You are on page 1of 28

“በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን”

• በሚ/ቴ/ዩንቨርስቲ የአማን ህክማና እና ጤና ሳይንስ ካምፓስ ግቢ ጉባኤ


 በሚ/ቴ/ዩ/የአማን ህክምና እና ጤና ሳይንስ ካምፓስ ግቢ ጉባኤ ከተመሰረተ ጀምሮ አሁን ላይ ካለበት ደረጃ
እስኪደርስ ድረስ የሰራቸዉን በጎ( መልካም) ስራዎች ያጋጠሙትን ፈተናዎች እንዲሁ ያለፈባቸዉን
አጠቃላይ ኩነቶች እንደሚከተለዉ እናቀርባለን።
 ይህ የሚ/ቴ/ዩ/ህ/ጤ/ሳ/ካምፓስ ግቢ ጉባኤ በማህበራችን ማህበረ ቅዱሳን በማዕከላችን በሚዛን ማዕከል
ከሚገኙት ስድስት(6) ግቢ ጉባኤ አንዱ ነዉ።
 ግቢ ጉባኤዉ ከዋናዉ (እናት) ግቢ ጉባኤ ሚ/ቴ/ዩ/ዋና ካምፓስ ግቢ ጉባኤ ተገንጥሎ ለብቻዉ መሆኑን
ተከትሎ በሾንጋ መንበረ ንግስት ቅድስት ቁስቋም ግቢ ጉባኤ ሲገለገሉ(ሲያገለግሉ) የነበሩ የጤና ተማሪዎች
ወደ አማን ህክምና እና ጤና ሳይንስ ካምፓስ መምጣታቸዉ ይታወቃል ። በመሆኑም እነዚህ ተማሪዎች ከ
አለማዊ ትምህርታቸዉ ጎን ለጎን መንፈሳዊ ትምህርታቸዉን የሚማሩበት ስለሃይማኖታችዉ የሚረዱበት እና
በመንፈሳዊ ህይወታቸዉን ከፍ የሚያደርጉበት እንዲሁም እራሳቸዉን በሃይማኖት በምግባር ጠንቅቀው
የሚያዉቁበት ከርቀትም አንጻር ጊቢ ጉባኤ መመስረቱ እጅግ አስፈላጊ ነገር ሆኖ ተገኝቷል።
 ስለሆነም ማህበራችን ማህበረ ቅዱሳን ለተማሪዎች የትኛዉ አጥቢያ ይቀርባቸዋል?
እንዲሁም ሰው (አገልጋይ) የሚያስፈልገው አጥቢያ የትኛዉ ነው የሚለውን
በማጥናት እና ከአባቶች ጋር በመነጋገር ተማሪዎች በአማን ደብረሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ና አቡነ
ሀብተማርያም ቤተ ክርስቲያን እንዲገለገሉ ና እንዲያገለገሉ ተወስኖ ግቢ ጉባኤዉ በ2013 አም የካቲት
21 ቀን ተመስርቷል።
ከዚህ በፊት የነበሩ ስራ አስፈጻሚዎች እንደነገሩን የአማን ደብረሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስና
አቡነሃብተማርያም ቤተ ክርስቲያን በመናፍቃን የተከበበና ያሉት ምዕመናን ትንሽ በመሆናችው በግቢ
ጉባኤው መመስረት የአከባቢው መዕመንና የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ደስታቸ ወደር የሌለው እንደሆነ
ነግረዉናል።
• የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ልጆቻችን ሲመጡ ዝም ብለን አንቀበላቸውም በማለት ከማህበረ ቅዱሳን ሚዛን ማዕከል
ጋር በመነጋገር ታላላቅ መምህራንና ዘማርያን በመጋበዝ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ አዘጋጅቶ የካቲት 21 /2013
ዓም ተማሪዎች በደመቀ ሁኔታ እንደተቀበላቸው መረጃች ይጠቁሙናል።

