You are on page 1of 9

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

የመካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የመካነ ሕይወት ሰንበት
ትምህርት ቤት

የኹለተኛ መንፈቅ ዓመት


የቤተ- መጻሕፍትና ሰሌዳ መጽሔት ክፍል የአገልግሎት ዘገባ

ነሐሴ 2015 ዓ.ም


አዲስ አበባ
የተሠሩ ሥራዎች
1. ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸውን መረጃዎች በማህበራዊ የመረጃ አውታርና በሌሎች ዘዴዎች ተደራሽ ማድረግ፡፡
 በአዳራሽ ወቅታቸውን የጠበቁ ጥቅሶችን መለጠፍ
 ለመጽሔት እና ለሰሌዳ መጽሔት የሚዘጋጁ ጽሑፎች በሰ/ት/ቤቱ የመረጃ መረብ ማቅረብ
 በበራሪ ጽሁፎችን በማዘጋጀት ለትንሣኤ የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት ማድረስ ተችሏል፡፡
 ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት ሚዲያን (ቴሌግራም፤ በፌስቡክ) ስንክሳር፤ ወቅቱን የዋጁ (ወራትን፤በዓላትን፤ ኩነቶችን ወዘተ) አጫጭር ጽሑፎችን

ለአንባቢያን ተደራሽ ማድረግ


 አራት የሐመር መጽሔትን አጭር ዳሰሳ በማድረግ ለአንባቢያን የይዘት ገለጻ ማድረግ ተሞክራል

2. የቤተ መጻሕፍትን አገልግሎት አሰጣጥ ማዘመንና ማስፋፋት


 ለቤተ መዘክር ግብዐት የሆኑ ነዋየ ቅድሳትን ማስተካከልና አጫጭር ገላጭ ጽሁፍ ማዘጋጀት፡፡
 የመጽሐፍ የውሰት አገልግሎትን በፖኬት ማስፋትና የቤተ መጽሐፍት አባላትን ቁጥርን 100 ማድረስ፡፡ በዚህም በውሰት አገልግሎት የተሸለ

ክትትልና ገቢ ማግኘት ተችሏል


 ቤተ መጻሕፍቱን ለንባብ ዘወትር በሥራ ቀናት ከዕለተ ሀሙስ በስተቀር ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት እስከ 2፡00 ሰዓት ክፍት ለማድረግ ተሞክሯል፡፡
 ከክፍላት ጋር በመነጋገር የንባብ ጊዜ ሰለዳን በማመቻቸት አገልግሎት መስጠት ተችሏል፡፡
 ቤተ መጽሐፍቱን ለትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ምቹ እንዲሆን በማድረግ ክፍላት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ ሆኗል
 የቤተ መጻሕፍቱን አገልግሎትና አዲስ የገቡ መጽሐፍትን ይዘት፣ ደራሲን፣ የታተሙበትን ዓመተ ምህረት ለአንባቢያን ማስተዋውቅ ተችሏል፡፡
የተሠሩ ሥራዎች የቀጠለ
 የንባብ መርሐ ግብር ማዘጋጀት፡- የንባብ መርሃ ግብሩን ለማጠናከር እና አንባቢያንን ለማፍራት የአንባቢያን ቤተሰብ የሚል ስያቤ

የተሰጠው በወር አንድ ጊዜ 14 በዋለ በሳምንቱ የሚደረግ የመጽሐፍ ዳሰሳ ዝግጅት ለመመስረት ተችሏል ፡፡በዚህም መርሀግብር

ላይ የሚገኙ የቤተሰቡ አባላት ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ አንድ መጽሐፍ እንዲያነቡ እና ስለተረዱት የመጽሐፍ ይዘት አባላቱ

እንዲገልጹ የሚደረግበት ሲሆን አሁን ላይ የመርሀ ግብሩ አባላት ጥቂት አባላት ሲሆኑ የመርሀግብሩ ውጤታማነት ታይቶ

ሌሎችንም ለማካተት ታስቧል ፡፡


 የልቡና ችሎት መጽሐፍ ገለጻ መርሐ ግብር ማዘጋጀት ተችሏል፤ በመርሐ ግብሩም ከአርጋኖን ፤ ባኮስ እንዲሁም ሌሎች

የመጽሐፍ መሸጫ መደብሮች ጋር አብሮ የመሥራት መግባባት ላይ የደረስን ሲሆን መርሐ ግብሩን በማህበራዊ ድረገጾቻቸው ከ 50

ሺ በላይ ለአባላቶቻቸው ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዚህም የሰንበት ት/ ቤቱን አገልግሎት በስፋት ማስተዋወቅ የተቻለ ሲሆን፡፡

በመርሐ ግብሩ ከ10 አቻ ሰንበት ት/ቤት አባላት እንዲሳተፉ ተደርጋል፤በምስለ ድምጽ በዕለቱ ላልተገኙ ተደራሽ ተደርጋል፡፡

 ፕሮጀክት 01. ዕርዕሰ ጉዳዮችን በመለየት የማጣቀሻ ምንጭ እንዲሆኑ መጽሐፍትን መለየትና ለአንባቢያን ምቹ እንዲሆኑ

በመሠራት ላይ ይገኛል
 የቤተ መጸሕፍት አስተዳደርን የሚያዘምን የአገልግሎት ሶፍትዌር ማበልጸግ የመጀመሪያ ምዕራፍ የተከናወነ ሲሆን ለግብረ

