You are on page 1of 2

ቀን ጥር 16 /2015 ዓ.

ለተከበራችሁ የቁጫ ወረዳ ከተማልማትና ኮንስትራክሸን ጽ/ቤት ሠራተኛ የሆናችሁ፤ለተከበራችሁ ከአርባምንጭ


የመጣችሁ የሞርካና አከባቢያዋ ተወላጅ የሆናችሁ ተወካዮች፤ ወድ የሞርካ ከተማ ማዘጃ ና የከንትባ ሀላፊዎች፣ተጋባዥ
የማህበረሰቡ አባቶች፣የሞርካ ከተማ አንደኛ ሙሉ ሁለተኛ ደረጃ ትም/ት ቤት አስተማሪዎችና ሪዕሰ መምህራን፣ የማሻ
ብረሃን አክስዮን አባለት ና ኮሚቴዎች በሙሉ፣የሕጻናት ወላጅ ቤተሰቦች በሙሉ፣የማሻ ብረሐን አጸደ ሕጻናት
መምህራን፣እግዚአብዘሄር አምላካችን እንኳን ለዛሬዋ ቀን አደረሰን! እግዚአብዘሄር አምላካችን ለዘሌአለም የተመሰገነ
ይሁን! እኛንም በሕይወት በመንገዳችን ሁሉ ይባርከን!

ከሠላምታየ በመቀጠል የቁጫ ከተማልማትና ኮንስትራክሸን ጽ/ቤትን አጸደ ሕጻናት ትም/ት በቱን ጽ/ቤቱ
ሳያዉቅ መጀመራችን ይቅርታ መጠየቅ እወዳለሁ፡፡

ትምህርት ቤቱን ለመክፈት የገፋፉን ዘርፈ ብዙ ችግሮች አሉን፡፡

1. የእግዚአብሔር ቃል እዉቀትን መጥላትና ማጣት ሕዝብን ያጠፋል ይላልና(ሆሴዕ 4፡6)፣አከባቢው ከተማ


ወደ መሆን ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በአከባቢዉ በሚያሳፍር ሁኔታ የዕዉቀት ጥላቻና ማነስ
ስለሚስተዋል፣የሞርካ አከባቢ ተወላጆችን ከተጋረጠባቸው ፈተና ለማስመለጥ ብቸኛው መንገድ
በእግዚአብሔር በመታመንና ማህበረሰቡን በማስተባበር ለውጥን በሕጻናት መጀመር ስላለብን፤
2. ቀጣይ ትዉልድ በአለም ሁሉ ካሉ ከአቻ ትዉልድ ጋር ተወዳዳሪ ሆኖ እንድወጣ መንገድ ማሳየት
ስላለብን
3. አሁን በኢት/ያ ሥር ስድዶ አንዱ ሌለሰውን እየፈጁ እንድስቁ ምክንያት ከሆነው የቋንቋ ግርዶሽ ቀጣይ
ትዉልድን ለመታደግና ወገኖቻችን የአከባቢዉን ቋንቋን፣የብሔራዊ ቋንቋን፣የአለም አቀፍ ቋንቋን በገባቡ
ተረድቶ፣ቋንቋን ጸጋ ስጦታና ችሎታም መሆኑን ተረድቶ እንዲያድጉ ከመርዳት ሌላ አማራጫ የሌለው
ጉዳይ ስለሆነ
4. ልጆቻቸውን ከሕጻንነታቸው ጀምሮ ለማስተማር ስፈልጉ የአጸደ ሕጻናት ትም/ት ቤት ባለመኖሩ
የሚጨነቁ ወላጆች ከፍተኛ ግፍት፤
5. ከእዉቀት ማነስ አንዱና ዋና እግዚአብሔርና የሰዉን ልጅ ክቡርነት አለማወቅ ምልክቶች ለምሳሌ
በእግዚአብሔር ቃል 1 ጰጥ 2፡17 ና ኤፈ 2፡13-22 የሰው ልጅ ክቡርነትና እኩልነት የሚያስተምረዉንና
ጥስት በፎሌትካዉ፣ በበቴ እምነቶችና በማህበረሰቡ መካከል ስር ሰድዶ የእግዚአብሔር ቁጣ
እንድነድድ ምክንያት በመሆኑ፣የሰውን ልጅ ኩቡርነትና እኩልነት ትውልድ ማወቅ ያለበት ከሕጻንነታቸው
መሆን ስላለበት፣ስረአትንና ፍርድን ከሕጻንነት ጀምሮ የተማሩ ልጆች ታላቅና ብርቱ የተባረኩ ዘጎች
እንደሚሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ ስለሚያስተምረን ዘፍ 18፡18
6. ቀድመን የመማር ዕድል ያገኘን በሚንማርበትም ሆነ አሁን ከደረስንበት ሁኔታዎች ስለ ሕዝባችንና
ስለቀጣይ ትዉልድ ከፍተኛ ቁጭትና ሀዘንም ጭንቀትም ስላሌብን ባልተመቻቸ ሁኔታም ብሆን
የማስተማር ስራዉን መጀመር እንዳለብን አስቾኩሎናል፡፡
7. ለዚሁም ጥሩ ዉጤት ማየት የሚንችለው በአለንበት ከተማ እንደሚደረገው በመንቶሶሪ ስስተም
ልጆችን ማስተማር እንዳለብን ስለታመነ
8. በአከባቢው የአጸደ ሕጻት ትምርት ቤት ሰልጥኖ ለብዙ አመታት ስራ አጥ ሆኖ ላሉት የሥራ
በርም ሆኖ ስለታየን ነው፡፡