• በዚሁ ቀን የአማን ወረዳ ማእከልና የሚዛን ማእከል የግቢ ጉባኤ ስራ አስፈጻሚዎች በመምረጥ ግቢ
ጉባኤውን በሞግዚትነት እንዲያስተዳድረው ለአማን ወረዳ ማእከል ሙሉ ውክልና ሰጥቶ ጉባኤው
ተጠናቋል።
ግቢ ጉባኤው ከተመሰረተ ጀምሮ የተሰሩ ስራዎችን ስንመለከት፡

• ከየካቲት 2013 እስከ መስከረም 2014 ዓም ድረስ


• ለግቢ ጉባኤው የአገልግሎት ማስኬጃ የሚሆን አዳራሽ ማስፈለጉን የተረዳው የደብሩ ሰበካ ጉባኤ
ስራ ጀምሮ ከቆየ በኋላ ከግቢ ጉባኤው ስራ አስፈጻሚዎች ወይም አመራሮች ጋር በመሆን “12 በ
20” የሆነ 240 ቅጠል ቆርቆሮ እንዲሰራ ተደርጓል።
• የግቢ ጉባኤው የስራ አመራሮች አገልግሎትን ለማስኬድ የሚወያዩበት ጽህፈት ቤት ያስፈልጋቸዋል
በማለት ካሉት ቤቶች አመቻችቶ በጠየቁት መሰረት ሰበካ ጉባኤው ሰጥቷቸዋል።
• ግቢ ጉባኤውና ሰበካ ጉባኤው እንዴት መቀጠል እንዳለባቸው ዉይይት ካደረጉ በኋላ የአደራሽ
ስራ በፍጥነት ተጀምሮ ለአገልግሎት እንዲደርስ መጀመር እንዳለበት ተነጋግረው በውሳኔ
አሳርፈዋል።
• በዚሁ ዓመት ማለትም የካቲት 2013 ዓም የአደራሽ ስራ ተጀምሮ የፍልጥ(የግድግዳ) ስራና ቆርቆሮ
የማልበሱ ስራ መጠናቀቅ እንደቻለ የቅርብ ቀን ትውስታችን ነው።
• ከአደራሽ ስራው ጎን ለጎን ለጽህፈት ቤት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በከፊል ተሟልተዋል።
• እነዚህም፡
 መደርደሪያ
 ባለድጋፍ ወንበር
 አግዳሚ ወንበር
 ጠረጴዛ ወዘተ ሟሟላት ተችሏል።
• ተማሪዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመጡ በማድረግ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ከፍ ለማረግ፡
 የኮርስ ትምህርት
 የሰርክ መርሃ ግብር
 የመዝሙር ጥናትን
 የቤተሰብ መዋቅር በመስራትና የንስሃ አባት በመስጠት አገልግሎቱ በተሳለጠ መልኩ እንዲቀጥል ከፍተኛ አስተዋጽኦ
ተደርጓል።
• ተማሪዎችን የህይወት ተሞክሯቸዉን በመካፈል እና ኝኙነታቸዉ እንዲቀጥል መንፈሳዊነትን በጋራ
እንዲአጠናክሩ ለማድረግ ጉዞ መርሃግብር እንዲሁም ልዩ መርሃግብር በማዘጋጀት ትልቅ
አስተዋጽኦ እንደነበር ይታወቃል።
• የሽሀይቤት እና የቤተ መጽሐፍት አገልግሎትም እንዲጀምር ተደርጓል።
• የ2013 ዓም ስራ አመራሮች(ስራ አስፈጻሚዎች) እነዚህን በጎስራዎች ከሰሩ ና ለግቢ ጉባኤዉ
ትልቅ መሰረት ከጣሉ በኋላ የስራ ዘመናቸዉን በእግዚአብሔር አጋዥነት አጠናቀዉ ስራዉን
የሚያስቀጥሉ አዲስ ስራ አስፈጻሚዎችን (አመራሮችን) በመምረጥ የጀመሯቸዉን እንዲያስቀጥሉ
