You are on page 1of 12

አማርኛ/Amharic

2019–2020
ስለማክበር መመሪያ

የሃይማኖት ብዝሃነት/RELIGIOUS DIVERSITY


በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)
www.montgomeryschoolsmd.org

Rockville, Maryland
Board of Education የትምህርት ቦርድ

Mrs. Shebra L. Evans ወ/ሮ ሸብራ ኤል. ኢቫንስ


President ፕሬዚደንት

Mrs Patricia B. O’Neill ወ/ሮ ፓትሪሻ ቢ ኦኔይል


Vice President ም/ፕሬዚደንት

Ms. Jeanette E. Dixon ሚስ ጃኔት ኢ. ዲክሰን

Dr. Judith R. Docca ዶ/ር ጁዲት አር. ዶካ


ራእይ
Ms. Karla Silvestre ሚ/ስ ካርላ ሲልቨስትሪ
ለእያንዳንዱና ለማንኛውም
ተማሪ እጅግ የላቀውን ህዝባዊ Mrs. Rebecca K. Smondrowski ወ/ሮ ርብቃ ኬ. ስሞንድሮውስኪ
ትምህርት በማቅረብ መማርን
እናበረታታለን። Ms. Brenda Wolff ሚስ ብረንዳ ዎልፍ

Mr. Nathaniel Tinbite አቶ ናትናኤል ትንቢተ


ተልእኮ Student Member የተማሪ አባል

እያንዳንዱ ተማሪ በኮሌጅ Montgomery County


እና በሥራ መስክ ውጤታማ Public Schools (MCPS) Administration
እንዲሆን/እንድትሆን፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አስተዳደር
በአካደሚክስ፣ ችግር
የመፍታት ዘዴ/ ብልሃት Jack R. Smith, Ph.D. ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)
ፈጠራ፣ እና የማህበራዊ Superintendent of Schools የት/ቤቶች ዋና ተቆጣጣሪ
ስሜት ክህሎቶች ይኖሩታል/
Monifa B. McKnight, Ed.D. ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. መክናይት
ይኖሯታል።
ም/ሱፐርኢንተንደንት

ዋና ዓላማ Maria V. Navarro, Ed.D. ማሪያ ቪ. ናቫሮ የትም/ዶክተር


Chief Academic Officer የአካደሚ ዋና ኃላፊ
ሁሉንም ተማሪዎች የወደፊት
ህይወታቸው እንዲዳብር/ Kimberly A. Statham, Ph.D. ኪምበርሊ ኤ. ስታተም (ዶ/ር)
እንዲበለጽግ ማዘጋጀት፡፡ Chief of School Support and Improvement
የትምህርት ቤት ድጋፍ እና መሻሻል ዋና ኃላፊ

ዋነኛ እሴቶች Andrew M. Zuckerman, Ed.D. አንድሪው ኤም. ዙከርማን (ዶ/ር)


Chief Operating Officer ዋና የሥራ ኃላፊ
መማር/እውቀት
ግንኙነቶች
አክብሮት
ልቀት
ፍትኃዊነት/ሚዛናዊነት
850 Hungerford Drive
Rockville, Maryland 20850
www.montgomeryschoolsmd.org
MARYLAND ሜሪላንድ

ውድ ወዳጆች፡-
የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የማህበረሰባችንን ብዙሃነት የሚያቅፍ እና
እያንዳንዱ ተማሪ ለስኬትና ለብልፅግና እድል እንዲኖረው ለሚያረጋግጥ የመከባበርና
ለርተአዊነት ባህል ቁርጠኝነት ቃል ገብቷል። ይህ ቁርጠኝነት በሞንትጎመሪ ካውንቲ
የትምህርት ቦርድ ፖሊሲ ACA ላይ ተካቷል፣አድሎ የሌለበት፣ እኩልነት/ፍትህ፣ እና
የዳበረ ባህላዊ ብቃት፣ ፍትሐዊነትን ለመፍጠር፣ ለመንከባከብ፣ እና ለማሳደግ፣ ሁሉን
የሚያካትት እና ሁሉን መቀበል/በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው የማህበረሰባችንን
የረዥም ጊዜ ጥረት የሚያረጋግጥ ነዉ። የዚያ ግዴታ በከፊል ተማሪዎቻችን የሃይማኖትና
ሃይማኖት-የለሽ እምነቶች እና ልምምዶች፣ ከኣድልዎ፣ ማሸማቀቅ፣ ወይም ወከባ ነፃ
በሆነ መንገድ የመግለፅ መብታቸውን ማረጋገጥ ነው። እንደ ት/ቤት ዲስትሪክት፤ ለእነዚህ
እምነቶች እና ልምምዶች ሊተገበር የሚችል እና ተቀባይነት ያለው ማመቻቸት ለማድረግ
ቆርጠን ተነስተናል።
ለዚህም ነው ይህን መመርያ ያዘጋጀነዉ። በዚህ ኣስፈላጊ ኣርእስት ትኩረት የሚያደርጉ
በርካታ የቦርድ መመርያዎችና የMCPS ደንቦችና ሂደቶች ኣሉ። የሚጠበቁብን
ለሰራተኞቻችን፣ ለተማሪዎቻችን፣ ለቤተሰቦቻችን፣ እና ለማህበረሰባችን ግልፅ እንዲሆኑ
ይህን ሁሉ መረጃ ኣንድላይ በኣንድ ቦታ ላይ ማሰባሰብ አስፈላጊ ሆኖ ስለተሰማን ነው።
ይህን መመርያ ለመፍጠር ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የስራ ኣስፈፃሚ የእምነት ማህበረሰብ
የስራ ቡድኖች እና ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር በቅርበት አብረን ሰርተናል፣
አጋርነታቸውንና ትብብራቸውንም እናደንቃለን። እነዚህ አጋርነቶች ስለትምህርት፣
ስለግንኙነቶች፣ ስለመከባበር፣ ስለልቀት፣ እና ስለፍትህ ያለንን ዋነኛ እሴቶቻችንና
የገባነውን ኣደራ ጥልቀት ይሰጡታል።
ይህን መመርያ ትምህርታዊ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ ኣለን። ለሁሉም ተማሪዎቻችን
ሰላማዊ፣ አወንታዊ፣ እና መከባበር የሰፈነባቸው የመማርያ አካባቢዎችን ለመፍጠር
በምናደርጋቸው ጥረቶች በቀጣይነት ስለምታደርጉልን ድጋፎቻችሁ እናመሰግናችኋለን።

ከአክብሮት ጋር፣

Shebra L. Evans ሼራ ኤል. ኤቫንስ


President, Montgomery County Board of Education
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፕረዚደንት

Jack R. Smith, Ph.D. ዶር. ጃክ ኣር. ስሚዝ


Superintendent, Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክስኩልስ ዋና ተቆጣጣሪ
መግቢያ
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የኃይማኖት ብዙህነትን ማክበር
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪዎቻችንን ሃይማኖቶች፣ እምነቶች፣ እና ልምዶች ብዙሃነት
መከባበርና አድናቆትን ለማስፈን በቁርጠኝነት ይሠራል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ብዙ ዓይነት
ባህል አጅጉን ከላቁት ጥንካሬዎቻችን ኣንዱ እንደሆነና በት/ቤቶቻችን አብረን ስንማር ማኅበረሰባችንን ማበልፀግ አለበት
ብሎ ያምናል። መከባበር የ MCPS ዋነኛ እሴት ነው፣ ስለሆነም፣ ሁሉም ቤተሰቦች አክብሮት እንዲሰማቸው የሚያደርግ
ባህል መኮትኮት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።
አገራችንና የሜሪላንድ ስቴት ለሃይማኖት ነፃነት ጥበቃ እና በቤተክርስቲያን እና በመንግስት መለያየት ለሁለቱም ጥልቅና
የቆየ ግዴታ ኣላቸው። የመጀመርያው የዩ.ኤስ. የህገ መንግስት ማሻሻያ አንቀጽ እንደሚለው፡- "ኮንግሬስ የሀይማኖት
መቋቋምን የሚያከብር ምንም ኣይነት ህግ ኣያወጣም፣ ወይም የዚያኑ ነፃ ትግባሬ የሚከለክል..." ይህም ማለት መንግስት
ኣንደኛውን ሃይማኖት ከሌላው በላይ ማራመድ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት-የለሽ ለይቶ መምረጥ፣ ወይም ጥላቻ መግለፅ
ወይም ሃይማኖትን መቃወሞ ኣይችልም።
የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል የሃማኖትን
ህዝባዊ ድጋፍ መስጠት ውድቅ እያደረጉ በሌላ በኩል የሁሉንም ተማሪዎች የሃማኖት ነፃነትን መብቶች መጠበቅ ኣለባቸው።
ት/ቤቶች ሃይማኖትን ማራመድ ወይም ማደናቀፍ የለባቸውም፣ ተማሪዎችም በኮርሶች ወይም በት/ቤት ስፖንሰር በሚደረጉ
እንቅስቃሴዎች፣ እንደ ምረቃ ወይም ስብሰባዎች በመሳሰሉ፣ የሃይማኖት እምነቶች ጥብቅና የማይደረግበት ኣካዴሚያዊ
ኣካባቢ መብት ኣላቸው። በተመሳሳይ መልኩ፣ ተማሪዎች ለሃይምኖታዊነታቸው ወይም ሃይማኖት-የለሽነት እምነቶችና
ልምዶቻቸዉ፣ ከኣድልዎ፣ ማሸማቀቅ፣ ወይም ወከባ ነፃ የሆነ መብት ኣላቸው፣ እናም MCPS ለነዚያ እምነቶችና ልምዶች
ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉና ተቀባይነት ያላቸው መገልገያዎች ለማድረግ ግዴታ ገብቷል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የስራ ኣስፈፃሚ የእምነት ማህበረሰብ የስራ
ቡድን ጋር በመተባበር እነዚህን መመርያዎች የፈጠረው፣ ተማሪዎች በት/ቤት ውስጥ እና በት/ቤት ስፖንሰር በሚደረጉ
እንቅስቃሴዎች ባሉበት ወቅት ስለ ሃይማኖት መመርያዎች ኣዘውትረው ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ነው።
ጠቃሚ ሆኖ እንዳገኛችሁት ተስፋ እናደርጋለን። በዚህ መመርያ ውስጥ ስላለ ማንኛውም ነገር ጥያቄ ካላችሁ፣ እባካችሁ
በቅድሚያ ከት/ቤታችሁ ኣስተዳዳሪዎች ጋር ተነጋገሩ። ሌላ ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሉዎት፣ የ MCPS Office of
the Chief of Staff, Student Welfare and Compliance በስልክ ቁጥር፦ 240-740-3215፣ ወይም COS-
StudentWelfare@mcpsmd.org ያግኙ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩል (MCPS) የሥራ ባልደረቦች ጥያቄዎን
ለመመለስ ካልቻሉ የትምህርት ቦርድ የሠራተኞች ኃላፊን/Board of Education Chief of Staff/Ombudsman
በስልክ ቁጥር፦ 240-740-3030፣ ወይም boe@mcpsmd.org ለማግኘት ይችላሉ።
እነዚህ መመርያዎች የተተለሙት፣ በነዚህ ርእሶች ዲስትሪክቱን የሚመሩትን በርካታ የሞንትጎመሪ ካውንቲ
(Montgomery County) የትምህርት ቦርድ መመርያዎች እና የMCPS ደንቦች፣ እንዲሁም የስቴትና የፌደራል ህጎችን
በሚመለከት፣ ፈጣን ማጣቀሻ ለመስጠት ነው። እነዚህ ህጋዊ ግዴታዎች ሊለውጡ የሚችሉ ናቸው እናም በዚህ ህትመት
ከተጠቀሱት መግለጫዎችና ማጠቀሻዎች ይልቅ የበላይነት እንዳላቸው እባክዎ ይገንዘቡ። ተጨማሪ መረጃ በእኛ ድረገጽ፣
www.montgomeryschoolsmd.org ይገኛል።

ፈጣን የማጣቀሻ መመርያ ተማሪዎች በትምህርት ቀን ፀሎት ማድረግ ይችላሉ


ወይ?
ዘወትር የሚቀርቡ ጥያቄዎች እዎን፣ በተወሰኑ ሁኔታዎች። ለልዩ ተጨማሪ መረጃ
እባካችሁ ፀሎትና ሃይማኖታዊ ኣለባበስ የሚለውን የነዚህን
የኃይማኖት በአላትን ለማክበር ተማሪዎች ሲቀሩ መመርያዎች ክፍል (ገፅ 3) ተመልከቱ።
ይቅርታ ይደረግላቸዋል ወይ?
አዎ ቤተሰቦች ቀሪዎችን ለማሳወቅና ለመሰነድ ሁሉንም ተማሪዎች ከሃይማኖታቸው ጋር የተዛመደ ልብስ
መደበኛ ሂደቶች መከተል አለባቸው። ለተጨማሪ መረጃ መልበስ ይችላሉ ወይ?
በኃይማኖት በዓላት ምክንያት መቅረት የሚለውን የነዚህን አዎ በቦርድ መመርያና በ MCPS ደንቦች መሰረት፣
መመርያዎች ክፍል (ገፅ 2) እባክዎ ይመልከቱ። ተማሪዎች ስካርቮች፣ ሂጃቦች፣ ያርሙልኮች፣ ፓትካዎች፣
ወይም ሌላ ከሃይማኖታቸው ጋር የተያያዘ ልብስ መልበስ
ተማሪዎች በበአላት ምክንያት ሲቀሩ ለተጓደለ ስራ ይችላሉ። ስለልዩ ተጨማሪ መረጃ እባካችሁ ፀሎትና
መተካት ይችላሉ ወይ? ኃይማኖታዊ ኣለባበስ የሚለውን የነዚህን መመርያዎች
አዎ ቤተሰቦች ለተጓደለ ስራ ማካካሻ ለማሳካት ከልጃቸው ክፍል (ገፅ 3) ተመልከቱ።
ት/ቤት ጋር አብረው መስራት አለባቸው። ይበልጥ
ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እባካችሁ ለሃይማኖት በዓላት በት/ቤት ስራዎች የሀይማኖት ርእሶች መወያያ ሊሆኑ
መቅረት የሚለውን የነዚህን መመርያዎች ክፍል (ገፅ 2) ይችላሉ ወይ?
ተመልከቱ። አዎ ተማሪዎች የስራ ግዴታዎችን እስካሟሉ
ድረስ፣የሃይማኖት እምነታቸውን ወይም ሃይምኖት-

