You are on page 1of 5

በኢትዮጵያ ወንጌል አመኞች ቤ/ክ ደብብ ሱዳን ጁባ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተ ክስርቲያን

አመታዊ ሪፖርት (ሃምሌ 1/2014-ሰኔ 30/2014)

1. የአባለት መረጃ
1.1 መጋቢት 2013 በፊት የተመዘገቡ አባላት 40(አርባ)ናቸው
1.2 ከሃምሌ 1/2013 -ሰኔ 30/2014

1.2.1- ለኢትዮጵያውያን እና ለደብብ ሱዳናውያን ወንጌል ተመሰክሮላቸዋል፡፡

1.2.2- ከተመሰከረላቸው ውስጥ ቼክ ፓይነት የሚበል የወንጌል ስርጭት ጣቢያ እና የመጠለያ ካንኘ ውስጥ
የሚኖሩ 120(መቶ ሀያ) ደብብ ሱዳናውያን ጌታን ተቀብለዋል፡፡ 3(ሶስት) ኢትዮጵያውያን መሰረታዊ
የክርስትና ትምህርት እየተማሩ ነው፡፡

1.3 አሁን የሚገኙ የቤተክርስቲያቱ አባላት 60(ስልሳ)ናቸው

ወንዶች- 37(ሰላሳ ሰባት) ሴቶች- 23(ሃያ ሶስት)

- አባላት 42 (አርባ ሁለት )


- ተበባሪ አባላት 18 (አስራ ስምንት)

2. ዋና ዋና የተከናወኑ መንፈሳዊ ስራዎች

2.1 በየጊዜው ለአባላት ጉብኝት እና ክትትል ይደረጋል፡፡


2.2 መደበኛ የቤ/ክ ፕሮግራሞች በቋሚነት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
2.3 መገፋሳዊ አንድነትን ለመጠበቅ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ(ማማከር እና እርቅ)፡፡
2.4 በጁባ እና ጁባ ውጪ አበረታች የወንጌል ስርጪት ስራ እየተሰራ ነው፡፡
2.5 የተለያዩ የዘርፍ አገልግሎቶች እንደጠናከሩ እየተሰራ ነው፡፡
- የመዘምራን ዘርፍ
- የድቁና ዘርፍ
- የወንጌል ስርጪት ዘርፍ
2.6 August 14/2022 በተለያዩ ዘርፍ የሚያገለግሉ 14 (አስራ አራት) ለሚሆኑ አገልጋዮች ስልጠና
ተሰጥቷል፡፡
2.7 በቤ/ክ ውስጥ አንድ ጊዜ ለ 21(ሃያ አንድ) ቀን ፆም ፀሎት በሌላ ጊዜ ደግሞ ለ 7 (ሰባት) ቀን
ተውጆ ለጉበኤው ሃይልና ተሃድሶ እንዲሆን ደግሞ ስለምድራች ወቅታዊ ሁኔታ ተፀልያል፡፡
2.8 በቼክ ፓይንት (check point) አካባቢ የሚደረገው ደብብ ሱዳናውያንን ያማከለ የወንጌል ስርጭት
አገልግሎት እንደቀጠለ ነው፡፡
2.9 በኒው ሰይት (new siglt) አካባቢ ደብብ ሱዳናወያንን ያማከለ እና በአካባቢው ያሉ
የቤተክርስቲያናችንን አባላት በማቀናጀት የወንጌል ስርጭት ስራ ለመስራት ቅድመ ሁኔታዎችን
ጨርሰናል፡፡
2.10 በቋሚነት የቤ/ክ አገልጋዮች ቀለብ፣የአደራሻ ኪራይ እና ሌሎችም ወጪዎች እየተከፈለ ይገኛል፡፡
2.11 የመፀሀፍ ቅዱስ ጥናት በተደረጀ እና በተጠናከረ ሁኔታ እና ለማሰቀጠል ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡
2.12 በጁባ ከሚገኙ አቢያተ ክርስቲያናት ጋር ህብረት ለመመሰረት እና በጋራ በምድሪቷ ላይ ወንጌል
ስራ ለመስራት እንቅሰቃሴዎች ተጀመሯል፡፡

3. መደበኛ ፕሮግራሞች በተመለከተ

3.1 በየሳምንቱ እሁድ አምልኮ እና ፀሎት ጊዜ፡፡


3.2 በየሳምንቱ ማክሰኞ የፀሎት ጊዜ፡፡
3.3 በየሳምንቱ ረቡዕ የፀሎት እና የማማከር ጊዜ)፡፡
3.4 በየሳምንት እሁድ ማለዳ የመዘመራት የልምምድ ጊዜ)፡፡
3.5 በየ 15 ቀኑ እሁድ ከመደበኛ አምልኮ በኋላ የመሪዎች ሰብሰባ ጊዜ ፡፡
3.6 አንደየ አሰፋላጊነቱ የጌታ አራት እና የህብረት ጊዜ፡፡
3.7 በየጊዜው የዳኑ ሰዎችን ማሰተማር እና ማጥመቅ፡፡
3.8 አመታዊ የበአላት ቀናቶች ወቅት የጋራ ማዕድ መቁረስ እና የአንድነት ጊዜ
ለምሳሌ፡- የገና በአላት
-የፋሲካ በአል
- የዘመን መለቃጫ