ሰጥተዉ መስከረም 2014 ዓም አስረክበዋቸዋል።
ግቢ ጉባኤዉ የገጠመዉ ችግር እና ፈተናዎቹ
ከመስከረም 2014ዓም እስከ ሰኔ 2014ዓም በነበረዉ የግቢ
ጉባኤ ቆይታ ስንመለከት
• በዋናነት የተጀመሩትን ስራዎች ማስቀጠል እና ግቢ ጉባኤዉን ከነበረዉ ከፍ ለማድረግ ትልቁን
አስተዋጽኦ አድርጓል።
• ከእነዚህም ዉስጥ፡
 አዳራሹን ለመምረግ እና የዉስጥ ስራዎችን ለመስራት ከፍተግኛ ግፊት አድርገዋል።
 ከሰበካ ጉባኤዉ ጋር በመወያየት ስለአደራሽ ስራው እና ለወደፊት ለሚሰራው ዉል በመዉሰድ ግቢ ጉባኤዉ ሙሉ
ሃላፊነት ወስዶ እንዲሰራ ዉሳኔ እንዳሳረፉ መረጃዎችን አስቀምጠዋል።
 የሽሀይ ቤት አግልግሎት እንዲሁም ሌሎች የልማት ስራዎችን ለመስራት እይተንቀሳቀሰ ከቆየ በኋላ ስራዉን እንዲሰራ
ግፊት አድርገዋል።
• ተጨማሪ ሌሎች አገልግሎቶች የተጀመሩትን በሀላፊነት ወስደዉ በቋሚነት አስቀጥለዋቸዋል።
• አዲስተማሪዎች ሲመጡ ተቀብለው ግቢ ጉባኤዉ እንዲቀጥል አድርገዋል።
• ተማሪዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመጡ በማድረግ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ከፍ ለማረግ፡
 የአብነት ትምህርት
 የኮርስ ትምህርት
 የሰርክ መርሃ ግብር
 የመዝሙር ጥናትን
 የቤተሰብ መዋቅር በመስራትና የንስሃ አባት በመስጠት አገልግሎቱ በተሳለጠ መልኩ እንዲቀጥል ከፍተኛ አስተዋጽኦ
ተደርጓል።
• ቀድሞ ተጀምሮ የነበረዉን የበገና ትምህርት በማስቀጠል እና ከግቢጉባኤው በማስተማር ከ10
በላይ የሆኑ የበገና ተማሪዎችን አስመርቀዉ ተምሮ ማስተማር በሚል ዛሬም ተምረዉ እያስተማሩ
ይገኛል።
• ልዩ ልዩ መርሀግብራትን በማዘጋጀት እና አባልትን በህይወታቸዉ ላይ መንፈሳዊነት እንዲበረታታ
ለማድረግ መንፈሳዊ ድራማ በማዘጋጀት አባላት እንዲቀርቡና ተሳትፎ እንዲኖራቸዉ አድርገዋል።
ከሰኔ /2014 ዓም እስከ ሰኔ /2015 ዓም ድረስ ግቢ
ጉባኤዉ የነበረዉ ቆይታ
• በዋናነት የተጀመሩትን ስራዎች ማስቀጠል እና ግቢ ጉባኤዉን ከነበረዉ ከፍ ለማድረግ ትልቁን
አስተዋጽኦ አድርጓል።
• አዳራሹን በዉስጥ እና በዉጭ በኩል የህንጻ አሰሪ ኮሚቴ በመምረጥ እና በማስተባበር እንዲመርግ
ተደርጓል።
• ለአዳራሹ ለግዜው የሚያስፈልጋቸዉን በሮች እና መስኮቶች በመለየት በሮቹ እና መስኮቶቹ
ተገጥመዋል።
• ከደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጋር በመነጋገር ለልማት የሚሆኑ ቤቶችን ሰርተን እንድንጠቀምባቸዉ
በምስፈቀድ ሽሀይ ቤት እና የሱቅ ቤት መርገን እንድንጠቀምባቸዉ ትልቅ አስተዋጽኦ
አበርክተዋል።