1
የለሽነታቸውን በት/ቤት ስራዎች መግለፅ ይችላሉ ለርእሱ ሃይማኖታዊ በዓል ከማክበር ጋር በተያያዘ ምክንያት
ተፈላጊ እስከሆነና አግባብነት እስካለዉ ድረስ፣ እናም ዘግይቶ መምጣት ወይም አስቀድሞ ለመለቀቅ ተቀባይነት
በዚህ መመርያ ላይ የተገለጹትን ሌሎች መመርያዎች ያላቸውን ጥያቄዎች MCPS ያስተናግዳል፣ ነገር ግን
እስከተከተሉ ድረስ። በተጨማሪ፣ በስነፅሁፍ፣ ታሪክ፣ በወላጅ/አሳዳጊ መፈቀድ አለባቸው።
እና በኪነጥበባት ውስጥ ስለ ሀይማኖት ያልተዛቡና ሀቀኛ
ትምህርቶች የስርአተትምህርት አካል ሊሆኑ ይችላሉ። ምንም እንኳን ማንኛውም የኣትሌቲክ ክውነት ወይም
ለተጨማሪ መረጃ ሃይማኖት በትምህርት ፕሮግራም ውስጥ ልምምድ ተሳትፎ በኣብዛኛው በክውነቱ ወይም
የሚለውን የነዚህን መመርያዎች ክፍል (ገፅ 3) እባክዎ በልምምዱ እለት ኣትሊቶቹ የተመደበላቸውን የትምህርት
ይመልከቱ። ፕሮግራም እንዲከታተሉ ተፈላጊ ቢያደርገውም፣
እንደ የሃይማኖት በኣል ኣከባበር የመሰሉ ኣስቀድመው
ት/ቤቶች የተማሪዎችን ሀይማኖት-ነክ የአመጋገብ የተመደቡ እንቅስቃሴዎች ያሏቸው ተማሪዎች አስቀድመው
ማእቀቦችን ያስተናግዳሉ ወይ? ከት/ቤታቸው ፈቃድ እስካገኙ ድረስ፣ በኣትሌቲክ
አዎ ት/ቤቶች ከሀይማኖት ጋር የተያያዙ የአመጋገብ ገደብ ክውነቶች ወይም ልምምዶች በቀሪው ቀን እንዲሳተፉ
ካለቸው ተማሪዎች ጋር ያለማቋረጥ ይሰራሉ። ለተጨማሪ ይፈቀድላቸዋል።
መረጃ ምግብና የሃይማኖት ስነ ስርኣትየሚለውን የነዚህን
መመርያዎች ክፍል (ገፅ 5) እባካችሁ ተመልከቱ። ነፃ የሃይማኖት ኣምልኮ የህገ መንግስት መብት ስለሆነ፣
ፍፁምነት ላለው የትምህርት ክትትል ሽልማት ያላቸው
ተማሪዎች የሀይማኖት የመረጃ ቁሳቁሶችን ማሰራጨት የMCPS ት/ቤቶች መቅረቶቻቸው ለተፈቀዱላቸው
ይችላሉ ወይ? ለሃይማኖት በኣላት ብቻ ለሆኑ ተማሪዎች ሽለማቶቹን
አዎ ተማሪዎች የሃይማኖት የመረጃ ቁሳቁሶችን ልክ ላይከለክሉ ይችላሉ።
እንደሌሎች ከት/ቤት እንቅስቃሴዎች ጋር ያልተያያዙ
የመረጃ ቁሳቁሶች ደንቦች መሰረት ማሰራጨት ይችላሉ • ለተጨማሪ ዝርዝሮች፣ የMCPS ደንብ JEA-RA፣
። ተማሪዎች ቁሳቁሶች የት፣ መቸ፣ እና እንዴት የተማሪ ክትትል፣ www.montgomeryschoolsmd.
እንደሚሰራጩ የት/ቤት ህጎችን ማክበር ኣለባቸው። org/departments/policy/pdf/jeara.pdfን
ለተጨማሪ መረጃ እባካችሁ የሃይማኖት መረጃ ቁሳቁሶች ተመልከቱ።
ስርጭትየሚለውን የነዚህን መመርያዎች ክፍል (ገፅ 5)
ተመልከቱ። ከሃይማኖት በኣላት ማክበር መቅረት በኋላ
ሀይማኖታዊ ከትምህርት ውጭ ክበቦች በት/ቤት የመተኪያ ስራ
ይፈቀዳሉ ወይ? ተማሪዎች ከት/ቤት በመቅረታቸው ላልሰሩት ስራ ሃላፊነት
አዎ አንደ ሌሎች በት/ቤት ከሚቀርበው ኣርእስት ጋር ኣለባቸው ባጠቃላይም እንዲተኩ ይጠበቅባቸዋል።
ቀጥታ ግንኙነት የሌላቸው የተማሪ ከትምህርት-ጊዜ-ውጭ የሃይማኖት በኣላት ሲያከብሩ የሚያመልጣቸውን ለመተካት
ቡድኖች፣ ተማሪዎች ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ ክበቦች መራዘሚያዎች ወይም ሌላ መገልገያዎች ለማሳካት
የማደራጀት ወይም ተሰብስቦ የሃይማኖት ስብሰባዎች፣ ኣስቀድመው ፕላን ማድረግ ለተማሪዎችና ለወላጆች/
የፀሎት ቡድኖች፣ ወይም ሌሎች ሃይማኖታዊ ልምዶችን ኣሳዳጊዎች የተሻለው ኣማራጭ ነው። ቢሆንም፣ MCPS
ከትምህርት-ጊዜ-ውጭ የማክበር መብት ኣላቸው። እነዚህ ይህ ሁልጊዜ ተግባራዊ ነው ወይም ሊሆን ይችላል ማለት
ሃይማኖት-ነክ ከትምህርት-ጊዜ-ውጭ ስብሰባዎች ወይም እንዳልሆነ ይገነዘባል። ቀሪነቱ ፈቃድ ካለው፣ የተማሪው/ዋ
ክበቦች በተማሪዎች የሚመሩ መሆን ኣለባቸው። ለተጨማሪ መምህር ያመለጠውን ጊዜ ለመተካት ተማሪው(ዋ)ን
መረጃ እና ልዩ መመርያ፣ እባካችሁ ከስርእተትምህርት ያግዘዋል/ታግዘዋለች/ያግዛታል/ታግዛታለች፣ ዳግመ-ፈተና
ውጭ የተማሪ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች የሚለውን ያቀርባል/ታቀርባለች፣ ወይም በተማሪው/ዋ የሃይማኖት
የነዚህን መመርያዎች ክፍል (ገፅ 6) ተመልከቱ። በኣል ሲከበር መፈፀም ለነበረበት የክፍል ስራ ወይም
የቤት ስራ ማራዘሚያ ጊዜ መስጠት። እያንዳንዱ ሁኔታ
በሃይማኖት በኣላት ምክንያት ቀሪዎች አንድ ባንድ መታየት እንዳለበት የተጠበቀ ሆኖ፣ ከተፈቀደ
የሀይማኖት በአል ለማክበር መቅረት በኋላ ተማሪዎች
እስከ ሶስት የትምህርት ቀኖች ለመተኪያ የማራዘም ብቃት
ክትትል እና የሃይማኖት በዓላትን ለማክበር
ይኖራቸዋል።
መቅረት
በየእለቱ በት/ቤት ተገኝቶ ክትትል ማድረግ ለተማሪ ስኬት በተጨማሪ፣ የቤት ስራ ሲሰጡ፣ ት/ቤቶች ለማህበረሰባችን
ወሳኝ ነው። ቢሆንም፣ ተማሪዎች በተለያዩ ምክንያቶች፣ አባላት ኣስፈላጊ የሆኑትን ባህላዊ፣ የዘር፣ የሃይማኖት፣
የሃይማኖት በዓላትን ለማክበር ጨምሮ፣ ኣልፎ ኣልፎ ከት/ እና ሌሎች በዓላት ወይም ክውነቶች ግንዛቤ ውስጥ
ቤት እንደሚቀሩ MCPS ይገነዘባል። አነዚህ የተፈቀዱ እንዲያስገቧቸው ያስፈልጋል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ
መቅረቶች ናቸው፣ ተማሪዎችም ለጎደሉ ስራዎች መተኪያ በድረገጽ ላይ፦ www.montgomerycountymd.
አንዲያደርጉ ይፈቀድላቸዋል። ተማሪዎች ከት/ቤት gov/mcg/commemorations.html. የሚገኙ፣
ከቀሩ፣ ትቤት ከተመለሱበት በሶስት ቀኖች ውስጥ የፅሁፍ የሃይማኖታዊ፣ የዘር፣ እና ከካውንቲ ነዋሪዎች ባህላዊ ቅርስ
ማብራርያ የሚሰጥ ማስታወሻ ከወላጅ/ኣሳዳጊ ማምጣት ጋር የተዛመዱ የተወሰኑ በዓላትን የሚያካትቱ፣ የሚከበሩ
ኣለባቸው። እለቶችን ዝርዝር አዳብሯል።

2
በ MCPS ድረ-ገጽ ላይ የሚገኘው የቀን መቁጠርያ Days የሃይማኖት ልብስ
of Commemoration/የክብረ በዓላት ቀኖችን የ MCPS በሚከተሉት ምክንያቶች ካልሆነ በስተቀር ተማሪዎች
የት/ቤት መዘጋት በመረጃነት በተጨማሪ፣ ለሰራተኞች፣ በኣለባበሳቸው ምክንያት ብቻ የዲሲፕሊን እርምጃ
ተማሪዎች፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች እና የማህበረሰብ አባላት ኣይወሰድባቸዋም፡-
ማጣቀሻ እንዲሆኑ እንዲታዩ ያደርጋል። የቀን መቁጠርያው • በት/ቤት እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ረብሻ
በ www.montgomeryschoolsmd.org/info/ የሚያስከትል መስሎ ከታየ፣
calendars/ ይገኛል። • ለጤና ወይም ለደህንነት ኣስጊ ከሆነ፣
• የኮርስ ወይም የእንቅስቃሴ ተገቢ ግዴታ ማሟላት
ፀሎት እና ሃይማኖታዊ ልብስ የሚሳነው ከሆነ፣
• ከወንበዴዎች ጋር ግንኙነት ካለው፣
ፀሎት በት/ቤት • ሴሰኛ፣ ስድ፣ ፀያፍ፣ ወይም የሚያጋልጥ ወይም ፆታዊ
እንቅስቃሴዎቹ በፍላጎት የሚካሄዱ፣ በተማሪ የተነሳሱ፣ ባህርይ ካለው፣ ወይም
እና የመማርያ ክፍል ትምህርትን፣ ሌሎች የት/ቤት • የትምባሆ፣ የኣልኮል፣ ወይም ሌሎች እፆች መጠቀምን
አንቅስቃሴዎችን፣ ወይም የሌሎችን መብቶች በጣም የሚገፋፋ/የሚያደፋፍር ከሆነ።
ካልረበሹ ወይም ካላደናቀፉ በስተቀር፣ ተማሪዎች ከሌሎች
ተማሪዎች ጋር በመሆን ለመፀለይና በሃይማኖታቸው አለባበሳቸው ከነዚህ መመርያዎች ጋር የሚስማማ እስከሆነ
ኣመለካከት ለመወያየት ነፃ ናቸው። ለምሳሌ፣ እንድ ተማሪ ድረስ፣ ተማሪዎች ከሀይማኖታቸው ጋር የተያያዙ ወይም
ከምግብ በፊት ወይም ከፈተና በፊት ኦፊሲየል ባልሆኑ የሀይማኖት መልእክት የያዙ ያንገት ሻሾች፣ ሂጃቦች፣
ቦታዎች፣ እንደ ካፊቴርያዎች ወይም መተላለፍያዎች፣ ያርሙልክስ፣ ፓትካስ፣ ወይም ሌላ ልብስ ወይም ጌጣጌጥ
ተማሪዎች ሃይማኖታዊ ባልሆኑ እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ መልበስ እንዲፈቀድላቸው ይገባል።
በተፈቀደላቸው መጠን፣ መፀለይ ወይም የሃይማኖት በሚቻል ወቅት፣ በኣካል ማጠንከርያ ትምህርት ወቅት
ፅሁፎችን ማንበብ ይችላል/ትችላለች፤ ወይም አንድ ወይም በት/ቤት ስፖንሰር በሚሆኑ እንቅስቃሴዎች
የተማሪ ኣትሊት ከውድድር በፊት ወይም የተችዳውን የተወሰኑ ልብሶችን፣ ከሃይማኖት እምነታቸው ኣንፃር
ወይም የጎል ግብ ካገኘ(ች) በኋላ ውድድሩን ከመጠን ኣስነዋሪ ሆኖ ከታያቸው፣ ለመልበስ ወይም ላለመልበስ
በላይ እስካላዘገየው ወይም እስካልረበሸ ወይም በሌሎች ተማሪዎች (ወይም ለወላጅ/ኣሳዳጊ በነሱ ፈንታ) ፈቃድ
ኣትሊቶች ወይም ተመልካቾች መብቶች ጣልቃ እስካልገባ ከጠየቁ ት/ቤቶች ተገቢ መስተንገዶ መስጠት ኣለባቸው።
ድረስ መፀለይ ይችላል/ትችላለች። ምንም እንኳን የዚህ አይነቶቹ መስተንግዶዎች/ማመቻቸቶች የተማሪን
ተማሪዎች የመፀለይ መብታቸውን በትምህርት ቀን ወይም በአንድ እንቅስቃሴ መሳተፍ አይከለክሉም/አያግዱም።
ከት/ቤት በተያያዙ እንቅስቅሴዎች ማስከበር ቢችሉም፣ ለምሳሌ፣ የሜሪላንድ ህዝባዊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች
ሌሎችን በፀሎት፣ ስብከት፣ ወይም በሌላ የሀይማኖት ኣቴሊቲኮች ማህበር በት/ቤቶች መካከል በሚካሄዱ
እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ወይም እንዲያዳምጡ ማስገደድ፣ ውድድሮች የሚሳተፉ ኣትሌቶችን "የራስ መሸፈኛ፣
ማዋከብ፣ ወይም መገፋፋት አይችሉም። ለምሳሌ፦ ጥምጣም፣ ወይም ሌላ አስፈላጊ የሆኑ ሀይማኖታዊ
በተማሪ-የተመሩ ፀሎቶች በት/ቤቱ የህዝብ ማስታወቂያ ልብስ ለተጫዋች ወይም ለሌሎች ሻካራ፣ ጠንካራ፣
ስርኣት ለሁሉም ክፍሎች ማሰራጨት ኣይፈቀድም። ወይም ኣደገኛ ያልሆነ፣ እናም በጨዋታ ጊዜ ተመንጥቆ
ኣንድ ተማሪ ለፀሎት የሚሆን ፀጥተኛ ቦታ ከጠየቀ/ች፣ እንደማይሄድ ሆኖ የተለበሰ እንዲለብሱ" ይፈቅዳል።
ቦታ እስካለ ድረስ፣ የተማሪ ደህንነት ለማረጋገጥ የአትሌቲኮች መስተንግዶዎችን የሚመለከቱ ስለሌሎች
የሚቆጣጠር ኣግባብ ያለው ሰራተኛ እስካለ ድረስ፣ እና ጥያቄዎች፣ እባካችሁ የት/ቤት አትሌቲክ ዳይሬክተር
የትምህርት ሂደት እስካልረበሸ ድረስ፣ ት/ቤቶች ጥያቄውን ወይም የ MCPS አትሌቲክ ክፍልን ያማክሩ።
ለማስተናገድ ተገቢ ጥረት ያደርጋሉ። ይህም በሚድያ
ማእከል፣ ባዶ የመማርያ ክፍል፣ ወይም በሌላ ክፍል ሃይማኖት በትምህርት ኣሰጣጥ ፕሮግራም
ውስጥ ኣንድ የፀጥታ የተሞላበት ስፍራ ማለት ሊሆን ውስጥ
ይችላል።

