሥዕሎችን፣ ፅሁፎችን፣ ወሬዎችን ፣ የሴት ገላ የሚያሳዩ የሙዚቃ ክሊፖችን ፣ የወሲብ
ፊልሞችን አጥብቀህ ሽሻቸው ።ስራህ ሁሉ አንተው እያራገብክ ለምን ይቃጠላል ?
እንዳይሆንብህ 
#መ. ዘወትር ልቡናህ የሚጠመድበትን ነገር ፈልገህ አድርግ ። ቦዘኔ አትሁን ትጉህ
ሰራተኛ ሁን ።ስራህም አይምሮህን የሚያሰራ ቢዚ የሚያደርግ ይሁን ። ትርፍ ሰአት
አይኑርህ ። የሚነበብ ወይም ሌላ የሚሰራ ስራ ፈጥረህ ሥራ 

#ሠ. "ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው " የሚለውን የወንጌል ቃል አስብ ። በዚህ ክፋ
ልማድ ተጠምደህ ሳለ ለብቻህ መሆንን አትውደድ ። ቢቻልህ አኗኗርህና መኝታህ
ከምታፍረውና ከምታከብረው ሰው ጋር ይሁን ። ይህም ጓደኛህ ወይም ከቤተሰብህ
አንዱ ሊሆን ይችላል። በፀሎት ከሚረዱህ መንፈሳውያን መምህራን አባቶች ጋር ጊዜ
ማሳለፍን ውደድ

#ረ. እንቅልፍ የያዘህ ስለ መሰለህ ብቻ ወደ መኝታህ አትሂድ ። አንዳንዴ ተኝተህ


ውለህ እንቅልፍ ያምርሀልና ። ነገር ግን ሰይጣን ሊፈትንህ ከሆነ በምትነኛበት ጊዜ
እንቅልፍ ከአይንህ ይርቃል ። ተከትሎም ፈተናው ይመጣና ወደ ዝሙት ህሊናህ
ይሳባል ። ከዛ ሴጋ ትፈፅማለህ። ስለዚህ ከመተኛትህ በፊት በደንብ መድከምህንና
ቶሎ ማሸለብ መቻልህን መርምረህ ተኛ

#ሰ. ጸሎት ማድረግንም አትርሳ የሚረሳ ነገር አይደለምና ። ስትተኛም በጀርባህ


ወይም በሆድህ አትተኛ ። ከዚህ ይልቅ በጎንህ ለመተኛት ሞክር። አመጋገብህ በልክ
ይሁን ፣ ፆምን ፁም ፣ ቅዱሳት መፃህፍትን አንብብ። መዝሙርንም አዳምጥ ዘምር

#ሀ. ግብረ አውናን እንደ ማር ጠብታ ነው ። የማር ጠብታ ልብስ ላይ የወደቀ እንደሆነ
በፍፁም የሚለቅ አይመስልም ፣ ነገር ግን ትንሽ ለቅለቅ ያደረጉት እንደሆነ ወዲያውኑ
ይለቃል። ይህ ክፋ ልማድም እንደማር በቀላሉ ባይሆንም ከልብ በመፀፀት በጠንካራ
መንፈስ ከተነሱ ሊያስወግዱት ይቻላል። በመጀመሪያ የሚያስፈልገው ከዚ ነገር
መቼም መላቀቅ አልችልም ብሎ ተስፋ አለመቁረጥ ነው ። ከፍተኛ ትግልና ጥረት
ይጠይቃል ። ስለዚህ ተስፋ መቁረጥ ፈፅሞ አይገባም 

#ለ. ሴጋ ልማድ ነው ። ልማድ ደሞ በሌላ ልማድ ይሸነፋል። ጠንክረህ ከተነሳህ ይህን


ተግባር በትዝታ ብቻ የምታስብበት ቀን ሩቅ አይሆንም ። ነገር ግን ከዚህ ልማድ ጋር
ለመዋጋት ከመነሳትህ በፊት "ይህን ክፋ ልማድ ምን ያህል ከልቤ ጠልቼዋለው ? "
በማለት ራስህን ጠይቅ ። መላልሰህ የምትሰናከለው ሳትፀፀት ወይም ሴጋን መተው
ስላልፈለክ ሳይሆን ጣዕሙ በልቡናህ ስላለና ጎጂነቱ ዘልቆ ወደልብህ  ስላልገባ ነው ።
ስለዚህ ይህን ነገር ከልብህ ልትጠላው ይገባል
#ሐ. ይህን ክፋ ልማድ እንደ እሳት የሚያያይዙት የራስህ ተግባርና በዙሪያህ ያሉ
ነገሮች ናቸው ። ከዚህ እኩይ ተግባር መላቀቅ ከፈለክ #ተዐቅቦ ያስፈልግሀል።
#ተዐቅቦ ማለት መከልከል መቆጠብ ማለት ነው ። የምትከለከለውም ወደዚህ
መጥፎ ሐሳብ ልቡናህን የሚስቡትን ነገሮች ከማየት ፣ ከመስማት፣ ከመንካትና ፣
ከመሳሰሉት ነው ። ስለዚህ የሴቶችን ገላ በፊልምም ፣ በአካልም ቢሆን በምንም
መልኩ ከማየት ተቆጠብ።  በመዋኛና በመጠመቂያ ቦታዎች ራስህን ጠብቅ የሴት
ልጅን መልክና ቅርፅ መርዘህና አተኩረህ አትመልከት ።  ስለ ዝሙት የሚያሳስቡ
ሥዕሎችን፣ ፅሁፎችን፣ ወሬዎችን ፣ የሴት ገላ የሚያሳዩ የሙዚቃ ክሊፖችን ፣ የወሲብ
ፊልሞችን አጥብቀህ ሽሻቸው ።ስራህ ሁሉ አንተው እያራገብክ ለምን ይቃጠላል ?
እንዳይሆንብህ 