• ሱቅ በመክፈት እና ሽሀይቤቱን በማጠንከር ለግቢ ጉባኤዉ ገቢ ማስገኛ ትልቅ አስተዋጽኦ


አበርክተዋል።
• ተማሪዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመጡ በማድረግ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ከፍ ለማረግ፡
 የአብነት ትምህርት
 የኮርስ ትምህርት
 የሰርክ መርሃ ግብር
 የመዝሙር ጥናትን
 የቤተሰብ መዋቅር በመስራትና የንስሃ አባት በመስጠት አገልግሎቱ በተሳለጠ መልኩ እንዲቀጥል ከፍተኛ አስተዋጽኦ
ተደርጓል።
 የበገና ትምህርትን በማስተማር እናም የተማሩት ያልተማሩትን በማስተማር ልጆችን ብቁ እንዲሆኑ እና ለውድፊት
ጥሩ አገልግሎት እንዲኖራቸዉ ማድረግ ተችሏል።
• ልዩ ልዩ መርሀግብራትን በማዘጋጀት እና መንፈሳዊ ጉዞ በማዘጋጀት የአባላትን እንክብካቤ ጥሩ
እንደነበር ይታወሳል።
ከሰኔ /2015 ዓም እስከ የካቲት 24 /2016 ዓም ድረስ የግቢ
ጉባኤዉ ቆይታ
• ግቢ ጉባኤው አሁን ላይ ያለበትን ደረጃ ስንመለከት
• በዋናነት የተጀመሩትን ስራዎች ማስቀጠል እና ግቢ ጉባኤዉን ከነበረዉ ከፍ ለማድረግ ትልቅ
አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።
• አሁን ላይ ባለዉ ጠቅላላ የግቢ ጉባኤው አባላት 351 ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ደግሞ በግቢ ጉባኤዉ
ተሳትፎ ኑሯቸው የሚገለገሉ እና የሚያገለግሉ 298 ገዳማ ናቸዉ።
• ከንዚህም መካከል በአብነት ትምህርት ላይ ያሉ ተማሪዎች ብዛት=
• በመዝሙር ላይ ያሉ ቋሚ አባላት ብዛት=
• በበገና ላይ ያሉ ጠቅላላ አባላት ብዛት=
• ይሁን እንጅ ተማሪው ትንሽ ከመሆናችን አንጻር ሲታይ አንድ ሰው ከሁለት ክፍላት በላይ
እየተገለገለ እና እያገለገለ ይገኛል።
ግቢ ጉባኤዉ አሁላይ እየሰጠው ያለዉ መርሀ ግብር
• ተማሪዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመጡ በማድረግ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ከፍ ለማረግ፡
 የአብነት ትምህርት=ከሰኞ እስከ አርብ ጧት እና ማታ ልማት ባለ ቀን ማክሰኞን ጨምሮ
 የኮርስ ትምህርት= ለሁሉም ባች እሁድ ከ 4፡00 እስክ 6፡00
 የሰርክ መርሃ ግብር= ሰኞ ልማት ከሌለ ማክሰኞና እረቡ ከ11፡45 እስከ 12፡45 እና በጽዋ ቀን
 የመዝሙር ጥናት= ሰኞ ማክሰኞ ሀሙስ ናቅዳሜ
 የቤተሰብ መዋቅር በመስራትና የንስሃ አባት በመስጠት አገልግሎቱ በተሳለጠ መልኩ እንዲቀጥል ከፍተኛ አስተዋጽኦ
ተደርጓል።
 የበገና ትምህርትን በማስተማር እናም የተማሩት ያልተማሩትን በማስተማር ልጆችን ብቁ እንዲሆኑ እና ለውድፊት
ጥሩ አገልግሎት እንዲኖራቸዉ ማድረግ ተችሏል።
• የልሳነ ግዕዝ ትምህርት ለሁሉም ባች በአንድ ላይ ሃሙስ በሰርክ ሰዓት እየተሰጠ ይገኛል።
• ልዩ ልዩ መርሀግብራትን በማዘጋጀት እና መንፈሳዊ ጉዞ በማዘጋጀት የአባላትን እንክብካቤ ጥሩ
ደረጃ ላይ ለማድረስ ተሞክሯል።
• ለአባላት እንደ አስፈላጊነታቸዉ ስልጠና እና ልዩ መርሀግብር ማዘጋጀት።
• ከልማት አንጻር ስንመለከት፡
• ከዚህ በፊት ከእንጨት ስራ እስከ መረጋ ድረስ ተሰርቶ የተረከብነዉን አዳራሽ የዉስጥ ስራዉን
ለመስራት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።
 ፓርትሽን መስራት መምረግ
 የአዳራሹን አዉደ ምህረት መስራት
 የአዳራሹን የዉስጥ አሰራ በስሚንቶ ማሰር
በተጨማሪም ለግቢ ጉባኤዉ አገልግሎት ሊዉሉ የሚችሉ 10 አግዳሚ ወንበር መስራት
ተችሏል።
በግቢ ጉባኤው በሙያና ተራድኦ በጎ አድራጎት ክፍል ተደራጅተዉ ትልቅ ስራ
ተሰርቷል
አሁን ላይ ግቢ ጉባኤዉ እየገጠሙት ያሉ ችግሮች እና
ፈተናዎቹ
1. የአባላት መቀነስ ፡ምክንያቱን ስናይ
 የአዲስ አባል ተማሪዎች ወደ ግቢ አለመግባት
 ግቢ ዉስጥ ያሉ ተማሪዎች Practice (ሌላ ቦታና ሆስፒታል ) ከግቢ መዉጣት
 ተማሪዎች ለእረፍት ሲወጡ እንደየ ዲፓርትመንት ስለሆነ በየጊዜዉ ይቀንሳል
 ከአለማዊ ትምህርት ጫና መብዛት የተነሳ የጊዜ ማጠር

