You are on page 1of 2

የቤተሳይዳ ልጆች ሕብረት

የምስረታ ቀን: - ጥር 13/ 2014 ዓ.ም.

መስራቾች:

በተለያየ ምክንያት ከወሊሶ ወጥተው በአዲስ አበባ የሚገኙ የቤተሳይዳ ደብረምጥማቅ ቅድስት ድንግል ማርያም ሃይመተ
ዲዮስቆሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት ልጆች፤

የሕብረቱ መመስረት አስፈላጊነት

- የሃይመተ ድዮስቆሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በትምህርት፣ በሥራ፣ ወዘተ ምክንያቶች ከወሊሶ ከወጡ
በኋላ፣ በሚኖራቸው አቅም ልክ ለሰንበት ት/ቤታቸው የበለጠ አስተዋፅኦ ማድረግ ሲችሉ፣ በቦታ ርቀት በመገታት፣
ሰንበት ት/ቤቱን መልቀቃቸው ለዓመታት በመቀጠሉ፤
- ይሄም ሰንበት ት/ቤቱን በቀጣይነት ነባር አባላት በማሳጣት ከአቅም በታች እንዲከውን በማድረጉ፤
- በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ለሚገኙ ነባር አባላት፣ እንደ ስበት ማዕከል ሊያገለግል የሚችል ሕብረት
በማቋቋም፣ የሃይመተ ዲዮስቆሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት ነባር አባላትን እንደ አባል መቀጠል የሚችሉበትን
መንገድ ምቹ በማድረግ፣ ሰንብት ት/ቤቱ ከነባር አባላቱ ማግኘት የሚገባውን በቀጣይነት ማግኘት መቻሉን
ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤

ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች፣ የቤተሳይዳ ልጆች ሕብረት ተመስርቷል፡፡

የሕብረቱ አባላት

- ከወሊሶ ውጪ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ የሰንበት ት/ቤቱ ነባር አባላት
- የሰንበት ት/ቤቱ አባል ለመሆን የሚፈልጉ፣ ነገር ግን በአዲስ አበባ የሚገኙ የቤ/ሳይዳ ልጆች

የሕብረቱ ርእይ

የሃይመተ ድዮስቆሮስ ሰንበት ትምህርት ቤትን በ 2020 ዓ.ም በደቡብ ምእራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት ትልቁ ሰንበት ት/ቤት እና
ስመ-ጥር መንፈሳዊ ተቋም ማድረግ፤

የሕብረቱ ተልዕኮ
በእውቀት ሁሉ የበረቱ፣ በመንፈሳዊ ፍሬዎች ያጌጡ፣ ለሐዋርያዊ አገልግሎት የሚተጉ፣ መንፈሳዊ አገልግሎቷን የሚረከቡ፣
የቅድስት ቤ/ክርስቲያንን እምነት የሚያስተምሩና የሚያስጠብቁ፣ በሀገራዊም ሆነ በዓለም ዓቀፋዊ ክስተቶች ላይ በጎ ተጽዕኖ
መፍጠር የሚችሉ የቤተክርስቲያን ልጆችን ማፍራት፤

እሴቶች

- መንፈሳዊነት

- መደጋገፍ፣ አንድነት

- ትጋት፣ ቀጣይነት፣ ሞልቶ መትረፍ

- ክርስቲያናዊ ኃላፊነት፣ ጽናትና ምስክርነት

- በፍቅር የሆነ አገልግሎት

- ዘመኑን መቅደም

- ተምሳሌትነት

ዓላማ
- የሰንበት ትምህርት ቤቱን መሰረተ-ልማቶችንና አሰራሮችን ማዘመን፣
- ለአባላት የቤተ ክርስቲያን ዕውቀትና ሕይወት ተኮር ትምህርትን ማስተማር፣
- መንፈሳዊ ኮርሶችን ቀጣይነትና ጥልቀት ባለው ሁኔታ በመስጠት፣ ሰንበት ት/ቤቱ በመምህራን ሙሉ በሙሉ ራሱን
ማስቻል፣
- በቂ ሪሶርስ ያለው ቤተ መፃህፍት ማደራጀት፣
- የሰንበት ት/ቤቱ አባላት በአለማዊ ትምህርታቸው የላቀ ውጤት ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻል፣
- ሐዋርያዊ አገልግሎትን ከወሊሶ ከተማ ወጣ ብለው በሚገኙ የአገልጋይ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች
ባሉ አብያተ ክርስቲያናት በተለያየ መንገድ (በጽሁፍ፣ በአካል፣ በድምፅ፣ በቪዲዮ) መስጠት

You might also like