#መ. ዘወትር ልቡናህ የሚጠመድበትን ነገር ፈልገህ አድርግ ። ቦዘኔ አትሁን ትጉህ
ሰራተኛ ሁን ።ስራህም አይምሮህን የሚያሰራ ቢዚ የሚያደርግ ይሁን ። ትርፍ ሰአት
አይኑርህ ። የሚነበብ ወይም ሌላ የሚሰራ ስራ ፈጥረህ ሥራ 

#ሠ. "ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው " የሚለውን የወንጌል ቃል አስብ ። በዚህ ክፋ
ልማድ ተጠምደህ ሳለ ለብቻህ መሆንን አትውደድ ። ቢቻልህ አኗኗርህና መኝታህ
ከምታፍረውና ከምታከብረው ሰው ጋር ይሁን ። ይህም ጓደኛህ ወይም ከቤተሰብህ
አንዱ ሊሆን ይችላል። በፀሎት ከሚረዱህ መንፈሳውያን መምህራን አባቶች ጋር ጊዜ
ማሳለፍን ውደድ

#ረ. እንቅልፍ የያዘህ ስለ መሰለህ ብቻ ወደ መኝታህ አትሂድ ። አንዳንዴ ተኝተህ


ውለህ እንቅልፍ ያምርሀልና ። ነገር ግን ሰይጣን ሊፈትንህ ከሆነ በምትነኛበት ጊዜ
እንቅልፍ ከአይንህ ይርቃል ። ተከትሎም ፈተናው ይመጣና ወደ ዝሙት ህሊናህ
ይሳባል ። ከዛ ሴጋ ትፈፅማለህ። ስለዚህ ከመተኛትህ በፊት በደንብ መድከምህንና
ቶሎ ማሸለብ መቻልህን መርምረህ ተኛ

#ሰ. ጸሎት ማድረግንም አትርሳ የሚረሳ ነገር አይደለምና ። ስትተኛም በጀርባህ


ወይም በሆድህ አትተኛ ። ከዚህ ይልቅ በጎንህ ለመተኛት ሞክር። አመጋገብህ በልክ
ይሁን ፣ ፆምን ፁም ፣ ቅዱሳት መፃህፍትን አንብብ። መዝሙርንም አዳምጥ ዘምር

#ሸ. እንዲህ ያለ ፈተና ሲነሳብህ /አድርግ አድርግ ሲልህ / ከቻልክ ስገድ ።ወይም የሆነ
እንቅስቃሴ /ስፖርት / ስራ ። ሽንት መሽናትም ጥሩ መፍትሄ ነው አይምሮህ ሽፍት
እንዲያደርግ ያደርገዋል። በየጊዜው ፀበል መጠመቅን ቸል አትበል ። የሴት ገላን
ሳታይ
#ቀ. ሰውነትህን አትነካካ ቢበላህ እንኳን አትከከው ። ስታክና ስትነካካው በዛው
አድርግ አድርግ ሊልህ ይችላልና ። ንፁህ ሁን ፣ ሻወር ውሰድ ፣ ወክ አድርግ ፣ አንብብ ።
ከምንም በላይ አጥብቀህ ፀልይ ።  ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን ።

#ሸ. እንዲህ ያለ ፈተና ሲነሳብህ /አድርግ አድርግ ሲልህ / ከቻልክ ስገድ ።ወይም የሆነ
እንቅስቃሴ /ስፖርት / ስራ ። ሽንት መሽናትም ጥሩ መፍትሄ ነው አይምሮህ ሽፍት
እንዲያደርግ ያደርገዋል። በየጊዜው ፀበል መጠመቅን ቸል አትበል ። የሴት ገላን
ሳታይ

#ቀ. ሰውነትህን አትነካካ ቢበላህ እንኳን አትከከው ። ስታክና ስትነካካው በዛው


አድርግ አድርግ ሊልህ ይችላልና ። ንፁህ ሁን ፣ ሻወር ውሰድ ፣ ወክ አድርግ ፣ አንብብ ።
ከምንም በላይ አጥብቀህ ፀልይ ።  ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን ።

🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
  
t.me/Orthodox_Addis_Mezmur
t.me/orthodox_spiritual_poems
t.me/Eotc_Books_By_Pdf
t.me/Lesangeez128

🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
  

You might also like