2. ከአባላት መቀነስ የተነሳ የግቢ ጉባኤዉ የገቢ ምንጭ ማነስ እና ያቀዳቸዉን ስራዎች ለመስራት
መቸገር
3. ግቢ ጉባኤዉ ያቀዳቸዉን ስራዎች በወቅቱ አለመስራት እና አለመጨረስ
4. ግቢ ውስጥ የግቢ ጉባኤዉን አባላት በጓደኝነት በፆታ ቅርርቦሽ ወደ ቢተክርስቲያን እንዳይቀርቡ
የማድረግ ጫና
5. የሰርክ መርሀ ግብር በግቢ ጉባኤው መሆን የመምህራን እጥረት የአባላት መቀነስ እና ሌሎች መርሀ
ግብር የጊዜ ማጠር
• ከፆታ ቅርርቦሽ ጋር ተያይዞ ከማይመሰላቸዉ ሃይማኖት (ከኢ አማኒያን) ጋር ከሃይማኖት ህግ እና
ስራዓት ውጭ መታየት
አጠቃላይ ግቢጉባኤዉ ከተመስረተ ጀምሮ ሁሌም
የሚያደርጋቸው መርሀ ግብሮች
• ባዓላትን ማክበር 1 የትንሳኤን ባዓል
2 የገናን(የልደት) ባዓል
ልዩ ልዩ መርሀ ግብራትን ማዘጋጀት
የጉዞ መርሀ ግብር ማዘጋጀት
ነዳያንን መጠየቅ
ጽዋወችን ማስኬድ
አዲስ ገቢተማሪዎችን ወደ ግቢ ሲመጡ መቀበል

You might also like