4. ከጁባ ወጪ የሚሽን አገልግሎት

4.1 ካፓይታ ስቴት

- በ 2011 የማደሪጀት ስራ ተሰርቷል፡፡

- 7 ሰዎች የድነት ትምህርት ተምረው 4 ሰዎች የውሃ ጥምቀት ወስደዋል፡፡

- አሁን የሚገኙ አባላት እና ተባባሪ አባላት 15 ናቸው፡፡

- መሪዎች እና ዲያቆናት ተሸመዋል፡፡

- የሙሉ ወንጌል ታፔላ ተላጥፎላቸዋል፡፡

- በየጊዜው በስልክ ክትትል ይደረግላቸዋል፡፡

- በባጀት ምክኒያት አገልጋይ በመላክ ጉብኝት ማድረግ አልተቻለም፡፡


4.2 ጉምሩክ ስቴት

በ 2012 ቁጥራቸው 13 አባላት ያለበት ህብረት የተጀመረ ሲሆን በአሁን ጊዜ የጉሙሩክ ስቴት (Gumruk
state) ከተማዋ በ June 6/2020 በተፋጠረው ሙሉ በሙሉ ስለወደመች በዚያ የነበሩ ቅዱሳን ንብረታቸው
ወድሞ ወደ የተለያየ ሰፍራ ተበትነዋል፡፡

4.3 ፒቦር ስቴት

- በ 2012 የማደረጀት ስራ ተሰርቷል፡፡

- መሪዎች ተመርጠዋል፡፡

- በመንፈሳዊ ህይወት ለደከሙ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡

- አንድ ሰው የውሃ ጥምቀት ወስዷል፡፡

- በአሁኑ ወቅት 7(አባት) የሚሆኑ በጋራ ይፀልሉ፡፡

- በበጀት ምክኒያት አገልጋይ በመላከ መጉብኘት አልተችለም፡፡

4.4 አዊል ስቴት

- በህብረት ደረጃ እንድንይዘችሁ የተወሰቡ ቄጥር ያላቸው ሰዎች ጥያቄ ቢያቀረቡም በበጀት ምክኒያት
ተቀብለን ለህብረት ለናደረጀችው አልቻልንም፡፡

5. የወደፊት ዕቅድ

5.1 መደበኛ ፕሮግራሞችን አጠናክሮ ማሰቀመጥ፡፡

5.2 የወንጌል ስርጭት ላይ አባላትን በማሳተፍ አጠባክሮ መስራት፡፡

5.3 ተጨማሪ የአጥብያይቱ መሪዎችን እና ዲያቆናትን በመምረጥ ሌሎችን ተጨማሪ የአገልግሎት


ዘርፎችን ማቋቋም፡፡

5.4 የአማኞች አንድነት ማጠበቅ፡፡

5.5 ሰፈ ያሉ መንፈሳዊ ኮንፍረንሶችን በማዘጋጀት መነቀቃትን እና ተሃድሶን ማምጣት፡፡

5.6 በወንጌል ማህበርተኝነት ላይ ሁሉምንም አባላት በማሳተፍ ለወንጌል ስራ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ
መፍጠር፡፡

5.7 የላሻላ የአምልኮ ቦታ እንደኖር ጥረት ማድረግ፡፡


5.8 ተተኪ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን ማዘጋጀት፡፡

5.9 በአጥቢያይቱ ስር ያሉትን ህብረቶች ማሳደግ፡፡

5.10 በተቻለ መጠን በጅማሮ ላይ የሚገኘውን የጁባ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ማጠናከር፡፡

5.11 የመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት (home cell) በተጠናከረ ሁኔታ ማሰቀጠል፡፡

5.12 የስርአት ማስፋፀሚያ ልብሶችን (ግብአቶችን) መግዛት፡፡

6. ዋና ዋና ተግዳሮቶች

6.1 የአባላት እና የአገልጋዮች ባልተጠበቀ ጊዜ ሀገር መቀየር(በአንድ ቦታ ፀንቶ አለመቆየት)፡፡

6.2 የአባላቱ የጊዜ እጥረት (በስራ መወጠር በሰአት አለፍ ምክንያት እንደ ልብ አለመገኘት)፡፡

6.3 የፋይናንስ (የበጀት) እጥረት፡፡

6.4 ቋሚ የማምለኪያ ቦታ አለመኖር፡፡

6.5 የአምልኮ አደራሽ ኪራይ በየጊዜው መጨመር፡፡

6.6 በየ ክፍለ ሀገሩ እዘረ የሚያገለግል አገልጋይ አለመኖር፡፡

6.7 በዚህ እኛ ጋር የሚያመልኩ ወገኖች አብዛኛች አስራታቸውን ወደ ኢትዮጵያ የሚልኩ መሆናቸው፡፡

6.8 የአገልጋዮች (መሪዎች፣ዲያቆናት….. በቁጥር መሳሳት እና አገልግሎቱ በሚመጥን ልክ ተገኝቶ


ያለመስራት፡፡

You might also like