ለጽ/ቤቱ አደራ ማለት የሚፈልገው፡ እኛ የአክስዮኑ አባለት ገንዘብ ስለበዛብን ምን እናድርግ ብለን
የተነሳሳን ሳንሆን ከልጆቻችን አፍ ነጥቀን የቀጣይ ትዉልድ እጣ ፋንታ ግድ ብሎን የጀመረን እንደሆነን
እንድታወቅልንና ጽ/ቤቱ በሀሳብም በማተሪያልም ከጎናችን በመቆም ከእግዚአብሔር በታች እንዲያበረታታን
እላለሁ፡፡
አሁን ቀጥሎ በቅርቡ እስከ 2016 መግቢያ ድረስ እግዚአብሔር ብፈቅድ አንድ በመንቶስሪ ስስተም በወላይታ
ብሩህ ተስፋ አጸዴ ሕጻናት ትም/ት ቤት እየሰለጠነች ያለች ተማሪ ተመሪቃ ትምጣለች

ተጨማሪ ነገሮችን ለማሟላት እግዚአብሄርን እንጸልያለን እርሱም ከእኛ ጋር እንደነበረ ለወደፊትም ይሆናል፡፡
የበኩላችን ድርሻ እናደርጋለን፡፡ያነ በኢሳያስ 62፡4 ከእንግድህ የተተወች አትባይም፤ምድርሽም ከእንግድህ ውድማ
አትባልም፤ነገር ግን እግዚአብሔር በአንች ደስሎታልና፣ ምድርሽ ባል ታገባለችና አንችም፡-ደስታዬ የሚኖርባት
ትባያለሽ ምድርሽም ባል ያገባች ትባላለች፤ጎልማሳ ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣እንድሁም ልጆችሽ ያገቡሻል
ተብሎእንደተጻፈ፤እኛ ተነስተን እንስራለን እግዚአብሔር ምኞታችንን ያሳካልናል፣ክብሩም ለእርሱ፣በረከቱ
ለምድራችን ይሆናል፡፡ መልዕክተን በጸጋ ስለተቀበላችሁ ከልብ አመሰግናችሁዋለሁ፡፡

መጋቢ እስራኤል ኢዮብ

0926026169 የአክስሆኑ ሰብሳቢ

You might also like