ተማሪዎች እና ወላጆች/ኣሳዳጊዎች መገንዘብ የሚኖርባቸው ሃይማኖት በት/ቤት ስራዎች ውስጥ


የ MCPS መምህራን፣ ኣስተዳዳሪዎች፣ እና ሌሎች መግለጫዎቻቸው ለኣርእስቱ ኣስፈላጊ እስከሆኑና የስራ
ሰራተኞች የተማሪ ፀሎቶች ወይም ሌሎች የተማሪ ግዴታዎችን እስካሟሉ ድረስ ተማሪዎች የሃይማኖት
ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች በትምህርት ሰኣቶች ወይም እምነቶቻቸውን ወይም ኣለማመናቸውን በት/ቤት ስራዎች
በት/ቤት ስፖንሶርድ በሆኑ ክውነቶች ኣያደራጁም፣ ለመግለፅ ነፃ ናቸው። በት/ቤት ስራዎች ግምገማ ላይ፣
ኣይመሩም፣ ኣያነሳሱም፣ ኣይደግፉም፣ ወይም በተግባር መምህራን በተማሪዎች ስራ ውጤቶች ላይ ከሃይማኖት
ኣይሳተፉም። በተማሪ ፀሎቶች ወይም ሌሎች በተማሪ ይዘት በመነሳት ኣድልዎ ኣይፈፅሙም። የት/ቤት ስራ
የሚመሩ የሃይማኖት እንቅስቃሴዎች የ MCPS ሰራተኞች የሚመዘነው በመደበኛ ኣካዴሚያዊ መመዘኛዎችና በሌሎች
ሊገኙ ይችላሉ ኣላማዎቹ ግን የተማሪንና የት/ቤት ደህንነት ህጋዊ የትምህርት ጥቅሞች ነው። ለምሳሌ፣ ኣንድ ስራ
ለማረጋገጥ ለመከታተልና ቁጥጥር ለማድረግ ብቻ ነው። ግጥም መፃፍን የሚያካትት ከሆነ፣ ተማሪ ያቀረበ/ችው

