You are on page 1of 1

1.

“ሥርዓተ ትምህርቱ ተግባራዊ እንዲሆን የቀረበው ጥሪ ተቀብለን ለተግባራዊነቱ የበኩላችንን ለመወጣት ቃል እንገባለን” ሲሉ
የ፵፪ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች ገልጹ

ከጥቅምት ፭ እስከ ፲ በተከናወነው ፵፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ
በቀረበው ፴፫ ነጥቦችን ባቀፈው የጉባኤው የአቋም መግለጫ እንደተገለጸው “የወጣቶችን የሰንበት ተምሀርት ቤት መስፋፋት
በተለይም በማደራጃ መምሪያ በኩል ተዘጋጅቶ ወደ እንቅሰቃሴ እየገባ በሚገኘው የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ
ለአጠቃላይ ዓለም አቀፍ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች የቀረበው ማብራሪያ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ብፁዕ ዋና ሥራ
አስኪያጅና መመሪያ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ፤ ሥርዓተ ትምህርቱ ተግባራዊ እንዲሆን የቀረበው ጥሪ ተቀብለን
ለተግባራዊነቱ የበኩላችንን ለመወጣት ቃል እንገባለን፡፡” በማለት ያሳወቁ ሲሆን በመቀጠልም ወደፊት የሚቀርቡት ማስተማሪያዎች
የወጣቱን ሥነምግባር ያማከለ ከቁማርና ከሱስ የሚጠበቁበት እንዲሆን በማለት ጉባኤው አሳስቧል፡፡

ለአምስት ቀናት በቆየው ጉባኤ የ፳፻፲፭ ዓ.ም የአኅጉረ ስብከቶች አፈጻጸም ዘገባዎች የቀረቡ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ም/ሰብሳቢ ዲ.ን ስንታየሁ ምስጋናው በሰንበት
ትምህርት ቤቶች እያስተገበረ ስላለው ሥርዓተ ትምህርት በተመለከተ ለጉባኤው ገለጻ ተደርጓል፡፡ በተያያዘም ለሁሉም አኅጉረ
ስብከቶች ከጠቅላይ ቤተክህነቱ በደብዳቤ የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡

2. በመንበረ ጵጵስና (አዳማ) የና/ደ/ታ/ም/ፀ/ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ/ክ ፈ/ብርሃን ሰ/ት/ቤት ለተማሪ ለወላጆች ስለ ሥርዓተ
ትምህርቱ ስልጠና ሰጠ፡፡ በ 2015 ዓ.ም በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት ዓመቱን ሙሉ ተምረው ትምህርቱን ላጠናቀቁ የሰት/ቤት
አባላትም ካርድ ተሰጥቷ፡፡ በዕለቱ ከ 1 ኛ ክፍል ፣ከ 2 ኛ ክፍል ፤ከ 4 ኛ ክፍል እና ከ 7 ኛ ክፍል ከ 1 ኛ – 3 ኛ ደረጃ ለወጡ
ተማሪዎችም ሰ/ት/ቤቱ የማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል፡፡

**********************

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲን በሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት ፣ በመንበረ ጵጵስና ወረዳ ቤተክነህት
የና/ደ/ታ/ም/ፀ/ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ/ክ ፈ/ብርሃን ሰ/ት/ቤት በ 2015 ዓ.ም በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት ዓመቱን ሙሉ
ተምረው ትምህርቱን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን የደብሩ የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ፣ የተማሪ ወላጆችና የሰ/ቤቱ አባላት በተገኙበት በቀን
11/02/2016 ዓ.ም ካርድ ሰጠ፡፡ በዕለቱ ለወላጆች ስለ ሥርዓተ ትምህርቱ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ከ 1 ኛ ክፍል ፣ከ 2 ኛ ክፍል
፤ከ 4 ኛ ክፍል እና ከ 7 ኛ ክፍል ከ 1 ኛ – 3 ኛ ደረጃ ለወጡ ተማሪዎችም ሰ/ት/ቤቱ የማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል፡፡

በመርሐ - ግብሩ የተሳተፉት የተማሪ ወላጆች ስለ ሥርዓተ ትምህርቱ አስተያየት የሰጡ ሲሆን ፤ ሰ/ት/ቤቱ ሕጻናትንና ወጣቶችን
ለማብቃት የሚሠራውን አገልግሎት አመስግነው ለሥርዓተ ትምህርቱ ትግበራ የሚያስፈልጉ የትምህርት ቁሳቂሶችንና ሌሎች
አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸው ገልጸዋል፡፡ በዕለቱ ለሰ/ት/ቤቱ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ በፈቃዳቸው
ቃል የገቡ የተማሪ ወላጆችም አሉ፡፡

የደብሩ አስተዳዳሩ መልአከ ገነት ቀሲስ ወንድወሰን ሐበነ ሰ/ት/ቤቱ መርሐ - ግብሩን መልዕክት ያስተላፉ ሲሆን ፤ ሥርዓተ
ትምህርት ትግበራን ጨምሮ ሌሎች የሚሠራቸው አገልግሎት አመስግነው ፤ ለሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ተጨማሪ የሚያስፈልጉ
የመማሪያ ክፍሎችም ሆኑ ሌላ የገንዘብ መሠል ድጋፍን ለማድረግ ሰበካ ጉባኤው ከሰ/ት/ቤቱ ጎን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት የተከናወነው መርሐ - ግብር ሊከናወን ታቅዶ የነበረው በ 2015 ዓ.ም የመጨረሻ ወር ውስጥ የነበረ ቢሆንም
በተለያዩ ምክንያቶች መርሐ - ግብሩ እየተገፋ መጥቶ ዛሬ የተከናወነ ሲሆን ፤ የ 2016 ዓ.ም የትምህርት ተጀምሮ እየተሰጠ መሆኑን
ሰ/ት/ቤቱ አሳውቋል፡፡

You might also like