You are on page 1of 2

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ቀን:

17/11/2015
ለ:ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሚድያ ዝግጅት ክፍል

ጉዳይ፦ ለመንፈሳዊ መሳሪያ ምርቃት መርኀ-ግብር ጥሪ ማቅረብን በተመለከተ

በቅድሚያ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እያልን ማኅበራችን ማኅበረ ኀዳፌ ነፍስ ላለፉት ሦስት
አመታት የበገና፣ክራር እና መሰንቆ መሳሪያዎችን በማስተማር ከ 300 በላይ የሚሆኑ ኦርቶዶክሳዊያን ያስመረቀ
ሲሆን። በተለያዩ የቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ላይ ተማሪዎቹን በማሳተፍ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት
እየሰጠ ያለ ማኅበር ሲሆን።

እንደ አምላካችን መልካም ፈቃድ በ 2015 ዓ.ም ከሦስት ወር ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ማኅበሩ
ሲያስተምራቸው የነበሩትን የበገና፣የክራር እና የመሰንቆ ተማሪዎች በቀጣይ ወር ማለትም በነሐሴ 27 ቅዳሜ
ዕለት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ባለው ትልቅ አዳራሽ ምርቃቱን ለማድረግ በሥራ ላይ
ይገኛል።

በዕለቱም የተጋበዙ ብጹዓን አባቶች፣የደብራት አስተዳዳሪዎች፣መምህራነ ወንጌል እና ዘማሪያን ይገኙበታል።


በእዚህ ታላቅ ዕለት ለወራት ሲማሩ የነበሩትን ተማሪዎቻችንን ባረክናክሙ እም ቤተ እግዚአብሔር ብለን
እንደ አባቶቻችን ሥርዓት እንመርቃቸዋለን። በእዚሁ ዕለትም የማኅበራችን መስራች የሆነው ዲያቆን
ዳግማዊ ሰለሞን “ኦርቶዶክሳዊ ወጣት እና ፈተናዎቹ” በሚል ርዕስ ያዘጋጀው መጽሐፍ በመምህራን የሚዳሰስ
እና በብጹዓን አባቶች የሚመረቅ ይሆናል።

ስለዚህም የቤተክርስቲያናችን ትልቁ ሚዲያ የሆነው ኢ.ኦ.ተ.ቤ ቴቪ በእዚህ መርኀ ግብር ላይ ይገኝልን ዘንድ
ከላይ በጉዳዩ እንደጠቀስነው እንጋብዛለን። መርኀ ግብሩን 7:00 የሚጀምር ሲሆን እስከ 10:30 የሚቆይ
ይሆናል።

መልሳችሁን እንጠብቃለን እግዚአብሔር አምላክ ለቤተክርስቲያን የምትፈጽሙትን አገልግሎታችሁን


ይባርክልን።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!


ዲያቆን ዳግማዊ ሰለሞን

የማኅበሩ ሰብሳቢ

You might also like