3
በፀሎት መልክ የተፃፈ ግጥም ስራ (እንደ መዝሙረ ዳዊት እና በኪነጥበባት የሃማኖቶችን ሚና እውቅና ይሰጣል።
ወይም ፒዩት/piyyut) በኣካዴሚያዊ መመዘኛዎች (እንደ እንዲያውም፣ የሃይማኖታዊ ተፅእኖዎችን ግንዛቤ ሳይሰጡ
የስነፅሁፍ ልቀት) ይገመገማል እንጂ በግጥሙ የሃይማኖት እነዚህን ርእሶች ማስተማር በጣም ኣስቸጋሪ ያደርገዋል። የ
ይዘት በመነሳት ኣይ(ት)ቀጣም ወይም ኣይ(ት)ሸለምም። MCPS ስርኣተትምህርት በባለበርካታ ባህል ኣገር ውስጥ
ሙሉ ዜግነትን ለማዘጋጀት በመንግስትና በሃይማኖት
ነፃነት መካከል ስላለው ግንኙነት የተማሪዎችን ግንዛቤ
በሃይማኖት ምክንያት ከትምህርት ፕሮግራም በተጨማሪ ይገነባል። በተገኘ ቁጥር፣ የሃይማኖት ገፅታዎች
የመቅረት ፈቃድ ጥያቄዎች ውይይት የሚደረግባቸው ስለ የሃማኖቶች ታሪክና ኣመዛዛኝ/
በተቻለ መጠን፣ በሃይምኖታዊ እምነቶቻቸው ላይ ትርጉም comparative ጥናት የሚመረጡ/elective የክፍል
ያለው ጫና ይፈጥርብናል ብለው ከሚያምኗቸው ከተወሰኑ ትምህርቶች ተማሪዎች መከታተል ይችላሉ።
የመማርያ ክፍል ውይይቶች ወይም እንቅስቃሴዎች ይቅርታ
እንዲደረግላቸው ከተማሪዎች፣ ወይም ከወላጆቻቸው/ ተማሪዎች ስለሃይማኖት ሲማሩ፣ መጠበቅ ያለባቸው
ኣሳዳጊዎቻቸው ተማሪዎቻቸውን በመወከል፣ የሚቀርቡ የትምህርት እንቅስቃሴዎች ርተአዊ፣ ያልተዛቡ፣ እና
ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ት/ቤቶች የትምህርት ማንኛውንም ሃይማኖታዊ ሆነ ኢሀይማኖታዊ እምነቶች
ፕሮግራሞችን ተቀባይነት ያላቸውና ተግባራዊ ሊሆኑ የማያንቋሽሹ ናቸው። የህብረ-ብዙ ህብረተሰብ ኣይነተኛ
የሚያስችሉ የማስተካከል ስራዎች ለመተግበር ሙከራ ባህርይ የተማሪዎችን የተለያዩ እምነቶች ማክበር ነው።
ማድረግ አለባቸው። ተማሪዎች፣ ወይም ወላጆቻቸው/ በመምህራን፣ ተማሪዎች፣ እና በእንግዳ ተናጋሪዎች
ኣሳዳጊዎቻቸው፣ እንቅስቃሴው የተማሪው(ዋ)ን ሃይማኖት የሚሰጡ ንግግሮች የተለዩ ሃይማኖታዊ ርእዮቶችን ከሌሎች
በማመልከት የተማሪው(ዋ)ን ብቸኝነት የሚደፍር መሆኑን ሃይማኖትዊ ወይም ኢሃይማኖታዊ ርእዮቶች ይሻላሉ ብሎ
ካመኑበት፣ ተማሪዎች፣ ወይም ወላጆቻቸው/ኣሳዳጊዎቻቸው መስበክ ወይም ማቀንቀን የለባቸውም። ተማሪዎች ስለ
ተማሪዎቻቸውን በመወከል፣ ከመማርያ ክፍሉ ለመቅረት ሃይማኖት ባህሎች ኣስተያየታቸውን ለማካፈል መምረጥ
እንዲፈቀድላቸው የመጠየቅ መብት ኣላቸው። አንድ/ ወይም ላለመምረጥ ይችላሉ። ተማሪዎችም በበኩላቸው
ዲት ተማሪ ከት/ቤት እንቅስቃሴዎች እንዲቀር/እንድትቀር ለሃይማኖታዊ ልምዶች ቃል ኣቀባዮች ወይም ወካዮች
ሲፈቀድለት/ላት፣ ተማሪዉ/ዋ ለት/ቤት እንቅስቃሴው እንዲሆኑ ኣንጠየቅም ብለው መጠበቅ ኣለባቸው። ለእንደዚህ
ወይም ስራ ተለዋጭ ኣማራጭ ይሰጠዋል/ይሰጣታል። ኣይነቱ ሁኔታ ተማሪዎችን ለይቶ ማውጣት ምቾት
እንዳይሰማቸው ሊያደርግ ይችላል፣ እናም የአንድን ተማሪ
እነዚህን መርሆች በመተግበር፣ተመሳሳይ የትምህርት የሃይማኖት ተሞክሮ የጠቅላላ ቡድን ወካይ ፈፅሞ መደረግ
ዓላማዎችን የሚያሟላ አማራጭ በመስጠት በሀይማኖታዊ የለበትም።
መስኮች/ስፍራዎች አንድ የተለየ የጽሑፍ- ምንባብ
ሥራ ላይ ተመርኩዞ ከተማሪዎች ወይም ከወላጆቻቸው/ እንደ የማስተማርያ መሳርያ ወይም መገልገያ፣ ት/ቤቶች
ሞግዚቶቻቸው የሚቀርብን ተቃውሞ ማስተናገድ ተገቢ የሃይማኖት ምስሎች/symbols ን እንደ የሃይማኖት
ሊሆን ይችላል። ቢሆንም፣ ተነጥሎ የመቅረት ጥያቄዎች ወይም ባህላዊ ናሙናዎች ኣድረገው ሊጠቀሙባቸው
ከመጠን በላይ እየበዙ ወይም ከመጠን በላይ እየከበዱ ይችላሉ። ነገር ግን እነዚህ የትምህርት መሳርያዎች ወይም
ከመጡ፣ ት/ቤቱ ጥያቄዎቹን ማስተናገድ ሊቃወሙ መገልገያዎች መታየት ያለባቸው ኣግባብ ያለው የመማርያ
ይችላል። ት/ቤቶች የተማሪን የሃይማኖት ልምድ ወይም ክፍል ትምህርት ለማጀብ ለጊዜያዊ ወቅት ብቻ መሆን
እምነት ለማስተናገድ ብለው የትምህርት ፕሮግራም ኣለበት።
መሰረታዊ ለውጥ ማድረግ፣ ወይም የተለየ የትምህርት
ፕሮግራም ወይም ልዩ የትምህርት ኮርስ መፍጠር የትምህርት ኣካል በማድረግ፣ ት/ቤቶች ስለሃይማኖታዊ
ኣይፈለግባቸውም። ለምሣሌ፦ ሙዚቃ የሜሪላንድ በኣላት እንደ እለታዊ ሃቅ/factual manner ማስተማር
ስነጥበብ ሥርዓተትምህርት መሠረታዊ አካል ስለሆነ ይችላሉ። የት/ቤት እንቅስቃሴዎች የበኣልን ኣለማዊ/
ኃይማኖትን መሠረት በማድረግ ምክንያት ትምህርት ቤቶች መንፈሳዊ ያልሆኑ ገፅታዎችን ማንፀባረቅ ይችላሉ፣ ነገር
ተማሪዎችን ከየሙዚቃ ትምህርት እንዲታቀቡ ማድረግ ግን የሃይማኖት እንቅስቃሴዎች በሃይማኖታዊ ልምድ
አይጠበቅባቸውም፣ ነገር ግን በተቻለ መጠን በኃይማኖታዊ ወይም ክውነት መሳተፍን ላያካትት ይችላል። የተለያዩ
ተቃውሞ ምክንያት ትምህርቱን እንዲጫወቱ ወይም ሃይማኖት ተከታይ ተማሪዎች፣ ወይም ወላጆቻቸው/
እንዲያዜሙ የሚጠበቅባቸውን ትምህርት ቤቶች ለማስወገድ ኣሳዳጊዎቻቸው፣ ተማሪዎች ከተወሰኑ የሃይማኖት
ይችላሉ። እንቅስቃሴዎች ከመሳተፍ ይቅርታ እንዲደረግላቸው
መጠየቅ ይችላሉ። መምህራን ጥያቄ ላቀረቡ ተማሪዎች
ኣማራጭ እንቅስቃሴ በማዘጋጀት እነዚህን ጥያቄዎች
በት/ቤት ስለ ሃይማኖት ወይም ስለ ሃይማኖት ለማክበር መስራት ኣለባቸው። የልደት ቀኖች ወይም
በዓላት ማስተማር ብዙዎች ኣለማዊ ናቸው ብለው የሚገነዘቧቸው ሌሎች
ት/ቤቶች ልጆች ከራሳቸው የተለዩ ባህሎችንና ቅርሶችን ወቅቶች፣ እንደ ሃሎዊን እና ቫሌንቲንስ ዴይ፣ በሌሎች
እንዲማሩና እንዲያደንቁ የሚችሉበት ኣካባቢ ማዳበር እይታ የሃይማኖት ኣዝማሚያነታቸዉ ያመዝናል ተብለው
እንዳለባቸው MCPS ያምናል። በዚህ ኣላማም፣ የ MCPS ሊታዩ ይችላሉ። ት/ቤቶች በነዚህ ኣካባቢ እንቅስቃሴዎች
ስርኣተትምህርት በስነፅሁፍ፣ በታሪክ፣ በሰብኣዊ ጥናቶች፣ ሊኖራቸው ይፈቀድላቸዋል—ኣለማዊ ጠባይ እስከያዙ