መልስ ዝግጁ ማድረግ ተችሏል፡፡


የተሠሩ ሥራዎች የቀጠለ

3. ቤተ መጻሕፍትን በዓይነትም ሆነ በብዛት በመንፈሳዊና በአስኳላ መጻሕፍት ማጠናከር


 78 አይነት መጽሐፍት በፖኬት ሽያጭ፤ በመጽሐፍ ውሰትና በስፖንሰር በተገኘ 23,000 ብር በ2015 ለአንባቢያን ተደራሽ የሆኑ

መጽሐፍትን መግዛት ተችሏል ፡፡


 ቆጠራና የተጎዱ መጽሐፍት ጥገና፡፡

4. የሕፃናት ማዕከል /Child Corner/ እና የመንፈሳዊና የቀለም ትምህርት አጋዥ መጻህፍትን ማደራጀትና ማቋቋም፣
 የሕፃናት ማዕከል /Child Corner/ እና የመንፈሳዊና የቀለም ትምህርት አጋዥ መጻህፍትን ማደራጀትና ማቋቋም ተሞክራል፣
 የሕፃናት ማእከል ግብአት የሚሆኑ እቃዎችን ማሰባሰብና ማደራጀት፡ ለህፃናት ማዕከት ግብአት የሚሆኑ የሥዕል ደብተርና ነጭ ቦርድ

የማሰባሰብ ሥራ ተከናውኗል፡፡
 ለሕፃናት ማስተማሪያና የመርጃ መሰሪያዎች ግዢ ተከናውኗል

5. የተደራጀ የሰሌዳ መጽሔት አገልግሎት መስጠት


 በክፍሉ ያሉ ጽሑፎችን ለሰሌዳ መጽሔት እንደየዘርፋቸው እና አገልግሎት ላይ እንደሚውሉበት ጊዜ ማደራጀት
 ሰሌዳ መጽሔቱን እድሳት በማድረግ ለአገልግሎት ብቁ እንዲሆንና በሚወሰንለት ቋሚ ቦታ ለማስቀመጥ ውሳኔዎችን መጠበቅ
6. ኦዲዮ ቪዥዋል ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ማጠናከር
 ቤተ መጽሐፍቱ ከ30ሺ በላይ መጸሐፍትን በሶፍት ኮፒ ማሰባሰብ ተችሏል፡፡
 ቨርችዋል ቤተ መጻሕፍት ለማደራጀት የሚሆን ቅድመ ሁኔታዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የተሠሩ ሥራዎች የቀጠለ

7. ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት መጽሔት ጥራትና ይዘት ማሻሻል፣


 ለመጽሔትና ለሰሌዳ መጽሔት የሚሆኑ ጽሑፎችን የማሰባሰብ ሥራ ተከናውኖ በየወሩ የዲጂታል

ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት መጽሔት ለአንባቢያን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዲጂታል

መጽሔቱም በአማካኝ በየወሩ 5000 ተመልካች ተደራሽ ሆነዋል፡፡

8. የአገልግሎት አፈፃጸምን ክትትልና ምዝና፡


 ለክፍሉ አባላት ግንዛቤ በመፍጠር የንዑስ ክፍላትን የሥራ ዕቅድና አፈጻጸም መከታተል
 ከቁጥጥር ክፍል ጋር በመሆን የሦስት ወር የክፍሉን አፈጻጸም መገምገምና ግብረ መልስ መስማት
 በየሳምንቱ ቅዳሜ ከ 12፡30 - 2፡00 ሰዓት የአገልግሎት አፈጻጸምና ሒደት ላይ መወያየት
 የክፍሉን አገልግሎት ክንውን ዘገባ ለሰ/ት/ቤቱ ጽ/ቤት ማቅረብ
 የኮምፒውተር ፍተሻ ማድረግ
 ክፍል አባላት ጋር የሕይወትና የአገልግሎት ውይይት ማድረግ
የተሠሩ ሥራዎች የቀጠለ
ያልተሠሩ ሥራዎች

 የአርትዖት ኮሚቴ መረጣ የተከናወነ ሲሆን ይፋዊ ምስረታ አለማድረግ


 የቤተ መጻሕፍቱን ኮምፒተር ፍተሻ ቢደረግም ጥገና ማከናወንና ለምስለ ድምጽ አገልግሎት ዝግጁ ማድረግ
 ከሌሎች ሰ/ት/ቤቶች ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረግ
 የሥነ ጽሑፍና ሌሎች ከክፍሉ የአገልግሎት ጋር ተያያዥነት ያለቸውን ስልጠናዎች ማዘገጀት
አገልግሎቱን ለማከናወን ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ መፍትሔዎች፡

ያጋጠሙ ተግዳሮቶች
 የክፍልን አገልግሎት ላይ ውስን ተሳትፎ ማድረግና በሌሎች አገልግሎቶች መጠመድ

 ከጽፈት ቤ/ት የሚጠበቁ ውሳኔዎች መዘግየት

 ከአፋዊ የዘለለ የክፍላት አብሮ የመስራት ፍላጎት ዝቅተኛ መሆን

 ከሰንበት ት/ቤት የሚመደብ በጀት እጥረትና ቅድሚያ አለመስጠት

የተሰጡ መፍትሔዎች
 ከአባላት ጋር የመነጋገር

 ከክፍላት ሰብሳቢዎች የክፍላትን አገልግሎት ላይ መወያየት በአንድ ላይ ማቀድ

 የአባላትን የትምህርት ዝግጅት መጠቀም

 ስፖነሰር ማፈላለግ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን!!!

You might also like