4
ድረስ—መሳተፍ ለማይፈልጉ ተማሪዎችም ይቅርታ ክፍል የኣመጋገብ ገደቦች ያሏቸው ተማሪዎች በምግቦች
ሊያደርጉላቸው ይችላሉ። ተለጣፊ ማስታወቂያ በማድረግ/labeling food እና/
ወይም ለቁርስ፣ ለምሳ፣ እና ለቅምሻዎች/snacks
ሃይማኖት በት/ቤት ስብሰባዎች እና በሙዚቃ እንደ የኣሳማ ስጋ-ነፃ፣ የተለያዩ ኣማራጮች በማቅረብ
በአላት ማገዝ ይችላሉ፤ ነገር ግን ት/ቤቶች የኣንድን ተማሪ
ልዩ የት/ቤት ክውነቶች፣ ስብሰባዎች፣ የሙዚቃ በአሎች፣ ልዩ ሃይማኖታዊ ፍላጎቶችን ለማርካት ልዩ ምግቦች
እና ፕሮግራሞች ኣለማዊና ያልተዛባ የትምህርት ፕሮግራም እንዲያዘጋጁ ኣይጠበቅባቸውም። ለተጨማሪ መረጃ፣
ለማራመድ መተለም ኣለባቸው እናም በኣንድ ሃይማኖት www.montgomeryschoolsmd.org ን ጎብኙ፤
ወይም የሃይማኖት በኣል ማተኮር የለባቸውም። ለምሳሌ፣ ምግብንና የስነምግብ ኣገልግሎቶች መፈተሽ።
የፕሮግራሙ ኣጠቃላይ መልእክት/effect ኢሀይማኖታዊ
እስከሆነ ድረስ የሃይማኖት ሙዚቃ በዊንተር የሙዚቃ በተመሳሳዩ፣ በሃይማኖት ምክንያት የሚፆሙ ተማሪዎች፣
በኣል መቅረብ ይችላል፣ እናም ኢሃይማኖታዊ ሙዚቃ ተገቢ የሰራተኛ ቁጥጥር እስካለ ድረስ፣ በምሳ ሰኣት
ሚዛናዊና ሁሉን የሚያካትት አካሄድ ኣካል ሆኖ በተጨማሪ ከካፊቴርያ ይልቅ ወደ ሚድያ ማእከል ወይም ወደ
ይካተታል። ሌላ የተለየ ቦታ እንዲሄዱ ሊፈቀድላቸው ይችላል።
በተጨማሪ፣ በሃይማኖት ምክንያት የሚፆሙና በኣካል
ስብሰባዎች ወይም ፕሮግራሞች የተማሪ የሙዚቃ ጓዶች ማሰልጠኛ ትምህርት ከከባድ እንስቃሴዎች ክመሳተፍ
ወይም ሌሎች የሙዚቃ ቡድኖችን ሲያካትቱ፣ ተሳታፊ ይቅርታ እንዲደረግላቸው የሚጠይቁ ተማሪዎች መጠነኛ
ተማሪዎች የሃይማኖት ሙዚቃ ማከናወን ከሃይማኖታቸው መስተንግዶ እንዲደረግላቸው ይገባል። ተማሪዎች
ኣንፃር ተገቢ ሆኖ ካልተሰማቸው ተቀባይነት ያለውና የተጠየቀውን ከፆም ጋር የተያያዘ መስተንግዶ የሚለይ
ሊከናወን የሚችል መስተንግዶ መጠየቅ ይችላሉ። የፅሁፍ ማብራርያ የሚያቀርብ ማስታወሻ ከወላጅ/ኣሳዳጊ
የመስተንግዶ ጥያቄዎችን ሲያስተናግዱ፣ የት/ቤት ወደ ት/ቤት ማምጣት ኣለባቸው።
ሰራተኞች ተማሪዎችን ከሚያሳፍር ሁኔታ፣ ወይም
ከመጋጨት ለማዳን ከተማሪዎችና ከወላጆቻቸው/
አሳዳጊዎቻችው ጋር መመካከር አለባቸው።
የሀይማኖታዊ መረጂያዊ ቁሳቁሶች ስርጭት
በስብሰባዎች የተማሪ ወይም የእንግዳ ተናጋሪዎች መመረጥ ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ የመረጃ ቁሳቁሶች
ያለባቸው ሃይማኖትን በማይደግፉ ወይም በማይቃወሙ ለማሰራጨት የተማሪ ጥያቄዎች
በርትአዊ መስፈርቶች ተመስርቶ መሆን ኣለበት። የተማሪን ተማሪዎች ከት/ቤት ስርኣተትምህርት ወይም
ወይም የእንግዳ ተናጋሪን ኣስተያየቶች (ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ጋራ ያልተያያዘ ሌላ መረጂያዊ ቁሳቁስ
ይሁኑ ኣይሁኑ) ት/ቤቱ ይደግፋል በማለት ወደ ሌሎች ለማሰራጭት በተፈቀደላቸው ተመሳሳይ ሁኔታዎች መሰረት
ተማሪዎች፣ ወላጆቻቸው/አሳዳጊዎቻቸው፣ ወይም ሃይማኖት-ነክ መረጂያዊ ቁሳቁሶች ለት/ቤት ጓዶቻቸው
እንግዶች የሚተላለፈውን ኣስተያየት ለማስወገድ ት/ቤቶች ሊያሰራጩ ይችላሉ። ይህም ማለት ስርጭቱ በስንት
ተገቢ፣ ነፃ የሆኑ ማስተባበያዎች ማድረግ ኣለባቸው። ሰኣት ሊከናወን እንደሚችል፣ የት ቦታ እንደሚቻል፣ እና
በተጨማሪ፣ ሃይማኖት-ነክ ርእሶች ወይም በኣላት እንዴት ሊደረግ እንደሚችል ት/ቤቶች መደንገግ ይችላሉ፣
የሚያካትቱ ስብሰባዎችና ሌሎች የት/ቤት ክውነቶች በት/ እነዚህ ጊዜ፣ ቦታ፣ እና የስነምግባር ገደቦች በሁሉም ከት/
ቤቶች ፕሮግራም እድሜ ታሳቢ እንደሚሆን ወላጆች/ ቤት-ጋር-ባልተያያዙ የተማሪ መረጂያዊ ቁሳቁሶች ፀንተው
ኣሳዳጊዎች መገንዘብ ኣለባቸው። ምንም እንኳን የሁለተኛ ተግባራዊ እስከሆኑ ድረስ ማለት ነው።
ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በርትአዊ መንገድ እንዲናገሩ
የተመረጡ ተማሪዎች ወይም እንግዶች ኣስተያየቶችን ት/ እነዚህ የጊዜ፣ ቦታ፣ እና የስርጭት ዘዴ ግዴታዎች በ
ቤት የማይደግፍ መሆኑን ሊገነዘቡ ቢችሉም፣ የመካከለኛና MCPS ደንብና ህጎች ውስጥ ተንፀባርቀዋል -የተማሪዎች
የኤሌሜንተሪ ተማሪዎች፣ የት/ቤት ሰራተኞች በኣግባቡ የሃይማኖታዊ መረጂያዊ ቁሳቁሶች ስርጭት፣ ልክ እንደ
ማስተባበያ ቢሰጡም፣ ይህን ለመለየት መቻላቸው ፖለቲካዊ ቁሳቁሶች ወይም ሌላ ከት/ቤት-ጋር-ያልተያያዘ
ኣጠራጣሪ ነው። መረጂያዊ ቁሳቁስ፣ መከናወን ያለበት ከትምህርት ጊዜ
ውጭ እና ረብሻ በማያካትት ሁኔታ ነው። ለምሳሌ፣
በእግር መንገዶችና በካፊቴሪያ፣ የተፈቀዱ ኮሪደሮች፣
ምግብና የሃይማኖት በኣል ወይም የተማሪ አስተዳደር ክፍሎች ወይም መስኮች
መረጂያዊ ቁሳቁሶች ለማሰራጨት ት/ቤቶች ለተማሪዎች
ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ የምግብ አይነት ሊፈቅዱላቸው ይችላሉ። የሆነ ሆኖ፣ ተማሪዎች ከት/
ገደቦችና ፆም ቤት-ጋር ያልተያያዙ መረጂያዊ ቁሳቁሶች በመማርያ
ተማሪዎች፣ ወይም ወላጆቻቸው/ኣሳዳጊዎቻቸው፣ ክፍሎች፣ የሚድያ ማእከል፣ ወይም በሌሎች ት/
አይማኖት-ነክ የኣመጋገብ ገደብና ፆምን ይሚያካትቱ ቤት ክፍሎች በትምህርት ቀን ማሰራጨት የለባቸውም፣
ተቀባይነት ያላቸውና ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ (ሀ) ክፍሉ እንደ የበጎ-ፈቃደኛ መሰብሰብያ ቦታ ተብሎ
መስተንግዶዎች እንዲያደርጉ ት/ቤቶችን መጠየቅ ጥቅም ላይ እስከዋለ ድረስ ወይም (ለ) መረጂያዊ
ይችላሉ። የMCPS የምግብና የኣመጋገብ ኣገልግሎቶች ቁሳቁሱ መመርያ ክፍል ውስጥ እንደ መደበኛ ትምህርት

5
ፕሮግራም አካል ወይም የበጎ-ፈቃደኛ መድረክ ወይም ቤት ጋዜጣ ማስታወቂያዎችን ያካትታል፣ እንደዚህ አይነቱ
በተማሪዎች የተካሄደ ሴሚናር ካልሆነ በስተቀር። መዳረሻ በት/ቤት ውስጥ ትምህርት ከሚሰጥበት ርእስ ጋር
በተጨማሪ፣ ተማሪዎች ሀይማኖታዊም ሆነ ፀያፍ፣ ግንኙነት ለሌላቸው የተማሪ ቡድኖች ተደርጎላቸው ከሆነ።
ስም-አጥፊ፣ የትምህርት አካባቢ ረባሽ፣ ወይም በት/ቤት እነዚህ ሃይማኖት-ነክ ከስርኣተትምህርት ውጭ ቡድኖች
አካባቢ የሚገኙ የሌሎችን መብቶች የሚደፍሩ መረጂያዊ በት/ቤት የኣመት መፅሄት ትምህርት ከሚሰጥበት ርእስ
ቁሳቁሶችን በት/ቤት መቼት ማሰራጨት አይችሉም። ጋር ግንኙነት ለሌላቸው ለስርኣተትምህርት ውጭ ቡድኖች
በተወሰነው ክፍል መዘርዘርም ይችላሉ።
• ለተጨማሪ መረጃዎች፣ የ MCPS ደንብ JFA-RA፣
የተማሪ ሃላፊነቶችና ግዴታዎችን ይመልከቱ። www. ሃይማኖት-ነክ ከስርኣተትምህርት ውጭ ቡድኖች ኣልፎ
montgomeryschoolsmd.org/departments/ ኣልፎ የውጭ ኣዋቂዎች ወይም የሃይማኖት መሪዎችን
policy/pdf/jfara.pdf መጋበዝ ይችላሉ። ቢሆንም፣ በት/ቤቱ ተማሪዎች
ያልሆኑ ግለሰቦች በተማሪ በተመሩ ከስርኣተትምህርት
• ስለ ተማሪዎች ባልሆኑ የቁሳቁሶች ስርጭት
ውጭ ቡድኖች ፀሎቶች ወይም ሌሎች ሀይማኖታዊ
መመርያዎች፣ የ MCPS ደንብ CNA-RA፣ የመረጂያዊ
እንቅስቃሴዎችን ዘወትር መምራት፣ መከታተል፣ ወይም
ቁሳቁሶች ማስታወቂያዎች ትርእይትና ስርጭት
መቆጣጠር ኣይችሉም።
ተመልከቱ www.montgomeryschoolsmd.org/
departments/policy/pdf/cnara.pdf በተማሪ-የሚመሩ ቡድኖች፣ ሃይማኖታዊም ይሁኑ
• በተጨማሪ የሚመለከቱት፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ኢሃይማኖታዊ፣ ኣካላዊ ጥቃት ወይም ጥላቻ የሚያራምዱ፣
ፐብሊክ ስኩልስ ደንብ/MCPS Regulation በህገ-ወጥ እንቅስቃሴ የሚሳተፉ፣ ትርጉም ያለው
KEA-RA፣ በፖለቲካ ዘመቻ መሣተፍ እና የዘመቻ ረብሻ በት/ቤት የሚቀሰቅሱ፣ የ MCPSን ፀረ-አድልዎ
ቁሳቁሶችን/ማቴሪያሎችን ማሠራጨት፦ www. መመርያዎችን የሚጥሱ፣ ወይም በት/ቤት ኣካባቢ የሌሎችን
montgomeryschoolsmd.org/departments/ መብቶች የሚደፍሩ ከሆነ በ MCPS ት/ቤቶች እንዲሰበሰቡ
policy/detail.aspx?recID=322&policyID=KEA- ኣይፈቀድላቸውም። የሆነ ሆኖ፣ የኣወዛጋቢና ውስብስብ
RA&sectionID=11 ማህበራዊና ህጋዊ ጉዳዮችን ውይይት በማካተታቸው
ምክንያት ብቻ ት/ቤቶች ተማሪዎችን ቡድኖች ከመመስረት
ከስርኣተትምህርት ውጭ የተማሪ መከልከል የለባቸውም።
ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ተማሪዎች በቅድመ- ወይም ድህረ-ትምህርት ክውነቶች
ሃይማኖታዊ ይዘት ባላቸው ክውነቶች ልክ በሌሎች
ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ ከስርኣተትምህርት ከስርአተትምህርት ጋር ባልተያያዙ በት/ቤት ግቢ
ውጭ እንቅስቃሴዎችና ክበቦች እንቅስቃሴዎች አንደሚደረገው መሳተፍ ይችላሉ።
ተማሪዎች ሃይማኖት-ነክ ከስርኣተትምህርት ውጭ ክበቦች
ለማደራጀት ወይም ሃይማኖታዊ ስብሰባዎች፣ የፀሎት የ MCPS ኣጠቃቀም በሃይማኖታዊ ድርጅቶች
ቡድኖች፣ ወይም ሌሎች የሃይማኖት ልምዶች ማክበር
ንብረት በሆኑ መገልገያዎች
ትምህርት ከሚሰጥበት ጊዜ ውጭ የማካሄድ መብት
ሃይማኖታዊ ያልሆነ ኣማራጭ ቦታ የሚቻልና
ኣላቸው። እነዚህ ሃይማኖት-ነክ ከስርኣተትምህርት
ለእንቅስቃሴ ወይም ተግባር ተቀባይነት ባለው ደረጃ
ውጭ ስብሰባዎች ወይም ክበቦች በተማሪዎች የሚመሩ
ተስማሚ መድረክ ሆኖ እያለ በሃይማኖታዊ ድርጅቶች
መሆን ኣለባቸው። የ MCPS ሰራተኞች የተማሪና የት/
ንብረት በሆኑ ወይም በነሱ በሚንቀሳቀሱ መገልገያዎች
ቤት ደህንነት ለማረጋገጥ ቁጥጥርና ክትትል ሊያቀርቡ
ለት/ቤት-ነክ እንቅስቃሴዎች ወይም ተግባሮች ት/
ይችላሉ፣ ነገር ግን በነዚህ ከስርኣተትምህርት ውጭ
ቤቶች እንደማይጠቀሙበት ተማሪዎችና ወላጆቻቸው/
ስብሰባዎች ወይም ክበቦች በሚካሄዱ ፀሎቶች ወይም
ኣስዳጊዎቻቸው ማወቅ ኣለባቸው። ት/ቤቶች ማንኛውንም
ሌሎች ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ማደራጀት፣
የግል ሃይማኖታዊ መገልገያን የዚህ ኣይነቱ መገልገያ
መምራት፣ ማነሳሳት፣ መደገፍ፣ ወይም በተግባር መሳተፍ
ከማንም የሃይማኖት ኣስተምህሮዎች ገፅታ ጋር በመያያዙ
ኣይገባቸውም።
በመመስረት ብቻ ኣይመርጡም ወይም ውድቅ
በተማሪዎች-መሪነት የሚካሄዱ ማናቸውም ኃይማኖታዊ ኣያደርጉም፤ እንዲያውም፣ እነዚህን ኣገልግሎቶች
የሆኑ፣ ተጨማሪ ሥርዓተ ትምህርት ክለቦች ወይም ለመምረጥ ለMCPS ቅርበት፣ የመገልገያው ተስማሚነት
እንቅስቃሴዎችን በት/ቤት ክልል ውስጥ በቂ ቦታ ለሚፈለገው ኣገልግሎት፣ ጤናና ደህንነት፣ ተመጣጣኝ
ለማግኘት በቅድሚያ የ MCPS አስተዳደርን ማነጋገርና ወጪ፣ እና መዳረሻን የመሳሰሉ ከሃይማኖት ነፃ የሆኑ
ማሳወቅ አለባቸው። ልክ እንደ ሌሎች ከስርኣተትምህርት መስፈርቶች ኣገልግሎት ላይ ይውላሉ።
ውጭ በት/ቤት ውስጥ ትምህርት ከሚሰጥበት ርእስ ጋር
ት/ቤት-ነክ የሆነ መገልገያ ወይም ተግባር በኣንድ
ቀጥተኛ ግንኙነት የሌላቸው የተማሪ ቡድኖች፣ የተማሪ
ሃይማኖታዊ ድርጅት ንብረት በሆነ ወይም በሚንቀሳቀስ
ሃይማኖታዊ ቡድኖች ለት/ቤት መገልገያዎች፣ መሳርያ፣
መገልገያ ውስጥ ከተካሄደ፣ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው/
እና አገልግሎቶች እኩል መዳረሻ ኣላቸው። ይህም
ኣሳዳጊዎቻቸው ት/ቤቱ መገልገያውን ከሃይማኖት ነፃ
የማስታወቂያ ሰሌዳዎችን፣ ኮምፒውተሮችን፣ እና የት/

6
ለሆነ ኣላማ እንደሚጠቀምበት ይለያል፣ በተቻለ መጠን ኣወንታዊና ክቡር የሆኑ ት/ቤቶችን ለመፍጠር
ደግሞ፣ ት/ቤት-ነክ እንቅስቃሴዎች በሚካሄዱበት ወቅት ከምናደርገው ጥረት ኣካል፣ ተማሪዎች ሰላማዊ የመማርያ
የሃይማኖት ምስሎች፣ መልእክቶች፣ ወይም የኪነጥበብ ኣካባቢ የማግኘት መብት ኣላቸው፣ ከማንኛውም
ስራዎች በክፍሎቹ እንደማይታዩ ያረጋግጣል። በተጨማሪ፣ ኣይነት ማሸማቀቅ፣ ወከባ፣ እና ከማስፈራራት ነፃ የሆነ
የት/ቤት-ነክ እንቅስቃሴ ወይም ተግባር ተሳታፊዎች የተማሪው/ዋ ሃቀኛ ወይም የሚገመቱ የግል ባህሪዮች ላይ
በሚያልፉባቸው ኣካባቢዎች የጎሉ ሃይማኖታዊ ምስሎች፣ የተመሰረተ ማስፈራራት፣ ሃይማኖትን ጨምሮ። ኣመፅ
መልእክቶች ወይም ኪነጥበባት መጋለጥን ለማስወገድ የደረሰባቸው ተማሪዎች፣ ኣመፅ የሚፈፅሙ ተማሪዎች፣
ወይም ለማሳነስ የተቻለ እርምጃ ሁሉ ይወሰዳል። እና ኣመፅ ቆመው የሚመለከቱ ተማሪዎች ለጤና፣ ደህንነት
እና ለትምህርት ኣሉታዊ ውጤቶች ኣደጋዎች የተጋለጡ
ናቸው። ማሸማቀቅን፣ ወከባን፣ ወይም ማስፈራራትን
ህብረት በት/ቤቶችና በእምነት ማህበረሰቦች
ለመከላከል እና ሲፈፀም በውጤታማነት ጣልቃ ለመግባት፣
መካከል እንዲሁም ማሸማቀቅ፣ ወከባ፣ ወይም ማስፈራራት
ልክ ከቢዝነሶችና ሌሎች የማህበረሰብና የሲቪል ቡድኖች ዘገባ በሚያቀርቡ ላይ የበቀል እርምጃ የሚፈፅሙትን
ጋር እንደሚያደርገው፣ MCPS ከእምነት ህብረተሰብ ጋር ለመከላከል MCPS ስርኣት-አቀፍ ኣቅርቦት ተልሞ
ሽርክናዎችን ለመንከባከብና ለማዳበር ይሰራል። እያንዳንዱ ተግባራዊ ኣድርጓል። ማንኛውንም የዚህ ኣይነት ተግባሮች
የህብረተሰብ ኣካል ትምህርትን ለመደገፍ ሲሰባሰብ ለማስታወቅ፣ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው/ኣሳዳጊዎቻቸው
ተማሪዎችና ት/ቤቶች እጅግ በጣም ያተርፋሉ። ከት/ቤት ኣስተዳዳሪዎች ጋር ማናቸውንም ጉዳዮች
ማንኛውም የእምነት ማህበረሰብ ሽርክና ፕሮግራም የጠራ ለመፍታት የ MCPS ን ቅጽ 230-35፣ Bullying,
ኣለማዊ/መንፈሳዊ ያልሆነ ኣላማ እንዲኖረው ያስፈልጋል Harassment, or Intimidation Reporting Form/
እናም ሃይማኖትን ማራመድ ወይም ማገድ የለበትም። ማሸማቀቅ፣ ወከባ፣ ወይም ማስፈራራት ማሳወቂያ
ተማሪዎች እንዲሳተፉ የሚመረጡት፣ በማናቸውም ቅጽ፣ በዚህ የሚገኘውን መሙላት፡- በ www.
ኃይማኖታዊ ቡድን አባልነት፣ወይም ማናቸውንም montgomeryschoolsmd.org/departments/forms/
ኃይማኖታዊ እምነትን ስለተቀበሉ ወይም ስላልተቀበሉ፣ pdf/230-35.pdf.
ወይም በማናቸውንም ዓይነት የኃይማኖት እምነት
እንቅስቃሴዎች ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኞች መሆናቸውና
ያለመሆናቸዉን መሠረት በማድረግ አይደለምም።

የእምነት ማህበረሰቦች በጎ-ፈቃደኞች የማንኛውም አጋርነት


ዓላማ በተፈጥሮ ትምህርታዊና ኢሀይማኖታዊ/ዓለማዊ
መሆኑን፣ እናም በጎ-ፈቃደኞች በኣንደኛ ማሻሻያ አዋጅ/
First Amendment የተማሪዎችን መብቶች ማክበር
እንዳለባቸው ማወቅ ኣለባቸው። በት/ቤት ስፖንሰር
በሚደረግ እንቅስቃሴ በመምራት ወይም በመሳተፍ ላይ
በሚገኙበት ወቅት በጎ-ፈቃደኞች ወይም ተሳታፊዎች
በማንኛውም የእምነት ማህበረሰብ የጋራ ፕሮግራም ስለ
ሃይማኖታቸው ለተማሪዎች መስበክ ወይም በሃይማኖታዊ
አምልኮ መሳተፍ አይችሉም። የእምነት ማህበረሰብ ሽርክና
ፕሮግራም በጎ-ፈቃደኞች እና ተሳታፊዎች በሌሎች
የማህበረሰብ ድርጅቶች እንደሚደረገው ሁሉ በMCPS
የመረጂያዊ ቁሳቁሶች ስርጭት ህጎችን መከተል ኣለባቸው።

ለሁሉም የመከባበር ባህልን ማዳበር/ማሳደግ


በሁሉም የ MCPS ማህበረሰብ መካከል የመከባበር ባህል
እንዲዳብር ለመርዳት እነዚህ መመርያዎች ተዘጋጅተዋል።
በማህበረሰቦች ውስጥ ካለው ከፍተኛ ብዙሃነት/diversity
ጋር፣ የመከባበር፣ መቀባበልና የመቻቻል ባህል ሲኖር
እርስ-በርሳችን የምንማረው በጣም ብዙ ይኖራል። ት/
ቤቶቻችን ደጋፊና ምቹ የመማር ኣካባቢ ለመፍጠር
ይሰራሉ፣ እናም ወላጆች/ኣሳዳጊዎች ከመምህራንና
ከኣስተዳዳሪዎች ጋር የቤተሰቦቻቸውን ፍላጎቶች
ሃይማኖታዊ እምነቶቻቸውንና ልምዶቻችውን ደጋፊ
እንደመሆናቸው ለመገንዘብ በቅርብ እንዲሰሩ ይበረታታሉ።

7
የሞንጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) የፀረ-መድሎ መግለጫ
MCPS Nondiscrimination Statement
የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ዘርን፣ ጎሳ፣ ቀለም፣ የዘር ሃረግ፣ የብሔር ማንነት፣ ኃይማኖት፣ የስደተኝነት ሁኔታ፣
ጾታ፣ ስነ-ጾታ፣ የጾታ ማንነት (gender identity)፣ የጾታ አገላለጽ (gender expression)፣ የጾታዊ ግንኙነት ዝንባሌ/ምርጫ (sexual
orientation)፣ የቤተሰብ/የወላጆች የኑሮ ደረጃ/አቋም/ሁኔታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ እድሜ፣ ድህነት፣ እና የማህበራዊ ኤኮኖሚያዊ አቋም፣
ቋንቋ፣ የአካል ወይም የአእምሮ ጉዳተኝነት፣ በህገመንግስት ጥበቃ የተደረገላቸው ሁኔታዎችን ባህሪያትን ወይም ተዛማጅነት ያላቸውን
(affiliations) መሠረት ያደረገ ሕገ-ወጥ አድሎ/መድሎ ይከለክላል። መድሎ ወይም አድሎአዊነት፤ በሕብረተሰባችን ለረዥም ጊዜ
እኩልነትን፣ ፍትሕ፣ አብሮነት፣ሁሉን አቀፍነትን፣ ለመፍጠርና ለማሳደግ/ለመንከባከብ፣ ሲደረግ የቆየ ትጋትን ይሸረሽራል/ያበላሻል።
አድልዎ የሚከተሉትን የተወሰኑ ምሳሌዎችን ያካትታል፦ጥላቻ፣ ሁከት፣ ደንታቢስነት፣ ወከባ፣ ማስፈራራት፣ ማሸማቀቅ፣ ንቀት፣ ወይም
ማጥቃት። የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ የሞንጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ደምብ/Policy ACA ስለ ጸረ-መድሎ፣ ፍትህ፣ የዳበረ
ባህል ይመርምሩ። ይህ መመርያ እያንዳንዱ ተማሪ አስፈላጊ/ተፈላጊ መሆኑ(ኗ)ን፣ በተለይም የትምህርት ውጤቶች የሚረጋገጡት በምንም
ዓይነት ግለሰብ ባለበት(ባለባት) ምክንያት ወይም ይሆናል ተብሎ የሚገመት ግላዊ ጠባዮች የሚተነበዩ አለመሆናቸውን የቦርዱን እምነት
ያረጋግጣል። ፖሊሲው በቅድሚያ መወሰድ ስላለባቸው የፍትህ እርምጃዎች የተዛባ አመለካከትን፣ ማረጋገጫ የሌላቸው የማዳላት/ልዩነት
አፈጻጸሞችን የሚያስከትሉትን አሉታዊነት፣ የትምህርት እና የሥራ መቀጠር እኩልነትን የሚያሰናክሉ መዋቅራዊ እና ድርጅታዊ አሠራር
ደንቃራዎችን በተለይ ያስገነዝባል።

በMCPS ሰራተኛ* ላይ ስለደረሰ መድሎዎ ጥያቄዎች ወይም በMCPS ተማሪዎች ላይ የአድልዎ ጥያቄዎች ወይም ቅሬታዎች
ቅሬታዎች ለማቅረብ ካላችሁ*
የሰራተኛ ተሳትፎ እና የሥራ ግንኙነት ጽ/ቤት Office of the Chief of Staff
የአፈጻጸም እና የክትትል/የምርመራ መምሪያ Student Welfare and Compliance
Department of Compliance and Investigations 850 Hungerford Drive, Room 162
850 Hungerford Drive, Room 55 Rockville, MD 20850
Rockville, MD 20850 240-740-3215
240-740-2888 COS–StudentWelfare@mcpsmd.org
OCOO-EmployeeEngagement@mcpsmd.org

* ክትትል፣ ቅሬታ/ስሞታ፣ ወይም ስንክልና ላለባቸው ተማሪዎች አመቺ ስፍራ ለመጠየቅ፤ ወደ ልዩ ትምህርት ተቆጣጣሪ ጽ/ቤት፣ የቅሬታ
ሰሚና መፍትሔ ሰጪ ን/ክፍል በ ስልክ ቁጥር 240-740-3230 ሊቀርብ/ሊመራ ይችላል። ለሰራተኞች መገልገያዎች ወይም ማሻሻያዎች
በሚመለከት የሚቀርቡ ጥያቄዎች ወደ Office of Employee Engagement and Labor Relations, Department of Compliance
and Investigations/ የሰራተኛ ተሳትፎ እና የስራ ግንኙነት የአፈጻጸም እና የክትትል (የምርመራዎች) መምርያ፣ ስልክ፦ 240-740-2888
ሊመሩ ይችላሉ። በተጨማሪ፣ አድሎአዊነት ቅሬታዎች ለሌሎች ኤጀንሲዎችም ፋይል ሊደረጉ ይቻላል። እነርሱም፦ the U.S. Equal
Employment Opportunity Commission, Baltimore Field Office, City Crescent Bldg, 10 S. Howard Street, Third
Floor, Baltimore, MD 21201, 1-800-669-4000, 1-800-669-6820 (TTY); ወይም U.S. Department of Education, Office
for Civil Rights, Lyndon Baines Johnson Dept of Education Bldg., 400 Maryland Avenue, SW, Washington, DC
20202-1100, 1-800-421-3481, 1-800-877-8339 (TDD), OCR@ed.gov, ወይም www2.ed.gov/about/offices/list/ocr/
complaintintro.html.

ይህ ሠነድ ካስፈለገ በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ከእንግሊዝኛ በሌሎች ቋንቋዎችና በሌላ አማራጭ ቅርፀት ሊገኝ ይችላል። በአካል
ጉዳተኝነት ስለሚኖሩ አሜሪካውያን ደንብ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች ኮሙኒኬሽን ዲፓርትመንት/MCPS Department
of Communications በስልክ ቁጥር፦ 240-740-2837፣ 1-800-735-2258 (ሜሪላንድ ማዞሪያ)፣ ወይም PIO@mcpsmd.org.
የምልክት ቋንቋ ትርጉም የሚፈልጉ ግለሰቦች ወይም የንግግር ትርጉም/ምልክት አገልግሎት ለማግኘት የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/
ቤቶች የትርጉም አገልግሎት ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር፦ 240-740-1800, 301-637-2958 (VP) ወይም MCPSInterpretingServices@
mcpsmd.org መገናኘት ይችላሉ። የሞንጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS)፤ ወጣት ስካውቶችን (ወንድ/ሴት) እና ሌሎችም
የሚመለከታቸውን ወጣት ቡድኖችን በእኩል ያስተናግዳቸዋል።

ጁላይ 2019

ROCKVILLE, MARYLAND

ህትመት፦ Department of Materials Management for the Office of Student and Family Support and Engagement
ትርጉም፦ የቋንቋዎች ትርጉም አገልግሎት ክፍል
Language Assistance Services Unit • Department of Communications
Copyright © 2019 Montgomery County Public Schools, Rockville, Maryland
1360.19 • Editorial, Graphics & Publishing Services • 7/19 • NP

You might also like